Monday, January 21, 2013

በቤተ ክህነት ፖለቲካው ማቅ ኪሳራ እየደረሰበት ነው

የማቅና የአቡነ ቀሌምንጦስ ፍቅር አልቋል  
ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ ማቅ አለቅጥ ጣልቃ በገባበት የቤተክህነት ጉዳይ በረጃጅም እጆቹ በርካታ ግብታዊ እርምጃዎችን እያስወሰደ፣ የሚቃወሙትን እያስነሣ የሚደገፉትን እያስቀመጠ ሲንቧችበት የነበረው ቤተ ክህነት በተወሰነ መልኩም ቢሆን በማቅ ላይ ፊቱን እያዞረበት መሆኑ እየታየ ነው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑት ማቅ በአንድ ጊዜ እላይ ወርውሮ መምሪያ ሃላፊ ያደረገውና በምርጫው ሥራዬን ይሰራልኛል ብሎ ተስፋ የጣለበት ሀይለ ጊዮርጊስ ተሽቀንጥሮ እታች መውረዱና በአሁኑ ጊዜ በወንጀል ተከሶ ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት መገኘቱ፣ የማቅ ዋና ወሬ አቀባባይ የሆነው ማንያዘዋል ቤተክህነት ግቢ እንዳይገባ በአቃቤ መንበር ናትናኤል መታገዱ፣ ይጠቀሳል።
ከሰሞኑ ደግሞ ማቅ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሊቀጳጳስ በሆኑት በብፁእ አቡነ ቀሌምንጦስ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈተ ሲሆን፣ በብሎጎቹ ላይ «ብአዴን እና ደህንነቱ» እያለ ስማቸውን በማጥፋቱ ብፁእነታቸው ማቅን «እኛ እኮ ከእኛ ጋር ተባብሮ ለቤተ ክርስቲያን ይሰራል ብለን ነው አርፎ የማይቀመጥ ከሆነ ሁለት መስመር ደብዳቤ ጽፈን እናዘጋዋለን» ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ከዚህ ቀደም ማቅ የመምሪያው ሃላፊ ከነበሩት ከአባ ሠረቀ ብርሃን ጋር ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ገብቶ በነበረ ጊዜ አቡነ ቀሌምንጦስ ከማቅ ጎን ቆመው ለማቅ ከፍተኛ ድጋፍ የሰጡ ሲሆን ያኔ ማቅን በሚገባ ባለማወቅና ለቤተ ክርስቲያን የቆመ መስሏቸው ያን ድጋፍ እንዳደረጉ እየተናገሩ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃንን «እኛ እኮ የእርስዎን ትግል ሳናውቀው ነው ከማቅ ጎን የቆምነው» ብለው ባለፈው በሆነው ነገር ሁሉ መጸጸታቸውን ምንጮች ይናገራሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቃቤ መንበሩ አንዳንድ ጳጳሳትና ከማቅ ጋር ግንባር ፈጥረው ቤተ ክርስቲያኗን እያመሱ የሚገኙ ባለስልጣናት አላሰራ ስላሏቸው ለመንግስት ደብዳቤ ጽፈው ድጋፍ መጠየቃቸውን ተከትሎ ብዙዎቹ ጳጳሳት ከሰው ጋር መገናኘታቸውን በልክ እንዳደረጉት ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡ አባ ህዝቅኤልም ከጸሀፊነታቸው ለቅቄአለሁ ሲሉ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ተከትሎ ሲኖዶሱ መልቀቂያ ያስገቡበትን ምክንያት እንዲያጣራ ኮሚቴ መሰየሙ ተሰምቷል። አባ ህዝቅኤል ቤተክህነት መካሪም አማካሪም ሰው የለበትም ወይ ያሰኘውን አሳፋሪውን የሲኖዶስ መግለጫ አላነብም በማለታቸውም የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም ናቸው ያነበቡት ተብሏል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቤተ ክህነቱን በአሁኑ ሰዓት እያመሱ ያሉት ሦስት ባለስልጣናት መሆናቸው ሲታወቅ እነርሱም ዋና ስራ አስኪያጁ አባ ፊልጶስ፣ ዋና ጸሀፊው አባ ህዝቅኤልና ምክትል ስራ አስኪያጁ ተስፋዬ ውብሸት ናቸው ተብሏል፡፡

5 comments:

 1. mkidusans ቤተ ክርስቲያንን እንደ አንድምድራዊት ድርጅት በመቍጠር፣ ህልውናዋን የእግዚአብሔርን ቃል በጥራት በማስተማር ሳይሆን በምድራዊ ጥበብና በሥጋዊ ኀይል ለማስጠበቅ ላይ ታች ይላሉ። የቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት በወንጌሉ ቃል ሳይሆን ተረት በመሰለ ትምህርት እንዲሞላ ለማድረግ ይታገላሉ። ቤተ ክርስቲያን በቃለ እግዚአብሔር ወልዳ ያሳደገቻቸውንና ደረሱልኝ ብላ ተስፋ የጣለችባቸውን አገልጋዮቿን፣ ብርሃኑን ጨለማ፣ ጨለማውን ብርሃን፣ መልካሙን ክፉ፣ ክፉውን መልካም፣ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውን ጣፋጭ [ኢሳይያስ 5:20] በማለት የተለያየ ስም እያወጡ ያሳድዳሉ። በሌሎች አስታከው ወንጌልንና የወንጌል እንብርት የሆነውን ኢየሱስን ይቃወማሉ። ውስጣዊ ዐይኖቻቸው በርተው እነዚህንና ሌሎችንም ክፉ ሥራዎቻቸውን፣ ለእግዚአብሔር በእውነት ቀንተው ስሙን ካስከበሩት እውነተኛ አገልጋዮቹ ሥራ ጋር ቢያስተያዩት ምንኛ ባፈሩ! ድርጊታቸውንም እንደ ጳውሎስ ጕዳትና ጕድፍ አድርገው በቆጠሩት ነበር።

  ቤተ ክርስቲያን የገሃነም ደጆች የማይችሏት ሆኖ በክርስቶስ የተመሠረተች የእግዚአብሔር መንግሥት እንጂ፣ በሰዎች ስምምነት የተቋቋመች ምድራዊ ድርጅት ወይም “ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር” አይደለችምና ጠባቂዋ ራሱ ጌታ እግዚአብሔር መሆኑ በቅድሚያ መታወቅ አለበት።ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ምክንያት መሰደድ እንጂ ማሳደድ ከክርስቶስና ከሐዋርያቱ የተማረችው፣ የተቀበለችውም ግብሯ አይደለም። የወንጌልን ማእከላዊ መልእክት ክርስቶስን በመስበክ የምሥራቹን ቃል ታበሥራለች እንጂ፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ክርስቶስንና ወንጌሉን አትቃወምም።

  አይሁድ ለሙሴ ሕግ ቀንተው ክርስቶስን በመስቀላቸው፣ ተከታዮቹ ሐዋርያትንም ተቃውመው እስከ ሞት ድረስ በማሳደዳቸው እግዚአብሔርን አሳዘኑት እንጂ ደስ አላሰኙትም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 22, 2013 at 1:34 PM

   Excellent message!

   Delete
 2. እንዲህ ባለው ቀናተኛነት ውስጥ ጳውሎስ የተባለው ሳውልም ዐልፏል። ለሙሴ ሕግ በመቅናት እግዚአብሔርን ያገለገለ እየመሰለው የክርስቶስን ተከታዮች በጽኑ ያሳድድ ነበር። በክርስቶስ ወደ ማመን ከተመለሰ በኋላ፣ በትዝታ ወደ ኋላ ተመልሶ በአይሁድ መካከል የሰጠው ምስክርነት ይህንኑ ያስረዳል። “እኔ … የአባቶቼንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ፣ ዛሬውንም እናንተ ሁሉ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ አይሁዳዊ ነኝ። ወንዶችንም ሴቶችንም እያሰርሁ ወደ ወኅኒም አሳልፌ እየሰጠሁ ይህን መንገድ [ክርስትናን] እስከ ሞት ድረስ አሳደድሁ” [የሐዋርያት ሥራ 22:3-4]። እንዲሁም ለፊልጵስዩስ ምእመናን በጻፈው መልእክቱ፣ “ስለ ቅንአት ብትጠይቁ፣ ቤተ ክርስቲያንን አሳዳጅ ነበርሁ፤” ብሏል [3:6]። ምናልባትም ይህ በዘመኑ አይሁድ ዘንድ የቀናተኛነት ጣሪያ ተደርጎ ሳይወሰድ አልቀረም። ምክንያቱም ጳውሎስ ‘በቅንአትም ቢሆን እኔን የሚበልጥ ማንም የለም’ እያለ ነውና የሚናገረው [ቁ.4]። ይህ ሁሉ ግን፣ የሙሴ ሕግ የተሰጠው ፍጹም የሆነው [ወንጌል] እስኪመጣ ድረስ መሆኑን ካለማወቅ የመጣ ዐጕል ቅናት እንደ ሆነ ለመገንዘብ አያስቸግርም። ያለ ዕውቀት መቅናት ይሏል ይህ ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 22, 2013 at 1:35 PM

   ይህ ሁሉ ግን፣ የሙሴ ሕግ የተሰጠው ፍጹም የሆነው [ወንጌል] እስኪመጣ ድረስ መሆኑን ካለማወቅ የመጣ ዐጕል ቅናት እንደ ሆነ ለመገንዘብ አያስቸግርም። ያለ ዕውቀት መቅናት ይሏል ይህ ነው።

   Absolutely right! God bless you!

   Delete