Tuesday, January 22, 2013

ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፥ ከአጣጥ ቍጥቋጦም ወይን አይቈርጡም!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
(እርማችሁን አውጡ! ክፍል 3)
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።
የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።
ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው?
ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን?
እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥
በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ማቴዎስ ወንጌል 7፣ 7- 12
እንዲህ ባለ ሁኔታ ሁለቱም እውነት ሊሆኑ አይችሉም። ወይ "ሊቃነ ጳጳሶቻችን" አልያም ደግሞ ላይሰጥ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ላይገኝ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ ላይከፍት መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል ያለ የቃሉ ባለቤት እግዚአብሔር ሐሰተኞች ነው። ታድያ ማን ይሁን እውነተኛ? እግዚአብሔር ወይስ እነ አቡኑ? መልሱ ቀላል ነው ቀጥለው እንደሚከተለው የሚቀርቡትን ሦስት መጠነኛ ትንተናዎች ልብ ብለን እንከታተል።
v    ቃሉ "ለምኑ ይሰጣችሁማል" እንዲል እነ አቡኑ ደግሞ በበኩላቸው "ከዚህ በላይ? ከዚህ በላይ ጸሎትማ ውሰደኝ እንደ ማለት ነው የሚሆነው … እንዲህ ያለ ልመና/ጸሎት/ሱባዔ የት አለ? ... ከመጸለይ/ከመለመን አልቦዘንም … ብለን ብለን ደክሞናል … ሳንለምን/ሳንጸልይ ቀርተን አይደልም የሚሰማ አጥተን ነው እንጅ" ያሉ እንደሆነ አንድ አስተዋይ ሰው "መቼም አለመናችሁም/አልጸለያችሁም አይባልም ግን ምን ብትለምኑ ነው?” በማለት በጥያቄ ላይ ጥያቄ መሰንዘሩ አይቀርም። እውነት ነው እነ አቡኑ ምን ቢለምኑ ይሆን ጸሎታቸውና ልመናቸው ሳይሰማ ቀርቶ አገር ምድሩን እንዲህ እያወኩትና እያመሱን የሚገኙ? እንደው እነ አቡኑ ጉዳቸው ብዙ ስለሆነ ምእመኑን "ሲፎግሩት" ነው እንጸልይ የሚሉ እንጂ ላይጸልዩም/ላይለምኑም ይችላሉ የሚል እምነትም አለ። ሰው ሰላምን ፍለጋ ጸልዮ ሲያበቃ ሁከትን የሚያጭድ ነገሩ እንዴት ቢሆን ነው? በማለት የሚጠይቁም ተሳስተዋል አይባሉም ጥያቄአቸው እውነትነት አለው፤ ባይለምኑ/ባይጸልዩ ነው እንጂ ሰላምን ፍለጋ ወደ እግዚአብሔር ጸልዬው ሲያበቁ የለመኑትን የማያገኙበት ምክንያት ምንም የለምና።
         እዚህ ላይ ግን ልብ ማለት የሚያስፈልገው ጸሎት ማለት ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ማለትም ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሰማውና መልስ የሚሰጥበት ጸሎት በፊቱ ቆመን ስናበቃ ለይስሙላ በአንደበታችን የምናነበንበው ሳይሆን በልባች የምናስበውና የምናሰላስለውን ነው። እንዲህ ካልሆነማ እግዚአብሔር ዓይን እያለው ከማያይ፣ ጆሮ እያለው ከማይሰማ፣ እጅና እግር እያለውም መዳሰስ ከማይችልና ከማይንቀሳቀስ ከዳጎን በምን ተለየ?  
v    ቃሉ "ፈልጉ ታገኙማላችሁ" እንዲል አሁንም አያፍሩምና ዓይናቸውን በጨው ያጠቡ አንዳንድ መነኮሳቶቻችን "በፍለጋ እግራችን ቀጠነ … ምላሳችን ደማ … እንደው ያልሞከርነው ሁከት ልቀቅብን ብለን በመጸለይ ሰላም እናገኝ እንደሆነ ነው ...” ማለታቸው አይቀርም። በነገራችን ላይ "ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው?” ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንዲል በአንጻሩ ደግሞ እነ አቡኑ የለመዱት በየመንደሩ የደቀሉት የሆነ እስኪሆን ድረስ "አላውቅልሽም!” ማለት ስለሆነ መታወቂያቸው ከእነ አባ ጋር በአባትና በልጅ መካከል ያለው የመስጠትና የመቀበል ርዕስ አንስተን መወያየት አይቻልም። የሀገሬ ሰው "በቅሎ አትወልድም የወለደም አትወድም" እንዲል እንጀራ ለለመነ ድንጋይ፣ ዓሣ ለሚለምንም እባብ ከመስጠት የማይመለሱ "ሊቃነ ጳጳሳቶቻችን" እግዚአብሔር በራሳቸው ልክ ቢሰፍሩት ምን ይደንቃል? እንደው ለእኔ የሚደንቀኝ ተቃራኒው ያደረጉ እንደሆነ ነበር።
v    ቃሉ "መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል" እንዲል አንኳኩተህ የሚከፈት በር ካለ የሚከፈት በር ብቻም ሳይሆን ተክፍቶልህ ገብተህ የጥያቄህ ያክል ማለት የፈለግከውንና የሚያስፈልግህን ይዘህ የምትወጣበት በር ካለ ሊቃነ ጳጳቱ የማን ቤት በር ለማንኳኳት ቢሰማሩ ነው አይሉም ውድ አንባቢ? ምሥጢሩ ያለው ወዲህ ነው የሚያስፈልግህ ብቻ ሳይሆን ምትፈልገውም አታገኝም እንጂ በር ለማንኳኳት ለኳኳቱማ ማንም ቤትም ቢያንኳኩ "ይቅርታ ተሳስተዋል … ምንም ልረዳዎት አልችልም …" ብሎ በሩን ጥርቅም አድርጎ ሊዘጋቦትም ይከፈታል። አላውቅም የማያውቀው "የተማረ" ቅሌታም ቤት ያንኳኩ እንደሆነም የተሳሰተ አቅጣጫ ሊጠቁምዎ በር ሲንኳኳ ሰምቶ ተንቀዥቅዦ በሩን መክፈቱ አይቀርም። ለአመሉ ማንኳኳት የማያስፈልገው ዘው ተብሎ የሚገባ በርም አለ። እንግዲያውስ "ሊቃነ ጳጳሳቶቻችን" ከእነዚህ ሦስት የመጨረሻ በሮች አንዱ በር ላይ ገብተው ለመቅለጣቸው የሚጠራጠር ሰው ካለ ይህ ሰው በሩን ከፍቶ ያስገባቸው ሰው ብቻ መሆን አለበት። ጨርሰው ቀልጠዋል አላልኩም። የገቡበት በር የተሳሳተ በር እንደሆነና መውጣት እንደሚገባቸውም በማመን አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ትክክለኛውን በር ለማንኳኳት የተጉና የተሰለፉ እንደሆነ ያለ አንዳች ጥርጥር በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ተባርከው፣ ለራሳቸው ሰላም አግኝተውና አርፈው ሌላውን እንደሚያሳርፉና ሰላም እንደሚሰጡ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ባለሙሉ እምነት ናቸው። 
በተፈረ ማናችሁም ብትሆኑ ፈሪሐ እግዚአብሔር ከራቀባቸው የተራ ተራ ግለሰቦች ጆሮቻችሁ ካልመለሳችሁ የምታመጡት/የምታወርዱት ሰላም አይኖርም። ይልቁንስ እዚም እዛም በመገኘትና በመሰባሰብም ለእግዚአብሔር ቤት የገባውን ገንዘብ በከንቱ በማባከን በበደል ላይ በደል አትፈጽሙ። በአማርኛ ቋንቋ ሲጻፍ ሰላምና ዕረፍት ያለው እግዚአብሔርን በመስማት፣ ራስህንም ከስሜትና አጉል ጥብቅና በመጠበቅ ውስጥ ነው ያለው እያልኩ ነው።
ለነገሩ እማኮ ቀሪ የማይገኝበት: በሌሊት በጨለማ እየገሰሰገሰ "አደራህን … አንተ ታውቃለህ ..." በማለት ያገኛትን በሙዳዬ ምጽዋትና ለነዳያን ጥሎና ሰጥቶ አጥር ተሳልሞ የሚመለሰውን በደንብ የማያውቃችሁ አጥር ተሳላሚ ምእመን ይመስለው እንደሆነ ነው እንጅ አንድ መሆን፣ መታረቅና መስማማት ያቃታችሁኮ ከራሱ ከእግዚአብሔር ስምምነትና አንድነት አቁማችሁ ያተረፋችሁ መስሎአችሁ ሀገራዊ ፍቅርም ሆነ የትውልድ ሸክም ከሌላቸውና ከማይሰማቸው ከምናምንቴዎች ጥላ ሥር ራሳችሁን የደበቃችሁት ዕለት ነው።
ይነበባል ወይ? እርስ በርሳችሁ መታረቅ ያቃታችሁ ለራሳችሁ ከራሱ እግዚአብሔር ስላልታረቃችሁ ነው። ለመሆኑ ማን ያበደ ነው ከግንዱ ከተለየ ቅርንጫፍ የሚበላ ፍሬ የሚጠብቀው? እስቲ በሮቻችሁን ዘግታችሁ ውዮ! በሉና ከዚህም በኃላ በሰው ፊትም የቆማችሁ ዕለት ሽታችሁ የሚያቅታችሁ ነገር ይኖር እንደሆነ እግዚአብሔር ውሸታም እናደርገው።
የዘንድሮ መነኮሳትና ሊቃነ ጳጳሳት እንደሆናችሁ ነገር ዓለሙ ተቀላቅሎባችሁ በቴሌቪዥን መስኮት መታየታችሁንና በሬድዮ ስማችሁን መጠራቱ ብርቅ ሆኖባችሁ ሰልፍ ያዛችሁ እንጅ የምትናገሩት ቋንቋና የምታስተላልፉት መልዕክት የምታውቁም አይደላችሁም። ይህ ሁሉ ትታችሁ ግን ስለ ራሳችሁ እንዲሁም የሕዝባችሁም በደል ይዛችሁ በፊቱ "ምሕረትህ ለዘልአለም ነው!” ብላችሁ ስታበቁ በሰላም ፈንታ የጦርነት መንፈስ ይወርድ እንደሆነ ለምን እግዚአብሔርን አንፈትነውም? መፈታተን እንጅ ፈትኑኝ ያለ እግዚአብሔር መፈተን ነውር የለውም። ልፋ ያለው መጫኛ ይጎትታል ነው የሚባለው ለነገሩ ለእግዚአብሔር የሚሆን ጊዜ  ሲኖራችሁ አይደለም ወይ?  
አንባቢ ሆይ! ዛፍ ሁሉ ከፍሬው እንደሚታወቅ የሚዘነጉት ሐቅ አይመስለኝም። ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፥ ከአጣጥ ቍጥቋጦም ወይን አይቈርጡም። እንግዲያውስ ሰው በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና መልካም ሰው ከልብ መልካም መዝገብ መልካሙን እንደሚወጣው፥ በስራውም ሁሉ መልካም የሆነ ነገር ሁሉ እንደሚያደርግ እንዲሁም ክፉ ሰው ደግሞ ከልብ ክፉ መዝገብ በሥራውም ሁሉ ክፉ ሥራ/ድርጊት እንደሚሰራና እንደሚፈጽም ጥያቄ ይኖሮታል ብዬ አልጠራጠርም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ "ቤተ ክርስቲያን" የሃይማኖት መሪዎች የገቡበት አዘቅትና የደረሰባቸው መንፈሳዊ ኪሳራም የሳምንትና የሁለት ሳምንት የጾም ጸሎት አዋጅ በማወጅ የሚፈታ ችግር ሳይሆን ራስህን ለእግዚአብሔር ግልጽ በማድረግና በማሰብ የሚፈታ ችግር ለመሆኑ በባለ አእምሮ ዘንድ እንዴት ይሳታል? ራሳችሁን ግልጽ  አድርጉ። በተከታታይ ለሦስት በተለያዩ ክፍሎች ተዘጋጅቶ ለንባብ የበቃውን ጽሑፍ እዚህ ይጠናቀቃል።


ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
United States of America
January 17, 2013

8 comments:

 1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 22, 2013 at 6:53 PM

  ጌታ ይባርክህ! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

  ReplyDelete
 2. ቃለ ሕይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 3. ኢንዳንተ ካለውም ኢባብ መርዝ ኢንጂ ምንም ኢንደማይገኝ በጽሁፍህ ላይ የሚታየው አነጋገርህ ይመሰክራል። ይልቅ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሳ። ጳጳሳቱ ጋር ችግር ካለብህ ለነሱ በአካል ሄደህ ወይም ጽሑፍህን ለነሱ ልከህ ንገራቸው። አለዚያም እውነተኛ ሃይማኖትና ምግባር ካለህ ሁሉን ለሚችለው አምላክ ልትጸልይ ኢንጂ ኡኡ አገር ይስማልኝ ጻጻሳት ተሳሳቱ ወዘተ እያልክ ለአንባቢያን መርዶ ውዥንብር መንዛት አይገባህም ነበር። ያንተን የት አስቀምጠህ በቤተክርስትያንዋ የወቅቱ ችግር ጳጳሳቱን ብቻ ተጠያቂ የምታደርገው። እስቲ ብዕርህን ለራስህ ማስተማርያ ተጠቀምበት። ምላስን ለመልካም ተጠቀምበት እንደ እባብ መርዝ አትትፋበት።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Kale hiywot yasemaln!!!

   Delete
 4. የዘንድሮ መነኮሳትና ሊቃነ ጳጳሳት እንደሆናችሁ ነገር ዓለሙ ተቀላቅሎባችሁ በቴሌቪዥን መስኮት መታየታችሁንና በሬድዮ ስማችሁን መጠራቱ ብርቅ ሆኖባችሁ ሰልፍ ያዛችሁ እንጅ የምትናገሩት ቋንቋና የምታስተላልፉት መልዕክት የምታውቁም አይደላችሁም። ይህ ሁሉ ትታችሁ ግን ስለ ራሳችሁ እንዲሁም የሕዝባችሁም በደል ይዛችሁ በፊቱ "ምሕረትህ ለዘልአለም ነው!” ብላችሁ ስታበቁ በሰላም ፈንታ የጦርነት መንፈስ ይወርድ እንደሆነ ለምን እግዚአብሔርን አንፈትነውም? መፈታተን እንጅ ፈትኑኝ ያለ እግዚአብሔር መፈተን ነውር የለውም። ልፋ ያለው መጫኛ ይጎትታል ነው የሚባለው ለነገሩ ለእግዚአብሔር የሚሆን ጊዜ ሲኖራችሁ አይደለም ወይ?

  ReplyDelete
 5. ሙሉጋኔን በረሃ ላይ እንደሚጮህ ቁራ ነህ። በዝባዝንኬ ፅሁፍ ተብዬህ ምን እንደምታወራ እንኳን አንባቢ አንተው ራስህ ሙሉጋኔን እንኳ አልገባህም። ለዚያውም 3ጊዜ ፅፈህ። መጀመሪያ ራስህ አይንህ ውስጥ ያለውን ምሰሶ አውጣ የሰው ጉድፍ ላውጣ ከምትል።

  ReplyDelete
 6. በእርግጥ አቡኑ አሜርካን እንደደረሰ የሚለምድ ሳይመስለው ጭንቀት በወጠረው ጊዜ እግዚአብሔርን በእንባው ይማጠን እንደነበረና የመምህር ዘበነ ጥቅሶች ዓይኑን እንደከፈቱለት፣ አንደበቱን አንደሳሉለት፣ ልቡን እንዳረጋጉለት፣ ምላሱን እንዳመነቱለት አልፎ አልፎ እንደውለታ ያነሳቸዋል። አሁን ታዲያ ያን ሁሉ እርስት አድርጎ ና ወንጌልን አስተምረን ተብሎ ሲጠራ “አንድ ዘማሪ ይዤ ካልሆነ አልመጣም” ይላል፣ ገንዘብም ይደራደራል። ታዲያ ሙያዉ ጋዘጠኝነት ነው ወይስ የወንጌል አስተማሪ? እንደውም ናሽቭል ቴንሲ ሄዶ አኩርፈው እና ተጣልተው የወጡት ወገኖች ነባሩን ቤተክርስቲያን የሚያፈርስ ትምህርት እየጠቀሰ ቤተክርስቲያን ማፍረስ የሚያጸድቅ መሆኑን እንዲያስተምር በጥሩ ክፍያ ተደራድሮ ሁለት ቀን ተኩል ደክሟል። እንደዉም ደጋግሞ “ወገኖቼ አሁን እዚህ የተሰበሰባችሁት ምክኒያቱ በግጭት፣ በቂም በቀል፣ በጥል፣ በልክ እና እንደዚህ ከሆነ ተመለሱ ካለበለዚያ ቤተክርስቲያን መሥርቱ” በማለት የባሰ አበጣብጦ እና መሠረት ጥሎ ገንዘቡን ተቀብሎ ሄደ። ነገር ግን ወንጌሉ የትም ቦታ ላይ አስታርቁ፣ አንድ አድርጉ፣ በጎቹን አውሬ እንዳይበላቸው በአንድ በረት ሰብስቡ እንጂ በትኑ የሚለውን ጥቅስ ከየት እንዳመጣው አይታወቅም፡፡ የድፍረቱና የንቀቱ ብዛት ከዚያ በፊት በተደጋጋሚ መጥቶ የቀደሰበትን የአምላኩን የመድኃኒዓለምን ቤት ሳይሳለም እና ወንጌል ያስተማረውን፣ እንጀራ በአፉ ያጎረሰውን፣ በኪሱም ደጎስ ያደረገውን ምእምን ሰላምታ ቀርቶ ሳያየው እንኳን መመለሱ እጂግ ከማሳዘኑም በላይ የራሱ በወንጌል አማኝነቱ ያጠራጥራል። ታዲያ ቤተክርስቲያን በቂም ካልተመሠረተ የተቀየመውን ሕዝብ እና እርሱን እራሱን አስታርቆ ወንጌሉን ለሁሉም ባስተማረ ይጸድቅ ነበር። ለማስታወስ ያክልም አቡነ አብርሃምም ልክ እንደዚሁ ነው ያደረጉት፤ ልዩነታቸው እሳቸው ታቦት ይዘው መምጣታቸው ብቻ ነው። የሚገርመው ነገር እሳቸወም ለሌላው አኩራፊ ያሉት “እኔ አሁን እዚህ የመጣሁት ቤተክርስቲያንን ልከፍል ሰዉንም ልለያይ አይደለም… ”ያላስተማሩት የለም ብቻ ብዙ ብለዋል እናሕዝቡን አስገርሞታል። እሳቸውም እንደመምህር አቡኑ የቀደሱበትን የመድኃኒዓለምን ቤተክርስቲያንና ሕዝብ ሰላም ሳይሉ ግን መጋዘን እና በረት ውስጥ ያለ ህዝብ ብለው ሙልጭ አድረገው ተሳድበው ሄዱ። አሁን ደግሞ ሰለእርቅ እና ስለሰላም እሳቸው ፊት የሚያነሳ መለዓክ፣ ጳጳስ፣ መነኩሴ፣ ቄስ፣ ምዕምን፣ ወታደር ወይም ወንድ እንኳን አይገኝም። ታዲያ እንዲህ ዓይነቱ ወንጌላዊነት ከሆነ እስላም አክርሮ ክርስቲያንን ማሳደድ ቁራናዊነት ትክክል ነው ማለት ነው።።

  ReplyDelete