Wednesday, January 23, 2013

የጸረ ተሀድሶ ሰባክያን ጥምረት ቡድን ተበተነ

ጥምረቱን ከመበተን ለማዳን አሉላ እየሰራ ነው
ማቅ በመለመላቸው ሰዎች ያደራጀውና በገንዘቡ የሚደግፈው የጸረ ተሀድሶ ሰባኪዎች ጥምረት እያለ ራሱን የሚጠራው ጸረ ወንጌል ቡድን መበተኑ ተሰማ፡፡ ባለፈው የቱሪስት ሆቴል መዘጋትን ተከትሎ በውስጡ ይሰበሰቡ የነበሩ ሰባኪዎች መሰብሰቢያ ማጣታቸውን ገልጸን ነበር። ባወጣነው ዘገባ መነሻነት መረጃው እንዴት ሾልኮ ሊወጣ ቻለ በሚል የቡድኑ አባላት እርስ በርስ ሲካሰሱና ሲጣሉ መሰንበታቸው ታውቋል፡፡ ለመረጃው ሾልኮ መውጣት የቡድኑን አባል ዘሪሁን ሙላቱን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን ይህን ተከትሎ በ5/5/2005 ወደ ሐረር እንዲጓዙ የተመደቡት ተስፋዬ ሞሲሳና ዘሪሁን የነበሩ ሲሆን ጥምረቱ ተስፋዬን ልኮ ዘሪሁን እንዲቀር አድርጓል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለተስፋዬ ሞሲሳ ጋብቻ የጥምረቱ አባላት 100 ብር በነፍስ ወከፍ በህሩይ ባዬ (ወቅታዊ ስሙ ማጠልሸት ነው የማቅን ስም ለማጥፋት ሆነ ብሎ የገባ ነው ይሉታል) እጅ እየሰበሰቡ የነበረ ሲሆን ዘሪሁን ከሀረር ጉዞው መታገዱን ተከትሎ ብሩ ይመለስልኝ ሲል ጠይቋል ተብሏል፡፡ ሌላው የቡድኑ አባል ጳውሎስ ዱከሌ ከ3ኛ የሴት ጓደኛው የተበረከተለት አይፎን ሞባይል በመጥፋቱ እጅግ በጣም ከማዘኑም በላይ ክፉኛ መደንገጡን ቅርብ ጓደኞቹ ተናግረዋል፡፡ የደነገጠውም ጸያፍ ምስሎችን ስለጫነበት ነው ተብሏል፡፡ አሁን  የጥምረት ተብዬው ትልቁ ስጋትና ፍራቻ ዘሪሁን በለመደ እጁ መጽሀፍ እንዳያወጣብን የሚል ሲሆን እርሱም በእርግጠኝነት እንደሚያወራው በቅርብ ቀን ጉድ ጠብቁ ብሏል ተብሏል፡፡

በዚህ ቡድን ዙሪያ ይህን ዘገባ ያወጣነው መረጃው ትክክለኛ ስለሆነ የግለሰቦቹን ስም ለማጥፋት ብለን አይደለም ማንኛውም ሰው እንደዚህ ካለ ድካም ነጻ አይደለምና፡፡ ነገር ግን የወንጌልን ስራ ለማደናቀፍና እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ከመድረክ በማግለል መድረኩን ለመቆጣጠር ማቅ የሰበሰባቸው እነማን እንደሆኑና አላማቸው ቤተክርስቲያንን ማገልገል ሳይሆን ለወንጌልና ለቤተክርስቲያን የቆሙትን እውነተኞች ማሳደድ፣ ወንጌልን መቃወምና በዚህ ገቢ ማግኘት መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ በቅርቡ ማለትም በህዳር ወር መጨረሻ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም በተዘጋጀው የሶስት ቀን ጉባኤ ላይ ከተጋበዙት መምህራን መካከል የጥምረቱ አባል ዳንኤል ግርማ አንዱ ነበር፡፡ እርሱም እንደለመደው ወንጌል ሳይሆን ተሀድሶን በመስደብና በመርገም ጊዜውን ሲገድለው ወንጌል ሊሰበክበት የሚገባውን አውደ ምህረት የስድብ መድረክ ማድረጉን መታገስ ያልቻለው የደብሩ ሰባኪ ወንጌል ማይኩን በመቀበል «ይህ የተቀደሰ ቦታ ጠብ ክርክር ነቀፋ የሚሰበክበት ሳይሆን ወንጌል ብቻ የሚሰበከበት ነው» በማለት ለምእመኑ ይበል የሚያሰኝ ማስተካከያ ሰጥቷል፡፡ ዳንኤል ግርማ በስድብ በተሞላ ስብከቱ ውስጥ «ሲጋራ የሚያጨሱ መነኮሳት አሉ» የሚል በአውደ ምህረት ላይ ሊነገር የማይገባ ነገር በመናገሩ የደብሩ አባቶች ተቆጥተው «እንዲህ ያለ ተሳዳቢና ስም አጥፊ ለምን ተጋበዘ? ሌላ ሰባኪ ጠፍቶ ነወይ» እስከማለት ደርሰው ነበር ተብሏል፡፡ የደብሩ ሰባኪ በሶስተኛው ቀን መምህር ተረፈን ጋብዞ ንጹህ ወንጌል በማስተማሩ ካህናቱም ሕዝቡም ንጹህ ወንጌል ሰምተው እጅግ ተደስተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የተበተነውን ጥምረትን ከውድቀት ለማዳን ሌተቀን እየለፋ የሚገኘው አሉላ ጥላሁን ሲሆን ይህ ግለሰብ አዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ ይሰራ የነበረና ከማቅ ጋር በቅርበት ይሰሩ የነበሩት  የጋዜጣው አዘጋጆች እነመስፍን ነጋሽ ከአገር ከወጡ በኋላ አሉላም ኢሚግሬሽን ፓስፖርት ለማውጣት ሄዶ የነበረ ሲሆን አንድ ቀን ሙሉ ታስሮ መዋሉ ታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደጀሰላም ድረገጽ ላይ ይጽፋል እየተባለ በስፋት የሚጠረጠረው እርሱ ነው፡፡ ምንም አይነት ስራ ሳይኖረው የቤት ኪራይ ቀለብ አሁን ውጭ ያለው ምንአልባትም ደጀሰላምን የመሰረተውና የከፈተው ኤፍሬም እሸቴ  በሚልክለት ገንዘብ አንዳንዴም ዳንኤል ክብረት የሚደጉመው መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ገንዘቡ ሲዘገይበት በኢንተርኔት መደወል እንደሚያዘወትር ለአሉላ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡

አሉላ አብዛኞቹን የመጽሄትና የጋዜጣ አዘጋጆች ስለሚያውቃቸው ማኅበሩ በግል ሚዲያ ለሚያስተላልፋቸው መልእክቶች በመካከል ሆኖ በመላላክ ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው እርሱ ነው ብለዋል፡፡ በአንድ ወቅት ዳንኤል ክብረት በማህበሩ ላይ የጻፈውን ጽሁፍ ከማቀነባበር ጀምሮ ብሎግ ላይ እስከማውጣት ያበቃው አሉላ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች በዚያ ሰሞን ዳንኤልና አሉላ አዘውትረው ይገናኙ እንደነበርና ከዚያ በኋላ ጽሁፉን እንደተለቀቀ ሲታወቅ ያ ወቅት ደጀሰላም በአሉላ የሚንቀሳቀስና የማህበሩ በተለይ ውጭ አገር ያሉ ሰዎች እጅ እንዳለበት የታወቀበት ጊዜ ነው ይላሉ ምንጮች፡፡         6 comments:

 1. Alula ye deje selam tsehafi beteamir ayihonim.We know him in Addis neger how much he is a committed person to truth. Those who write in dejeselam are persons simple minded like you.

  ReplyDelete
 2. Egzioo ewenet mechem tekoyalech enji mech tedbeka tekeralech Egziabher yebarekachehu abaselamawoch ene betam azenalhu be mk mk mk eourop ( be Germen Frankfurt) yalut tikit mk betkersteyanin agelgayochen betibet adergew neber Egziabeher gin tilk new sew yerasu hateyat tasadedewalech yetbalew be nesu taye ahun kefrankfuert Q mareyam tergerg belew hedewal hizebum awekowachewal bertu ewenet endetsehay tewetalech

  ReplyDelete
 3. አይ አቶ ዘሪሁን ሙላቱ የቤተክርስቲያንቱን ትምህርት ሳትማር ሊቀ ጠበብት አሉህ
  ጋና ዲዘርተሸን አንኳን ሳታቀርብ ዶ/ር አሉህ ታዲያ አንተን የመሰለ አፉ ምድጃ አግንጫው ጭስ ማውጫ የሆነ ሁለ እንደ ፍየል ቅጠል የምትበላ (ጫት ቃሚ) እንደ ውሻ ያበለህ ሁሉ ጌታህ የሁነ 10 ብር ካሳዩህ ለእስላምና ሳይቀር ጹሑፍ የምትጽፍ ስላንተ የማይታቅ መስለሆህ ከሆነ ተሳስተሃል ይህን ጹሑፍ ያንተ መሆኑን በሚጋባ ይታወቃል ከዚህ በኃላ አርፈህ የማትቀመጥ ከሆነ፡-
   የሴት ጋደኞችህን ዝርዝር ከነፎቶዋቸው
   ለሙስልሞች በገንዘብ ኢየሱስ ክርስቶስን ሰደብህ የጻፍከውን ጹሑፍህን ከነሙሉ እጅ ጹሑፍህ
   በአሁኑ ሰዓት በምን ተግባር ላይ እንደሚተገኝ የሚያትት ጹሑፍ ይፋ ይሆናል
  ባላጌን ከሳደጌ የገደለ ይጸድቃል፡፡ አንተን መታገስ ይብቃ እስክ አንተ በእጅህ ላይ ያሰረከው የሱዳኑ ጥንቆላ የሚያደርገንን እናያለን ያንተ ሠይጣን የሰው እጅ እዳትሳለምና ቀይ ነገር እነዳታይ ከልክሎሃል አሁን ግን ሁሉን ካልከለከለህ……..

  ReplyDelete
 4. አባ ሰላማዎች
  የተሐዲሶ በሎግ መሆኑን አውቀናል
  እናንተም ከማውራት ያለፈ ነገር የላቸሁም
  በእናተው ብሎግ ቅዱሳን ተሰደቡ
  እመቤታችን ተሰደበች
  ጅብኮ የማያቁት ሀገር ሄዶ ነው ቁርበት እንጥፉልኝ የሚለው
  አባ ሠረቀና መሳዮቹኮ ከአባ ጳውሎስ ጋር ተቀብራዋል በድነ ሥጋቸው ነው የሚሄደው
  ምን እናድርግ ከእግዚአብሔር መቅደም አይቻልም በቃ ተሐዲሶኮ ግባተ መሬቱ ተፈጽሟል
  ርዥራዦች ብጮሁ የት ልደርሱ በቃ በቃ በቃ ቻው

  ReplyDelete
 5. we want to know the reality (truth). why people attack the truth?

  ReplyDelete