Saturday, January 26, 2013

ለአቶ ማንያዘዋል የተጻፈው ደብዳቤና አንድምታው

ስለማንያዘዋል ከዚህ ቀደም ስንዘግብ ነበር፡፡ አንዳንዶች የምንዘግበውን ሐሰት ነው ሲሉ የቆዩ ቢሆንም ከአቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የተጻፈው ደብዳቤ ግን እስካሁን ስንዘግብ የነበረው ሁሉ እውነት መሆኑን ያረጋገጠ ነው፡፡ ማንያዘዋል በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ ስላሴ ኮሌጅ ገብቶ በሰዎች ድጋፍ እንደምንም «ተመርቆ» ቢወጣም ቤተክርስቲያኗ በአቶነቱ ነው የምታውቀው፡፡ «ፊደል ዳገቱ» ማን ያዘዋል ለማቅ «መምህር» ቢሆንም እኛ ግን በትክክለኛ ማእረጉ አቶ ማንያዘዋል እያልን ነበር የምንጠራው፡፡ የአቃቤ መንበሩ ደብዳቤም አቶ ሲል ነው የጠራው፡፡
በዘንድሮው የጥምቀት በዓል በተሰራ አንድ ፕሮግራም ላይ ማን ያዘዋል በኢቴቪ መስኮት ብቅ ብሎ ስለ ቤተክርሰቲያን ለማስረዳት ሲውተረተር ታይቷል፡፡ ይህን አቶ በመምህር ደንብ ጋብዘው እንዲደሰኩር እድሉ ተመቻችቶለታል፡፡ ይህም አንዳንድ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ውስጥ ያሉ የማቅ ሰዎች ያደረጉት እንደ ሆነ ይታወቃል፡፡ ቤተክርስቲያን «አቶ» ያለችውን ማንያዘዋልን ደብዳቤ ከተጻፈበት በኋላ ከቤተክህነት ግቢ ቢታገድም አለ ለማለት ያህል ይህ እንደተደረገ ተገምቷል፡፡ ኢቴቪ ላይ ስሙ ተጽፎ የተነበበውም አቶ ማንያዘዋል አበበ ተብሎ ነው፡፡
በአቶ ማንያዘዋል ላይ አቃቤ መንበሩ በጻፉት ደብዳቤ ውስጥ «የነገረ መለኮት ምሩቃን ማህበር ኃላፊ ነኝ በሚል ሰበብ በመንበረ ፓትርያርክ ቅጽረ ግቢ ሲንቀሳቀሱ የሚታዩት ….» እያለ ይቀጥላል፡፡ ባለፈው ባቀረብነው ዘገባ ላይ የጠቆምነው ይህንን ነበር፡፡ የቴዎሎጂ ምሩቃንን ያላቀፈውና በቴዎሎጂያን ስም የማቅን ጥቂት ቅጥረኞች ያሰባሰበውና ራሱን «የነገረ መለኮት ምሩቃን ማህበር» እያለ የሚጠራው የማቅ ፓርቲ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ ቢሮ የከፈተው የውጭ ምንዛሬን ጨምሮ ሌሎች ድብቅ ስራዎችን ለመስራት እንደ ሆነ መጥቀሳችን ይታወሳል፡፡ የአቃቤ መንበሩ ደብዳቤ ቢሮው የተከፈተው ለሰበብ መሆኑን መጥቀሱ ይህን የማቅ ድብቅ ሥራ ሳይደርስብት እንዳልቀረ አመላካች ነው፡፡
ለደብዳቤው መጻፍ ምክንያት የሆነው ግለሰቡ ያሳየው ጣልቃ ገብነት ነው፡፡ «አቶ ማንያዘዋል አበበ ከአንድ መንፈሳዊ ሰው በማይጠበቅ መንገድ በማይመለከታቸው ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ቤተክርስቲያኒቱን ለመከፋፈል ላይና ታች እያሉ አላስፈላጊ ተግባር ሲፈጽሙ እንደሚገኙ ተደርሶባቸዋል፡፡» ይላል ደብዳቤው፡፡ ማቅ አቡነ ጳውሎስ ካረፉ ወዲህ በቤተ ክርስቲያኒቱ መጠነ ሰፊ ጣልቃ ገብነት እያሳየ መሆኑ ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ ለዚህም በዋናነት ሲንቀሳቀስ የነበረው በማንያዘዋል በኩል ነው፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሱዳን ወደ አዲስ አበባ መጥተው ለቤተክርስቲያናችን ካህናት ተሐድሶን የሰበኩት የግብጽ ቀሳውስት በልማት ኮምሽን ህንጻ ውስጥ በሚሸኙበት ፕሮግራም ላይ ማንያዘዋል የራሱን ጣልቃ ገብነት ለመሸፈን ሲል «መንግስት ጣልቃ እየገባ አስቸገረን እኮ» በማለት ፊት ለፊት መናገሩ ተሰምቷል፡፡ (የግብጽ መነኮሳትን የተሐድሶ መልእክት በቅርቡ ለማቅረብ እንሞክራለን)፡፡
ማንያዘዋል ከዚህ በፊትም ጳጳሳትን በመለያየት ቤተክርስቲያንን የመከፋፈል ከፍተኛ ስራ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይህ በተጨባጭ ስለተደረሰበትም ነው ቢሮው እንዲታሸግ እርሱም ፈጽሞታል የተባለው አላስፈላጊ ድርጊት እስኪጣራ ድረስ ከጥር 3/2005 ጀምሮ ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ዝር እንዳይል እገዳው የተጣለበት፡፡
ተፈጽሞአል የተባለው ድርጊት ምን ይሆን? ለነገሩ አቶ ማንያዘዋል ስሙ ተጽእኖ ሳያደርግበት አይቀርምና ማንም አያዘኝም በሚል ከደብረ ብርሃን ጀምሮ በሃይማኖት ስም ወንጀል እየፈጸመ የመጣና ከደብረ ብርሃን የወጣውም በወንጀል መሆኑን የሚያመለክት ዘገባ ከደብረ ብርሃን ምንጮቻችን ደርሶናል ወደፊት እናቀርባለን፡፡
  

4 comments:

  1. Are you saying the TPLF government is not interfering in our church's internal affairs? I don't know much about Manyazewal's personality. However, I agree with him about government's interference in our church's matter. It is well known fact. Who is leading the church in Ethiopia now ? Of course TPLF :: Who else ???

    ReplyDelete
  2. KEMAYREBA THEOLOGIAN WEYM LELA SHUM ATO BE SINT TAMU...AHUN ANTE MA TBAL YIHON...LIQE LIQAWNT WEYS LIQE DIYAQON..WEYS MEGABI...WEYS PASTOR...SINT MAFERIA ALE ?

    ReplyDelete