Sunday, January 27, 2013

የዳንኤል ክብረት ክሽፈት ጥር 2005
አቶ ዳንኤል ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው እውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ አንጂ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም፤ አቶ ዳንኤል ሳላውቀው በጻፈው ላይ አስተያየት ስሰጥ ይህ ሁለተኛዬ ነው፤ ከዚህ በፊት በአንድ ጋዜጣ ላይ በጣም የታወቀውን የአየርላንድ ችጋር 150 ዓመታት ያህል አቅርቦት በማየቴ አስተያየት ሰጥቼበት ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ስለመክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ በጻፈው ላይ አጭር አስተያየት ልስጥ፤ እንዲያው እንትንን እንትን ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል የሚባለውን በመከተል እንጂ ትርፍ ይኖረዋል ብዬ አልገምትም፤ ከደርግ ዘመን ጀምሮ የተለያዩ ካድሬዎች ደብተራዎችም ጭምር ማነብነብን እንደተናጋሪነት ሠልጥነውበታል፤ ስለዚህም ሰውም ማነብነባቸውን እንደእውቀት እየወሰደው ይወናበዳልና በጊዜው መልስ መስጠት ግዴታ ይመስለኛል፤ የሰው ልጅ በምን ይታፈራል? በወንበር፤ በወንበር አይደለም በከንፈር፤ ይባላል፡፡
ነገር ሳላበዛ ጥቂት ነጥቦችን በማንሣት የአቶ ዳንኤልን የማንበብ ችሎታና የተንኮል ክህነት ብቻ ለአንባቢዎች ላሳይ፤ ስለአስተያየቱ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ አይደለም፡፡
አንደኛ ደጋግሜ እንብቤዋለሁ ይላል፤ ይህንን ባይነግረን ጥሩ ነበር፤ በመናገሩ ብቻ እንዳናምነው ማስረጃ ይሰጠናል፤ ያላነበበውን ደጋግሜ አንብቤዋለሁ ማለት ያስፈለገበት አስገዳጅ ምክንያት ምንድን ነው? አውቃለሁ ብሎ በመነሣት ለማሞኘት ወይም ለማታለል ካልሆነ በቀር ሌላ ምክንያት ያለ አይመስለኝም፤ እንደአቶ ዳንኤል ያለውን ለማስጠንቀቅ ደጋግሜ አነበብሁት በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ‹‹የዩኒቨርሲቲን ዓለም የማያውቁ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት እንዳይሳሳቱ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በአካል በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሆነው ልባቸው ከደብተራ ተንኮል ላልጸዳም ቀናውን የእውነት መንገድ እንዲያመለክታቸው እመኛለሁ፤›› የሚል ተጽፎ ነበር፤ ይህንን አቶ ዳንኤል አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡
ሁለተኛ ‹‹ለመሆኑ ታሪክ ይከሽፋል? የክሽፈት ታሪክ ሊኖር ይችላል እንጂ የከሸፈ ታሪክ ሊኖር ይችላል? የስኬት ታሪክ ይኖራል እንጂ የተሳካ ታሪክ ይኖራል? አንድን ታሪክ ከሽፏል ወይም ተሳክቷል የሚያሰኘው ምን ምን ሲሆን ነው? … በመጽሐፉ የምናጣው ታላቁ ነገር ይሄ ነው፤›› በዚህ ትርጉም የማይሰጥ የቃላት ድርደራ ላይ ምንም አስተያየት መስጠት አይጠበቅብኝም፤ ይቀጥልና ‹‹.. የታሪክን ክሽፈትና ስኬት መበየኛ ነገሮችን አስቀድመው በማሳየት አንድ ታሪክ ከሸፈ ወይም ተሳካ የሚያሰኙትን መመዘኛዎች …›› ይላል አቶ ዳንኤል፤ ካላነበበውደጋግሜ አንብቤዋለሁበማለት ብቻ ጭንቅላቱ ውስጥ አይታተምለትም፤ የሚከተለው እንደሚነበብ ሆኖ የተጻፈ ነበር፤ ‹‹መክሸፍ የምለው አንድ የተጀመረ ነገር ሳይጠናቀቅ ወይም ሳይሳካ እንቅፋት ገጥሞት መቀጠል ሳይችል ዓላማው ሲደናቀፍና በፊት ከነበረበት ምንም ያህል ወደፊት ሳይራመድ መቅረቱን ነው፤›› ይህ ተጽፎአል! አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡
ሦስተኛ፤ ‹‹ታሪክ ጸሐፊዎቹን ከታሪኩ ጋር አብሮ መውቀጥ ከተልባ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ ዓይነት ይሆናል››! ይላል፤ ይህ ሰው አንብቤአለሁ፤ አውቃለሁ፤ ሲል በመሃይም ድፍረት ነው፤ የሚከተለው ተጽፎአል፤ ‹‹አንድ ሰው በአገርና በሕዝብ ጉዳይ ላይ ከጻፈ ‹‹ማንም ዜጋ በጉዳዩ ላይ የመሳተፍና ሀሳቡን በሙሉ ነጻነት የመስጠት መብት አለው፤ አለዚያ በየጓዳችን በሐሜት ብቻ እየተዘላዘልን እውነትን አንጥሮ በአደባባይ የማውጣቱን ዘዴ ሳንማር ሌላ ሦስት ሺህ ዓመታት እንቀጥላለን፤›› ይህንን አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡
አራተኛ በራሱ ላይ ሲፈርድ ቶሎ ሳይጽፍ መቆየቱን ለማስረዳት ምናልባት ከእሱ የተሻለ ሰው ቢጽፍ፣ ምናልባት ፕሮፌሰር ባሕሩ ቢጽፍ፣ ምናልባት የታሪክ ሊቃውንትቱ ተማሪዎች ቢጽፉ፣ ምናልባት የታሪክ ክፍሉ ቢጽፍ በማለት ጠብቆ እንደነበረ ይገልጻል፤ እነዚህ ሁሉ የሱን ምኞት እሱ በፈለገው ፍጥነት ሳያሙዋሉለት ቀሩና እነፕሮፌሰር ባሕሩን ላጨበት ሥራ ራሱን አቀረበ፤ የሱ ድፍረት የሌሎቹን እውቀት የሚበልጥ ለማስመሰል ጻፈ፤ ድፍረቱን ልናደንቅለት ይገባል፤ በማያውቁት ጉዳይ ደረትን ገልብጦ በሙሉ እምነት ማነብነብ የካድሬዎች ባሕርይ ሆኖ በቤተ እግዚአብሔርም ገብቶአል፡፡
አምስተኛ አቶ ዳንኤል ከአዋቂነት ወደመንፈሳዊነት ይሸጋገርና ‹‹አንድን አካል መልስ ለመስጠት በማይችልበት ጊዜና ሁኔታ መሄስና መውቀስ ከሞራል አንጻር ፍትሐዊ አይሆንም፤ የሀገሬ ሰውሙት ወቃሽ አትሁን››› እዚህ ደግሞ ጭራሽ ሊወጣበት ከማይችለው የአለማወቅ ማጥ ውስጥ በድፍረት ገባ! ‹‹ሞራል›› ስለሚለው ነገር ምንም እንደማያውቅ ሳያውቅ አወጀ፤ ድፍረት ብቻውን በምንም መንገድ እውቀት አይሆንም፤ ለመራቀቅ ፈልጎ ራሱን በአለማወቅ አዘቅት ውስጥ ከተተ፡፡
ስድስተኛ፤ በጽሑፉ መደምደሚያ ላይ የደብተራ ተንኮል አፈትልኮ ይወጣል፤ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ያነሣና በደብተራ ተንኮል አንዱን ‹‹ዶክተር›› የሚለውን መልክ የሌለውና ስም የሌለው የደብተራ ምሥጢር ያደርግና፤ ‹‹እኒህ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ዶክተር ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዘንድ በማን በኩል እንደሄዱ ፕሮፌሰር መስፍን ያውቃሉ፤›› ብሎ ይለጥፍብኛል፤ እግዚአብሔር ያሳያችሁ ስሙን ያልጠቀሰውንና የማላውቀውን ሰው የእኔን ስም ጠርቶ እንደማውቀው አድርጎ ሌላ ስሙን ያልጠቀሰውንና እኔ የማላውቀው ‹‹ዶክተር›› ወደመንግሥቱ ያቀረበ እያለ ውሸት ሲያጠነጥንና ሲፈትል ጊዜ ያጠፋበት ምክንያት አልገባኝም፤ ተንኮሉ እዚህ ላይ አያበቃም፤ ታደሰ ታምራትን ‹‹መንግሥቱ ከመሸኘቱ በፊት ግንከዶክተር እገሌ ጋር ቅሬታ አላችሁ መሰል፤ አንዳንድ ነገር ነግሮኝ ነበር፤ እዚያው ተነጋግራችሁ ፍቱት፤ አላቸው፤›› ይልና የመጨረሻዋን የደብተራ ተንኮል ጣል አድርጎ ይደመድማል፤ ‹‹አሁን እዚህ መጽሐፍ ላይ ቤተ መንግሥቱን አየሁት፡፡›› ምን እንዳየ፣ የት እንዳየ፣ ምንና ምን እንደተገናኘ የደብተራ ምስጢር ነው፤ ያቀረበውን ሁሉ የማን ባለሙዋል ሆኖ ያገኘው እንደሆነም አይናገርም፤ እንዲህ ያለ ሞላጫነት! ስለእውቀት ከተጻፈ መጽሐፍ ተነሥቶ ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ጓዳ ገብቶ፣ ስሙ የማይጠራ ዶክተርን መነሻ አድርጎ፣ ይህን ሁሉ እኔ እንደማውቅ ተናግሮ በድንቁርና ምርጊት ይደፍነዋል! እንዲህ ያለ ሰው ስለእውቀት ለማውራት ለምን ይነሣል? ከበሽታ በቀር ምን ሌላ ይገፋፋዋል?

42 comments:

 1. ለማስተማሪያ አግባብ ያለው ቆንጆ መልስ ፡፡ ልጅ አባቱን አሻቅቦ ... ደስ አላለኝም ነበር ፡፡ ለዛውም የብዙዎችን የቀለም አባት ፡፡

  ReplyDelete
 2. «በአካል በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሆነው ልባቸው ከደብተራ ተንኮል ላልጸዳም ቀናውን የእውነት መንገድ እንዲያመለክታቸው እመኛለሁ፤››
  ራሱን በአዋቂ ረድፍ ላስቀመጠውና ከደብተራ ተንኮል ላልጸዳው ለአቶ ዳንኤል፤ ፕሮፌሰሩ የተናገሩት የሚመጥነው አባባል ነው።

  ReplyDelete
 3. አቶ ዳንኤል ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው እውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ አንጂ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም፤

  ቂቂቂቂቂቂቂ! ውድ ፕሮፌሰር እንዲህ አድርገው እንዴት በደንብ አወቁት? ሰውዬው/አቶ ዳንኤል/ የቄስ ቀሚስ አቧራ በማራገፍና በጭፍን የቤተክርስቲያን ደጋፊዎች እየታጀበ፤ እየተሞካሸ አማርኛ ለቃቅሞ ዐ/ነገር ከሚሰራ በቀር እውቀት ጎደል ሰው እንደሆነ ከላይ የሰጡት ቃል በደንብ ይገልጠዋል። እንዳይማር ያውቃል። እንዳያውቅ አይማርም። ሰውዬው በተረት ብዛት ያወቀ ስለሚመስለው ለደረጃ የሚመጥን ትችት ማቅረብ ስላቃተው ትንሽዬ አእምሮውን ሲያጋልጥ ይገኛል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Danieln siletesadebe wodedachihut. First u have to read the professor's book. It is full of nonsense things, he write it in envy of others. even he doesn't know how to write, not knoe about literature. full of contradictions, here & there things. Thanks to Daniel, manim yemaygezaw metsihaf Daniel siletsafebet eyetenebebe new.Leza enkuan liameseginut yigeba neber. 80 years old man, full of yekeshefe life. Min yetesaka tarik alachew professoru? Beka awora mote type, no tegbar.

   Delete
  2. ወዳጄ ምን አለ በቅጡ በምታውቀው ቋንቋ ብትጽፍ?

   Delete
 4. በማያውቁት ጉዳይ ደረትን ገልብጦ በሙሉ እምነት ማነብነብ የካድሬዎች ባሕርይ ሆኖ በቤተ እግዚአብሔርም ገብቶአል፡፡

  ReplyDelete
 5. ‹‹የዩኒቨርሲቲን ዓለም የማያውቁ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት እንዳይሳሳቱ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በአካል በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሆነው ልባቸው ከደብተራ ተንኮል ላልጸዳም ቀናውን የእውነት መንገድ እንዲያመለክታቸው እመኛለሁ፤››aye professer mekuratwo new?

  ReplyDelete
  Replies
  1. እርሳቸው አይኮሩም እንጂ ቢኮሩም በእውቀት ሙሉ ሰው ናቸው፡፡ አንተ ጥብቅና ከቆምክለት በባዶው እና ሙሉ መስሎ ለመታየት ከሚጥረው ግን ካልተሳካለት ከዳንኤል ክስረት ወክሽፈት ጋር የሚወዳደሩ ሰው አይደሉም፡፡ በአንተ አፍ እንዲህ የሚባሉ ሰውም አይደሉም፡፡ ስለዚህ አንዴ ለመጻፍ ደጋግመህ አስብ፡፡

   Delete
  2. ፕሮፌሰሩ ስለቤተ ክርስቲያን የውድቀት ዘመናት ጣል አድገው ጽፈው ቢያስነብቡን ትልቅ መማሪያ ይሆናል፡፡ ኮርተው የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ ውሃ ሽቅብ ይፈሳል እንዳይሆንብህ

   Delete
 6. ድሮም ሆነ ዛሬ አውቃለሁ እያሉ የሚያፋችሉ፤ የሚረግጡትን ሳያስተውሉ፤
  ላይ ታች የሚዘሉ ከዕውቀት ደጋ ወደቆላ ድንቁርና የሚሉ አይጠፉም እናም ወቃሽና ተወቃሽ በዚሁ ቢቀጥሉ ወደመጨረሻ ርማት ያገኙና ራሳቸውን የሚያስተካክሉ ይሆናሉ።
  መነቃቀፉ መጻጻፉ የሚከፋ አይደለም። እንቀጥል ቀጥሉ!

  ReplyDelete
 7. something is cooking for Mahibere Kidusan in Ethiopia. Just wait and see.

  ReplyDelete
 8. ከሸፈው ማነው ? ዳንኤል ክብረት ወይስ ፕሮፌሰር መስፍን ?
  ፕሮሰሩ ሲጀምሩ ''ነገር ሳላበዛ ጥቂት ነጥቦችን በማንሣት የአቶ ዳንኤልን የማንበብ ችሎታና የተንኮል ክህነት ብቻ ለአንባቢዎች ላሳይ፤ ስለአስተያየቱ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ አይደለም፡፡'' .... ስለ አስተያየቱ ነው አሰተያየት መስጠት የሚያስፈልገው ወይስ ስለክህነቱ?

  ReplyDelete
 9. ፕ/ር መስፍን ለዳንኤል ክብረት የሰጡት መልስ መክሸፍ ነው:: ከርዕሱ ጀምሮ ለምን ተነካሁ የሚል ቡራ ከረዮ ነው:: እኔ አውቃለሁ ለማለት የተፃፈ የትምክህት ደብዳቤነው!የመፃሕፍት ሂስ ላይ የተሰነዘረ ስድብ ነው! ያየሁት የፕሮፌሰሩ ታላቅ ስህተት ነው! ሃሳቡን ሳይሆን ሰውዬውን ለመሞገትና ለመስደብ የቆመ ኢ- አመክኖኣዊ የህፀፅ ክምችት ነው! ለሳቸው የነበረኝን ያ ሁሉ አክብሮት ናዱት::እስከዛሬም ካገኙት ጋር የመጋጨት አባዜ ነው እንዴ ለካ zare ያሉበት ያቆማቸው? ብዬ ለመጠየቅ ተገደድኩ

  ReplyDelete
 10. I know the professor is an outstanding Geographer. But, he is not considered as successful politician or historian. He started as mediator towards the end of Derg EPRDF war , was Human Rights leading activist, he surpassed us joining the leadership of Kinijit and finally leading the faction of Andinet. Hence, I do not take him seriously.
  The professor should have argued without being polemical to point errors of Deacon Daniel. This is not expected at least from a person around 80 years old and who has the respect of the society even with the mentioned inconsistencies..
  with due respect

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Anonymous, i feel sorry for u, when u you know the truth u will definetly blame urself.
   Becasue Daniel is some one who u can never trust and play a word game but Proffessor Mesfin is playing Mentality game and he stands for the reality . Unlike daniel who stand for Ehadig and his daily meal . Simply don't worry he Dn Daniel started the blame game so hwere i will not blame but God will give us the time that all the truth about this Evil Daniel will be reviled.

   Delete
 11. የኢትዮጵያን ነባር ምሁራን ደብተራ እያሉ በአሉታዊ መልኩ ማንቋሸሺ ምን ማለት ነው ? ይህ ድረ ገጽስ ቢሆን የደብተራዎች መድረክ መስሎይ ? ዳንኤልን በግሉ ተግባር መተቸት መብት ነው። እርሱንና ለዘመናት ኢትዮጵያዊ ማንነትን ተብቀው ለዚህ ትውልድ ያስተላለፉትን ምሑራን አንድ ላይ መቀጥቀጡ ግን፤ በእውነትም የራስን አዋርዶ የባዕዳኑን ከፍ ለማድረግ የተደረገ ሙከራ ነው። የስነ ልቦና ሰለባ የሚባለው ይኽ ነው ። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ዘመቻ ሁኖ አይታይም ? ፕሮፌሰር ምን ነካዎት ? እርስዎስ የት መነጩ ? እነ አባ ሰላማስ ምንድን ነው የምትሉት ስለዚህ ሁኔታ ?

  ReplyDelete
 12. ዲ/ን ዳን ኤል ክብረት መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ በሚለው መጽሃፍ ላይ የራሱን እይታ አስቀምጣል:: በዚህ ግን ሊሰደብ አይገባውም በስራቱ አስተያየት ሊሰጥ ይገባል እንጂ::

  ReplyDelete
 13. "በጽሑፉ መደምደሚያ ላይ የደብተራ ተንኮል አፈትልኮ ይወጣል፤ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ያነሣና በደብተራ ተንኮል አንዱን ‹‹ዶክተር›› የሚለውን መልክ የሌለውና ስም የሌለው የደብተራ ምሥጢር ያደርግና፤ ‹‹እኒህ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ዶክተር ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዘንድ በማን በኩል እንደሄዱ ፕሮፌሰር መስፍን ያውቃሉ፤›› ብሎ ይለጥፍብኛል፤'' Is this an Ethiopian person ? Is this really Professor Mesfin Woldemaryam who wrote this ? Is he really? or Isayias Afeworqi or Daud Yibsa or Lencho Leta ? These are the ones who have been ridiculed Ethiopian Church scholars in their past writings and oral propaganda.They have said ''Ankoberite Debteras"

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምቀኝነትና ተንኮል በምእመኑ ዘንድ የተዘራው ከደብተራዎች መሆኑን እስከዛሬ አታውቅም ነበር?

   Delete
 14. I think the professor has given him a piece of lesson.Does Daniel has formal education? What is his mission by the way? Thank you for sharing the artile.

  ReplyDelete
 15. ምን እንዳየ፣ የት እንዳየ፣ ምንና ምን እንደተገናኘ የደብተራ ምስጢር ነው፤
  ያቀረበውን ሁሉ የማን ባለሙዋል ሆኖ ያገኘው እንደሆነም አይናገርም፤ እንዲህ ያለ ሞላጫነት!
  ስለእውቀት ከተጻፈ መጽሐፍ ተነሥቶ ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ጓዳ ገብቶ፣ ስሙ የማይጠራ ዶክተርን መነሻ አድርጎ፣ ይህን ሁሉ እኔ እንደማውቅ ተናግሮ በድንቁርና ምርጊት ይደፍነዋል!

  Ye kes mist aweksh aweksh siluat mestafun aweta atebech alu.

  Thank you Prefessor Mesfin for the right comment.

  ReplyDelete
 16. Profesor mehon lesidib ina le atinkugn bayinet kehones yikiribign.

  ReplyDelete
 17. ፕ/ር መስፍን በቅርቡ በጻፉት መጽሃፍ ዙርያ ዳንኤል ክብረት አስተያየት ሰጥቶ ነበር። ከአስተያየቱ ጭዋነት የተሞላበት ነቀፌታ እና ሂስ ቢኖርም በደምብ ደፈር ብሎ ሃሳቡን ገልጿል ለማለት ይከብዳል። እንዲያውም ፈራ ተባ እያለና በአሽሙር መሳይ እየጠቆመ የተወው ይበዛል። ይህም ሁኖ ጽሁፉ ፕ/ሩን አበሳጭቷቸዋል እና መልስ ሰጥተዋል።
  እርግጥ ፕ/ሩ ለዳንኤል የሰጡት ምላሽ ስድብ ይበዛበታል። ስድቡም ስድስተኛው ተራ ቁጥር ላይ ካነሱት ነጥብ ጋር የተያያዘ መሆኑ ግልጽ ነው። ቢያንስ ከዚያ ውጭ ባሉት ነጥቦች ሃሳብን በሃሳብ መመለስ ሲገባቸው ደጋግመው መሳደባቸው የአመል ሆኖባቸው እንጂ በስድስተኛ ነጥብ የጠቀሱት ይበቃ ነበር። እዚያም ላይ ፕ/ሩንና መንግስቱ ሃይለማርያምን የሚያገናኝ ጉዳይ ሲጠቁም የሰዎች ስም ሳይጠቅስ በገደምዳሜና ባሽሙር ጽሁፉን መደምደሙ አበሳጭቷቸዋል። እሱም የደብተራ ተንኮል ሸብቦት እንጂ ዘርዝሮ ለመጻፍ መረጃ አንሶት ወይም አቅሙ ገድቦት አይደለም። እዚያ ላይ መነቀፉ ተገቢ ነው። ይህ ማለት ግን ታሪኩ ውሸት ነው ማለት አይደለም። ፕ/ሩ እዚህ ላይ ግልጽ መሆን አለባቸው። ለምሳሌ የተፈራሩበት(በደብተራኛ ብቻ እየተነቋቆሩ) ያለፉት ሚስጥር እንዲህ እናብራራው፦
  1. መልክ የሌለው፣ ስም የሌለው “እኒህ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዶክተር...” የተባለው ሰው ነብስ ይማርና ሟቹ ዶክተር ብርሃኑ አበበ ናቸው።
  2. ዳንኤል ጽሁፍ ላይ መንግስቱ ሃይለማርያም ፕ/ር ታደሰ ታምራትን ቤተመንግስት ጠርቶ‹ከዶክተር እገሌ ጋር ቅሬታ አላችሁ መሰል፤ አንዳንድ ነገር ነግሮኝ ነበር፤ እዚያው ተነጋግራችሁ ፍቱት፤ አላቸው፤›.... በሚለው ዓረፍተነገር “ዶክተር እገሌ” የተባሉት ራሳቸው ፕ/ር መስፍን ናቸው። እሳቸውም ይህንን አላጡትምና የተናደዱትም ለዚህ ነው።
  3. ...‹‹አሁን እዚህ መጽሐፍ ላይ ቤተ መንግሥቱን አየሁት፡፡›› ምን እንዳየ፣ የት እንዳየ፣ ምንና ምን እንደተገናኘ የደብተራ ምስጢር ነው፤ ያቀረበውን ሁሉ የማን ባለሙዋል ሆኖ ያገኘው እንደሆነም አይናገርም... ሲሉ ዳንኤልን ያብጠለጠሉበት ነጥብ ላይም ዳንኤል በማህበረ ቅዱሳን በኩል የደብተራዎች ማአከል ወደሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ታሪክ ትምህርት ክፍል እንደተጠጋ፣ ተነቃፊዎቹን የታሪክ ባለሙያዎች በተለይም ፕ/ር ታደሰ ታምራትን ወክሎ እንደጻፈ፣ መረጃ ያገኘውም የሺፈራው በቀለ “ባለሙዋል” ሁኖ እንደሆነም ግልጽ ነው።
  4. በደርግ ዘመን እነዚህ ምሁራን ማለትም ፕ/ር መስፍን፣ ፕ/ር ታደሰ፣ ዶክተር ብርሃኑ አበበ እና ሺፈራው በቀለ ቤተመንግስት ውስጥ ምልልስ አዘውታሪዎችና አማካሪዎች ነበሩ። በተናጠልም በጋራም መንግስቱ ሃይለማርያም ጋር ይገናኙ እንደነበር ለማያውቅ በቅርቡ የታተመው የኮሎኔል መንግስቱ መጽሀፍ (ትግላችን ገጽ 4‐5) መመልከት ነገሩን ግልጽ ያደርጋል። ይህ ሲጠቀስ ፕሮፌሰር ለምን እንደተቆጡና ዳንኤልም ለምን በዝርዝር መግለጽ እንዳልፈለገ መቼስ ይገባችኋል። ሁሉም ተጠያቂነትን ይፈራሉ።
  እነዚህ ነጥቦች ግልጽ ስለሆኑ ፕ/ር መስፍን የሚጠበቅባቸው መናደድና መሳደብ ሳይሆን ስለራሳቸውም ስለ ነዚህ ሰዎችም እውነቱን መናገር ብቻ ነው። አገርንና ትውልድን ክሽፍ ብሎ ከመሳደብ ይልቅ በቅርብ ስላለ ትንሽ ነገርም እውነት መናገር እጅግ ይሻላል። እውነት ከቅርብ ይጀምራል፤ ምሁርነትም ራስን ከመንቀፍ ይጀምራል! ፕሮፍ ስለራሳቸውም እቅጯን ነግረው ያስተምሩን እንጂ በስድብና በርግማን አይሸውዱን። የቋንቋቸው ማማር የጽሁፋቸውን ይዘት አሳማኝ አያደርግም።written by....Woldebirhan Ze Adi-Haqi

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Woldebirhan Ze Adi-Haqi,I like your analysis.

   Delete
 18. This is not the way you should reply to his comments. There are other ways you can address your point. I am very disappointed with your no argumentative writing.

  ReplyDelete
 19. ፕሮፌስር መስፍን ለዳንኤል ክብረት የሰጡት መልስ በራሱ ልዩነታችሁ አጉልቶ ያሳያል፡፡ እርሰዎ በማእረግ በጣም የላቁ ሲሆኑ(ፕሮፌስር?)÷ ዳንኤል ደግሞ በ እውቀት ከርሰዎ በእጂጉ እንደምበልጥ መልሰዎ ይመሰክራል፡፡ ዳኒ ባለዎት መልካም ሰብእናና ሙሁራዊ አስተዋፅኦ በመዘርዘር ሲጀምር ፕሮፌስር ደግሞ ለማእረጋቸው በማይመጥኑ የሲድብ ቃላት ታጭቀዋል፡፡
  ስድስት ነጥብ በማሰቀመጥ በስድስት ደረጃ ከ ዳንኤል ያነሱ መሆነዎን(ለግዜው) ነገሩን፡፡ "ዶክተር እገሌ" ለርሰዎ ብደበቅም አኛስ በሚገባ አውቀነዋል፡፡ ቤተ-መንግሰቱ አይደለም ዳኒ እኛም በሚገባ አይተነዋል፡፡ ለርሰዎ ል ለሚን እነዳልገባዎት ጭምር ገብቶናል-----አማርኛው ከአቅመዎ በላይ ሆነ አይደል ፕሮ……?

  ReplyDelete
 20. ብዙ ብዙውን ትተን ፕሮፌሰሩ «መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ» በማለት ጽፈዋል። ዳንኤል ደግሞ «የክሽፈት ታሪክ ሊኖር ይችላል እንጂ የከሸፈ ታሪክ ሊኖር ይችላል? የስኬት ታሪክ ይኖራል እንጂ የተሳካ ታሪክ ይኖራል?» እያለ ይጠይቃል።
  የፕሮፌሰሩ ጽሁፍ የሚያጠነጥነው የኢትዮጵያ ታሪካዊ እድገት ከነበረበት ከማደግ ይልቅ እንደግመል ሽንት የኋሊት መሄዱንና መክሸፉን ነው።
  የዳንኤል የሂስ ትረካ ግን ውል የሌለው ልቃቂት ይመስላል። የፕሮፌሰሩን ጽሁፍ ሲተች በንጽጽር ይህንን በማለት ያቀረቡት በዚህ አስረጂ ውድቅ ነው። ስኬታችን ይህን ይህንን እየመሰለ ሳለ እርስዎ ያቀረቡት የክሽፈት ታሪክ ሚዛኑን የሳተ ነው፤ በማለት የሂሰቱን ጭብጥ ከነማስረጃው ማቅረብ ሲገባው አማርኛውን በማቆላለፍ ዐረፍተ ነገር በመስራት የሄሰ መስሎት ««የክሽፈት ታሪክ ሊኖር ይችላል እንጂ የከሸፈ ታሪክ ሊኖር ይችላል? የስኬት ታሪክ ይኖራል እንጂ የተሳካ ታሪክ ይኖራል?» በማለት በጥያቄ ያምታታል። የክሽፈት ታሪክ ካለ የከሸፈ ታሪክ የማይባልበትን ምክንያት አይናገርም። የስኬት ታሪክ መኖሩን አምኖ ከተቀበለ በኋላ የተሳካ ታሪክ ይኖራል? እንዴ ብሎ ጅልኛ ይጠይቃል። የስኬት ታሪክ፤ የተሳካ ታሪክ የማይባልበት ምክንያት ዳንኤል በፈጠረው የጭንቅላቱ ዓለም ውስጥ ካልሆነ በስተቀር የገሃዳዊው ዓለም የስኬትን ታሪክ የተሳካ ታሪክ ብሎ ይጠራዋል፤ የክሽፈት ታሪክንም የከሸፈ ታሪክ ያሰኘዋል። ከዚህ ውጪ አማርኛን ማምታታት ካልሆነ ሌላ መውጪያ መንገድ የለም። ዳንኤል ግን ይህንን በመካድ ወይም በመቃወም ሳይሆን በማምታታት፤ ድርጊትና ተደራጊውን አመሳቅሎ ሊሸውደን ይፈልጋል። ብዙ ጭፍን ደጋፊዎቹ ለምን ተነካብን ሲሉ በአስተያየቶቻቸው የአዞ እንባ ያለቃቅሳሉ። ለዳንኤል የተወረወረው የፕሮፌሰሩ የሽንቆጣ መልስ ሰርስሮ እንዳመማቸው ያህል ይቆራመዳሉ። በግምኛ ድጋፍ ከማዘን ይልቅ አቶ ዳንኤል ከተናገረውና የከሸፈውን ታሪክ መጽሐፍ ለመተቸት የሰነዘረውን የከሸፈ ዐ/ነገሩን በመተርጎም እስኪ እርዳታችሁን አሳዩት።
  «የክሽፈት ታሪክ ሊኖር ይችላል እንጂ የከሸፈ ታሪክ ሊኖር ይችላል? የስኬት ታሪክ ይኖራል እንጂ የተሳካ ታሪክ ይኖራል?» ማለት ምን ማለት ነው?
  ማኅሌት በመቆም ብቻ ሳይሆን ዐውደ ነገሥት በመግለጥም ደብተራዎችን ማንም አያማቸውምና እስኪ ለዚህ ቃል ከመጽሐፋችሁ ግለጡልን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. «የክሽፈት ታሪክ ሊኖር ይችላል እንጂ የከሸፈ ታሪክ ሊኖር ይችላል? የስኬት ታሪክ ይኖራል እንጂ የተሳካ ታሪክ ይኖራል?» ማለት ምን ማለት ነው? History is a means to understand the past and present,even if it narrates about failure and trajedy ,history by itself is good/not bad . why?b/c The different interpretations of the past allows us to see the present differently and therefore imagine—and work towards—different futures. Through the study of history we can investigate and interpret why society developed as it has and determine what influences have affected the past and present and shape the future. It helps one to understand the immense complexity of our world and provides insights to help cope with the problems and possibilities of the present and future. History also provides a sense of identity to understand the collective past that has have made us what we are today. ……….እንዲያ ከሆነ ደግሞ ታሪክ የአንድን ማኅበረሰብ የስኬትም ሆነ የክሽፈት፣ የድልም ሆነ የሽንፈት፣ የውጤትም ሆነ የኪሳራ፣ የልዕልናም ሆነ የተዋርዶ ጉዞ የሚያሳየንና የምናጠናበት፣ የምንመዘግብበትና የምናይበት ነገር ነው ማለት ነው፡፡ስለ ክሽፈቱ እናይበት ይሆናል እንጂ ራሱ የሚከሽፍ አይመስለኝም፤ ስለ ስኬቱ እናጠናበታለን እንጂ ራሱ የሚሳካ አይመስለኝም፡፡ ሰው የስኬት ታሪክ ይኖረዋል እንጂ ታሪኩ አይሳካለትም፡፡ የሽንፈት ታሪክም ይኖረዋል እንጂ ታሪኩ አይሸነፍበትም፡፡ ....

   Delete
  2. ዳንኤልን ለመደገፍ ያመጣኸው ጽሁፍ ምንጩ ይህ ነው። http://www.siena.edu/pages/3289.asp
   ይህን ጽሁፍ መጥቀስህ ባልከፋ፤ ነገር ግን ድረ ገጹ የታሪክን ምንነት የተነተነበት መንገድና አንተ ዳንኤልን ከወቀሳ ለማዳን የሄድክበት መንገድ በጭራሽ አይገናኝም።
   በመሰረቱ ታሪክ ወይም / History/ በጣም ሰፊና ጥልቅ የእውቀት መስክ ነው። ዓይነቶቹና ክፍላቸውም ብዙ ነው። ከብዙዎቹ መካከል አንዱ የሆነው ማኅበራዊ ታሪክ /Social History/ በስሩ ብዙ ዘርፍ ያለው ስለሆነ በጥቅሉ የምንናገረው ቃል ሊገልጠው አይችል ይሆናል። ለምሳሌ ያህል፤

   1/Demographic history
   2/Black history
   3/History of education
   4/Ethnic history
   5/Family history
   6/Labor history
   7/Rural history
   8/Urban history
   የመሳሰሉትን ንዑስ ክፍሎች ያጠናል።
   «History is the analysis and interpretation of the human past that enables us to study continuity and change over time» ይህም ዐ/ነገር በተዛማጅ ትርጉሙ «ታሪክ ማለት የሰው ልጆችን ያለፈ ማንነት በመተንተንና በመተርጎም ቀጣይነቱን ከለውጣዊ የትመጣነቱ ጋር የምናጠናበት መንገድ ነው» ይለናል። አያይዞም «ታሪክ የሕይወት መምህር ነው ይለናል» History is magister vitae, "teacher of life."
   ከዚህ ተነስተን የተማሪን ሕይወት በታሪክ ጎዳና በምሳሌነቱ ብንመለከት፤ተማሪ በሕይወት ዘመኑ ይወድቃል ይነሳል። የጠንከረ የትምህርትን ፈተናና ውጥረት በትግሉ ይወጣዋል። ፈተናውን ማለፍ ያልቻለ ይወድቃል፤ ብሎም ከትምህርቱ ጎዳና ይወጣል።
   በትግሉ ከፈለገው ግብ የደረሰ የስኬት ታሪኩ ነው። የስኬት ታሪክ የተሳካ ታሪክ ውጤት ነው። የከሸፈው ታሪክ የሚባለው ደግሞ ክሽፈትን ያስተናገደ የታሪክ ሂደት መገለጫ ነው። ድርጊቱ የተገለጸበት ወይም የተጓዘበት ስኬት ይሁን መክሸፍ፤ ታሪክ በታሪክነቱ የከሸፈ ማለትም ያልተሳካ በማለት በጥናታዊ ስያሜው ይጠራዋል። በጥቅሉ የስኬት ታሪክ፤ የተሳካ ትግል ውጤት ሲሆን የከሸፈው ታሪክ ደግሞ ስኬትን መጨበጥ ያልቻለ የትግል ውድቀት መገለጫው ነው። ከዚህ ሌላ አማርኛ የለም።

   Delete
  3. lemin tenekahu maletot yasafral.chewanet bimaru yshalotal


   Delete
  4. Please don't mess around!Daniel has to learn before he tries to comment.The professor comment is not insult rather rebuke which is necessary for the 'tiraz netek ye kalat techawach lehone sew'.

   Delete
  5. ጥሬ ጨው
   መስለውኝ ነበረ፤
   የበቁ የነቁ
   ያወቁ የረቀቁ
   የሰው ፍጡሮች፣
   ለካ እሱ ናቸው፤
   ጥሬ ጨው…ጥሬ ጨው
   ጥሬ ጨዋዎች፣

   Delete
 21. አይ የናንተ ነገር ዳንኤል፥ ማቅ ሲባል ስማቸው ሲነሳ ምንም ነገር ለማገናዘብ እድሉን እንኳ ሳታገኙ ዘው ብላችሁ ትነከራላችሁ። እናንተ ማለት ልክ የበሬ ወንድ ፍሬው ከአሁን አሁን ወደቀልኝ እያለ ለሃጩን እያዝረበረበ እንደሚከተል ውሻ ናችሁ። የሚወድቅ ፍሬ የለም። ትናንት እኮ የስም ማጥፋታችሁ አካል አንዱ የሚያጠነጥነው ማቅና ፕሮፍ መስፍን ላይ ነበር። በዛ የምርቃና ፅሁፋችሁ አቡነ መስፍን ያላችኋቸው መስፍን ዛሬ ዳንኤል ስለ ተቻቸው የፃፉትን ስድብ ስታገኙ ምራቅ ባፋችሁ ሞላ እና አቡንነታቸውን ረሳችሁት። እኛ አንረሳም። እናንተ ዛሬም የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ ናችሁ። ሁሉንም ያገኛችሁትን ጭቃ ሁሉ እየወረወራችሁ ነው። እስካሁን የወረወራችሁት አልተሳካምና አሁንም ከመወርወር ወደኋላ አትሉም። የወረወራችሁት ጭቃ እስከሚለጠፍ። አንድ ነገር እንዴት አንዴ ደጋፊ አንዴ ተቃዋሚ መልሶ ደጋፊ ከዛ ተቃዋሚ ማድረግ ይቻላል? ለናንተ ይቻላል። ምክንያቱም ጭቃ ውርወራ ላይ ናችሁና።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Bruck Hun Anoymous Jan. 29, 2013 at 7:06pm.

   Delete
 22. አይ ጉድ ፕሮፌሰር መስፍን ምን ነካዎ? የምሁር አንደበት አይመስልምና ቢረጋጉና ቢጽፉት አስተማሪ ሊሆን በቻለ ነበረ። የሆነ ሆኖ የባላባታዊ ዘመነ ሥርዓትን አስታወሰኝ መቺም እርስውም የዛው ዘመን ውጤት ስለሆኑ በአንድ በኩል አይፈረድብዎትም። የጽሁፍው አጀማመሩ ስሜታዊ በመሆኑ ብቻ ለንባብ ስለማይጋብዝ ለውደፊቱ ቢያስቡበት መልካም ነው። ዲ/ን ዳንኤል ሆነ እርስዎን በተወሰነ ደረጃ ስለማውቃችሁ ሁለታችሁንም ስለምንፈልጋችሁ መተራረሙ መልካም ሲሆን በኢትዮጵያዊ ሥነ ምግባር ቢሆን ይመረጣልና በተለይ ፕሮፌሰር ቢያስቡበት መልካም ነው። የእውቀት ብቻ ሳይሆን የእድሜ ጸጋም እንደታደልዎት አይዘንጉ። እኔ በመሰለኝ መልክ ሀሳቤን አቅርቤአለሁ የኅሊና ዳኝነቱ ከርስዎ ነው።

  ReplyDelete
 23. By which criteria Daniel become stupid? professor you are not a standard to classify persons. Daniel is an outstanding, all rounded person of this generation. No one is like him including you. Erswo be Ethiopia hizb endetewededu wode mekabirwo, endih sayijajalu bihedu melkam new, Danin lekek. Be ayinachin metu.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ALL round? Is that mean circling by his personal idea? U don’t know the meaning of all round and u don’t know daniel

   Delete
 24. ፕሮፌሰር መስፍን እጅግ ተዋረዱ
  ዐዋቂውን ሁሉ እጅ ነሥተው ሄዱ

  ReplyDelete
 25. Be ewunet betam yasaznal min aynet gize lay endederesen telkum tenshum eyetenesa ashakbo mesadeb ye kuta newu. Profeser minim belu besenesrat lemn endih alu belo meteyek sechal ye hulu aseyafi anegager betam ye miyasazn newu. Danelm behon manewuna newu esachewun yemitechewu min ayenet astedadeg newu talaken manguatet kefelege endelemedewu mesaf newu yerasun hasab sewu besafewu laye hulu agul awaki neg belo merakeku gen asfelagi ayemeselegem. Enantm aseyafi kalat yemtetekemu hulu betetaremu tiru newu.

  ReplyDelete
 26. ፕሮፌሰር መስፍን ለዳንኤል ክብረት በሰጡት ምላሽ በአብላጫው እስማማለሁ:: በአንድ ወቅት አንብቦ, አሰላስሎና አስተውሎ የሚጽፍ መስሎኝ የሚጽፋቸውን ሁሉ እከታተለው ነበር:: አሁን ግን እውነቱን ለመናገር ስሙን እንኳን ለማንበብ የማልፈልግበት ደረጃ “አድርሶኛል”:: ጽሁፎቹ ሞጋች ስለሆኑ አይደለም… በጣም ሲበዛ ግልብና ብስለት የጎደላቸው በመሆናቸው ነው:: የፕሮፌሰር መስፍንን መጽሐፍ ለመተቸት ቀርቶ ለማንበብና ለመረዳት እንኳን አቅም የሌለው ድኩም ሰው ያላቅሙ ሲንጠራራ ማየት ያሳፍራል::

  ሳያነብብ አንባቢ, ሳያውቅ ለቅላቂ የሆነን ደብተራ ማስተንፈስ የግድ ይላል:: አለበለዚያ አቅሙን ሳያውቅ ያለእውቀቱ ገብቶ ሲያቸፈችፍ ብዙ ነገር ያበላሻል:: በዚህ ዘመን ከሚጽፉ ብዕረኞች በጣም ጮርቃ የሆነ ስራ እያቀርቡ, እያደናገሩ ታላቅ ነን እያሉ ከሚኮፈሱ እቡያን ሰፈር የምመድበው ዲያቆን አቅሙ የማይመጥንለትን ነገር መንካቱን ነው ፕሮፌሰር ያሳዩት:: ቋንቋቸው እንደተለመደው ተንኳሽ ነው… ፕሮፌሰርን ከሌሎቹ ልዩ የሚያደርጋቸው ይኽው አቀራረባቸው ነው::

  አሁንም ከተንኳሽ ብዕራቸው የሚወጣውን ለማንበብ እድሜና ጤና ተመኝቼላቸዋለሁ!

  ReplyDelete