Tuesday, January 29, 2013

ጌታ በወንጌል ስለ እናቱ የተናገራቸው ንግግሮች ለምን ቀጥተኛ አልሆኑም?

በትውፊት እንደሚነገረው ጥር 21 የእመቤታችን የእረፍቷ መታሰቢያ ቀን ነው፡፡ ሆኖም የእረፍቷን መታሰቢያ ማድረግ ካስፈለገም በዚያው ባረፈችበት ቀን ብቻ መሆን ሲገባው ወርሃዊ ተደርጎ በቤተ ክርስቲያናችን ያሉትን የበዓላት ቁጥር ከፍ እንዲል አድርጎታል፡፡ ይህ በእርሷ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም ቅዱሳን ስም የተሰሩት በዓላት ላይ ሁሉ የሚስተዋል ነው፡፡ ነገር ግን መስተካከል አለበት፡፡
በዚህ ጽሑፍ ስለዕረፍቷ የምለው ነገር የለም፡፡ ጌታ ከእናቱ ጋር በተያያዘ ለተጠየቃቸው ጥያቄዎች የሰጣቸው መልሶች፣ በእርሷ ዙሪያ የሰጣቸው አስተያየቶች ቀጥተኛ አልነበሩምና ለምን ቀጥተኛ አልነበሩም? የሚል ጥያቄ ለማንሳትና በዚያ ላይ ሐሳቤን ለማካፈል ነው፡፡ እውነት ነው፤ እናት አባትህን አክብር ብሎ ያዘዘን ጌታ የሰጣቸው ምላሾች ቀጥተኛ አለመሆናቸው እናቱን ለማቃለል ፈልጎ እንዳልሆነ በእርግጥኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ታዲያ ምክንያቱ ምን ይሆን? እስኪ በመጀመሪያ ጥቅሶቹን እንመርምራቸው፡፡
·        «ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። አንዱም። እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው። እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።» ማቴ. 12፥46-48
·        «እናቱና ወንድሞቹም ወደ እርሱ መጡ፥ ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሊያገኙት አልተቻላቸውም። እናትህና ወንድሞችህ ሊያዩህ ወድደው በውጭ ቆመዋል ብለው ነገሩት። እርሱም መልሶ፦ እናቴና ወንድሞቼስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው አላቸው።» ሉቃ. 8፡19-21
·        ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም። ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው። እርሱም፦ ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው። ሉቃ. 2፡48-49
·        «ይህንም ሲናገር፥ ከሕዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ። የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው አለችው።» ሉቃ. 11፡27
·        «የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።» ዮሐ. 2፡3-4
·        «ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፥ አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።» ዮሐ. 19፡26-27
በእነዚህ ኢየሱስ ስለ እናቱ በተናገራቸው ንግግሮች ውስጥ የምናስተውለው አንዱና ዋናው ነገር እርሱ የመጣው በስጋ ዝምድና ቤተሰቡን ለማገልገል ሳይሆን ለዓለም ሁሉ ሕይወት ለመሆን ነው፡፡ ጌታ የስጋ ዝምድናን በማጠንከር ቢመላለስ ኖሮ የመጣበትን ተልእኮ ዘንግቷል ባሰኘው ነበር፡፡ ጠፍቶ ቤተመቅደስ ውስጥ በተገኘ ጊዜ የተናገረውም ይህን ይበልጥ ያሳያል፡፡ «ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን?»
ከእለታት በአንዱ ቀን ጌታ «እናትህ ትፈልግሃለች» ሲባል ጉባኤውን «ይቅርታ እናቴን አንድ ጊዜ አናግሬያት ልምጣ» አላለም። ወይም «አስተምሬ እስክጨርስ ጠብቂኝ በሏት» አላለም፡፡ «እናቴና ወንድሞቼ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት ናቸው» አለ እንጂ፡፡ ስለዚህ የጌታ ምላሽ ቀጥተኛ አልነበረም፡፡
በሌላ ጊዜ ደግሞ ጌታ ሲያስተምር በንግግሩ የተመሰጠች አንዲት ሴት «ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፥ የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው» ባለችው ጊዜ «አዎን እውነት ተናገርሽ» ብሎ አላደነቃትም፡፡ የሰውን ትኩረት ከተሸከመችው ማህጸንና ከጠባቸው ጡቶች ላይ ማንሳትና ብፅእና የሚገኝበትን ምስጢር መግለጥ ነው የፈለገው፡፡ ስለዚህ «አዎን፥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው አለ።» አሁንም መልሱ ቀጥተኛ አይደለም፡፡
በቃና ዘገሊላው ሰርግ ላይና በመስቀል ላይ ሳለ ከእናቱ ጋር በተያያዘ የተናገረውም «አንቺ ሴት» የሚል እናቱን የማክበር ነገር ግን የማራቅ አጠራር አለበት፡፡ እናቱን ለዮሐንስ አደራ ሲሰጠው «አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ፣ እርሱንም እነኋት እናትህ ነበር ያለው፡፡ በዚህ ውስጥ ለእናቱ እንዳሰበላትና በመከራው እንዳትጎዳ እንደፈለገ ግልጽ ነው፡፡ ለዮሐንስም አደራ ሰጥቷታል፡፡ ዮሐንስም ወደቤቱ ወስዷታል፡፡ ነገር ግን እናቱን የጠራበት አጠራር ማለትም «እናቴ ሆይ» ወይም እንደእኛ «እማዬ» በማለት ፋንታ «አንቺ ሴት» በሚል የአክብሮትና ለሩቅ ሰው የሚጠቀሙበትን አጠራር መጠቀሙ ሁሉን አዋቂው ጌታ ወደፊት የሚሆነውን አስቀድሞ ስላየ ሆነ ብሎ ነው እንዲህ ያለው ማለት ይቻላል፡፡ ስህተትም አይሆንም፡፡
ቀደም ካለው ጊዜ ጀምሮ በልዩ ልዩ ምክንያት ሰዎች ያዳናቸውን ጌታ ትተው በሥጋ የወለደችውን እናቱን ማርያምን በማክበር ስም የጀመሩት አሰራር እርሷን ከፈጣሪ ጋር ወደማስተካከልና እንድትመለክ ወደማድረግ አድጓል፡፡ ዛሬ ማርያም ሌላ አምላክ እንጂ የጌታ እናት ብቻ ሆና እንደማትታይ ግልጽ ነው፡፡ ሰዎች ወደዚህ ጥፋት እንዳይደርሱ ጌታ በወንጌል ውስጥ ምን ያህል እንደተጠነቀቀ ከላይ የተዘረዘሩት ጥቅሶች ያስረዳሉ፡፡ ስለዚህ ጌታ ከእናቱ ጋር በተያያዘ የተናገራቸው ንግግሮች ቀጥተኛ አለመሆናቸው የሚያስተላልፉት መልእክት ይኸው ነው፡፡ ስለዚህ ማርያምን በማክበር ስም እየተደረገ ያለው አምልኮት ሁሉ ከንቱ ነገር ነውና እባካችሁን እርሷን በጌታ እናትነቷ በማየት የሚገባትን የእናትነት ክብር እንስጥ እንጂ አናምልካት፡፡
እዚህ ላይ መቼ አመለክናት? የሚል ይኖራል፡፡ እያከበርናት ሳይሆን እያመለክናት እንደ ሆነ ለማወቅ ስለእርሷ በቃልም በጽሁፍም የምንሰብከው ስብከት፣ ስለእርሷ የምንዘምረው መዝሙር፣ ስለእርሷ የምንቀኘው ቅኔ ሁሉ ቢፈተሽ ነገሩ አምልኮት እንጂ አክብሮት ሊባል አይችልም፡፡ ስለዚህ ጌታ በስሟ እንዲህ እንደምናደርግ ስላወቀ የእግዚአብሔርን ሐሳብ እንዳንስት ስለእናቱ በተጠየቃቸው ጥያቄዎችና በቀረቡለት ሐሳቦች ውስጥ ቀጥተኛ ያልሆነ መልስ በመስጠት ዛሬ ለእመቤታችን ሳይሆን በስሟ ለሚነግደው ርኩስ መንፈስ የምናደርገውን ሁሉ አስቀድሞ ያወቀው ጌታ እንዳናደርገው አስጠንቅቆናል፡፡ ስለዚህ ጌታ ከከለከለው ከአምልኮተ ማርያም ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እንመለስ፡፡
ጸጋ ታደለ  

37 comments:

 1. 1- ሁለት አጭር ጥያቄዎች ላንተ አለኝ የጻፍከውን ጽሁፍ ለመጻሀፍ የተነሳኸው? የጥቅሶቹ ትርጉም እንደዛ መሆናቸውን ጌታ እራሱ ነግሮህ ነው ወይስ አንተ እንደገባህ ነው? ስለዚህ ጌታ ከእናቱ ጋር በተያያዘ የተናገራቸው ንግግሮች ቀጥተኛ አለመሆናቸው የሚያስተላልፉት መልእክት ይኸው ነው፡፡ ስለዚህ ማርያምን በማክበር ስም እየተደረገ ያለው አምልኮት ሁሉ ከንቱ ነገር ነውና እባካችሁን እርሷን በጌታ እናትነቷ በማየት የሚገባትን የእናትነት ክብር እንስጥ እንጂ አናምልካት፡፡
  2- በተለይ የዚህን ጥቅስ ትርጉም በቃ እንደዚህ ነው የገባህ ለወደፊት እንደገና አንብበህ ከሚያውቁ ጠይቀህ ይህን ጽሁፍ ታሰተካክላለህ?
  እሰከዛ ስምህን ቀይረው ጸጋ ታደለ የሚለውን ጸጋ ጐደለ

  ReplyDelete
 2. tehadeso menafekan meneme bytaweru le emebatachen ledenegele mariyam yalenene fekerena akeberote kelebachen letawetute atechelum le lejewa ye ameleko segedet le ersewa ye tshga segedete enesegedalen esekezelealem .!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 3. ወንድም ጸጋ አይሁዳዊ ወይም ግሪካዊ ሳይሆን ፣ የአይሁድንና የግሪኮችን የአነጋገር ዘይቤ እየተረጎመ ሃሳቡን ስላካፈለን ፣ እኔም በርሱው መንገድ በመጓዝ ሃሳቤን አካፍላለሁ ፡፡ በአለፈው ርዕስ ያቀረብኩት አስተያየት እንደተጠበቀ ሁኖ የዛሬውን ሃሳብ በተመከርኩት መሠረት ትጉሃን አንባቢዎች እንዳይማረሩ አጠር አድርጌ አቀርባለሁ ፡፡

  ሀ/ አንቺ ሴት

  - በአይሁድ ባህልና የአነጋገር ፈሊጥ መርምሮ እቅጩን የሚነግረን ካልተገኘ በስተቀር ፤ ጡቷን ጠብቶ ያደገ ልጅ ፣ እናቱን ለማራቅ ስለፈለገ አንቺ ሴት አላት ማለት ግራ ይሆንብኛል ፡፡ ሥጋና ነፍሷን ነስቶ ወይም ከፍሎ ከልዩ አካሉ አዋሕዶ በደልን ለመሻር ተገለገለበት እያልን እያመንንና እያመለክን ምን የሚባለውን ማራቅ እንናገራለን ? በመስቀል ላይ ደሙን እያዘራ ፣ ስቃዩን ታግሶ አደራ የሰጠ ልጅ ፣ አርቋታል ማለትስ እንደምን ለአእምሮአችን አይከብደንም ? ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነው ስንል የሰው ባህርይ የሆኑትን ሁሉ ተጋርቷል ፡፡ እኔ ለእናቴ የምሰጠውን ፍቅርና ክብር ፣ ርሱ በአምላክነቱና በአስተማሪነቱ እጥፍ ድርብ አድርጎ ፈጽሞታል ፡፡ እኔ ተሰቅዬ ሳይሆን ይሙት በቃ የሚለውን ቃል እንኳን ቢያሰሙኝ ፣ የማስበው ስለ አሟሟቴ ነው እንጅ ስለ እናቴ አይሆንም ፡፡ ርሱ ግን ከኛም ባህርይ በላይ ንጹህ ሰውና አምላክ ስለሆነ ስለእናቱ ተናገረ ፡፡

  መጽሐፍን ከተመለከትነው በዘመናቸው ይህን የመሰለ የአነጋገር ፈሊጥና ልማድ ፣ የአጻጻፍ ሥርዓትም እንደነበረ ያሳያል ፡፡ ምክንያቱም አንቺ ሴት የሚለውን ቃል ፣ ኢየሱስ ከድንግል ማርያም ሌላ ፣ ለተለያዩ ሴቶች (ማቴ 15፡28 ፤ ዮሐ 8፡1ዐ ፤ ሉቃ 13፡12 ፤ ዮሐ 2ዐ፡15) እንደ ተጠቀመበት ሁሉ ፣ መላእክት ፣ ጳውሎስና ጴጥሮስም አንቺ ሴት እያሉ ስለተናገሩ የማቅረብና የማራቅ ትርጉም ሊያሰጠው አይቻልም ፡፡ (1 ቆሮ 7፡16 ፤ ሉቃ 22፡57 ፤ ዮሐ 2ዐ፡13)

  ይልቁንም እናቱን አንቺ ሴት በማለት ደጋግሞ የሚጠራት ፣ ቀደማዊ አደም ከበደል በፊት የአካሉን ክፋይ ሴት ብሏት ነበርና ፣ ኢየሱስ ደግሞ በዳግማዊ አዳምነቱ ንጽህት ፣ ብፅዕት ሆና በመገኘቷና የአካሏ ክፋይ በመሆኑ ይህን መጠሪያ ሊሰጣት ችሏል ፡፡ የተቀሩትን ሴቶች ግን በልማዳቸውና ወጋቸው መሠረት እንዲያ ብሏቸዋል ያሰኛል ፡፡ እኔም በአንድ ዘመን ከሰዎች ተምሬ ያገኘሁትንና የማናግረውን ሴት ሁሉ አክስቴ እያልኩ እጠራ እንደ ነበር ማለት ፡፡

  ለ/ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን ። እርሱም፦ ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን?

  - አባትህ ብላ በወጋቸው መሠረት ስታናግረው ፣ የባሕርይ አባቱ እግዚአብሔረ አብ መሆኑን መግለጹ ነው ፡፡ አላስተዋሉም ማለትም ይኸን ሥውር አነጋገሩን ነው ፡፡
  ሌላውም በቤተ መቅደስ (በአባቴ ቤት) ያለሁትን ሰው አደጋ ያጋጥመዋል ብላችሁ መስጋት አይገባችሁም ነበር ለማለት ነው ፡፡ ሌባና ዘራፊ ወንበዴና ቀማኛ በመንገድና በጫካ እንጅ በእንደዚህ ባለ ቅዱስ ሥፍራ አይኖርም ማለቱ ነው ፡፡ የዛሬን አያድርገውና …

  ሐ/ እናቴና ወንድሞቼ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት ናቸው

  - ይህኛውንም ባለፈው ርዕስ ዘርዝሬዋለሁ ፡፡ ተንኰለኞችና ተቀናቃኞች በቤተሰብ ምክንያት አሳበው የሚያስተመረውንና የሚያደርገውን ተአምራት እንዲያቋርጥ ፣ ኀብረተሰቡም እንዲበተን በመፈለግ ነው የነገሩት ፡፡ ርሱም በአምላክነቱ ዓላማቸውን ተረድቶ ፣ ያፈለገው ቢመጣ የጀመርኩትን አላቋርጥም በማለት እንደመለሰላቸው ነው ፡፡ በሌላ አገላለጽ ደግሞ እግዚአብሔር በክብር እንደሚበልጥ ሲያስተምር ነው ፡፡ ምክንያቱም የመንግስተ ሰማያትን ቃል ለህዝብ እያዳረሰ ፣ በደዌ የተጠቁትን እየፈወሰ ስለነበረ ፡፡

  መ/ የእናትህ አካሎች ብፁዓን ናቸው ፡፡ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው

  - እናቱ ብፅዕት እንደምትባል የሚያውቀው አምላካችን ፣ ይኸን ለተናገረች ሴት ስለመጣበት ርዕስ ሊያስተምራትና ርሷም ዕድል እንዳላት ሊያበሥራት ስለፈለገ የተጠቀመበት አገላለጽ ነው እንጅ እናቴ ብፅዕት አይደለችም ብሎ የወንጌልን ቃል መሻሩ አይደለም ፡፡

  ሠ/ ጌታ በስሟ እንዲህ እንደምናደርግ ስላወቀ የእግዚአብሔርን ሐሳብ እንዳንስት

  - ወንድም ጸጋ የአክብሮት ነው እንደምንልም ብዙ ጊዜ ስላነበበው ያውቃል ፡፡ ርሱ ግን ተገልጦለት ይሁን በምን አላውቅም አሁንም የአምልኮ ነው እያለን ነው የሚከራከረው ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ከባለቤቱ ያወቀ ይባላል ፡፡ በሰዎች አእምሮና ልቦና ውስጥ ያለውን የመረዳት ክህሎትም ተጐናጽፏል ለማለትም ይገፋፋኛል ፡፡

  ሌላው ደግሞ ኢየሱስ ኢትዮጵያውኖች እንዲህ አድርገው እናቱን እንደሚያከብሩ ስላወቀ ለዓለም በሚሠራጨው ወንጌል ትምህርቱን በስውር ቃል አሠራጨ እያለን ነው ፡፡ እንዴት ነው ለመሆኑ ? እኛን ለመገሰጽ ፣ እናንተ ኢትዮጵያውያኖች እንዲህ እንዳትሉ ብሎ በቀጥታ አንድ ቃል ከመናገር ይልቅ በየሥፍራው የተለያየ ጥያቄ ሲቀርብለት ቀጥተኛ ያለሆነ መልስ በመስጠት የተቸገረው ፡፡ ይፈራናል እንዳንል ፣ እየጠፈጠፈ ያበጀን አሻንጉሊቶቹ ፣ እስትንፋሱን ሰጥቶ ሕይወት የዘራብን ነን ፡፡ እንደ እኔ ከሆነ ምኑም አያስኬድም ፡፡ ስለዚህም የወንጌል ጸሐፊዎች ያላቸውን የአነጋገር ባህልና የአጻጻፍ ዘይቤ የሚያውቅ አይሁዳዊና ግሪካዊ ቢመሰክርልን ይመረጣል እላለሁ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !February 1, 2013 at 11:23 AM

   Hi,ምእመን.
   I just want to you answer me this question: Do you believe that our mother Saint Marry had had original sin? Please! short answer (yes, or no)

   Thanks

   Delete
  2. well explantion but the thing is they want to make a confusion thats they target & thats how they started to attack our church but our church have always answer for all question so pls if anybody give you some question that u dont know just ask the church will give to you very well God bless ou all & bless our tewhado church

   Delete
  3. ለAnonymous February 2, 2013 at 10:03 AM

   ስለ አስተያየትህ በጣም አመሰግናለሁ ፤ የምቀበለው ቀና ምክር ነው ፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ የተባለው ዓይነት ግልጋሎት ለመስጠት ፣ እንደ ግብጾች ትንሽ በሥርዓት መደራጀት ይኖርብናል ፡፡ ሌላ ሥውር ነገር ማለቴ አይደለም የጥያቄና መልስ አምድ እንደ http://www.suscopts.org/q&a/ ቢከፍቱ በተመቸህ ጊዜ ያልገባህን ጥያቄ ታቀርባለህ ፡፡ እነርሱም መጽሐፍ ፈትሸው የተስተካከለ መልስ ይሰጡሃል ፡፡ ይህ ቢደረግ ከርስትናህን በዕውቀትም ጭምር ታዳብራት ነበር ፡፡

   የኛን ሥራ ብትመለከተው ግን ለምሳሌ በ http://eotcssd.org/ የሚቀርበውን ትምህርተ ሃይማኖት እንኳን ኮፒ ፔስት እንዳታደርገው መሠሪ ነገር አድርገውበታል ፡፡ የታደሉትና ሃይማኖታቸው እንዲስፋፋ ፣ ሁሉም እንዲያውቀው ፣ በአነጋገሩ እንዳይሳሳት የሚፈልጉ ደግሞ መጽሐፍ እንኳን ወደ ኮምፒዩተርህ አውርደህ እንድታነብ ይደረድሩልሃል ፡፡ እኛ ጋ ግን አልተለመደም ፤ ሁሉም ያወቀ እንደሆነ የሚከሥሩ ወይም ሥራቸውን የሚያጡ ይምሰላቸው አላውቅም የማይካድ ትልቅ ድክመት አለ ፡፡ ይኸም ሆኖብን ነው ፣ በየፊናችን ያለዕውቀትና ብልሃት ያልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል የምናደርገው ፡፡ ቢሆንም ከፊታቸው የተጋረጠውንና ለጊዜው ያለባቸውን ችግር ፈተው ተስተካክለው ሲሠሩ ደግሞ ለውጥ ያመጡ እንደሁ ወደፊት እናያለን ፡፡ እስከዚያው ግን ኩራዛችን አትጠፋም ፡፡ ከኔም ለባሱና ምንም ለማያውቁ ወገኖች ሃሳብ በማጋራት ትጠቅም ይሆናል ፡፡ ለሰዎች እንዲመች አሳጥራለሁ ስል ማለት የፈለግሁትን ሁሉ አላስቀመጥኩም ፤ በድጋሚ የቀረበው ላይ ተመልክተህ ከሰጠሁት አስተያየት ስህተት የምትለውን ብትጠቁመኝ እማርበታለሁ ፡፡

   Delete
  4. የቀደመው ስላልወጡ ፣ ሁለተኛ መልስ

   ሰላም የተሰቀለው
   ወንድሜ ለወሩ ያስቀመጥከው አዲስ ቃል ወይንም ሰሞኑን አጥንተህ ያዘጋጀህልኝ አንዳች አዲስ ነገር ካለህ ፣ እንደልማድህ ማለት ትችላለህ ፡፡ ምክንያትና ሰበብ ከእኔ ዘንድ አትፈልግ ፡፡ አንተ አንድን ሰው ክርስቲያን ነው ብለህ በሰላም የምትቀበለውና የምትወያየው በራስህ ጣባና ዋንጫ ለክተህ ወይም ሰፍረህ ትክክል ሲመጣልህ ብቻ ነው ፡፡

   እውነት የጠየቅኸኝ ቸግሮህ ቢሆን፣ መልስ የሚሆንልህ አቋሜ በመግለጫዬ ተካቷል ፤ ረጋ ብለህ መርምረው ፡፡ አይ ይሄም አልበቃኝም የምትል ከሆነ ደግሞ በሚከተሉት አድራሻዎች ያሉትን ንባቦች ሁሉ ፈትሻቸው ፡፡ እዛ ውስጥ በአኖኒመስ ስም ጥርት ያለ አቋሜና ምክንያቶቼ ተዘርዝረዋል ፡፡ ስህተት አድርገሃል ብለህ የምታስተምረኝ ወይም የምታርመኝ ፣ ሰዎች እስከ ዛሬ ያላሉት ፣ ያልጻፉት ፣ ያልገለጹት ፣ ያልፈተሹት አዲስ ግኝት ወይም ያላቀረቡት ምሥጢር ካለህ ወዲህ በለውና ልመልከተው ፡፡ እኔ እስከ አሁን የሚባለውን ሁሉ ሥራዬ ብዬ አይቼዋለሁና በከንቱ ድጋም እንዳትደክም ለማለት ነው ፡፡

   ላቀረብከው ጥያቄ ዝርዝር መልስ የሚሰጡህ አድራሻዎች
   http://www.abaselama.org/2012/06/blog-post_15.html
   http://www.abaselama.org/2012/07/blog-post.html
   http://www.abaselama.org/2012/07/blog-post_06.html
   http://www.abaselama.org/2012/12/blog-post.html

   ከዚህ በተረፈ አሁን የቀረበልን ርዕስ ጥንተ አብሶን በተመለከተ ስላልሆነ ከተገለጸው ውጭ ተጨማሪ መልስ አትጠብቅብኝ ፡፡

   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
 4. በጣም የታወረ ትንታኔ ነው አንተም እንደሚሳሳቱት ጌታን እኮ አሁንም ያማልዳል የቀደመው የድህነት ስረው ፍፁም አይደለም ከሚሉት ወገን ትመስላለህ

  ReplyDelete
 5. you menafik, there is a bibilical statement saying " yihen metshaf bla" literal meaning -eat this book, sorry for my English. so, why don't you eat then.?

  ReplyDelete
 6. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 30, 2013 at 8:03 AM

  Thank u

  ReplyDelete
 7. I don't think this article is written by someone with the right mind - as it is stated in the article, written by በጌታ በሚነግደው ርኩስ መንፈስ እንጅ.Don’t go around the bush say what your master enemy of the women (The beast) is putting in your mind clearly. I am one of her child with the promise from my LORD.

  ReplyDelete
 8. yetu gar new embetachnn amlak nat yalnat? kechalchhu asayugn.please don't confuse us.

  ReplyDelete
 9. lemndnew comment yalawtachut yegd enanten medegef alebgn wey? ahunm yetu gar new embtachnn amlak nat yalnat? I need prove please.

  ReplyDelete
  Replies
  1. "እዚህ ላይ መቼ አመለክናት? የሚል ይኖራል፡፡ እያከበርናት ሳይሆን እያመለክናት እንደ ሆነ ለማወቅ ስለእርሷ በቃልም በጽሁፍም የምንሰብከው ስብከት፣ ስለእርሷ የምንዘምረው መዝሙር፣ ስለእርሷ የምንቀኘው ቅኔ ሁሉ ቢፈተሽ ነገሩ አምልኮት እንጂ አክብሮት ሊባል አይችልም፡፡"

   Delete
 10. የቀደመው ስላልወጣ አንዳንድ መሻሻሎች ተደርጎበት በድጋሚ ቀርቧል ፡፡ ከዚህ በፊትም ይኸን የመሰለ ችግር አንድ ሁለቴ አጋጥሞኝ ነበር ፡፡ ማስነበብ የፈለግሁትን ግን ማገድ አልቻላችሁም ፡፡ ይልቁንም ከሌላ ቦታ አምጥታችሁ አቀረባችሁት ፡፡ ያንን መንገድ አንድገመው ፡፡ በሂደት አስተካክላችሁ ስታስተናግዱን ቆይታችኋልና አንባቢ የተለያየ ሃሳብን እንዲያስተናግድ የሁሉንም ያለ ተጽእኖ አቅርቡ ፡፡ የቀረበው አስተያየት

  ወንድም ጸጋ አይሁዳዊ ወይም ግሪካዊ ሳይሆን ፣ የአይሁድንና የግሪኮችን የአነጋገር ዘይቤ እየተረጎመ ሃሳቡን ስላካፈለን ፣ እኔም በርሱው መንገድ ሃሳቤን አካፍላለሁ ፡፡ በአለፈው ርዕስ ያቀረብኩት አስተያየት እንደተጠበቀ ሁኖ የዛሬውን ሃሳብ በተመከርኩት መሠረት ትጉሃን አንባቢዎች እንዳይማረሩ አጠር አድርጌ አቀርበዋለሁ ፡፡

  ሀ/ አንቺ ሴት

  - በአይሁድ ባህልና የአነጋገር ፈሊጥ መርምሮ እቅጩን የሚነግረን ካልተገኘ በስተቀር ፤ ጡቷን ጠብቶ ያደገ ልጅ ፣ አንድ የሥጋ እናቱን ለማራቅ ወይም እንደ ኀብረተሰብ ለመቁጠር ስለፈለገ አንቺ ሴት አላት ማለት ግራ ይሆንብኛል ፡፡ ሥጋና ነፍሷን ነስቶ ወይም ከፍሎ ከልዩ አካሉ አዋሕዶ በደልን ለመሻር ተገለገለበት እያልን እያመንንና እያመለክን ምን የሚባለውን ማራቅ እንናገራለን ? በመስቀል ላይ ደሙን እያዘራ ፣ ስቃዩን ታግሶ ፣ በአደራ ይወደው ለነበረ ደቀ መዝሙር የሰጣት ልጅ ፣ አርቋታል ማለትስ እንደምን ለአእምሮአችን አይከብደንም ? ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነው ስንል የሰው ባህርይ የሆኑትን ሁሉ ተጋርቷል ፡፡ እኔ ለእናቴ የምሰጠውን ፍቅርና ክብር ፣ ርሱ በአምላክነቱና በአስተማሪነቱ እጥፍ ድርብ አድርጎ ፈጽሞታል ፡፡ እኔ ተሰቅዬ ሳይሆን ይሙት በቃ የሚለውን ቃል እንኳን ቢያሰሙኝ ፣ የማስበው ስለ አሟሟቴ ነው እንጅ ስለ እናቴ አይሆንም ፡፡ ርሱ ግን ከኛም ባህርይ በላይ ንጹህ ሰውና አምላክ ስለሆነ ስለእናቱ ተናገረ ፡፡

  መጽሐፍን ከተመለከትነው በዘመናቸው ይህን የመሰለ የአነጋገር ፈሊጥና ልማድ ፣ የአጻጻፍ ሥርዓትም እንደነበረ ያሳያል ፡፡ ምክንያቱም አንቺ ሴት የሚለውን ቃል ፣ ኢየሱስ ከድንግል ማርያም ሌላ ፣ ለተለያዩ ሴቶችም (ማቴ 15፡28 ፤ ዮሐ 8፡1ዐ ፤ ሉቃ 13፡12 ፤ ዮሐ 2ዐ፡15) እንደ ተጠቀመበት ሁሉ ፣ መላእክት ፣ ጳውሎስና ጴጥሮስም አንቺ ሴት እያሉ ተናግረዋል (1 ቆሮ 7፡16 ፤ ሉቃ 22፡57 ፤ ዮሐ 2ዐ፡13) ፤ ስለሆነም በምንም የቋንቋ ብልሃት የማቅረብና የማራቅ ትርጉም ሊያሰጠው አይቻልም ፡፡
  ይልቁንም እናቱን አንቺ ሴት በማለት ደጋግሞ የሚጠራት ፣ ቀደማዊ አደም ከበደል በፊት የአካሉን ክፋይ ሴት ብሏት ነበርና ፣ ኢየሱስ ደግሞ በዳግማዊ አዳምነቱ ንጽህት ፣ ብፅዕት ሆና በመገኘቷና የአካሏ ክፋይ በመሆኑ ይህን መጠሪያ ሊሰጣት ችሏል ፡፡ የተቀሩትን ሴቶች ግን በልማዳቸውና ወጋቸው መሠረት እንዲያ ብሏቸዋል ያሰኛል ፡፡ እኔም በአንድ ዘመን ከሰዎች ተምሬ ያገኘሁትንና የማናግረውን ሴት ሁሉ አክስቴ እያልኩ እጠራ እንደ ነበር ወይም አንዳንድ የከተማ ልጆች አዲስ አነጋገርን እንደሚጠቀሙት ይመችህ ፣ ይመችሽ ፣ እንዴት ነው የሚሉ ቃላቶች ማለት ፡፡

  ለ/ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን ። እርሱም፦ ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን?

  - አባትህ ብላ በወጋቸው መሠረት ስታናግረው ፣ የባሕርይ አባቱ እግዚአብሔር አብ መሆኑን መግለጹ ነው ፡፡ በዚህም እግዚአብሔር በምልአት መኖርና መገኘት ባሕርዩ እንደ ሆነ ሁሉ ርሱም በመለኰቱ የማይገኝበት ሥፍራ እንደሌለ መንገሩ ነው ፡፡ አላስተዋሉም ማለትም ይኸን ሥውር አነጋገሩን ነው ፡፡
  ሌላውም በቤተ መቅደስ (በአባቴ ቤት) ያለሁትን ሰው አደጋ ያጋጥመዋል ብላችሁ መስጋት አይገባችሁም ነበር ለማለት ነው ፡፡ ሌባና ዘራፊ ወንበዴና ቀማኛ በመንገድና በጫካ ይገኛል እንጅ በእንደዚህ ባለ ቅዱስ ሥፍራ አይኖርም ማለቱ ነው ፡፡

  ሐ/ እናቴና ወንድሞቼ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት ናቸው

  - ይህኛውንም ባለፈው ርዕስ ዘርዝሬዋለሁ ፡፡ ተንኰለኞችና ተቀናቃኞች በቤተሰብ ምክንያት አሳበው የሚያስተመረውንና የሚያደርገውን ተአምራት እንዲያቋርጥ ፣ ኀብረተሰቡም እንዲበተን ስለፈለጉ ተናገሩት ፡፡ ርሱ ግን በአምላክነቱ ዓላማቸውን አውቆባቸው ፣ ያፈለገው ቢመጣ የጀመርኩትን አላቋርጥም ለማለት መመለሱ ነው ፡፡ በሌላ አገላለጽ ደግሞ እግዚአብሔር በክብር እንደሚበልጥም ሲያስተምር ነው ፡፡ ምክንያቱም የመንግስተ ሰማያትን ቃል ለህዝብ እያዳረሰ ፣ በደዌ የተጠቁትን እየፈወሰ ስለነበረ ፡፡

  መ/ የእናትህ አካሎች ብፁዓን ናቸው ፡፡ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው

  - እናቱ ብፅዕት እንደምትባል የሚያውቀው አምላካችን ፣ ይኸን ለተናገረች ሴት ስለመጣበት ርዕስ ሊያስተምራትና ርሷም ዕድል እንዳላት ሊያበሥራት ስለፈለገ የተጠቀመበት አገላለጽ ነው እንጅ እናቴ ብፅዕት አይደለችም ብሎ የወንጌልን ቃል መሻሩ አይደለም ፡፡ አዎን ብፅዕት ናት ብሎ ቢቋጨው ትምህርት አይናገርም ነበር ፡፡ ነገር ግን ሁሉን አዋቂ ጌታችን አንዲትም ነፍስ በርሱ ትፈለጋለችና ምሥጢር ነገራት ፡፡

  ሠ/ ጌታ በስሟ እንዲህ እንደምናደርግ ስላወቀ የእግዚአብሔርን ሐሳብ እንዳንስት

  - ወንድም ጸጋ የአክብሮት ነው እንደምንልም ብዙ ጊዜ ስላነበበው ያውቃል ፡፡ ርሱ ግን ተገልጦለት ይሁን በምን አላውቅም አሁንም እንኳን የአምልኮ ነው እያለን ነው የሚከራከረው ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ከባለቤቱ ያወቀ ይባላል ፡፡ በሰዎች አእምሮና ልቦና ውስጥ ያለውን የመረዳት ክህሎትም እንደ ተጐናጸፈ ያህል ይመስለኛል ፡፡

  ሌላው ደግሞ ኢየሱስ ኢትዮጵያውኖች እንዲህ አድርገው እናቱን እንደሚያከብሩ ስላወቀ ለዓለም በሚሠራጨው ወንጌል ትምህርቱን በስውር ቃል አሠራጨ እያለን ነው ፡፡ እንዴት ነው ለመሆኑ ? እኛን ለመገሰጽ ፣ እናንተ ኢትዮጵያውያኖች እንዲህ እንዳትሉ ብሎ በቀጥታ አንድ ቃል ከመናገር ይልቅ በየሥፍራው የተለያየ ጥያቄ ሲቀርብለት ቀጥተኛ ያለሆነ መልስ በመስጠት የተቸገረው ፡፡ ይፈራናል እንዳንል ፣ እየጠፈጠፈ ያበጀን አሻንጉሊቶቹ ፣ እስትንፋሱን ሰጥቶ ሕይወት የዘራብን ፍጥረቶቹ ነን ፡፡ እንደ እኔ ከሆነ ምኑም አያስኬድም ፡፡ ስለዚህም የወንጌል ጸሐፊዎች ያላቸውን የአነጋገር ባህልና የአጻጻፍ ዘይቤ የሚያውቅ አይሁዳዊና ግሪካዊ ቢመሰክርልን ይመረጣል እላለሁ ፡፡

  አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
 11. le amelake enaten mamsegen yemitela diyabilose becha new ega gen enamesegenatalen ye akeberote yetshga segedete enesegedelatalen.fekeruwane kelebobacene yeminetkeben yelem.yehen eweku tehadeso menafekane.

  ReplyDelete
 12. to use your lojic.lemindin new JESUS sle amlaknetu,sle yeayhud ngusnetu,sle tinsaew siteyek ketitegna mels yalsetew?

  ReplyDelete
  Replies
  1. thanks brother, u r right. what about keteleyaye tikis yesebesebinachew 3 amlakochachin,Ab. wold Menfeskidus 1 & again 3 yeminlachew?

   There is no a single verse that directly express about trinity. That is why nowadays when scholars asked by muslims about this, tirs gitit, ayin fitit yehonut.

   It is easier to accept the position of Marry in orthodox church than the complex concept of trinity, which is not stated clearly in bible & the devinity of christ.

   Delete
  2. AnonymousFebruary 1, 2013 at 2:34 AM ኦርቶዶክሳውያን የድንግል ማርያም ቅድስናን ለማጽደቅ ሚስጥረ ስላሴን አንክድም!!!እኛ ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ባሕርይ፤ አንድ መንግሥት አንድ መገለጥ አንድ አኗኗር አንድ ሥልጣን አንድ አመለካከት አንድ መለኮት አንድ ዐሳብ አንድ ፈቃድና ሥርዐት አላቸው እንላለን፡፡ ፈቃዳቸው አንድ ነው ዐሳባቸው አንድ ነው፣ ሥርዐታቸውና ሕጋቸው አንድ ነው፣ ኀይላቸው አንድ ነው፣ እንደ አሕዛብ ልማድ ሦስት አማልክት አይባሉም፡፡ በሦስት አካል አንድ አምላክ ይባላሉ እንጂ፡፡ አንዱ አንዱን አይከተለውም ሁለተኛውም ሦስተኛውን አይከተለውም ከያዕቆብ አስቀድሞ ይስሐቅ ከይስሐቅ አስቀድሞ አብርሃም እንደነበረ ሁሉ ከአንዱ በፊት አንዱ አልነበረም፡፡ጥያቄ፡ የሥላሴ ሀልዎታቸው ከመቼ ጀምሮ ነው?
   መልስ፡ አብ ሀልዎቱን ባገኘ ጊዜ፡፡
   ጥያቄ፡ አብ ሀልዎቱን መቼ አገኘ?
   መልስ፡ ያልነበረበት ጊዜ ስለሌለ በዚህ ጊዜ ተገኘ ተብሎ አይነገርም፡፡
   ጥያቄ፡ ወልድስ መቼ ተወለደ?
   መልስ፡ አባቱ ባልተወለደ ጊዜ፡፡
   ጥያቄ፡ መንፈስ ቅዱስስ መቼ ሰረጸ?
   መልስ፡ ወልድ ባልሰረጸ ነገር ግን በተወለደ ጊዜ፡፡
   ደጋግመው ለሚጠይቁን ደጋግመን ይሄን መልስ እንሰጣቸዋለን፡፡


   የአብ አኗኗር ከወልድ በፊት አልነበረም የመባርቅት ብልጭታ መታየት ታህል የዐይን ሽፋን እንቅስቃሴን የምታህል አይቀድመውም፡፡ እናት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ታመናለች እንዲህም ታሳምናለች፡፡...

   Delete
  3. AnonymousFebruary 1, 2013 at 2:34 AM ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ “መጽሐፈ ምሥጢር” “የጥምቀት ምንባብ” ከሚለው የተወሰደ ነው ! ...እናታችንም ቤተ ክርስቲያን በረድኤተ እግዚአብሔር ጥላ ሥር ጸንታ ትኖራለች፡፡ አቤቱ በረድኤት ጥላ ሥር ጸንቶ የሚኖር ማን ነው? መቅደስህም በተሠራበት ቦታ አድሮ የሚኖር ማነው? ተብሎ እንደተጻፈ በሙሽራዋ ክርስቶስ ደስ እያላት የወልድን ኀይል አምና በምእመናን ፀንታ ትኖራለች፡፡ ቀኝ ክንዱ ታቅፈዋለች ግራ ክንዱም ከራሴ በታች ናት ተብሎ እንደተጻፈ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃንነት ወደ ገነት ዓፀዶች ትመራለች፡፡ መንፈሰ ረድኤትህ መርቶ ወደ ምድረ ጽድቅ ያድርሰኝ ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ /መዝ.14፥1/

   ከዚህም በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቅን ስትፈልግ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ትመለሳለች፤ በዮርዳኖስ ወንዝ ለልጁ በመሰከረ በእግዚአብሔር አብ ስም አንድ ጊዜ ትጠመቅ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ትወርዳለች፡፡ ዳግመኛም በዘካርያስ ልጅ በዮሐንስ እጅ በተጠመቀ በእግዚአብሔር ወልድ ስም ትጠመቅ ዘንድ ሁለተኛ ትወርዳለች፡፡ ዳግመኛም በዘካርያስ ልጅ በዮሐንስ እጅ በተጠመቀ በእግዚአብሔር ወልድ ስም ትጠመቅ ዘንድ ሁለተኛ ትወርዳለች የርግብ መልክ ባለው አካል አምሳል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በተቀመጠ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም ሦስተኛ ትጠመቃለች፡፡ከዚህም በኋላ ከዮርዳኖስ ወንዝ ወጥታ አመተ ክርስቶስ ትባል ዘንድ ቅብዓ ሜሮንን ተቀብታ ማዕተበ ክርስትናን ገንዘብ ታደርጋለች፡፡ ቅብዓ ሜሮን የሃይማኖት ኀይል ነውና በጥምቀት የተወለደ ሰው አምላክ ከድንግል የተወለደውን ልደት ይመስላል፤ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም እንደተወለደ ከርሷም ከተወለደ በኋላ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ተገኘ፡፡
   በጥምቀት የተወለደ ሰውም እንደዚሁ ነው ከውኃውም ከወጣ በኋላ ወደ ጥምቀተ ባሕር የገባበትና የወጣበት ምልክቱ አይገኝም፤ መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው ተብሎ በመዝሙረ ዳዊት እንደተነገረ ዱካህም ከጥልቅ ውኃ ውስጥ ነው ፍለጋህም አይታወቅም፡፡ከዚህም በኋላ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሰላም የተሰበከላችሁን የወንጌል ኀይል ተጫምታችሁ ያለውን ቃል ሰምታ የወንጌልን ቃል ጫማ በመጫማት አካሔዷን አሳምራ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትገባለች ኤፌ.6፥15 በራሷም ላይ የዕንቊን ዘውድ ትቀዳጃለች ይኸውም የሃይማኖት አክሊል ነው ዳግመኛም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በራሳችሁ ላይ የሚያድነውን የራኀስ ቊር ድፉ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ በእጃችሁ ያዙ ይሄውም የእግዚአብሔር ቃል ነው ብሎ እንደተናገረ፡፡ ኤፌ.6፥17 በጣቶቿ ላይም የክብር ቀለበትን ታደርጋለች ይሔውም የድኅነት ምልክት የሆነ የክብር ማዕተብ ነው፡፡

   ከዚህም በኋላ አብርሃም ወዳለባት ይስሐቅም በበግ መሥዋዕትነት ወደ ዳነባት ከምድር እስከ ሰማይ ድረስ የእግዚአብሔር መላእክትም ሲወጡባትና ሲወርዱባት ያዕቆብ ባያት የወርቅ መሰላል ወደ ሙሸራው አዳራሽ ትገባለች፤ በእስራኤል ልጆች በደል ምክንያት ምስክር የሚሆኑ ሕግና ትእዛዝ የተጻፈባት ሙሴ የተሸከማት ጽላት ናት መልከጼዴቅም የቤተ ክርስቲያንን ምሥጢረ ቊርባን ሥርዐት የሚገልጽ የኅብስትና የወይን ግብር ያቀረበባት ናት ዘፍ.14፥18

   ዳዊትም አቤቱ አንተ ታቦትህን ይዘህ ወደምታርፍባት ቦታ ተነሥ፡፡ እያለ የእግዚአብሔር ሕግ በተጻፈባት ታቦት ተነሥ፤ እያለ የእግዚአብሔር ሕግ በተጻፈባት ታቦት ፊት ምስጋና ያቀረበባት ናት አሳፍ የተቀኘላት፣ የቆሬ ልጆችም በምስጋና መሰንቆዎች የሚዘመሩላት የቆሬ ልጆችም በምስጋና መሰንቆዎች የሚዘምሩላት ናት፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ ዐለቱን ሰንጥቆ የደብተራ ኦሪቱን ንዋየ ቅድሳት ያስቀመጠባት፣ የተሠነጠቀችውን ዐለት መልሶ እንደነበረችው ያደረጋት፣ እንደ ብረት መዝጊያም የሆነችለት፣ ቁልፎቿንም ለፀሐይ አደራ የሰጠባት ናት፡፡ መዝ.131፥8፣ ተረፈ ኤር.83፥18

   ኤልያስ መልአኩ ያቀረበለትን የተዘጋጀ ኅብስት የበላባት፣ በተመገበው ምግብ ኀይልም ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት የተጓዘባት ናት፡፡ ዕዝራ ሱቱኤል መጻሕፍተ ብሉያትን የምታሳውቀውን ከመልአኩ ዑራኤል እጅ ተቀብሎ የምስጋና ጽዋን የጠጣባት፣ አእምሮውም በዕውቀት ተሞልቶ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት ብሉያትን አፉ ከመናገር ሳያቋርጥ የቆየባት ናት፡፡ /1ነገ.19፥5-8 ዕ.ሱ.3 40/ ዘካርያስ ነጫጭና ጥርኝ ፈረሶችን ያየባት ናት፡፡ ዘካ.1፥8

   ዳንኤልም የእሳት ሠረገላን ያየባት ናት፤ ዘመናት የማይወስኑት አምላክ ከሰው ልጅ ጋር ከበላያቸው ላይ የተቀመጠባቸውን ዙፋኖች ዳንኤል ያየባት ናት፤ ዕንባቆም በሁለቱ እንስሳት መካከል እግዚአብሔርን ያየባት ነቢያትም ሁሉ ደስ የሚያሰኝ ድምጽ የትንቢት ምስጋናን የሚያሰሙባት ናት፡፡ የገሊላ ሕፃናትም ኅሊናን የሚመስጥ፣ ልቡናን የሚማርክ፣ አጥንትን የሚያለመልመውን ማኅሌታዊ ምስጋናን የሚያመሰግኑባት ናት፡፡ ዳን.7፥9፣ ዕን.3፥2

   ጴጥሮስ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ የተቀበለባት፤ ጳውሎስም የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ይሆን ዘንድ የተጠራባት፤ ዮሐንስም እንደነጋሪትድምጽ እያሰማ ምሥጢረ መለኮትን የሰበከላት፤ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን በአምሳለ እሳት የተቀበሉባት ናት፡፡ የእግዚአብሔርን መሥዋዕት የሚያቀርቡበትን መንበረ ታቦት ለመጐብኘት ማኅበረ መላእክት የሚፈሯት ማኅበረ ሰማዕታትም የመከራቸውን ዋጋ ተቀብለው የክብር አክሊልን የሚቀዳጁባት ናት፡፡

   ከዚህም በኋላ በሙሽራይቱ መጋረጃ ውስጥ ለምእመናን ምሳ ይሆን ዘንድ ሙሽራው ይሠዋባታል፤ መሥዋዕቱንም ከማየቷ የተነሣ ጉልበቶቿ ይብረከረካሉ፤ በደሙ ጽዋ ውስጥ ደሙ ሲንጠፈጠፍ ባየችም ጊዜ አንጀቷ ይላወሳል፤ ሥጋውን በፍርሃት፤ ትበላለች ደሙንም በመንቀጥቀጥ ትጠጣለች፤ ከዚህም በኋላ የሃይማኖት ነበልባል በልቡናዋ ውስጥ ይቀጣጠላል፤ ከሆዷም ውስጥ የፍቅር ሞገድ ይናወጣል፡፡

   አሁንም በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ላይ የክህደትን ቃል የተናገረውን የአርጌንስን ነቀፋ እነሆ ፈጽመን ፍጥረቱን ሁሉ ፈጥሮ ለሚገዛ ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና፣ የመንግሥትና የነገሥታት ጌታ ለሆነው ለወልድ ስግደት፣ ልቡና ያሰበውን ኩላሊት የመላለሰውን መርምሮ ለሚያውቅ ለመንፈስ ቅዱስ ጌትነት ይገባል እንላለን፡፡ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

   Delete
  4. የቀደመው ስላልወጣ

   ለAnonymous February 1, 2013 at 2:34 AM

   የሥላሴ ትምህርት በቤተ ክርስቲያናችን ፣ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን (እንደ ምሥጢረ ሥጋዌ ፣ ጥምቀት ፣ ቁርባን ...) ተብለው ከተዘረዘሩት ትምህርቶች ውስጥ የሚገኝ አንድ ክፍል ነው ፡፡ እነዚህን ምሥጢራት በእምነት ካልሆነ በስተቀር በየትኛውም ምድራዊ ጥበብና ፍልስፍና ፣ ስሌትና ቀመር ሊረዱአቸው ወይም ሊደርሱባቸው ፣ አይቻልም ፡፡ ስለዚህም ነው ምሥጢር መባላቸው ፡፡ በግልጽ የሚረዳቸው አንድ አምላክ ብቻ ስለሆነ የማለት ያህል ፡፡

   በኦሪት ዘፍጥረት ሦስተኛው ምዕራፍ አጋማሽ ድረስ ስለ አንድ አምላክ ሥራ እየነገረን መጥቶ በዘፍ 3፡22 ላይ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ (ከእኛ እንደ አንዱ) ፤ በዘፍ 11፡7 ደግሞ ኑ እንውረድ (ኑ እንውረድ)፣ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን እንደባልቀው (እንደባልቀው) በማለት ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል ፡፡ በምዕራፍ 18፡2 ደግሞ በሦስት ሰዎች ተመስለው እንደተገለጹም ተጽፏል ፡፡ የብሉይን መጽሐፍት በሙሉ እንዲሁ ብንመለከታቸው በተደጋጋሚ አንድነቱንና ከአንድ በላይ መሆኑን ይገልጻሉ ፡፡

   ሦስትነቱን በተናጠል ያመለክተን ደግሞ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ (ሦስት ጊዜ ቅዱስ ማለቱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በማለት ኢሳያስ በትንቢት ቃሉ ነው ። ኢሳ 6፡3

   በጥላ የነበረው ሲገለጥ ወይም ሲያልፍ ፣ መጠሪያቸውን በወንጌል ለይቶ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ እያለ ገልጾልናል፡፡ ማቴ 3፡16-17፤ 28፡19 ፤ ማር 1፡10-11፤ ሉቃ 3፡21-22፤ ዮሐ 1፡32-34፤ ዮሐ 16፡27-28፤ 15፡26-27፤ 2ቆሮ 13፡14

   በትክክል በፍጡር ባይነጻጸርላቸውም ፣ የቀደሙት አባቶች ደግሞ ለማስረዳት ያህል ሥላሴን በፀሃይ መስለውታል ፤ ክበቡን እንደ አብ ፣ ብርሃኑን እንደ ወልድ ፣ እንዲሁም ሙቀቱን እንደ መንፈስ ቅዱስ ፡፡ ሁሎችም በየራሳቸው አካል ፣ ስምና ግብር ይገለጻሉ እንጅ ፣ አንዱ አንዱን አይተካም ፣ አንዱ ከአንዱ አይቀድምም ፣ አንዱ ከአንዱም አይበልጥም ፡፡ ስለዚህም ሥላሴ በስም ሦስት ሲሆኑ አንድ አምላክ ፤ አንድ አምላክ ሲሆን ሦስት አካል ፣ ሦስት ግብር ፣ ሦስት ገጽ እያልን እንማራለን ፡፡

   በምድራዊ ቀመር ራሳቸውን ያነጹና ያስተካከሉ ግን ሁል ጊዜም ይህን ምሥጢር ይስቱታል ፤ ሊረዱት አይችሉምም ፡፡ ልጅ ስንል ፣ የአካላዊ ተራክቦ ውጤት አድርገው ስለሚረዱት ይከብድባቸዋል ፡፡ እነዚህን ርሱ ራሱ እንዲያስተምራቸው መጸለይ ብቻ እንጅ በሰው አንደበት አስረድቶ ማሰልጠን አይቻልም ፡፡

   እግዚአብሔር ይርዳን ፡፡

   Delete
 13. ምንም የሚሻሻል(የሚስተካከል) ነገር የለም፡፡ ተዋህዶ ትክክል ናት!

  ReplyDelete
 14. THE BIBLE IS CLEAR ONLY JESUS IS LORD OF LORD.THANK YOU.

  ReplyDelete
 15. የሚገርም ፅሁፍ ነው, ጅራፍ ራሳ መትታ ራሳ ትጮሀለች

  ReplyDelete
 16. Betam yemigermew degafiyachihun kalihone comment atawetum ayidel? Yihun esti, lemanignawim Egna tewun Emebirhan yeAmlak enat endehonech Fetarim endemesekeralt eninageralen. LeEsua Kinne Mezmurna werb siyansat new, yeAmlak Enat hona endet makiberachinin tikoninalachihu? Betam yamigermew neger Esti andd ken sileEslam Tsafu? Esti andd ken sileProtestant tsafu (Ewnet tehadiso/protestant kalihonachihu), esti andd ken sileBaptist weyim sileKatholic tsafu. Beka hule Orthodox tewahedo layy endih torr mesbek min yibejal. Ewnet enante endalachihut atifiten kehone lenisiha gizze situn, Enantenim Libb yistachihu. Ere tewun ebakachihu ere tewun, minale egna bewededinat egna bakebernat enanten akatelachihu. Yihe mechem yeseyitan likift weyim Tsere-Mariyaminet new. Libb yisten!

  ReplyDelete
 17. ዮሐ. 10፥ 33 ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።

  34 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው። እኔ። አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን?

  35 መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥

  36 የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን። ትሳደባለህ ትሉታላችሁን? ==================አሁን ይሄ ቀጥተኛ ምላሽ ነው ?እርሱ የተጥየቀው ስለ አምላክነቱ እርሱ ግን ያወራው አምላክ ዘበጸጋ ስለተባሉት ነቢያት ነው እና ይሄንንስ ምን ትሉት ይሆን???? ======= የማርቆስ ወንጌል10፥
  17 እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና፦ ቸር መምህር ሆይ፥ የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።
  18 ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም አለው። ኢየሱስ ለምን ቸር ትለኛለህ ብሎ እግዚአብሄር ብቻ ቸር ነው ሲል እርሱ ቸር አይደለም ማለት ነውን???? እንዲሁም በሌላ ስፍራ ጌታ ኢየሱስ "ስለ ምን ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ትሉኛላችሁ?" ብሎ ሲጠይቃቸው እናያለን። እቃ በወደቀ በተነሳ ቁጥር እየሱስ ጌታ ነው ማለት አታብዙ እያለ ይሆን?ይሄውም "እኔ ጌታ እና አምላክ መሆኔን ከልባችሁ ሳታምኑ በአፋችሁ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይማለትን አታብዙ (እቃ በወደቀ በተነሳ ቁጥር እየሱስ ጌታ ነው! ማለት አታብዙ እያለ ይሆን?) እኔ ልባችሁን አያለሁ" ማለት ነው።ታድያ ጸጋ ታደለ ጌታ እየሱስ አምላክነቱን እና ቸርነቱን የማራቅ አጠራር አለበት === ትለኝ ይሆን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለ ቃልህ አመሰግናለሁ ፡፡
   ንጹህ ልቦና ላለው ያቀረብክልን ትልቅ ማስረጃ ነው ፤ አባቶች በሚተረጉሙት ካልተመራን በስተቀር መጽሃፉን እንዳገኘን ከነዳነው መጨረሻችን ክህደት ይሆናል ፡፡ ሌላውም ስለዚሁ ጉዳይ ማስተዋል ያለብን ፣ ይኸ የማራቅ ቋንቋ ተዋሕዶውንም የማፍረስ ነገር መሆኑን ነው ፡፡ ዮሐንስ በመልዕክቱ “ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን ፤ ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤” 1 ዮሐ 1፡1-2 ብሏል፡፡

   ዮሐንስ ከመጀመሪያ የነበረውንና የሰማነውን ሲል ከአባቶች በትንቢትና በትምህርት የደረሰውን ወልድን ማለቱ ነው ፣ መለስ አድርጎ ደግሞ ያየነውን ፣ የተመለከትነውን የዳሰስነውን እንመሰክራለን የሚለው በሥጋ አካል ያወቁትን ፣ እነርሱን ለሐዋርያነት የመረጣቸውን ፣ ያስተማረና የባረካቸውን ነው ፡፡

   አዋቂዎቹ ሆነ ብለው ሰውን ለማደናገር ካልሆነ በስተቀር ፣ ይህ ኢየሱስ ለእኛ በሰውነት የተገለጠበት ሥጋና ደም ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ግርዶሽ ከእናቱ የከፈለው ነው ፡፡ በእግዚአብሔር ቃልነቱ ቢሆንማ የርሱን ቀዳማዊ ልዩ አካል ልንዳስሰው ፣ ልናየው አንችልም ነበር ፡፡ ያወቅነውም በርሷ አካል ስለተገለጠና ስለቀረበን ብቻ ነው ፡፡ እርሷን አራቃት ወይም ሊያርቃት በማሰብ ብሎ መተንተን ከአካሉ ጋር ቅራኔ እያደረገ ወይም ተዋሕዶውን ሊሽር እየታገለ የማለት ያህል ይሆናልና ፣ የመጽሐፍ አተረጓጐማቸው ስህተት መሆኑን የሚያመላክት ነው ፡፡

   Delete
 18. የሰውን ትኩረት ከተሸከመችው ማህጸንና ከጠባቸው ጡቶች ላይ ማንሳትና ብፅእና የሚገኝበትን ምስጢር መግለጥ ነው የፈለገው፡፡.... kezih ketlo yalew ጽሑፍ ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ “መጽሐፈ ምሥጢር” ምዕራፍ 6 ላይ “የልደት ምንባብ” ከሚለው የተወሰደ ነው=በሌላም ቃል “አገልጋዬ ዳዊትን አገኘሁት፤ ልዩ ዘይትንም ቀባሁት ኀይሌ ትረዳዋለች፣ ሥልጣኔም ታጸናዋለችና ጠላት በእርሱ ላይ አይሠለጥንበትም፣ የዓመፅ ልጆችም መከራ ማምጣትን አይደግሙም፣ ጠላቶቹንም ከፊቱ አጠፋለሁ፣ የሚጠሉትን አዋርዳቸዋለሁ፣ ይቅርታዬና ቸርነቴ ከእርሱ ጋር ነው በስሜም ሥልጣኑ ከፍ ከፍ ይላል፤ ግዛቱንም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ አደርግለታለሁ፤ ሥልጣኑም ከዳር እስከ ዳር ይሆናል እርሱም አባቴ ይለኛል እኔም ልጄ እለዋለሁ፤ በዐራቱ ማእዘን ከነገሡት ነገሥታት ይልቅ ታላቅ ንጉሥ አደርገዋለሁ፡፡ (መዝ.88፡20-27) በሌላ ቃልም እኔ ለዳዊት ሥልጣንን እሰጣለሁ ለቀባሁት መብራትን አዘጋጃለሁ፤ ጠላቶቹንም የኀፍረት ማቅን አለብሳቸዋለሁ፤ በእርሱ ቅድስናዬ ያፈራል፡፡” (መዝ.131፡17-18) በሌላም ቃል “ቀብቶ ላነገሠው ምሕረትን ያደርግለታል፤ ለዳዊትና ለዘሩ እስከ ዘላለም ድረስ ያደርጋል” ይላል፡፡

  ኢሳይያስም “ከዕሤይ ሥር በትር ትወጣለች፣ ከግንዱም አበባ ይወጣል፡፡ በእርሱም የእግዚአብሔር መንፈስ ያርፍበታል” አለ፡፡(ኢሳ.11፡1) እነሆ የእግዚአብሔር በረከት ወደ ዳዊት ቤት አለፈች፡፡ የዘይት ቀንድ በራሱ ላይ ፈላ፡፡ የመንግሥትም በትር ከቤቱ በቀለች፡፡ ከዘሩም እግዚአብሔር የድኅነታችንን ቀርን [ሊያድነን ሥልጣን ያለው ክርስቶስን] አስነሣልን። ኾኖም ግን [የይሁዳ ዘር፥ የዳዊት ዘር ስለኾኑ ብቻ፤ በነገሥታቱ ዙፋን ላይ ስለተቀመጡ ብቻ! ብሎ፦] ወደገሊላ ነገሥታት ግቢ አልገባም። [የጊዜው ንጉሥ ልጅ ስለኾነች ብቻ! ብሎ፦] የሄሮድስን ልጅ አልመረጣትም። ከይሁዳ መሳፍንትና መኳንንት ልጆች ይልቅ የድኾች [ ኢያቄም እና ሃና] ልጅ [የሆነችውን ንጽሕት፥ ቅድስት ድንግል ማርያምን] መረጠ። ፈጣሬ ዓለማት እሱ እግዚአብሔር ባንዲት ሴት ማሕፀን ዐደረ።ደም ግባቷን ወድዶ ባፈቀራት ጊዜ በጽርሐ አርያም እናት ትሆነው ዘንድ ወደ ሰማይ አላወጣትም፡፡ እርሱ ራሱ ወርዶ በጠራቢው በዮሴፍ ቤት አደረ /ሰው ሆነ/ እንጂ፡፡ በዚያ ትፀንሰው ዘንድ ወደ ኪሩቤል ሠረገላ ላይ አላወጣትም፡፡ ናዝሬት ገሊላ በምትባል አገር ሳለች ራሱ በማኅፀኗ አደረ እንጂ፡፡ በጌትነቱ ሰው በሆነ ጊዜ አላሰፋትም፡፡ ገብርኤልን “በሆዷ ዘጠኝ ወር ትሸከመኝ ዘንድ ድንግልን ወደዚህ አምጣት” አላለውም፡፡እርሱ ትሕትናዋን ተሳትፎ ከገብርኤል ጋር ወርዶ ወደ ድኻይቱ ቤት ገባ፡፡ መልአኩ “መንፈስ ቅዱስ ወዳንቺ ይመጣል” ባላት ጊዜ የአምላክ እናት ለመሆን በመንፈስ ቅዱስ መውረድ ከበረች፡፡ “የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል” ብሎ በደገመ ጊዜ በሰማያዊ አባቱ ሥልጣን ወልድን ለመፅነስ በቃች፡፡ “ከአንቺ የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል” አላት፡፡ ያን ጊዜ ከእርሷ የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ያንን ተረዳች፡፡ እርሷም ወልድ ከአባቱ ጋር ወዳለበት ወደ ጽርሐ አርያም ኅሊናዋን አወጣች /አሳረገች/፡፡ እርሱም ራሱን ዝቅ አድርጎ በትሐትና ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በማኅፀኗ ተፀነሰ፡፡ ዳግመኛ ድንግል መልአኩን “እንደ ቃልህ ይደረግልኝ” አለችው፡፡(ሉቃ.1፡26-32) ያን ጊዜ አካላዊ ቃል ከእርሷ በተዋሕዶ ሰው ሆነ፡፡ አይታው እንዳትደነግጥ ተመልክታው እንዳትፈራ ኪሩቤልን ከእርሱ ጋር አላመጣም፡፡ በወዲያኛው ዓለም በአባቱ ሥልጣን እንዳለ በዚህ ዓለም ለቅዱሳን ተልእኮ የሚጠቅም ምድራዊ ሕግን ሠራ፤ የማይታይ የማይመረመር ኀይል በዚህ ዓለም እርሱ ብቻውን በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ህልው ሆነ፤ በወዲያኛውም ዓለም የማይዳሰስ መለኮት ከሚዳሰስ ሥጋ ጋር በዚህ አለ፡፡....

  ReplyDelete
 19. የልደት ምንባብ ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ...በወዲያኛው ዓለም የእግዚአብሔርን መንበር የተሸከሙ ኪሩቤል አሉ፡፡ በወዲህኛውም ዓለም ሥጋ የተገኘባቸው ዐራቱ ባሕርያት አሉ፡፡በዚያ ያለእናት አባት አለው፤ በዚህ ደግሞ ያለምድራዊ አባት እናት ኾነችለት... በዚያ በጽርሐ አርያም ከማይታይ አባት ተወልዶ የልደት ክብር የልደት ጌትነት የልደት ምስጋና፤ በዚህም በቤተልሔም እርሱ ብቻውን ከድንግል እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ህልው ሆነ በወዲያኛው ዓለም ቅዱስ ገብርኤል በፍርሃት ይቆማል፡፡ በዚህኛው ዓለም ቅዱስ ገብርኤል በደስታ ያበሥራል፡፡ በዚያ በጽርሐ አርያም ከአብ የማይታይና የሚደነቅ የልደት ክብር አለው፡ ሰማያውያን ካህናት በወርቅ ጽንሐሕ የዕጣን መዓዛ ያቀርቡለታል፡፡፡ በዚህኛው ዓለም ከሰብአ ሰገል ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ ይቀርብለታል፡፡በወዲያኛው ዓለም ከግርማው የተነሣ ሱራፌልና ኪሩቤል ይንቀጠቀጣሉ፡፡ በዚህኛው ዓለም ድንግል ማርያም ትታቀፈዋለች፣ ሰሎሜም ትላላከዋለች፡፡ ከዚያ በፊቱ የመባርቅት ብልጭልጭታ ከፊቱ ይወጣል የእሳት ነበልባልም ከአዳራሹ ቅጥር ይወጣል፡፡ በዚህ አህያና ላም በእስትንፋሳቸው ያሟሙቁታል፡፡በዚያ የእሳት መንበር በዚህ የድንጋይ ዋሻ አለ፡፡ በወዲያኛው የተሠራ የሰማይ ጠፈር (ዘፀ.24፡10) በዚህ የላሞች ማደሪያ /ማረፊያው/ ሆነ፡፡ በዚያ ትጉሃን መላእክት የሚገናኙበት ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፤ በዚህኛው የእረኞች ማደሪያ የሆነች ዋሻ አለች፡፡ ዘመኑ የማይታወቅ ተብሎ በዳንኤል የተነገረለት ብሉየ መዋዕል አምላክ በወዲህኛው ዓለም የዕድሜው ቁጥር በሰው መጠን የሆነ አረጋዊ ዮሴፍ አለ፡፡ በጽርሐ አርያም ፀንሳው ቢሆን ኖሮ ክብርና ልዕልና ለብቻዋ በሆነ ነበር፡፡ እኛም በእርሷ ክብር ክብርን ባላገኘን ነበር፡፡ በሰማያት የሚደረገውን ምሥጢር ምን እናውቃለን? በአርያም ያለውን ስውር ነገር በምን እናየው ነበር?

  በኪሩቤል ሠረገላ ላይ እንዳለ ብትወልደው ኖሮ በእቅፍ መያዙን ማን ባየ ነበር፤ አካሉንስ ማን በዳሰሰው ነበር በምድር ላይ ባይመላለስ ኖሮ የጥምቀቱን ምልክት ማን ባየ ነበር፤ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ብሎ አብ ለማን በመሰከረ ነበር፤ መንፈስ ቅዱስስ በነጭ ርግብ አምሳል በማን ራስ ላይ በወረደ ነበር፤ የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ባይገለጽ ኖሮ በማን ስም እንጠመቅ ነበር? ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱን “ሒዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው” አላቸው፡፡ (ማቴ.28፡19) አብ ማን ነው? ወልድስ ማን ነው? መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? እንዳይሉ በዮርዳኖስ ወንዝ የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ተገለጠ፤ በሰው ልጅ አምሳል ባይጎለምስ፣በሰው ልጅ አምሳል ባይታይ እኛን ስለማዳን ማን መከራን በተቀበለ ነበር? እነሆ! የሰው ልጅ ከሰማይ መላእክት ይልቅ ከበረ፤ እግዚአብሔር ከሴት ተወልዷልና፡፡ ስለዚህ ነገር ጳውሎስ “የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” አለ፡፡(ዕብ.2፡16)...

  ReplyDelete
 20. I do not understand people sometimes why they say bad thing about anybody it is sine to say bad thing to anybody. This is only openion and idea ofcurse few people well educated and people read the BIBLE well have a very good maner and talent, good knowladge. But most of the people just write what they think they have no clear Biblical knowladge and background and most of the time the people have no knowldge of the Bible alwyse fast to say something bad about any body's believes.Please let us read the Bible it is clear to understand it is not complecated to see that only Jesus Christ is LORD we have to worship him alone he is the only way the truth the light to eternal life only through him.For history purpose it is ok to know more but for salvation we only need to know Jesus and the father and holy sprite.I am sorry if I ofended anybody..

  ReplyDelete
 21. I did not see any problem with the writer no body should not be angry for what? he write the right thing according the Bible all the verses are right anybody can enterprate the way they understood. The Bible is clear we have to focuse on Jesus not on anybodyelse.

  ReplyDelete
 22. yebeglemid lebisew yimetalu ketebalut wegenoch mehonachihu behulum zenid tawukuwal silezih minim bitisifu manim ayisenakelim einaniten gin libona yisitachihu'''

  ReplyDelete
 23. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ቦታዎች በብዙ ምሳሌና
  በግልጽ የተነገረላት እመቤት ናት፤ በብሉይ ኪዳን ከተነገሩላት ምሳሌዎች መካከል ጥቂቶቹን
  ብቻ ከዚህ ቀጥሎ እንመለከታለን፦
  ሀ. የመጀመሪያይቱ ምድር
  እግዚአብሔር አምለክ በመጀመሪያ ምድርን ከፈጠረ በኋላ ለሰው ሕይወትን የሚሰጥ ፍሬ
  ያፈራችው ዘር ተዘርቶባት ሳይሆን እንዲሁ በቃሉ ብቻ መልካም የሆነውን ፍሬ እንድታፈራ
  ይሁን ስላለ ነው። ዘፍ.፩፥፲፩ ቅድስት ድንግል ማርያምም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን
  የጸነሰችውና የወለደችው፤ እውነተኛውን የሕይወት ፍሬ ያፈራችው በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል
  የብስራት ቃል ብቻ ስለሆነ የመጀመሪያይቱን ምድር ትመስላለች።
  ለ. ዕጸ ሳቤቅ
  እግዚአብሔር የአብርሃምን የእምነት ጽናት ለመለካት ልጁን ይስሐቅን ይሰዋለት ዘንድ
  አዘዘው፤ አብርሃምም አምላኩን እግዚአብሔርን በእውነትና በፍጹም ያመልክ ስለነበር
  የፈጣሪውን ትእዛዝ ሊፈጽም ወደ ሞሪያ ተራራ ልጁን ይስሐቅን ይዞ ወጣ፤ ሰይፋንም መዝዞ
  ልጁን ይስሐቅን ለማረድ ሲዘጋጅ በእግዚአብሔር መልአክ እጅ የተያዘ በዕጸ-ሳቤቅ (ሐረግ)
  የታሰረ በግ እንዲሠዋ ይስሐቅን እንዳይገድል ከእግዚአብሔር ቃል መጣ ከዚያም በጉን ሰዋው
  ይስሐቅም ዳነ። ዘፍ. ፳፪፥፩-፲፫
  በዚህ ታሪክ ውስጥ ብዙ ምሳሌዎች ተነግረዋል፤ ቅድስት ድንግል ማርያም የተመሰለችው
  በእጸ-ሳቤቅ (ሐረግ) ነው፤ በበጉ ደግሞ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ በጉ በሐረጉ ታስሮ
  እንደተገኘ ኢየሱስ ክርስቶስም በእርሷ ማኅፀን ተወስኖ ሰው በመሆኑ በእጸ-ሳቤቅ
  ትመሰላለች።
                                                                                                        
  ሐ. ሰላማዊት ርግብ
  በኖኅ ዘመን በደረሰው የጥፋት ውሃ ኖኅና ቤተሰቦቹ ሊድኑ የቻሉት በመርከብ ተሸሽገው
  ነበር፤ ከዚያም ለመውጣት የጥፋት ውሃው መድረቁንና አለመድረቁን ለማወቅ ርግብን ላኳት
  እርሷም በአፏ የቄጠማ ዝንጣፊ ይዛ ተመለሰች፤ ውሃውም እንደጎደለ አወቁ ከመርከቢቱም
  ወጥተው እንደገና ሰላማዊ ሕይወት መኖር ጀመሩ የላኳት ርግብ ይዛ የመጣችውና
  ያበሰረቻቸው ሰላምን ነው ጥፋት መወገዱን ነው፤ እንደዚህም ሁሉ እመቤታችን ይዛ
  የመጣችው ኢየሱስ ክርስቶስን ነው የሰላሙን መሪ ከሰይጣን እስራት የፈታንን ስለሆነም
  እርሷ በርግቧ፤ ልጇ ደግሞ በቄጠማው ይመሰላሉ።
  መ. እጸ-ጳጦስ ዘሲና (የሲና ሐመልማል)
  በኦሪት ዘጸአት ፫፥፩-፮ ላይ እንደተጻፈው ሙሴ በጎች በመጠበቅ ላይ እንዳለ በኮሬብ ተራራ
  ላይ ቁጥቋጦው በእሳት ሲነድ ነበልባሉ ሐመልማሉን ሳያቃጥለው አየ፤ እርሱም ወደዚያ
  ለመቅረብ በፈለገ ጊዜ ከቁጥቋጦው ውስጥ የእግዚአብሔር ድምጽ ተሰማ፤ ለሙሴም እንዲህ
  አለው፦ ወደዚህ ስፍራ ከመምጣትህ በፊት ጫማህን ከእግርህ አውጣ እኔ የአባትህ
  የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤ ሙሴም በፍርሃት ተውጦ ፊቱን ሸፈነ፤ ነበልባሉ
  ያላቃጠላት ያቺ የሲና ቁጥቋጦ ሐመልማል ምሳሌነቷ ለእመቤታችን ነው እሳተ መለኮት የሆነ
  ጌታ እግዚአብሔር ወልድን በማሕፀኗ ይዛለችና።
  ሠ. የኤልሳዕ ማሰሮ
  ኤልሳዕ መምህሩ ኤልያስ በእሳት ሰረገሎች ተነጥቆ በአውሎ ንፋስ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ
  በኢያሪኮ ተቀምጦ ሳለ የከተማይቱ ሰዎች እንዲህ አሉ፥ እነሆ ጌታችን ሆይ የዚህች ከተማ
  ኑሮዋ ጥሩ ነበር ነገር ግን ውሃዋ መራራ ነው ያረገዙ ሴቶች ሲጠጡት ይጨነግፋሉ፤
  እርሱም አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ ጨውም ጨምሩበት አላቸው። እነርሱም እንዲሁ
  አደረጉ፤ እርሱም ወደ ውሃው ሄዶ ጨውን ጨመረበት፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ይህንን
  ውሃ ፈውሶታል፤ ሞትና ጭንገፋ በዚህ ውሃ ምክንያት አይሆንም አላቸው። ፪ነገ ፪፥፲፱-፳፩
  በአዲስ ማሰሮ የተመሰለቸው እመቤታችን ነች፤ በጨው የተመሰለው ደግሞ ልጇ ኢየሱስ
  ክርስቶስ ነው፤ በመራራው ውሃ የተመሰለችው ደግሞ ይህቺ ዓለም ነች፤ ከማሰሮው የወጣው
  ጨው ውሃውን እንዳጣፈጠው ከድንግል ማርያም የተገኘው እግዚአብሔር ወልድ ዓለሙን
  ከመራራ ኃጢያት ታድጎታል።
  ፪. በአዲስ ኪዳን
  ሀ. የቅዱስ ገብርኤል ብስራት
  “በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ ከዳዊት ወገን
  ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ” ሉቃ.
  ፩፥፳፮ እርሱም “...ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ...” እያለ በማመስገን አምላክን
  እንደምትወልድ አበሰራት በዚህ የቅዱስ ገብርኤል ብስራት ውስጥ ስለ እመቤታችን ድንግልናና
  ጸጋ የሞላባት ስለመሆንዋ፣ የምትወልደውም አምላክ ስለመሆኑና ይህም የሚሆነው ከመንፈስ
  ቅዱስ የተነሣ እንደሆነ መስክሯል።
  ለ. የኤልሳቤጥ ሰላምታ
  የዘካርያስ ሚስት እርስዋም የመጥምቁ ዮሐንስ እናት ቅድስት ኤልሳቤጥ ወዳጇና ዘመዷ
  የሆነች ድንግል ማርያም ልትጠይቃት ወደ ቤቷ በሄደች ጊዜ የማርያምን የሰላምታ ቃል                                                                                                    ስትሰማ በማኅጸኗ ውሰጥ ያለው ጽንስ ዘለለ፤ እርሷም (ኤልሳቤጥም) “የጌታዬ እናት ወደ
  እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ጽንሱ
  በማኅጸኔ በደስታ ዘሎአልና ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብጽእት ናት” አለች።
  ሉቃ. ፩፥፴፱-፵፭
  እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጌታ እናት መሆኗን መንፈስ ቅዱስ ለኤልሳቤጥ
  ገለጸላትና የጌታዬ እናት አለች፤ በማኅጸኗም ያለው ጽንስ ከእርሱ በኋላ ለሚወለደው
  ለጌታውና ለእናቱ በደስታ ዘለለ/ሰገደ ራሷ ድንግል ማርያምም የመልአኩን ብስራት ከተቀበለች
  በኋላ “ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል” ሉቃ.፩፥፵፱ በማለት ተናግራለች።
  ስለዚህ ቅድስት ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር የተመሰከረላት የሰው ልጆች የድኅነት
  መሠረት ናት፤ እኛም ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ለምኝልን እያልን ዘወትር እንጠራታለን።
  ሐ. የመስቀል ስጦታ
  ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሲል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ
  በወዳጁ በቅዱስ ዮሐንስ አማካኝነት ለሰው ሁሉ የሰጠው ታላቅ ስጦታ እመቤታችንን ነው።
  ዮሐ.፲፱፥፳፮-፳፯
  ሰዎች ዛሬ በጌታችን የልደት ዘመን የተለያዩ ስጦታዎችን ይሰጣጣሉ፤ ለነፍስ የማይጠቅም
  አላቂ ሃላፊ ቁሳቁስ ይሰጣጣሉ፤ የሚኮነን ልምድ ባይሆንም ከጌታ የተሰጠችንን ታላቅ
  ስጦታ ግን ከሁሉ አስቀድሞ መቀበል ይገባል፤ እመቤታችን በልጇ ልደት ጊዜ አብራው
  ነበረች፤ በስደቱ ጊዜም አብራው የተንገላታች ነች፤ በመጨረሻው ሰዓት በአስጨናቂው ጊዜ
  በመስቀሉም አጠገብ የተገኘች እርሷ ናት፤

  ReplyDelete
 24. Please do not confuse yourself or angbody the whole Bible is tolking about Jesus Christ.Even Jesue say the whole Book is tolking about him. you make it sound the Bible is about Mary. All the verse you gave from the old testment you are just assuming. the bible is not complecated. any body can understand do not give your owne interpetation it is offense aginst God. Only God knows what kind of theology school did you go to get this kind of interpetation. You need aprayer so God can reveal his word to you.

  ReplyDelete
 25. "tsega SMALL" DO U KNOW WHY I WRITE YOUR NAME IN SMALL LATTER & "SMALL" IN CAPITAL LETTER? B/C U ARE SMALL MORE THAN SMALL.LET ME ASK U ONE THING ARE U ORTHODOX CHRISTIAN ......... I THINK, NO NO NO NO NO NO. I AM CHERENT FROM AXUM UNIVERSITY.10 Q

  ReplyDelete
 26. የእመቤታችን የቅድስት ማርያምና የሌሎች ቅዱሳን በዓላት መቀነስና አለመቀነስ መስተካከሉና አለመስተካከሉ ይመለከትሐል;……. አንተ ነህ እንዴ ህግና ስርዓት ደንብ የምታወጣው በብሎጉ ላይ የለጠፍካቸው ሊቃውንት እንኳን ይቀነስ አላሉም ፡፡በእርግጥ ከእነዚህ ውስጥ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በደንብ ጠንቅቄ አውቃቸዋለሁ፤”የእረፍቷን መታሰቢያ ማድረግ ካስፈለገም በዚያው ባረፈችበት ቀን ብቻ መሆን ሲገባው ወርሃዊ ተደርጎ በቤተ ክርስቲያናችን ያሉትን የበዓላት ቁጥር ከፍ እንዲል አድርጎታል፡፡ ይህ በእርሷ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም ቅዱሳን ስም የተሰሩት በዓላት ላይ ሁሉ የሚስተዋል ነው፡፡ ነገር ግን መስተካከል አለበት፡፡” ያልከው ሀሳብ ፍጹም ከኦርቶዶክሳዊነት የራቀ ኑፋቄ ነው፡፡ ምክያቱም አባታችን ዳዊት በመዝሙሩ ፃድቅን የሚጠሉ ይፀፀታሉ፤የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፡፡ይላል!ይህ አይነት አስተምህሮ እንደ አርዮስ ያስወግዛል ፤እኔም እንደ ምዕመንነቴና እንደ ዲያቆንነቴ አውግዤዋለሁ!!!!!!ወርኃዊ በዓላቱ ይቀነስ የምትል ከሆነ የቅዱስ ያሬድን ድርሰት የሆነው ድጓና ዚቅ ይጥፋ እያልክ ነው፡፡ዝም ብሎ ሊቃውንትን ሳያናግሩና ሳያማክሩ ቀኖናውንና ስርዓቱን አራስ አመለካከት አይቶ መለወጥ ፍጹም ስህተት ነው፡፡
  አወቅሁ! አወቅሁ!አትበል ልታውቅ የሚገባ ብዙ ነገር አለና
  እ/ሔር ልቡናን ይስጥህ

  ReplyDelete