Thursday, January 10, 2013

የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ለሶስት ተከፍሏል ሲል የእኛ ፕሬስ ጋዜጣ ዘገበ

በ1/5/2005 ለንባብ የበቃውን ዘገባ እንደሚከተለው አጠናቅረናል
የ6ኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት ከጥር 8 ቀን 2ዐዐ5 ጀምሮ ሥራ እንዲጀምሩ የሚያዝ ደብዳቤ እንደተፃፈላቸው የ«የኛ ፕሬስ» ምንጮች ይፋ አድርገዋል፡፡  ጥር 6 አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ የዕርቁ ሂደት በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት አጠቃላይ ጉባኤ ቢጠራም ይህ ምስጢራዊ ደብዳቤ የጉባኤው ጥሪ ከመተላለፉ በፊት መውጣቱና ለፓትርያርክ አስመራጮች ሥራ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ ሥጋት ማሳደሩን አስተያየት ሰጪዎች ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ደብዳቤ በጠቅላይ ቤ/ክ ዋና ፀሐፊ አቡነ ፊሊጶስ ተፈርሞ እንዲወጣ የተደረገው በብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስና በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ግፊት መሆኑ ተገልጾአል፡፡ 13ቱ የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት የተመረጡበት ደብዳቤ የተፈረመው በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ፊርማ መሆኑ ይታወሳል፡፡

          ላለፉት ሦስት ዓመታት ሁለቱን ሲኖዶስ ለማስታረቅ ሲንቀሳቀስ የነበረው አስታራቂ ጉባኤ ያወጣው መግለጫ “ለሽምግልና ከተቋቋመ አካል አይጠበቅም” በሚል ተቃውሞአቸውን የገለጡት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጉባኤው ይቅርታ ካልጠየቀ አብረውት ለመሥራት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ይህንንም አቋም አስቀድመው ይፋ  ያደረጉት ወደ ሰሜን አሜሪካ የተላኩት ልዑካን ሲሆኑ በመግለጫቸውም አስታራቂው ስሕተት ፈጽሞአል፣ ይቅርታ ካልጠየቀ አብረነው አንሠራም ማለታቸው የዕርቁ ተስፋ ላይ ጥላ አጥልቶበት ሰንብቶአል፡፡

          ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሰሜን አሜሪካ የድርድር ጉዞ የተመለሱት ልዑካን ለቋሚ ሲኖዶስ የጉዞአቸውን ሪፖርት ማቅረባቸውን የዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ልዑካኑ በሰሜን አሜሪካ ቆይታቸው ዕርቀ ሰላሙ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደነበር ገልጠው እነርሱ በድርድር ላይ እንዳሉ በአዲስ አበባ የአስመራጭ ኮሚቴ መመረጡ የአስታራቂ ኮሚቴው መግለጫ እንዲያወጣና ጉዳዩን እንዳወሳሰበው ጠቁመዋል፡፡ ልዑካኑ እጅግ እንዳዘኑ በገለጡበት በዚህ የአስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ ምክንያት የዕርቀ ሰላም ሂደቱ ለጊዜው ቢስተጓጐልም ሌሎች ሽማግሌዎችን በመጨመር መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

          አረጋውያኑን አባቶች ገለል በማድረግ እየተሠራ ያለውን ሥራ እንደማይቀበሉት የገለፁት ልዑካኑ ጉዳዩ በጥቂት ሊቃነ ጳጳሳት ብቻ የሚታይና የሚወሰን ባለመሆኑ ሁሉም አባቶች የሚገኙበት ስብሰባ እንዲጠራ አሳስበዋል፡፡ በመጀመሪያ ጉባኤው ከጥር አሥራ ስድስት እስከ አሥራ ስምንት እንዲሆን ሐሳብ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ቀን ምልዓተ ጉባኤው በጥር ስድስት እንዲደረግ እና ለዚህም በአገር ውሰጥም ከአገር ውጪም ያሉት ሁሉም አባቶች ተሟልተው እንዲገኙ እንዲደረግ ተወስኗል፡፡
         
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ ያሉበት ወገን ከዕርቀ ሰላሙ በፊት ምርጫውን እናስቀድም፣ አስመራጭ ኮሚቴው ሥራውን ይቀጥል፣ ምርጫው በቶሎ ይፈፀም በማለት መሙአገቱን ያስረዱት ምንጮች ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሚገኙበት ወገን ደግሞ ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም፣ ለምርጫ አንቻኮል በማለት ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ የኛ ፕሬስ የሲኖዶስ አባላት ለሦስት ወገን መከፈላቸውን በተመለከተ ከሁሉም ወገን የሚገኙ አራት ሊቃነ ጳጳሳት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው በመደወል ባነጋገረችበት ወቅት አንደኛው አባት ዝምታን አንደሚመርጡ ሲናገሩ፣ የተቀሩት ሦስቱ አባቶች ተመሳሳይ በሚባል ሁኔታ ስለ ጉዳዩ የሲኖዶሱ ፀሐፊ በጋራ ከሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በቀር በተናጠል የሚሰጥ ማብራሪያ እንዲቆም የተወሰነ በመሆኑ ምንም መናገር እንደማይችሉ አስረድተዋል፡፡
         
የጥር 6 አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ የተጠራው የቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ስብሰባ መቅድሙና ዋና ዋና ሐሳቡ እንጂ ዋናው ይዘቱ ያልተደመጠውን የዕርቀ ሰላም ልኡካኑን ሪፖርት አዳምጦ ለመምከር፣ የሰላምና አንድነት ጉባኤውን በአዲስ መልክ ለማቋቋም ወይም ነባሩን በተጨማሪ ቁጥር ለማጠናከር እንዲሁም በቀጣዩ የሰላም ጉባኤ ላይ መክሮ ለመወሰን ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የፓትርያርክ ምርጫ ሕገ ደንቡን ምልአተ ጉባኤው በአግባቡ በተጠበቀበት ሁኔታ ለማፅደቅ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህም ጋራ በሕገ ደንቡ መሠረት «ልዩነት በሌለው የምልአተ ጉባኤው ድምፅ ተቋቁሞአል» ስለሚባለው የፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ ሁኔታ ለመወሰን ነው፡፡
         
ከአስመራጭ ኮሚቴው በፊት የዕርቀ ሰላም ልኡካኑን ሪፖርት ማዳመጥና የሰላም ጉባኤውን ውጤት መጠበቅ ይገባል በሚል አቋም የያዙ ብፁዓን አባቶች እንደሚተቹት፣ የፓትርያርኩ ምርጫ ሕገ ደንቡ በጸደቀበት የስብሰባ ሥነ ሥርዐት በትንሹ ከ16 ያላነሱ የቅ/ሲኖዶስ አባላት አልተሳተፉም፤ በስብሰባው ያልተሳተፉትም፤ ብፁዓን አባቶች በህገ ደንቡ መሠረታዊ አንቀጾች ላይ መሠረታዊ ተቃውሞ/ ልዩነት አላቸው፡፡

          ከዚህም ባሻገር ከአምስት ያልበለጡ ከሦስት ያላነሱ የፓትርያርክ ዕጩዎችን የሚያቀርበው አስመራጭ ኮሚቴ ሲቋቋም ምልአተ ጉባኤው «ልዩነት በሌለው ድምፅ» እንዲወሰን ተደርጎ በስያሜው ደብዳቤ ላይ መጻፉ ትክክል አይደለም ተብሎአል፡፡ ኮሚቴው የተቋቋመበት አወዛጋቢ ስብሰባ ሲካሄድ፣ ከውይይቱ ራሳቸውን ያገለሉ፤ በውይይቱ ተሳትፈው ተቃውሞአቸውን የገለፁ፣ ከውሳኔው በሁዋላም በቃለ ጉባኤው ላይ የአቋም ልዩነታቸው እንጂ ፊርማቸውን ለማስፈር ያልፈቀዱ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በአስመራጭ ኮማቴው አባልነት ቢመረጡም የተመረጡበትን ደብዳቤ ያልተቀበሉ፣ በተግባርም እንደማይሳተፉ በግልፅ ያሳወቁና እስከ አሁን ውክልናውን ለመቀበል ያልወሰኑ የሚገኙበት መሆኑ የጉዳዩን አንገብጋቢነት ያመለከታል ሲል የዘገበው ደግሞ ሀራ ዘተዋሕዶ የተሰኘው ድረ ገጽ ነው፡፡

          ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ባለው እውነታ፣ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ እና ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የአስመራጭ ኮሚቴው አባል ሆነው መመረጣቸውን ለመቀበል አልፈቀዱም፡፡ የላክሁት መልክተኛ ሳይመለስ በመልእክቱ ላይ አልወስንም በሚል የተቃወሙት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ወደ ሰሜን አሜሪካ አምርቶ የነበረው ልኡክ ሪፖርቱን ሳያቀርብ አስመራጭ ኮሚቴ መቋቋሙን በጽኑ ከመቃወም አንስቶ  ከፓትርያርክ ምርጫው በፊት ለዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ እንዲሰጥ በብርቱ ተሟግተዋል፡፡ የልዩነት አቋማቸው በቃለ ጉባኤ እንዲሰፍርም አስታውቀዋል፡፡ የአስመራጭ ኮሚቴው አባል  ሆነው የተመረጡትን ደብዳቤም እንደማይቀበሉ በተግባርም እንደማይሳተፉ በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የአስመራጭ ኮሚቴው አባል ተደርገው የተመረጡት ግልጽ ተቃውሞአቸውን እያሰሙ በነበረበት ሁኔታ ነው፡፡ ከታዋቂ ምእመናን መካከል አቶ አለማየሁ ተስፋዬ፣ ቀኝ አዝማች ኀይሉ ቃለ ወልድ፣ አቶ ታቦር ገረሱ *ያታዋቂው አርበኛው ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ልጅ( በአባልነት መመረጣቸውን ጨምሮ በአጠቃላይ ሂደቱ ላይ የሚያነሱአቸው ጥያቄዎች በርካታዎች ናቸው፡፡

          የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት ሥራቸውን እንዲጀምሩ የሚያሳስብ ደብዳቤ የፃፉት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ ብፁዕ  ዋና ሥራ አስኪያጁ ታሕሣሥ 26 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. በስማቸው ተፈርሞ በወጣውና ለ13 የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት በጻፉት የማሳሰቢያ ደብዳቤ፣ የኮሚቴው አባላት ጥር 8 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ተገኝተው ሥራቸውን እንዲጀምሩ አዝዘዋል፤ ለዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ግልባጭ መደረጉ ተመልክቶአል፡፡

          13ቱ የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት የተመረጡበት ደብዳቤ የዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ፊርማና ቲተር አርፎበት በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤቱ በየአድራሻቸው ወጪ ተደርጐ እንደነበር የሚያስታውሱ የመንበረ ፓትርያሪኩ ተቺዎች፣ ሁለተኛው ደብዳቤ በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ወጪ እንዲሆን መደረጉ ዐቃቤ መንበሩና ዋና ፀሐፊው በጉዳዩ ላይ የጠለቀ ልዩነት እንዳላቸው አሊያም የተለያየ አቋም ለመውሰዳቸው አስረጂ እንደሚሆን ይገልጻሉ፡፡

          /ሲኖዶሱ እስከ ጥር 3ዐ ቀን ድረስ ለ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ከአምስት ያልበለጡ ከሦስቱ ያላነሱ ዕጩዎች የሚያቀርብ አስመራጭ ኮሚቴ ያቋቋመው ታህሳስ 6 ቀን ሲሆን ለአስመራጭ ኮሚቴው መቋቋም መሠረት የሆነውን የፓትርያርክ ምርጫ ሕገ ደንብ ያፀደቀው ግን ታሕሣሥ 8 ቀን ነበር፡፡ ለአስመራጭ ኮማቴው አባላት የተሠራጩት ደብዳቤዎች አነስተኛ የማይባሉ ተመሳሳይ ግድፈቶችና ድግግሞሽ የታዩባቸው መሆናቸው ተጠቁሞአል፡፡


14 comments:

 1. ይህ ጉዳይ አባቶችን እሚመለከት ነው ። እናንተም እንደ ነፃ ፕሬስ ሳታወላግዱ፤ ቅመማ ቅመም ሳትጨምሩ፤ በየትኛውም ጥግ ከቆሙት ከአንዳቸውም ሳትወግኑ፤ ሪፖርቱን እንዳለ ማቅረባችሁ በውነቱ ያስመሰግናችኋል። ምመናን እዚህ ምንም እሚያገባን ነገር የለም። ይህ ፖለቲካ አይደለም። አባቶች ቢያጠፉም ቅጣታቸው ከግዜር እንጂ ተምእመን አይደለም። በተለይም አንዳንዶቻችን ለእንተርኔት በመቅረባችን በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ምኑም ሳናውቀው እየቀባጠርን እንገኛለን። አባቶች ከያዝነው አቋም አንድ ሳይሆኑ ሲቀሩ እናስፈራራለን፤ እናብጠልጥላለን። ይሄ ተገቢ አይደለም። መከራከራቸውም አንጥላው። በተለይም በሰለጠነ አለም የምንገኝ ሰከን ማለትን፤ ለሌላ አመለካከት ሩም መስጠትን አገር ቤት ካለው ህዝባችን እንማር።

  ReplyDelete
 2. Tthank you brother for your great info.

  ReplyDelete
 3. በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሊቀ ጳጳሱ ሐዋርያዊ ተልዕኮ በአምስት ነጥቦች ሊጠቃለል ይችላል።

  ወንጌልን መስበክ።
  ኦርቶዶክሳውያን ጳጳሳት የክርስቶስን ወንጌል ለቤተ ክርስቲያንና ለዓለም ማወጅና መተርጐም አለባቸው። ጳጳሳት ሊመረጡ የሚገባቸው በይበልጥ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማወቃቸውና ለሌላው ለማስረዳት ባላቸው ችሎታ መሆን አለበት። ለእንዲህ ዓይነቱ ጳጳስ በምሳሌነት ሊጠቀስ የሚችለው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው። ኦርቶዶክሳውያን ጳጳሳት ወንጌልን በታማኝነት ሊከተሉና የአገልግሎታቸው ማዕከል ሊያደርጉ ይገባል።

  ይህ ከሆነ ወንጌል ምንድነው? ወንጌል እግዚአብሔር ሰው የሆነበት፥ ወደ እግዚአብሔር ኅብረት ይመልሰው ዘንድ የወደቀውን የሰውን ልጅን ሰብእና ገንዘብ ያደረገበት፥ ኃጢአትን ድል ያደረገበትና ሞትን ያጠፋበት « መልካም ዜና» ነው። ይህን ያደረገው በክርስቶስ ሕይወት፥ ሞት፥ ትንሣኤና ወደሰማይ ማረግ ነው። ይህ መልካም ዜና በማናቸውም የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ሰጪ አገልግሎቶች ማለትም በምሥጢራት፥ በአምልኮትዋ፥ በጾምና በጸሎት ውስጥ መሠረት ሊሆን ይገባል።

  ጳጳሳት ይህን መልካም ዜና ማለትም የክርስቶስን ሕይወት ሞትና ትንሣኤ ለቀሳውስቶቻቸውና ለምእመኖቻቸው ሊሰብኩ ይገባል። ሰዎችንም ወደንስሐና ወደእምነት ሊጠሩ ይገባል። ሰዎች በቤተ ክርስቲያን አጸድ ስለተገኙ ብቻ ክርስቲያኖች እንደሆኑ አድርገው መገመት የለባቸውም።

  ላለፉት አራት አሠርት አመታት ስናገር ኖሬአለሁ። አሁንም እስከ ዕለተ ሞቴ እናገራለሁ። በኦርቶዶክሱ ዓለም ላይ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ዋና ነገር ቢኖር፥ በልማድ ብቻ ያሉ ዓለማውያን ኦርቶዶክሳውያን በክርስቶስ ላይ እምነት እንዲኖራቸው የማስተማርና የመስበክ ውስጣዊ ተልዕኮ እንዲኖረን ነው። ጳጳሳት በመጀመሪያ የወንጌል አስተማሪዎች፥ ሰባኪዎችና ወንጌላውያን ሊሆኑ ይገባቸዋል። የመጀመሪያው ሐዋርያዊ ተግባራቸውም ይህ ነው።

  እኛ ምእመናንም ከአስተዳደራዊና ከዕለት ተዕለት የሥራ አስኪያጅነት ተግባር በተወሰነ ደረጃ ነጻ ልናደርጋቸው ይገባል። እርግጥ ነው፥ አስተዳደራዊ ሥራዎችን ሊመሩ ይገባል። ነገር ግን እነዚህ አስተዳደራዊ ተግባራት ከወንጌል አገልግሎት ይልቅ ብዙ ትኩረትን ሲወስዱ፥ ምዕመናን በጳጳሳቶቻቸው ላይ ታላቅ ኃጢአት እያደረጉ ነው። ከሌሎች ተግባራት ነጻ በማድረግና በማስተማር፥ በመስበክና ሌሎችን በእግዚአብሔር ቃል በማገልገል፥ በሐዋርያዊ ተግባራቸው ላይ እንዲያተኩሩ ጳጳሳቱን መደገፍ የእኛ ኃላፊነትና ተግባር ነው።

  2. ምሥጢራትን መፈጸም።
  ጳጳሳት የቁርባን ምስጋናና በበላይነት መምራት፥ በየአጥቢያዎቹ የምስጢራት ንጽሕና የተበቀ እንዲሆን ማድረግ አለባቸው። ቅዱስ ቍርባን በወንጌል ላይ የተመሠረተ ነው። « ይህን ኅብስት በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።>> (1 ቆሮ 11፥26) የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት፥ ትንሣኤና ዳግም መምጣት የዚህ ምሥጢር ውስጥ ዋነኛ ማዕከል ነው። ጳጳሱም ሊሰብከውና ሊያከናውነው የተጠራውም ይኸንኑ ነው። ጳጳሱ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አብዝቶ የሰጠውን የፍቅሩን መልካም ዜና ለመናገር የአዋጅ ነጋሪ ነው። ሕይወትየሚሰጠው እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር፥ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የሚያመላክተውም ይህንኑ መልካም ዜና ነው። ለመንጋዎቹ ይህን የወንጌል ምሥጢር በታማኝነት መግለጥና የሕይወታቸው ማዕከል እንዲሆን ማድረግ የሊቀ ጳጳሱ ተግባር ነው። ወንጌሉን አለመግለጥና የሕይወት ማዕከል እንዲሆን አለማድረግ ዛሬ ብዙዎች ወጣቶችን በስም ክርስቲያን እንዲሆኑና ነገር ግን በሕይወት እንዲጠፉ አድርጎአቸዋል። ስለእግዚአብሔር ያውቃሉ። ምንም እንኳ ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ቢመላለሱም፥ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውን እምነት፥ የሕይወታቸው እምነት እንዲያደርጉት ተጠይቀው አያውቁም። ጳጳሳት ( እንዲሁም ካህናትና ምእመናን ሁላችንም የወንጌልን አገልግሎት ልናከናውን ይገባል።

  3. እምነትን፥ አንድነትን እና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ
  በአሁኑ ዘመን የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ ኃላፊነትን መውሰድና ቆራጥነትን ይጠይቃል። የወንጌል ጠበቃ መሆን ማለት በቀላሉ « ትውፊትን ማጠብቅ» ማለት አይደለም። የወንጌል ጠበቃ መሆን ማለት ቤተ ክርስቲያንን ከመንፈሳዊ ድንቁርናና እርጅና መጠበቅም ነው። በዚህ ሰሞን በሌላ ሀገር የሚኖር አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወንድሜ የኤፌሶን መልእክት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይገኛል ወይ ብሎ ጠየቀኝ። እንዲህ ዓይነቱን ጥያቄ በመጠየቄ በጣም አዘንኩ። ይህ ሰው ሊያደርገው የሚገባው ነገር ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስን መክፈትና ማውጫውን መመልከት ነበር። በኦርቶዶክሱ ዓለም ብዙዎች ያሉበት ደረጃ ያ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ « በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ክፋቶች ሁሉ ምንጭ ቅዱስ መጽሐፍን አለማወቅ ነው» ብሎ የተናገረው አለምክንያት አይደለም።

  4. ለሥነ ምግባር ፥ ለቅድስናና ለሁለንተናዊነት ምሳሌ መሆን
  ይህ የሚያመለክተው ጳጳስም፥ ቄስም ይሁን ምእመን ከአንድ በአብ፥ በወልድ፥ በመንፈስ ቅዱስ ከተጠመቀ ክርስቲያን የሚጠበቀውን የሕይወት አካሄድና መንፈሳዊነት ነው።በሊቀ ኅሩያን ቀሲስ መልአኩ http://www.kesis.org/2013/01/blog-post_3.html....

  ReplyDelete
 4. 5. በጳጳሳትና በመንጋዎቹ መካከል ያለውን ክፍተት ማጥበብ ...ዋናውም ነገር በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ያለው የክርስቶስ ወንጌል መልካም ዜና ነው። ግቡ ወንጌል ከሆነ ወንጌልን ግልጥና ማዕከላዊ ማድረግ የኦርቶዶክሳዊ ጳጳስ ሐዋርያዊ ተልእኮ ነው ማለት ነው። እውነተኛ የጵጵስና አገልግሎት ጥሪ ወንጌልን መግለጥና በቤተክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ማዕከላዊ አድርጎ መጠበቅ ነው። ይህ ከሆነ እንግዲያውስ ክርስቲያናዊ አመራር ስላለው የአገልጋይነት ባህርይ ምእመናን በተሳሳተ መንገድ እንዲረዱ ያደረጉ፥ ከጵጵስና አገልግሎቶች ጋር የተለጠፉ በየዘመናቱ የተከማቹ ሥልጣኖችን እንደገና ልንመረምር ይገባል። ቁስጥንጥንያ በኦቶማን ቱርክ ሥር ከወደቀች በኋላ (1453 ዓ. ም) የቁስጥንጥንያ ጳጳሳት፥ የመንጋዎቻችን የፖለቲካና የመንፈሳዊ ሕይወት መሪዎች ነን ሲሉ የወደቁትን ነገሥታት አክሊሎች ማድረግ ጀመሩ። « ክቡር» « ርእስ» የሚል የማዕረግ ስሞችን መጠቀም ጀመሩ። የካቴድራሉ ሊቀ ጳጳስ ሹመትም « በመንበር (በዙፋን) መቀመጥ» ተደርጎ መገለጥ ጀመረ። ጌታችን ኢየሱስ በዚህ ዘመን ቢኖር ስለዚህ ምን ይል ይሆን? « የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ።በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን» ቆም ብለን ካስተዋልነው ይህ የቅዳሴያችን ጸሎት በአንድነት ዙሪያ ለሚፈጠሩ ለሚችሉ ብዙ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ነው። የመጀመሪያው አንድነታችንን የምናገኘው ከየት ነው የሚል ነው? አንዱ ሕብስት ክርስቶስን የሚያመለክት ነው። ይህ ሥጋዬ ነው እንዳለ። ሞቱንና ትንሣኤውን የምንናገርበት የምናውጅበት ነው። ከላይ ደግመን ደጋግመን እንደጠቀስነው ይህ አንድነት ከክርስቶስ የሚሰጠን እንጂ እኛ የምንፈጥረው አይደለም። ቤተ ክርስቲያን አንዲት የሆነችው ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር አንድ ከመሆኑ የተነሣ ነው። « በኵሉ፡ ልብ፡ ናስተብቍዖ፡ ለእግዚአብሔር፡ አምላክነ፡ ኅብረተ፡ መንፈስ ቅዱስ፡ ሠናየ፡ ከመ፡ ይጸግወነ። በፍጹም ልብ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንለምነው፥ ያማረ የመንፈስ ቅዱስን አንድነት ይስጠን ዘንድ» በማለት ዲያቆኑ በቅዳሴ ጊዜ የሚያሳስበንም ለዚህ ነው።


  ሁለተኛው አንድ የሚሆኑት እነማን ናቸው? በኅብስቱ ውስጥ የሚገኘው የስንዴ ደቂቅ « በተራራና በኮረብታ በበረሓና በቈላ የተበተነች ስትሆን እንደ ተሰብሰብች» በክርስቶስ አንድነት የሚሰበሰቡት ማኅበረ ምእመናን (ቤተ ክርስቲያን) ከተለያዩ የሕይወት ጉዞዎች የሚሰበሰቡ ናቸው። ዘማሪው « ለኛ ወገኖችህ ኃጢአት ላደከመን፤ የመስቀልህ ጥላ ማረፊያ ይሁነን » ብሎ እንደተቀኘ፥ በክርስቶስ አንድ የሚሆኑት፥ ኃጢአት ያደከማቸውና በመስቀሉ ጥላ ያረፉ ናቸው። ያለፈ ሕይወታቸው፥ ያለፈ ኑሮአቸው ከክርስቶስ ጋር አንድ በመሆናቸው ላይ ለውጥ አያመጣም፤ በክርስቶስ የመስቀሉ ጥላ እስካረፉ ድረስ። የቤተ ክርስቲያን አንድነት በአንዱ በክርስቶስ እውነት ላይ የተመሠረተ ነው ብለናል። ይህንም ያልንበት ምክንያት የምንቆርሰው አንዱን ኅብስት ነው። የምንጠጣውም አንዱን ጽዋ ነው። የምንሰብከውም አንዱን ክርስቶስን ነው።አንድ የሚሆኑት በመላው ዓለም ተበትነው ያሉ ክርስቲያኖችና አብያተ ክርስቲያናት ናቸው። የሁሉ ጌታ አንዱ ክርስቶስ ስለሆነ በአፍሪካ በእስያ፥ በአሜሪካ ቢሆኑ፤ ወይም የጥንቱን ይዘን በኢየሩሳሌም፥ በአንጾኪያ በሮምና በእስንድርያ ቢሆኑ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር አለ። ቤተ ክርስቲያን በገጠር ብትሆን በከተማ፥ በወርቅ በብር ያማረች ትሁን በእንጨት የተሠራች ፥ ራሷና መሪዋ አንዱ ክርስቶስ ነው። የሚመራት እውነቱን የሚገልጥላት አንዱ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። የምታመልከው በአንድነቱ በሦስትነቱ የሚመሰገነውን አንዱን እግዚአብሔርን ነው። ይህ የአንድነቷ መሠረት ነው። http://www.kesis.org/2013/01/blog-post_9.html

  ReplyDelete
 5. በአሁኑ ወቅት ግን የተሰባሰብንባቸው እውነቶች ከክርስቶስ የራቁ ናቸው። ጥቂቶቹን ብንዘረዝር፥ ዘር፥ ባህል፥ ሥልጣን፥ የክርስቶስን እውነት ሸፍነውና ጣዖት ሆነው ለአንድነታችን አደጋ ሆነዋል። የትግራዩን ተወላጅ በጥርጣሬ ማየት፥ የጎንደሩን ወንድም ማሽሟጠጥ፥ የሸዋውን ሰው መጎነጥ ለአውደ ምሕረታችን እንግዳ አይደለም። የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ይህን የዘረኝነት በሽታ ለምእመናን በማስተላለፋችን መቼ በእግዚአብሔር ፊት በይፋ ንስሐ እንደምንገባ አላውቅም። ይህ አሁን የመጣ ክስተት አይደለም። ልደታ የጎንደር፥ በዓታ የሸዋ፥ ጎፋ የጎጃም፥ እያልን አብያተ ክርስቲያናቱን በጎሣ ከፋፍልነ ማስቀመጥ የጀመርነው ገና ቀደም ብለን ነው። ለምእመኑ ያጋባንበት ስንል አለምክንያት አይደለም። ያ ሕዝብ ይህን የቤተ መንግሥት ሽኩቻ የወለደውን ዘረኝነት አያውቀውም። ጎጃሜዋ ሴት ወይዘሮ ቅኔ ሊማር ለመጣው ተማሪ እንጀራዋን ከሌማትዋ አንስታ ስትሰጠው « ተሜ» ብላ ነው እንጂ ጎሳውን ጠይቃ አይደለም። ጎንደር ለአቋቋም የሄደውም በወግ በማእረግ የሚማረው በቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ ነው። ወሎ ዋድላና ደላንታ የሚሄደውም እንዲሁ። የቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ የአንድነቱ መሠረት ነው። አሁን ግን ከቤተ ክርስቲያናችን ስም አጠገብ የጎሳችንን ቅጽል እስከማስቀመጥ እና እስከ መከፋፈል ደርሰናል። የእነ እከሌ ቤተ ክርስቲያን እስከ ማለት። መሠረታዊ የሆነው እና ልንሰበሰብበት የሚገባን የወንጌል እውነት የሚነግረንን ፍቅርን፥ ሰላምን፥ ትህትናን፥ ራስን አሳልፎ መስጠትን መለማመድ ሲገባን፥ በቀኖናችን፥ በባህላችን፥ በወጋችን አንዳችን አንዳችንን በማውገዝ ላይ ነን። በዚህም አንድነታችን አደጋ ላይ ነው። የወንጌልን እውነት ለመከተል ውስጣዊ ለውጥ ያስፈልጋል። በመሆኑም ያ ውስጣዊ ለውጥ ሲያስቸግር ውጫዊ ላይ ማተኮር ይመጣል። ዛሬ በየአደባባዩ ያለውን መቆራቆስ እንመልከት፤ ብዙዎች ቤተ ክርስቲያናቸው እንደተደፈረች እንደ ጠፋች እየቆጠሩ ያሉበት ነገር ከዛሬ ሃያ ዓመት በኋላ የምንስቅበት ነገር። ይህም በልጅነት ሕይወቴ ያየሁትን ያሳስበኛል። የዛሬ 20ዎቹና 30ዎቹ ዓመታት ገደማ የሴቶች በቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ መዘመር ቤተ ክርስቲያንን እንደማርከስ ተደርጎ ይቆጠር ነበር። በመቋሚያ የተደበደቡ እህቶቻችን ብዙዎች ናቸው። ዛሬ ግን የቤተ ክርስቲያን ውበት ናቸው። የዛሬ ሃያዎቹ ዓመታት ገደማ ስብከተ ወንጌል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትርፍ ነገር ነበር። የዛሬ ሃምሳ አመት ገደማ የቤተ ክርስቲያናችን ሰባክያን የነበሩት ባህታውያን ብቻ ነበሩ። የዛሬ መቶ አመት ገደማ ብላታ መርስኤ ሐዘን ወልደ ቂርቆስ በትውስታቸው ላይ እንዳመለከቱን፥ ሰባክያን ተብለው የሚታወቅቱ የአንድምታ መምህራን ነበሩ። በቀጥታ የእለቱን ምንባብ በንባብ ማውረድ፤ ዛሬ ደግሞ ዘመናዊውን የስብከት ዘዴ (ሆምሌቲክስ) ሥርዓት ያወቁ፥ በነገረ መለኮት ተቋማት የተመረቁ፥ በየአደባባዩ ሕዝቡን ወደቤተ ክርስቲያን እየማረኩት ነው። ባህል ይቀየራል። ባህል ማለት ሌማት ማለት ነው። ባህል ማለት ጻህል( ሳሕን) ማለት ነው። ምግቡ የሚቀመጥበት። ሌማቱን የሚሠራው ዘመኑ ነው። ቅዳሴው የሚተላለፍበት ፕሮጀክተር ሲተክል ፊልም ቤት አደረጉት የሚል ትውልድ፥ አድማሳቸው ሰፊ የነበረውን የቀደሙትን አባቶች ታሪክ በሚገባ ያላስተዋለ ትውልድ ብቻ ሳይሆን፥ ወንጌልንም በሚገባ ያልተገነዘበ ትውልድ ነው። ቅዱስ መጽሐፍ «ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚለቅሱም ጋር አልቅሱ።» ይህንን ታላቅ ድርጊት ደግሞ ራሱ ቤዛችንና መድኅናችን አድርጎታል። በኃጢአት ፍላጻ ተነድፎ ለሞት የተሰጠውን የሰው ልጅን ከወደቀበት ሐዘቅት ያድነው ዘንድ፥ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን መስሎአል። የቤተ ክርስቲያን ጥሪዋና ድምጽዋ በውጭ ላሉት ሊደርስ ያልቻለው፥ እኛ « በውስጥ» ያለነው ብዙ ጊዜ የምንጨነቀው ራሳችን ከሌሎች ለመለየት እንጂ ከተጠቁት፥ ከተገፉት፥ ልባቸው ከተሰበረውና ግራ ከገባቸው ጋር አንድ ለማድረግ አይደለም።? ከጥንት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን በቅዳሴዋ ስትጸልይ የነበረው ይህ አንድነት እውን እንዲሆን ነው። በቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድና በአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ትምህርት ( Teaching of the Twelve Apostles, 9) ቤተ ክርስቲያን የሚከተለውን ጸሎት ትጸልያለች። « ይህች ኅብስት በተራራና በኮረብታ በበረሓና በቈላ መካከል የተበተነች ስትሆን እንደ ተሰበሰበች፥ ተሰብስባም አንዲት ፍጽምት ኅብስት እንደሆነች፥ እንዲሁም እኛንም በመለኮትህ ከክፉ የኃጢአት አሳብ ሁሉ ለይተህ በፍጹም ሃይማኖትህ ሰብስበን።» ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤ ቊ. 91። በአሁኑ ወቅት ግን የቤተ ክርስቲያኒቱን አደባባይ ያጣበበው ድምጽ የኑፋቄ ፖለቲካ ነው፤ የምንቃወመውንና የምንጠላውን ወገን በኑፋቄ ጠልፎ መጣል። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ከዛሬ መቶ አመት በፊት ጐሐ ጽባሕን ሲጽፉ ለአገርና ለወገን ጠንቅ የሆኑ ብለው ካነሡዋቸው ነገሮች አንዱ ቤተ መንግሥቱን ጥግ አድርጎ የንጹሐንን ደም ማፍሰስ ነው። የነአባ ዘሚካኤል የነደቂቀ እስጢፋኖስ ደም የፈሰሰው በዚህ መንገድ ነው። እነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍል ተገፍተው የወጡት በዚህ መንገድ ነው። ዛሬም ያን የኑፋቄ ፖለቲካ ያነገቡ ሰዎች የጥንቶቹን ስመ ጥር ሊቃውንት እነ አቃቤ ሰዓት ከብቴን ይወገዙልን እያሉ እንደሆነ እየሰማን ነው።እውነት ነው የተሃድሶ እንቅስቃሴ አለ!!!!!!እኛም ልጆቹዋ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ይበጃል የምንለውን አሳብ የምናቀርበው ቅዱሳት መጻሕፍትን፥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ትውፊትና ታሪክ አጣቅሰን ነው በዘመናዊነት አስተሳሰብ ተገርኝተን አይደለም። የአውሮፖውያን የአብርሆት ፍልስፍናና አመክንዮ፥ ወይም አምልኮትን ከቃለ እግዚአብሔር የለየው የ16ኛው ክፍለ ዘመን የሃይማኖት እንቅስቃሴ፥ ወደ ደረቅ ምርመራ ሰውን ሁሉ ስለመራ ዛሬ አውሮፓ የክርስትና ምድረ በዳ ሆና የሐዋርያ ያለህ እያለች ነው። በመሆኑም አውሮፓን ያደረቀና እምነት አልባ ያደረገ አካሄድ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልምላሜን ሊያመጣ አይችልም። ስለሆነም ኦርቶዶክሳውያን ከፕሮቴስታንቶች የምንለይበትን ድንበር ማፍረስ አይገባም!!!በሌላ በኩል ደግሞ ትውፊታችንን ታሪካችንን ስንል ደግሞ በጭፍን ያለፈውን ጉድለታችንን ሳንመዝን አናግበሰብስም። አሁን ግን የሚታየው ከዚህ የተለየ ነው የቃላት ወለምታን እንደ ኑፋቄ የምግባር ጉድለትን እንደ ክህደት የሚቆጥር ደግሞም ይቅር የማይል ሁሉንም የሚጠራጠር ትውልድ ላይ ደርሰናል ታስታውሱ ከሆነ መምህር ግርማም የዚሁ ጠርጣራ ትውልድ ሰለባ ሁነው ነበረ! እውነተኛ ልጆቹዋ እነማን እንደሆኑ የሚያውቀው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሲሆን ውጫዊ ምልክቶች ግን አሉዋቸው። ከእነዚህም ምልክቶች ዋነኛው ፍቅር ነው። አገልግሎት የሚመነጨው ከዚህ ፍቅር ነው። እምነታቸው እንኳ ለገላትያ ሰዎች ቅዱስ ጳውሎስ እንደጻፈው « በፍቅር የሚሠራ እምነት» ከዚህ የተነሣ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ስለሚጠፉት ሰዎች ይገዳቸዋል። በእንባና በጸሎት ያስተምራሉ ይመክራሉ የመድኃኔ ዓለምን ሞቱንና ትንሣኤውን ይመሠክራሉ። ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ ማለት ትውፊትን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን ከመበስበስና ከድንቁርና መጠበቅ ማለት ነው !!!!!!!! ይሁንና ቤተ ክርስቲያናችን አሁን ላለችበት ሁኔታ ተጠያቂ የምናደርገው አንድን ቡድን ወይም አካል ሳይሆን ሁላችንንም ነው።kesis.org

  ReplyDelete
  Replies
  1. 17 ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።

   ቀደም ብለን እንዳልነው በኃጢአት ዓለም ውስጥ ያለ ሰው የሚለየው ከሰማያዊ አባቱ ብቻ ሳይሆን ከእውነተኛው ማንነቱም ነው:: በመሆኑም ጌታ በምሳሌው የጠፋው ልጅ የአባቱን ቤት ያሰበበትን ወቅት ወደልቡ የተመለሰበት ወቅት አደረገው:: በምን ምክንያት ወደ ልቡ ተመለሰ? እንዴት ተመለሰ ብለን ስንጠይቅ ፍሎክሴኒዩስ ወይም ፊልክስዩስ የተባለው የቤተ ክርስቲያን አባት እንደተናገረው ከሆነ ምንም እንኳ በኃጢአት አለም ቢሆንም እግዚአብሔር አባትነቱን አልነፈገውም:: ምንም እንኳ ከእርሱ ፊት ሸሽቶ ወደ ሩቅ አገር ቢሄድም አባቱ አልረሳውም:: ወደ እውነተኛ ማንነታችን ስንመለስ የመጀመሪያው የምንገነዘበው ነገር ቢኖር የሕይወታችንን ዓላማ ነው:: እስከዛሬ ይህ ልጅ የጠፋ ልጅ ነው:: ይህ ልጅ አባካኝ ልጅ ነው:: ይህ ልጅ በመጨረሻ የአሳማ እረኛ ነው:: አሁን ግን ወደ ልቡ ሲመለስ << አባቴ>> አለ:: ማለት የባለጸጋው የርህሩሁ አባት ልጅ እንደሆነ አስተዋለ::

   18 ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና። አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥19 ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።20 ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ።
   “አባቱ ገና ሩቅ ሳለ አየውና አዘነለት፤ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው፡፡ አገልጋዮቹንም ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አልብሱት፤ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡት፡፡ የሰባውን ፍሪዳ አምጥታችሁ እረዱት እንብላም ደስ ይበለን፡፡ ልጄ ሞቶ ነበር ሕያው ሆኗልና፡፡ ጠፍቶ ነበር ተግኝቷልና፡፡” አላቸው፡፡ ሉቃ. 15፡20-24፡፡

   አባቱ የልጁን መመለስ የሚናፍቅ እንደነበረ ከቃሉ ጀርባ ያለው ፍቅሩ ይነግረናል፡፡ ወላጆች ጊዜያዊ ቁጣቸው እስኪያልፍ የልጆቻቸውን ፊት ማየት ላይፈልጉ ቢችሉም እንኳን ቆይተው ግን መጨከን አይችሉም፡፡ የገረፉትን ልጃቸውን እንባ የሚያብሱት ራሳቸው ናቸው፡፡ ልጃቸው መጽናናት አልችል ሲል “እንዲህ አደርግልሃለሁ” በማለት ሀዘኑን ያስረሳሉ፡፡ የእግዚአብሔር ጽኑ ፍቅሩንና አባታዊ ርህራሄውን የሚከተል ፍለጋውንም በወላጆቻችን ፍቅር እናያለን፡፡

   እግዚአብሔር ወደ እርሱ ለመመለስ መንገድ ለሚጀምሩት ቅርብ ነው፡፡ መመለሳችንን በናፍቆት ይጠብቃል፡፡ በአንድ እርምጃ ጉዞ ወደ እርሱ ስንጀምር ሁለት እርምጃ ወደ እኛ መጥቶ ይቀበለናል፡፡ መጎሳቆላችን እና በሙላት ወጥተን በባዶነት መመለሳችን ያሳዝነዋል፡፡ እጆቹን ዘርግቶ ያቅፈናል፡፡ በመዳፉ በረከት ጉስቁልናችንን ያስወግዳል፡፡ በእቅፉ ሙቀት መከራን ያስረሳናል፡፡

   በምድር ሥርዓት ያጠፋን መቅጣት እንጂ መሸለም አልተለመደም፤ አባታችን እግዚአብሔር ግን ይህን አድርጓል፡፡ አዳም በድሎ ሩቅ ቆሞ ሳለ አይቶ አዘነለት፡፡ በገነት ጫካዎች ተገልጦ ፈለገው፤ በሰው ቋንቋ ጠራው፤ የፍቅር ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ የአዳም የቅጠል ልብሱ ስላላማረበት ራቁቱን የሚሸፍን የማያረጅ ልብስ ሸለመው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ፡፡ 1ዮሐ. 3፡1፡፡

   ዓለሙን እንዲሁ የወደደው አብ አንድያ ልጁን አሳልፎ ሰጠ፡፡ ዮሐ. 3፡16፡፡ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ልጁ ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ፡፡ ኃያሉ ወልድ(ክርስቶስ) ፍቅር ከዙፋኑ ስቦት ለመስቀል ሞት ታዘዘ፡፡ አዳምን እስከ መቃብር ወርዶ ፈለገው፡፡ የተራቆተውን የሰው ልጅ ሀፍረት በጸጋው ሸፈነው፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ራቁታችንን የሸፈነ ያልተሠራ የጽድቅ ልብሳችን፤ ከሰማይ የወረደ የማያስርብ ሕያው እንጀራችን፤ ለዓለም የሚበቃ እና የሚያጠግብ ፍሪዳችን፤ በሞት ጀርባ ላይ የሚያስኬድ በሞገድ የማይሰበር መርከባችን፤ የማያረጅ ጌጣችንና የማያልቅ ሀብታችን ነው፡፡

   በአንድያ ልጁ ጨክኖ ለዓለም የራራ፤ በልጁም ትውልድን የተቀበለ፤ ጠፍተን የነበርነውን በልጁ ሞት ያገኘ፤ መገኘታችንንም ያወጀ፤ በልጁ ሕያውነት ሕያዋን ያደረገን፤ ሕያውነታችንንም በቃሉ የነገረን፤ በእኛ መመለስ ደስታ ያደረገ እግዚአብሔር አብ ይመስገን፡፡ 1ዮሐ. 4፡14፡፡
   ለዓለም ራርቶ በአዳም ላይ የወደቀውን ፍርድ በራሱ ላይ አድርጎ፤ ከገነት ጫካዎች እስከ ጎልጎታ የፈለገን፤ አንገቱን ደፍቶ ቀና ያደረገን፤ ወድቆ ያነሳን፤ ተርቦ ያጠገበን፤ ተጠምቶ ያጠጣን፤ ተራቁቶ ያለበሰን፤ ቆስሎ የፈወሰን፤ በሞቱ ሞታችንን የሻረ፤ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመስገን፡፡ ኢሳ. 53፡3-10፡፡17.... kesis.org,http://betelhemm.blogspot.com/

   Delete


  2. ትልቁ ልጅ በእርሻ ነበር፤ መጥቶም ወደ ቤት በቀረበ ጊዜ የመሰንቆና የዘፈን ድምጽ ሰማ ከብላቴናዎችም አንዱን ጠርቶ ይህ ምንድነው? ብሎ ጠየቀ እርሱም ወንድምህ መጥቷልና በደህና ስላገኘው አባትህ የሰባውን ፍሪዳ አረደለት አለው፡፡ ተቆጣም ሊገባም አልወደደም፡፡ የትልቁ ልጅ ቁጣ፡፡

   ትልቁ ልጅ በጠፋው መመለስ በሞተው ሕያው መሆን አልተደሰተም፡፡ በቤቱ በሆነው ደስታ መሳተፍ አልፈለገም፡፡ የቤቱን ደስታ ሊረብሽ ሞከረ፡፡ አባቱ በለመነው ጊዜ “ይህን ያህል ዓመት እንደ ባርያ ተገዝቼልሀለሁ፡፡ ከትእዛዝህም ከቶ አልተላለፍሁም፤ አንድ ጠቦት እንኳን አልሰጠኸኝም ነገር ግን ገንዘብህን ከጋለሞቶች ጋር በልቶ ይህ ልጅህ በመጣ ጊዜ የሰባውን ፍሪዳ አረድህለት” አለው፡፡

   በአባቱ ቤት መኖር ትልቅ ሀብት መሆኑን አላስተዋለም፡፡ በአባቱ ቤት ሲኖር አልከሰረም፤ አልተጎሳቆለም፣ አልረከሰም፤ የቀድሞ መልኩን አላጣም፤ የሰው ፊት አላየም፤ አጥቶ አልተራበም፤ ተርቦ አልለመነም፤ ግን ይህን ማሰብ አልቻለም፡፡ ስለዚህ አባቱ “ልጄ ሆይ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ ለእኔ የሚሆነው ሁሉ ያንተ ነው፡፡ ይህ ወንድምህ ጠፍቶ ነበር ስለተገኘ ሞቶም ነበር ሕያው ስለሆነ ደስ እንዲለን ይገባል፡፡” አለው፡፡ ሉቃ. 15፡32፡፡
   “ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ….ሰፊ ነው የእርሱ መንግስት፡ፍቅር ይበልጣል ከሀብት፡፡”
   በቤቱ መኖራችን ትልቅ ትርፍ ነው፡፡ መቆማችን ዋጋ አለው፡፡ በሕይወት መኖራችን ትልቅ ሀብት ነው፡፡ የልመናችንን ባንቀበል እንዳሰብነው ኑሮአችን ባይቃና በእቅፉ መኖራችን እረፍት ነው፡፡

   ንጉሥ ዳዊት በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት መኖርን መርጧል፡፡ ልጁ ሰሎሞን ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ማረፍን እጅግ ወዷል፡፡ መዝ. 26፡4፣ መኃ. 2፡3፡፡ ታላላቆች የተመኙትን እድል ታናናሾቹ ልንንቀው አይገባም፡፡ በቤቱ በመኖራችን ብቻ እናመስግነው፤ በዓለም ከተቃጣው መቅሰፍትና በወጡት ከደረሰው ክስረት ተርፈናልና፡፡

   በጠፋው መገኘት፣ በተበተነው መሰብሰብ፣ በወደቁት መነሳት፣ በራቁት መቅረብ፣ በሞቱት ሕያው መሆን ደስ የማይላቸው ትልልቅ ልጆች በመቅደሱ ደጅ አሉ፡፡ ድሮ ዲያቆናቱ ወደ ዘፈን ይሄዱ ነበር፤ ዛሬ ዘፋኞቹ ወደ መዝሙር ሲመጡ ትልቁ ልጅ ይቆጣል፡፡ ወጣቱ ጫት ጥሎ ክፉን ጠልቶ መጥቶ ደጀሰላሙ በመንጋው ሲሞላ የትልቁ ልጅ ፊት ይጠቁራል፡፡ ተተኪ አገልጋዮች ዐውደምሕረቱን ሲሞሉ ትልቁ ልጅ ይከፋዋል፤ በጸጋ የበረቱትን ሲያይ ያመዋል፡፡ በወንድሙ መባረክ ይከፋል፡፡ ዝማሬው ሲደምቅ ሕዝብም እውነትን ሲያውቅ ትልቁ ልጅ ይሳቀቃል፡፡

   ትልቁ ልጅ ከውስጥ በሚወጡት እንጂ ከሌላ በረት በሚመጡት አይደሰትም፡፡ የክርስቶስ ትእዛዝ ደግሞ “ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ” የሚል ነው፡፡ ትልቁ ልጅ የኃጢአተኛውን መመለስ አይፈልግም፡፡ የራሱ መዳን እንጂ የሌላው መጥፋት አይገደውም፡፡ ኃጢአተኛው በክርስቶስ እግር ስር ተደፍቶ ሲያይ ሳይጸየፍ የተቀበለውን ጌታ ያቃልላል፤ በልቡም ይረግማል፡፡ የኃጢአተኛውን ታሪክ እየዘረዘረ ያሳጣል፡፡ አምላኩ የተወለትን የነበር ታሪክ ይተርካል፡፡ ይቅር የተባለለትን ኃጢአት ይቆጥራል፡፡ ስምዖን ትልቁ ልጅ ኃጢአተኛዋን ይጸየፋል፡፡ ወደ ክርስቶስ ስትቀርብ ተበሳጭቷል፡፡ ጌታ ደግሞ ኃጢአተኞችን ተቀብሎ ያነጻል፡፡ ወደ እርሱ የሚመጡትን ወደ ውጭ ከቶ አያወጣም፡፡ የትልቁን ልጅ የጠቆረ ፊት እያዩ ከመቅደስ የተመለሱትን፤ቁጣውም የሰበራቸውን ቤት ይቁጠራቸው፡፡
   “ስምዖን ዞር በል ይከፈት በሩ
   ይብቃ ሲምረኝ ማንጎራጎሩ”
   ትልቁ ልጅ ይሁዳ የኃጢአተኞችን መመለስ ሳይሆን የኃጢአተኞችን መብዐ ይፈልጋል፡፡ ለሕዝቡ መዳን የማይጨነቁ፤ ገንዘቡን ግን አሟጠው የሚበሉ ጅቦች በየአብያተ እምነቱ ታስረዋል፡፡ ከየት እንደመጣ የማያውቁትን የአመጻ ገንዘብ የሚሰበስቡ፤ ሰጭውን በውዳሴ ከንቱ እየሸነገሉ ከመዳን የሚያዘገዩ ብዙዎች ናቸው፡፡ የተላክነው ለነፍሳቸው እንጂ ለገንዘባቸው አይደለም፡፡ ገንዘብ ለመሰብሰብ በደም ዋጋ የተገዛውን መንጋ አንበትን፡፡ ብር ሲያመጡ እናስጨበጭባለን ስለ ሕይወታቸው ሥርዓት ግን አይገደንም፡፡

   ዮናስ ትልቁ ልጅ በሕዝቡ መትረፍ ይቆጣል፡፡ በነነዌ መዳን በሰማይ ታላቅ ደስታ ሆኗል፡፡ የተበደለው እግዚአብሔር እንኳን ደስ ብሎት ነበር፡፡ ነቢዮ ዮናስ ብቻ ደስተኛ አልነበረም፤ ተቆጣ እንጂ፡፡ ዮና. 4፡1፡፡ እግዚአብሔር ለነነዌ ድኅነትን በመስጠቱ ምክንያት ከተደረገው ታላቅ ደስታ ተካፋይ ከመሆን ራሱን አቀበ፡፡

   ሲጀመር እግዚአብሔር ነነዌን የማስተካከል እንጂ የማጥፋት አላማ አልነበረውም፡፡ እግዚአብሔር በሚፈሩት ላይ የጭካኔ በትር አያሳርፍም፡፡ የሚመለሱትን ይቀበላል እንጂ አይበቀልም፡፡ የተበደለው እግዚአብሔር ለክብሩ ሳይቆረቆር ዮናስ ግን ለክብሩ መቆርቆር ጀመረ፡፡ ሕዝቡ ስለዳነ እርሱ ሞትን መረጠ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ “ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከ120 ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሳት ላሉባት ለነነዌ አላዝንምን?” አለው፡፡ ዮና. 4፡11፡፡

   ትልቁ ልጅ ለራሱ ክብርና ጥቅም እንጂ ለሌላው አይገደውም፡፡ የእግዚአብሔር የቁጣ ጅራፍ ተነስቶ ትውልዱን ቢገለባብጥ ደስተኛ ነው፡፡ ፍርዱ እርሱንም እንደሚያገኘው አያስብም፡፡ ትልቁ ልጅ የብዙዎች መጥፋት አይገደውም፡፡ እግዚአብሔር በዓለም ላይ የመፍረድ ስልጣን ለሰከንድ ቢሰጠው ዓለምን ያጠፋል፡፡ ትልቁ ልጅ የአባቱን ርህራሄና የወንድሙን ጉዳት የማይረዳ ነው፡፡

   ትልቁ ልጅ ለእግዚአብሔር ምሕረት ድንበር ይከልላል፡፡ እግዚአብሔርን በቦታ ይወስነዋል፤ ከቤተክርስቲያን አጥር ውጭ የሚሰራ አይመስለውም፡፡ መዳን የሚፈልገው በጥረቱና በራሱ ስሌት ነው፤ በአምላኩ ቸርነት አይደገፍም፡፡ ትልቁ ልጅ ብቻውን መውረስ ይፈልጋል፡፡ በእግዚአብሔር ፍርድ ውስጥ ጣልቃ መግባት ይፈልጋል፡፡ “ጥጦስ ለምን ገነት ይገባል? በ11 ሰዓት የመጣው ለምን ከእኔ ጋር እኩል ይከፈለዋል?” እያለ ይከራከራል፡፡ ለራሳቸው ሳይድኑ ሊድኑ ለመጡት መስፈርት የሚያወጡ፤በሥራቸው ተመክተው የደከሙትን የሚያደክሙ ብዙዎች ናቸው፡፡ የእርሱ መስዋዕት ስለተናቀ ሳይሆን የወንድሙ ስለተወደደ ያዝናል፡፡ የትልቁ ልጅ ዐይን ምቀኛ ናት፤ የአንደበቱም የቁጣ ቃል ይሰብራል፡፡

   እግዚአብሔር የተቀበላቸውን ልንቀበል፤ ያከበራቸውን ልናከብር፤ በደላቸውን የተወላቸውን ልንተውላቸው ይገባል፡፡ እግዚአብሔር አሰራሩን በሰው ሥርዓት ከመቃወም ይሰውረን!! የዓለምን መዳን የወደደ፤ በፈቃዱም ከአብና ከወልድ ጋር አንድ የሆነ፤ ትውልድን እያነቃ ወደ መዳን የሚያደርስ፤ ያላመኑትን የሚወቅስ፤ ትውልድን ለቤዛ ቀን የሚያትም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይመስገን፡፡ ዮሐ. 16፡7-10፡፡

   Delete
 6. በብዙ ጨለማዎች ፊት ብርሃን መሆን አልተቻለም፡፡ አልቅሰው መጥተው አልቅሰው የሚመለሱ፣ በጉድለት መጥተው በጉድለት የሚሸኙ፣ ከእነርሱ መንፈሳዊነት የእኔ ዓለማዊነት ይሻላል የሚሉ በዝተዋል፡፡ ክርስትናው መፍትሔ መሆኑ ቀርቶ ችግር፣ መልስ መሆኑ ቀርቶ ጥያቄ እየሆነ መጥቷል፡፡ ለዚህ ብቸኛው ምክንያት ደግሞ መልከኛ እንጂ እውነተኛ የእግዚአብሔር ፍቅርና ሃይል ያለው ክርስትና መዳከሙ ነው፡፡ ምላስ ረዝሞ እጅ ከተሰበሰበ፣ የምናወራው እግዚአብሔር እንጂ የምንኖረው እግዚአብሔር ከሌለ፣ የምናቅደው እንጂ የምንተገብረው መልካም ካነሰ መልከኞች እኛ ነን፡፡ በእውነትና በመንፈስ ስለማምለክ ተረድተን እንደ ፈቃዳችን ካመለክን፣ በመንፈስ ጀምረን በሥጋ ከጨረስን፣ ከእግዚአብሔር የልቡ ምክር አፈንግጠን ለዚህ ዓለም ከንቱ መለፍለፍና በብልሃት ለተፈጠረ ተረት ከተገዛን በእርግጥም መልከኞቹ እኛ ነን፡፡ ተራቁተን እንደለበስን፣ ደህይተን እንደበለፀግን፣ ታውረን እንደተኳልን፣ አንሶን እንደተረፈን ከተሰማን ተወዳጆች ሆይ መልከኞች እንጂ ኃይለኞች አይደለንም፡፡ “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ እራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ” (ያዕ. 1÷23) ተብሎ እንደተፃፈቤተ ፍቅር

  ReplyDelete

 7. ሸምጋዮችን ለመሸምገል (አስታራቂ የሆኑ አባቶችን ለማስታረቅ) ራሱን የቻለ ሽምግልና ይጠይቃል፡፡ የሲኖዶሱን መከፋፈል እንጀራቸው ያደረጉና አገልግሎታቸውን ከጥቅም ጋር ያዛመዱ፣ ሀገር ቤት ሲመጡ የዚህ፣ ባህር ማዶ ሲሄዱ የዚያ… ብቻ ደህና ለተከፈለበት ሰልፍ አሳማሪዎች፤ ሲላቸው ደግሞ በተመቻቸው ሚዲያ እየቀረቡ ራሳቸውን ለማሳወቅ የሚሮጡ፣ አንድ ጥግ ይዘው በቆሙበት ዐውደ ምሕረት ሞቅታ በተሰማቸው ቁጥር ሌላኛውን እየነቆሩ ልዩነቱ እንዲሰፋ ሚና የሚጫወቱ ሰዎች ዛሬ አስታራቂ ሆነው ማዕከላዊ (ገለልተኛ) ነን ቢሉ የማይታመንና የሚያሳፍር ነው፡፡

  የሦስት ሺህ ዓመት ታሪክ ያላትን ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለመፍታት የተሰበሰቡ ሽማግሌዎች ቢያንስ ንጹሓን ባይሆኑ እንኳን አዳፋ መሆን የለባቸውም፡፡ እንደሚታወቀው ዛሬ ራሳቸውን ሽማግሌ አድርገው የቀረቡት አደራዳሪዎች ትናንት የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ አስተማራቸውና፤ ሰርተፍኬት ሰጣቸው፤ ዛሬ ባሉበት ሀገር ስደተኛው ቀጠራቸው፤ ዐውደ ምሕረት ላይ ሲወጡ የሀገር ቤቱን እየኮነኑ ወንጌልን የሥጋ ጥቅማቸው ማጋበሻ አደረጉት፡፡ ምዕመናኑ አንድ፤ ቤተ ክርስቲያንዋም አንዲት ሆና ሳለ፤ ያገለግሉት የነበረው ትውልድ እንኳ ሳያልፍ ዛሬ ደግሞ ዓይናቸውን በጨው ታጥበው አስታራቂ ነን ብለው ተነሱ፡፡ ታዲያ እነዚህ አደራዳሪ ናቸው ወይስ ተደራዳሪ?


  በስነምግባራቸውና በሃይማኖታዊ አቋማቸው የተመሰከረላቸው መልካም አባቶች በመካከላቸው መኖራቸው እርግጥ ነው፡፡ ሆኖም ቅን አሳቢዎቹ የተሰለፉት ከቅጥረኞች ጎን ስለሆነ ራሳቸውን ከተኵላዎቹ መለየት አለባቸው፤ ባጭሩ እንክርዳዱ ከስንዴው ይለይ፡፡ ቀድሞውንም ሕዝቡ ሳያውቃቸው ቀርቶ ሳይሆን ትኩረቱ ዕርቀ ሰላሙ ላይ ስለሆነ እስከ መከር ይቆይ ብሎ ነው፡፡ አሁን መከሩ ደርሷል፤ ስለዚህ እርቁን እንዳያጨናግፉ ይታጨዱ፡፡ ውስጥ ያሉት መልካሞቹ የቀበሮ ባህታውያንን ያስወግዱና ለአንድ ወገን ያላደላ ሚዛናዊ ጉዞ ያድርጉ፤
  አጭር መልዕክት ለሀገር ቤቶቹም ለስደተኞቹም…

  ለሀገር ቤት አባቶች

  · በቤተ ክርስቲያኒቱ በጀት ከአዲስ አበባ ወደ ሀገረ አሜሪካ ልዑካንን በመመደብ ያለመሰልቸት ለዕርቅ መመላለሳችሁ ለአንድነቱ ያላችሁን ሙሉ ፈቃደኝነትና ጉጉት ያሳያል፡፡ የለፋችሁበት እንዲሳካ ከዚህ በታች ያሉት ነገሮች ተግባራዊ ቢሆኑ መልካም ነው፡፡
  1. የፓትርያርክ ምርጫውን ከእርቁ ባታስቀድሙ፤
  2. ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት በየገዳማቱ ለሚገኙ አበውና፤ ለሕዝበ ክርስቲያኑ የተወሰነ የጾም አዋጅ ብታውጁ፤
  3. ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን፤ ማኅበረ ካህናትን፤ ሰባክያነ ወንጌል አገልጋዮችንና ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን ምሁራንን በየደረጃ በማሰባሰብ በጉዳዩ ዙሪያ ብታወያዩ የተሻለ ይሆናል፡፡

  ባህር ማዶ ላላችሁት
  · የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ለዕርቅ ጥረት ማድረግ የጀመረው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሉስ እረፍት በፊት መሆኑ እሙን ነው፡፡ እርሳቸው በሕይወት እያሉ እርቁ ቢሳካ ኖሮ 20 ዓመታት የቆዩበትን መንበር ይልቀቁልን እንደማትሉ ይታመናል፡፡ መቼም አንተ ተዋርደህ እኔ ከብሬ እንታረቅ ብሎ ድርድር የሚጀምር በታሪክ ውስጥ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ስለዚህ የተጀመረው ዕርቀ ሰላም በመልካም ሁኔታ እንዲፈጸም፡-
  1. የቅዱስነታቸውን የአቡነ መርቆርዮስን ወደ መንበራቸው መመለስን የዕርቅ ድርድር ውስጥ ባታስገቡ፡፡ የምትታረቁት ለሹመት አይደለምና፡፡ የሀገር ቤቱ ሲኖዶስም በተደጋጋሚ አሜሪካ ድረስ በመመላለስ ለዕርቀ ሰላሙ እና ለአንድነቱ ያለውን ፈቃደኝነት ሲያሳይ የቅዱስነታቸው አቡነ መርቆርዮስን አባትነት አምኖ መሆኑን መዘንጋት የለባችሁም፡፡ ዕርቁና ሹመቱ ተለያይተው ቢታዩ መልካም ነው፡፡ ቅዱስነታቸው አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ የሚጠላ የለም፤ ለዚህ ግን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተፈጠረ ቅሬታ ካለ ቅድሚያ እሱን መፍታት ይኖርባችኋል፡፡ ያ ደግሞ ራሱን የቻለ ጊዜ ይፈልጋልና ይህንን በመሳሰሉት ምክንያት የሥልጣንን ጉዳይ ሳይሆን በቅድሚያ እናንተ ብትስማሙና የሹመቱን ጉዳይ ለመንፈስ ቅዱስ ብትሰጡ መልካም ነው፡፡
  2. የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ከላይ እንደተጠቀሰው አሜሪካን ድረስ ልዑካን መድቦ ለበርካታ ጊዜያት ሲመላለስ ገንዘብ፣ ጊዜና የሕይወት ዋጋ መክፈሉ የታወቀ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ለሰላሙ ጉዳይ ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስተው አዲስ አበባ ሲደርሱ በአየር ግጭት (መዛባት) ምክንያት ወዲያውኑ ሕይወታቸውን ያጡት ታላቁ ሊቅ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የማይረሱ አባት ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህንን በማሰብ በተለሳለሰ ሁኔታ የልባችሁን በር ለዕርቁ ብትከፍቱና ሁኔታዎች በፍጥነት እንዲስተካከሉ ብትተባበሩ መልካም ነው፡፡ ደግሞስ ሁሌ ከዚህ ብቻ መኬዱ ለምንድን ነው? ለምን እናንተስ ኢትዮጵያ በመምጣት ለዕርቁ ያላችሁን ፍላጎት አታሳዩም? ምን አልባት ከመንግሥት ጋር ያለውን መቃቃር እንደ ምክንያት ትጠቅሱት ይሆናል፡፡ መቼም ሁላችሁም ከመንግስት ጋር እንዳልተቃረናችሁ ግልጽ ነው፡፡ እጃቸውን ፖለቲካ ውስጥ ያላስገቡ አዳዲስ ብፁዓን ኤጲስ ቆጶሳት እንዳሉ ይታወቃል፤ ነገር ግን እስካሁን ከእናንተ ወደዚህ የመጣ ልዑክ የለም፡፡ ከዚህ አንጻር ለዕርቁ ከፍተኛ ፍላጎት የሚታይበት የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ነው ቢባል ማጋነንም ማድላትም አይሆንም፤ ምክንያቱም ገንዘብ፣ ጊዜና ሕይወት ከፍሏልና፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከእናንተ ከባህር ማዶዎቹ አባቶች የአባትነት መዓዛ ይፈልጋል፡፡ እንደ ሀገር ቤቶቹ እናንተም የዕርቁ ጉዳይ ዋጋ የሚያስከፍል ከሆነ ዋጋ ክፈሉ፡፡ ሀገራቸው መግባት የሚችሉ ልዑካን ከዚያም ይምጡ፡፡
  3. በተደጋጋሚ እንደሚጠየቀው የቅዱስነታቸው የአቡነ መርቆርዮስ ሐሳብ ምን እንደሆነ ከአንደበታቸው ቢሰማ የተሻለ ነው፡፡ በዙሪያቸው ያሉት ሰዎች እሳቸውን ደብቀው የሚደራደሩባቸው ጉዳይ ግልጽ አይደለም፡፡ እናንተም በሩን ዘግታችሁ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ጋር ለዕርቁ የመጡ አባቶችን አለማገናኘት ራሱ ሌላ ነገር ነው፡፡ ፡መ/ር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ/http://yetbet.blogspot.com/2013/01/blog-post_3.html#more

  ReplyDelete
 8. ዛሬ በአገራችን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሱሰኝነት፣ ሴሰኝነት፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ ግበረሰዶማዊነት፣ ሞራለ ቢስነት፣ ግለኝነት፣ ጭካኔ እየተስፋፋ ባለበት ሁኔታ እንዴት ነው ቤተ ክርስትያንን ወደ ቀደመ ለልናዋ ማምጣት የሚቻለው መባል ሲገባ ምንድነው ለመታረቅ ይህን ያህል ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት?ይሄ በአስከፊ ሁኔታ እየተስፋፋ ያለው ትውልድ ሞት ሊታያቸው ያልቻለው?ዛሬ በአገራችን ብዙ ሺሕ ካህናት ሰባክያን ቤትክርስትያን @ጠባቂ@ ማህበር አሉን እያሉ ማኅበራዊ ሴሰኝነት፣ ግብረሰዶም፣ ጭካኔና ክህደት፣ ሙስናና ሌብነት ተስፋፍቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው ሲኖዶስ እና ጳጳሳቶቻችንን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ቢወጡ ነውን?

  ReplyDelete
 9. “መንገድ ስትሄድ፣ ድንጋይ (እንቅፋት) ቢመታህ፤ ምንም አይደል። ድንጋይነቱ አይለወጥም፣ አንተም ሰውነትህ አይለወጥም። ያው ድንጋይ ሁለተኛ፣ ሦስተኛ ቢመታህ ግን፣ ድንጋዩ መታሰቢያነቱ ” - አንድ ስሕተት ደግመው ደግመው ለሚሠሩ በሙሉ፤ ያውም ታሪካዊ ስሕተት። ብዬ መፈላሰም አማረኝ!!!!!

  ReplyDelete
 10. ይህ ምሳሌ በተለምዶ << የጠፋው ልጅ ምሳሌ>> ተብሎ ነው የሚጠራው:: በነገራችን ላይ ስያሜው የመተርጉማን ነው እንጂ የወንጌል ወይም የጌታ አይደለም:: ጌታ ምሳሌውን የሚጀምረው አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት ነው የሚለው::

  ይህን ታሪክ ላይ ላዩን ስንመለከት የሁለቱ ልጆች ታሪክ ይምሰል እንጂ የታሪኩ ዋና እምብርት አባትየው ነው:: አባትየው ከ12 ጊዜ በላይ ሲጠቀስ በልጆቹ በኩል ደግሞ በተዘዋዋሪ በብዛት ተጠቅሶአል:: ሉቃስ በዚህ ታሪክ ላይ ከምንም በላይ ሊያጎላን የሚፈልገው ይህ አባት ለልጆቹ ምን ያህል ፍቅር እንዳለው እና ፍቅሩንም ለሁለቱ ልጆች እንደገለጠ ይነግረናል:: ታሪኩን በጥንቃቄ ከተከታተልነው ሁለቱ ልጆች እነማን እንደሆኑ እንመለከታለን:: መጀመሪያ የታናሹን ልጅ ታሪክ እንመልከት


  12 ከእነርሱም ታናሹ አባቱን። አባቴ ሆይ፥ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው።

  ይህን የመጀመሪያውን ክፍል በዚያ ዘመን የነበሩ ሰዎች ሲሰሙ ምን ያህል ድንጋጤ እንደሚሰማቸው አልነግራችሁም:: ምክንያቱም የታናሹ ጥያቄ ሁለት ታላላቅ ስህተቶችን የያዘ ነው:: በዚያን ዘመንም ሆነ አሁንም ውርስ ከሞት በኋላ ነው:: ስለሆነም አባት ገና በህይወት እያለ የሚደርሰኝን ስጠኝ ማለት ለአባት ታላቅ ስድብ ነው:: ይህ ማለት አባቴ ሆይ እስከ ዛሬ ብዙ ጠበቅሁኝ አንተ አትሞትም:: አሁን ግን አንተን ማየት ስለሰለቸኝ አንተን አልፈልግህም ገንዘብህን ግን ስጠኝ ማለት ነው:: አስተውሉ <> ነው ያለው: እንጂ ገንዘቤን ስጠኝ አላለም:: ገንዘቡ የአባቱ ነው:: በሁለተኛ ደረጃ ይህ ታናሹ ልጅ የኖረን ይትበኻል ያፈረሰ ነው:: በዚያን ዘመን ይትበሃል የመጀመሪያው ወራሽ በኩር ልጁ ነው:: ታላቁ ልጅ ነው:: ሆኖም ታላቁ ልጅ እያለ ነው ታናሹ የጠየቀው:: ሌላ አባት ቢሆን ኖሮ በዚህ ልጁ ድርጊት አዝኖ እና ተናዶ ከልጅነት ይፍቀው ነበር ይህ አባት ግን እንዲ አላደረገም:: ምንም እንኳ አባቱን በጸያፍ ጥያቄ ቢያስነውርም ምንም እንኳ የታላቅ ወንድሙን ክብር ቢጋፋም አባትየው ግን አባቱ የልጁን ጥያቄ ሲፈጽምለት እናያለን::

  13 ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፥ ከዚያም እያባከነ ገዘቡን በተነ።

  የአባቱ ቸርነት ግን ይህን ታናሽ ልጅ ወደ ማስተዋል አላመጣውም ነበር:: እንዲያውም በአባቱ ለጋስነት መጠን ኃጢአትን ማድረግን ፈለግ:: የአባቱን ጸጋ አባከነ በተነ:: ወደሩቅ አገር የሄደው ምናልባትም የአባቱን ተግሳጽ ላለመስማት ይሆናል:: ወደ ሩቅ አገር የሄደው አባቱ እንዳይመለከተው ይሆናል:: ለማንኛውም የሄደበት አገር ግን የፍሬ ሳይሆን የብክነት የማከማቸት ሳይሆን የመበተን አገር ነበር::

  እነዚህ ጥቅሶች ላይ ቆም እንድርግና እግዚአብሔር ለልጆቹ የሚሰጠውን ጸጋ እናስተውል:: በማቴዎስ 5:45 ላይ የሚገርም ነገር ይነግረናል:: << እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።>> ማለት እግዚአብሔር ጸጋውን ሲሰጥ ጸሎትን ሲመልስ ለሁሉም ልጆቹ ነው:: እደግመዋለሁ ለሁሉም ልጆቹ ነው:: ጥያቄው ግን በተሰጠን ጤንነት በተሰጠን የጸሎት መልስ በተሰጠን ዕድሜ ምን ሰራንበት:: ይህ ልጅ ሊሰጠው የማይገባውን ጸጋ ለእርሱ የማይገባውን ጸጋ እንደተሰጠው ተመልከቱ:: ነገር ግን የተባለው << ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ::>>

  የእግዚአብሔርን ጸጋ መቀበል የጸሎትን መልስ ማግኘት: በእግዚአብሔር ክንድ መፈወስ አንድ ነገር ነው:: ታላቁ ነገር ግን ከባለጸጋው አምላክ ይህን ቸርነት ይህን ፍቅር ይህን ሰውን መውደድ ከተቀበልን በኋላ ምን አደረግነው ነው:: በእግዚአብሔር ቤት በቆየሁባቸው አጭር እድሜዬ ከእግዚአብሔር ታላላቅ ጸጋዎችን የተቀበሉ ሰዎችን አይቼአለሁ:: ሲቀድሱ ሰውን ወደሰማየ ሰማያት የሚወስዱ ማኅሌቱ ውስጥ ሲገቡ አንዱ የሃያና የሰላሳ ሰው ኃይልና ውበት ያላቸው:: ሲሰብኩ አፍ የሚያስከፍቱ:: ከምእመናንም አይቼአለሁ:: የትምህርት የእውቀት ጸጋ የሰጣቸው:: ነገር ግን በዚያው መጠን ደግሞ እንዚያ ሰዎች እንዴት እንደወደቁ አይቻለሁ:: በእግዚአብሔር ቤት ጸጋውን መቀበል ብቻ ሳይሆን በዚያ ጸጋ መኖር ታላቅ ነገር ነው::

  14 ሁሉንም ከከሰረ በኋላ በዚያች አገር ጽኑ ራብ ሆነ፥ እርሱም ይጨነቅ ጀመር።

  ይህ ልጅ መቀበሉን እንጂ መኖሩን አላወቀበትም:: ስለሆነም ከሰረ:: መቀበልን እንጂ መኖርን ያላወቁ ለማግኘት ሩቅ አትሂዱ ሎተሪ እጣ የደረሳቸው ሰዎችን ጠይቁ:: የሚበዙቱ መቀበልን ብቻ ያወቁ ናቸው::

  ይህ ረሃብ መንፈሳው ረሃብን የሚያመልክት ነው:: የእግዚአብሔርን ቃል ረሃብ የሚያመለክት ነው:: << እነሆ፥ በምድር ላይ ራብን የምሰድድበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት አይደለም።>> አሞጽ 8:11::

  15 ሄዶም ከዚያች አገር ሰዎች ከአንዱ ጋር ተዳበለ፥ እርሱም እሪያ ሊያሰማራ ወደ ሜዳ ሰደደው።16 እሪያዎችም ከሚበሉት አሰር ሊጠግብ ይመኝ ነበር፥ የሚሰጠውም አልነበረም።

  ይህ ታሪክ እየተነገረ ያለው ለእስራኤላውያን ነው::በመሆኑም ይህን የልጁን ድርጊት ሲሰሙ ሳያስደነግጣቸው አይቀርም:: ምክንያቱም ልጁ ምን ያህል ችግር ውስጥ እንደገባ የሚገልጥ ነው:: በእነርሱ ዘንድ እሪያን መንካት እንኳ የሚያረክስ ነው:: በመሆኑም መብላት ብቻ ሳይሆን ማርባትም ክልክል ነው:: ከአባቱ ጸጋ ከአባቱ ቤት ስለወደቀ ይህ ልጅ የእሪያዎች እረኛ ሆነ:: ይህ ብቻ አይደለም አንዴ ከእግዚአብሔር ጸጋና ከእግዚአብሔር ፍቅር ሰው ሲወድቅ የሚሆነውን ተመልከቱ:: ጴጥሮስ ክሪሶሎጎስ እንዳለው << ይህ በአባቱ ላይ መታመንን እምቢ ያለና ራሱን ለባእድ ያስገዛ>> ነው:: በመሆኑም << ባለጸጋ መጋቢ ከሆነው አባቱ ሮጦ ከጽኑ ፈራጅ ዘንድ አደረ:: >> የኃጢአት አስከፊነት ሰውን ፍጹም ማንነቱን እንዲረሳ ማድረጉ ነው:: ያ ክብርና የባለቤትነት ክብር ፍጹም ስለተረሳ አሁን እሪያዎቹ ከሚበሉት መብላት እንዲመኝ አደረገው::

  እሪያዎች ቅጠላ ቅጠል ብቻ ሳይሆን ያገኙትን ሁሉ የሚበሉ ናቸው:: ምግብ ፍለጋ መሬቱን ሁሉ ስለሚያነፈንፉ አካባቢያቸውን ሁሉ ያጨቀዩታል:: ያን የተጨማለቀ አሰር መመኘቱ ሳያንስ መጽሐፍ የሚለን እርሱን እንኳ << የሚሰጠው አልነበረም:: >> ....kesis.org

  ReplyDelete
 11. 17 ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።

  ቀደም ብለን እንዳልነው በኃጢአት ዓለም ውስጥ ያለ ሰው የሚለየው ከሰማያዊ አባቱ ብቻ ሳይሆን ከእውነተኛው ማንነቱም ነው:: በመሆኑም ጌታ በምሳሌው የጠፋው ልጅ የአባቱን ቤት ያሰበበትን ወቅት ወደልቡ የተመለሰበት ወቅት አደረገው:: በምን ምክንያት ወደ ልቡ ተመለሰ? እንዴት ተመለሰ ብለን ስንጠይቅ ፍሎክሴኒዩስ ወይም ፊልክስዩስ የተባለው የቤተ ክርስቲያን አባት እንደተናገረው ከሆነ ምንም እንኳ በኃጢአት አለም ቢሆንም እግዚአብሔር አባትነቱን አልነፈገውም:: ምንም እንኳ ከእርሱ ፊት ሸሽቶ ወደ ሩቅ አገር ቢሄድም አባቱ አልረሳውም:: ወደ እውነተኛ ማንነታችን ስንመለስ የመጀመሪያው የምንገነዘበው ነገር ቢኖር የሕይወታችንን ዓላማ ነው:: እስከዛሬ ይህ ልጅ የጠፋ ልጅ ነው:: ይህ ልጅ አባካኝ ልጅ ነው:: ይህ ልጅ በመጨረሻ የአሳማ እረኛ ነው:: አሁን ግን ወደ ልቡ ሲመለስ << አባቴ>> አለ:: ማለት የባለጸጋው የርህሩሁ አባት ልጅ እንደሆነ አስተዋለ::

  18 ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና። አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥19 ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።20 ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ።“አባቱ ገና ሩቅ ሳለ አየውና አዘነለት፤ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው፡፡ አገልጋዮቹንም ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አልብሱት፤ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡት፡፡ የሰባውን ፍሪዳ አምጥታችሁ እረዱት እንብላም ደስ ይበለን፡፡ ልጄ ሞቶ ነበር ሕያው ሆኗልና፡፡ ጠፍቶ ነበር ተግኝቷልና፡፡” አላቸው፡፡ ሉቃ. 15፡20-24፡፡

  አባቱ የልጁን መመለስ የሚናፍቅ እንደነበረ ከቃሉ ጀርባ ያለው ፍቅሩ ይነግረናል፡፡ ወላጆች ጊዜያዊ ቁጣቸው እስኪያልፍ የልጆቻቸውን ፊት ማየት ላይፈልጉ ቢችሉም እንኳን ቆይተው ግን መጨከን አይችሉም፡፡ የገረፉትን ልጃቸውን እንባ የሚያብሱት ራሳቸው ናቸው፡፡ ልጃቸው መጽናናት አልችል ሲል “እንዲህ አደርግልሃለሁ” በማለት ሀዘኑን ያስረሳሉ፡፡ የእግዚአብሔር ጽኑ ፍቅሩንና አባታዊ ርህራሄውን የሚከተል ፍለጋውንም በወላጆቻችን ፍቅር እናያለን፡፡

  እግዚአብሔር ወደ እርሱ ለመመለስ መንገድ ለሚጀምሩት ቅርብ ነው፡፡ መመለሳችንን በናፍቆት ይጠብቃል፡፡ በአንድ እርምጃ ጉዞ ወደ እርሱ ስንጀምር ሁለት እርምጃ ወደ እኛ መጥቶ ይቀበለናል፡፡ መጎሳቆላችን እና በሙላት ወጥተን በባዶነት መመለሳችን ያሳዝነዋል፡፡ እጆቹን ዘርግቶ ያቅፈናል፡፡ በመዳፉ በረከት ጉስቁልናችንን ያስወግዳል፡፡ በእቅፉ ሙቀት መከራን ያስረሳናል፡፡

  በምድር ሥርዓት ያጠፋን መቅጣት እንጂ መሸለም አልተለመደም፤ አባታችን እግዚአብሔር ግን ይህን አድርጓል፡፡ አዳም በድሎ ሩቅ ቆሞ ሳለ አይቶ አዘነለት፡፡ በገነት ጫካዎች ተገልጦ ፈለገው፤ በሰው ቋንቋ ጠራው፤ የፍቅር ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ የአዳም የቅጠል ልብሱ ስላላማረበት ራቁቱን የሚሸፍን የማያረጅ ልብስ ሸለመው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ፡፡ 1ዮሐ. 3፡1፡፡

  ዓለሙን እንዲሁ የወደደው አብ አንድያ ልጁን አሳልፎ ሰጠ፡፡ ዮሐ. 3፡16፡፡ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ልጁ ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ፡፡ ኃያሉ ወልድ(ክርስቶስ) ፍቅር ከዙፋኑ ስቦት ለመስቀል ሞት ታዘዘ፡፡ አዳምን እስከ መቃብር ወርዶ ፈለገው፡፡ የተራቆተውን የሰው ልጅ ሀፍረት በጸጋው ሸፈነው፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ራቁታችንን የሸፈነ ያልተሠራ የጽድቅ ልብሳችን፤ ከሰማይ የወረደ የማያስርብ ሕያው እንጀራችን፤ ለዓለም የሚበቃ እና የሚያጠግብ ፍሪዳችን፤ በሞት ጀርባ ላይ የሚያስኬድ በሞገድ የማይሰበር መርከባችን፤ የማያረጅ ጌጣችንና የማያልቅ ሀብታችን ነው፡፡

  በአንድያ ልጁ ጨክኖ ለዓለም የራራ፤ በልጁም ትውልድን የተቀበለ፤ ጠፍተን የነበርነውን በልጁ ሞት ያገኘ፤ መገኘታችንንም ያወጀ፤ በልጁ ሕያውነት ሕያዋን ያደረገን፤ ሕያውነታችንንም በቃሉ የነገረን፤ በእኛ መመለስ ደስታ ያደረገ እግዚአብሔር አብ ይመስገን፡፡ 1ዮሐ. 4፡14፡፡
  ለዓለም ራርቶ በአዳም ላይ የወደቀውን ፍርድ በራሱ ላይ አድርጎ፤ ከገነት ጫካዎች እስከ ጎልጎታ የፈለገን፤ አንገቱን ደፍቶ ቀና ያደረገን፤ ወድቆ ያነሳን፤ ተርቦ ያጠገበን፤ ተጠምቶ ያጠጣን፤ ተራቁቶ ያለበሰን፤ ቆስሎ የፈወሰን፤ በሞቱ ሞታችንን የሻረ፤ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመስገን .......... http://betelhemm.blogspot.com/,kesis.org

  ReplyDelete
 12. ወንድሞች ሆይ ስላለፈው ጊዜ ስንነጋገር ብንውል ለዛሬ ችግራችን መፍትሔ አይሆነንም።ብዙዎች መንግስት በቤተ ክርስቲያን ላይ ስለሚያደርገው ተፅእኖ ይናገራሉ። እነዚህ ሰዎች አላማቸው አሁን በቤተ ክርስቲያኑ ካለው ሁኔታ የራሳቸው ትርፍ ማጋበስ እንጂ ቤ/ክ መርዳት አይደለም። እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ማሰብ ያለብን የዘለቄታውን ነው። ወደፊት የሚጠብቁን ፈተናዎች ማሸነፍ እምንችለው ጠንካራ አባት ሲኖረን ብቻ ነው። ጠንካራ አባት ካለን እኮ መንግስትም ተጽእኖ ለማሳረፍ አይሞክርም። ለምን ከአባታችን ከአቡነ ቴዎፍሎስ አንማርም። ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በሃሰተኛው የደርግ “ተሃድሶ ኮሚሽን” ተወንጅለው ለስራት ከመዳረጋቸው በፊት አንዳንድ ወዳጆቻቸው እንዲሸሹ መክረዋቸው ነበር። ቅዱስነታቸው ግን የሚደርስባቸውን ማንኛውንም መከራ ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ቆርጠው ስለነበረ ምክሩን አልተቀበሉትም፤

  እኔ አሉ ቅዱስነታቸው “ እኔ ከዚህ ደረጃ የደረስሁት ከትቢያ ተነስቼ ነው። በሰላሙ ጊዜ ስሾም ስሸለም አባ! አባታችን! እየተባልሁ ስከበር ኑሬአለሁ።ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ከንጉሰ ነገስቱ ጀምሮ ያሉ ታላላቅ ሰዎች እየታሰሩ ያለ ፍትህ እየተገደሉ ናቸው እኔም በሃገሬና በቤት ክርስቲያን ስም የሚደርስብኝን ማንኛውንም መከራ መቀበል እንጂ መሸሽ ተግባሬ አይደለም። አባቶቼ ሃዋርያትና ሰማእታት ሰለ ቀናች ሃይማኖታቸው ሲሉ በሰይፍ ተቆርጠው፤ በገመድ ታንቀውና በእሳት ተቃጥለው በሰማእትነት ተሰውተዋል፤ እኔም እንደነሱ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያን ክብር ስል እስከ ሞትም ድረስ ቢሆን መከራና ስቃይ ከመቀበል በቀር ወደ ኋላ የምልበት ምክንያት የለም።

  ቀደም ሲል በነአቡነ ጴጥሮስ ላይ የደረሰውን የሰማእትነት ሞት እኔም የነሱን ፅዋ ቆርጨ እንድቀበል እንጂ እንድሸሽ አይገፋፋኝም፤ ለእኔ ህይወት ሲባል በብዙ ድካም የተገኘውን የቤተ ክርስቲያን ክብር አላዋርድም፤ ባንገቴ ላይ ስለት (ሰይፍ) እያንዣበበ እንደሆነ ይታወቀኛል፤ ቢሆንም እዚሁ ሁኜ የሚመጣብኝን መከራ ለመቀበል ዝግጁ ስለሆንኩ በምንም ተአምር አልሸሽም” ነበር ያሉት። እኔ የአቡነ መርቆሬዎስ መመለስን አልቃወምም። አባት ናቸው። ችግሩ አሁን ላለው ፈተና ብቁ ናቸው ወይ ነው ጥያቄው። መሸሽ አልነበራቸውም፤ውጭ ወጥተው ሲኖዶስ ማቋቋም አልነበራቸውም።
  ReplyDelete