Sunday, January 6, 2013

እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ

እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።” ሉቃስ 2፡10-11
የጌታ ልደት በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዓሉን የምናከብርበት መንገድና በዓሉን አስመልክቶ የምናስበው ጒዳይ የተለያየ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን በዓሉ የክርስቶስ ልደት መሆኑን ረስተን በዚህ ወቅት የምንመሰክረው ስለ ተወለደልን መድህን ሳይሆን፣ ስለ ሳንታክላውስ፣ ስለ ገና ጨዋታ፣ አለፍ ሲልም በሌለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ስለ ሰብአ ሰገል ኢትዮጵያዊነት ይሆናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን የጌታ ልደት ለእኛ ለክርስቲያኖች የሚያስተላልፈውን መልእክት የሚያደበዝዙ ጣልቃ ገብ ጉዳዮች ናቸው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የጌታ ልደት ጥቅሙ ለእኛ መሆኑን ይናገራል፡፡ “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።” በዚህ ጥቅስ ውስጥ ልናስተውለው የሚገባው በተለይ “መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል” የሚለውን ኃይለ ቃል ሲሆን፣ ከጥቅሱ ሶስት ቁም ነገሮችን ማብራራት አለብን፡፡
1. የተወለደው መድኀኒት ነው፡፡
2. የተወለደው ስለ እኛ ነው “ተወልዶላችኋል” ነው የተባለው፡፡
3.  የእርሱ መወለድ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ የምሥራች ነው፡፡

እርስዎ የጌታን ልደት ሲያከብሩ እነዚህን ነገሮች ልብ ብለዋልን? የተወለደው መድኃኒት ነው፡፡ መድኃኒትነቱ ደግሞ ለእርስዎ ነው፡፡ እርስዎን ከኃጢአት ለማዳን ነው የተወለደው፡፡ ልደቱ የመድኃኒትዎን ሰው ሆኖ መምጣት እውን ያደረገ የመዳንዎ ዋዜማ ነው፡፡ ይህ የተወለደው መድኃኒትዎ የእርስዎን ኃጢአትና በደል ተሸክሞ በመስቀል ላይ በእርስዎ ምትክ በመሞት ቤዛዎት ሆኗል፡፡ ለእርስዎ መድኃኒት ሆኗል፡፡ ስለዚህ ልደቱን ሲያስቡ ሰው ሆኖ መወለዱን ብቻ ሳይሆን የተወለደው መድኃኒትዎት ሆኖ ለመሞት እንደ ሆነና ሞቶም እንዳዳነዎት ያስቡ፡፡

የክርስቶስን ልደት ሲያስቡ ልደቱ የእርሱ ቢሆንም እንደ ማንኛውም ሰው ልደት የእርሱ ልደት እንደሆነ ብቻ ማሰብ የለብዎትም፡፡ እርሱ የተወለደው ለእርስዎ ነው፡፡ “ተወልዶላችኋልና” የተባለው ለእኛ ለሁላችን ነው፡፡ “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና” ሲልም ኢሳይያስ የሚናገረውም ጌታ የተወለደው ለእኛ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ከእኛ መካከልም እርስዎ አንዱ ነዎት፡፡ ስለዚህ ልደቱ ለእርስዎ እንደ ሆነ አስበው በጌታ ደስ ሊልዎ ይገባል፡፡ ጌታ የተወለደልዎት ሊያድንዎት ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ጥያቄው ሊያድንዎት በመጣውና ዛሬ የልደቱን መታሰቢያ በሚያከብሩለት ጌታ ድነዋል ወይ? እርሱ ሊያድንዎት መወለድ ብቻ ሳይሆን ሞቶ ተነሥቷል፡፡ እርሱ ስለተወለደ፣ ስለሞተና ስለተነሳ ግን ድነዋል ማለት አይደለም፡፡ ለመዳን በተወለደው መድህን ሞትና ትንሳኤ ማመንና ለእርስዎ የተከፈለ መድኃኒት መሆኑን መቀበልና የራስዎ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡ እርሱ ዓለምን ለማዳን እንደሞተና እንደተነሳ ተጽፏል፡፡ የሚድነው ግን ያመነበት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በተወለደው መድኃኒት አሁኑን ይመኑና ከሚመጣው ቁጣ ያምልጡ፡፡

የጌታ ልደት ለተወሰነ የሰው ዘር ብቻ ሳይሆን ለሰው ዘር ሁሉ የሚሆን የምሥራች ነው፡፡ ለምን “ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች” ተባለ? በራሱ ወይም በሌላ እድንበታለሁ ብሎ በሚያስበው መንገድ መዳን ለማይሆንለት ሰው፣ ፈጽሞ የሚያድነው ጌታ ሰው ሆኖ ስለተወለደ ነው፡፡ ከኃጢአት በሽታ የሚፈውሰው መድኃኒት ጌታችን ክርስቶስ ሰው ሆኖ መምጣቱ በእውነት ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች ነው፡፡ ይህ የምሥራች ለእናንተ መሆኑን ያልሰማችሁና ልደቱን በየዓመቱ “የጌታችን ልደት” እያላችሁ ስታከብሩ የነበራችሁም ጌታ የተወለደው ለእናንተ ነውና በዚህ ጌታ በማመን የዘላለም ሕይወት ባለቤት እንድትሆኑና በእርሱ በመኖር የእርሱን ፈቃድና ሐሳብ እንድታገለግሉ እንጋብዛችኋለን፡፡

መልካም በዓለ ልደት ይሁንልዎ!

12 comments:

 1. "አለፍ ሲልም በሌለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ስለ ሰብአ ሰገል ኢትዮጵያዊነት ይሆናል፡፡" አሁንስ ኦርቶዶክሳዊነታችሁን ብቻም ሳይሆን ኢትዮጵያዊነታችሁንም እንድንጠራጠው እየገፋችሁን ነው። እስቲ ሰብአ ሰገል ዛሬ ከሚታወቁት አገሮች ከትኛው እንደሆነ ንገሩን ? ከመካከላቸው ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያውያን ነበሩ ብንል የክርስቶስን ልደት እንደማስተባበል ይሆንብናል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ወይስ በኢትዮጵያ ማንነት ላይ አሉታዊ እምነት ያላቸውን የሻብያንና ወያኔን መንፈስ የምትጋሩ የሥጋና የመንፈስ ወገኖቻቸው ናችሁ ? እነሱ ናቸው በምዕራብ አገሮች በሚገኙት አብያተ መጻሕፍት ስለ ኢትዮጵያ ረጅም የታሪክ ባለቤትነት የሚመሰክሩትን መጻሕፍት እየቀደዱ የሚጥሉ። ያም ሆነ ይህ መልካም የልድተ ክርስቶስ በዓል ይህንላችሁ /ይሁንልን ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Kebede Bogale, be wise!

   Delete
  2. ወንድሜ ከበደ እኔ አንድ ነገር ብታስተውል መልካም ይመስለኛል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የማይገኝለትን ክፍል ለእኛ በሚመቸን መንገድ ጠቅሰን ኢትዮጵያዊ ማድረግ ለምን አስፈለገ? በእኔ እምነት መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን ብንናገር፣ እርሱ ዝም ካለ ደግሞ ዝም ብንል ከስሕተት እንድናለን፡፡ አንተ ከተሳሳትከው ልጥቀስ "እስቲ ሰብአ ሰገል ዛሬ ከሚታወቁት አገሮች ከትኛው እንደሆነ ንገሩን? ከመካከላቸው ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያውያን ነበሩ ብንል የክርስቶስን ልደት እንደማስተባበል ይሆንብናል ብላችሁ ታስባላችሁ? ወይስ በኢትዮጵያ ማንነት ላይ አሉታዊ እምነት ያላቸውን የሻብያንና ወያኔን መንፈስ የምትጋሩ የሥጋና የመንፈስ ወገኖቻቸው ናችሁ?" በእውነቱ እንዲህ ማለት ልምን እንዳስፈለገህ አልገባኝም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሰብአ ሰገል ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መምጣታቸውን እንጂ ከኢትዮጵያ ነው አይልም። ከአትዮጵያ አለመምጣታቸውን "ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።" የሚለው ማስረጃ ሊሆን ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ አትገኝምና፡፡ ስለዚህ አባ ሰላማ ድረገጽ ያልተጻፈውን አገራቸውን በመላምት ሊነግረን አይጠበቅበትም፡፡
   ሁለተኛ፣ ከመካከላቸው ኢትዮጵያውያን ነበሩ ብንል ልደቱን እንደማስተባበል ለምን ታስባላችሁ ያልከውም ስህተት ነው፡፡ በቅድሚያ ከሰብአ ሰገል መካከል ኢትዮጵያዊ ነበረ የሚያሰኝ ማስረጃ አላቀረብክም፤ ያለማስረጃ ከሚወራው ወሬ በቀር፡፡ ስለዚህ ምናለበት በሚል ሰብአ ሰገልን ኢትዮጵያዊ ማድረግ ትክክል አይሆንም፡፡ ማስረጃ የሌለውን ይህን ተረት በማጋለጣቸው ነገሩን ከሻዕቢያና ወያኔ ጋር ማገናኘት አንተን ግልብ ነው የሚያሰኝህ እንጂ ምንም ትርፍ የለውም፡፡ ሰብአ ሰገል ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ ኢትዮጵያዊ ብናደርጋቸው ታሪካችንን ተአማኒ ያደርገዋል ብለህ ታስባለህ? አይመስለኝም፡፡ እነርሱ ኢትዮጵያዊ አለመሆናቸው መገለጹም ከታሪካችን ላይ የሚቀንሰው ውሸቱን እንጂ እውነቱን አይሆንም፡፡ በእርግጥ ጉዳዩ የክርስቶስን ልደት አያስተባብልም አልክ እንጂ እንክት አድርጎ ያስተባብላል፡፡ እኔና አንተ እንኳ የተነጋገርነው ከዋናው ጉዳይ ጋር ማለትም ከተወለደልን ክርስቶስ ጋር ምንም ግንኙነት በሌለው ታሪክ ላይ ነው፡፡ አንተን የከነከነው የሰብአ ሰገል ጉዳይ እንጂ የተወለደልህ ክርስቶስ አይደለምና ይህም ታላቅ ኪሳራ ነው፡፡ ስለዚህ ከቤ ከተረት ሰፈር ወደ ወንጌል ሰፈር ብትወጣ ይሻላል፡፡ ማስረጃ ስለሌለው የሰብአሰገል ኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ከምትከራከር አንተን ሊያድን በተወለደው በክርስቶስ አዳኝነት እመንና ዳን፡፡

   Delete
  3. AnonymousJanuary 7, 2013 1:11 PM

   ስለዚህ ከቤ ከተረት ሰፈር ወደ ወንጌል ሰፈር ብትወጣ ይሻላል፡፡ ማስረጃ ስለሌለው የሰብአሰገል ኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ከምትከራከር አንተን ሊያድን በተወለደው በክርስቶስ አዳኝነት እመንና ዳን፡፡

   Thank you very much for your reply to Kebede (kelele)

   Delete
  4. bengerachn lay ethiopiawyan likawnt yesebasegeln ethiopiawinet aykebelum!!! ferenjoch nachew andu tkur sew ymslal! bemalet twldun kethiopiawyan gar yakoraghut..... ferenj slale bcha tkkl aydelem

   Delete
 2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 6, 2013 at 2:08 PM

  Melekame Ledete leholchen! I am passing my greetings to Abaselamwech. Betu!

  ReplyDelete
 3. ለዚህች ቀን ስላደረሰኝ እግዚአብሔርን በጣም አመሰግነዋለሁ !!
  “እንኳን አብሮ በሰላምና በጤና ለጌታ ልደት አደረሰን”

  እናንተ ሦስተኛ ዓመታችሁን ስትጀምሩ ፣ እኔ ደግሞ ሁለተኛ ዓመቴን ከናንተው መድረክ ጋር ቀጥያለሁ ፡፡ ያሰነበተኝም ፣ የምትጻጽፉት ሁሉ ፈተና ስለሆነና መልስ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን ሥራዬ ብዬ በአግባቡ እንድፈትሸው ስላደረገኝ ነው ፡፡ በእርግጥ መንገዳችሁን የማልሄድበት መሆኑን ባውቅም አልፎ አልፎ ከምታስነብቡትና ሌሎች ወገኖች ከሚሰጡት መልስ እጅግ ብዙ በመማር ፣ በእምነቴ ጽናትንና ጥንካሬን ፣ በቀለም ዕውቀትም ቢሆን መሻሻልን ጨምሮልኛልና አብረን ለመቆየት ምክንያቴ ሆነ ፡፡

  ብዙ ሊያስተምሩን የሚችሉ ወገኖች ፣ ምን የነካ እንጨት እንደሚሉት ፣ ትዕግስቱ ስለሌላቸው ፣ ጽሁፋችሁን ለማንበብ ፍላጐቱ የሌላቸው ይመስለኛል ፡፡ አብዛኛው አንባቢ ደግሞ ልንማማርበት የሚችል ጭብጥ ከማስቀመጥ ይልቅ ፣ ድፍን ያለ ተቃውሞና ጸያፍ ቃል አሰቀምጦ ይፈነጠራል ፡፡ ይህ ዓይነቱ ክርስቲያናዊ ያልሆነ አካሄድ ማንንም አያስተምርም ፤ የጠፉትን ወገኖችም አይመልስም ፤ እንዲያውም በክህደታቸው እንዲበረቱና ሌሎችም ተጨምረው እንዲደመሩ ያደርጋል ፡፡

  ከተጻፉት ቢያንስ ከአራት እጅ ሦስቱ ስለ ማኀበረ ቅዱሳን የሚያትቱ ናቸው ፡፡ ፖለቲከኛ ፣ ሲራራ ነጋዴ ፣ የሲአይኤ ወኪል ፣ ወግ አጥባቂ ወይም አክራሪ ፣ ዘረኛ …. የሚሉ ናቸው ፡፡ ሌሎች ደግሞ እነሱን ይደግፋሉ የተባሉ አባቶችን ሁሉ ይመለከታል ፡፡

  የብልጦቹ ጨዋታ ተረት ለሳቅ ለፈገግታ

  አንድ አባት ነበሩ ፡፡ ስጋዊ ስሜት አሸነፋቸውና የምታገለግላቸውን ኮረዳ ሊዳፈሩ አሰቡ ፤ ኋላም ለማግባት ጠየቋት ፡፡
  ኰረዳ ፡- እንዴት አባት ሆኖ ልጁን ሰው ያገባል ? ሃይማኖታችንም ደግሞ አይፈቅድም አለቻቸው
  አባት ፡- መጽሐፍ የሚለውን የማያውቁ ናቸው እንዲያ የሚሉ ፡፡ እንዲያውም እን አባ እንቶኔ ቤት እንሂድና ያስተምሩሻል አሏት ፡፡

  አመሻሹ ላይ እራት ከበሉ በኋላ ተያይዘው እነ አባ እንቶኔ ቤት ሄዱ ፡፡ አባ እንቶኔም መጽሐፍ ኤጲስ ቆጶስ የአንድ ሴት ባል ሊሆን ይገባዋል የሚለውን ፣ የጳውሎስን ትምህርት አነበቡላት ፡፡ ቀጥለውም ሥርዓቱ በቁርባን መፈጸም ስለሚገባው እኔው አቆርባችኋለሁ ብለው ከወደጓዳ የሚያቆርቡበትን ይዘው መጡ ፡፡
  ኰረዳ ፡- ምነው አባቴ በቤተ ክርስቲያን መሆን ሲገባው እንዴት በግለ ሰብ ቤት ይፈጸማል?
  አባ እንቶኔ ፡- ማንም ተራ እንትን ካጨማለቀው እኔ አባትሽ ያሰናዳሁት አይበልጥም?
  ኰረዳ ፡- በምንተፍረት ሌላ ማፍረሻ አቀረበች ፤ እራታችንን በልተን ነው እኮ የመጣነው አባቴ ፤ እራት ከተበላ በኋላ እንዴት ይደረጋል ?
  አባ እንቶኔ ፡- ጌታም እኮ ደቀ መዛሙርቱን ያቆረበው እራት ከበሉ በኋላ ነው ፡፡
  ኰረዳ ፡- እንዲያ ከሆነስ ብላ አፉዋን ከፍታ ተቀበለች ፡፡

  ማስታወሻ ፡- የጽሁፉ ጽንሰ ሃሳብ በናንተው ብሎግ የቀረበ ነው ፡፡ ስለሚያሰቀኝ አጠናሁት ፡፡

  ሌሎች በብዛት የተዘረዘሩ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ነው ስለምትሏቸው ትምህርቶችና ልምምዶች ፣ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፣ ስለ ቅዱሳን መላእክት ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ለየት ባለ መልኩ አቅርባችኋል ፡፡

  በተረፈ ባለፈው አመት በዛሬዋ ዕለት የተወቀሳችሁበትን ዛሬ አርማችሁ በመገኘታችሁ ትልቅ መለወጥ ስለሆነ አሁንም በርቱ ፡፡ የሦስተኛው ዓመታችሁን በተለየ መንፈስ ለመሥራት ያቀዳችሁ መስሎኛልና እግዚአብሔር ይርዳችሁ ፡፡

  መልካም በዓል እንዲሆን ለመላው ክርስቲያን ህዝብ እመኛለሁ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Your comment and Kebede Bogale very similar. One Mheber kidusan teketaye with two languages.

   Delete
  2. ማኀበረ ቅዱሳንJanuary 7, 2013 at 11:06 AM

   አንድን አስተያየትና መልዕክት ለመቃወምና ለመጻፍ ፤ ቢያንስ አሳማኝ የሆነ ማስረጃና ማፍረሻ ሃሳብ ይዘህ መሆን አለበት ፡፡ በጥላቻ ተሸፍነህ ጻፍኩ ለማለት የማይረባ ነገር አትለቅልቅ ፡፡ በሥርዓቱ ነገሮችን ብታጤን ደግሞ ፣ ማኀበረ ቅዱሳን ነኝ ማለት አያስገርፍም ፤ ወይም አያስገድልም ፡፡ ምነው መሆን ወንጀል ይመስል ዝም ብለህ ባየኸው ሁሉ ላይ ለመለጠፍ ታገልህ ፡፡ የተጻፈውን ማርከሻና መከራከሪያ ሃቅ ብታጣ የማይጣበቅልህን ለማያያዝ ሞከርክ ፡፡ አሁንም እመክራለሁ ፤ በተጨባጭ ከምታውቀውና ማስረጃ ከምታቀርብበት ውጭ ስላቃዠህ ብቻ አትጻፍ ፡፡ አሁን ከጽሁፍህ አስከትዬ አንተ መናፍቅ ፣ ኘሮቴስታንት ብል ምን ይሰማሃል ? እስቲ ከተጻፈው ውስጥ ይኸኛው ውሸት ነው አላሉም ወይም አልተባለም በልና ቃል ምዘዝ ፡፡ እንዲያውም ባሻሽልና ሥራቸውን እንዲታዘቡ በማለት በተረት አስነበብኩላቸው ፡፡

   Delete
 4. yeafaligugn meliekit deje selam yet gebach yederesechibetin yayachu tekumun ebakachu?

  ReplyDelete