Friday, January 18, 2013

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ

የጥምቀት በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ጽድቅን ለመፈጸም ሲል በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ መጠመቁን የምናስብበት በዓል ነው፡፡ በዚህ እለትም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሲሕነትና የእግዚአብሔር ልጅነት በአብና በመንፈስ ቅዱስ ተመስክሯል። የምወደው ልጄ እርሱ ነው እርሱን ስሙት ሲል አብ በደመና ሆኖ ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስን ልንሰማ እንደሚገባን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በዓለ ጥምቀት ያሳስበናል፡፡ እርሱ ደግሞ እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችሀለሁ ብሏል፡፡ ይሁን እንጂ እርሱን እንዳንሰማ የዚህን በዓል መንፈስ የሚለውጡ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡

የዚህ በዓል ማእከል የተጠመቀው ኢየሱስ መሆን ሲገባው ከቤተ ክርስቲያን እቃዎች (ንዋያተ ቅድሳት) አንዱ የሆነው ታቦት አምልኮት ይቀርብለታል፡፡ ይህም የበዓሉን መንፈስ የሚያደፈርስና አላማውን የሚያስት ነው፡፡ ለማንኛውም በዓሉ ጌታ የሚታሰብበት እንጂ ታቦት የሚመለክበት ሊሆን አይገባውም፡፡ ታቦት መቼ ተመለከ የሚል ምላሽ በሰፊው ሊሰጠን እንደሚችል ከወዲሁ እንገምታለን፡፡ ታዲያ እየቀረበ ያለው እልልታ ጭፈራና ስግደት ለማን የሚቀርብ ነው? ብንል ምላሹ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፡፡ ለማንኛውም በታቦት ዙሪያ «አልተሳሳትንም» በሚል ርእስ ስለታቦት ለሰበከው ምህረተአብ «ፍልፍሉ» ወይም አንዳሻው ከተሰጠው «አልተሳሳትንምን?» ከተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 34 ላይ የሚከተለውን ለዛሬ እንድታነቡ ጋብዘናል፡፡

ታቦታት በኢትዮጵያ
የቃል ኪዳኑ ታቦትና የኢትዮጵያ ታቦታት ምንም ዐይነት ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ቢታወቅም፥ የኢትዮጵያን ታቦታት በብሉይ ኪዳን ዘመን ከነበረው የቃል ኪዳኑ ታቦት ጋር አያይዞ መናገር የተለመደ ሆኗል፡፡ «የታቦት አገልግሎት በብሉይ ኪዳን ተጀምሮ የቀረ አይደለም፡፡ ጽላተ ሙሴ ወደ ኢትዮጵያ ስለ መጣች ሀገራችን ኢትዮጵያ ከክርስትና በፊት ብሉይ ኪዳንን ተቀብላ አምልኮተ እግዚአብሔርን አጽንታ ቆይታለች፡፡ ... የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርአተ ኦሪትን ከስርአተ ወንጌል አጣምራ የያዘች ስለ ሆነ በክርስትና ጊዜ ከብሉይ ኪዳን ያገኘቻቸውን በክርስትና መንፈስ እየተረጐመች ትገለገልባቸዋልች፡፡»[i] የሚለው አመለካከትም ይህንኑ ያስረዳል፡፡ ይህም አስተሳሰብ የቃል ኪዳኑ ታቦትና የኢትዮጵያ ታቦታት አንድ አይነት ተደርገው እንዲቆጠሩ በር ከፍቷል፡፡ በሌላም በኩል በአገራችን «ታቦት» ቀርጾ አምልኮ መፈጸም መቼ እንደ ተጀመረ በርግጠኛነት መናገር እንዳይቻል እክል ፈጥሯል፡፡

ብሉይ ኪዳን የተሰጠው በሥጋ ከአብርሃም ዘር ለተወለዱት እስራኤላውያን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው በሰጠው ተስፋ መሠረት በሲና ተራራ ላይ ቃል ኪዳኑን በሙሴ በኩል አስታወቃቸው፡፡ እነርሱም እግዚአብሔር የሰጣቸውን ቃል ኪዳን ለመቀበልና ለመጠበቅ ተስማሙ (ዘጸ. 19፡3-8)፡፡ ቃል ኪዳኑም በደም ተመረቀ (ዘጸ. 24፡3-8፤ ዕብ. 9፡18)፡፡ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ከእነርሱ በቀር ቃል ኪዳን የተጋባው ሌላ ሕዝብ የለም፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ «ቃሉን ለያእቆብ ስርአቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይናገራል፤ ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም ፍርዱንም አልገለጠላቸውም» (መዝ. 147፡8-9)፡፡ «አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጡአቸው» (ሮሜ 3፡2) ተብሎ የተነገረላቸውም እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ ኦሪታቸውም እንዲህ ይላል «በዐይናችሁ ፊት ዛሬ እንደማኖራት እንደዚች ህግ ሁሉ ጽድቅ የሆነች ስርአትና ፍርድ ያለው ታላቅ ሕዝብ ማነው?” (ዘዳ. 4፡7-8)፡፡

ከእነርሱ ጋር በተለያየ መንገድ ግንኙነት በመፍጠር የማንነታቸው መገለጫ የሆኑትን ነገሮች ሌሎች ሕዝቦች መውረስ ይችላሉ፡፡ በኢኦተቤክ ዛሬ የሚታዩት ልዩ ልዩ ኦሪታውያን ስርአቶችና ልማዶችም በተለያዩ መንገዶች ከአይሁድ የተወረሱ ናቸው፡፡ ይህ ግን የባህል መወራረስ ተብሎ ይወሰዳል እንጂ ብሉይ ኪዳንን መቀበል ተብሎ ሊገለጽ የሚችልበት ሁኔታ አይኖርም፡፡

እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ብዙ ጊዜ የገለጸው በባልና ሚስት መካከል እንደሚደረግ ቃል ኪዳን ነው (ሆሴ. 2፡21-22፤ ኤር. 3፡14)፡፡ የባልና ሚስት ቃል ኪዳን ከባልና ሚስቱ አልፎ ሌሎች የሚታቀፉበት ቃል ኪዳን እንደማይሆን እርግጥ ነው፡፡

ለመሆኑ ኢትዮጵያ ብሉይ ኪዳንን መቼ ተቀበለች? ማንስ ሰጣት? እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር በገባው ብሉይ ኪዳንስ እንዴት ልትታቀፍ ትችላለች? ከላይ እንደ ተመለከትነው ይህ ባልና ሚስት በመካከላቸው ስለሚኖረው የፍቅር ግንኙነት በገቡት ቃል ኪዳን ሌላው ወገን ለመታቀፍ እንደ መሞከር አይቆጠርም ወይ?

ሌላው ነጥብ ኦሪት ከነሙሉ ጓዙ የተሰጠው ለእስራኤል ብቻ በመሆኑ ከአሠርቱ ትእዛዛትና እነርሱን ከመሳሰሉት ሕግጋት በቀር ቤተ ክርስቲያን ከኦሪት በቀጥታ አምጥታ ወይም በክርስትና መንፈስ ተርጉማ የምትገለገልባቸው የኦሪት ስርአታትና ንዋያተ ቅድሳት አይኖሩም፡፡
§  “ይሻር የነበረ” (2ቆሮ. 3፡11)
§  “ደካማና የሚናቅ” (ገላ. 4፡9)
§  “ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ” (ቆላ. 2፡17)
§  “የምትደክም፣ የማትጠቅምም” (ዕብ. 7፡18-19)
§  “ምሳሌና ጥላ” (ዕብ. 8፡5)
§  “ነቀፋ ያለበት” (ዕብ. 8፡6)
§  «አሮጌና ውራጅ» (ዕብ. 8፡13)
ወዘተ እየተባለ ከተገለጸው ብሉይ ኪዳን በክርስትና መንፈስ የሚተረጐም ምን የተሻለ ነገር ይገኛል? ብሉይ ኪዳን በአዲስ ኪዳን ተፈጻሚ ከሚሆን በቀር ተሻጋሪ የኦሪት ስርአትም ሆነ የተቀደሰ እቃ በአዲስ ኪዳን ውስጥ አይኖርም፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ወንጌልን ብቻ እንጂ ኦሪትንና ወንጌልን በአንድ ላይ እንድታስኬድ የታዘዘችበት ሁኔታ ፈጽሞ የለም፡፡ አለ ከተባለ ግን ብሉይ ኪዳንን ያስረጀውን አዲስ ኪዳንን (ዕብ. 8፡13) አሻግሮ አለማየት ወይም ዝቅ አድርጎ መመልከት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡

አሁን በየቤተ ክርስቲያኑ የሚገኙት ታቦታት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አገራችን የገቡት ከግብጽ እንደ ሆነ የደስታ ተክለ ወልድ ያማርኛ መዝገበ ቃላት ይናገራል፡፡ «ከግብጽ መጥተው የነበሩ የመዠመሪያዎቹ ታቦቶችም ታቦተ ማርያምና ታቦተ ሚካኤል ናቸው፡፡»[ii] በ4ኛው ምእተ አመት ክርስትናን በኢትዮጵያ ያስፋፋው ፍሬምናጦስ ወይም ሰላማ ከሳቴ ብርሃን በጊዜው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ከነበረው ከአትናቴዎስ ጵጵስናን ተሹሞ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ የተለያዩ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚሰጡ ንዋያተ ቅድሳትን እንደ ሰጠውና ከእነዚህም መካከል አንዱ ታቦት እንደ ሆነ በስሙ የተደረሰው የገድል መጽሐፉ ይተርካል፡፡[iii] ይህ ሁሉ ግን ያው እንደ ተለመደው ኢትዮጵያዊው ታቦት ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ጉዳዩን ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለማያያዝ የተፈጠረ ልቦለድ ታሪክ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ምክንያቱም «ይህ እንግዳ ነገርና በየትኛውም ባህል የማይታይ ሲሆን ከአክሱም መንግሥት ወደ ክርስትና መለወጥ ማለትም ከ331 እስከ 1959 ጳጳሳትንና ኤጲስ ቆጶሳትን ለኢትዮጵያ ስትልክ የኖረችው የአሌክሳንድርያዋ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያንም እንኳ አትቀበለውም፡፡»[iv] 

የመጀመሪያዎቹ ታቦታት ከግብጽ መጡ ወይም አቡነ ሰላማ ታቦትን ወደ አገራችን አመጣ የሚለውን ሐሳብ ለመቀበል የሚያስቸግረው ግን ግብጾች እንደ ኢትዮጵያው ያለ ታቦት የሌላቸው የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ታቦት በመጀመሪያ ከግብጽ መጥቶ ቢሆን ኖሮ ግብጾች ዛሬ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ያለውን ታቦት ይዘው በተገኙ ነበር፡፡ እነርሱ ቅዱስ ቁርባንን የሚፈትቱበት «ሉሕ» የተባለ ሰሌዳ አላቸው፡፡ እርሱም እንደ መሰዊያ እንጂ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ታቦት የሚታይ አይደለም፡፡ በተለያዩ ቅዱሳንና ሰማዕታት ስም ተሠይሞ የበዓል ቀን ተለይቶለት ቀሳውስት ተሸክመውት የሚያነግሱትም አይደለም፡፡ እንደዚህ አድርገው ቢገኙ እንኳ እነርሱም ስሕተተኞች መባላቸው አይቀርም ነበር፡፡ ስለዚህ እየሰጡ ካለው አገልግሎት አንጻር «ታቦት» እና «ሉሕ» በከፊል ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም ጉልህ ልዩነቶችም ይታዩባቸዋል፡፡ ሌሎቹም የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት «አንዲሚንስዮን» የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ «ሜንሳ» በማለት የሚጠሯቸው ንዋያተ ቅድሳት ለስጋ ወደሙ መፈተቻነት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡[v]

አሁን ያለውን ታቦት መቅረጽና አገልግሎት ላይ ማዋል መቼ እንደ ተጀመረ በውል መናገር ባይቻልም፣ ከአጼ ዘርአ ያዕቆብ ወዲህ ይበልጥ የተስፋፋ ይመስላል፡፡ አባ እስጢፋኖስ ዘጉንዳጉንዶ በአጼ ዘርዐ ያዕቆብ ከተከሰሰባቸው ጉዳዮች አንዱ በታቦት ላይ ልታቀርብ ሲገባህ «ቁርባንን በጠረጴዛ ላይ ታቀርባለህ» ተብሎ ነበር፡፡ እርሱም «በመጽሐፍ ውስጥ በጠረጴዛ ላይ እንዳያዘጋጁ የሚከለክል ቃል ስላላገኘሁ ከዕንጨት በተሠራ ጠረጴዛ ላይ ቊርባንን እንዲያዘጋጁ ወንድሞቼን አማክሬያቸዋለሁ» በማለት ክሱን ተከላክሏል፡፡ ታቦት የሚቀረጸውም ከእንጨት መሆኑን ጠቅሶ ሌላው ግን ከወርቅ ወይም ከብር በተሠራ ታቦት ላይ ሊያዘጋጅ ቢወድ ተቃውሞ እንደሌለው ገልጧል፡፡ «ንጉሡም ይህስ መልካም ነው» ማለቱ ተዘግቧል፡፡[vi] ምናልባትም ይህን ያለው አሁን ያሉት ታቦታትና አገልግሎታቸው ገና እየተዋወቀ ያለበት ጊዜ ስለ ነበረ ሊሆን ይችላል፡፡

ባንድ ቤተ ክርስቲያን አንድ ታቦት ብቻ ሳይሆን ከአንድ በላይ ድርብ ታቦታት በደባልነት እንዲቀመጡ ትእዛዝ የወጣው በአጼ ዘርአ ያዕቆብ ዘመን ነው፡፡[vii] ይህም ሁኔታ ያ ዘመን በየቤተ ክርስቲያኑ የታቦታት ቊጥር እንዲጨምርና የታቦት አምልኮ እንዲስፋፋ ያደረገ ዘመን መሆኑን ይጠቁማል፡፡

ታቦት የተባለው ሁለት ገጽ ያለው ዝርግ ሰሌዳ እንደ መሆኑ በፊትና በጀርባው የተለያዩ ነገሮች ይቀረጹበታል፤ ይጻፉበታል፡፡ በአንደኛው ገጽ የተለያዩ ሐረጋትና ስእላት፣ እንዲሁም ምስጢራውያን የተባሉ የእግዚአብሔር ስሞች ይቀረጹበታል፡፡ «በሁለተኛ ገጽ መሰረታዊ ታሪክ ያለበት ጽሑፍ ይገኝበታል፡፡ ይኸውም ንጉሡ፣ ጳጳሱ፣ ጊዜው፣ ወይም ምስለኔው፣ የጭቃ ሹሙና ገበዙ ይጠቀሱበታል፡፡ በዚሁም ታቦቱ የተተከለበትን፣ ቤተ ክርስቲያኑ የተቋቋመበትንና የተመረቀበትን ጊዜና ቦታ ባጭሩ የሚገልጽ ታሪክ ሆነ ማለት ነው፡፡»[viii] በተለይ በሰሌዳው ሁለተኛ ገጽ ላይ የሚጻፈው ይህ መረጃ ሰሌዳው አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሲተከል ከሊቀ ጳጳሱ የሚሰጥ የፈቃድ ማስረጃ እንደ ነበር ይጠቁማል፡፡[ix] በሂደት ግን እንደ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ይቆጠር የነበረው ሰሌዳ «ታቦት» ተብሎ አሁን ወደሚገኝበት ደረጃ ተሸጋግሯል ማለት ነው፡፡

በቤተ ክርስቲያናችን ስለ ታቦት የሚነገረውና የሚታመነው ሁሉ በየትኛው የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ እንደ ተወሰነ ግልጽ አይደለም፡፡ ስለ ታቦት በእምነት መግለጫችንም ሆነ በአምስቱ አዕማደ ምስጢር አስተምህሮአችን ውስጥ አልተወሳም፡፡ በአጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በተተረጎመው ፍትሐ ነገሥት ውስጥ ግን ስለ አሰራሩ እንዲህ ተብሏል፤ «ወይኩን ታቦት በዘይፈልስ እመካን ውስተ መካን ከመ እብነ ደቂቀ እስራኤል ዘፈለሰ እመካን ውስተ መካን፡፡ - ታቦቱ ከቦታ ወደ ቦታ ይዛወር እንደ ነበረው እንደ እስራኤል ልጆች ታቦት ከቦታ ወደ ቦታ የሚዛወር ይሁን»[x] መቼም ከኢትዮጵያ በቀር ታቦት ያላት ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ የለችም፡፡ ፍትሐ ነገሥትን ባስተረጎመችን በግብጽ ቤተ ክርስቲያንም ሉሕ እንጂ ታቦት የለም፡፡ ታዲያ ስለ ታቦት በፍትሐ ነገሥት እንዴት ሊጻፍ ቻለ? የሚለው አነጋጋሪ ነው፡፡

«በርግጥ የፍትሐ ነገሥት የግእዙ ትርጉም ከዐረብኛው ጋር ሲተያይና ሲነጻጸር ስሕተቶችና የአለመጣጣም ሁኔታዎች ያጋጥማሉ»[xi] ስለ ተባለ ምናልባት ከታቦቱ ጋር በተያያዘ ከላይ የተጠቀሰው ትእዛዝም የዚሁ ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ይህ የታቦት አሠራር ደንብ፥ የኢትዮጵያን የታቦት ስርአት ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን የመጣ ለማስመሰል በስርዋጽ የገባ ይሆናል፡፡      

የኢትዮጵያን ታቦታት የተመለከተ ትችትና ተቃውሞ በተነሳ ጊዜ ከቤተ ክርስቲያናችን በኩል ምላሽ የሚሆኑ ማስተባባያዎች ይሰጣሉ፡፡ እነዚህም በአብዛኛው ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት የተነገሩትን መጽሐፍ ቅዱሳውያን ጥቅሶች ለኢትዮጵያ ታቦታት በመጥቀስ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ በማስተባበያው ውስጥም ትችቱንና ተቃውሞውን የሚሰነዝሩት ወገኖች በብሉይ ኪዳን የነበረውን የቃል ኪዳኑን ታቦት እንደ ነቀፉ ተደርጎ ነው የሚቀርበው፡፡ እነርሱ ታቦት በብሉይ ኪዳን እንደ ነበረና ዛሬ እንደሌለ አገልግሎቱም እንዳበቃ በመናገራቸው ተሳስተዋል ለማለት የሚቀርብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ግን አይኖርም፡፡

በቤተ ክርስቲያናችን ስለ ታቦት ያለው ትምህርትና እምነት ግን ይህ ብቻ ነው ማለት አይደለም፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረው የቃል ኪዳን ታቦት ጥላና ምሳሌ እንደ መሆኑ በዐዲስ ኪዳን እርሱን የተካው አካሉና አማናዊው ታቦት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ ይታመናል፡፡ ከእርሱ በቀር የታቦትን ጥላነት የሚተካ አማናዊ ታቦት የለም፡፡ የምእመናን ልብ ግን ቃሉ የሚጻፍበት ጽላት ተብሎ ተገልጿል (ኤር. 31፡33፤ 2ቆሮ 3፡3)፡፡[i] የኢኦተቤክ እምነት ርአተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት (1988 62) ጎርጎርዮስ (ሊቀ ጳጳስ) (197494)፡፡
[ii] 1962 1250)፡፡
[iii] ገድለ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን (1998 10-11)፡፡
[iv]  ሐንኮክ (ገጽ 1995 125)፡፡
[v]  ጎርጎርዮስ (ሊቀ ጳጳስ) (1974 95)፡፡
[vi] ገድለ አቡነ እስጢፋኖስ ዘጉንዳጉንዶ (1996 134-135)፡፡
[vii] ተክለ ጻድቅ (1966 239)፡፡
[viii] መሠረት (ዓ.ም. ያልተገለጸ፣  12-13)፡፡
[ix] ጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቁጥር 15 ገጽ 16)፡፡
[x] ፍትሐ ነገስት (1990 21)፡፡
[xi] ዲበኩሉ (/) (1986 80)፡፡

13 comments:

 1. Why don't you focus on value adding stuff? We are proud of the Tabot, which is unique to Ethiopia and EOTC. We only need to better spread the Gosple of Jesus Christ. To do that, we don't have to despise our good tradition and religious culture.

  ReplyDelete
 2. Who said Mahibere Kidusan can FULFILL its POLITICAL AGENDA under the UMBRELLA OF THE EOTC? THAT IS WHAT MK ARE DOING!!!

  Mahibere Kidusan is the political party that is destroying our mother church.

  ReplyDelete
 3. Dear SELAMA,

  CAN YOU PLEASE TELL US EXACTLY WHERE YOU DISAGREE WITH THE LUTERANS (PROTESTANTS).

  CAN YOU DRAW THE LINE between PROTESTANTS AND the ORTHODOX CHURCH ACCORDING TO YOUR THOUGHTS!!!

  ReplyDelete
 4. እውነት ይህን ጽሑፍ ከላይ ከድረ ገጹ ላይ ፎቶአቸው የተደረደሩት አባቶች ይቀበሉታልን?

  ReplyDelete
 5. tabot yasgebaw MK new endet zares alalachihum?

  ReplyDelete
 6. እግዚአብሔር የጋብቻ ስርአት የፈጸመው ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ነው?????
  " እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ብዙ ጊዜ የገለጸው በባልና ሚስት መካከል እንደሚደረግ ቃል ኪዳን ነው። ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር በገባው ብሉይ ኪዳንስ ጋብቻ እንዴት ልትታቀፍ ትችላለች?
  ኦሪት ከነሙሉ ጓዙ የተሰጠው ለእስራኤል ብቻ በመሆኑ ከአሠርቱ ትእዛዛትና በቀር ቤተ ክርስቲያን ከኦሪት በቀጥታ አምጥታ ወይም በክርስትና መንፈስ ተርጉማ የምትገለገልባቸው የኦሪት ስርአታትና ንዋያተ ቅድሳት አይኖሩም፡፡ "
  እንዴት እንዴት ተባለ!? እያቄምና ሃና ከእስራኤል ወገን አይደሉምን? ቅድስት ድንግል ማርያም ከእስራኤል ወገን አይደለችምን? ይህ ታዲያ ክርስቶስን በሥጋ ከእስራኤል ወገን አያደርገውምን?
  ታዲያ ጸሐፊው ባል እና ሚስት ብለው ከጻፉ ብሉይ ኪዳንንና ሐዲስ ኪዳንን ማጋባት እንዴት አቃታቸው

  Genesis 11:1-32 Genesis 10:6-20 Acts 8:27-39 Acts :27 Isaiah 43:3 2 Kings 19:9 Jeremiah 13:23 Isaiah 20:2-6 Psalm 68:31 Jeremiah 46:9 Psalm 87:4 Psalm 66:11 Esther 1:1 2 Chronicles 14:9-15 2 Chronicles 12:3 Zechariah 14:2 Isaiah 11:11 1 Chronicles 1:9 Zephaniah 2:12 Habakkuk 3:7 Amos 9:7 Daniel 11:43 Daniel 11:1-45 Ezekiel 39:1-29 Ezekiel 38:5 Ezekiel 38:1-23 Ezekiel 30:4-9 Jeremiah 39:15-18 Ezekiel 29:10 Jeremiah 38:7-13 Isaiah 46:9-10 Isaiah 46:9 Isaiah 18:1-6 Isaiah 18:1 Isaiah 11:1 Psalm 105:23 Job 28:19 2 Chronicles 16:8 1 Kings 7:26 Numbers 12:1 Leviticus 1:1-17 Genesis 10:6 Genesis 1:1-31 Genesis 1:1 Acts 17:26 Acts 13:1-52 Acts 8:32-38 Matthew 5:1-48 Matthew 1:1 Isaiah 45:14 1 Kings 7:23 1 Kings 7:1-51 1 Kings 1:1-13 Genesis 14:1-24
  እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከሐዲስ ኪዳን በፊት ካላወቃት ይህ ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መጠቀሱ ከየት መጥቶ ነው። ኩሽ፣ አብስኒያና ኢትዮጵያ እየተባለች የተጠቀሰች የትኛዋ ሀገር ናት ታዲያ??? እናትና ልጁን ተቀብለን ጽላቱን ለማን ጣልነው ለነገሩ ጽሐፊው እናቱን መቀበሉ ያጠራጥረኛል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. You're just delutional and arguing with you is pointless. There are a bunch of places and countries mentioned in the Bible, so what?? We're not anything special. God made a covenant with Abraham and his descendants, are you a descendant of Abraham?

   Delete
  2. ኢትዮጵያ ጥንትም እግዚአብሔርን ስታመልክ የነበረች ሀገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ ገነትን እንዲያጠጣ ወንዝ ባለቤት ነች ዘፍ. 2፡13፤ የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል፡፡ እግዚአብሔርን በማወቅዋ ሙሴ አጋሩን ኢትዮጵያዊት ነበረች ዘሁ. 12፡1፤ ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ። በንጉስ ሰሎሞን ጊዜም ኢየሩሳሌም ድረስ የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራ ለማየት ንግስቲትዋ ተጉዛለች 1ኛ ነገ. 10፡1፤ የሳባም ንግሥት በእግዚአብሔር ስም የወጣለትን የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች። በዚህ ጊዜ ነው ቀዳማዊ ምኒሊክ የተፈጠረው እናም ኢትዮጵያ ብትወልደውም ካደገ በሁዋላ ወደ አባቱ ልካው ብዙ ዘመን ከኖረ በሁዋላ እግዚአብሔር በሚያውቀው ካደገ ከአይሁድ ካህናት ጋር ታቦቱን አብሮ ብዙዎችን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሰ ታሪክ ይነግረናል ፡፡ይህንንም ለማመላከት ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ተብላ በነቢዩ ዳዊት ተነግሮላታል መዝ. 66(67)፡ 31 መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። እግዚአብሔር ከእስራኤልም አስበልጦ እንደሚያየን ሲናገር ት. አሞ. 9፡7፤ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። በእግዚአብሔር ላይ ያለንን የጠበቀ እምነት ሲገልጥ ት. ኤር. 13፡23 በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? ይላል፡፡ እግዚአብሔርን በብሉይ ኢየሩሳሌም ድረስ በመሄድ አምልኮትዋን ታከናውንም ነበረ ኢትዮጵያዊውም ጃንደረባ ለዚሁ ሄዶ ነበር በሐዋርያው ፊሊጶስ በመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ ያጠመቀው ያውም መጽሐፈ ብሉይን እያነበበ ባለበት ወቅት፡፡ ለእግዚአብሔር መስዋእተ ኦሪት ስትሰዋ የነበረች ሀገረ እግዚአብሔር የሆነች ኢትዮጵያ በመስወእተ ሀዲስ የሆነውን የጌታን ስጋና ደም ታቀርባለች ለዚህ አገልግሎት ታቦቱን መንበር አድረጋ ትፈጽማለች፡፡ ጥንትም ታቦቱ ላይ መስወእተ ኦሪት የሀጢያት ማስተሰሪያ ይሰዋ ነበረ በአዲስ ኪዳን ግን ይህ መስዋእተ ኦሪት አማናዊ በሆነው በጌታ ስጋና ደም በመተካቱ አሁን ይሰዋበታል፡፡ የተሻረም በሉ ፤ደካማና የሚናቅ፤ ሊመጡ ያሉትን ጥላ፤ የምትደክም የማትጠቅምም፤ምሳሌና ጥላ፤ነቀፋ ያለበት፤አሮጌና ውራጅ ምንም በሉ ምን ከቅዱስ ታቦት ጋር ሳይሆን ግንኙነቱ ከብሉይ ኪዳን መስዋዕት ጋር ነው ፡፡

   Delete
 7. yegziabher kal letenegeracw beca endebalena mist kal new ktbale getan lemen tekebelachu
  geta yeteweledew yastemarew
  esrael aydelemen#
  *alawaki sami neft yelekelekal*

  ReplyDelete
 8. ሀ/ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ብሉይ ኪዳንን መቼ ተቀበለች? ማንስ ሰጣት?
  ጸሐፊው ምን ለማወቅ እንደፈለገ እንኳን በግልጽ ማወቅ አይቻልም ፡፡ የታሪኩን አመጣጥ ለመረዳት ወይንስ ኢትዮጵያ በብሉይ ኪዳን አልተዳደረችም ለማለት ፈልጎ ይሆን ? ሃይማኖትስ በምን መልኩ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ቆየና ማን ሰጣት ፣ ማን ተቀበላት ይባላል ? እግዚአብሔር ለእሥራኤላውያን አዳልቷል ወይም ያዳላል የሚል ትምህርት ለማስረጽ ተፈልጎ ይሆን ? የማንፈተንበት መከራ የለምና የጥያቄው ዓላማ ስለአልተብራራ በመሰለኝ ከተረዳሁት ለንባብ ያህል በጽሁፍ ያለውን ሰነድን (ክብረ ነገሥትን) የተመለከተ በንግሥተ ሳባ ዘመን ብሉይ ኪዳንን ተቀብለናል ለማለት ያስደፍራል ፡፡ ምክንያቱም ከዛ በፊት የጸሐይ አምላክ እንደሚከተሉ ተጽፏልና ነው ፡፡

  መጽሐፍን በጥሬ ቃል ስንረዳው ወንጌልም ብትሆን ለእሥራኤላውያን እንጅ ለአሕዛብና ለሌሎች አልታቀደችም ነበር ያሰኛል ፡፡ ይህንንም ለመረዳት ከአንድም ሁለት ጊዜ የተገለጸውን ከሚከተለው እንመልከት ፡፡ ኢየሱስም የተላከው ለጠፉት በጎች ለሚላቸው እሥራኤላውያን ወገኖቹ እንደሆነ መግለጹ ፤ ማቴ 15፡24 ፡፡ ሐዋርያቱንና አርድዕቱን ለሥራ በሚያሰማራበት ወቅትም ወደ ጠፉት በጎች ማለትም እሥራኤላውያን ዘንድ እንጅ ወደ ሳምራውያን ከተማ እንዳይገቡ ማዘዙ ፡፡ ማቴ 1ዐ፡5-6 አስረጅ ነው ፡፡

  እንዲህ የሚለው ትእዛዝና ትምህርት ተቀይሮ ለአሕዛብ ሁሉ ምስክር ይሆን ዘንድ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል ስለተባለ ወይንም እንዲያስተምሩ በትእዛዝ ስለተሻሻለ (ማቴ 24፡14 ፤ ማቴ 28፡19-2ዐ) ከእርገቱ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተመልተው ሐዋርያቱ ማስተማር በጀመሩበትና በስደት ላይ በነበሩበት ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ተመለሱና ፤ በሳምራውያን በብዙ መንደሮችም ወንጌልን እንደ ሰበኩ ተዘግቧል ሥራ 8፥25 ፤ ለአሕዛብ የተሰበከችው ወንጌል ለእኛም ቢሆን ወንጌል በቅድሚያ ደርሳለች ፡፡ ከርኩሰት መጠበቅ የሚያስፈልግ ቢሆን ፣ መራቅ የነበረባት ብሉይ ናት ሐዲስ ፡፡
  ለአሕዛብ ቢባልም ደግሞ ኢየሱስ በተወለደበት ዘመን ደግሞ ኢትዮጵያ ከአሕዛብ ተራ አልነበረችም ፡፡ ታድያ ወንጌልንን በምን ምክንያት ተቀበለችና ዛሬ ሁሉም ክርስቲያን ነኝ ለማለት ደፈረ?

  ለ/ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ላይ ስለቀረበው የታቦት ማዳበል ሥርዓት ፤ ምናልባት በርሱ ዘመነ መንግሥት ተጀመሮ ከነበረ (አሁን የኢትዮጵያ ክርስትና ትምህርትና ሥርዓት በሙሉ ከዚሁ ሰው ጋር እየተቆራኝ ስላስቸገረ ሁሉንም መጠራጠር ጀምሬአለሁ) የክርስትና ትምህርትን ለማስፋፋት እንዲረዳው ይሆናል እንጅ በሌላ ምክንያት አይሆንም ፡፡ ምክንያቱም በምሥራቅ የአፋር ሱልጣን ፣ በደቡብ ደግሞ የእስልምና ተስፋፊዎች መጥተውበት ስለነበር ፣ ሕዝቡን እየሰበሰበ የሚያስተምርበት ስልት ነው ፡፡

  ይኸም ማለቴ በገጠሩ ህዝባችን አጥቢያ የሚባል ነገር እንዳለ አውቃለሁ ፡፡ ማለትም እንደ አሁኑ የገበሬ ማኀበርና የቀበሌ ነዋሪ ማኀበራት ኀብረተሰቡ ተገናኝቶ የሚወያየው ፣ ስለ ሃይማኖትም የሚማረው በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ ነው (በዛ ዘመን ሬዲዮ ፣ ቴሌቪዥን የሚባል ነገር የለም ፤ የሰማህ ላልሰማ አሰማ የሚባልበት ወቅት ነው) ፡፡ በአንድ የአካባቢ ቤተ ክርስቲያን (አጥቢያ) ሁለት ታቦት አለ ማለት ኀብረተሰቡ ቢያንስ በወር ውስጥ ሁለት የመገናኛና የመማሪያ ተጨማሪ ቀኖች ይኖሩታል ማለት ነው ፡፡ ስለዚህ መጥፎ ውሳኔ ተደርጎ የሚታየው ዛሬ ሊሆን ይችላል ፡፡ በወቅቱ ብንኖርና ስለ ሃይማኖታችን የምንጨነቅ ቢሆን ግን በደንብ እንረዳው ነበር፡፡

  ክፍል ሁለት ከቀሲስ መላኩ መጽሐፍ ይቀጥላል

  ReplyDelete
 9. ክፍል ሁለት
  ይኸኛውን ክፍል አንድ ወንድማችን ስውሩ አደጋ በሚል ርዕስ ቀሲስ መላኩ ባወቀ ተፈራ የጻፉትን መጽሐፍ ፣ እንዳነብ በጋበዘኝ መሠረት ሳነብ በማግኘቴ ነው ያመጣሁት፡፡ ግብዣው መልካም መሆኑን ለመመስከር ፍሬው ይኸው ቀርቧል ፡፡

  ታቦት በኢትዮጵያ ውስጥ በልማድ ያለ አይደለም ወይም አንዳንድ የዋሆች እንደሚሉት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ኦሪትን ከሥርዓተ ወንጌል ጋር ባባላንጣነት የምታታግል አይደለችም ፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከክርስትና በፊት የብሉይ ኪዳን አገር የነበረችው ኢትዮጵያ በክርስትና ጊዜም ከብሉይ ኪዳን ያገኘቻቸውን ጠቃሚ ነገሮች በክርስትና መንፈስ እየተረጎመች ትጠቀምባቸዋለች ፡፡ ከብሉይ ኪዳን ከወሰደቻቸውም አንዱ ጽላተ ኪዳን ታቦተ ሕግ ነው ፡፡ አዲስ ቤተ ክርስቲያን በሚሰራበት ጊዜ ከእጽ ወይም ከእብነ በረድ ተቀርጾ በላይ የእግዚአብሔር ምስጢራዊ ስም (ህቡእ ስም) ((አልፋ ኦሜጋ)) የመጀመሪያውና የመጨረሻው ማለት ነው ፡፡ ይህ ቃል ከተጻፈበት በኋላ በኤፒስ ቆጶሱ እጅ ተባርኮና ሜሮን ተቀብቶ በመንበሩ ይሰየማል (ይቀመጣል) ፡፡ በቅዳሴም ጊዜ ሕብስቱና ወይኑ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ቄሱ ሥርዓተ ቅዳሴውን የሚያከናውነው ሕብስቱን ሥጋ መለኮት ፣ ወይኑን ደመ መለኮት ወደ መሆን የሚለውጠው በዚህ በታቦቱ ላይ ነው ፡፡ የደብተራ ኦሪት ጽላት እግዚብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገጥበት ዙፋን ነበር ፡፡ ይህ ግን የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ፡፡ ሥጋዬን ብሎ ደሜንም ጠጡ እያለ ያመኑትን ሁሉ የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊ) ነው ፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ስለዚህ ነው ፡፡


  አባ ጎርጎርዮስ ፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 95
  “ከኢትዮጵያም ሌላ በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ታቦት የተለመደ ሕግ ነው ፡፡ ሥጋውን ደሙን የሚፈትቱት በታቦቱ ላይ ነው ፡፡ ለምሳሌ ግብጻውያን ታቦቱን ሉህ ይሉታል ፡፡ ጽላት ሰሌዳ ማለት ነው ፡፡ ያለ እርሱ ሥጋውንና ደሙን አይፈትቱም ፡፡ የምሥራቅ አብያት ክርስቲያናት ተብለው የሚጠሩት የግሪክ የሩሲያ የሩሜንያና ሌሎችም ወደ ክርስትና የተመለሱት ከአረማዊነት ስለሆነ የታቦትን ምሥጢር አያውቁትም ፡፡ በታቦቱ ፈንታ ከመንበር የማይነሳ እንደ ታቦት የሚከበር የጌታ የስቅለቱ ወይም የግንዘቱ ስዕል ያለበት የነጭ ሐር መጎናጸፊያ አላቸው ፡፡ ያለ እርሱ ሥጋውን ደሙን አይፈትቱም ፡፡ ይህንን በጽርእ ((አንዲሚንሲዮን ይሉታል ፡፡ ((ህየንተ ታቦት)) ስለ ታቦት ፈንታ ማለት ነው ፡፡ የሮማ ካቶሊኮች ሜንሳ ይሉታል ጠረጴዛ ማለት ነው ፡፡ ))

  ቤተ ክርስቲያናችን በሙሴና በክርስቶስ ፣ በብሉይና በሐዲስ ወይም በጣዖትና በእውነት በምሳሌና በአማናዊ ያለውን ልዩነት ስለምታውቅ ለሚጠይቂዋት ሁሉ ይህን እምነቱዋን ከማስረዳት ተቆጥባ አታውቅም ፡፡ ታቦት በሐዲስ ኪዳንም በቤተ ክርስቲያናችን አምልኮተ እግዚአብሔር ይፈጸምበታል ፡፡ ታቦት እውነተኛው የሕይወት ምግብ የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚቀርብበትና የሚፈተትበት መሠዊያ ነው ፡፡ የሚከበረውና የሚሰገድለትም ስለዚህ ነው ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምበት ታቦተ ምሥዋዕ (መሠዊያ) ቅዱስ ቁርባን የሚከብርበት ነው እንጅ እንደ ብሉይ ኪዳን የምንጠቀምበት አይደለም

  የኘሮቴስታንት ታቦት
  1. ጠረጴዛ ነጭ ልብስ አልብሰው ሕብስትና ወይን በዚያ ላይ ያስቀምጣሉ በፊቱ ይንበረከኩና ይሰግዳሉ ፡፡ በጠረጴዛው ግራና ቀኝ አልፎ አልፎ ሻማ ወይም አበባ ያስቀምጣሉ ፡፡ በአባ እስጢፋኖስ ተመክረው ይሆን ይህን የሚያደርጉት
  2. ባዶ ወንበር - ጌታ ወደ ጉባኤያችን መጥቶ ይቀመጥበታል ብለው ሲለሚያምኑ ባዶውን ከፓስተሩ ጎን የሚቀመጥ ነው ፡፡ ወይም ከፊት ለፊት ካሉት ባዶ ወንበሮች አንዱን ክፍት ያደርጋሉ
  3. በጠረጴዛ ላይ የተቀመጠ የተከፈተ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ሲያስፈልግም ከፍ አድርገው በማንሳት ክብር ይሰጣሉ
  4. የተለያዩ ቁሳቁሶች - እኒህ ደግሞ መንፈስን ለመጎተት ወይንም ከመንፈስ ለመገናኘት የሚጠቀሙበት ነው ፡፡ ፖይንት ኦፍ ኮንታክት በመባል ይታወቃል ፡፡

  ReplyDelete
 10. same old story that we had heard from protestants earlier .the only difference is you pretend yourself as orthodox and they officially declaring as protestants.

  ReplyDelete
 11. ከፕሮቴስታንቶች አስተምህሮ እናንት የማትስማሙበትን ብታብራሩልን

  ReplyDelete