Tuesday, January 8, 2013

ጥያቄዎቻችሁና መልሶቻቸው

ምንጭ፦ ጮራ (http://www.chorra.net/)
 ጥያቄ፥ ከጎይትኦም “መጽሐፍ ቅዱስ አጋንንት ከሰዎች ውስጥ በኢየሱስ ስም እንደሚወጡ በግልጽ ይናገራል። አንዳንድ አጋንንትን እናስወጣለን የሚሉ ሰዎች ግን በኢየሱስ ስም ብቻ ሳይሆን በጻድቃንና በሰማዕታት ስም እናስወጣለን ይላሉ። በተጨማሪ አጋንንቱ ካደሩበት ሰው ጋር ትግል መግጠም፥ ሰውዮውን በመቊጠሪያ፥ በጧፍ፥ በመስቀል ወዘተ. መደብደብና የመሳሰሉ ድርጊቶችን ይፈጸማሉ። እነዚህንም ድርጊቶች በሲዲ እያሠራጩ ከክርስትና ትምህርት ውጪ የሆኑ ልምምዶችን ያስፋፋሉ። እውን እነዚህ ነገሮች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ናቸውን?

መልስ ከመምህርት ሲያዴ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አጋንንት ከሰዎች ሲወጡ የምናነበው በሐዲስ ኪዳን ክፍል ውስጥ ነው። አጋንንትን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያወጣ የምናገኘውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው። እርሱም አጋንንትን በሥልጣን ቃል እንዲወጡ ያዝዝ፥ አጋንንትም ከሰዎች ይወጡ፥ ሰዎቹም ነጻ ይሆኑ ነበር (ማቴ. 4፥24፤ 8፥16-17፡28፤ 9፥33፤ 12፥22፤ ማር. 1፥34፡39፤ 5፥2፡8፤ 7፥29-30፤ 16፥9፤ ሉቃ. 4፥35፡41፤ 8፥2፡33፤ 9፥42)። አጋንንትን የሚያወጣው በእግዚአብሔር መንፈስ፥ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጣት መሆኑን ተናግሯል (ማቴ. 12፥28፤ ሉቃ. 11፥20)።

ጌታ ኢየሱስ በስሙ አጋንንትን ከሰዎች የማውጣትን ሥልጣን በመጀመሪያ ለተከታዮቹ ሐዋርያትና ቀጥሎም ለኋለኞቹ ሰባው ተከታዮች (አርድእት) ሰጥቷል፤ እነርሱም አጋንንትን በስሙ አውጥተዋል (ማቴ. 10፥8፤ ማር. 3፥15፤ 6፥12፤ ማር. 9፥38-40፤ ሉቃ. 9፥1፤ ሐ.ሥ. 16፥18)። ሐዋርያትና ሰባው አጋንንትን እንዲያወጡ የተሰጣቸው ስም ኢየሱስ ብቻ ነው። “ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው። ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል” ማለታቸው በወንጌለ ሉቃስ ተመዝግቧል (ሉቃ. 10፥7)።

በእርሱ የሚያምኑትን ከሚከተሏቸው ምልክቶች መካከል አንዱ በስሙ አጋንንትን ማውጣት ነው (ማር. 16፥17)። በትክክል የኢየሱስ ተከታዮች ያልሆኑ አንዳንዶች አጋንንትን በኢየሱስ ስም ማውጣታቸውና ለማውጣት ሙከራ ማድረጋቸው ተጽፏል (ማቴ. 7፥22፤ ሐ.ሥ. 19፥13)። በተለይ “አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች፥ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ። የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት። ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፦ ኢየሱስንስ ዐውቀዋለሁ ጳውሎስንም ዐውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው። ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው፤ ቈስለውም ከዚያ ቤት ዕራቊታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው፤ አሸነፋቸውም። ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሀት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤ አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር። ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ ዐምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ። እንዲህም የጌታ ቃል በኀይል ያድግና ያሸንፍ ነበር” (ሐ.ሥ. 19፥13-20)።

ይህ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ የተመዘገበው ታሪክ ወደ ጎይትኦም የጥያቄ መልስ ያንደረድረናል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥልጣኑ፥ እርሱ ሥልጣን የሰጣቸው ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ደግሞ በኢየሱስ ስም አጋንንትን ሲያወጡና ሰዎችን ነጻ ሲያደርጉ፥ ጌታ በሥጋ ከመገለጡ በፊትና በሥጋ ተገልጦ በተመላለሰበት ወቅትም ከአይሁድ አንዳንዶቹ አጋንንትን እያወጡ ይዞሩ ነበር። አጋንንትን ያወጡ የነበረው ግን በኢየሱስ ስም አልነበረም። በኢየሱስ ስም ካልሆነ ታዲያ በማን ስም ነበር አጋንንትን ያወጡ የነበረው? ቢባል በአስማት ነው። ይኸውም ሊታወቅ ሐዋርያት ሲያደርጉ አይተው በኢየሱስ ስም ክፉዎች መናፍስትን ለማውጣት ሞከሩ። ክፉው መንፈስ ግን “ኢየሱስንስ ዐውቀዋለሁ ጳውሎስንም ዐውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ?” በማለት አባረራቸው፤ አሸነፋቸውም። ይህን ተከትሎ በሕዝቡ ላይ ፍርሀት ሲወድቅ፥ የጌታ የኢየሱስ ስም ተከበረ። ብዙዎችም ወደ መዳን ሲደርሱ፥ “ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ።” እነዚህ አስማተኞች አጋንንትን በኢየሱስ ስም ለማውጣት ከሞከሩትና ካልተሳካላቸው ወገን እንደ ነበሩ ምንም ጥርጥር የለውም። ለዚያ ነው እስከዚያ ሰዓት ድረስ ይዘዋቸው የነበሩት የአስማት መጻሕፍት በሐሰት እንጂ በእውነት አጋንንትን ማስወጣት እንደማይችሉ የተረዱትና በሰው ሁሉ ፊት ያቃጠሏቸው። ዛሬም በኢየሱስ ስም ሳይሆን በሌሎች ስሞችና በልዩ ልዩ ዘዴዎች አጋንንትን እናወጣለን የሚሉ ምድባቸው ከእነዚህ ወገን ነው።

ጠያቂአችን እንዳሉት፥ እነዚህ ወገኖች አጋንንትን ለማውጣት የኢየሱስን ስም ብቻ ሳይሆን የሌሎች ፍጡራንን አስማት ይጠራሉ። አጋንንትም እየጮሁ “ወጣን” ሲሉ ይታያል። ይህ ከአይሁድ አንዳንዶች አጋንንትን እያወጡ ይዞሩ ነበር ካለው ጋር ሊገናዘብ የሚችል ነው። የአጋንንቱ መውጣት ሰዎች ወደ ክርስቶስ እንዳይመጡ ለማዘናጋት ካልሆነ በቀር እውነተኛ አይደለም። ዛሬ በዚህ መንገድ ከአጋንንት እስራት ነጻ ወጡ የተባሉቱ ብዙ ጊዜ ጌታን  ሲከተሉት አይታይም። እንዲያውም እርሱንና የእርሱን ወገኖች፥ የመንግሥቱንም ሥራ ሁሉ የሚቃወሙ ናቸው። ጌታ ከአጋንንት ነጻ ያወጣው ሰው ግን ጌታን ይወዳል፤ እርሱንም ለመከተልም አያንገራግርም፤ ለወንጌልና ለመንግሥቱ ሥራ መስፋት ደጋፊ እንጂ ተቃዋሚ አይሆንም (ማር. 5፥18)። ስለዚህ ሁሉም በፍሬው ይታወቃል።

ሌላው ጠያቂአችን ያነሡት ነጥብ፥ አጋንንትን ከሰዎች ውስጥ በኢየሱስ ስም ብቻ ከማስወጣት ይልቅ አጋንንቱ ካደሩበት ሰው ጋር ትግል መግጠም፥ በመቊጠሪያ፥ በጧፍ፥ በመስቀል መደብደብና የመሳሰሉ ድርጊቶችን መፈጸም አጋንንትን የማስወጫ መንገዶች ተደርገው እየተወሰዱ ነው። ነገር ግን ስሕተት ነው። አጋንንት የሚወጡት ከኢየሱስ ስም ኀያልነት እንጂ እኛ ሰዎች ከምንጠቀመው ኀይልና ልዩ ልዩ ዘዴ የተነሣ አይደለም። ስለዚህ አጋንንትን ለማስወጣት የኢየሱስን ስም በእምነት መጥራት ብቻ በቂ ነው። ርኩሳን መናፍስትም በእውነት ከሰው የሚወጡት በዚህ ኀያል ስም ሲታዘዙ ብቻ ነው። ሐዋርያትም ሆኑ ሰባው አርድእት አጋንንትን እንዲያወጡ የታዘዙትና ያስወጡት በኢየሱስ ስም ብቻ ነው እንጂ ሌላ ስም አልጠሩም፤ ሌላ ዘዴም አልተጠቀሙም። ደግሞስ የተዘረዘሩትንና ሌሎችን የኀይል ርምጃዎች መውሰድ ሥጋና ደም የሆነውንና ርኩሳን መናፍስት ያደሩበትን ሰው አካል ከመጐዳትና ሲከፋም ለሞት ከመዳረግ ውጪ መንፈስ በሆነው ጠላት ላይ እንዴት ማሳረፍ ይቻላል?

ጌታችን አስቀድሞ እንደ ተናገረው ኀይለኛውን ሳያስሩ የኀይለኛውን ቤት መበዝበዝ አይቻልም (ማቴ. 12፥29)። ኀይለኛው ሊታሰርና በቊጥጥሩ ሥር ያዋላቸው ሰዎች ነጻ ሊወጡ የሚችሉት ደግሞ በኢየሱስ ስም ብቻ ነው፤ ስለዚህ ሌላ ምንም ዐይነት ሰዋዊ ዘዴ ወይም ስልት መጠቀም ሳያስፈልግ፥ ኢየሱስ የሚለውን ነጻ አውጪና ፈዋሽ ስም በእምነት መጥራት ከአጋንንት እስራት ነጻ ያወጣል።

46 comments:

 1. Beyesus kamenk ewnet esty leb kaleh kedame weyem heude estifanose betekrstian hed! Wendneth ytayal. Yanen yeyesus ,eyesuas emetlew yeleyal !!

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 8, 2013 at 4:24 PM

   Are you talking about Ato Grima? Amenzera teweld meleketen yeshale. Abaselamwech we need you to say some thing about Ato Girma.

   Delete
 2. ምእመን ዘማኀበረ ቅዱሳንJanuary 8, 2013 at 2:04 PM

  የፈዋሽና ተፈዋሽነት ሚናን ብንረዳው
  ኢየሱስ “ድውዮችንም ሊፈውሱ ፣ ሙታንን ሊያስነሱ ፣ ለምጻሞችንም ሊያነጹ ፣ አጋንንትንም ሊያወጡ ሥልጣን ይሆንላቸው ዘንድ አሥራ ሁለት (ደቀ መዛሙርት) አደረገ፤” ማር 3:15 ፤ ማቴ 10:8 ፤ ሉቃ 9፡1 ፡፡ ከተሰማሩባቸው አካባቢዎች ሰብዓውም ሲመለሱ ፣ “ጌታ ሆይ አጋንንት እንኳን በስምህ ተገዙልን ፤” በማለት ደስታቸውን መሠከሩለት ፡፡ ሉቃ 1ዐ፡17 ፡፡ በዚህ ቃልና መመሪያ መሠረት ፣ ፈዋሽ የሚሆነው ሰው የጌታ አማኝና በህይወት ዘመኑ ሁሉ የርሱ ተከታይ መሆን ፣ ለአገልጋይነት የተመረጠና ፣ የእግዚአብሔርን ጸጋን የታደለ (ፈቃዱ የተሰጠው) ሊሆን ይገባዋል ማለት ነው ፡፡

  ከቃሉ እንደተረዳሁት ጌታችን የፈወሰው በስሙ ሳይሆን በእግዚአብሔር መንፈስ (ከራሱ በሚወጣ ኃይል) ነው ፡፡ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ግን “አጋንንትን በአጋንንት አለቃ ያወጣል” ብለው ስላመኑ ይህንኑ በጌታችን ላይ ተናገሩበት ፡፡ እርሱ ግን አጋንንትን የሚያወጣው በእግዚአብሔር መንፈስ (ትኩረት) መሆኑን ካስረዳቸው በኋላ ፤ እኔ አጋንንትን በአጋንንት አለቃ ካወጣሁ ፣ ልጆቻችሁ አጋንንትን በምንድር ያወጣሉ ? በማለት ጠየቃቸው ፡፡ በመጨረሻ ይህንኑ መልእክቱን ሲቋጭ “እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።” አላቸው ፡፡ ማር 3፡22 ፣ ሉቃ 11፡15 ፤ ማቴ 1፡24 ፣ ማቴ 12፡27-28 ፤

  እንደገለጽኩት በስሙ ለማገልገልና በአጋንንትም ሆነ በደዌ የተጐዱ ሰዎችን ለመፈውስ ፣ በመጀመሪያ በጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ይጠይቃል ፤ ሁለተኛም ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን (ጸጋ ፈውስን) መሰጠት ይኖርብናል ፡፡

  በኢየሱስ የማያምኑ ግለሰቦች ከላይ እንደተመለከተው የመፈወስ ጸጋው ስለማይሰጣቸው ፣ መጀመሪያውኑ አይፈውሱም ፤ በአሻፈረኝ ከቀጠሉ ደግሞ በወገን ላይ የባሰውን የከፋ ጉዳትን ያስከትላሉ ፡፡ ስለሆነም ያለ ስጦታቸው ፣ በየሥርቻው ሰዎችን በቡድን እየያዙ የሚያሰቃዩ ይኖራሉና ፣ የኢየሱስን ስም በመጥራት እንፈውሳለን በማለት ከሚያጭበረብሩ ዋሾዎችም እንድንጠነቀቅና እንድንጠበቅ እመክራለሁ ፡፡ ይህንኑ በተመለከተ የመጽሐፍ ማስረጃዬን አስተውሉ ፡፡

  “አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች ፣ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን ፤ እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ። የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት። ክፉው መንፈስ ግን መልሶ ፤ ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ፤ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው። ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም።” ሥራ 19፡13-16

  ለመፈወስ ስለ እምነት አስፈላጊነት ምሳሌ፡-
  አሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም ሲፈሳት የኖረችው ሴት ፣ የኢየሱስን ስሙን ሳትጠራ ፣ ወይም ሌላ ሰው ስለርሷ ሳይጠራላት በእምነት ብቻ ኢየሱስ የለበሰውን ጨርቅ ነካች ፡፡ ወዲያውም የደምዋ (ፈሳሽ) ምንጭ ደረቀ ፤ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች። ማር 5:25-29 ፣ ሉቃ 8፡44

  ” ኢየሱስም ከእርሱ ኃይል (ትኩረት) እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎ። ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው? አለ።” ማር 5፡30 ፡፡ ሴትየዋም ከፊቱ በቀረበች ጊዜ ፤ “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወሽ” አላት። ማር 5፡34 ፤ ማቴ 9፡22

  ”እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፡፡”ሥራ 19:11 ፡፡ በእራፊ ጨርቅ ሲፈወሱ ስም እየተጠራ እንዳልሆነ እናስተውል ፡፡

  በተረፈ በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንዲያገለግሉ በማመናቸው የተጠሩና የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የተሰጣቸው ሁሉ ጌታችን ያከናወነውንና ፤ የበለጠ ተአምርም መፈጸም እንደሚችሉ ራሱ አስረድቶናልና (ማቴ 17፡2ዐ ፣ 21፡21 ፤ ሉቃ 17፡6) በአስማት ካልሆነ አይፈውሱም ማለት ፈሪሳዊና ጸሐፍትን መሆን ነው ፡፡

  በተጨማሪም ፈውስ ፈላጊው በድውይና በአጋንንት የተጠቃ ወገን ፣ አማኝ መሆን ወይም ለመሆን ፍላጐት ያደረበት ሊሆን ይገባዋል ፡፡ እምነትን በልቡ ያሳደረ ማንኛውም ሰው ፣ የጌታን ጨርቅ በመንካት እንደ ተፈወሰችዋ ሴት ፣ የሐዋርያቱን (ጳውሎስን) እራፊ ጨርቅ ቆርጠው በመውሰድ እንደዳኑበት ድውዮች ሁሉ በማንኛውም ቅዱስ ዕቃ ሊፈወሱ ይችላሉ ፡፡

  እባክዎትን መልስ ከመስጠትዎ በፊት ፣ የጻፍኩትን ሁላ ከመጽሐፍ ቅዱስዎ እያነጻጸሩ ያንብቡና ሊያስተምረኝ የሚችለውን ሃሳብ ያስቀምጡልኝ ፡፡

  በጭፍኑ መንገዳችሁ ማለታችሁ ስለማይቀር ፣ እንደፈቃዳችሁ ስሜን ዛሬ በወጉ አስተካክያለሁ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dar dar yemitilew wondime zare beeyesus sim aganint yemiyawetutin litiqawem new.Minew bizu bota metsihaf qidus beeyesus sim teamer endemidereg yetenagerewin ende Mk 16 yalewin alteqeskim. Bertana anibew. Do not defend blindly the tradition. Today it is different. Every body is reading her/is Bible at home. You no more cheat the people with fancy and many words, God is teaching the people about the truth.

   Delete
  2. አቶ ደምሰው መጀመሪያ በኢየሱስ ስም አጋንንት አይወጡም የሚል ቃል ከጽሁፌ ካለ አስነብበኝ ፡፡ ለምን በአእምሮአችሁ ያለውን እንደ ተፃፈ አድርጋችሁ ታሰፍራላችሁ? ቢያንስ ጽሁፌን ስጀምር የሰባውን አርድዕት ምስክርነት ስገልጽ ሉቃ 1ዐ፡17 ጠቅሼ በስሙ እንደ ፈወሱ ገልጫለሁ ፡፡

   በመቀጠል ደግሞ የጌታን ቃል አስረጅ በማድረግ በእግዚአብሔር መንፈስ እንደሚፈውስ የመሰከረውን አስነብቤአለሁ ፡፡ እርሱ እግዚአብሔር ሆኖ እንዴት እንዳይሉ ደግሞ ፣ ወረድ ብዬ ሴትየዋ ለአሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ከሰውነቷ ፈሳሽ ሲፈሳት የነበረውን በእምነት አልባሳቱን ነክታ መዳኗን ፣ ጌታም ኃይል ከኔ ወጥቷል ማለቱን ገልጫለሁ ፡፡

   በተረፈ ግን ስም ስም ለሚሉን ወንድሞች እምነትንም እንዳይረሱ ለማሳሰብ ጽፌአለሁ ፡፡ የጻፍኩት ተራ ወሬ ሳይሆን በወንጌል የሠፈረ ቃል ነው ፡፡ ለማቀናጀት እግዚአብሔር በፈቀደ ትናንሽ ቃላቶች ከራሴ አክያለሁ ፡፡

   አንተ ግን ስትወቅስ አንድ የመጽሐፍ ቃል እንኳን አልጠቀስክም ፡፡ እንዴት ያለ መጽሐፍ ቃል ለመከራከር ትደፍራለህ ? እኔም ለማታለል ሳይሆን ፣ እስከሚገባኝ ለማንበብ ስለምታገል አትዋሹኝ ፤ መጽሐፍ የሚለውን ቃልም እባካችሁ አታወላግዱ ለማለት ደፍሬአለሁ ፡፡

   መልካም የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እመኝልሃለሁ

   Delete
  3. I can tell you many versus and quote from the Bible. That does not make any smarter than who I am. Now I am more concerned about our humility. The spirit we express when defending our positions. Let it be in a humbled spirit we speak the truth, God's truth. Let's be more teachable than becoming more aggressive when defending our positions. On top of that whatever we speak let us speak according to God's word. (1 Pet 4:11). Let's learn from one another. I thing why Abaselama is there. God judges so let's leave that part to him. I am sorry if I wrongly understood you. Enimamar. Demissew, this is exactly my name.

   Delete
  4. ደምስው ስምህ እንደሆነ ከሁለት ዓመት በፊት ገደማ በቁም ፊደል ከጻፍከው አስተያየት አውቄአለሁ ፡፡ ከዚህ ቀደምም እንዲሁ በዛው አጻጻፍ ዓይነት አስተያየት የተለዋወጥን መሰለኝ ፡፡ አሁን ግን በትናንሾቹ ፊደሎች መጠቀም ጀምረሃል ፡፡ መማማር ያልከውን እኔም የማምንበትና የምቀበለው ነው ፡፡ ማንኛችንም ጻድቅና ሊቅ አይደለንም ፡፡ ከትናንሽ ድክመቶቻችን ጋር የሚሰማንን ፣ የተረዳነውን እናቀርባለን ፡፡ ከሚሰድቡኝ እንኳን እማራለሁ እላለሁ እንኳንስ በቀና አእምሮ ለሚቀርበኝ ፡፡ እናም የተቆጣሁና ኃይለ ቃል የተጠቀምኩ ከመሰለህ በጣም ይቅርታ ፡፡ ዕድሌ ነው መሰለኝ ሰዎች አይረዱልኝም ፡፡ እኔ በተቻለኝ ሁሉ እጅግ ዝቅ ብዬ በለስላሳ ቋንቋ መልዕክቴን ለመግለጽ እየሞከርኩ ነው ፡፡ ለማንኛውም አስተያየትህን ተቀብየዋለሁ ፡፡
   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
 3. please Aba Selamawoch, share these all anti Gospel actions. Geta Yibarkachihu. you can see this link.
  http://www.youtube.com/watch?v=Rk17aumME6U

  ReplyDelete
 4. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 8, 2013 at 4:18 PM

  Geta Eyesus yebarkachew Abaselamowech! Gena betho gude yewetale. Only by the name of lord Jesus can deliver evil sprits from any one caught by. Wow! Our church hid us lord Jesus, but the good thing by his time lord Jesus is preaching by electronics. Let me share you one story, at the Gena eve I discuss about bible with one lady at church. I was amazed when she told me that most orthodox Christian including the majority of bishops (kahenate) accepting Jesus is the only way to heaven.

  Thank you Abaselmawoch!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ልጄ “በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፥ ጥርሱንም ያፋጫል ይደርቃልም፤ እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፥ አልቻሉምም አለው።” ማር 9:18 ፤ ሉቃ 9:40
   በኢየሱስ ስም መፈወሳቸውን ከተናገሩና ከተደሰቱበት በኋላ ፣ ስለምን ይህኛውን ወገን በኢየሱስ ስም ለማውጣት አቃታቸው ? የኢየሱስ ስም አንዴ ያድናል ሌላ ጊዜ ደግሞ አያድንም ልትለኝ ትሞክር ይሆን ?

   Delete
  2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 9, 2013 at 7:56 AM

   ሉቃ 9:40 በኢየሱስ ስም መፈወሳቸውን ከተናገሩና ከተደሰቱበት በኋላ ፣ ስለምን ይህኛውን ወገን በኢየሱስ ስም ለማውጣት አቃታቸው ?
   Luke 9:40 doesn't say like that , the disciples couldn't cast out the evil, and Lord Jesus was mad about how his disciples were faithless and perverse generation. at Luck 9:42 Lord Jesus rebuked the unclean spirit and healed the child. I don't understand why you mentioned ሉቃ 9:40? I know you who you are? The father, the son and the holy spirit is not a merchandise. Do you understand??? Go to heal with your association and Girma!
   What is your intention to know about 9:40

   Delete
  3. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 9, 2013 at 7:56 AM

   Please edit the post I sent!
   Thank you!

   Delete
  4. ወንድሜ ሳታውቀው መናፍስት ጠሪ ሆነሃል ወይስ ከአሥራ ሁለቱ ፣ አንዱ አንተ ነህ ማለት ነው ? "Go to heal ለማለት የደፈርከው ፡፡ ኧረ ተው እንዲህ አይደለም ክርስትና የሚያስተምረን ፡፡ ራስህን በጣም አሳብጠኸዋል፡፡ ፈራጅ ነኝ እያልከኝ ነው ያለኸው እኮ ፡፡

   ምን የሚሉት የመታበይ መንፈስ ነው እንዲህ የሰፈረብህ ፡፡ ምናልባት ወደ አገር ቤት ከሄድክ እኝህ ሰው የሚሠሩበትን ጠይቀህ አንድ ነገር አድርግ ፡፡ ይኸ ዓይነቱ ነገር በብዙ ቦታ ተደጋገመብህ ፡፡
   በተረፈ ስለሁሉም እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ፡፡

   እኔ አሁንም እንኳን አልከፋም ፡፡ የሚያጽናናኝን ጌታ በልቤ ከትሜአለሁ ፡፡ ምላስህ ላይ አንጠልጥለህ በምታዝረከርከው ፣ የልብ ክርስትና እንደሌለህ ከቃልህ መረዳት ችያለሁ ፡፡ ስለ እኔ እምነትና መንገድ ከዚህ በኋላ አትጨነቅ ፡፡ አጉል መካሪም አትሁነኝ ፡፡

   Delete
 5. ለመሆኑ ye protestantochu pasteroch ከመምህር ግርማ አጋንንት በየሱስ/ሸሱስ ስም ሊያወጡ ሲሞክሩ በተግባር አጋንንቱ የርሱ አገልጋዮች መሆናቸውን ሲንግራቸው እርሳቸው ግን በኢየሱስ ስም ገስጸው ሲያስውጡት ለምን እይተመለከታችሁ አላመናችሁም? “አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች ፣ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን ፤ እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ። የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት። ክፉው መንፈስ ግን መልሶ ፤ ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ፤ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው። ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም።” ሥራ 19፡13-16የተባለውስ ቃል በተግባር bepasterochu lay ሲፈጽም እንዴት ለማመን ዘግያችሁ?ክርስቲያኖች የመሆናችን ምንጭ ክርስቶስ ነው። ክርስቶስ ደግሞ የተወለደው ንጽሕት ከምትሆን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ነው። ከድንግል ማርያም የተወለደው እርሱ እኛን በጸጋ ልጆች የምንባልበትን ስልጣን ሰጠን፤ ስለዚህም እናታችን ማርያም እንላለን፣ በሙሉ ጥብዐትም የቅድስት ማርያም ዘር ነን እንላለን። እንግዲህ ሰው የትኛውን ይጠራጠራል? በክርስቶስ ክርስቲያን መሰኘቱን ነው ወይስ ክርስቶስ ከቅድስት ማርያም መወለዱን? ወይንስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጡን? በአንድ ስፍራ ቅዱስ ጴጥሮስ ጸጋው ለሁሉም እንደተሰጠና የሚሰጥበትን ምክንያት ሲገልጽ “እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመነው ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን ያን ስጦታ ለእነርሱ (ለአሕዛብ) ከሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከልከል እችል ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?” ይላል። (ሐዋ11፥17) ዳግመኛም “ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ።” ይላል።(ሉቃ1፥30) በሌላም ስፍራ “ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።” ይላል። (1ዮሐ4፥3) የተባለውስ ቃል badebabay sishrut mnew zm alachu...”የመጀመሪያው ማንሳት የምፈልገው ነጥብ በኖር ሴት ዘር የላትም የሚለውን እውነት ነው:: ዛሬ የህክምናው አለም ሴት እንቁላል እንጂ ዘር የወንድ እንደሆነ በግልፅ አስቀምጦታል:: በዘፍጥረት ሶስት የተጠቀሰችው ሴት የዮሴፍ እጮኛ ማሪያም እንደሆነችና በድንግልናዋም ኢየሱስን እንደወለደች የዚህም ዘር ምንጩ እግዚአብሄር እንደሆነ ብዙ ማስረጃዎች ተፅፎልናል::በድንግልናዋ ምክንያት የማሪያም ማህፀን ደረቅና ባዶ ነበር:: እግዚአብሄር የራሱን ቃል ዘር በማሪያም ማህፀን ዉስጥ እንዴት እንደሚተክለው ኢሳያስ ከሩቅ ተመለከተ::”http://www.aklweb.com/forum/index.php?PHPSESSID=e21d4c881616b165bac97be3ddf04389&topic=228.0 እያሉ በተግባር የሴትዋና የልጁ ጠላት ሲሆኑ ምነው ዝም አላችሁ? BENATACHU YETNEKABETN ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ።YEMILEWN CHFN WUSHET ATWASHUN ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው። እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም። ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፥ እርስ በርሱ ተለያየ፥ እንግዲህ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች? እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች። ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል። ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።ማቴ ምዕራፍ 12 ቁር 22 እስከ 30ለመሆኑ MINERUN አጋንንት በሌላ MAJOR አጋንንት REPLACE በማድረግ የሚሰራው የነንትና መንፈስ ያዳኛችንን ስም እንዴት እንደሚጠሩት አላያችሁምን? ለመሆኑ ስሙንስ ብትክክል መች የጥሩትና....ሥሥሥስ ዉደቅቅ በእሱስ ስም...እያሉ አይደል እንዴ ልክ እንደኛዎቹ አውደንገስት ገላጭዎች በሚመስል ቃል አንዱን አጋንንት በ በሌላ አጋንንት የሚተበትቡት!!! እንርሱና የኛዎቹ DEBTERA አውደነገስት ገላጮች እና ጠንቋዮች መሆናቸውን አጣችሁትን? ለመሆኑ የነርሱ ልሳንና የኛው አውደነግስት ተምሳሳይ መሆናቸውን አስተውላችሁ ታውቃላችሁ?ታምፓርራምርርርርራድሶንትራዐ YEPASTEROCHU NEW ሜርርርርርርርርርርርርርርርርኤኮስ..... YE አውደንገስት ገላጭዎች – «ተመሳሳይ ክንፍ ያላቸው ወፎች አብረው ይበራሉ» እንደሚባለው ዓይነት!....BEKFL HULET EMELSBETALEHU YKOYEN

  ReplyDelete
 6. መምሕር ግርማ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ብዛት ካላቸው ምእመናን ENA PASTEROCH በናዝሬቱ ኢየሱስ ስም አጋንንት ሲያወጡ YOUTUBE LAY ተመልከቱ!ጸበሉ በተፈለገው ዓይነት መንገድ ይፍለቅ፡ በሰው ላይ የሚፈጥረው መንፈሳዊ ክስተት ኃያልና እውነትነት የተሞላበት ነው።
  ከፍተኛ መንፈሳዊ ጦርነቶች በሚካሄዱባት አገራችን ዲያብሎስ ህዝባችንን እያዘናጋ ወደርሱ ወጥመድ ለማግባት ሌት ተቀን ደፋ ቀና እንደሚል፡ ቤተክርስቲያኖቻችን፡ ጸበላችንና መስቀላችን ከርሱ ጦር መከላከያ ይሆኑን ዘንድ የተሰጡን ውድ በረከቶች መሆናቸውን የፈለግ ብትጮሁ አንስተዉም!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you, i see all and i believe Memihir Girma is the gift of Ethiopia by God.

   Delete
 7. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 8, 2013 at 5:04 PM

  To: "ምእመን ዘማኀበረ ቅዱሳን???"

  You were telling us that you’re not MK. why you had chosen to lie, Christian never lie. Not only I am upset that you lied to us but also I will never believe you. But, I thanks God that he gave me the wisdom to know about you and told you that you are the follower of the deceivers (MK) (http://www.abaselama.org/2013/01/blog-post_3.html#comment-form) Good to know about you! Who knows ande kene telewete yehonale, stay in this website.

  እባክዎትን መልስ ከመስጠትዎ በፊት ፣ የጻፍኩትን ሁላ ከመጽሐፍ ቅዱስዎ እያነጻጸሩ ያንብቡና ሊያስተምረኝ የሚችለውን ሃሳብ ያስቀምጡልኝ ፡፡

  What kind of answer are you expecting? Do you expect an answer who support your argument? I understand your intention, I gave you a short answer, I have not read like you had, but by the name of father, Son and holy sprite, the devil sprite only deliver by the name of Jesus.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምእመን ዘማኀበረ ቅዱሳንJanuary 8, 2013 at 8:57 PM

   ወንድሜ ቢገባህ ማኀበረ ቅዱሳን ማለትና መባል እንደ ንፍጣም የስድብ ቃል አይደለም ፡፡ ከአንድም ሁለት ጊዜ አባል አለመሆኔን ከነገርኩህም በኋላም ፣ ስምህን ሸሽገህ አሁንም ነህ በማለት ስላስቸገርከኝ የወሰድኩት ርምጃ ነው ፡፡ ማኀበረ ቅዱሳን በመሆንና ባለመሆን መሃከል ልዩነቱን ፈጽሞ አላወቅሁም ፡፡ የገባህ ነገር ቢኖር አስረዳኝ ፡፡

   ስለስሜ መቀየር ምክንያት አስረጅ
   http://www.abaselama.org/2013/01/blog-post_6.html#more
   Anonymous January 7, 2013 7:17 AM
   Your comment and Kebede Bogale very similar. One Mheber kidusan teketaye with two languages

   ለዚህ ሰው (ምናልባትም አንተው ትሆናለህ አኖኒመስ ያልከኝ) የሰጠሁት መልስ በማኀበረ ቅዱሳን ስም ነው ፡፡

   በተረፈ የተጻፈውን በሙሉ ሳታነብ ፣ በደመ ነፍስ የምትጽፍ መሰለኝ ፡፡ ስለ ስም አጠቃቀሜ ምክንያት ገልጨላችሁ ነው ደስ እንድትሰኙ ፈቃዳችሁን ለማሟላት ይህነን የተጠቀምኩት ፡፡ ባታስተውለው ነው እንጅ የጽሁፌ የመጨረሻ ቃል እንዲህ ይነበባል ፡፡
   “በጭፍኑ መንገዳችሁ ማለታችሁ ስለማይቀር ፣ እንደፈቃዳችሁ ስሜን ዛሬ በወጉ አስተካክያለሁ ፡፡”

   ወንድሜ ከቻልክ ይልቁን የአንተን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኝነት አስረዳኝ ፡፡ ዶግማና ቀኖናዋን ሳያከብሩ የኦርቶዶክስ ተከታይ ነኝ ማለት ማፌዝና ማታለል ነው ፡፡ ስለሆነም በትልቁ እየዋሸህ ያለኸው አንተ ነህ እንጅ እኔ አይደለሁም ፡፡ ምን ለማትረፍስ ይዋሻል?

   የወንጌልን ሙሉ ቃል የምታምን ከሆነ ፣ የጻፍኩትን ካልተስማማህበት ለመቃወም ቃል አንሳ ፡፡ በጭፍን እምነት ሳይኖራቸውና የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሳይጠቀሙ ኢየሱስ ፣ ኢየሱስ ለማለት ያህል የማያምኑ ሁሉ እንዲያ ማለታቸውን አስነብቤሃለሁ ፡፡
   ስሜ ከሆነ የተጻፈውን እንዳታነብ የሚያደርግህ ፣ ወደፊት ደግሞ በአናኒመስ ስም እሞክርልሃለሁ ፡፡ ግራ ገባኝ ፡፡

   Delete
  2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 9, 2013 at 10:06 AM

   ስሜ ከሆነ የተጻፈውን እንዳታነብ የሚያደርግህ ፣ ወደፊት ደግሞ በአናኒመስ ስም እሞክርልሃለሁ ፡፡ ግራ ገባኝ ፡፡ I read some your comments written with anonymous. Geta Eyesus ant laye yalewen wonglen yemitamemwen menfese yegesesew.Beleh beleh degemo ye Girma degafe honke? Begeta seme!

   Delete
  3. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 9, 2013 at 10:10 AM

   Don't call me ወንድሜ. BE Eyesus yemaymen wondeme lehone aychelem ( you can't be my brother unless you believe on the Lord Jesus)

   Delete
  4. ምእመን ዘማኀበረ ቅዱሳንJanuary 9, 2013 at 12:38 PM

   Beleh beleh degemo ye Girma degafe honke? Begeta seme!

   ግለሰቡ ጋር አትውሰደኝ ፤ እኔ እግዚአብሔርን ነው በሠራው ሁሉ የማመሰግነው ፡፡ ከላይ ገልጫለሁ ፡፡ እግዚአብሔር ፈቃዱና ፍላጐቱ ከሆነ በደረቀ አጥንት ይፈውሰናል ፡፡ ያንን መቀበልና ማመን አጥንቱን እደግፋለሁ ማለት አይደለም ፡፡ ደግሞም እንዳየሁት በኢየሱስ ስም ካሉ በኋላ የሌሎች ቅዱሳንን ስም ይጠራሉ ፡፡ እግዚብሔር ከአንቺ ጋር ነው (ያለ ጊዜ ገደብ) የተባለች የጌታችን እናት ስም ስለተጠራ እኔን በምንም አያመኝም ፡፡ እንዲያውም ጌታ የቅዱሳኑ ስም እንዲወሳ ፈቅዷልና ምክንያት ፈጥሮ እንዲመሰገኑ ሲያደርግ እኔም እጠነክራለሁ ፡፡

   ወንድሜ ፣ ወንድሜ የምልበት ምክንያት ስለ ክርስትናዬ ስል ነው እንጅ በተፈጥሮና በምድራዊ መልዕክቱ አይደለም ፡፡ ቃሉን ላለማንበብ መብትህ ነው ፡፡ እኔም ደግሞ ቃሉን የመጠቀም መብት አለኝ ፡፡ ክርስትናዬን ሰዎችን ለማስደሰት ስል የምቀያይራት ፤ ካገኘሁት ጋር የማመሳስላት አይደለችምና አሁንም ወንድሜን ይቅርታ እጠይቃለሁ ፡፡

   መልካም ውሎ

   Delete
  5. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 9, 2013 at 2:29 PM

   ምእመን

   I am tell you again, if you don't accept that Jesus is your only savior and the father, you can't be my brother.

   እንዲያውም ጌታ የቅዱሳኑ ስም እንዲወሳ ፈቅዷልና ምክንያት ፈጥሮ እንዲመሰገኑ ሲያደርግ እኔም እጠነክራለሁ ፡፡
   where is that in the bible or in the Gedele(Ye debetra book)?
   Delete
  6. “I am tell you again, if you don't accept that Jesus is your only savior and the father…”
   የማይተማመን ምንድር በየጉድባው ሲማማል ይውላል ነው ያድራል የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ያለን መሰለኝ ፡፡ ምስክርነቴን ስላልተቀበልከው ብደጋግመውም አንግባባም ፡፡ በተረፈ እኔ ወንድሜ ለማለት ፈቃድ መጠየቅ ያለብኝ አይመስለኝም ፡፡ አንተ ወንድምነቴን ያለመቀበል መብትህን አከብርልሃለሁ ፡፡ የኔንም ደግሞ በተቻለህ ሁሉ ሞክርልኝ ፡፡

   በተረፈ ጌታ ስማቸው እንዲታሰብ የፈቀደበት ምዕራፍና ቁጥር ይኸ ነው ፡፡
   ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማቴ 10:41

   ከብሉይ ኪዳን ደግሞ እነዚህ ተቀራራቢዎች ስለሆኑ አንብባቸው ፡፡
   በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ። ኢሳይያስ 56:5፤

   የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፤ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ። ሚልክ 3፡16

   Delete
  7. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 9, 2013 at 7:27 PM

   ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማቴ 10:41

   Do you think your father "Aba Girma" is a prophet? That is why you accepting him as prophet? KENTU!

   Delete
  8. ወንድሜ እንዴት እንደማስረዳህ ጠፍቶኛል ፡፡ እግዚአብሔር በአህያ ፣ በውሃው ፣ በጨርቅ ፣ በሌላም ነገር ፣ እንዲያውም ይግረምህ ብሎ በጥላ ሳይቀር ተአምር ፈጽሟል ፡፡ አባ ግርማ ማለት ለእኔ ከእነዚህ ከዘረዘርኳቸው የእግዚአብሔር መገልገያዎች እንደ አንዱ ነው ፡፡ እርሱን ትተህ እግዚአብሔር የሚፈጽመውን ሥራውን ተመልከት ፡፡ ሽባ ሆና ለረጅም ዓመታት ሃኪም ዋጋ የላትም ብሏት በእንፉቅቅና በተሽከርካሪ ወንበር የምትኖረውን ወጣት ፣ እንደ ጌታ ተነሽ ተራመጅ ብሎ ወንበሯን እየገፋች ስትሄድ በተንቀሳቃሽ ምስል አይቻለሁ ፡፡ ይኸ ጥበብ የመጣው ከርሱ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነው ፡፡ እግዚአብሔር ሊጠቀምበት ስለፈለገ ጸጋውን አጐናጽፎታል ፡፡ እኔና አንተ እርሱ የሚጠቀምበትን መቁጠሪያ ይዘን ሰው እንፈውስብህ ብንል አይሠራልንም ፡፡ ምናልባት እንፈነክትበት ወይም ገላን እናበልዝበት ይሆናል ፡፡ ለርሱ ግን ሥልጣን ተሰጥቶታልና ይፈውስበታል ፡፡ ስለዚህም እንደ መገልገያ ቁስ አድርገህ ቁጠረው ፡፡ ክብር ለርሱ ሳይሆን ፣ እርሱን እንዲህ ላስታጠቀው ለፈጣሪአችን ስጥ ፡፡ በተረፈ ስም ያልኩህ ለመፈወስ የሚጠራቸውን ስሞች ነው ፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስን ስም ከጠራ በኋላ የቅድስት ድንግል ማርያምን ፣ የቅዱሳን መላእክትንና የጻድቃኑን ይጠቀማል ፡፡ ያን ማለቴ ነው እንጅ ነቢይ ሆኗል ብዬ አልጻፍኩም ፡፡

   Delete
 8. መምህር ግርማ ቢያገኙህ እንዲህ እውነታውን እየጋረደ የሚያሳስትህን መንፈስ በኢየሱስ ስም ይገስጹልህ ነበር ፡፡yalmknyat aydelem endih yalkuh.endtdn new!yedanu bzu nachew.....ex.. The pastor, based in Hararge, eastern Ethiopia, reveals the deleterious plan of protestants on ETOC. Being famous in the town, he was abused by protestants to implement their destructive mission. He brought back all the materials which originate from USA. These materials are prepared to deceive and wage religious war on ETOC. Some of them are New King James version bible, many CDs and manuals partly prepared by him and are planned to be distributed. He explained why they hate Saint Mary, the cross and the arc of covenant. Later in his life his two legs were crippled and he has to use a stick to walk. watch memhr grma Part 15 (disk B)at youtube.

  ReplyDelete
 9. A graduate of the Addis Abeba University Law School ,Fikerte Tibebu, has been healed from blindness after being baptised with Holy Water in St. Stephen's Church of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church ,Addis Abeba , Ethiopia. Fikerte was blinded some 19 years ago when she was a 7th grade student . Before joining Ethiopia's Human Right Commission as a Legal Expert, she worked at different departments of the Addis Abeba City Administration.
  Many couldn't beleive their eyes when they noticed the lady they knew for many years writing with a braille and walking with a stick, suddenly running.

  live scene of the the baptism and ''exorcism'' explains that she has been blind for almost two decades and able to see after being baptised in St. Stephen's Church of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church ,Addis Abeba , Ethiopia.

  This is a miracle! It has been also proved by the modern world science .

  Her last message to the Radio audience and people at large was unifingly principled "May the Creator visit all those people who are worried like me , according to their own faiths/religions! "

  When i was at home , I have been able to see first hand similar types of religious miracles in Entonto St.Mary Church, one of the oldest churches in north of Addis Abeba , built by King Menelik II and his wife Empress Tayetu a century and half ago.

  Since coming to Europe I have been hearing of similar miracles happening in St. Stephen Church in the middle of Addis Abeba.

  The head preacher and baptiser ,now ''Priest'' according to sources, @Girma Wondimu @, has been the person religiously helping the process of healing and cure in St. Stephen Church . There are around two dozens of video CDs produced so far showing the types,means,and ways of healing by the same Priest exorcist . All these miraculous healing are done according to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's ways and practices .
  It was part of my plan to interview Priest Girma Wondimu in the past few months ,tough. I promise to interview him as soon as possible and produce a good report.

  Until then ,I leave you with an article I wrote some five years ago about some of the amazing miracles i witnessed in the Entonto St. Mary Church.
  I had witnessed and heard of testimonies of people cured from various diseases such as HIV/AIDS,Cancer and so on and also people were able to be healed from complete blindness,and other disabilities in the Church of Entoto St.Mary .http://ethiopianorthodoxmiracles.blogspot.com/search/label/The%20story%20of%20Fikrte%20Tibebu

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዚአብሔር ይባርክህ
   ስለ ምስክርነት ቃልህ እናመሰግናለን

   Delete
 10. ለመሆኑ ዝነኛው fake ፈዋሽ ፓስተር ዳኔል /ጋኔል/ በቅርቡ ራሱን እንደ መልከጽዴቅ ለዘላለም ካህን ነኝ (በሌላ አባባል ኢየሱስ ነኝ) ማለቱንስ ስእምታችሁ ይሆን? በመልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ የተጠራው ይህ ሰው ለውደፊት ምን እንደሚል እግዜር ይወቀው!ብቻ አላማየ የነንትናን የፈውስ (አጋንንት)አዙሪት እና mindgame ena psycho እንድታስተውሉት ነው!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ykrata aba selama betam slanadedachihugh besmiet slemayagebagh guday tsafku.lelaw degmo smachew mokshe yhun alawkm le sebawi mebt yemitagel paster daniel yemibal endale awkalehu mnalbat yetsadebkut ersun kehone tenberkkie ykrta eteykalehu!

   Delete
  2. thou shall not lie = thou not kill !!
   may God forgive u

   Delete
  3. wushet altsafkum !!!100 argagtlhalehu በመልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ የተጠራ paster ale yawum badebabay beawaj .yikrta yteykut besme mokshe shtet fetsme kehone bicha new!!!

   Delete
 11. የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ መሰረት ላይ የታነፀች ስልሆነ በእውነት ለሚያምን ሰው ፡የቤተክርስቲያኑ አጥር ፣ አፈሩ ፣ ቅዱሳን ስእላት ፣ንዋየቅዱሳናቱ ፣የቅዳሴው ድምፅ ፣የዝማሬው ድምፅ ፣ፀበሉ፣ ወዘተ ፈውስን ሲሰጡ ቆይተዋል ።
  ከጥንት ጀምሮ አባቶቻችን አይደለም ለክርስቶስ ባርያዎች ሆነው ሲያገለግሉ በነበረበት ስም ፣በፀሎት እቃቸው ማለትም በመቀማቸው ፣ በመቁጠሪያቸው ፣በፂማቸው፣በልብሳቸው ሁሉ አጋንንትን ሲያስሩና ሲያወጡ ኖረዋል አሁንም በየቤተክርስቲያናችን በፀበል ቦታ እና አውደምህረት ላይ ከክርስቶስ በተሰጣቸው ፀጋ አባቶቻችን ይህን ያደርጋሉ ።ይህን ካላመንን ከማን ወገን ነን ብለን እራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል ። እምነትን ይጨምርልን ፡
  ወስብሀት ለእግዚአብሄር ።

  ReplyDelete
 12. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 8, 2013 at 8:57 PM

  Even you can see more miracles by Ato Grima that doesn't considering him a christian. This the last day as the bible told us on Luke 21 , for example in Luke 21-17-18 the bible said:" you shall be hated of all men for my name's but there shall not an hair of your head perish." About Ato Girma the bible at Luke 21-8," take you be not deceived: for many shall come in my name , saying that I am Christ."

  Please read Luke 21 it is the last day for example the true bible preachers in Ethiopia and abroad getting hard time because of preaching Lord Jesus while Ato Girma is praising like a God.

  Eyesus Geta Newe!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜና ጌታዬ ጌታ የመጨረሻውን ቀን እኔም ሆንኩ መላእክት አያውቁም እያለን ፤ አንተ አውቃለሁ እያልኩ ነውና ራስክን አስተካክል ፡፡ መጽሐፉ ከተጻፈ ሁለት ሺህ ዓመት ሆኖታል ፡፡ በሃይማኖት መለያየት ሁለት ሺህ ዘመን ሁሉ የነበረ ነው ፡፡ ታድያ ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረና የመጨረሻው ነው የመጨረሻው ነው ያስብላል ፡፡ የመጽሐፍን ቃል አታምን ከሆነ አላምንም በለን

   Delete
  2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 9, 2013 at 11:13 AM


   The disciples of Jesus asked the Lord Jesus about the last day and he answered: please! read (Matthew 24) ምእመን ዘማኀበረ ቅዱሳን.

   Delete
  3. አንተ እውነትም በጣም ብልጥ ሰው ነህ ፡፡ አኖኒመስ እኔ መሆኔን እንዴት አወቅህ እባክህ ? እንዲህ የምልህ ስቀልድህ ነው ፤ እንድታስበኝ መንገድ የሰጠሁህ እኔው ነኝ ፤ ሁለት ሺህ ዘመን እያልኩ ፡፡ ደግሞ በዚህ ምስክርነቴ አጉል እንዳላሳስትህ ፈራሁ ፡፡

   ማቴዎስ 24፡4 “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።” ብሎናልና ጌታችን ፤ እንዳንስት መጠንቀቅ ያስፈልገናል ፡፡
   በቁጥር 24 “ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።" ይላል ፡፡ እስቲ እንግዲህ እኔ ኢየሱስ ነኝ ያሉና ያስተማሩትን ሐሳዊ መሲሖችን ቁጠርልኝ ፡፡

   በቁጥር 32 ደግሞ “ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤” ይኸን ማለቱ አንድ ወይም ሁለት ሰው ምልክቶቹን ይረዳል ማለት ሳይሆን በለሷን ያየ ሁሉ ያውቃል ማለቱ ነው ፡፡ ስለዚህም የሚያምኑትም ሆነ የማያምኑት ምልክቶቹን በማየት ቀኑን ይለዩታል እንጅ አንድ የተሰቀለው ብቻውን የመጨረሻ መሆኑን አይረዳም ማለቲ ነው፡፡ ቀኑ ደርሷል እያልን እንዲያው በመሰል እንዳንጨነቅ ደግሞ በቁጥር 36 ላይ “ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።” በማለት ከቁጥጥራችንና ከግምታችን ውጭ መሆኑን ያስረዳናል ፡፡

   እንደ አንተ ቃል ቢሆን ግን ፣ በነገርከኝ ቁጥር አንድ ሦስት ጊዜ መጸዳጃ ቤት በተመላለስኩ ፤ ለማረፍም ወደ አልጋዬም መሄድ በተውኩኝ ነበር ፡፡ ወንድሜ “አትፍራ ፤ እመን ብቻ ፤ ትድናለህ” በሚለው የመጽሐፍ ቃል ተጽናና ፡፡ ማር 5፡36 ፤ ሉቃ 8፡5ዐ ፤ ሥራ 16፡31

   ከመዝሙር መጽሐፍም ይህንን ደጋግመህ በለው ፍርሃትህ ይወገዳል ፡፡
   “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል። ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።” ምዕራፍ 23፡1-4

   Delete
  4. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 9, 2013 at 7:24 PM

   በቁጥር 24 “ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።" ይላል ፡፡ እስቲ እንግዲህ እኔ ኢየሱስ ነኝ ያሉና ያስተማሩትን ሐሳዊ መሲሖችን ቁጠርልኝ ፡፡

   Eventually, You worshiping Grima more than Lord Jesus,you and your likeness.

   Delete
  5. እኔና ቤቴስ እግዚአብሔርን እናመልካለን ፡፡ አትጠራጠር ፡፡

   Delete
  6. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 10, 2013 at 12:32 PM

   እኔና ቤቴስ እግዚአብሔርን እናመልካለን ፡፡ አትጠራጠር ፡፡

   I will.

   Delete
 13. ወንድሞቼና እህቶቼ ጊዜዉ እርስ በራሳችን የምንነቋቀርበት ሳይሆን
  አምላካችንን በቅድስናና በንስሃ የምንጠብቅበት መሆን አለበት።በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ ይላል ጌታ ኢየሱስ። ጎበዝ እንንቃ
  የሐዋርያት ሥራ
  ምዕራፍ 37 ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ፥ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት። ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉአቸው።

  38 ጴጥሮስም። ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።

  40 በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና። ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ ብሎ መከራቸው።

  41 ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤

  42 በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 11, 2013 at 9:40 AM

   AnonymousJanuary 9, 2013 8:29 AM

   God Bless You! my brother.Kalehwiot Yasemalen.

   Delete
 14. God blese CHORRA, for teaching the gopspl without any mention of any individual's name, gossiping does not glorify God, please some ABASELAMA's writers has to see themselves on the light of God's word(the bible)stay blessed

  ReplyDelete
 15. I am just wondering why the fight is between the two who are claiming to believe in Jesus. I think the struggle is to defend where the truth lies. Actually you do not argue for God. He himself knows the truth. Where is the love in our discussions? What I saw was simply "ene ebelit ene ebelit" kind "mugit". There is no humility in our writings. If we had that spirit we would be filled by the notion that my brother is better than me and go on respecting others. As I was reading your comments I realized that nobody dares to come to the other position. If that is so if we cannot win one to the other side. We better humble ourselves before God let him teach us the truth. Insulting one another does not help much.

  ReplyDelete
 16. ወንድም Demissew ከላይ ባስቀመጥኩት ጽሁፍ አስቀይሜህ ቢሆን ለመካስ በማለት ይህን ለመማማር አቅርቤአለሁ ፡፡

  ሳይበጠበጥ አይጠራምና ፣ እርስ በርሳችን ለመግባባት እንድንችል በነገር መፋጨቱ የሚቀጥል ይመስለኛል ፡፡ ጊዜ ይወስድ እንደሁ እንጅ በእርግጠኝነት የምተነብየው በሂደት ሁላችንም አንድ እንደምንሆን ነው ፡፡ እስከዚያው ድረስም ሲወቅሱህ ፣ ሲቆጡህና ሲዘልፉህ ፣ ጽድቅህን የምታስብ ከሆነ ትጽናናለህና ክፉን በክፉ አትመልስም ፡፡ ሆኖም ግን ሁል ግዜ በሰዎች ጥፋት መጽደቁ ህሊናህን ስለሚከብደው ፣ ድክመታቸውንና ስንፍናቸውን እያሳየህ ፣ እንዲያርሙና እንዲታረሙ ትመክራለህ ፡፡ ይኸኛውን ስታደርግ ደግሞ ሁለተኛውን ጽድቅ በራስህ በጐ ሥራ አገኘኸው ያሰኛል ፤ እንደ የታረዘውን ማልበስ ፤ የተራበውን ማብላት ያህል ዓይነት ፡፡ አንተ ያነሳኸውን የአንድነት ቃል ለመፍጠርና መመካከር ያስችለን እንደሁ በማለት አሰብ አድርጌ ያመጣኋት ጥንቅር እንዲህ ናት ፡፡

  በኢየሱስ ስም መፈወስ ይቻላል ፤ ይኸን ጥያቄ ውስጥ ማንኛችንም ብንሆን አናስገባውም ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ስም ውጭ አብረውት የሚጣመሩ ጉዳዮች ወይም መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች አሉ እላለሁ ፡፡ እነዚህም

  1. እምነት - አገልጋይም ሆነ ተገልጋይ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ማመን ያስፈልጋቸዋል ፡፡ ሳያምኑ መፈወስና መፈወስ (አንዱን ጠበቅ ሌላውን ላላ) ሊኖሩ አይችሉም ፡፡ ያለ እምነት ስሙ ያድናልና ብለው ቢሞክሩት ትርፉ ድካም ብቻ ነው የሚሆነው ፡፡ ከዚህ ባለፈ ደግሞ ተገልጋዩም በኢየሱስ ስም እድናለሁ ብሎ ማመን ይጠበቅበታል ፡፡ መጽሐፍም የምትፈልጉትን በጸሎት ሆናችሁ ለምኑ ፤ እንደ አገኛችሁትም እመኑ ይለናልና መዘንጋት የለብንም ፡፡

  2. ለአገልግሎት መመረጥ ወይም መጠራት - ይኸኛው ሙሉ ለሙሉ አገልጋዩን የተመለከተ ነው ፡፡ በቅድሚያ በመንፈስ ቅዱስ ሳይጠሩ ለማገልገል መፍጨርጨር መዋረድን ያስከትላል ፡፡ የተጠሩበትንም በሥርዓቱ ሳይለዩ የመጽሐፍ ቃልን ስለተረዱ ብቻ መደናበርም ገደል ይሰዳል ፡፡ ስለዚህም አገልጋዮቻችን ለምን ለምን እንደ ተጠሩ ወይም እንደ ተመረጡ ማወቅ ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው ፡፡

  3. የጸጋ ስጦታን ማግኘት - ይኸም ቢሆን ከሁለተኛው ነጥብ ጋር የተያያዘ ስለሆነ አገልጋዮችን የሚመለከት ነው ፡፡ ለአገልግሎት የተመረጡ ወንድሞችና እህቶች የጸጋ ስጦታቸውን በውል ማወቅ ይገባቸዋል ፡፡ የስብከቱን ጸጋ ፣ የመጽሐፍ ቃልን ስለተረዱና በስሙ መፈወስ እንደሚቻል ስላወቁ ብቻ ፣ ለመፈወስ ቢጠቀሙበት አይሠራም ለማለት ነው ፡፡ ይኸ አለመሳካት ደግሞ የጥርጣሬ እንክርዳድን በልብ ውስጥ ይተክላልና ራሳችንን ባልሆነው ሁሉ ላለመፈተን እንጠንቀቅ ፡፡

  ከነዚህ ሦስት ጥምረቶች ውጭ እንዲያው በኢየሱስ ስም መፈወስ ይቻላል ተብሏልና ፣ እኔም እንዲሁ ብሎ የሚያምን ወገን ካለ ፤ ሊያስረዳኝና ሊያስተምረኝ ዝግጁ ነኝ ፡፡ በአገራችንም በየሜዳው የወደቁ አያሌ ሕሙማን ይገኛሉና ወጥታችሁ በተግባርም አሳዩንና እንታረም እላለሁ ፡፡

  አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
 17. mekuteryaw yeselot hayel yalew new bezu sewoch bemekuterya egzeio meharne kristos yelubetal 41 gize belibu kin ena yewah yehone sew bekristos sim hayel yegnal u dont need to be a professor to caste out devils u pents are really jokers of the century american style of christanity is lie yegna americans kkkkkk

  ReplyDelete