Thursday, February 28, 2013

ኦርቶዶክሳውያን ብፁዕ አቡነ ማትያስን 6ኛ ፓትርያርካቸው አድርገው መረጡ

የማኅበረ ቅዱሳን መንደር በሐዘን ተውጧል
የብዙዎችን ከፍተኛ ትኩረት ስቦ የሰነበተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ብፁዕ አቡነ ማትያስን በከፍተኛ ድምፅ በመምረጥ ተጠናቀቀ፡፡ ሁሉም የየራሱን አባት ለማስቀመጥ ባለ በሌለ ሀይሉ እንደተንቀሳቀሰ በተወራለት በዚህ የፓትርያርክ ምርጫ በተለይ ማኅበረ ቅዱሳን በዋናነት አባ ማቴዎስን ለማስመረጥና አቡነ ማትያስ እንዳይመረጡ ለማድረግ ከ3-10 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ ሲንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው የታመኑ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ እንቅስቃሴውም የራሱ እጩ የሆኑትን የአቡነ ማቴዎስን ሰብእና አለቅጥ በማጋነን ላይ የተመሠረተ ብቻ ሳይሆን መንበሩን ይይዙብኛል ብሎ በከፍተኛ ሁኔታ የሰጋቸውን ብፁዕ አቡነ ማትያስን ለማስጠላት ከፍተኛ በጀት መድቦ በከፍተኛ ሁኔታ መንቀሳቀሱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ማቅ ብፁዕ አቡነ ማትያስን ለማስጠላት የዘረጋው ወጥመድ ግን እርሳቸውን ከማስጠላት ይልቅ ትልቅ ተቀባይነትን እንዲያገኙ በከፍተኛ ሁኔታ ረድቷል ነው የተባለው፡፡ ይህም ማቅ ተሰሚነቱ እየቀነሰ መምጣቱን ነው የሚያሳየው ተብሏል፡፡ ማቅ በብዙዎቹ ጳጳሳት ዘንድም ተሰሚነቱ እየቀነሰ እንደመጣ የሚናገሩት ምንጮች ቀድሞም ቢሆን አቡነ ጳውሎስን ለመጣል እነአባ ሳሙኤል የጎነጎኑትን ሴራ ለማጠንከር ያበሩ አባቶች ሁሉ ከእርሳቸው ማለፍ በኋላ ከማቅ ጋር ተባብረው የሚሰሩበት የጋራ ነገር በማጣታቸው ሊተባበሩ አልቻሉምና ብዙዎቹ ማቅ አቡነ ማትያስ እንዳይመረጡ ባደረገው የሎቢ ስራ ተባባሪ አልሆኑም ተብሏል፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው ነው የቆሙት፡፡

በስደት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የ ፓትርያርክ ምርጫ አስመልክቶ መግለጫ አወጣ

መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

Wednesday, February 27, 2013

ማኅበረ ቅዱሳን መራጮችን “ሎቢ” ሲያደርግ ዋለ

በ6ኛው የፓትርያርክ ምርጫ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ የሚገኘውና በወኪሎቹም በኩል ብዙም ያልተሳካለት ማቅ ለምርጫው አንድ ቀን በቀረበት ዕለት ከየአህጉረ ስብከቱ የመጡትን መራጮች በምግብ ቤቶቹ ምሳና እራት በመጋበዝ ለማኅበሩ እጩ ለአባ ማቴዎስ ድምጽ እንዲሰጡ እያግባባና “መንግስት ድምጽ ለአቡነ ማትያስ ስጡ ብሎናል በሉ” እያለ ባሰማራቸው ሰላዮቹ አማካይነት የማግባባት ስራ ሲሰራ መዋሉን የሎቢው ሰለባ ከሆኑት መራጮች አካባቢ የደረሰን ዜና ያመለክታል፡፡ ሎቢ ከተደረጉት መካከል አንድ የሀገረስብከት ስራ አስኪያጅ ሎቢ ሊያደርጋቸው ላሰበው የማቅ ሰው “እናንተ የምትሉት ነገር አልገጠመኝም፡፡ እናንተ በየድረገጹ ከምትሉት ውጪ ከመንግስት በኩል እገሌን ምረጡ የሚል ነገር አልሰማሁም፡፡ ደግሞስ መንግስት ፈጸመ ያላችሁትን ስህተት እናንተ በግልጽ ለምን ትደግማላችሁ? ስማ እኔ እገሌን ምረጡ ልል አልችልም፡፡ ሁሉም የሚመርጠውን ያውቃልና እናንተ ለምን አርፋችሁ አትቀመጡም” ማለታቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡

Monday, February 25, 2013

ሲኖዶስ ለእጩነት የቀረቡትን 5 ሊቃነ ጳጳሳት ስም ይፋ አደረገ

በአባ ሳሙኤል የምረጡኝ ቅስቀሳ የታጀበው የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ በአጠቃላይ ከተጠቆሙ 36 ጳጳሳት መካከል በየደረጃው ማጣራት ከተደረገ በኋላ የ5ቱን እጩዎች ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡ በዚሁ መሰረት ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ ብፁእ አቡነ ኤልሳዕ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እና ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እጩ ሆነው መመረጣቸውን የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁእ አቡነ እስጢፋኖስ በመግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ብፁዕነታቸው እንደገለጹት ለእጩነት ከቀረቡት ጳጳሳት መካከል መስፈርቱን ያሟሉትን 5ቱን ኮሚቴው አጣርቶ ካቀረበ በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን ገልጸዋል፡፡

Saturday, February 23, 2013

አባ ሳሙኤል ዕጩ አለመሆናቸውን ተከትሎ ሲኖዶሱን ሲበጠብጡ ዋሉ

አባ አብርሃም መንግስት ጣልቃ ገብቷል ሲሉ የከሰሱ ሲሆን፣
«አቡነ ማትያስ በተሀድሶ ብሎግ ላይ ተወድሰዋልና ሃይማኖታቸውን እጠረጥራለሁ ተሀድሶ ይሆናሉ» ብለዋል፡፡

ስለራሳቸው ብዙ ያወሩትና ያስወሩት፣ በእርሳቸው ላይ ግን ብዙ የተወራባቸው፣ ድፍረት እንጂ እውቀት የሌላቸው (ትምህርት ከ7ኛ ክፍል እንዳቆሙ ይነገርላቸዋል፤ yes እና ok ነው የሚያውቁት)፣ ዓለማዊነት እንጂ መንፈሳዊነት የማይታይባቸው (ሌላውን ሁሉ ትተን እኔን ምረጡኝ ብሎ ዘመቻ ማድረግ በየትኛውም መስፈርት ዓለማዊነት ነው) ትእቢት እንጂ ማስተዋል የሌላቸው አባ ሳሙኤል እንኳን ፓትርያርክ ሊሆኑ በእጩነትም ለመቅረብ መስፈርቱን ስላላሟሉ በአስመራጭ ኮሚቴው በኩል ለምርጫው በእጩነት ሳይቀርቡ መቅረታቸው ዛሬ በተጀመረው ስብሰባ ላይ ተመልክቷል፡፡ ከ5 መቶ ሺህ ብር በላይ ቤተ ክርስቲያን በሶማሌና በአፋር ክልል ለልማት እንድታውለው በድጋፍ የተገኘውን ገንዘብ ስልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም ወጪ አድርገው ለምርጫ ቅስቀሳ ቢያውሉትም፣ ከተራ ተላላኪዎቻቸውና ጉቦ አቀባባዮቻቸው እስከ ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎች ብዙዎችን ገዝተውበት አስመራጭ ኮሚቴውን በጠቋሚ ብዛት ቢያጨናንቁትም (ከ9000 ጠቋሚዎች 7200ው የአባ ሳሙኤል ደጋፊዎች ናቸው) «መጠቆም መታጨት አይደለም» የሚለውን መርህ ይዞ የእጩዎችን የሕይወት ታሪክ ሲያጣራ ከቆየ በኋላ የኮሚቴውን ሥራ ብዙ ልቦለድ ታሪኮችን እየጨመሩ ለሀራ ዘተዋህዶ በማቀበል ድረጹን ስተው ያሳቱት የቅርብ ጊዜው የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆኑት የጭድ ተራው የመንደር ቀኛዝማች ኃይሉ ቃለ ወልድ ለአባ ሳሙኤል አድረው ፈቃደኛ ባይሆኑም አባ ሳሙኤል ለእጩነት መቅረብ አይችሉም ብሏል፡፡ ከተጠቆሙት መካከል 5ቱን ብፁዕ አቡነ ማትያስ  ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እና ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕን ለይቶ ለዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ ያቀረበ ሲሆን በአባ ሳሙኤልና በአባ አብርሃም ተቃውሞና በብዙሃኑ ጳጳሳት ድጋፍ እጩዎቹ አልፈዋል፡፡

Friday, February 22, 2013

ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር የረታ ይቅርታ!

ከዕንቁ  መጽሔት የተወሰደ - ጸሐፊው በፍቅር ለይኩን፡፡

በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ጓደኞቿና የነፃነት ትግሉ አጋሮቿም፡- ‹‹እናዝናለን ኤሚፍቅርሽ፣ ርኅራኄሽ፣ ለሰው ልጆች ነፃነትና መብት መከበር ያለሽ ጽኑ አቋም በልባችን ለዘላለም ይኖራል፡፡ ትግላችን እንዳቺ ያሉ የእውነት፣ የፍትሕ ጠበቃዎችንና ሐቀኞችን በአጥፍ ጨምሮ ይቀጥላል፡፡ ኤሚ እንወድሻለን፣ ሁሌም እናስታውስሻለን! አንቺ የዘረኞችን የመለያየት ግንብ የናድሽ ጀግናችን ነሽ፣ አንቺ በልባችን ውስጥ ለዘላለም ሕያው ነሽሞት በአንቺ ላይ ስልጣን የለውም፣ ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር ያሸነፈሽ የሕዝባችን ታላቅ ሰማዕት ነሽና ደህና ሁኚ ኤሚ ደህና ሁኚ፣ ሁሌም እንወድሻለን…!›› በማለት ወደ ትውልድ አገሯ አሜሪካ በእንባና በመሪር ሐዘን ሸኟት፣ ተሰናበቷት፡፡
                                                                                          
ውቧ፣ ማራኪዋና ከዓለማችን አስር ምርጥ ከተሞች ተርታ የተመዘገበችው የደቡብ አፍሪካዋ የኬፕታውን ከተማ የደቡብ አፍሪካ የታሪክ፣ የቅርስ፣ የባህልና የፖለቲካ ማዕከል ናት፡፡ የድኅረ ምረቃ ትምህርቴን የተከታተልኩባት ኬፕታውን ለአምስት መቶ ዓመታት ያህል አፍሪካውያን ያለፉበትን ውስብስብ የታሪክ ጉዞ የሚያስቃኙ፣ የጥቁር ሕዝቦችን የአይበገሬነትና የነፃነት ተጋድሎ የሚዘክሩ በርካታ ቅርስና ሕያው አሻራ ያላት ታሪካዊ ከተማ ናት፡፡

Thursday, February 21, 2013

የማኅበረ ቅዱሳን ስም የማጥፋት የቸከ ስልት በፓትርያርክ ምርጫ ዙሪያ

ከመምህር ታየ ከቤተ ክህነት
ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመሾም እየተዘጋጀች ባለችበት በዚህ ወሳኝ ወቅት አባ ሳሙኤል ራሳቸውን ለመሾም የምርጫ ዘመቻ የከፈቱ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ የ20 ጎረምሳ አባት የሆኑትን አባ ሉቃስንና መሰሎቻቸውን በመናጆነት አቅርቧል፡፡ ፓትርያርክ እንዲሆኑ የሚፈልገው ግን በዘረኝነት የሚታወቁትን አባ ማቴዎስን ነው፡፡ እርሳቸውን ለማሾም የሚከፈለውን ማንኛውንም መሥዋእትነት እከፍላለሁ ማለቱን ማኅበረ ቅዱሳን አካባቢ እየተናፈሰ ነው፡፡ ማህበሩ ዕጩ ፓትርያርክ እንዲሆኑ ያሰባቸውን ጳጳሳት ዝርዝር ታሪክ ባወጣበት በሀራ ዘተዋህዶ ድረገጹ ላይ ይፋ እንዳደረገው ዋና ፍላጎቱ አቡነ ማቴዎስ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን አቡነ ማትያስ ግን እንዲሆኑ ከቶም እንደማይፈልግ በዘወርዋራ መንገድ ገልጿል፡፡

Wednesday, February 20, 2013

አባ ሳሙኤል በምረጡኝ ዘመቻቸው ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠማቸው ነው

ለፕትርክና የምረጡኝ ዘመቻ ሲደረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሹመቱ መንፈሳዊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ራስን ከማቅረብ ይልቅ የእግዚአብሔር ጥሪ  ያስፈልገዋል፡፡ የሚያገለግለው ህዝብም ይሁንታ ያስፈልገዋል፡፡ ለሹመቱም በትምህርትና በልምድና በምግባር ብቁ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ መንፈሳዊ ሹመት ያሰፈረው መመዘኛ እነዚህን ጉዳዮች ያካተተ ነው፡፡ 1ኛ ጢሞቴዎስ ምእራፍ 3ን ይመልከቱ፡፡ ከዚህ ውጪ በኃይል ወይም በሌላ ዘዴ ወይም እንደዓለማዊ ሥልጣን በምረጡኝ ዘመቻ ወደ መንፈሳዊ ስልጣን መምጣት ቢቻል እንኳን የዚያ ሰው የስልጣን ዘመን በችግሮች የተሞላ እንደሚሆንና ተቀባይነት እንደሚያጣ ብዙ መሰናክሎችም ከፊቱ እንደሚደቀኑበት ኃላፊነቱንም እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ መወጣት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡

Tuesday, February 19, 2013

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ አጠቃላይ ዘገባ


ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ ደፋ ቀና ሲል የነበረው የሰላምና አንድነት ጉባኤ አጠቃላይ ዘገባ አወጣ። ዘገባው እስካሁን የተደረጉ የሰላም እና አንድነት ስብሰባዎችን ይገመግማል፤ የአራተኛውና ባለፈው ወር በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ሊደረግ የነበረው የአንድነት ጉባኤም እንዴት ሊደናቀፍ እንደቻለ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይሰጣል።

ሙሉውን ዘገባ እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ

Monday, February 18, 2013

የአባ ሳሙኤል አቤሴሎማዊ መንገድ

አቤሴሎም የዳዊት ልጅ ነው፡፡ የእህቱ የትዕማር በአባታቸው ልጅ በወንድማቸው በአምኖን መደፈር የእግር እሳት ቢሆንበትም፣ የሆዱን በሆዱ ይዞ ሁለት ዓመታትን በዝምታ አሳልፏል፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ግን በጎቹን ለማሸለት ባዘጋጀው በዓል ላይ አባቱን ዳዊትን አሳምኖ አምኖን በዝግጅቱ ላይ እንዲገኝ አደረገ። ከዚያም በወይን ጠጅ አስክሮ ራሱን ሲስት በአገልጋዮቹ አስገደለው፡፡ ከዚያም የእስራኤልን ምድር ለቆ ወደ ጌሹር ሸሸ፡፡ ሶስት ዓመታትንም በዚያ አሳለፈ፡፡

ዳዊት ከልጁ ከአምኖን ሞት ከተጽናና በኋላ ወደ አቤሴሎም ይሄድ ዘንድ ልቡ ናፍቆ ነበር፡፡ ይህን ያስተዋለው የዳዊት የጦር አለቃ ኢዮአብ አንዲት ብልህ ሴትን ተጠቅሞ አቤሴሎም ከኮበለለበት ወደኢየሩሳሌም እንዲመለስ ትልቅ ስራ ሰራ፡፡ ይሁን እንጂ ዳዊት ፊቱን እንዲያይ ስላልፈቀደለት አቤሴሎም ከአባቱ ጋር ሳይተያይ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ አቤሴሎም የንጉሡን ፊት ማየት አለብኝ ብሎ ወደኢዮአብ በተደጋጋሚ መልእክት ላከ፡፡ ኢዮአብ ግን አልሰማውም፡፡ ስለዚህ በእርሱ እርሻ አጠገብ የነበረውን የኢዮአብን እርሻ እንዲያቃጥሉ በማድረግ ኢዮአብን እንዲመጣ አስገደደው፡፡ ከዚያም ከንጉሱ ጋር እንዲያገናኘው አደረገ፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር አቤሴሎም የዳዊትን መንግሥት ለመገልበጥ እንቅስቃሴ የጀመረው፡፡ ታሪኩን ከመጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ ምዕራፍ 13-19 ላይ ማንበብ ይቻላል፡፡

የፓትርያርክ ምርጫው ወዴት እያመራ ነው?

በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የተጀመረው የዕርቅ ሂደት ከተደናቀፈ ወዲህ የአዲስ አበባው ሲኖዶስ በብዙ ውዝግብ ተሞልቶ 6ኛውን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ ወደ ጫፍ እየደረሰ ይመስላል፡፡ ሁሉም የየራሱን ፓትርያርክ ለማሰቀመጥ እየተራወጠ ባለበት በዚህ ወቅት ማህበረ ቅዱሳን የእኔ ያላቸውን ከአባ ማቴዎስና ከአባ ሉቃስ አንዱን ለማስቀመጥ የተቻለውን እያደረገ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል የማቅ ድጋፍ እንዳይለያቸው ማቅን በጥንቃቄ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የቆዩት አባ ሳሙኤል የማቅ ድጋፍ የተለያቸው መሆኑ እየታየ ቢሆንም በራሳቸው መንገድ ከፍተኛ በጀት መድበውና ቀስቃሾችን አሰማርተው በከፍተኛ ሁኔታ እየሠሩ ይገኛል፡፡ በቀስቃሾቹ አማካይነትም ብዙዎችን የማሳመን ስራ እየሰሩ ነው ተብሏል፡፡ በዚህ በኩል የቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ተማሪዎችንና የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስራ አስኪያጆችንና የደብር አስተዳዳሪዎችን በተለያየ መንገድ በማሳመን ቀጣዩ ፓትርያርክ አባ ሳሙኤል ናቸው የሚል ነገር በስፋት እንዲወራ እየተደረገ ነው፡፡ በየሀገረ ስብከቶችም ተመሳሳይ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑ ይነገራል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ደግሞ ኦዲህ ባለ መንገድ ፓትርያርክ መሆን አይገኝም እያለ ነው፡፡ የአባ ሳሙኤል ስብእና ግን ለፓትርያርክነት የሚያበቃ እንዳልሆነ ከዚህ ቀደም ያወጣናቸው የተለያዩ ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡

Thursday, February 14, 2013

የአቦይ ስብሐት ነጋ ‹‹ይሰቀሉ፣ ሞት ይገባቸዋል!›› የሚል የበቀል መንፈስ ከወዴየት ነው!?

በፍቅር ለይኩን
አቦይ ስብሐት ባለፈው ሳምንት ‹‹ከላይፍ›› ወርኻዊ መጽሔት ጋር ያደረጉትን ሰላም ሰላም የማይሸት፣ ፍቅርን የተራቆተ፣ የይቅር ባይነት መንፈስ ፈፅሞ የተለየው፣ በቀልንና ጥላቻን የሚሰብክና ‹‹ዕርቅ ለመፈጸም በማለት ሰዎችን ሲልኩ የነበሩ ቄሶች ስቅላት፣ ሞት ይገባቸዋል!›› የሚል የሞት ፍርድ አዋጅን የሚያስተጋባ የሚመስል ቃለ-መጠይቃቸውን እያዘንኩም፣ እያፈረኩም ለማንበብ ተገድጄያለሁ፡፡
ማፈሬና ማዘኔም እኔ እጅግ በጥቂቱም ቢሆን የማውቃቸው አቦይ ስብሐት እንደ ፖለቲከኛና ከፍተኛ የመንግሥት ሰው ሳይሆን እንደማንኛችንም ኢትዮጵያውያን በጎረቤት፣ በወዳጅ ዘመድ፣ በጓደኛ መካከል… በደስታውም በሐዘኑም የሚገኙ፣ ማህበራዊ ግዴታቸውን የሚወጡ፣ መልካም የሆነ ማህበራዊ ግንኙነት እንዳላቸው በጥቂቱ ስለማውቅ ነው፡፡

Tuesday, February 12, 2013

እምነትና ምግባር ምንና ምን ናቸው?

“የሃይማኖትና የመልካም ሥራ ትርጓሜያቸው ይህ ነው፤ ሃይማኖት ለመጽደቂያ መልካም ሥራ የሃይማኖት መግለጫ ነው፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ መዳን የሚገኘው በእምነት ነው እንጂ በሥራ አይደለም ይላል፡፡ መልካም ሥራም የእምነት መግለጫ መሆኑን ይናገራል፡፡ ጥንታዊው የኢትዮጵያ እምነትም መዳን የሚገኘው በእምነት ነው፤ መልካም ሥራ ደግሞ የእምነት መግለጫ ነው የሚል ነበር። ነበር ለማለት የተገደድነው ዛሬ ይህን እውነት የሚቃረን ስብከት እየተሰበከ ስለሆነ ነው፡፡ አዋልድ መጻህፍት እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ለምኔ ያሉ የሚመስሉት ጸረ ወንጌል አቋም ያላቸውና ከእኛ በላይ ኦርቶዶክስ የለም የሚሉ ግለሰቦችና ማህበራት ይህን የወንጌል እውነት ሲቃወሙት ኖረዋል፡፡ በምትኩም መዳን የሚገኘው አዋልድ መጻህፍት በሚሰብኩት ስራ ነው እንጂ መጽሀፍ ቅዱስ በሚያስተምረው ወንጌል አይደለም እያሉ በግልጽ ይናገራሉ፡፡ እውነታው ግን ይህ አይደለም፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሴ በጣሊያን ወረራ ተሰደው እንግሊዝ በነበሩ ጊዜ በስደት የነበረችው ቤተክርስቲያን በ1931 ዓ.ም “የቤተ ክርስቲያን ጸሎት” በሚለ ርእስ ያዘጋጀችው፣ አሁንም ድረስ በቤተክርስቲያናችን የሚሰራበትና ብዙ ሰዎች ልብ ያላሉት መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሀፉ በቤተክርስቲያን የሚሰራባቸውን ልዩ ልዩ የጸሎት ስርአቶችን ይዟል፤ ቀጥሎ የቀረበው ግን የመዳንን መንገድ ያብራራል፡፡ በእርግጥም ሰው ይህን ዋና ነገር ካላስተዋለ ወደመዳን አይደርስም፡፡ ስለዚህ ሰው ሁሉ እንዲያነበው፣ እንዲያስተውለው፣ ራሱን እንዲፈትሽበትና እንዲድንበት ጽሁፉን ከዚህ ቀጥሎ እንዳለ አቅርበነዋል፡፡

Sunday, February 10, 2013

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 10
የግንቦቱ ቅዱስ ሶኖዶስ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ላይ በምስራች አገልግሎት ላይ ካቀረባቸው “ኑፋቄዎች” መካከል ሁለቱን ባለፈው ክፍል አቅርበን ነበር፡፡ ቀሪዎቹ ሁለቱ “ኑፋቄዎች” ደግሞ እነሆ ቀጥለው ቀርበዋል፡፡

“ ‘ሐ. ከተአምረ ማርያም ጀምሮ አዋልድ መጻህፍት ከቀኖና ሃይማኖት ትምህርት ጋር አንዳች ዝምድና የላቸውም፤ ልብ ወለድ ድርሰቶች ናቸው’ በማለት የቤተክርስቲያናችንን አዋልድ ቅዱሳት መጻህፍትን ይነቅፋል፡፡ ኆህተ ብርሃን መጋቢት 2003 እትም፥ ገጽ 4”
“ ‘መ. ሰይጣን ያጻፋቸው ብዙ እንግዳ መጻህፍት ወደ ቤተክርስቲያን ገብተው ዛሬ የውስጥና ውጭ መድረኮችን ተቆጣጥረዋል፤ እነዚህ እንግዳ መጻህፍት (ባዕዳነ ወንጌላት) ገዳማትን መሳለም፣ በቅዱሳን ስም መሰየም፣ በገድልና በድርሳናት መታመን፣ የቅዱሳንን መታሰቢያ ማድረግ፣ ለንስሀ አባት መናዘዝ፣ ፍትሀትና ተዝካር ማድረግ፣ በገዳማት መቀበር፣ ሰባቱን አጽዋማት መጾምና መመጽወት ሰውን ያጸድቃል ከሚለው ትምህርት ጋር በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘውን የእግዚአብሔር ጽድቅ ሸፍኖታል፣ ክርስቶስ የህግ ፍጻሜ ነው፡፡ በገድልና በድርሳን ታሪክ ለደነዘዘ ጆሮ ሞኝነት ሆኖ እንዲቆጠር ተደርጓል፡፡’ በማለት የቤተክርስቲያናችን መጻህፍት ሰይጣን ያጻፋቸው ሲል ይጸርፋል፤ ይነቅፋል፡፡ የቅዱሳንን መታሰቢያ አጽዋማትንና በዓላትን ይቃወማል፡፡ ኆህተ ብርሃን መጋቢት 2002 እትም፥ ገጽ 17 እና 18”

Saturday, February 9, 2013

"ማህበረ ቅዱሳንን" ያያችሁ!


በአንድም በሌላም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እምነት ተከታይ ሆኖ ራሱን "ማህበረ ቅዱሳን" በማለት የሚጠራ ነፍሰ ገዳይ ሳለ መንፈሳዊ ጭምብል አጥልቆ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሆነ ንዋያተ ቅድሳትና የተለያዩ ቅርሳቅርሶች ከዬ ገዳማቱና አድባራቱ እያደነ ከመዝረፍና ከመመዝበር አንስቶ ለዓላማው ያልተንበረከኩ ሊቃነ ጳጳሳት: ካህናትና ዲያቆናት በማሳደድና ነፍስ እስከ መግደል ድረስም የተሰማራ የጥቁር ራስ ስብስብ መሰሪ ድርጅት የማያውቅ ሰው ይኖራል የሚል እምነት የለኝም፡፡
በእርግጥ ማህበሩ በመላ ሀገሪቱ ባሰማራቸው ለዓመታት በስለላ የሰለጠኑ አባላቱና በተለያዩ የመንግስት የሃላፊነት ቦታዎች የተቀመጡ ግለሰቦች ጭምር በመጠቀም "ማህበረ ቅዱሳን የተቃቃመው ጥንታዊትና ሐዋሪያዊት የሆነችው የኢ//// ስርዓተ አምልኮ ለትውልድ ማስተላለፍ ነው፡፡ ዓላማውም አበው ትተውልን ያለፉት ትውፊት፡ ደንብና ስርዓት ጠብቆ ማስጠበቅ ነው።" ሲሉ በነጋ በጠባ ቁጥር ሳይታክቱ እንዲለፍፉ በማድረግ በሰራውና እሁንም ድረስ እየሰራው ባለ ፕሮፖጋንዳ "ማህበረ ቅዱሳን" ሲባል "ብዙዎቻችን" የምናወቀው ሃጢአት የማያውቃቸው፡ ቅዱሳን፡ ንጹሐንና የመላእክት ዘር ያለባቸው ንኡዳን አድርገን በመቁጥር ነው። እንግዲህ ይሄው ቀኑ ደረሰና "የቤተ ክርስቲያን ስርዓትና ትውፊት ጠብቆ ለማስጠበቅ የቆምኩ መንፈሳዊ ማህበር ነኝ" እያለ ሕዝብ ሲያደኖቅር ዓመታት ያስቆጠረ ድርጅት የሃይማኖት መሪዎች እየፈጸሙት ላለው ጥፋት ይሄው ጭራሽ መራጭና አስመራጭ ሆኖ በመሪ ተዋናይነት ተሰልፎ ሽርጉድ እያለ ይገኛል። (ስም ማጥፋት ወይንም ደግሞ ተራ ውንጀላ አይደለም እየተባለ ያለው ለማረጋገጥ ከተፈለገ የሚቀጥለውን ሊንክ በመጨቆን እውነቱን ሊያረጋግጡ ይችላሉ። http://www.ethiotube.net/video/24565/ETV-News--Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-Churchto- elect-its-6th-Patriarch-on-February-28--February-7-2013)

Thursday, February 7, 2013

የአዲስ አበባው ሲኖዶስ የ6ኛ ፓትሪያርክ ምርጫ የካቲት 21 ቀን ያጠናቅቃል


ከተለያዩ አካላት በተውጣጡ 13 የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት የሚመራው ምርጫ የካቲት 21 (በሦስት ሳምንት ውስጥ ማለት ነው)  ቀን ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለህዝብ ይፋ እንዲሚያደርግ አስመራጩ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አስታወቀ።
አስመራጭ ኮሚቴው ከሚከተሉት አካላት የተውጣጣ ነው።
  • ሊቃነ ጳጳሳት
  • ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች
  • ከአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች
  • ከሰንበት ትምህርት ቤት
  • ከማህበረ ቅዱሳን   
የወጣው መግለጫ ማንም ሰው ጥቆማ መጠቆም እንደሚችል ያሳወቀ ሲሆን 5 እጩዎችን ግን የሚመርጠውና ይፋ የሚያደርገው አስመራጭ ኮሚቴው ነው። አስመራጭ ኮሚቴው 5ቱን እጩዎች እንዴት እንደሚመርጥ ግልጽ አይደለም። ከ5ቱ እጩዎች በምን መስፈርት እንደተውጣጡ ባልታወቁ 800 ሰዎች የካቲት 21 ቀን በድምጽ ብልጫ አንድ ፓትርያርክ ይመረጣል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተሰጠው መግለጫ መሰረት ምርጫው የካቲት 21 ቀን ተካሂዶ በዚሁ እለት የተመረጠው አባት ለህዝብ ይፋ ይሆናል። በዓለ ሲመቱ የካቲት 24 እንደሚሆንም ገልጸዋል።


የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 9
የግንቦት 15ቱን «ውግዘት» የተመለከተ ዘገባችንን ካቆምንበት እንቀጥላለን፡፡ ሲኖዶሱ ጠርቶ ሳያነጋግራቸው በሕገ ወጥ መንገድ ካወገዛቸው ማህበራት መካከል አንዱ የምሥራች አገልግሎት ነው፡፡ በክፍል 3 ይህ አገልግሎት ተገኙበት የተባሉት ኑፋቄዎች ተዘርዝረዋል፡፡ የግንቦቱ ቅዱስ ሶኖዶስ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ላይ በምስራች አገልግሎት ላይ የቀረቡት “ኑፋቄዎች” “ኆህተ ብርሃን” በተሰኘው የአገልግሎቱ መጽሔት ላይ የተወሰዱ መሆኑን ቃለ ጉባኤው ያመለክታል፡፡ ጥቅሱ በትክክል ይጠቀስ ወይም ለክስ በሚመች መልኩ ይቅረብ ለማረጋገጥ ባንችልም፣ ቃለ ጉባኤው ያሰፈረውን መሰረት አድርገን ግን ኑፋቄ የተባሉት ነጥቦች ኑፋቄ መሆን አለመሆናቸውን እንመረምራለን።

“ሀ. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መታደስ አለባት፤ ታዲያ የሚታደሰው የቱ ነው ቢባል፦ ከመሰረተ እምነት ውጭ ያለው ግድግዳዋ ነቅቷል፥ ተሠነጣጥቋል፥ መልኳ ወይቧል፥ ጣራዋ ዳዋ በቅሎበታል፥ ያፈሳል፥  እነዚህን ማደስ ያስፈልጋል» በማለት ጽፏል፡፡ ኆህተ ብርሃን መጋቢት 2002 እትም፥ ገጽ 14”

Tuesday, February 5, 2013

ግብጻውያን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ እንደሚያስፈልጋት የጠቆሙበት ሥልጠና እያነጋገረ ነው

ባለፈው ታኅሣሥ ወር ላይ ከግብጽ ወደኢትዮጵያ የመጡ 40 አባላት ያሉትና በሊቀጳጳስ የሚመራ ቡድን በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ላሉ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ለ5 ቀናት ሥልጠና ሰጥተው ነበር፡፡ ሥልጠናው በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መሆኑ በወቅቱ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረገጽ ላይ የተገለጸ ሲሆን ለስልጠናው የሚሆነው ወጪ ከ250 ሺህ ብር በላይ ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነው በግብጻውያኑ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ የማቅ ብሎግ የሆነውንና ደጀሰላምን ተክቶ ብቅ ያለው ሀራ ዘተዋህዶ የተሰኘው ብሎግ ወጪው አባ ሳሙኤል በሚመሩት የልማት ኮምሽን እንደተሸፈነ አስመስሎ ሐሰት ጽፏል (የDecember 12/2012ን ዘገባ ይመልከቱ)፡፡ ይህም የአባ ሳሙኤልን ገጽታ ለመገንባት ተብሎ የተደረገ መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ፡፡

Sunday, February 3, 2013

የዘርዓ ያዕቆብ የግብር ልጅ ማንያዘዋል እና የደብረ ብርሃን «ገድሉ»

ማንያዘዋል አበበ «የራስ ገዝ አስተዳደር» ይሉታል የሚቀርቡት ሰዎች ስለእሱ ሲገልጹ፡፡ በብዙ ሁኔታዎች ላይ ከራሱ በቀር የሚሰማው ሰው የለውም፡፡ ራሱ አስቦ ራሱ አቅዶ ራሱ ያለው ብቻ እንዲፈጸም የሚያደርግ ራስ ገዝ ነው፡፡ ምንም አይነት ክህነት የሌለው እና ለተንሥኡ ተሰጥኦው እግዚኦ ተሣሃለነ መሆኑን እንኳ ያወቀው ኮሌጅ ከገባ በኋላ ነው ይባልለታል፡፡
 ወደ ቤተክርስቲያንም የመጣበት መንገድም ሆነ ስላሴ ኮሌጅ እስኪገባ ድረስ የነበረው አቋም በአሁኑ ጊዜ ከጥምቀት ተመላሾች እንደሚባሉት ልጆች ያለ ነው፡፡