Thursday, February 7, 2013

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 9
የግንቦት 15ቱን «ውግዘት» የተመለከተ ዘገባችንን ካቆምንበት እንቀጥላለን፡፡ ሲኖዶሱ ጠርቶ ሳያነጋግራቸው በሕገ ወጥ መንገድ ካወገዛቸው ማህበራት መካከል አንዱ የምሥራች አገልግሎት ነው፡፡ በክፍል 3 ይህ አገልግሎት ተገኙበት የተባሉት ኑፋቄዎች ተዘርዝረዋል፡፡ የግንቦቱ ቅዱስ ሶኖዶስ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ላይ በምስራች አገልግሎት ላይ የቀረቡት “ኑፋቄዎች” “ኆህተ ብርሃን” በተሰኘው የአገልግሎቱ መጽሔት ላይ የተወሰዱ መሆኑን ቃለ ጉባኤው ያመለክታል፡፡ ጥቅሱ በትክክል ይጠቀስ ወይም ለክስ በሚመች መልኩ ይቅረብ ለማረጋገጥ ባንችልም፣ ቃለ ጉባኤው ያሰፈረውን መሰረት አድርገን ግን ኑፋቄ የተባሉት ነጥቦች ኑፋቄ መሆን አለመሆናቸውን እንመረምራለን።

“ሀ. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መታደስ አለባት፤ ታዲያ የሚታደሰው የቱ ነው ቢባል፦ ከመሰረተ እምነት ውጭ ያለው ግድግዳዋ ነቅቷል፥ ተሠነጣጥቋል፥ መልኳ ወይቧል፥ ጣራዋ ዳዋ በቅሎበታል፥ ያፈሳል፥  እነዚህን ማደስ ያስፈልጋል» በማለት ጽፏል፡፡ ኆህተ ብርሃን መጋቢት 2002 እትም፥ ገጽ 14”
ሲኖዶሱ ኑፋቄ ሲል በጠቀሰው በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ጽሁፉን ያስነቀፈው «ኑፋቄ» ምን እንደሆነ ቃለ ጉባኤው አልገለጸም፡፡ ይህ ጽሁፍ የኦርቶዶክስ መሰረተ እምነት ትክክለኛ መሆኑን ይመሰክራል፡፡ ከመሰረተ እምነት ውጪ ያለው ነገሯ በአብዛኛው እንደተበላሸና ተሀድሶ እንደሚያስፈልገው ግን በዘይቤ ገልጾአል፡፡ የግድግዳዋ መንቃትና መሰነጣጠቅ፣ የመልኳ መወየብ፣ የጣራዋ ዳዋ  ማብቀልና ማፍሰስ ማንም ሊክደው የማይችለው እውነት ነው፡፡ ቤተክርስቲያኗን በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር ለተመለከታት ከላይ በዘይቤ የቀረቡት ችግሮቿ ሁሉ ፍንተው ብለው ይታያሉ፡፡ ስለዚህ ለዚህች ቤተክርስቲያን መፍትሔዋ ተሀድሶ ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ይህን ድምፅ እንኳን ተሀድሶ ብለው የተነሱ ወገኖች ቀርተው የማህበረ ቅዱሳን ሰዎችም «ተሀድሶ» የሚለውን ስም በመጠቀም ቤተክርስቲያኗ ተሀድሶ እንደሚያስፈልጋትና ተሀድሶው ግን ተሀድሶ የተባሉት እንደሚሉት ሃይማኖታዊ ሳይሆን የአስተዳደር ተሀድሶ እንደሆነ በየብሎጉና በየመጽሄቱ የጻፉበት ጊዜ አለ፡፡ ይነስም ይብዛ ኦርቶዶክስ ተሀድሶ የሚያስፈልጋት መሆኑን ማንም አይክድም፡፡ እንኳን ኦርቶዶክስ ሌሎቹም የፕሮቴስታንትም ሆኑ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት በየጊዜው ተሀድሶ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ታዲያ ኦርቶዶክስ በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር ስትቃኝ መሰረተ እምነቷ ችግር የለበትም፤ ከዚያ ውጪ ያለው አብዛኛው ነገሯ ግን በችግሮች የተተበተበ ነውና መታደስ አለበት የሚል ሐሣብ ማቅረብ እንዴት ተደርጎ ኑፋቄ ሊባል ይችላል? እንዴትስ ለውግዘት የሚያበቃ ኑፋቄ ተደርጎ ተጠቀሰ? የሚሉት ጥያቄዎች ገና አልተመለሱም፡፡ ስለዚህ ውግዘት አሁን ባለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምን ያህል ተራ ተግባር እየሆነ እንደመጣ ያሳያል፡፡ የሳተን ለመመለስ ሲባል ጠርቶ በመጠየቅና ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ አልመለስ ካለ፣ በኑፋቄው ከገፋበትም ህገ ቤተክርስቲያንን ተከትሎና ለቤተክርስቲያን ደህንነት ሲባል የሚተላለፈው ውግዘት እንኳን ይህ ትክክለኛ አሰራሩ ስለተበላሸ ተሀድሶ ያስፈልገዋል፡፡

“ ‘ለ. ምንኩስና ሥርዓተ ተፈጥሮን ይቃወማል፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይሽራል፥ ዝሙትን ያስፋፋል’ በማለት ሥርዓተ ምንኩስናን በመቃወም ጽፏል” ኆህተ ብርሃን መጋቢት 2002 እትም፥ ገጽ 8”
እስኪ በዚህ ጥቅስ ውስጥ አሁን ምን ስህተት አለ? ምንኩስና የሩቅ ምሥራቅ ሃይማኖቶች ባህል እንጂ የክርስትና ስርአት እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ እግዚአብሔር ከመጀመሪያ ሰውን “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት” ሲል አዘዘ እንጂ አትጋቡ ወይም መንኩሱ አላለም፡፡ ለምንኩስና እየተሰጠው ካለው ተገቢ ያልሆነ ስፍራና ከሚታየው ጋብቻን የማጣጣል ሁኔታ አንጻር ምንኩስና የተፈጥሮን ህግ ጭምር እየተቃወመ ነው ቢባል ትክልል እንጂ ስህተት አይደለም፡፡ ምንኩስናን የቀደሙ አባቶች ከቡድሃና ከሂንዱ ስርአት ወርሰው የክርስትና መልክ በመስጠት ወደ ቤተክርስቲያን ያስገቡት ወደቤተክርስቲያን ገብቶ የነበረውን ዓለማዊነትን ለመከላከል ነበር፡፡ ምንም እንኳን ወደቤተክርስቲያን የገባው ዓለማዊነትን ለመከላከል ቢሆንም በቆይታ ግን መልኩን ለውጦ የጽድቅ ጣሪያ ተደርጎ ተወሰደ፡፡ ሰው በወንጌል ሲያምን ለሀጢአት ሞቻለሁ ለጽድቅ ተነስቻለሁ ሲል በጥምቀት የሰጠውን ምስክርነት ከምስክርነት ባለመቁጠርና በመቃረን «ለዓለም ሞቻለሁ» የሚል ሌላ ቃል ኪዳን የሚገባበት ስርአት መሆኑ ምንኩስና ወንጌልን የሚቃወምና የክርስቶስን ሞት ከንቱ አድርጎ ጽድቅ በጥረት ይገኛል ብሎ የሚሰብክ የሰው ስርአት ነው ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ስለምንኩስና ፈጽሞ አያወራም፡፡ የሚናገረው ስለድንግልና ነው፡፡ ስለድንግልና የጻፈው ቅዱስ ጳውሎስ “ስለ ደናግልም የጌታ ትእዛዝ የለኝም፥” ብሏል፡፡ 1ቆሮ. 7፡25፡፡ ሆኖም ከዘመኑ ችግር አንጻር ሚስት ያላገባ፣ ጌታን በሙሉ ልብ ማገልገል የፈለገና ጥሪው ያለው በምንኩስና ሳይሆን በድንግልና ሊኖር እንደሚችል ጽፏል፡፡ ዛሬ በትክክለኛው የሕይወት ጥሪ በድንግልና ከሚኖሩት ከጥቂቶች በቀር ወደ ምንኩስና እየጎረፉ ያሉት ብዙዎቹ ሹመትና ገንዘብ የጠራቸው ናቸው፡፡ በድንግልና ለመኖር ትክክለኛ የሕይወት ጥሪ የሌላቸው በመሆናቸውም ለሹመትና ለገንዘብ የገቡበትን ምንኩስና መጠበቅ እያቃታቸው በዝሙት የሚፈተኑና የሚወድቁ ታማኞች ያልሆኑ ከመነኮሳት እስከ ጳጳሳት እንዳሉ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ታዲያ ምንኩስና ዝሙት እየተስፋፋበት ያለ ስርአት አይደለም ማለት እንዴት ይቻላል?

ታዲያ ሃይማኖት ያልሆነውና መጽሀፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለው የሰው ስርአት የሆነው ምንኩስና ችግሮች አሉበትና ሊስተካከል ይገባል የሚለው ሀሳብ እንደ ጥሩ አስተያየት ተወስዶ ስህተትን ከማረም ይልቅ ኑፋቄ አድርጎ መውሰዱና “ለምን ታረሙ ትሉናላችሁ?” በሚል አውግዣለሁ ማለት ወፈገዝት መሆን ነው፡፡ በአንዳንዶች በቆብ ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን አመፅና ርኩሰት ግን ማስተባበል አይቻልም፡፡ ስለዚህ ጽሁፉ የተቃወመው በምንኩስና ስም የሚፈጸመውን ይህን የአመፅ ሥራ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ይቀጥላል

 

 

 


18 comments:

 1. Thank you for this post.It is very imporant issue.
  we all understand the problem but how do we fix our problem?This is a big problem in Ethiopia I am just pray for our ethiopian's God to open our eyes and heart so God to help us and gide us to the right direction.Change is big problem in my country.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Bakeh Astewul ketesasate gar abreh atesasat!!! what does it mean ...."pray for our ethiopian's God..." u mean Ye-ethiopian God and any other country God is diffrent??? u see how u r wrong!!! Hulem lemesaf atchekul bakeh.

   Delete
 2. የጣራና የግድግዳ ቀለም እድሳቱ ሃይማኖት ነክ ስላልሆነ ርሱን አልፌ ስለ ምንኩስና ከዚህ ቀደም ከተወያየንበት ጋር የተዛመደ አጠር ያለ ጥንቅሬን ቢዘገይም ለአንባቢ ለማካፈል አቀርበዋለሁ ፡፡

  የሰው ተፈጥሮና የምንኩስና ሕይወት

  እግዚአብሔር የሰውን ስጋና ደም ፣ አጥንተና ጅማት ከምድር አፈር አበጀ ፤ በማብቂያውም የሕይወት እስትንፋስን በአፍንጫው እፍ አለበትና ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር እንዲሆን አደረገው ፡፡ እንስሳቱ ይኸ ሕያው ነፍስ የሚያደርገው እስትንፋስ ስላልተሰጣቸው ፣ ከሰዎች በባሕሪያቸው ይለያሉ ፡፡ ከዚህም አፈጣጠራችን ስንነሳ ፣ ሰው የስጋዊና የመንፈሳዊ አካል ጥምረት ወይም አንድነት ውጤት መሆኑ ነው ፡፡ ሁለቱንም በማመጣጠን በምድራዊ ሕይወቱ ይጠቀምባቸዋል ፡፡ አልፎ አልፎ ግን አንዱን ሌላውን የሚያኮስስበትና የሚውጥበት ጊዜም ይከሰታል ፡፡

  ስጋዊው ስሜትና ፍላጐት በሚያይልበት ወቅት ፣ ሰው እንስሳዊ ባህርዩን አጉልቶ ያሳያል ፡፡ መብላት ፣ መጠጣት ፣ ማመንዘር … ሥጋዊ ምግባራትን ማሟላት ያስደስቱታል ፡፡ እንደ እንስሳም መኖር ይለማመዳል ፡፡ ወደ ፈጣሪው አይጸልይም ፣ በልቶ ጠጥቶ አያመሰግንም ፡፡ ...

  መንፈሳዊ አካሉ ስትጐለብት ግን ለጽድቅና ለቅድስና ሥራ ይተጋል ፣ የሥጋን ስሜቶች ይገድልና ወደ ፈጣሪው ለመቅረብ ይጣጣራል ፡፡ አምላኩን በጸሎት ያስባል ፣ ስሙን እየጠራ ያወድሳል ፡፡ ይኸኛው እየጠነከረ ሲሄድ ሙሉ ሕይወቱን ለዚሁ አገልግሎት ለመስጠት ይወስንና ፣ ሰማያዊውን ብቻ እያሰበ ለመኖር ይለያል ፡፡ ምንኩስና የሚባለው መሆኑ ነው ፡፡ መነኮሳቱ ሰማያዊውን ሳይሆን ምድራዊ ጥቅምን በመሻት ፣ ወደ ገዳም ገብተው ከሆኑና ከወደቁ ፣ በሰዎች ደካማ ባህሪና በዲያብሎስ ፈተና ተደረገ እንላለን እንጅ ፣ ሁሉን በአንድነት ጨፍልቀን ልምምዱን ማውገዝ አይገባንም ፡፡ ምናልባት እንደሚወራው ፣ ኋላ ላይ ጳጳስ እሆናለሁ ብለው ፣ በምድራዊ ቀመር አስልተው ወደ ገዳም የገቡ ካሉ ሥጋዊ ፈተና ሊጥላቸው ግድ ይላል ፡፡ ነገር ግን ይኸንንም የማስበውና የምለው ስለሃሜታው ብዛት እንጅ መረጃና ማስረጀ ስለኖረኝ አይደለም ፡፡

  መጀመሪያውኑ የገዳም ትርጉሙ ዓለምን የናቁ መናኞች ፣ ባሕታውያንና መነኮሳት መኖሪያ ፤ ዓለማዊ /ምግባር/ የሌለበት ስፍራ ፣ ዱር ፣ በረሐ ፣ ደን ፤ መማጠኛ ስፍራ ፣ ጭው ያለ ቦታ ማለት ነው ፡፡ ከሥጋዊ ፍላጐት መገዛት የሚለዩበት ፣ ዓለማዊ ህይወትን ክደው የሚኖሩበት ሥፍራ ነው ፡፡

  የታሪክ ሰዎች ይህ ዓይነቱን ልምምድ ከቡድሃና ከሂንዱይዝም እምነት ጋር አቆራኝተው በመተረክ ፣ ክርስትናም ከነርሱ እንደቀዳ አድርገው ይገልጻሉ ፡፡ ክርስቲያን እንደመሆናችን መጠን ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር የሚቀራረበውን ልምምድ እጠቅሳለሁ ፡፡

  - በመጽሐፍ ቅዱስ ቃሉ በቀጥታ ገዳም ባይባልም ፣ ሙሴ አርባ ቀንና ለሊት ያለ እህልና ውሃ የከረመበት ተራራ ልምምድ ፤ ዘጸ 34፡28
  - ኤልያስ በኮራት ፈፋ ውስጥ ተሸሽጎ ፣ ቁራዎች የሚያመጡለትን እየተመገበ መሰንበቱ ፤ 1 ነገ 17፡3-6
  - ነቢዩ ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ተጥሎ ከአንበሶች ጋር ያደረባት ዕለት ፤ ዳን 6፡16-19
  - መጥምቁ ዮሐንሰ ከህጻንነት ዕድሜው ጀምሮ የኖረበት የምድረ በዳ ሕይወት (የበረሃ አንበጣና ማር ብቻ እየበላ ፣ የግመል ጸጉር እየለበሰ) መሆኑ ፣ ሉቃ 1፡8ዐ ፤ ማቴ 3፡1-2 ፡፡ ኢየሱስም ይህን ሁሉ አጠቃሎ ስለ ዮሐንስ ሲገልጽ ከሴቶች ከተወለዱት ሁሉ በላይ ብሎታል ፡፡ ሌላው ከዚሁ ጋር መጠቀስ ያለበት አይሁዳውያን ከግብጾችም አባት አስቀድመው የገዳማዊ ሕይወት አኗኗር እንደነበራቸው ለማስረጃ መሆኑን ነው ፡፡
  - ጌታችንም ለመፈተን ወደ ምድረ በዳ (ገዳመ ቆሮንቶስ) በመንፈስ ተወስዶ አርባ ቀንና ሌሊት ያለ ምግብና ውሃ የሰነበተበት ሕይወት ማቴ 4፡1-2 ፤ ማር 1፡13 ፤ ሉቃ 4፡1-2 ፡፡ አዎ እዚህ ላይ ልናስተውለውና ልንጠነቀቅበት የሚገባው ፣ ጌታችን እንደተቀሩት መንፈሳውያን አባቶች ጽድቅንና ቅድስናን ለማግኘት ሲል ወደ ምድረ በዳ እንዳልሄደ ነው ፡፡ ነገር ግን እንደ ጥምቀታችን ሁሉ ይኸንንም ሊባርክልንና ሥርዓትን ሊመሠርትልን ፈጽሞታል ፡፡ እንዲያውም የሚደንቀው ባሳለፋቸው የአገልግሎት ሦስት ዓመታት ፣ አንድም ቀን እንኳን እነ እገሌ ቤት አደረ ፤ የማያንቀላፋ ይመስል ፣ እነ እገሌ መኝታ አነጠፉለት አለመባሉ ነው ፡፡ ማለትም ሦስቲም የሥራ አመቶቹ እንደ ምናኔ ሕይወት የሚቆጠሩ ናቸው ያስብለኛል ፡፡ ምክንያቱም ሲመሽ ሌሎቹ ሲተኙ ልጸልይ ወደ ተራራ እንደወጣ በተደጋጋሚ መገለጹ ነው ፡፡ ማቴ 14፡23 ፤ ሉቃ 6፡12 ፤ ማር 6፡46 ፤ ሉቃ 9፡28-37 ፡፡

  - የሚከተሉትን ቃሎችን ደግሞ ኢየሱስ አስተምሮናል ፡፡
  o ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው (ማቴ 5፡6)
  o ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው ፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና ማቴ 5፡1ዐ
  o ለባለ ጠጋው ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ ማለቱ ማቴ 19፡21
  o ስለ መንግሥተ ሰማያት ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ ፤ ማቴ 19፡12 ፡፡ በዚህኛውም ግንዛቤአችን ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያናችን እንድትጸድቁ ራሳችሁን ስለቡ ብላ አታስተምርም ፡፡ ብዙ ተባዙ ብሎ ያወጀልን አምላክ ጃንደረባነትን ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አለ እንጅ አላወገዘውም
  o በተጨማሪም ሐዋርያው ጴጥሮስ እነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ሲለው ፣ በመንግሥተ ሰማያት ፈራጅ እንደሚሆኑ ፣ ያጠፋውን እጥፍና የዘላለም ሕይወትን እንደሚወርሱ መንገሩ የማቴ 19፡27-29 ፤ ሉቃ 18፡28-3ዐ ፤ ማር 1ዐ፡28-3ዐ

  በተረፈ መነኰሳት በገዳም ሁነው ስለ ራሳቸው ፣ ስለ ሃገርና ስለ ወገን ይጸልያሉ ፣ ይጾማሉ ፣ አምላክን ያወድሳሉ ፤ ለቤተ ክርስቲያን የሚያገለግሉ (ጥንት ከነበረው ልማድ በመነሳት) መጽሐፍትን ይጽፋሉ ፤ ወንጌልን ይማራሉ ፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሲፈቅድላቸውና ለአገልግሎት ሲጠራቸው ደግሞ ወደ ሕዝብ ወጥተው ያስተምራሉ ፤ ቤተ ክርስቲያንን ይመራሉ ፤ ያስተዳድራሉ (ካህናት ጳጳሳትና ፓትርያርክ በመሆን) …. ፤ በቤተ ክርስቲያን ላይ የጥፋት ዘመቻ ሲነሳ ንዋየ ቅድሳትን ለማትረፍ በማሸሽም ከዚህ ቀደም ቁም ነገር ሠርተዋል ፡፡

  ጉዳዬን የምቋጨው አንድ ሉተር ሞክሮ ስላልተሳካለትና ስለነቀፈ ብቻ ፣ ጌታ እንዳለው የሚችል ይሞክረው ያለውን ዓይን ጨፍኖ መውቀሱ ይቁምልን በማለት ነው ፡፡


  ReplyDelete
  Replies
  1. father son & hollysprit i always open this page to learn from your kind of people that knows deeply our religion & i always wondering why other religions blame & try to destroy our tewahedo church why is that always they point to our church ? even if i wrote message for you to get your address but the host didnt post it cause they know what they want to do that is to confuse christine peoples i dont think they post this one too what ever our church build by mercyfull lord jesus christ & we always pray to give us mercy & this is for you meamen this is my email saha2011@yahoo.com pls try to contact me thank you

   Delete
  2. በዋሻና በገዳም ወይም ከዚህ ዓለም ምቾትና ምኞት መለየት ትክክለኛ መሆኑን ማንም አይክደውም። ያ ማለት ግን ምንኩስና በሚለው ቀንበር ስር በህግና በድንጋጌ ስር ቆቤን እንዳልጥል በሚል ፍርሃት ለመደበቅ ሳይሆን ሀገር ለሀገር የወንጌልን ቀንበር ተሸክመው መከራና ስቃይን ተቀብለው ለክርስቶስ ቃል መዳረስ ለመታገል ዘወትር የሚተጉ ማለት ነው። ልክ እንደሐዋርያው ጳውሎስ! እንደ12ቱ ሐዋርያት! 72ቱ አርድእት! 36ቱ ቅዱሳን አንስት!
   ማንም የሚወደኝ ቢኖር መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ማለቱ ሴት ሽሽት ጫካ ይግባ ማለት ሳይሆን አዳኝ የሆነው ክርስቶስ ለዓለሙ ሁሉ ደሙን ማፍሰሱን እንዲሰብኩ፤ እንዲያስተምሩ፤ እንዲያዳርሱ ረሃቡን፤ጥሙን መከራውን ሁሉ ችለው እንዲታገሉ ማለት እንደሆነ መታወቅ አለበት። ሐዋርያትና አርድእትም ያደረጉት ይህንን እንጂ ዋሻ ዘግተው ተቀመጡ የሚል አላነበብንም። ስለወንጌል የሚያውቁ ካላስተማሩ ማን ሊያስተምር ነው?

   Delete
 3. The Protestant Reformation began in 1517 when Martin Luther nailed his 95 Theses to the door of a prominent mind control center in Wittenburg, Germany. This began a process from which eventually came a new franchise of Christianity, i.e. Protestantationalism, whose followers later became known as Protestants. They knew what they didn't like but never agree what to replace it with, which is why you have 1,000 Protestant denominations but only one Catholic church today.Lutheranism is a form of some religon founded by Herr Martin Luther sometime during the 1500s. Scholars generally agree that the exact year was 1517, but no one really cares. he broke off from Church to make a new Church.Historically, Lutheran theology accepts the theory of Personal Infallibility. This is the concept that everyone except the Pope, Catholics, or other non-Lutherans, are able to interpret the scriptures how ever every one with no chance of error. They also believe that since the death of Jesus, all sin is negated for followers of Christianity. This allows them to lead completely-guilt free lives of sin and debauchery while still being guaranteed entry to Heaven. Martin Luther was a monk at a local monastery near Wittenberg when he decided to write the Pope with a list of suggestions to improve the Catholic church. However as he started to write them all down, Luther got angrier and angrier and by item 95 (or 'abuse') , he had enough and marched round to the cathedral with a hammer and box of nails. There he pinned up the list for everyone to read and signed it Lex (Lexis) Luthor to confuse the authorities.
  The list was a long ramble of various things that had irked Luther. Like the day his bran flakes had been prepared by a woman or the time he was forced to share a shower with a horse. However it did include these following points:-
  Paying money to release your soul from eternal damnation doesn't work
  The Pope knows Jack Shit
  The Catholic Church is big business dressed up as a religion
  The Jews are to blame for everything
  Monasteries and nunneries are full of sin. I know, I've done it
  Please cancel the milk delivery today!source..un-cyclopidea

  ReplyDelete
 4. ብዙ መጠላላትና መነቃቀፍ ብዙ ቦታ ተሰጥቶት መገኘቱን በየእለት ውሎአችን እናያለን። እውነት፤ እውነቱን መነጋገር ቢቻልም መነቃቀፍ በበዛበት ዓለም እውነቱን በእውነታ ለመቀበል የሚቸገርም ሞልቷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የእምነት ዓምድ /ዶግማ/ ማለትም ምሥጢረ ሥላሴን አብርታ፤ አምልታና አስፋፍታ በማስተማር፤ እንዲሁም ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ሥጋ የለበሰበትን ረቂቅ ምሥጢር ፤ ምሥጢረ ሥጋዌውን አብራርታ በመስበኳ የታነጸችበትን ሃይማኖታዊ አለት/ ኰክሕ/ ስንመለከት በእውነትም የእግዚአብሔር ደጅ ናት ብንላት ቢያንሳት እንጂ አይበዛባትም። በክርስቶስ መሠረት ላይ የታነጸች፤ በሐዋርያት ትምህርት ያደገችና በሊቃውንቱ በእነአትናቴዎስ፤ ባስልዮስ፤ ጎርጎርዮስ ወዘተ የምሁራን አስተምህሮ የበለጸገች መሆኗን ማንም ሊክደው የማይችል የታሪክ እውነት ነው።

  ዳሩ ግን ይህንን መሠረቷን የሚንዱ፤ ወንጌሏን ወደጎን የሚገፉ፤ አጋንንታዊ ልምምዶችን በስመ ሥሉስ ቅዱስ የሚያስፋፉ፣ ተከታዮቿ ዓይናቸውን ከክርስቶስ ላይ ነቅለው በየምናምኑ ላይ እንዲተክሉ የሚያበረታቱ ብዙ አሳዛኝ መጻሕፍት በተረት፤ በእንቆቅልሽ፤ በወግና በአስማት ተሸፍነው የቤተክርስቲያኒቱን የወንጌል አስተምህሮ ማእድ በመበከል መርዛቸውን ታቅፋ እንድትኖር መገደዷን አስተዋዩ በደንብ ሲረዳው፤ እልከኛውም በአፉ ለመመስከር ያቅተው እንደሆን እንጂ ችግር እንዳለ ልቡናው እንደሚመሰክርበት እናስባለን። የወንጌል ፋይል ሳይዘጋ በፊትና ወንጌል ሥፍራውን ሰይጣንን እናስታርቃለን ለሚሉ ጸረ ወንጌል ስብከቶች ቦታውን ሳይለቅ በፊት ወንጌል ብቻውን ነግሶ ነበር። ሰይጣን መነኮሰ፤ሰይጣን ተገዘረ፤ ሰይጣን ቀለም አስተማረ፤ ጀጀጀ፤ ጨጨጨ፤ ኤኮስ፤ ለማስ፤ኤነከምካም ………ወዘተ ዓይነት ትምህርት ቦታውን ተረክቦ ትምህርቱ ሁሉ በሚያስደነግጥ መልኩ ስለሰይጣን ደግነት የሚወራበትና ምንጩ ያልታወቀ አስማት የሚጠራበት ከመሆኑ በፊት ያለውን የቤተ ክርስቲያናችን ሕይወት መልካም ውበት እንደነበረው እናምናለን። ርስቶስን በምታውቅ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ልጆቿ እናት ቤታቸውን ለቀው እንዲኮበልሉ በምንም መልኩ የምንፈልገው አይደለም። እንዲያውም «ኢየሱስን ተቀበሉ» እየተባሉ ድክመቶቿን እያዩ ሌሎች ያስከበለሏቸው፤ ልጆቿ ወደእናት ቤታቸው እንዲመለሱ እንታገላለን። «አንድ ሳር ቢመዘዝ፤ ቤት አያፈስም» በሚል እልከኛና ትምክህተኛ መፈክር የተነሳ ልጆቿ ሲኮበልሉ ግድ ከማይሰጣቸው የሰይጣን መልእክተኞች በስተቀር አንድም ኦርቶዶክሳዊ ሲኮበልል ምንም የማይስማንና ግድ የማይለን ምንደኞች አይደለንም። «ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም» እንደተባለው እናት ቤታችን የነፍስ ማእዱ ሞልቶላት ሳለ ጠላት የበተነውን አፈር የሚያነሳ በመጥፋቱና የመንፈስ እንጀራ የሚመግብ እውነተኛ መሪ ባለመገኘቱ የተነሳ የሚኮበልል በዝቶ ስናይ «ጌታ ሆይ ይህ እስከመቼ?» ብለን ወደሰማይ ማንጋጠጣችንን ስንናገር፤ እውነታውን የሚመለከት ዳኛ በሰማይ ስላለን አናፍርም።

  በሌላ መልኩም የቤተክርስቲያኒቱን ምእመናን የሚጠብቅ፤ ንጹህ ውሃና ለምለም ሳር ወዳለበት የሚያሰማራ እረኛ በመጥፋቱ በላይ ያሉቱ እርስ በእርሳቸው የሚነካከሱና የሚካሰሱ ሆነው ሁለትና ሦስት ጎራ ለይተው ለየራሳቸው የአሸናፊነትን ሰይፍ ሲመዙ ስናይ ይበልጥ እናዝናለን። ቤተክርስቲያኒቱ የስንዴ ክምር ሆና የዝንጀሮ መንጋ ትውልድ ሰፍሮባት እያፈረሰ ከመጋጡ በላይ የሚዘርፈው፤ የሚሸጠው፤ የሚለውጠው፤ እንደአፍኒንና ፊንሐስ በቅጽሯ የሚያመነዝር የአስነዋሪ ትውልድ መፈልፈያ ሆና ስናይም ልባችን ያለቅሳል። ተወልደን፤ባደግንባት ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደዚህ ዓይነት የመከነ ትውልድ ሆነን የመገኘታችን ምስጢር ምን ይሆን? ብለን እንጠይቃለን degagmen!«እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ፤ እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም።» ራእይ 3፤2 የሚለው ቃል ዛሬም መልእክቱ ለእኛ የሚሆን ይመስለኛል።መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ»«ብልጥ ከሰው ስህተት ይማራል፤ ሞኝ ግን በራሱ ስህተት ይማራል» we have to learn from the failure of catholic and other modrn churches!ብልጥ ከሰው ስህተት ይማራል፤ ሞኝ ግን በራሱ ስህተት ይማራል» !!!

  ReplyDelete
 5. የምንኩስና ሕይወትና አጀማመርን ስናስተውለው መሠረታዊ ዓላማው ለብቻ የመሆን፣ የመናቅና የመሸሽ ግብ ብቻ ሳይሆን በነዚህ መመሪያነት ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትን መፍጠር ብሎም ከእግዚአብሔር ፍጡራን ጋር ሰላማዊ ትስስር ላይ መድረስ ነው። በርግጠኝነት ገዳማዊ ሕይወት መቼና የት እንደተጀመረ መናገሩ አዳጋች ነው። ምክንያቱም ገዳማዊ ሕይወት ሌላ ሳይሆን የክርስትናን ሕይወት ለመኖር ሲባል የተጀመረ እንጂ የተሻለ ተብሎ የተመሠረተ አይደለም፤ ስለዚህም በግላዊ የጸጋ ሕይወት ውስጥ የግለሰቡና የእግዚአብሔር ግንኙነት የሚያሳድጉት ዓይነት ስለሆነ ይህንን በጊዜና በቦታ ማለትም በታሪክ ማመላከቱ አስቸጋሪ ነገር ነው።

  ለመጀመሪያዎቹ ሦስት ክፍለ ዘመናት ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት እጅግ ይሰደዱና ይገደሉም ስለነበር የሰማእትነት ዘመን ነበር፤ ሆኖም ግን ከአራተኛው ክ.ዘ. ማለትም ከ313 ዓ.ም. ጀምሮ በነገሥታት ደረጃ የክርስትና እምነት ተቀባይነት እያገኘ መምጣት ሲጀምር ስደትና ሰማእትነቱም እየቀነሰ መምጣት ጀመረ። ስለዚህም የምነና ሕይወት የሰማእትነትን ዋጋ እንደሚተካ በማሰብ መዘውተር ቀጠለ። አንዳንድ ክርስቲያኖችም ስለ እምነታቸው ባይገደሉም እንኳ በሕይወታቸው ዋጋን ለመክፈል ይበልጥ እንዲመቻቸው ወደ ምድረ በዳ/በረሃ በመሄድ የጽሞናና የዓላማ ሕይወትን መኖር ጀመሩ። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ነጥብ ገዳም የሚለው ቃል በግእዝ ቋንቋ ሥርወ ትርጉሙ ምድረ በዳ ወይም በርሃ መሆኑን ነው፤ ስለዚህም ገዳም ገባ ስንል ትክክለኛ ታሪካዊ አንድምታውን ያስተላልፍልናል። ሆኖም ግን ያ በምንም መልኩ ዛሬ እንደምንረዳው ገዳማዊ ሕይወት ነው ማለት አይደለም።መነኮስት የምንኩስናን ሕይወት ሲጀምሩ ከነበረው ጊዜያዊ ዓለም በመራቅ ወደ ምድረ በዳ፣ በረሃ ወይም ጫካ ውስጥ መሄዳቸው የእግዚአብሔር ፍጥረት የሆነችውን ዓለም በመጥላት ሳይሆን ይበልጥ በእግዚአብሔር ዓይን ስላይዋት ስለርስዋ ለመጸለይ እንዲመቻቸው ነው።ሐሳቡም ከዓለም ሕይወት ተለይቶ ለእግዚአብሔር በጸሎትና በአምልኮ መጠመድ ነው፡፡
  ጌታስ፣ ‘ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድኾች ስጥና ተከተለኝ’ ብሎ የለ? ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ደናግላንና
  መበለቶች ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ አላዘዘምን? ሐዋርያት የዓለም ፍጻሜ እጅግ ቅርብ እንደ ሆነ
  ያሳስቡስ አልነበረም? ታዲያ ዓለምን ንቆ ገዳም መግባት ምን ይገርማል?

  ReplyDelete
 6. በዋሻና በገዳም ወይም ከዚህ ዓለም ምቾትና ምኞት መለየት ትክክለኛ መሆኑን ማንም አይክደውም። ያ ማለት ግን ምንኩስና በሚለው ቀንበር ስር በህግና በድንጋጌ ስር ቆቤን እንዳልጥል በሚል ፍርሃት ለመደበቅ ሳይሆን ሀገር ለሀገር የወንጌልን ቀንበር ተሸክመው መከራና ስቃይን ተቀብለው ለክርስቶስ ቃል መዳረስ ለመታገል ዘወትር የሚተጉ ማለት ነው። ልክ እንደሐዋርያው ጳውሎስ! እንደ12ቱ ሐዋርያት! 72ቱ አርድእት! 36ቱ ቅዱሳን አንስት!
  ማንም የሚወደኝ ቢኖር መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ማለቱ ሴት ሽሽት ጫካ ይግባ ማለት ሳይሆን አዳኝ የሆነው ክርስቶስ ለዓለሙ ሁሉ ደሙን ማፍሰሱን እንዲሰብኩ፤ እንዲያስተምሩ፤ እንዲያዳርሱ ረሃቡን፤ጥሙን መከራውን ሁሉ ችለው እንዲታገሉ ማለት እንደሆነ መታወቅ አለበት። ሐዋርያትና አርድእትም ያደረጉት ይህንን እንጂ ዋሻ ዘግተው ተቀመጡ የሚል አላነበብንም። ስለወንጌል የሚያውቁ ካላስተማሩ ማን ሊያስተምር ነው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የላይኛው ግልባጭ
   መልዕክትህን አንተው እንድትፈትሸው ፣ ገዳም የሚገቡ ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? በሚል ጥያቄ ዙሪያ ብንዟዟር መልሳችን በዓለም ያለ ማንኛውም የሰው (ጥቂት የወንጌል አዋቂ ወይም አንዳች ቃል የማያውቅ) ዝርያ መሆን ይችላል ፡፡ ወደ ገዳም የኰበለለ ሁሉ አንተ ሐዋርያ እያልክ እንደገመትካቸው ያሉ ዓይነት አይደሉም ፡፡ ስለዚህም ገዳም ማለት የመነኰሳት መኖሪያ ብቻ ሳይሆን ፣ ለእኔ የሃይማኖት ትምህርት ቤትም ጭምር ነው ፡፡ በገዳም ሲኖሩ ሙሉ ለሙሉ በመንፈሳቸው ዕድገትን ያገኛሉ ፣ ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔርን ለመቅረብ ይታገላሉ ፡፡ ይጾማሉ ፤ ይጸልያሉ ፤ ለዕለት ፍጆታቸው ይሠራሉ ፤ መጽሐፍን ይማራሉ ፤ ይጽፋሉ ፡፡ በወንጌል ትምህርትና ትርጓሜ በሥርዓቱ ከሰለጠኑ በኋላ ደግሞ ፣ አዲስ መጪ ምእመናንን የሃይማኖትን ነገር ያስተምራሉ ፤ ለማቁረብ ያዘጋጃሉ ፤ ለምንኩስና ያበቃሉ ፡፡ ሲሆንላቸውና በፈጣሪ ሲጠሩ ደግሞ ወደ ዓለማውያን እየወጡ ያስተምራሉሉ ፤ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ሲሉም ሙሉ ለሙሉ እምነታቸውንና ምግባራቸውን ሳይለውጡ ከዓለማውያን ይቀላቀላሉ ፡፡ እናም በገዳም ያለ ወገን በሙሉ የወንጌል ሊቅና ሐዋርያ አድርጎ መመልከቱ ትንሽ ነገርን የሚያዛባ ፣ ፍርድንም የሚያጣምም ይሆንብኛል ፡፡

   ሁለተኛው መመልከት ያለብን ነጥብ ደግሞ ፣ እነዚህ ሰዎች ዓለምን ለመካድ የወሰኑት የግል ነፍሳቸውን ለማትረፍ እንጅ ፣ እኔንና አንተን የማዳንን ነገር አስበውና አቅደው አለመሆኑ ነው ፡፡ ምንኩስና ራስን ወደ ከፍተኛው የእግዚአብሔር መንግሥት መንጋ ለመቀላቀል የሚደረግ የነፍስ ወከፍ ትግል እንጅ ፣ ሌሎች አማኞችን መጎተት ዓላማው አይደለም ፡፡ እኔ ገዳም ብገባ ፣ እግዚአብሔር ይቅር እንዲለኝ እታገል ቢሆን እንጅ ሌላ ተጨማሪ ግዴታ አላስብም ማለቴ ነው ፡፡ እነርሱ ግን እግዚአብሔር ሲፈቅድላቸው ከራሳቸው አልፈው ለሌላው ክርስቲያን ወገን የሚተርፉበት ጊዜ እጅግ ብዙ ነው ፡፡

   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
 7. የሰው ልጅ ሰው መሆኑን ማወቅ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ራሱንም ሆነ በዙሪያው ያሉ ነገሮችን ተፈጥሮ ለማወቅ ጥረትን ያደርጋል። ይህ ጥረት በውስጡ ለሚነሡ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስን ከመስጠት ይልቅ ጥያቄዎችን እያበዙበት ይሄዳሉ። ስለዚህም ቶሎ የሚረዳው ነገር ቢኖር ቁሳዊ ነገሮችም ሆኑ የራሱ ማንነት የሕይወት ጥያቄዎችን ለመመለስ አቅመ ቢስ መሆናቸውን ነው። አንዳንዴም ሰው የሕይወት ጥያቄው በሥጋዊ ምኞት፣ በእውቀት፣ በሃብት ወይም በሥልጣን እና በመስል ነገሮቻቸው መልስን የሚያገኝ መስሎት በእድሜው ይዳክራል፤ ማንነቱንም ያባክናል። ተስፋ አድርጎ መልስ ይሆኑኛል ብሎ የሚጓጓላቸው ነገሮች ጋር ሲደርስ ይበልጥ ባዶ ፍጡር መሆኑን ሲነግሩት፤ ሰው ርካታንና የማንነቱን ሙላት ጠለቅ ባለ ዓላማ ውስጥ እንደሚገኝ ያየዋል። ስለዚህ በዘመናት ሂደት ወይም በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ሰው ሕይወቱን ይሞላልኛል ብሎ ላመነበት ዓላማ ማንነቱን መስጠቱ የተለመደ ክስተት ነው። ምክንያቱም የሰው ሕይወት ቁምነገሩ ኖሮ ማለፉ ብቻ ሳይሆን በዓላማ መኖሩ ነው። ስለዚህ ከዚህ ሰዋዊ ዝንባሌ አንጻር ስናየው ሰው ብቻውን ገለል ብሎ በሆነ ዓላማ ለመኖር መወሰኑ የምንኩስና ሕይወት በተወሰነ መልኩ ተፈጥሮአችን ውስጥ አለ ለማለት ያስደፍራል።

  ሰው በኖረባቸው ዘመናት ሁሉ በተለያየ ስምና ከብዙኃኑ ሕዝብ ተለይተው በአንድ ግብ የሚጓዙ የማኅበረሰብ ክፎሎች ነበሩ። በትዳር መተሳሰርን ትተው፡ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው በመራቅ ከሃብትና ንብረት ይልቅ ለአንድ ዓላማ የሚኖሩ ጥንታውያን ግሪካውያን፡ ሮማውያን . . . ነበሩ።

  አንዳንዶቹ በሚያጠኑት የእውቀት ዘርፍ ፍጹም የሆነ እውቀትን /ጥበብን/ ለመገብየት፣ በያዙት ሙያ ጫፍ ላይ ለመድረስ /በስፖርት፣ በፖለቲካ/ ለብቻቸው የሚኖሩ ነበሩ። በፕሌቶ /አፍላጦን/ <> በሚለው መጽሐፉ እንደተገለጸው ለፍትሐዊና ሰላማዊ የሕዝብ አስተዳደር ራሳቸውን ከብዙኃኑ ለይተው - ወላጆቻቸውን እንዳያውቁ ተደርገው፣ ለ30 ዓመታት ያህል ልዩ ትምህርት እየተሰጣቸው፣ የግል ንብረት ሳይዙ በጋራ በመኖር ሙሉ ሕይወታቸውን ለፖለትካዊ ፍልስፍና የሚሰጡ ወንዶችና ሴቶች እንደነበሩ እናነባለን።

  እንዲሁም ከማኅበራዊ ሕይወትና ራስን በማግለል ሁሉን ነገር በመመነን ውስጣቸው ያገኙትን እውነት /እውቀት/ ሙሉ ለማድረግ የሚጥሩ ፈላስፎች እንደነበሩ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ4ኛው ክ.ዘ. መጀመርያ ላይ የነበረው ዲዮጋን የሚባል ግሪካዊ ፈላስፋ ምሳሌያዊ ነው። ዲዮጋን ሙሉ ምርምር ለማካሄድና በነጻነት ጥልቅ ሃሳቦችን ለማሰላሰል ያግዘው ዘንድ በማሰብ ውሃ ከሚጠጣባት ጣሳ በስተቀር ሁሉን ነገር መነነ። ይጓዝ የነበረውም ባዶ እግሩን ሲሆን ቀንም ሌሊትም የሚለብሳት አንዲት ካባ ነገር ብቻ ነበረችው። ዲዮጋን ፈላስፋው በዚህ ሁኔታ ሳለ አንድ ቀን አንድ ሕፃን ልጅ በአንድ የወንዝ ዳርቻ ሆኖ በእጁ ውሃ እየጨለፈ ሲጠጣ አየው። ይህንንም ሁኔታ ፈላስፋው በማስተዋል <> በማለት ለመጠጫነት ይጠቀምባት የነበረችውንም ጣሳ እንደተዋት ይነገራል።

  ይህንን እና መሰል ቅድመ ክርስትና ታሪኮችን ስናስተውል ገለል ብሎ ተፈጥሯዊ ስሜቶችን በመቆጣጠር ከነርሱ ባርነት ነፃ በመሆን የሆነ ዓላማን የመከተል ሕይወት በክርስቲያናዊ ምንኩስና ያልተጀመረና ሁሉን አቀፍ መሆኑን ያስረዳናል። በዚህም ምክንያት ከክርስቶስ ልደት በፊትና በኋላም የተነሡ ሃይማኖቶች ዓላማቸውና መልካቸው ቢለያይም የየራሳቸው የምንኩስና ሕይወት አላቸው። ክርስቲያን ባልሆኑ ሃይማኖቶች ቀደም ብለው በተለያዩ ዓላማዎች እነዚህ ነገሮች ነበሩ። በአዲስ ኪዳንም ምናኔ ከሚገልጹ ጽሑፎች መካከል 1ቆሮ. 7:31፤ ማር.10:17-31፤ ማቴ.6:19-20፤ 10:16-23፤ 19:12፤ 19:16-22፤ ሉቃ.12:13-21 ን መጥቀስ ይቻላል። ክርስቲያናዊ የምንኩስና ሕይወት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚዘወተር ራሱን የቻለ ዓይነት የአናኗር ዘይቤ ነው። ይህን ሕይወት የሚመርጡ ክርስቲያን ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ክርስቲያኖች ሁሉ ሊኖሩት የሚገባቸውን የጥምቀት ጸጋ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር በመለየትና በመስጠት በተለየ ሁኔታ እርሱን በማኅበራዊ ሕይወት ለመከተል የሚሹ ናቸው።

  በርግጠኝነት ገዳማዊ ሕይወት መቼና የት እንደተጀመረ መናገሩ አዳጋች ነው። ምክንያቱም ገዳማዊ ሕይወት ሌላ ሳይሆን የክርስትናን ሕይወት ለመኖር ሲባል የተጀመረ እንጂ የተሻለ ተብሎ የተመሠረተ አይደለም፤ ስለዚህም በግላዊ የጸጋ ሕይወት ውስጥ የግለሰቡና የእግዚአብሔር ግንኙነት የሚያሳድጉት ዓይነት ስለሆነ ይህንን በጊዜና በቦታ ማለትም በታሪክ ማመላከቱ አስቸጋሪ ነገር ነው። ስለ ክርስቲያናዊ ምናኔ ስናወራ በመጀመሪያው ክ.ዘ. ደናግልና መበለቶች የጀመሩት ዓይነት ሕይወት እንደነበረ አውስተናል፤ ሆኖም ግን ያ በምንም መልኩ ዛሬ እንደምንረዳው ገዳማዊ ሕይወት ነው ማለት አይደለም።

  ለመጀመሪያዎቹ ሦስት ክፍለ ዘመናት ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት እጅግ ይሰደዱና ይገደሉም ስለነበር የሰማእትነት ዘመን ነበር፤ ሆኖም ግን ከአራተኛው ክ.ዘ. ማለትም ከ313 ዓ.ም. ጀምሮ በነገሥታት ደረጃ የክርስትና እምነት ተቀባይነት እያገኘ መምጣት ሲጀምር ስደትና ሰማእትነቱም እየቀነሰ መምጣት ጀመረ። ስለዚህም የምነና ሕይወት የሰማእትነትን ዋጋ እንደሚተካ በማሰብ መዘውተር ቀጠለ። አንዳንድ ክርስቲያኖችም ስለ እምነታቸው ባይገደሉም እንኳ በሕይወታቸው ዋጋን ለመክፈል ይበልጥ እንዲመቻቸው ወደ ምድረ በዳ/በረሃ በመሄድ የጽሞናና የዓላማ ሕይወትን መኖር ጀመሩ። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ነጥብ ገዳም የሚለው ቃል በግእዝ ቋንቋ ሥርወ ትርጉሙ ምድረ በዳ ወይም በርሃ መሆኑን ነው፤ ስለዚህም ገዳም ገባ ስንል ትክክለኛ ታሪካዊ አንድምታውን ያስተላልፍልናል።

  ልንገምት እንደምንችለው ይህ ሂደት በግለሰብ ደረጃ የሚጀምርና የኋላ ኋላ ግን ማኅበራዊነትን ያስከተለ መሆኑን ነው። በርግጥም በዚያ ዘመን እንደ ባሕታዊ ሆኖ ወደ ምደረ በዳ መግባቱ እየተዘወተረ መጣ። ነገር ግን ብዙም ሳይዘገይ እነዚህ ባሕታውያን ተሰባስበው በምድረ በዳ/በገዳም በአንድነት መኖር ጀመሩ። ይህ ማለት ግን የግል ጸሎት ሕይወታቸው ተቋረጠ ማለት አይደለም። ከአምላካቸው ጋር የሚገናኙበት የግል ጊዜ አላቸው፤ እንዲሁም ከወንድሞች ጋር የሚወያዩበትና የሚመገቡበት የጋራ ጊዜ ነበራቸው። በአንድ ላይ በመሆንም ይወያያሉ የሕይወት ተሞክሮቻቸውን ይካፈላሉ፣ አንዱም ሌላውን ያገልግላል። በዚህም መልኩ ያላቸውን ንብረት በመጋራት፣ በመተሳሰብና አንድ ልብ በመሆን ይህ ሕይወት በሐዋርያት ሥራ 2:42 ላይ የምናገኛትን የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ማንጸባረቅና የመላይቱ ቤተ ክርስቲያን አነስተኛ አምሳል መሆን ጀመረ። ምናኔን በድፍኑ ጥሩ ነው ወይም መጥፎ ነው ብለን ፈርጀን ከማለፍ ይልቅ ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን የሚ ችልበትን ነገር አስበን ከታሪኩ ተምረን ማለፍ melkam ነው http://www.ethiocist.org/index.php/nex-blog/2012-04-07-00-12-49/573-7

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከጽሁፍህ ስለ መነኰሳት ሕይወት ሲያብራራ “ከአምላካቸው ጋር የሚገናኙበት የግል ጊዜ አላቸው፤ እንዲሁም ከወንድሞች ጋር የሚወያዩበትና የሚመገቡበት የጋራ ጊዜ ነበራቸው። በአንድ ላይ በመሆንም ይወያያሉ የሕይወት ተሞክሮቻቸውን ይካፈላሉ፣ አንዱም ሌላውን ያገልግላል። በዚህም መልኩ ያላቸውን ንብረት በመጋራት፣ በመተሳሰብና አንድ ልብ በመሆን ይህ ሕይወት በሐዋርያት ሥራ 2:42 ላይ የምናገኛትን የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ማንጸባረቅና የመላይቱ ቤተ ክርስቲያን አነስተኛ አምሳል መሆን ጀመረ።” የሚለውን ሳነብ ልቤ ተነካ ፡፡

   በዚህም ምክንያት በበዓለ ሃምሳ የተፈጸመውን ተአምር ከተመለከቱትና የሐዋርያው ጴጥሮስን ስብከት ካዳመጡት መሃከል “ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤ በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር። ነገር ግን በሰው ሁሉ ፍርሀት ሆነ፤ በሐዋርያትም እጅ ብዙ ድንቅና ምልክት ተደረገ። ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤ ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር። በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ፥ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።” ሥራ 2፡41-47 የሚለውን መልሼ አነበብኩት ፡፡

   የመነኰሳቱን አኗኗር በቅርብ ሆኜ እስከ ዛሬ ስላልተመለከትኩት ከዚህኛው የመጽሐፍ ቃል አልተዛመደልኝም ነበር ፡፡ ከዚህ መግለጫ ስነሳ ግን በዓለማውያን ዘንድ ካለችው ቤተ ክርስቲያን ይልቅ ፣ በገዳማውያን የምትዘወተረዋ የዕለት ተዕለተ ተግባርና ኀብረት ሐዋርያዊ ናት ማለት ነው ፡፡ ትክክለኛዋና እውነተኛዋ የኢየሱስ ተከታዮች ልምምድም የምትገኘዋ በነርሱ ዘንድ ብቻ ነው ለማለት ያስደፍራል ፡፡ እኛ ሁላችን የቀለም ምላጮች ሆነን ነገርን እያጠላለፍን ፣ የራሳችንን መድረሻ በርግጠኝነት አጣርተን ሳናውቅ ፣ በግላቸው ሊድኑ የሚታገሉትንና የሚደክሙትን ፣ ለራሳቸው ቀናውን መንገድ የመረጡትን አባቶችና እናቶች ያለ አንዳች ሃፍረት እንቃወማለን ፡፡ እግዚአብሔር ለሁላችንም ቀና ልቡና ሰጥቶ እውነትን ያስተምረን እላለሁ ፡፡

   ሁሉን የቃኘ ዘገባ ያቀረበውን ወገኔንም በጣም አመሰግናለሁ ፡፡

   Delete
  2. ምእመን... በድንግልና ሕይወት እግዚአብሔርን ስለ ማገልገል መጽሐፍ ቅዱስ በሚገባ ያስተምራል። ማቴ 19፤10- 1ቆሮ 7፤25-39 ጥያቄው ግን «ድንግልናና ምንኩስና አንድ ናቸውን?» የሚለው ጥያቄ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በድንግልና የኖሩና በድንግልናም ስለመኖር የተናገረበት መንፈስ መነኩሴ ስለመባሉ ምንም ያለው ነገር የለም። ምንኩስናን ደናግላን ብቻ ሳይሆኑ መአስባንም /ባለትዳሮችም/ የሚከተሉት ህግ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ስለደንግልና ከሚናገረው ሃሳብ ጋር የምንኩስና ህግ ምንም ግንኙነት እንደሌለው ነው። ምንኩስና በጫካና በበረሃ ኑር የሚልን ልምምድ የሚያስተምር ሲሆን ወንጌል ግን ለእግዚአብሔር ቃል መስፋፋት ያለጋብቻ በድንግልና መኖር ጠቃሚ እንደሆነ እንጂ ወደጫካ መሄድ አስፈላጊ ስለመሆኑ አያስተምርም።
   ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ድንግልናን የሚደግፈው፤


   1/ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ጥሪ መሠረት ለአገልግሎት ራሳቸውን የለዩ ማለትም እግዚአብሔርን ለማገልገል ብለው ሃሳባቸውን በዚህ ዓለም የትዳር ፈተና /ሚስትና ልጆችን በመውለድ/ ምክንያት ልባቸው ተከፍሎ የእግዚአብሔር መንግሥት መስፋፋት ሥራ እንዳይተጓጎል የሚያደርጉት ውሳኔ ነው። /እንደሐዋርያው ጳውሎስ ማለት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ለወንጌል አገልግሎት የተለየና በድንግልና የኖረ ሰው እንጂ መነኩሴ አልነበረም/

   2/ በተፈጥሮ ጃንደረባ የሆኑ ወይም ሰዎች ጃንደረባ ያደረጓቸው ከትዳርና ልጅ ከመውለድ ሕይወት ጋር የተራራቁ ስለሚሆኑ ራሳቸውን በድንግልና ሕይወት ውስጥ መኖር እንደሚችሉ ሲያገነዝበን ይታያል።


   እንደመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ከዚህ ውጪ ሰዎች በድንግልና እንዲኖሩ የሚገደዱበት መንገድ የለም። ይሁን እንጂ ምንኩስና የሚባለው ሕግ ለደኅንነት፤ ለጽድቅና መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ተብሎ በድንግልና መኖርን የሚሰብክ መንገድ ነው። ይህ መንገድ የሰዎች ህግ እንጂ የእግዚአብሔር ቃል መሠረትነት የሌለው ለጽድቅና ለመዳን የሚደረግበት የትግል መድረክ በመሆኑ በልዩ ልዩ ፈተናና ውድቀት ውስጥ የሚታለፍበት መንገድ መሆኑም እርግጥ ነው። ይህም «የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም» ያለው ቃል እንደተፈጸመ ያሳያል። ሮሜ 10፤3 ምክንያቱም ጽድቅ በክርስቶስ ደም የተሰጠንና በእምነት የምንቀበለው ስጦታ እንጂ እኛ በምናደርገው ተጋድሎ የሚገኝ አይደለም። በእምነት የተቀበለውን ጽድቅ ሥራ ከመጠበቅ ውጪ በጥረት የሚመጣ አይደለም። ሮሜ 5፤16 ኤፌ 4፤24 በኢትዮጵያ ውስጥ ይሁን በዓለም አቀፍ ሃይማኖቶች ውስጥ እየታየ ያለው የምንኩስና አስነዋሪና የፈቲው ውድቀቶች እየጎሉ በመምጣታቸው የተነሳ በትግል የማይወጡት መሆኑን መነሻም በትግል ጽድቅ ለመስራት የመሞከር ውጤት ነው።
   ዓለማውያኑን በመፈወስና ከእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል በማገናኘት ወደዘላለማዊው መንገድ መምራት የሚገባቸው ሰዎች ለመጽደቅ የተመረጠው መንገድ ምንኩስና ነው በማለታቸው ሰባኪና መምህር ጠፍቶ ዓለማውያኑ ከእውቀት ማነስ የተነሳ በኃጢአት ውስጥ በመኖር በመነኮሳቱ የጽድቅ ስራ ላይ የመዳን ተስፋ እንዳላቸው እንዲያስቡ ተደርገዋል። ዛሬም በመነኮሳቱ የቀደመ ሥራ ላይ ተስፋን በማድረግ አማልዱኝ የሚሉ ድምጾች የመብዛታቸው ምክንያት ይሄው ነው። ክንፍ የበቀለበት ቀን፤ እግር የተቆረጠበት እለት፤ መሬት የቀደዱበትና ሱራፌል የሆኑበት መዓልት እያሉ በየገዳማቱ እየዞሩ በጸሎትዎ ያስቡኝ፤ ጻድቁ አይርሱኝ የሚለው ልመና መሠረቱ መነኮሳቱ በሥራቸው ጸድቀው፤ያጸድቃሉ፤ እኔ ግን ኃጢአቴ ብዙ ስለሆነ የመዳን ተስፋዬ የመነመነ ነው ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።

   Delete
  3. ምእመን...የክርስትና ጽድቅ ክርስቶስ እንደሆነ የዝንጋዔ ልቡና በሕዝቡ ውስጥ ያሰረጸው ይህ ምንኩስና የሚሉት ፍልስፍና ነው። «ወንጌል ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ» ሲል የክርስቶስን የማዳን መንገድ የሚከተሉ ማለቱ እንጂ በመነኮሳት ተጋድሎ ላይ የሚንጠላጠሉ ማለቱ አልነበረም። ጽድቅ በሰው ልጆች ትግልና ውጣ ውረድ የሚመጣ ቢሆን ኖሮ ሐዋርያው « እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ» ሮሜ 5፤18 ባላለም ነበር።


   የምንኩስና መስራቾች የ4ኛው ክ/ዘመን ግብጻውያን ሰዎች መሆናቸው እርግጥ ነው። እነዚህ ሰዎች ጀምረውታል ከመባሉ ከ4ኛው ክ/ዘመን በፊት በቤተክርቲያን ውስጥ እንዳልነበረ ይታወቃል። ድንግልናን በመከተል ይሁን መአስብነትን በመተው ከምንኩስና ሕግ ጋር የመስማማት መሠረቱ በአንዳንዶች በኩል የዓለማዊ አስተሳሰብ ወደቤተክርስቲያን በመግባቱ የፈጠረባቸውን ሃዘን ለመሸሽ፤ አንዳንዶቹም ዓለማዊው ኑሮ አስቸጋሪ ሲሆንባቸው ከዚህ ለመገላገል፤ ሌሎቹም የመኖር ተስፋቸው ሲሟጠጥ «ሄጄ እዚያው ልሙት» ከሚል አስተሳሰብ የተነሳ እንደሆነ ከምንኩስናው መጽሐፍ ስንረዳ ሰው ሰራሽነቱን ያጎላዋል። ሥርዓቱን ቤተኛ ያደረጉት ሰዎች ተዋጽዖ «አባ በእንተ ነፍሱ፤ አባ በእንተ ከርሱና አባ በእንተ ልብሱ» ናቸው። የምንኩስና የሕይወት መገለጫዎች መሆናቸውን መናገሩ የምንኩስናን መሠረት ሰዋዊ ሥርዓት መሆኑን እንደማሳያ መውሰድ ይቻላል። ምንም እንኳን «አባ በእንተ ነፍሱ» የተባለው እጸድቅበታለሁ ብሎ ቢገባበትም ጽድቅ የሰው ልጆች ትግል ገጸ በረከት ስላይደለች ዓላማው መንገዱን የሳተ ከመሆን አያልፍም። ምንኩስና ከመጽሐፍ ቅዱሱ ቃል ጋር ራሱን በማስጠጋትና መንፈሳዊ ምስል በመቀባት ቤተክርስቲያን ውስጥ የተተከለ ሰው ሰራሽ ስርዓት ነው። የተፈጠረበት ዓመተ ምህረት እንደሚያስረዳው አመጣጡ ከቅዱሱ የእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የግኖስቲኮች ጋር ሲስማማ ይገኛል። ውርርሱም ከሂንዱይዝም፤ ቡድሂዝምና ዞሮአስተራኒዝም ጋር ነው። ምንኩስና የሚባለው ስርዓት በ4ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ሳይተከል ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረ ስርዓት ነው። ወንጌል ደግሞ አዲስ የሕይወት መንገድ እንጂ የቡድሂዝምን የምንኩስና ስርዓት አስፈጻሚ ባለመሆኑ አንድም ቦታ የዚህን ስርዓት ጠቃሚነትና አስፈላጊነት አልተናገረም። ስለሆነም ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው ይህ ሥርዓት የክርስትናን መልክና ቅርጽ ይዞ በግብጽ በኩል ወደ ዓለም ሊሰራጭ በቅቷል።
   ይህች ግብጽ ለዓለም ያበረከተችው ይህንን ብቻ አይደለም። የእስላሙን መስራች መሐመድን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አጣምመው ያስተማሩት መነኩሴ ግብጻዊ እንደነበሩ ታሪክ ይናገራል። የቶማስ ወንጌል፤ የማርያም መግደላዊት ወንጌል፤ የባርናባስ ወንጌል፤ የይሁዳ /ሰያጤ እግዚኡ/ ወንጌልን ጽፈው ለዓለም አበርክተዋል። እነዚህ መጻሕፍት እንደቤተክርስቲያን ቅዱሳት ባይቆጠሩም ለብዙዎች መሰናከያ ሆነዋል። ግብጻውያኑ ብዙ የክህደትና የፍልስፍና መጻሕፍት ምንጮችም ነበሩ። ከዚህ የተነሳ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የነበረውን የምንኩስና ሥርዓት ጎትተው በማምጣት ክርስቲያናዊ መልክ ቀብተው በዓለም ቢያስፋፉት ብዙም አያስገርምም። አሳዛኙ ነገር ዓለሙ ሁሉ ይህንን ስርዓት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አድርጎ በመቁጠር የወንጌል ዘመን አዲስ ግኝት አድርጎ በህግ መተግበሩ ነው።
   የምንኩስና ሕግጋት የምሥራቃውያንን ሃይማኖቶች የተከተለ ስርዓት ነው። ቢጫ መልበስ፤ መቁጠሪያ መቁጠርና መሬት ላይ እየወደቁና እየተነሱ መስገድ ከክርስትና መምጣት 500 ዓመት በፊት ሲደረግ የመቆየቱ ነገር ዛሬም ይኼው ስርዓት ከክርስትናው ጋር በተመሳሳይ መልኩ ይከናወናል። እንጨት አለዝቦ፤ ቅርጽ ቀርጾ፤ በሚያስቡት የኅሊና ፍላጎት መልኩ መላእክትን፤ የሚያመልኩትን ጌታ ስእል ስሎ፤ እጣን ማጠንና ለእነሱም መስገድ የቡድሂዝም ቀደምት እምነት መሠረቶች ናቸው። ይህንኑ ድርጊት በክርስትናው ዓለም ያስፋፉት እነዚሁ የቡድሂዝምና ሂንዱይዝም ቅጂ ግብጻውያን መነኮሳት ስለመሆናቸው የድርጊቱ ተወራራሽነት አመላካች ነው።

   Delete
  4. ምእመን...መጽሐፍ ቅዱስ «ጋብቻ ክቡር፤ መኝታውም ንጹህ ይሁን» ይላል እብ 13፤4 አንተና አንተን መሰሎች ደግሞ፤
   «እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፥ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል እንዲርቁ ያዝዛሉ» 1ኛ ጢሞ 4፤3 ተብሎ እንደተነገረባችሁ ትንቢት ጋብቻን የሚቃወም ህግ አስፈላጊ ነው፤ከምግብም ተከልክሎ ራሱን ማድከም አለበት ብላችሁ ይህንኑ ትንቢት ትፈጽማላችሁ። መጋባትን የሚከለክል ህግ ያለምንኩስና በዚህ ምድር ላይ ምን አለ? ወንድሜ እስኪ ጋብቻ ጥሩ አይደለም የሚል ስርዓት ሌላ ይኖር ይሆን?የአንተ የምንኩስና ህግ በበረሃ እስከህይወትህ ፍጻሜ ለጽድቅ ስትል ኑር የሚል ሲሆን የመጥምቁ ዮሐንስ መንገድ ደግሞ አዋጅ እየተናገርክ ስለእውነተኛው ብርሃን በአደባባይ መስክር የምትል ናት።

   Delete
  5. ለ Anonymous February 13, 2013 at 6:33 AM

   - ድንግልናና ምንኩስና አንድ ናቸውን ?
   መጀመሪያ እኔ በድንግልና ስለመኖር ለማስተማር አልጻፍኩም ፤ የልጆች አባት ስለሆንኩ በድንግልና ኑር አትኑር በሚልም አልተከራከርኩም ፡፡ የወንጌል ቃል የሚለውንና ጌታም በጃንደረባነት የሚኖሩትን እንዳላወገዘ ለአስረጅነት ብቻ ጠቅሻለሁ ፡፡ በድንግልና መኖር ፣ ጾምና ጸሎትን የማያምንበትና የሚከብደው ሰው ሁሉ እንደ ፍላጐቱ መሆን ይችላል ፡፡ የመጽሐፍ ቃል ግን እንዲያ እንደምትፈልጉት በዓለምና በሥጋ ነገር ተጠምዳችሁ ሁኑ እንደማይል መታወቅ ይኖርበታል ፡፡ የሥጋን ነገር የሚያስብ ስለ ስጋው ፈቃድ ይጨነቃል ፤ የሥጋ ስሜቱን የናቀና የገደበ ግን ለመንፈሳዊው ተጋድሎ ይነሳሳል ፡፡ የአንዳንዱ ሰው ዝንባሌ ፣ በድንግልናም ሆነ ያለ ድንግልና በምንኩስና ሕይወት መኖር ከሆነ ፣ ምርጫውና ፍላጐቱ መከበር አለበት የሚል እምነት አለኝ ፡፡ ለምሳሌ ሉተር ምንኩስናን ጀመረ ፤ የሥጋ ፍላጐቱ አስቸገረው ከሮም ጳጳስ አተካራ ገጠመና አቋሙን ገሃድ ሲያወጣ ብጤውን መነኩሲት (Kathryn von Bora) አግብቶ ስድስት ልጅ ወለደ ፤ አራት ማደጎዎችን አሳደገ ፤ በመጨረሻም ትዳር ከገዳም የተሻለ ትምህርት ቤት ነው ብሎ መግለጫ አወጣ ፡፡ ይኸ ሰው ለራሱ የሚስማማውንና የሚመቸውን መንግድ መርጧል ፤ ከዛ አልፎ ግን በሽፍን የርሱ መንገድ ትክክል ነው ፣ ህግ ይሁንላችሁ የሚለው ስብከት ለእኔ አይጥመኝም (ናችሁ ለማለት ሳይሆን የመጀመሪያው የምንኩስና ተቃዋሚ ስለሆነ ተጠቅሷል)፡፡

   ምንኩስና ዓለማዊውንና ስጋዊውን ፍላጐት ገድቦ ፣ ተፈጥሯዊ ስሜትን ተቆጣጥሮ ፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ለመኖር ተጋድሎ የሚደረግበት ሥጋዊና መንፈሳዊ ልምምድ ነው ፡፡ ለዚሁ ትግል ጥሪው በልጅነት ከሆነ በድንግልና ሲጀመሩት ፣ ያገቡና ልጅ የወለዱም ቢሆኑ ድክመታቸውን በሚገነዘቡበት ሰዓት ዓለምን ንቀው ፣ ሃብት ንብረታቸውን ትተውና ዋጋ ነስተው የምንኩስናን ሕይወት እንደሚመርጡ አውቃለሁ ፡፡ አሁንም እኔ ማንንም በድንግልና ቆይተህ መንኩስ ለማለት አልደፍርም ፡፡ ክርስትና በምርጫ እንደሆነች ሁሉ ምንኩስናም የግለሰብ ፍላጐትና ምርጫ ነው ፡፡ ማንም በሌላው ላይ የሚጭነው ሥርዓት አይደለም ፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ንስሓ ግቡ ፣ ሥጋወ ደሙን ተቀበሉ በማለት ታስተምራለች እንጅ መንኑ ፣ መንኩሱ ብላ አትሰብክም ፤ እንዲያውም እንዳትሳሳቱና እንዳትወድቁ በማለት የጽሞና ጊዜ ሰጥታ በጾምና በጸሎት ራሳቸውን እንዲፈትሹ ታደርጋለች ፡፡ የዚህን ዓለም ጣጣ ለመካድ ከበቁላት ደግሞ ፈቃዳቸውን ትፈጽማለች ፣ አክብራ ትይዛለች ፣ እንዳይሳሳቱም ታበረታታለች ፡፡ ሥርዓቱ ከባድ የሥጋ ፈተና መሆኑ ስለሚታወቅ ፣ የጠየቀ ሁሉ ዕለቱን አይመነኩስም ፡፡ ከዚህ አልፎ ምንኩስናን እንደምታስተምርና እንደምታደፋፍር አድርጎ የሚዘግበው የተቃዋሚ ጎራ ነው ፡፡ ግለሰዎች በራሳቸው ተነሳሽነት መንገዱ ይኸ ነው ብለው ሲመርጡት ግን አታወግዛቸውም ፤ መጽሐፋችንም ከዓለም የሚለዩትን አይቃወምም፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን ዋና ትምህርት በሃይማኖትና በቅድስና በዓለም እንድንኖር ወንጌልን በሰዎች ልቡና ለማስረጽ ነው ፡፡

   - “ምንኩስና በጫካና በበረሃ ኑር የሚልን ልምምድ የሚያስተምር ሲሆን ወንጌል ግን ለእግዚአብሔር ቃል መስፋፋት ያለጋብቻ በድንግልና መኖር ጠቃሚ እንደሆነ እንጂ ወደጫካ መሄድ አስፈላጊ ስለመሆኑ አያስተምርም።”
   አንተ ያለህ ዕውቀት ለራስህ ይሁንልህ ፡፡ ጌታችን ለመፈተን ወደ ምድረ በዳ (ገዳመ ቆሮንቶስ) የተወሰደው ወንጌልን ለማስተማር ወይንስ ጽድቅን ፈልጐ ነው ? ለእኔ ግን እኛ መከተል ያለብንን ሥርዓት ሊመሠርትልን ነው ፡፡ የስጋን ፈተና መቋቋምህን በትክክል ሳታረጋግጥ ማኪያቶ እየጠጣህ ለማስተማር ከወጣህ ፣ ይሄ በየመስኰቱ የምናያቸውን የመድረክ ተጫዋቾች ነው የምትሆነው ፡፡ ስለ ሰማያዊው ለማስተማር ፣ ራስን መጀመሪያ ከምድራዊ ፍላጐትና አስተሳሰብ ነጻ ማድረግ ፣ በጾምና በጸሎት መትጋት ፣ በምግባርም እየታነጹ ሰማያዊውን በአንክሮ ማየት ፣ እግዚአብሔርም እነዲረዳ መለመን ያስፈልጋል ፡፡

   - “ለመጽደቅ የተመረጠው መንገድ ምንኩስና ነው በማለታቸው ሰባኪና መምህር ጠፍቶ”
   አሁን የኔ አክስት መንኩሳ ነበር ፤ ማንን እንድትሰብክ ይጠበቅባት ነበር ፡፡ ምንኩስና የሚጀመረው የራስክን ጽድቅ በመፈለግ ነው እንጅ ወንጌል አዋቂ በመሆንህ አይደለም ፡፡ ማለትም ከአንዳንዶች በስተቀር ለማስተማር በቂ ዕውቀት የላቸውም ማለቴ ነው ፡፡ ትምህርቱና የወንጌል ዕውቀቱ በሂደት የሚጐናጸፉት ነው እንጅ ፣ አስቀድመው የተካኑትና ምነው እዚህ ቢያስተምሩት የሚሉት አይደለም ፡፡ አንዳንድ መጽሐፍ አዋቂዎች ቢሰደዱም በዛው አካባቢ ለማስተማርና መጽሐፍ ለመጻፍ ስለሚጥሩ ለወንጌል መስፋፋተ የበኩላቸውን አስተዋጸዖ በተዘዋዋሪ ያደርጋሉ ፡፡ እግዜር ሲፈቅድም ወጥተው ያስተምራሉ ፡፡

   - “የምንኩስና መስራቾች የ4ኛው ክ/ዘመን ግብጻውያን ሰዎች መሆናቸው እርግጥ ነው።”
   ይኸ ደግሞ የማን መግለጫ ነው ?
   ከላይ የጻፍኩት የኔ መከራከሪያና ማስረጃ እንደዚህ አይልም ፡፡ እግዚአብሔርን በማገልገል ጽድቅን ማግኘት በማለት ከዓለም መለየት የተጀመረው በብሉይ ኪዳን ዘመን እንደሆነ ከላይ ዘርዝሬአለሁ ፡፡ ሌላ ማስረጃም ከአይሁዳውያን መሃከል ናዝራውያን ፣ አሴናውያን ፣ ቴራፐውት ፣ ቁምራን ማኀበረሰቦች የምንኩስና መሰል ልምምድ እንደነበራቸው ይገልጻል ፡፡ ክርስትና ኋላ መጣሽ ስለሆነ ከርሱ ጋር በተዛመደ መልኩ ብቻ የግብጽ አባቶች ጀመሩ ማለት ይቻል ይሆናል እንጅ የምንኩስና ህይወት ከክርስትና በፊትም ነበረ ፡፡ በቀላሉ መጥምቁ ዮሐንስን ያሳደጉ ፣ ስለ ጽድቅ በማለት ከህዝብ ተለይተው በመልካም ምግባርና በእምነት የሚኖሩ አይሁዳውያን መነኰሳት (Ashina) ናቸው ፡፡

   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
 8. THER ARE SO MANY UNNESSASERY BELIEVES going on in Ethiopia now days why we do not believe in God the father and son Jesus Christ and the Holey sprite instade of anothe unnssesery weastful thing. Only Jesus Crist the way the truth to Heaven. Please understand this believe and follow the rest himself will lead you to the right path.Do not wast your time believe he died for your sin on the cross accept him as your saver.

  ReplyDelete
 9. "እንኳን ኦርቶዶክስ ሌሎቹም የፕሮቴስታንትም ሆኑ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት በየጊዜው ተሀድሶ ያስፈልጋቸዋል፡፡" What does that mean ? Beleh beleh amnebatalehu ,eflegatalehu,ekorekorelatalehu yemtelaten ye- ኦርቶዶክስ betkrstiyan ke-ፕሮቴስታንት ena ke-ካቶሊክ betekrstiyan asanesekat eko.Ayeh endet Dabelos endemichawotebeh!!! Egzeabher mihrtun yelakeleh!!!

  ReplyDelete