Sunday, February 10, 2013

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 10
የግንቦቱ ቅዱስ ሶኖዶስ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ላይ በምስራች አገልግሎት ላይ ካቀረባቸው “ኑፋቄዎች” መካከል ሁለቱን ባለፈው ክፍል አቅርበን ነበር፡፡ ቀሪዎቹ ሁለቱ “ኑፋቄዎች” ደግሞ እነሆ ቀጥለው ቀርበዋል፡፡

“ ‘ሐ. ከተአምረ ማርያም ጀምሮ አዋልድ መጻህፍት ከቀኖና ሃይማኖት ትምህርት ጋር አንዳች ዝምድና የላቸውም፤ ልብ ወለድ ድርሰቶች ናቸው’ በማለት የቤተክርስቲያናችንን አዋልድ ቅዱሳት መጻህፍትን ይነቅፋል፡፡ ኆህተ ብርሃን መጋቢት 2003 እትም፥ ገጽ 4”
“ ‘መ. ሰይጣን ያጻፋቸው ብዙ እንግዳ መጻህፍት ወደ ቤተክርስቲያን ገብተው ዛሬ የውስጥና ውጭ መድረኮችን ተቆጣጥረዋል፤ እነዚህ እንግዳ መጻህፍት (ባዕዳነ ወንጌላት) ገዳማትን መሳለም፣ በቅዱሳን ስም መሰየም፣ በገድልና በድርሳናት መታመን፣ የቅዱሳንን መታሰቢያ ማድረግ፣ ለንስሀ አባት መናዘዝ፣ ፍትሀትና ተዝካር ማድረግ፣ በገዳማት መቀበር፣ ሰባቱን አጽዋማት መጾምና መመጽወት ሰውን ያጸድቃል ከሚለው ትምህርት ጋር በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘውን የእግዚአብሔር ጽድቅ ሸፍኖታል፣ ክርስቶስ የህግ ፍጻሜ ነው፡፡ በገድልና በድርሳን ታሪክ ለደነዘዘ ጆሮ ሞኝነት ሆኖ እንዲቆጠር ተደርጓል፡፡’ በማለት የቤተክርስቲያናችን መጻህፍት ሰይጣን ያጻፋቸው ሲል ይጸርፋል፤ ይነቅፋል፡፡ የቅዱሳንን መታሰቢያ አጽዋማትንና በዓላትን ይቃወማል፡፡ ኆህተ ብርሃን መጋቢት 2002 እትም፥ ገጽ 17 እና 18”

ብዙ ሰዎች አዋልድ መጻህፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወለዱ ናቸው ብለው ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ስላይደለ ራሱን አስመስሎና አሳክሎ መጻህፍትን ሊወልድ አይችልም፡፡ ስለዚህ አዋልድ መጻህፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ ተወለዱ የሚለው አባባል ፍጹም ስህተት ነው፡፡ የክርስትና ትምህርት ምንጩና መሰረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ሌሎች መጻህፍት ሁሉ መጽሀፍ ቅዱስን መሰረት አድርገው ይጻፋሉ፡፡ ነገር ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ እኩል የሚታዩ አይደሉም፡፡ ስህተት ሊገኝባቸው ይችላል፡፡ እውነተኛነታቸው የሚረጋገጠውም በመጽሀፍ ቅዱስ ከተመዘኑ በኋላ ነው፡፡

በዚህ መመዘኛ ሲፈተሹ ኆህተ ብርሃን የተሰኘው መጽሄት አሰፈረው የተባለውና “ከተአምረ ማርያም ጀምሮ አዋልድ መጻህፍት ከቀኖና ሃይማኖት ትምህርት ጋር አንዳች ዝምድና የላቸውም፤ ልብ ወለድ ድርሰቶች ናቸው” የሚለው እውነት እንጂ ሐሰት ነው አይባልም፡፡ እነዚህ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም፣ በመላእክት፣ በጻድቃንና በሰማእታት ስም የተደረሱ አዋልድ የተባሉ መጻህፍት ልብ ወለድ ድርሰቶች መሆናቸውን መካድ አይቻልም፡፡ ተአምረ ማርያምን ጨምሮ ሌሎቹም አዋልድ ድርሳናትና ገድላት በአብዛኛው አገር በቀል ልብ ወለድ ድርሰቶች ናቸው፡፡ በአዋልድ መጻህፍት የሚተላለፈው መልእክት በአብዛኛው በመጽሀፍ ቅዱስ የተላለፈውን እውነት ይቃረናል፡፡ አዋልድ መጻህፍት ከመጽሀፍ ቅዱስ የተወለዱ ናቸው የሚለው አነጋገር የተሳሳተ ነው የምንለው ከዚህ በመነሳት ነው፡፡ መጽሄቱ እንኳን መወለድ ዝምድናም የላቸውም ያለውም ስለዚህ ነው፡፡

ይህን ለማብራራት እንሞክር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ መዳን የሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት በማመን ነው ብሎ ያስተምራል፡፡ አዋልድ መጻህፍት ግን መዳን በቅዱሳን በመማጸንና በስማቸው አዋልድ መጻህፍት እንዲደረጉ የሚያዙትን አንዳንድ ነገር፣ ለምሳሌ በስማቸው ዝክር መዘከር፣ በስማቸው መጠራት፣ በስማቸው የቤተክርስቲያን ህንጻ ማሰራት፣ በስማቸው ወደተገደመው ገዳም መጓዝ ወዘተርፈ ለመዳን ምክንያት እንደሚሆን ይሰብካሉ፡፡ ሁሉም ለማለት በሚቻል ሁኔታ የሚሰብኩት በጻድቁ ወይም በሰማእቱ በኩል መዳን እንደሚገኝ ነው፡፡ ለምሳሌ ተአምረ ማርያም የሚያስተላልፈው ዋና መልእክት መዳን የሚገኘው በማርያም በኩል ነው የሚል ነው፡፡ ድርሳነ ሚካኤልም እንደዚሁ መዳን የሚገኘው በሚካኤል በኩል ነው የሚል ዋና መልእክት ነው የሚያስተላልፈው፡፡   

የአዋልድ ደራሲዎች አላማ በስሙ ድርሰት የሚደርሱለትን መልአክ ወይም ጻድቅ ከፍ ከፍ ማድረግ ስለሆነ ለእነርሱ የሚሰጡት ስፍራ ከአምላክ ጋር ሊስተካከል ይችላል፡፡ በአዋልድ ላይ እንደሚነበበው ቅዱሳኑ በስማቸው የሚደረገውን ነገር ሁሉ ተቀብለው ምህረት ሲያሰጡ፣ ከሞተ በኋላ ወደ ሲኦል የገቡ ነፍሳትን ጭምር ከሲኦል ሲያወጡ በድርሰቱ ውስጥ ያስነብባሉ፡፡ እንዲህ ያለው ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውጪ ነው፡፡ ሰው ከሞተ በኋላ ንስሀ የመግባት እድል የለውም፡፡ መላእክትም የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽሙ እንደመሆናቸው ወደሲኦል የገቡ ነፍሳትን በየጊዜው ከሲኦል ሊያወጡ አይችሉም፡፡ እነ ሚካኤል ከሲኦል እጅግ በርካታ ነፍሳትን በክንፋቸው ተሸክመው አወጡ የሚለው የአዋልድ ስብከት ተረት ተረት ከመሆኑም በላይ ሰው በሕይወቱ እያለ በክርስቶስ እንዳያምንና መልካም ስራን እንዳይሰራ የሚያደርጉና ተስፋውን በመላእክት ላይ ጥሎ እንደፈለገው እንዲኖር የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የበላኤሰብ ታሪክ የሚያስተላልፈው መልእክት ምንድነው? ብለን ብንጠይቅ ሰው እግዚአብሔርን እስከመካድ ደርሶ ቢበድልና በማርያም ቢማጸን ይድናል የሚል ነው፡፡ ይህም ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን አጋንንታዊ ትምህርት ነው፡፡

በተአምረ ማርያም ውስጥ በአጠቃላይ ማርያም ተብላ የተሳለችው ገጸባህሪ በመጽሀፍ ቅዱስ ከምናውቃት ትሁት ከሆነችው የጌታ እናት ማርያም ፍጹም የተለየች ናት፡፡ ስለዚህ ተአምረ ማርያም ልብወለድ ቢባል ትክክለኛ እንጂ የተሳሳተ አይሆንም፡፡ እንዲህ ያለ ይዘት ያላቸውን፣ ሊታረሙና ከቤተክርስቲያን ወደሙዚየም ሊዛወሩ የሚገባቸውን አዋልድ መጻህፍትን “ቅዱሳት” የሚል የማይስማማቸውን ቅጽል መስጠት ቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት እንደሌሏት፣ ካሏትም ሚናቸውን መጫወት እንዳልቻሉ አመላካች ሆኗል፡፡ አዋልድ እንኳን “ቅዱሳት” ሊባሉ ለሃይማኖት ትምህርት ሊጠቀሱ የማይችሉ ድርሰቶች መሆናቸው በሊቃውንቱ ዘንድ ይታወቃል፡፡ በማህበረ ቅዱሳንና በመሰሎቹ ምእመናን ዘንድ ግን ዋና ተደርገው ነው የሚታዩት፡፡

በአጼ ዮሐንስ ዘመን በኦርቶዶክስ አንጃዎች መካከል ቦሩ ሜዳ ላይ በተደረገው የሃይማኖት ክርክር ላይ አለቃ ስነ ጊዮርጊስ የተባሉትን ሊቅ አጼ ዮሐንስ “ሶስት ልደት የሚል ደረቅ ንባብ አምጣ” ቢሏቸው “በደብረ ብርሃን ተአምረ ማርያም ተጽፏል አሉ፡፡ ከምታስተምረው ከአራቱ ጉባኤ አጣህና ስለ ሃይማኖት ተአምረ ትጠቅሳለህን? ቢሏቸው ከጉባኤው መጽሀፍስ የለም አሉ፡፡” (የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ከአባ ጎርጎርዮስ ገጽ 72)፡፡ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ተአምረ ማርያምን ጨምሮ እርሱን የመሰሉ አዋልድ መጻህፍት ስለሃይማኖት ትምህርት ለመጠቀስ የማይበቁና በጉባኤ ቤት ትምህርት የማይሰጥባቸው ልብ ወለድ ድርሰቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የቀደሙት ሊቃውንትና ነግስታቱ ጭምር የሚያምኑት ይህን ነበር፡፡ የዛሬዎቹ ጳጳሳት ግን ለመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሊቀጸል የሚገባውን “ቅዱሳት” የሚለውን ቅጽል በ“ጨዋ” ደንብ ለአዋልድ መጻህፍት በመቀጸል ጨዋነታቸውን አሳይተውናል፡፡ የአዋልድን ትክክለኛ ስፍራ መግለጽ የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስወግዝ ባልሆነም ነበር፡፡ ሲኖዶሱ ግን በሊቃውንት ሳይሆን በምእመናን አመለካከት እየተመራ ስለሆነ ይህን እውነተኛ ምስክርነት ኑፋቄ ሲል ፈርጆ አውግዣለሁ አለ፡፡       
በፊደል “መ” የቀረበውም ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነው፡፡ የተዘረዘሩት የአዋልድ መጻህፍት በጎ ምግባራት ለምሳሌ ገዳማትን መሳለም፣ በቅዱሳን ስም መሰየም፣ በገድልና በድርሳናት መታመን፣ የቅዱሳንን መታሰቢያ ማድረግ፣ ለንስሀ አባት መናዘዝ፣ ፍትሀትና ተዝካር ማድረግ፣ በገዳማት መቀበር” እንዲሁም መጽሀፍ ቅዱሳዊ በጎ ምግባራት “(ሰባት አጽዋማት የሚል በመጽሀፍ ቅዱስ ባይኖርም) መጾምና መመጽወት” ሰውን ያጸድቃሉ ተብለው መሰበካቸው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘውን የእግዚአብሔር ጽድቅ ሸፍነውታል፡፡ ይህን ሀቅ አሌ ማለት አይቻልም፡፡ ይህ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን ከሆነ ከእግዚአብሔር አይደለምና ሊሆን የሚችለው ከሰይጣን ነው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ትምህርቷን መፈተሽና ራሷን ማስተካከል ሲገባት በባዶ ሜዳ ለምን ተነካሁ ማለቷ ራሷን ትዝብት ላይ ይጥላታል እንጂ እውነተኛ አያሰኛትም፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ “መንፈስ ግን በግልጥ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤” 1ጢሞቴዎስ 4፡1-2 የተባለው በቤተክርስቲያናችን ደርሶ ከሆነም ንስሀ ለመግባት ጊዜ አልረፈደም፡፡ የክርስቶስን አዳኝነት ከማስተባበልና ሌሎች አዳኞችን ከመሰየም የበለጠ ምን ሃይማኖትን መካድ አለ? ስለዚህ የአዋልድ ትምህርት ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከአጋንንት ነው መባሉ በእኛ እምነት ምንም ስህተት የለውም፡፡

 ይቀጥላል

 

 

 


12 comments:

 1. enante eneman nachihu? ebakih? Yeayit miskirau.... Yeleba miskir leba new. bekirsitna memtswot tilik metsedkia endehone alemamenh rasu kihdet new. yihe timihrt leprotestantum altekemachew lengeru antes yaw aydeleh. anten bilo lorthodoxawyan metsedkia menged astemari wogegna yilkis nisha gibana rash tsidek.

  ReplyDelete
 2. its funny you quote this "“መንፈስ ግን በግልጥ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤” ለራሳችሁ መሆን አለበት የጠቀሳችሁት!!ባለጌ ሲተርት እራሱን ይሰድባል ማለት እንዲህ ነው

  ReplyDelete
 3. Why only Ethiopian Orthodox church only not following only the Bible.The whole world have only one Bible but Ethiopia Orthodox has meny different books no body even know. Please let us follow the Bible. Do not confused us by bringing different Books.and also only Jesus Christ is lord. Salvation is only by Him. The father the son and Holy sprit.Please Ethiopian Orthodox do not confuse the inosent people.

  ReplyDelete
 4. በሰዎች ያልተጻፈ መጽሐፍ ቅዱስ የት ነው የሚገኘው ? ክርስቶስ የተናገረው እንጅ የጻፈው መጽሐፍ የት ነው የሚገኘው ? ሐዋርያው ጳውሎስ መቸ ነበር ወደ ክርስትና የተለወጠው ?ቅዱስ አትናቴዎስ አይደለም ወይ በ367 ዓ.ም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት 27 ብቻ መሆናቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ የወሰነው ? በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እንዲሁም በሌሎች ቅዱሳን፥ በመላእክት፥ በሰማዕታት ምልጃ ማመን የክርስቶስን አምላክነት መካድ ሁኖ እንዴት ይቆጠራል ? ገዳማትን ማክበርና መጠበቅ ሊያስኮንን ይችላል ? ይህን ሁሉ የምናደርግስ እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት ብቻ ነን እንዴ በዓለም ውስጥ የምንገኘው ? አነዚህን ሁሉ የሚቃወመው የምዕራቡ )ዓለም ፕሮቴስታንት ብቻ ነው። እስቲ ለነዚህ ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ስጡይ....

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከበደ ምናለ ከመጻፍህ በፊት ስለ አጠቃላዩ ትምህርተ ሃይማኖት ጥቂት ብትማር? መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ያለ መጽሐፍ መሆኑን ካላወቅህና ከአዋልድ ተራ ከመደበኸው የአንተ አላዋቂነት ነው ጎልቶ የሚታየው፡፡ በቅድሚያ መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር በተላኩ ቅዱሳን ሰዎች የተጻፈ መጽሐፍ መሆኑን መቀበል አለብህ፡፡ እንደ አዋልድ ማንም ተራ ሰው ተነሥቶ የጻፈው አይደለም፡፡ እነርሱን ለእግዚአብሔር ቃል ግድ የሌላቸው ተራ ሰዎች ናቸው የጻፏቸው፡፡ ለምሳሌ የተአምረ ማርያም ደራሲ ሥጋ ወደሙን መቀበል ያልቻለ ተአምሯን ሰምቶ ይሂድ ሥጋ ወደሙን እንደ ተቀበለ ይቆጠርለታል ይላል፡፡ ይህን የጻፈ ሰው የአንተ ብጤ ተራ ሰው እንጂ በእግዚአብሔር መንፈስ የተመራ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ እባክህ ስምህ ከብዶ አንተ ቅልል አትበል፡፡ ከመጻፍህ በፊት በመንፈስ ባይሆን እንኳ በአእምሮህ ጥቂት ለማሰብ ሞክር፡፡ አትናቴዎስ የዐዲስ ኪዳን መጻሕፍት 27 መሆናቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ መወሰኑን ጠቅሰሃል፡፡ ለምን ወሰነ ይስልሃል? ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወይም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የሚጻፍ መጽሐፍ ስለሌለ ነው፡፡ ወይም መጽሐፍ ቅዱስን አስመልክቶ ሌላ መገለጥ ስለሌለ ነው፡፡ አትናቴዎስም ሆነ ሌሎቹ አበው የጻፏቸው መጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ያደረጉና እርሱን የሚያብራሩ እንጂ አዲስ መገለጥ አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ አዋልድን የጻፏቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ልዩነቱ መጽሐፍ ቅዱስን በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው ቅዱሳን ሰዎች ሲጽፉት፣ አዋልድን ግን በሰይጣን መንፈስ የተመሩ አምልኮተ ባእድን ለማስፋፋት ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ስሑታን ሰዎች ናቸው የጻፉት፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ከሚለው ያለፉና በቃሉ ላይ ሌላ ትምህርት የጨመሩ፣ ከቃሉም ላይ ያጎደሉ ናቸውና መገለጫቸው ይኸው ነው፡፡
   ከበደ ለአንተ ግን ማስተዋሉን ይስጥህ፤ ደጋግመህ ሳታስብ ከመጻፍም ይጠብቅህ

   Delete
  2. Are you really spiritual person ? Yes I am layman who have no theological knowledge. That is why I asked questions from anyone who knows the scripture better than me. However, I did not expect an insult and intimidation from the person(s) who claims to be the teacher of the word of God. Indeed very sad !

   Delete
 5. Jesus Christ said to his Desiple on John 14:6-7"I am the way and the truth and the life no one comes to the father except through me.2 If you know me, you will know my father also". So please answer me why does anybody needw to worship angels or anywhere since he said I am the way what is the problem to understand this?Anybody who read the Bible this is clear to understand. the Bible is not complecated. Does Ethiopian Orthodox has different Bible? we don't have to fight God is above all thing he can order Angels for us to watch over us but he did not say worship the angel he say worship only your God.Does Ethiopian's orthodox church encurage the member to read the Bible?

  ReplyDelete
 6. የተሐድሶ ኑፋቄው ያልተቋረጠ ጥቃት ዋነኛ ዓላማ፤ ምእመናንን ከእናት ቤተ ክርስቲያን እቅፍ በማስኰብለል የበግ ለምድ ለለበሰ ተኩላ አሳልፎ መስጠት ነው

  ውድ የቤተክርስቲያን የስስት ልጆች ሆይ፤ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደተነገረው ቤተክርስቲያናችንን ለመውረስ ረቀቅ ያለ ዘዴ ቀይሰው እየተንቀሳቀሱ ያሉት መናፍቃን የእኛው በሆኑ ግን ለሆዳቸው ባደሩ ጥቂት የማይባሉ ባንዳዎች ሰርገው በመግባት በርካታ ጥፋት እያደረሱ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሲነቃባቸውም “ተሀድሶ የለም” እያሉ የዋሁን ህዝብ ሊያታልሉ ይሞክራሉ፤ ስለዚህ እኛ ልጆቿ ልጅነታችንን በምግባራችን ልናረጋግጥና በቃችሁ ብለን ልናስቆማቸው ይገባል፡፡ ከዚህ በፊት ተሃድሶን በተመለከተ ብዙ ቪዲዮችን በአውነተኛ የተዋህዶ ልጆች ጥረት ሊጋለጡ ችለዋል:: ብዙ ለመስራት ያቀዱት አቅድም ሆነ ያሰቡት አንክርዳዳቸውንም በመምህሮቻችን ምክንያት ትምህርታቸውም ሆነ ያቀዱት አቅዳቸው ለጊዜው ሊከሽፍ ችሏል:: ይህ ማለት ግን ተሃድሶ ጠፋ ማለት አይደለም አሁንም ቢሆን ነቅተን ሁልጊዜ መጠበቅ ይኖርብናል ጌታችንም ቤቴ የጸሎት ቤት አንጂ የንግድ ቦታ አይደለም ብሎ ጠራርጎ አንዳባረራቸው ሁሉ አኛም ከጌታችን በተማርነው መሰረት አነዚህን ተሃድሶአውያንን ጠራርገን ልናስወጣ ይገባል ምክንያቱም ቃሉን ሸቀጥና ንግድ መነገጃ አደረጉት አንጂ ለቤተ ክርስቲያን አና ለሕዝቧ የተቀሙት አንድም ነገር የለም:

  ReplyDelete
 7. its funny you quote this "“መንፈስ ግን በግልጥ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤” ለራሳችሁ መሆን አለበት የጠቀሳችሁት!!ባለጌ ሲተርት እራሱን ይሰድባል ማለት እንዲህ ነው.I Like this comment!!!

  ReplyDelete
 8. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !February 12, 2013 at 11:04 AM

  Geta yebarkeh!

  ReplyDelete
 9. ከጊዜ ማጠር የተነሳ አጠር ያለች መልስ ለማቅረብ ተገድጃለሁ ፡፡
  መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን ለማብራራትና ለመግለጽ በትውፊትና በአባቶች ትምህርት መታገዝ እንደሚያስፈልገው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በማስረጃ አቅርቤአለሁ ፡፡ አሁንም ሌሎች ማስረጃዎችን መደርደር እችል ነበር ፤ እንደ እኔ ያሉ ደካማዎችን ወደ ክህደት ሊመሩ ስለሚችሉ ወይም ተቀናቃኞች መልሰው በትር ስለሚያደርጉብን ማቅረብ አልፈለግሁም ፡፡ ስለዚህም ምክንያት የመጽሐፍ ትርጉምና ፍቺን ለመርዳት የግድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ መመልከት እንደሚኖርብን መቀበል ይኖርብናል ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን (Sola Scriptura! Sola Gratia! Sola Fide! Meaning; Scripture only, Grace only, Faith only) ብቻ ብሎ ጉባኤ ያበዛው ማን እንደሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን ፡፡

  ስለ አዋልድ መጽሐፍም ጭፍን ያለ የጥላቻ ቋንቋ ከማስነበብ ይልቅ በቀናነት ግባቸውንና መልእክታቸውን መመልከቱ ጠቃሚ ነው ፡፡ በወንጌል የጸጋ ስጦታን ምንነት አንብበናል ፡፡ በገድላትና በድርሳናት የሚተረኩት ለአንዳንዶች ተረት የሚመሰሉ መጽሐፍት ግባቸው የእግዚአብሔርን ቸርነትና ረዳትነት ፣ ጸጋውን በተግባር መተርጎሙን ማሳየትና ማጉላት ነው ፡፡ ገብርኤል ከእሳት አወጣ ቢባል ፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ፡፡ የጻድቃኑም ሆነ የቅዱሳኑ ቢባል እንዲሁ እግዚአብሔር ፈቀደላቸው ፤ ረዳቸው ፤ በማለት እንጅ በራሳቸው ሥልጣንና ፈቃድ አደረጉ አልተባለም ፡፡ የእግዚአብሔርን ክብርና ጸጋ ክደው በሌላ አምልኮ የሚጓዙ ከተገኙ ማስተማር ተገቢ ነው ፡፡ ስለ ቅዱሳኑም በስማቸው መዘከር የሚለውም ቢሆን በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም (ማቴ 1ዐ፡42)። ከሚለው የወንጌል ትምህርት የመጣ ነውና ልባችሁን አቃኑት ፡፡

  ReplyDelete