Monday, February 25, 2013

ሲኖዶስ ለእጩነት የቀረቡትን 5 ሊቃነ ጳጳሳት ስም ይፋ አደረገ

በአባ ሳሙኤል የምረጡኝ ቅስቀሳ የታጀበው የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ በአጠቃላይ ከተጠቆሙ 36 ጳጳሳት መካከል በየደረጃው ማጣራት ከተደረገ በኋላ የ5ቱን እጩዎች ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡ በዚሁ መሰረት ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ ብፁእ አቡነ ኤልሳዕ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እና ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እጩ ሆነው መመረጣቸውን የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁእ አቡነ እስጢፋኖስ በመግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ብፁዕነታቸው እንደገለጹት ለእጩነት ከቀረቡት ጳጳሳት መካከል መስፈርቱን ያሟሉትን 5ቱን ኮሚቴው አጣርቶ ካቀረበ በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን ገልጸዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ “ጊዜው የማህበረ ቅዱሳን ነውና ማህበሩ ጣልቃ ገብቶ የሚፈልገውን ፓትርያርክ ማስቀመጥ ካልቻለ ከዚህ በኋላ ምንም ማድረግ አንችልምና አቧራ ማስነሳት አለብን” ያለ የሚመስለው ሀራ ዘተዋህዶ የራሱን ቅጥ ያጣ ጣልቃ ገብነት አስቀምጦ መንግስት ጣልቃ ገብቷል በሚል እየከሰሰ ይገኛል፡፡ ሀሰተኛና የፈጠራ ዘገባዎችን ማስነበቡን የቀጠለው ሀራ ዘተዋህዶ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ያለስምምነት ተቋጨ የሚል ዘገባ በእለቱ አውጥቶ የነበረ ሲሆን እውነታው ግን በአባ ሳሙኤልና አብርሃም ልዩነት በሙሉ ድምጽ ነበር ተወስኖ ነበር ስብሰባው የተቋጨው፡፡ በዚህ ደስ ያልተሰኘው ሀራ ውሳኔውን እርሱ በሚፈልገው መንገድ መዘገብን መርጧል፡፡ ለእርሱ አመለካከት ተስማሚ ሆነው ያልተገኙትን ሁሉ ወርፏል፡፡ ከሁሉም ያስገረመው የማህበረ ቅዱሳን ወኪል ሆኖ በአስመራጭ ኮሚቴው ውስጥ በአባልነት የተሰየመው ባያብልን ለምን እቅዳችንን እንዳናሳካ ትክክለኛ ስራ ሰራህ የሚል ድምጸት ያለውን ትችት አውርዶበታል፡፡ ባያብል በህዝብ ግንኙነት ሃላፊነቱ ሪፖርቱን በማቅረቡ “በኮሚቴው ዋና ጸሐፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ ምትክ የኮሚቴውን ሪፖርት ያቀረበው የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው ለቅ/ሲኖዶሱ ጠረጴዛና ለአጀንዳው ታላቅነት የማይመጥን፣ ውክልናውን   ያጸደቀለትን ማኅበር የሚያስንቅና የሚያስወቅስ ደርዝ የሌለው ንግግር፣” አድርጓል በማለት ማህበሩ እርሱን የወከለበትን አላማ በሚገባ አልተወጣም በሚል ወቅሶታል፡፡

በዚህ ምርጫ እኔ የምለው ብቻ እንጂ ሌላ ማንም መሰማት የለበትም ያለ የሚመስለው የማቅ ልሳን ሃራ መንግስት መራጮችን በከፍተኛ ሁኔታ እያስፈራራ መሆኑን የዘገበ ቢሆንም የማቅ ወኪሉ ባያብል በማቅ አመራሮች ፊት ይህን ማስተባበሉን አውስቷል፡፡ “ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በምርጫው ወቅታዊ ኹኔታ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ በተጠራው የማኅበረ ቅዱሳን የአመራርና የአስፈጻሚ አባላት ጉባኤ ላይ ሪፖርት ያቀረበው የአስመራጭ ኮሚቴው ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ፣ የመንግሥትን ተጽዕኖ  አስመልክቶ የሚቀርቡ ዜናዎች ፍጹም ሐሰት መኾናቸውን፣ በምትኩ ‹‹እኛ ሄድን እንጂ መንግሥት አልጠራንም›› በሚል በርካታ ዘገባዎችን አስተባብሎ ነበር፡፡” ሲልም ጽፏል፡፡ ማቅ እንዲህ በሂደቱ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራት ለምን አስፈለገው? በኮሚቴው ውስጥ የተሰየመውን ወኪሉን ጠርቶ ማነጋገርስ ጣልቃ ገብነትን አያሳይምን? ወኪሉ ላይ ጫና ለማሳደርና የማህበሩን ፍላጎት እንዲያስፈጽም ለመገፋፋት ካልሆነ ለሌላ ለምንም ይህን እንደማያደርግ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ባያብል አደረገ ያለውን ንግግር በሲኖዶስ ፊት ወይም በሌላ ዘንድ ቢናገረው መቼም መንግስትን ፈርቶ ነው ይባል ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን ያለው በማቅ አመራር ፊት ስለነበር ያለውን እውነታ ነው ሊናገር የሚችለው የሚለው የብዙዎች ግምት ነው፡፡ ስለዚህ ሐራ የሐሰት ጭፍራ ብለናል፡፡


ሐራ አክሎም “የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው ቀደም ሲል በጠቀስነው የተወከለበት ማኅበር የአመራሮችና አስፈጻሚዎች የጋራ ስብሰባ ላይ÷‹‹ልዩነት አይደለም በድምፅ ብልጫ እንኳ የወሰነው ውሳኔ የለም፤ ሁሉንም በስምምነት ነው የወሰነው፤›› በማለት ተናግሯል፡፡” ታዲያ ለማቅ ማቅ ከወከለው ከባያብል ውጪ ማን ይታመናል? ነው ወይስ ባያብልም የመንግስት ደጋፊ ነው ለማለት ነው?


ሀራው ሌላ እርስ በርሱ የተጋጨበት ዘገባ አባ ሳሙኤል አሉት ያለው ነው፡፡ ከቅዳሜው ስብሰባ በፊት አባ ሳሙኤል መንግስት የሚፈልገው እኔን ነው ብለዋል እያለ አባ ሳሙኤልን ከመንግስት ጋር ለጥፏቸው ነበር፡፡ አሁን ደግሞ አባ ሳሙኤል ራሳቸው በስብሰባው ላይ ‹‹መንግሥት ፓትርያሪክ አይመርጥልንም›› ሲሉ በአጽንዖት አሳስበዋል፡፡” ሲል ተናገረ የቱን ይታመናል? ይህ ማቅ የማይደግፈውን ሁሉ ከመንግስት ጋር ለማጣበቅ በመሞከር በህዝብ የማስጠላት ስትራቴጂው እንደሆነ ይታወቃል፡፡

“ኮሚቴው ምላሽ ከሰጠባቸው ይልቅ ያልሰጠባቸው ጥያቄዎች በዝተው ዝምታው፣ አንገት መድፋቱ መተከዙ፣ መቆዘሙ (በተለይ በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ እና በብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ላይ ጠንክሮ ታይቷል፤ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የተቃውሞ/ልዩነት ቃል ቢናገሩ ምላሳቸው እንደሚቆረጥ የሚገልጽ ጽኑ የማስፈራሪያ ቃል ከአንድ ጎምቱ ባለሥልጣን እንደደረሳቸው ተዘግቧል፤)፡፡” ታዲያ አባ ቄርሎስ ምን አስፈራቸው? ሀራ የተናገረው እውነት ከሆነና አባ ቄርሎስም እውነተኛ አባት ከሆኑ ለእውነት መስክረውና እውነት ተናግረው ለምን ሰማእት አይሆኑም? በእውነት የማይመስል ነገር ነው፡፡

ኮሚቴው በዕጩ ልየታው ሂደት ላይ እያለ ጫና ለማሳደርና አባ ሳሙኤልን አጉልቶ ለማውጣት ሲል “የጠቋሚዎችን ቁጥር አስመልክቶ በተላለፉት ዘገባዎች፣ ጠቅላላ ብዛቱ ዘጠኝ ሺሕ ያህል እንደሚኾንና ከዚህም 7200 ለብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እንደኾነ ገልጦ ነበር፡፡ መቼም የመረጃ ችግር ኖሮበት ነው እንዳንል ከኮሚቴው ጥቂት የማይባሉት በተለይም የማቅና በሰንበት ትምህርተ ቤት በኩል የተወከሉት የማቅ አባላት እንደሆኑ ከምእመናን ወገን ተብለው ከገቡትም የመንደር ቀኛዝማች የሆኑት ሃይሉ አካለወልድ ምንጮቹ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ ታዲያ እነርሱ አሳስተውት ነው እኛን ጭምር ያሳሳተው ወይስ ሆነ ብሎ? ለማንኛውም እንደዚህ አሃዝ ሁሉ በርካታ መረጃዎችን በተሳሳተና ለማቅ በሚጠቅም መንገድ እየዘገበ እንደ ሆነ ራሱን በራሱ አጋልጧል፡፡ ስለዚህ ሀራንካራሱ በቀር የሚያምነው የለም፡፡

ከዚህ ሁሉ በስተጀርባ ያለው ማቅ እንደ ሆነ ለአፍታም መዘንጋት አይገባም፡፡ ማቅ እኔ የምፈልገው ጳጳስ ፓትርያርክ መሆን አለበት ብሎ አቋም ስለያዘና በኮሚቴው ውስጥ እጩ ጳጳሱ አባ ማቴዎስ ቢካተቱም አቡነ ማትያስ ያሸንፉብኛል ብሎ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሰጋ ስማቸውን ከመንግስት ጋር በማያያዝ በህዝብ የማስጠላት ስራውን በከፍተኛ ሁኔታ እየከወነ ይገኛል፡፡ ይህም የሚያደርገው አቡነ ማትያስ ከተመረጡ እንደ አባ ጳውሎስ አይሸከሙኝም ብሎ ፈርቶ ነው የሚሉ አሉ፡፡


15 comments:

 1. Endya New Enj Aba Selamawoch Kezelabedu Ayqer Dehna Adrgo Mezelabed new Yalew Yagerye Sew? Keto Mechi Yhon Andqen Sile Ewunet Yemtnagerut. Behonem Balhone Mahibere Kidusan Mekises New Beqa Sirachu? Bebete Kiristian Sir Tedebqachu Sewun Kemabalat Lemin wederasachu Bet Athedum. Ewunetengnoch Kehonachu Min Asferachu. Yemtamnutin Emnet Beglis Memesker Min Asferachu Ena new Bematamnubet Emnet wist Gebtachu Endh Yemtbetebtu?

  ReplyDelete
 2. Do you know that MK has stock holder of ESAT media.

  ReplyDelete
 3. አሁን ማንን ለማሳመን ነው የምትሞክሩት ? ወያኔ ጣልቃ አልገባም ነው የምትሉት ? ምን አይነት ክርስትና ነው ያላችሁ? እረ ባካችሁ እግዚኣብሔርን ፍሩ! አየ አንች ኢትዮጵያ ምን አይነት ዜጎችን እያፈራሽ ነው? አባ ማትያስ ወያኔ አይደሉም ነው የምትሉን? kkkkkkkkkkkkkkk

  ReplyDelete
  Replies
  1. አባ ማትያስ ወያኔ አይደሉም ነው የምትሉን? So, What? What is your problem? It is not a sin to be Woyney. It is a sin to hate each other.

   Delete
 4. Abaselamam tamagn lemehon lelochun wushetam malet jemerech. Aye zemen yihun esti legizewum bihon yetesakalachihu mesilual. Lemin hul gize yemitiwukisutil deje selamin alitekesachihum. Lebetekirstian kena yehone hulu beka MK new benanite bete. Yechelemaw budin andiken gudachihu yifelal.

  ReplyDelete
 5. Yihe alubalta yibalal! write your own opinion don't make other your subject. Are you saying that mengist eju yelebetim? ha ha ha ha. Go and tell it to your protestant church.

  ReplyDelete
 6. Don't you have any agenda rather than MK? am very sory for you not having your own mission/agenda rather than Insulting/talking about MK.

  ReplyDelete
 7. Hara Tewahedo opposed MK leadership calling it capitulation fro not supporting restoration of Abune Mekorios Deacon Abayneh know it opposed Bayabel. Is Hara promoting MK? Any body can say its judgment. You are saying this hoping that to isolate Mk from EOTC fathers.

  What else do we expect from tehadiso except creating ansrachy sothat they can steal the sheeps.

  ReplyDelete
 8. ማቅ የቤተክርሰቲያን ጠላት ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማቅ የቤተ ክርስቲያን ሁኖ አያውቅም። ሊቃውንት አባቶቻችን ማቅና ደበሎ ለብሰው ነበር ቤተ ክርስቲያናችንን ከመናፍቃን ሲጠብቁ የኖሩት። ዛሬ ያስቸገረን ጥቁር ለባሽ ነው። የቤተ ክርስቲያንችን ዋናው ጠላትም ራሱን 'ሕዛባዊ ወያናይ ሕዝቢ ትግራይ''ብሎ የሚጠራው የባዕዳን ቅጥረኛ ብቻ ነው ።

   Delete
 9. Geta lebe yesetachehu selamawoch! lemehonu mk kalalachehu emananebe yemeselachehuwal? ahunes betam asetelachehune Geta mesekera new betam yedeberal egna yemenefelegewu alubalta sayehone be Geta kale yetashe ewunet new.

  Be degami

  ReplyDelete
 10. ሁሉንም ነገር እግዚአብሔር የፈቀደው ይሆናል። አቡነ ማትያስንም እግዚአብሔር ከፈቀደላቸው ማንም ጥሩም ሆነ መጥፎ ስለ እርሳቸው ብናገር ልያስቀራቸው አይችል።የእግዚአብሔር ፈቃድ መቀበል እንጅ ገና ለገና ፓትርያርክ ይመረጣሉ ተብሎ ከአንድ መንፈሳዊ አባት ነኝ ከሚል ሰው አፍ ተሐድሶ ናቸው ብሎ መናገር በጣም አሳዛናል አጸያፍ ጥበብ ነው። ምክንያቱም እያንዳንዳቸው ሊቃነ ጳጳሳት ነኝ ብለው የሚናገሩት አባቶች ምን ያህል በእግዚአብሔር ቃል እንደማያምኑ ስራቸው እና ድርግታቸው እየመሰከረ ነው። ለምን እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ነን የምንል ሰዎች ሁሉ ነገር የምፈጸመው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብለን ማመን አቃተን? ለምን ሁሉን ነገር ከመንግስት ጋር በጥላቻ መልክ መግልጥ እንቸኩላለን? ከፉዉንም መሪ በእኛ ልበ ደንዳናነት በስልጣን ላይ ማድረግ የሚችለው እንግዚአብሔር አይደለምን? ደጉንም መሪ በገዥነት ላይ የሚያስቀምጠው ሁሉን ቻይ አምላክ መሆንን ለምን አናምንም? እባካችሁ ቃልኑ ስንናገር እያስተዋል ብሆን መልካም ነው። ካለበለዚህ በእምነታችን ላይ ለሎች እንደምሉት ችግር አለ ማለት ነው። በየበታችንና በየቤተ ክርስቲያኑ የተቀመጠው ወንጌልና እኛ እየሳራን ያለው ነገር የማይጣጣም የምቃረን ነገር ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት የእግዚአብሔር አላማ ሰለነበረው እርሱ በፈቀደው ሰዓት ሆነ። የሰው ፈቃድ ግን ሌላ ነበር ። አሁንም እኛ ፈቃድ ሌላ ነው እግዚአብሔር አምላክ ለእኝህ አባት ይህ ቦታ ይሰጣቸዋል ካል የሰው ድርሽ አይደለም የእርሱ ፈቃድ ነው የሚሆነው ። እባካችሁ እምነታቸው የልማድና ሰው ሰራሽ አታድረጉት ። ማቅም እየሳራ ያለው ከፉ ሰራው በራሱ ተንኮል እራሱን እያጠፋ ያለ ቡድን ነው። ፕረዝዳት ኦባማን እንኳን እግዚአብሐር ይሆናል ስላለው በጥቁርነቱ ማንም አላስቀረውም ። ከእግዚአብሄር ድንቅ ስራው እያየን አስተዋይ አእምሮ አጣን? ክፉ ትውልድ ስለሆን ዛሬን ለእግዚአብሔር አልተመቸንም። እርሱ ያለው ይሆናል አንጠራጠም። ከነቀፋ ሕይወት ወደ መልካም መንገድ እንመለስ ለማንም አይጠቅምም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰዎች ለሚሠሩት ኃጢአት ሁሉ እግዚአብሔር ስለፈቀደው ነው ማለት ነው ? እነ ሒትለር ፥ ሙሶሎኒ፥ ስታሊን፥ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን የመሳሰሉት በሰው ልጆች ላይ ለፈፀሙት አረመናዊ ጭፍጨፋ ሁሉ እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው ነው ማለት ነው ? እንዲያማ ከሆነ ጽድቅና ኩነኔ የሚገኘው ሰዎች ባላቸው እምነተ እግዚአብሔርና በጎ ሥራ ሳይሆን እግዚአብሔር ሊያጸድቀው የፈለገውን ኃጢአትም ቢሰራ ያጸድቀዋል ፥ መልካምም ቢሰራ ይኮንነዋል ማለት ነው ? ወይ ግሩም ካልቪንስቶችም ወደ ኢትዮጵያ ገቡ ማለት ነው !

   Delete
 11. ማቅ የቤተ ክርስቲያን ጠላት ሁኖ አያውቅም *። ሊቃውንት አባቶቻችን ማቅና ደበሎ ለብሰው ነበር ቤተ ክርስቲያናችንን ከመናፍቃን ሲጠብቁ የኖሩት። ዛሬ ያስቸገረን ጥቁር ለባሽ ነጭ ለባሺ ነው። የቤተ ክርስቲያንችን ዋናው ጠላትም ራሱን 'ሕዛባዊ ወያናይ ሕዝቢ ትግራይ''ብሎ የሚጠራው የባዕዳን ቅጥረኛ ብቻ ነው ። *ከላይ ትላንት በስህተት ነብር በአዎንታዊነት ለማለት የፈለኩት ነገር በአሉታዊነት አስቀምጨው ስላየሁት ዛሬ አስተካክየው ኣለሁ። 'ማቅ የቤተ ክርስቲያን ጠላት ሁኖ አያውቅም! ዛሬ ያስቸገረን ጥቁር ለባሺ የሆነው የወያኔ ነጭ ለባሺ ብቻ ነው፡፡ 'ነጭ ለባሺ' ማለት ምን ማለት እንደሆን ትረዱት ይሆናል ብየ አስባለሁ።

  ReplyDelete