Thursday, February 7, 2013

የአዲስ አበባው ሲኖዶስ የ6ኛ ፓትሪያርክ ምርጫ የካቲት 21 ቀን ያጠናቅቃል


ከተለያዩ አካላት በተውጣጡ 13 የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት የሚመራው ምርጫ የካቲት 21 (በሦስት ሳምንት ውስጥ ማለት ነው)  ቀን ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለህዝብ ይፋ እንዲሚያደርግ አስመራጩ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አስታወቀ።
አስመራጭ ኮሚቴው ከሚከተሉት አካላት የተውጣጣ ነው።
 • ሊቃነ ጳጳሳት
 • ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች
 • ከአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች
 • ከሰንበት ትምህርት ቤት
 • ከማህበረ ቅዱሳን   
የወጣው መግለጫ ማንም ሰው ጥቆማ መጠቆም እንደሚችል ያሳወቀ ሲሆን 5 እጩዎችን ግን የሚመርጠውና ይፋ የሚያደርገው አስመራጭ ኮሚቴው ነው። አስመራጭ ኮሚቴው 5ቱን እጩዎች እንዴት እንደሚመርጥ ግልጽ አይደለም። ከ5ቱ እጩዎች በምን መስፈርት እንደተውጣጡ ባልታወቁ 800 ሰዎች የካቲት 21 ቀን በድምጽ ብልጫ አንድ ፓትርያርክ ይመረጣል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተሰጠው መግለጫ መሰረት ምርጫው የካቲት 21 ቀን ተካሂዶ በዚሁ እለት የተመረጠው አባት ለህዝብ ይፋ ይሆናል። በዓለ ሲመቱ የካቲት 24 እንደሚሆንም ገልጸዋል።


6 comments:

 1. ወይ ጉድ የእነ አባ ሳሙሄል ስራ

  ReplyDelete
 2. በጣም ይገርማል የቀበሌ ሊቀመንበር የሚመርጡ መሰላቸዉ እንዴ?????

  ReplyDelete
 3. የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እጇን ዘርግታ ሁሉንም የዳይስፖራ አባቶች ሀገር ውስጥ ተገኝተው በምርጫው እንዲሳተፉ ጥሪዋን አድርጋለች።
  "፬ኛው ፓትርያርክ ወደመንበሩ ካልተመለሱ ይህንን መንፈሳዊ ጥሪ አንቀበልም" ያላችሁ አባቶች ምርጫችሁን አስተካክላችሁ የውጭዋን
  የእንጀራ እናታች ሁን ይዛች ሁ ቁጭ በሉ፤ ለኢትዮጵያ ሰላምን ስጧት።
  ምርጫው ካለቀ በኋላ መንግሰት ያልቃ ገብቶ፥ ዘረኛው አቡነ የከሌ፥ ጥቅመኛው ማሕብረ እገሌ እያላችሁ ምዕመናንን አትበጥብጡ።
  ነገር ግን መንግስት ግልበጣ አሳባች ሁን ወድጀላችኋለሁ፤ ላገራችን ሁላችንንም ለሃገራችን አፈር ያበቃናል፤ ሕዝቧም በሙት እየተገዛ አይኖርም።

  ReplyDelete
 4. where is the church article that allows Mahibere Kidusan to elect a patriarch?
  please show us; otherwise, let get revolution.

  ReplyDelete
 5. ለማኅበረ ቅዱሳን አባ ሳሙኤል ይሻሉታል ወይስ አባ ማቴዎስ? ስውር ጫወታው እዚህ ላይ ነው። በየትኛው እንደሚጠናቀቅ ለጊዜው እልባት ላይ አይድረስ እንጂ የሩጫው መቋጫ ከሁለቱ ባንዱ ላይ ይደመደማል። ማኅበረ ቅዱሳን የአቡነ መርቆሬዎስን መመለስ እንደሚፈልግ በየሚዲያው የሚጮኸው ሀገር ቤት የሚያስመርጠው ፓትርያርክ እንዳይታወቅበት የስልታዊው ስውር እንቅስቃሴ መሸፈኛ እንደሆነ ታውቋል። ያገኘነው መረጃ ማኅበረ ቅዱሳን አንዱን ለማስመረጥ ሩጫውን መጨረሱን ነው። ይህንን እንደሚያካሂድ በመንግሥትም ድጋፍ አግኝቷል። ስራውን ከጨረሰ በኋላ ግን የማኅበረ ቅዱሳን ፋይል ደግሞ መታሰቢያ እንዳይኖረው ተደርጎ ይዘጋል። ማኅበረ ቅዱሳን 2005 የእድገቱ ማብቂያ የመጨረሻ ዘመኑ ነው። የኔን አስተያየት እንደትንቢት አትቁጠሩ። ነገሩ በትክክል ሲሆን መጥታችሁ ይህንን አስተያየት አንብቡ።

  ReplyDelete
 6. ITS L GOOD BALEGIZE YAWETAWEN BALEGIZE YAWERDEWAL.
  ENGEDIHE YE EGEZIABHEREN FIRED ENETEBEQALEN

  ReplyDelete