Thursday, February 28, 2013

ኦርቶዶክሳውያን ብፁዕ አቡነ ማትያስን 6ኛ ፓትርያርካቸው አድርገው መረጡ

የማኅበረ ቅዱሳን መንደር በሐዘን ተውጧል
የብዙዎችን ከፍተኛ ትኩረት ስቦ የሰነበተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ብፁዕ አቡነ ማትያስን በከፍተኛ ድምፅ በመምረጥ ተጠናቀቀ፡፡ ሁሉም የየራሱን አባት ለማስቀመጥ ባለ በሌለ ሀይሉ እንደተንቀሳቀሰ በተወራለት በዚህ የፓትርያርክ ምርጫ በተለይ ማኅበረ ቅዱሳን በዋናነት አባ ማቴዎስን ለማስመረጥና አቡነ ማትያስ እንዳይመረጡ ለማድረግ ከ3-10 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ ሲንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው የታመኑ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ እንቅስቃሴውም የራሱ እጩ የሆኑትን የአቡነ ማቴዎስን ሰብእና አለቅጥ በማጋነን ላይ የተመሠረተ ብቻ ሳይሆን መንበሩን ይይዙብኛል ብሎ በከፍተኛ ሁኔታ የሰጋቸውን ብፁዕ አቡነ ማትያስን ለማስጠላት ከፍተኛ በጀት መድቦ በከፍተኛ ሁኔታ መንቀሳቀሱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ማቅ ብፁዕ አቡነ ማትያስን ለማስጠላት የዘረጋው ወጥመድ ግን እርሳቸውን ከማስጠላት ይልቅ ትልቅ ተቀባይነትን እንዲያገኙ በከፍተኛ ሁኔታ ረድቷል ነው የተባለው፡፡ ይህም ማቅ ተሰሚነቱ እየቀነሰ መምጣቱን ነው የሚያሳየው ተብሏል፡፡ ማቅ በብዙዎቹ ጳጳሳት ዘንድም ተሰሚነቱ እየቀነሰ እንደመጣ የሚናገሩት ምንጮች ቀድሞም ቢሆን አቡነ ጳውሎስን ለመጣል እነአባ ሳሙኤል የጎነጎኑትን ሴራ ለማጠንከር ያበሩ አባቶች ሁሉ ከእርሳቸው ማለፍ በኋላ ከማቅ ጋር ተባብረው የሚሰሩበት የጋራ ነገር በማጣታቸው ሊተባበሩ አልቻሉምና ብዙዎቹ ማቅ አቡነ ማትያስ እንዳይመረጡ ባደረገው የሎቢ ስራ ተባባሪ አልሆኑም ተብሏል፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው ነው የቆሙት፡፡
የሐሰት ጭፍራ የሆነው ሐራ “አባ ማቴዎስ ከምርጫው ራሴን አግልያለሁ አሉ፤ የአባ ማቴዎስ መራጮች ድምጹን ለአባ ዮሴፍ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፣ መራጮች ስለአባ ዮሴፍና ስለአባ ማቴዎስ እየተነጋገሩ ነው” ወዘተ የሚሉ ሐሰተኛ ዘገባዎችን በማውጣት መራጮችን ለማሳሳት ሞክሯል፡፡ የእነዚህ ዘገባዎች መልእክት ማቅ ሎቢ ላደረጋቸው መራጮች የደረሰ ቢሆንም ሁለቱም የማቅ እጩዎች ያገኙት ድምጽ 98፣ 98 መሆኑ ግን ማቅን ደጋፊዎቹ እየሰሙት እንዳልሆነ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ ማቅ እንዳሰበው ሚዛኑ ወደአቡነ ማትያስ እንዳጋደለ ባስታወቀው ምርጫ አባ ማቴዎስ አልፈልግም ብለው ከምርጫው ራሳቸውን አግለዋል ያለው፣ ድምጹ ሁለት ቦታ ከሚከፈልና ብዙ የለፈፈላቸው አባ ማቴዎስ ጥቂት ድምጽ አግኝተው ከሚዋረድ፣ ለፀረ ወንጌሉና እነመምህር ጽጌንና መምህር ግርማ በቀለን ደብረ ሊባኖስ ገዳም ተልከው ሳለ ከወገሯቸው መካከል ዋናው መሆናቸውን በግንቦቱ ውግዘት ላይ እንደ ጀብድ ሲያወሩ የነበሩትና “እነዚህን ምን ማውገዝ ያስፈልጋል በጥይት መደብደብ ነው እንጂ” ሲሉ የተሰሙት፣ ማቅ ግን ታላቁ የፀረ ተሐድሶ ጀግና ሲል የሚያሞካሻቸው  አባ ዮሴፍን እንዲመርጡ ቢያግባባም እርሱም አልተሳካም፡፡ እንዲያ ቢሆን ኖሮ አባ ማቴዎስና አባ ዮሴፍ እኩል 98 ድምጽ በማግኘት በእኩል ደረጃ እጅግ ዝቅ ብለው ሁለተኛ አይወጡም ነበር፡፡ የማቅ መራጮች የተላለፈላቸውን መልእክት ቢሰሙ ኖሮ ግን የ11ኛው ሰዓት የማቅ እጩ አባ ዮሴፍ 196 ድምጽ ሊያገኙ ይችሉ ነበር፡፡

ምርጫውና የድምጹ ቆጠራ እጅግ ግልጽና በታዛቢዎችና በጋዜጠኞች ፊት የተከናወነ ሲሆን ድምጽ ሲሰጥም ሆነ ሲቈጠር በግልጽነት መከናወኑ ሁሉንም ወገኖች  አርክቷል ተብሏል፡፡ ማቅ በአገር ሽማግሌ ስም ታዛቢ አድርጎ አስርጎ ያስገባቸው የፔፕሲው እነአቶ ደርቤ ስነ ጊዮርጊስ “እናሸንፋለን፤ አንጠራጠርም” ብለው ለመታዘብ ቢገቡም በከፍተኛ የድምፅ ልዩነት አሳዛኝ ተሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በ500 መራጮች መመረጣቸው ሲነገር እነአቶ ደርቤን ጨምሮ በስፍራው የነበሩ የማቅ ሰዎች ፊት ላይ ከፍተኛ የሐዘን ደመና አጥልቶ መታየቱንና እርር ድብን ማለታቸውን መታዘብ ተችሏል፡፡ ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ፓትርያርክ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ በማቅ መንደርም ከፍተኛ ሐዘን መንገሱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ይህም ማቅ ብዙ የደከመለት እቅዱ ባመለሳካቱና አቡነ ማትያስ እንዳይመረጡ ለማድረግ ያደረገው ጥረት ግቡን ሳይመታ በመቅረቱ በማቅ ላይ ወደፊት አንዳንድ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ የሚል ስጋት ላይ መውደቁን  ያሳያል ይላሉ፡፡

ብፁዕ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ሆነው እንዲሰሩ በአብላጫ ድምጽ ተመርጠዋል፡፡ እርሳቸው በሚገባ እንዲሰሩና ቤተክርስቲያኗን ወደተሻለ ነገር እንዲያመጡ ብዙ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ አይጠረጠርም፡፡

1ኛ. በመጀመሪያ ፓትርያኩን ሥልጣን አልባ በማድረግ እና እነርሱ እንዳሻቸው ለመፈንጨት እነአባ ሳሙኤል ያረቀቁት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚቃረነውና መንፈሳዊነት የጎደለው ህገወጥ ደንብ መነሳትና ቤተክርስቲያን ወደቀደመው ሕግ  መመለስ አለባት፡፡

2ኛ. ማቅና እነአባ ሳሙኤል በአቡነ ጳውሎስ ሞት በፍቅር በከነፉበት ጊዜ ቋሚ ሲኖዶስ እያለ በህገ ወጥ መንገድ አቃቤ መንበሩን ለማገዝ በሚል የተቋቋመው G8 ቡድን መፍረስ አለበት፡፡

3ኛ. ቤተክርስቲያንን እያወከ ያለውና የሸዋን መንግስት ለመመሥረት በሃይማኖት ስም እያደባ የሚገኘውን ማቅን አደብ ማስገዛት ያስፈልጋል፡፡

4ኛ. የቅዱስ ሲኖዶስን ክብር ዝቅ እያደረጉና መንበሩን እያዋረዱ ያሉትን እንደእነ አባ አብርሃምና ሳሙኤል ያሉትን የስም ጳጳሳት በየደረጃው መንፈሳዊ ሥነሥርአት ማስያዝ ካልሆነም ስልጣናቸውን በመግፈፍ ሲኖዶሱን ወደቀደመ ክብሩ መመለስ ይገባል፡፡

36 comments:

 1. what a sad day for mahibere kidusan. To mahibere kidusan, this is what you get when you practice politics in the name of religion under the umbrela of the Ethiopian orthodox tewhdo church. Don't underestimate God; stay away from church since you have political agenda....

  mahibere kidusan, ask for forgiveness from God.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከ3-10 ሚሊዮን ብር በጀት !!!!! false do you think that mk is have a problem of planing, like this. really you are one of the problem of our church. like tehadeso!!!!!!!!!!!!!!

   Delete
 2. አይ ፅጌ ከአንተና ከጋለሞታዋ ጀርባ ስንት ጉድፍ አለ አይደል እንዴ? አንተ ትናንት በጥንተ አብሶ ጉዳይ አቡነ ማቲያስን ለራሳቸው የተወገዙ ናቸው እያልክ ታንቧችር አልነበር እንዴ? ቢያንስ በዚህ ጉዳይ አንተ ፅጌም ሆንክ ሰረቀ ተሸንፋችኋል። ምንፍቅናችሁ ከአባ ጳውሎስ ጋር መቃብር ወርዷል። የሙስና ንግስትህ ጋለሞታዋም ብትሆን ሙስናዋን የማቆሚያ ቀን ይመጣል። እንዲህ ብሎ ነበር ውስጥ ከተገባማ አንተ አንድን ነገር በስድስቱም ገፅ አይደል እንዴ የተለያየ ስድስት ነገር የምታወራው? ቀላሉ ማሳያ ራሱ ሃራ ዘተዋህዶ። ማህበሩን ሰደበልኝ ብለህ ትንፋሽ እስኪያጥርህ የፃፈውን እያመጣህ ትለጥፍ አልነበር? አንተ ስታደርገው ብቻ ለፅድቅ ነው? እንደው ግብዝ ቅጥረኛ መናፍቅ ነህ። ችክ ብለህ ሁሌ እኔ ያልኩትና ያደረኩት ብቻ ትክክል ነው ማለት በሽታ ነው። ከምር ፅጊቱ።

  ReplyDelete
 3. ''ወያኔያውያን አባ ማትያስን መረጡ''ተብሎ ይስተካከል። የኦርቶዶክሳውያን አባትማ በወያኔዎች በግፍ ተሰደው በስደት አገር አሉ። ወዲ አደይ ፤ እውነቱ ይህ ነው !

  ReplyDelete
 4. መቼም እንዲሁ በምቀኝነት ነው እንጂ ማቅ የምርጫውን ሂደት በቴክኒክ በከፍተኛ ደረጃ ሲያግዝ እንደነበረ የአደባባይ ምስጢር ነው። አምስቱም አባቶች ለማህበሩ ያላቸው አመለካከት መልካም ስለሆነ ማንም ተመረጠ ማን የሚያመጣውም ለውጥ የለም። ይህንን እናንተም ታውቁታላችሁ። ስለዚህ እናንተም ብታወሩም የሚመጣ ምንም ነገር የለምና አትልፉ። ባይሆን እናንተም መስመራችሁን አስተካክላችሁ ከማኅበሩ ጋር ቁሙ አለበለዚያ ወሬኛ ብቻ ሆናችሁ ትቀራላችሁ። ይህን የምለው አባል ሆኜ ሳይሆን እውነታውን ጠንቅቄ ስለማውቀው ነውና ለናንተም እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ። ለንባብ ባታበቁትም ካነበባችሁት ይበቃል። አንድ ቀን ወደ እራሳችሁ እንደምትመለከቱ ተስፋ አለኝ እንዲህ ሆናችሁ አትቀሩም።

  ReplyDelete
 5. You know what, Our Lord God have a great plans for his peoples. Thanks our father God for your doing great and wonderful things for our church.No body knows our God plan. Just we need to obey his word and law.Do not drive your self on your way,because you don't know your distention, only under his hand.

  ReplyDelete
 6. really so sad for MK.Please did you seen what God done on this great planet. it so amaze his wonderful work for us. why Mk followers they do not under stand the truth word of God? They never accept the truth,too bad. good luck for his

  ReplyDelete
 7. ኦርቶዶክሳውያን ብፁዕ አቡነ ማትያስን 6ኛ ፓትርያርካቸው አድርገው መረጡ ታዲያ እናንተ ምን አገባችሁ? አቡነ ማቲያስን የመረጡት ኦርቶዶክሳዊያን እንጂ ተሐድሶዎች አይደሉም:: መዘገብ ለምን አስፈለጋችሁ?

  ReplyDelete
 8. ማህበረ ቅዱሳን በራሱና በመረጠው የትምክህት መንገድ መጠራረጉ የማይቀር ሂደት ነው፡፡ ዋናው ነገር ግን በጎሰኛውና ጎጠኛው ማህበረ ቅዱሳን አሳዳጅነት ወደውጭ ሀገር ፤በየግልና በየመንግስት መሥረያ ቤት ለእንጀራ ፍለጋ የተሰደዳችሁ፤ አንገታችሁን የደፋችሁ፤ቤተክርስቲያን በጥሪቷ ያስተማረቻችሁ ኦርቶዶክሳውያን መምህራን፤ወንጌላውያን፤ካህናት እግዚአብሄርን አመስግኑ፤ እርሱ ቤተክርስቲያንን ከጨለምተኞች ነጻ ያወጣልና፡፡ እሰከዛሬ እንዳትዘሩት የተነፈጋችሁትን የወንጌል ፍሬ በጎሰኛውና ጎጠኛው ማህበረ ቅዱሳን አማካይነት የተዘራውን ወንጀል ለማጥፋት ተጠቀሙበት፡፡ አባቶች ጳጳሳትም ከማህበረ ቅዱሳን የወንጀል መንገድ ራሳችሁን በመለየት፤ሥጋዊ መንገድን ንቃችሁ በማስተዋል ለቤተክርስቲያን ሥሩ፡፡ መንፈሳዊ ሥልጣኑ አለአግባባ የተጫነባችሁ የምትመሥሉና ነውር የሰለጠነባችሁም በተደጋጋሚ በሁለት ቢላ የምትበሉም ጭምር ሥልጣናችሁን ለቅዱስ ሲናዶስ መልሱና በንስሐ ኑሩ፡፡ በድጋሜ ለማ/ቅ ፈረስ አትሁኑ!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. It is absolutely right, mk doesn't care about Gods plan, but God,is doing his job. God Never make mistakes believe me God is Good all the time, evel/mk/ is will pay the price of our beloved Orthodox church and memenan. Shame on mahbere seytan. maferiya, Mesakiya, dedeboch. The rest of your life be miserable. as u do church Fathers miserable. Yteregemachehu hunu ende alekachehu diabilos.

   Delete
 9. I like this new Patriarch. His importance for the image of the country is inevitable, and his skills of various languages is an asset too. Long live Matias!

  ReplyDelete
 10. በቅንነት ስለፈረደ ሁላችንም ፈጣሪን እናመስግን
  ብጹዕ አቡነ ማትያስ…….እንኳን ደስ አለዎ
  ክብር ለጌታ ለኢሱስ ክርስቶስ ይሁን
  አሜን

  ReplyDelete
 11. Do u think Abun Matyas will do like you are thinking? never .......SIAMRACHEHU YEKIR..KESHIM POLETICKEGNOCH NACHEHU GIN ATECHILUBTIM..LELA MOKIRU.......
  I KNOW HIM VERY WEL..........KIKIKIKIK

  ReplyDelete
 12. የጨለማው ቡድን ቁጥር ከሌላው ሕዝበ ክርስቲያን ይበልጣልን???
  ወይስ ሌላው ማውራትና ማንቋሸሽ እንጂ መሥራት ስለማይችል???
  ከጥቂት ወራት በፊት በነበረው ዘመን ሁሉ እኮ በተግባርም ይሁን በአስተሳሰብ የጨለማው ቡድንና ብፁዕ አቡነ ማትያስ የሚተዋወቁበት ጊዜ አልነበረም፡፡
  የጨለማው ቡድን የምንለው ይህን ያህል መገለባበጥ የሚችል ከሆነ ሌሎቻችን ከነሱ የተሻለ መሥራት ዕንዴት አንችልም???
  መፍትሔው፡- የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመጠየቅ እሳቸውን የራሱ እውነተኛ አባት የማድረግ ድርሻ እንዳለው
  ተረድቶ ሕዝበ ክርሰቲያኑ በፍቅር እና በመደማመጥ ተስፋ ባለ መቁረጥ መትጋት ሲችል ነው ፡፡
  ይህን ሳናደርግ ስንቀር ጊዜ ግን ከየጨለማው ቡድን የባሱም ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ መረዳት ይኖርብናል፡፡
  እግዚአብሔር ሁላችንም የወሬ ብቻ ሳይሆን የተቀደሰ ሥራ ባለቤቶች ያድርገን
  አሜን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለማንኛውም ተሸንፋችኋል፡፡

   Delete
 13. what makes so happy, when MK is so sad?( if it is actually sad), MK did not say bad things about aba matyas, what MK denaunces is the election process as the government is fully interfering, intimidating electors and the involvement of the dark-team behind the curtain, but you try to talk as if it has not accepted his empowerment.this signifies that you are from the side of the devil. if aba matyas leads the church positively ( cleaning corruption, which is at the highest stage in bete-kihnet, and fighting for anti-church elements including you-the tehadiso menafkans and the dark-team; spreading gospel, treating every true servants equally), then no disappointment with him, otherwise we will keep on battling for the truth.

  ReplyDelete
 14. የማኅበረ ቅዱሳን መንደር በሐዘን ተውጧል!!!!!!I appreciate your temptation!please don't worry about MK. If He is God Who is working with them, who can be againist them???please worry about your self b/s if He is God Who chose Abune Mathias for His Holly Church, 'Aba selama' blog (will be) በሐዘን ተውጧል!!! lerasish alkishi!

  ReplyDelete
 15. Yededeboch wore. I hope some dedeb rhobots are writing this all

  ReplyDelete
 16. besak anebebikuat. min tilu yihon biye eyetebekihu neber.

  ReplyDelete
 17. OK!!!!!!!!!!!!! How could your entire time and resources are just devoted to negate MK.
  You must be losers who don't know what to do with your time and resource.

  MK knows what it is doing. It received the voters as well as facilitate the election. it discharged its responsibilities as usual.

  I am sure the 6th patriarch works hand in hand with MK.

  Get used to the presence of MK in EOTC! MK could only get stronger....every year!

  ReplyDelete
 18. Mk is not sad about the result. It is your desire to attack and bring more enemirs to mk. But the newly elected Abune Matiyas knew mk more thsn you think ever. He is one among few fathers who stand against the hertical teaching in the US. and he works with mk usa before he lefy for jerusalem. the gossip you want to spread against mk will have no effect whatsoever.

  ReplyDelete
 19. እንደዚህ አይነት ቆሻሻ ብሎግ አላየሁም:: ሁሌ ስለ ማህበረ ቅዱሳን መፃፍ ለምን አስፈለገ? እናንተ ማናችሁ? የቤተክርስቲያናችን ጠላቶች ናችሁ! ፖለቲከኞች እንጂ እግዚአብሔርን ለማገልገል የማትሰሩ ተራ ወረኞች!

  ReplyDelete
 20. ጽሁፋችሁ የእትዮጲያ ኦርቶዶክስ ምእመናንን ንቃተ ህሊና ያላገናዘበ ነው። ምእመኑ ከናንተ በተሻለ የማህበረ ቅዱሳንን ማንነት በውሬ ሳይሆን በተግባር ያውቃል። የእናንተንም ማንነት ደግሞ ከጽሁፋችሁ ይረዳል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስማ ጽሑፍ እውነት ነው፡፡ ለማቅ ግን ምንም ቢጻፍ አይጥምም፡፡ ለማንኛውም የሸዋን መንግስት ለመመስረት የጀመራችሁት ጉዞ ለአሁን አልተሳካም፡፡

   Delete
 21. what a sad day for Tehadiso menafikan ., this is what you get when you practice nufake in the name of religion under the umbrela of the Ethiopian orthodox tewhdo church. Don't underestimate God; stay away from church since you have nufake agenda....

  menafikan , ask for forgiveness from God.
  Reply

  ReplyDelete
 22. bla blaaaa abune matiyasem honu mk mengeste semayat yemiyasgeba kulf alyazum kulfu beamlak ejje new thanks to god it is not on mks hund they will not go to heaven and they dont late aany one get there either. i hate mks ye betekrstiyanachen telat ye zereyakob bochloch...

  ReplyDelete
 23. Aba selamas,
  Please stop attacking the shewa amahras. I share your concern about the desructive role mk played aganist church. Mk has nothign to do with shewa amhara. You have got to stop the ethinics poltics. I am your frequent readers this not the first time when you attack shewa amhras.Shea amhar is the victim of weyane like other amharas. you need to Stop it, grow up and come to your senses.

  ReplyDelete
 24. Immediate actions of His Holiness should be

  1. Clear and cleanse mahibere Kidusan aka mk from our church so they may practice their politics outside


  2. Warn or fire any archbishops who are agents of mk
  3. Create awareness to the followers of EOTC the hidden agendas of MK

  Thank you aba selama for revealing the true and evil face of mahibere kidusan

  Thank you

  ReplyDelete
 25. ....let me ask you one question let us assume you are true orthodox Christians who wants to preach the real gospel...why you always write about MK?

  ReplyDelete
  Replies
  1. It is amazing to hear all negative things abount MK. It appears to be that most of the bloggers are supporters of the corrupted Woyane regime and currepted election process of Abune Mathias, which actually is and appointement for political purpose. I respect people who stand for what they believe and who say what if fact. MK, please do not afraid to speak your mind. Fear is not what God ingtended for his people. Jesus was not afraid of the Pharasis when he threw their good around the church and said my father's house is not a market place. If you are true christians you teach the truth and do the right thing. If you think the lection is currpted! it is corrupted period. Do not sugar coat the trus. Those of you who disrespect MK, be carefule! do not be critics, think about yourself first. I for one, I am not afraid to say the election was corrupted by Woyane! and it should be null by all Ethiopian Orthodox Church followers. Don't try to be accepted by cooperating with injustice. Stand firm and God will help those who do the right thing.

   Those who are happy with the assignment of the Abune are Woyane supporters not the church supporters.

   Delete
 26. barking dogs over this blog!! mindin new mk sitera rasachihu yizoral?

  ReplyDelete
 27. he mahber seytan

  ReplyDelete
 28. እግዚአብሄር ይስጥልን! ማህበረ ቅዱሳን የተሰኘ የንግድ ድርጅትም ለኪሳራ ይዳርግልን በንግድ ሚኒስቴር ተይዞ በፍትህ አደባባይ የሚጠየቅበት ግዜ ያሳየን!ግብር ከፍሎ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ አውጥቶ የሚነግድበት ግዜ ይስጠው!!

  ReplyDelete
 29. ማህበረ ቅዱሳን የተሰኘ ማህበረ ሰይጣን መፍረስ አለበት ! እግዚሄር ይደርምሰው!!

  ReplyDelete