Sunday, February 3, 2013

የዘርዓ ያዕቆብ የግብር ልጅ ማንያዘዋል እና የደብረ ብርሃን «ገድሉ»

ማንያዘዋል አበበ «የራስ ገዝ አስተዳደር» ይሉታል የሚቀርቡት ሰዎች ስለእሱ ሲገልጹ፡፡ በብዙ ሁኔታዎች ላይ ከራሱ በቀር የሚሰማው ሰው የለውም፡፡ ራሱ አስቦ ራሱ አቅዶ ራሱ ያለው ብቻ እንዲፈጸም የሚያደርግ ራስ ገዝ ነው፡፡ ምንም አይነት ክህነት የሌለው እና ለተንሥኡ ተሰጥኦው እግዚኦ ተሣሃለነ መሆኑን እንኳ ያወቀው ኮሌጅ ከገባ በኋላ ነው ይባልለታል፡፡
 ወደ ቤተክርስቲያንም የመጣበት መንገድም ሆነ ስላሴ ኮሌጅ እስኪገባ ድረስ የነበረው አቋም በአሁኑ ጊዜ ከጥምቀት ተመላሾች እንደሚባሉት ልጆች ያለ ነው፡፡
መጀመሪያ ቤተክርስቲያን ሲጀምር አቦ ጸበል በመጠመቅ ነው የጀመረው፡፡ እና ያኔ መንገድ ለመንገድ እየዘመረ ሲሄድ ብዙ ሰው ማንያዘዋል መንፈሳዊ ሆነ እያለ ደስታውን ይገልጽ ነበር፡፡ ወዲያው አቡነ ኤፍሬምን ተጠግቶ የአቡኑ በትረ ሙሴ ያዥ ለመሆን በቃ፡፡ ያኔማ ምድር በእሱ ቁጥጥር ውስጥ የሆነች እስኪመስለው ድረስ ተኮፍሶ መንጎድ ጀመረ፡፡ እሱ ያለው ካልሆነ በቀር ሌላ ነገር ሲፈጸም የማይፈልግ ሆነ፡፡
የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅን አስነስቶ ሌላ እስኪያስሾም ድረስም በአቡነ ኤፍሬም ዘንድ ያለው ተሰሚነት በጣም ጨመረ፡፡ የቤተክርስቲያን ስራ አስኪያጅን ያሾማል ያሽራል፡፡ በእያንዳንዱ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ይወስናል፡፡ በአጭሩ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ሆነ፡፡
ማንያዘዋል የአቡነ ኤፍሬም ወዳጅ ሆኖ ሁሉን በሚያደርግበት በዚያ ጊዜ ታዲያ በደብረ ብርሃን ከተማ የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ስር እያሰደደች መጥታ ነበር፡፡ ከዋናው አጥቢያ ውጭ ሁለት ንዑሳን አጥቢያዎች በ04 እና በ08 ቀበሌዎች መከፈቱ ማንያዘዋል እና የልብ ወዳጁን መምሬ አየለን እረፍት ነስቷቸው ነበር፡፡
በእነዚህ ሰዎች ላይ ምንድን ነው የምናደርገው እያሉ ባሉበት ጊዜ አንድ ሁሉን የሚያበሳጭ ሁኔታ ተከሰተ፡፡ አንዲት የአቡነ ኤፍሬም የመንፈስ ልጅ የነበረች እጅግ በጣም የሚወዱዋት ወጣት ነበረች፡፡ ይህች ልጅ የስላሴ ቤተክርስቲያን ሰንበት ተማሪ የነበረች ስትሆን፣ ሱባኤ እንኳ ስትገባ በር በሌለው መቃብር ቤት ውስጥ የምትዘጋ፣ ሰው ሁሉ ከአይን ያውጣሽ የሚላት እና በመንፈሳዊ ተጋድሎዋም የተመሰከረላት ልጅ ናት፡፡ «ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ መንፈሳዊ ከሆኑስ እንደ እገሊት ነው» እስኪባል ድረስ የተመሰከረላት ልጅ በድንገት ጴንጤ ሆነች፡፡ ያኔ ነገሩ እጅግ በጣም መክረር ጀመረ፡፡ የእስዋ የሙሉ ወንጌል አባል መሆንም ብዙዎችን ረበሸ፡፡ የመምሬ አየለ እና የማንያዘዋል ቁጣም መልክ አጣ፡፡ በዚህ መሃል የ06 ቀበሌ ወጣቶች ለምን እነዚህን ጴንጤዎች አናጠፋቸውም የሚል ሀሳብ ይዘው ብቅ አሉ፡፡
በዚህ ሀሳብ የተበረታቱት እነማንያዘዋልም ደብረብርሃን ከተማ ላይ የሚገኙትን ሰንበት ተማሪዎች መናፍቃኑን እናጥፋቸው በሚል ጥሪ ማስተባበር ይጀምራሉ፡፡ ሰንበት ተማሪ ያልነበረው እና በወቅቱ ምንም አይነት የቤተክርስቲያን ትምህርት ያልተማረው ማንያዘዋል አዝማች ሆኖ ነገሩን ከመምሬ አየለ ጋር ማስተባበር ይጀምራል፡፡ ሥላሴ ቤተክርስቲያን 06 ቀበሌ ውስጥ በመሆንም የሀሳቡ ጠንሳሾች የጉዳዩን እምብርት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አደረጉት፡፡
ጠንቋይ ቤት በመመላለስ የሚታወቀው መምሬ አየለ ቤተክርስቲያን መድረክ ላይ ብዙ ጊዜ “ምዕመናን ሥላሴን አታስቸግሩ፡፡ አንዳንድ አዋቂዎች አሉ እነሱን ጠይቁ፡፡” ይል እንዳልነበር አሁን የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ መስሎ ህዝቡን ለጥፋት ማስተባበሩን ቀጠለ፡፡ ነገሩን የሰሙት አቡነ ኤፍሬምም እንዲህ ያለ ነገር መደረጉን አጥብቀው ተቃመሙ፡፡ “ተዉ ልጆቼ እንዲህ ያለ ነገር ማድረግ ጥሩ አይደለም፡፡ የቤተክርስቲያን ድርሻዋ አስተምሮ መመለስ ነው እንጂ ጦር መምዘዝ አይደለም፡፡” ይሉም ነበር፡፡ አቡነ አፍሬም ተዉ እንዲህ ያለውን ስራ አስተምረን እንመልሳለን ሲሉ መምሬ አየለ እና ማንያዘዋል “ምዕመናን አባታችን ልክ ናቸው እሳቸውን መስማት ነው…” እያሉ በእጅ ምልክት እያሳዩ ግን እናርዳቸዋለን ይሉ ነበር፡፡
በወቅቱ ጉልህ አገልግሎት የነበረው የስላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት ስለሆነ አማጺው ቡድን የተነሣው ከስላሴ ነበር፡፡ እነማንዘዋል መሪ ሆነው አቡነ ኤፍሬም ተዉ እያሉ ህዝቡ ወደ ሁለቱም የሙሉ ወንጌል ቅርንጫፎች ቢላ፣ መጥረቢያ፣ ጩቤ እና ቦምብም ጭምር ይዘው በመሄድ ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ፡፡
በዚያን ጊዜ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ማናያዘዋልን እና መምሬ አየለን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ታሰሩ፡፡ ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ቀርቦም በዋስ ተለቀቁ፡፡ በዚያን ጊዜ አቡነ ኤፍሬም ማናያዘዋልን ይወዱት ነበርና ቶሎ ብለው ዲቁና እንኳ ሳይኖረው መመሪያ ጥሰው ወደስላሴ ኮሌጅ ላኩት፡፡ ለዚህም ማንያዘዋል ምንም አይነት ክህነት ሳይኖረው ከስላሴ ኮሌጅ ተመርቆ የወጣ የመጀመሪያው ሰው ያደርገዋል፡፡
የአቡነ ኤፍሬም ማንያዘዋልን ማሸሽ ግን በርካታ ወጣቶችን አስቀይሞ ነበር፡፡ ከነሱም መካከል በተለይ ተክሉ የተባለ፣ ቄራ ይሰራ የነበረና ከነቄራ ማረጃ ቢላው እና መጥረቢያው ወጥቶ ጭፍጨፋውን የተሳተፈ ወጣት በጣም ያዝን ነበር፡፡ አሁን ግን ፉዞ ሆኖ መንገድ ለመንገድ ይታያል፡፡
በነማንያዘዋል መሪነት የተካሄደው የደብረ ብርሃኑ ጭፍጨፋ በወቅቱ ለንደን ላይ ይካሄድ በነበረ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ስብሰባ ላይ ቀርቦ መወያያ ሆኖ ነበር፡፡ ትንሽ ቆይቶም መምሬ አየለ ከአቡነ ኤፍሬም ጋር ተጣልቶ እዚህ አትሰራም ተብሎ ተባረረ፡፡ መምሬ አየለ ቅድመ ቅስና ወታድር የነበረ ሲሆን ከገጠር ወደደብረ ብርሀን የመጣው ሰው ገድሎ ነበር፡፡ በኋላ ላይ አንድ ወጣት የአባቴ ገዳይ ብሎ በገበያ ቀን ገደለው፡፡
በዘርዓ ያዕቆብ ምድር መናፍቃን አይፋንኑም በሚል መፈክር ጭፋጨፋው ቢካሄድም ሰዎችን ወደቤተክርስቲያን መመለሻው መንገድ አቡነ ኤፍሬም እንዳሉት ትምህርት እንጂ ጭፍጨፋ አይደለም እና ያኔ የጨፈጨፏቸው አሁን ለቁጥር እስኪያታክቱ በዝተዋል፡፡
ማንያዘዋል በአጋጣሚው ያገኘውን የትምህርት እድል ጨርሶም ወደደብረ ብርሃን ከተማ ሲመለስ የደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን ለልማት በሚል ዛፍ እያስቆረጠ ይደርሳል፡፡ ያኔም እርሱ በለመደው አፉ ተዉ መቁረጥ አይቻልም ብሎ ቢቃወምም ሰሚ በማጣቱ አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተክህነት በመምጣት እግድ አጽፎ ሄደ፡፡ ያኔም ከቤተክርስቲያኒቱ ካህናት ጋር የከረረ ጸብ ውስጥ ገባ፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ካህናት እና ምዕመናንም ጠቅላይ ቤተክህነት መጥተው እግዱን አስነስተው ሲመለሱም ማንያዘዋልን ቤተክርስቲያኒቱ ግቢ ውስጥ እንዳይገባ ከለከሉት፡፡ በዚያ ምክንያትም እስካሁን ድረስ ስላሴ ቤተክርሰቲያን ገብቶ አያውቅም፡፡ ወዲያውም በዚሁ ምክንያት ከአቡነ ኤፍሬም ጋር በመጣላቱም እሳቸውም ከሀገረ ስብከታቸው ሥራ እንዳይሰራ ያግዱታል፡፡ አሱም አዲስ አበባ መጥቶ ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ መምሪያ ተቀጥሮ መስራት ጀመረ፡፡ ያኔ ታዲያ ማንያዘዋል “ዝንጀሮን የጎዱ መስሎዋቸው ክምሩ ላይ ጣሏት” እያለ ይተርት ነበር፡፡
ከራሱ ውጭ የሚሰማው የሌለው ማንያዘዋል በአሁኑ ወቅት ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ መምሪያ ስራ ውጭ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ እንዳይደርስ ቢታገድም  እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአባ ሳሙኤል ተከልሎ ልማትና ክርስቲያናዊ መምሪያን እየመራ ነበር ይላሉ፡፡ «ልማትና ክርስቲያናዊ መምሪያን እየመራ ያለው እኮ ማንያዘዋል ነው» ሲባል የሰማ አንድ ወንድም «እንደዛ ካልሆነማ ከማንያዘዋል ባህሪ አንጻር እሱ ራሱ መች አጠገባቸው ይደርስ እና ስለ ሰሙትና ስለታዘዙት ነው እንጂ አብሮዋቸው ያለው» ሲል ተደምጧል፡፡
ታዲያ ማንያዘዋል የዘርዓ ያዕቆብ የግብር ልጅ አይደለም ትላላችሁ?

17 comments:

 1. አይ ማኔ የአንተ ጉድ መቼም ተነግሮ አያልቅ!!!!!

  ReplyDelete
 2. ይህ ፅኁፍ በዐውደ ምሕረት ብሎግ ከግንቦት 2004 ሲኖዶስ ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ 23/ 05 /2012(15/09/2004) የቀረበ ጽሁፍ ነው፡፡ ይህ ሰው አስመልክቶ አባ ሰላማ ካወጣችው ዘገባ ጋር ተያያዥነት ስላለው አንባቢ እንዲያነበው ኮቢ አድርጌያታለሁ፡፡
  //////// ////// /////
  ሰሞኑን የሲኖዶስ ስብሰባን ሂደት ያየ ሰው ሊለው የሚችለው ብዙ ነገር ይኖረዋል። በተለይ በስብሰባ ላይ በተነሳ ሀሳብ ሁሉ ላይ ከውጭ ካለው አየር ምክር የሚሹ አንዳንድ ጳጳሳት አካላቸውን ሲኖዶሱ ላይ አድርገው ልባቸው ማኅበረ ቅዱሳን ቢሮ ውስጥ አስቀምጠው በማቅ ሳንባ ነው የሚተነፍሱት፤ የሚተነፍሱበት አየር ደግሞ በልዩ ሁኔታ ማንያዘዋል በሚል ኬሚስት የተሰራ ነው። ይህ ታዋቂ ኬሚስት የሚቀምመው ነገር የሚባል ኬሚካል ሲሆን በመጀመሪያ የሚሞክረውም አባ ሳሙኤል የሚባሉ ባለመንታ ችግር ጳጳስ ላይ ነው። እሳቸው ላይ በትክክል እንደሰራ ሲያውቅ እሳቸውን አስጨብጦ በእለቱ በየሚተነፍሱት አየር ለሚያጥራቸው ሌሎች ጳጳሳት ይልከዋል።
  ከዛማ ገበርዲኑን ለብሶ ቤተ ክህነት ግቢ ላይ መዞር ነው። ከዛ ጋሻ ጃግሬዎቹ ሲከቡት የዛሬ አጀንዳ ይህ ይህ ነው የሚወሰነውም ይሔ ነው እያለ ራሱን በመንፈስ ቅዱስ ቦታ አስቀምጦ ያወራል። ማታ ላይም የኮሌጁ ምሩቃን ቢሮ ላይ መብራት አጥፍቶና መጋረጃ ጋርዶ ሰው የሌለ አስመስሎ ይቀመጣል እንዲህ እንደሚያድርግ የሚያውቁ የኮሌጁ ተማሪዎች ታድያ ማንያዘዋል የሚባል የሌሊት ሰይጣን አለ ብለው “በመፍራት” ወደ ምሩቃኑ ቢሮ አካባቢ አይሄዱም።

  ይህ ሰው ታድያ መሸት ሲል ሶስት ወይም አራት ሰዓት ላይ በአባ ሳሙኤል ስልክ ጥሪ መሰረት ወደ አባ ሳሙኤል ሄዶ ስብሰባው እንዴት ነበር? ብሎ ይጠይቃል። ታድያ አባ ሳሙኤልም በተለመደው ጀብደኛ ባህሪያቸው እንዲህ ተብሎ እንዲህ ተደርጎ እንዲህ ተወሰነ ብለው ይነግሩታል። አጅሬም 6ሰዓት ወይም 7 ሰዓት ላይ ወጥቶ ይሄዳል። አንዳንዴም እዛው ያድራል። ያደረም ቀን ወጥቶ የሄደም ቀን ተማሪ ያየዋል። ተማሪ ለጥናት ማታን ይመርጣልና ሹክክ ብሎ ከአባ ሳሙኤል ቤት ሲወጣ ያዩታል። ቀን ለደጀ ሰላም ብሎ አስቀድሞ ያዘጋጀውን ሪፓርት ያወጣና እሳቸው ካሉት ጋር ያስተያየዋል። የሚሻሻል ካለ አሻሽሎ ቅመም መጨመር ካለበትም ጨምሮ ደጀ ሰላም ላይ ፖስት እንዲደረግ ለአሉላ ይልካል። አንዳንዴም ለአሉላ በስልክ ይነግረውና እሱ የራሱን ቅመም ጨምሮ ያመጣዋል። ታድያ ይህ ሁሉ ቅንጅት እያለ ደጀ ሰላም እውነት የማታወራው ብሎ ለሚጠይቅ ጠያቂ እንዲህ የሚል መልስ እንሰጠዋለን። ብዙ ጊዜ ደጀ ሰላም የተሳሳተ ዘገባ የምታወጣው በሶስት ዋና ዋና ምክናቶች ነው።
  የመጀመሪያው በአባ ሳሙኤል ሪፖርት አሰጣጥ ስህተት ነው። ሁለተኛው ደግሞ በማንያዘዋል ስህተት ነው። ሶስተኛው ደግሞ በአላማ ነው።
  ማንያዘዋል ስብሰባውን እሱ እንደሚመራው እሱ እንደሚወያይበት እሱ እንደወሰነው አድርጎ ሲያስብ ኩራት ይሰማውና ለራሱ በመስታወት ፊት ቆሞ እህሳ ፓትርያርክ ማንያዘዋል እንዴት ነህ? ይለዋል። እራሱን እንደፓትርያርክ ስለሚያስብም በኔ ላይ ተደረቡብኝ ብሎ የሚያስባቸውን ቅዱስ ፓትርያርኩን አምርሮ ይጠላል። በእሱ ፊት ወዳጄ ብሎ የሚጠራቸውን ሰዎች ሁሉ የወዳጅነት መስፈርት አንድን የግድ ማሟላት አለባቸው። እርሱም ፓትርያርኩን መጥላት ነው። አንዳንድ ወገኖች ማንያዘዋል ለምንድን ነው ነጭ ልብስ መልበስ የሚወደው? ብለው ይጠይቃሉ። ታድያ መላሾች ሲመልሱ አንዳንዶቹ ቅኖች ፈሪሳዊ ስለሆነ ነው ይላሉ ሌሎች ደግሞ ላደገበት አካባቢ ያለውን ፍቅር በአለባበስ ለመግለጽ ነው ይላሉ ውስጠ ሚስጢሩን የሚያውቁ ደግሞ በጓዳ በሚሰራው ስራ ፓትርያርኩ እኔ ነኝ ብሎ ስለሚያምን የፓትርያርክነት ህልሙን ያሳካ ስለሚመስለው ነው ይላሉ። ፓትርያርክነት ህልሙ ስለሆነ ህልመያርክ እንበለው ይሆን?

  23/ 05 /2012(15/09/2004) ዐውደ ምህረት ብሎግ ላይ የቀረበ

  ReplyDelete
 3. ይህ ደግሞ አውደ ምህረት ላይ በ14/6/12(7/10/2004) የቀረበ ነው

  ማንያዘዋል አበበ
  ማንያዘዋል ደግሞ የሚመራው የኮሌጅ ተማሪዎችንና ለማኅበሩ ያደሩ ጳጳሳትን ነው። የስላሴ ኮሌጅ ምሩቃን ኅብረት ሊቀመንበር በመሆኑ ተማሪዎችን በቅርብ የማግኘት ዕድል ስላለውና ከአቡነ ሳሙኤል ጋር ከፍተኛ ቅርርብ ስላለው ሁለቱንም ለመምራት ዕድል ሰጥቶታል።
  ማንያዘዋል መንፈሳዊነትንና መንፈሳዊ ባህሪያትን በአባቶቻችን የአርበኝበት መንገድ ለማሳካት የሚፈልግ ሰው ነው። በእጅጉ ኢትዮጵያዊ በእጅጉ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ብሎ ያምናል። እነዚህን የሚቃወሙትን ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን ሰዎች ከፊቱ ለማስወገድ እስከ መግደል ድረስ የሚደርስ ጭከና አለው። በደብረ ብርሃን ከተማ በሙሉ ወንጌል ቸርች ህዝቡን አስተባብሮ ያደረሰው ጭፍጨፋ ለዚህ አንዱ ማስረጃ ነው። ድቁና እንኳ የሌለው ማንያዘዋል ስላሴ ኮሌጅ የገባው በደብረ ብርሃን ከተማ በእሱ መሪነት በደረሰው ጭፍጨፋ በፖሊስ ስለሚፈለግ ከዓይን እንዲርቅ ለማድረግ ነበር።
  በአሁኑ ሰዓት ለእርሱ ትልቁ ግቡ አቡነ ጳውሎስን ከስልጣን ማውረድ ነው። ለእሳቸው ያለው ጥላቻ ወደር የሌለው ነው። ሳይደክምም ሳይታክትምም ይኼ ነገር እንዲሳካ ጥረት ያደርጋል። ላመነበት ነገር ጽኑ በመሆኑ የማኅበሩ አመራሮች ከሱ ጋር ያላቸው አቀራረብ ጥንቃቄ የተሞላ ነው። እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው እንደሚባለው ቀረብ አደርገው ኃላፊነት እየሰጡ ብዙ ሚስጢሮች እንዳያውቅ ደግሞም እንዳይገባው አድርገው ገፋ እያደረጉ በጥንቃቄ የያዙት ሰው ነው።
  የኮሌጅ ተማሪ እያለ ሁልጊዜ ፈተና ሲደርስ ይታመም ነበር ይባላል። የሚታመመው ግን እውነተኛ ህመም ሳይሆን አሞታል ተብሎ ፈተና ላይ እንደልቡ እንዲወራጭና ፈተና ላይ አድርጎት የሚገባው ጋቢ ላይ የሚሰፋትንን አጠሪራ በቀላሉ ለማንበብ እንዲረዳው ነው። እንዲህ እያደረገ አምስት አመት ማሳለፉን ተማሪ ሁሉ ያውቃል። እንዲያውም አንድ ተማሪ ማኔና ህመሙ የሚል ግጥም ጽፎ አጠሪራውን እንዴት እንደሚጠቀምበት በሚያስቅ መንገድ ገልጾ እንደነበር ይነገራል። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ስለሆነ ማንያዘዋል ስለዚህች ግጥም ምንም ሳያውቅ ይኖራል።
  ጨካኝ ክፉና በአላማው ጽኑ ነው እንጂ አስተዋይ ስላልሆነ የሚያወራውን አያውቅም። ከአንድ ወር በፊት እንኳ የሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎችን ሰብስቦ “እኔ እኮ ለዚህ ግቢ የማልሆነው የለም ደጀ ሰላም ላይ ስለዚህ ጊቢ ተጽፎ በሁለት ሰዓት ውስጥ ያስጠፋሁ ሰው ነኝ” አለ አሉ። አይ ሞኞ እግረ መንገድህን ደጀ ሰላምን ማን እንደሚያዘጋጅ ጠቆምክ እኮ!! አሉላ ይኼን ሰምተሃል?

  ReplyDelete
 4. ይህን ሰው አውቀዋለሁ፡፡ አረመኔ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ የሚያሳዝነው ይህንን ጭከናውን ሀይማኖት ማድረጉ ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. I heard lots of negative things about this guy. Most of the persons informing me are theology graduates. Would you please show me his picture?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህ ደግሞ አውደ ምህረት ላይ በ14/6/12(7/10/2004) የቀረበ ነው

   ማንያዘዋል አበበ
   ማንያዘዋል ደግሞ የሚመራው የኮሌጅ ተማሪዎችንና ለማኅበሩ ያደሩ ጳጳሳትን ነው። የስላሴ ኮሌጅ ምሩቃን ኅብረት ሊቀመንበር በመሆኑ ተማሪዎችን በቅርብ የማግኘት ዕድል ስላለውና ከአቡነ ሳሙኤል ጋር ከፍተኛ ቅርርብ ስላለው ሁለቱንም ለመምራት ዕድል ሰጥቶታል።
   ማንያዘዋል መንፈሳዊነትንና መንፈሳዊ ባህሪያትን በአባቶቻችን የአርበኝበት መንገድ ለማሳካት የሚፈልግ ሰው ነው። በእጅጉ ኢትዮጵያዊ በእጅጉ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ብሎ ያምናል። እነዚህን የሚቃወሙትን ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን ሰዎች ከፊቱ ለማስወገድ እስከ መግደል ድረስ የሚደርስ ጭከና አለው። በደብረ ብርሃን ከተማ በሙሉ ወንጌል ቸርች ህዝቡን አስተባብሮ ያደረሰው ጭፍጨፋ ለዚህ አንዱ ማስረጃ ነው። ድቁና እንኳ የሌለው ማንያዘዋል ስላሴ ኮሌጅ የገባው በደብረ ብርሃን ከተማ በእሱ መሪነት በደረሰው ጭፍጨፋ በፖሊስ ስለሚፈለግ ከዓይን እንዲርቅ ለማድረግ ነበር።
   በአሁኑ ሰዓት ለእርሱ ትልቁ ግቡ አቡነ ጳውሎስን ከስልጣን ማውረድ ነው። ለእሳቸው ያለው ጥላቻ ወደር የሌለው ነው። ሳይደክምም ሳይታክትምም ይኼ ነገር እንዲሳካ ጥረት ያደርጋል። ላመነበት ነገር ጽኑ በመሆኑ የማኅበሩ አመራሮች ከሱ ጋር ያላቸው አቀራረብ ጥንቃቄ የተሞላ ነው። እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው እንደሚባለው ቀረብ አደርገው ኃላፊነት እየሰጡ ብዙ ሚስጢሮች እንዳያውቅ ደግሞም እንዳይገባው አድርገው ገፋ እያደረጉ በጥንቃቄ የያዙት ሰው ነው።
   የኮሌጅ ተማሪ እያለ ሁልጊዜ ፈተና ሲደርስ ይታመም ነበር ይባላል። የሚታመመው ግን እውነተኛ ህመም ሳይሆን አሞታል ተብሎ ፈተና ላይ እንደልቡ እንዲወራጭና ፈተና ላይ አድርጎት የሚገባው ጋቢ ላይ የሚሰፋትንን አጠሪራ በቀላሉ ለማንበብ እንዲረዳው ነው። እንዲህ እያደረገ አምስት አመት ማሳለፉን ተማሪ ሁሉ ያውቃል። እንዲያውም አንድ ተማሪ ማኔና ህመሙ የሚል ግጥም ጽፎ አጠሪራውን እንዴት እንደሚጠቀምበት በሚያስቅ መንገድ ገልጾ እንደነበር ይነገራል። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ስለሆነ ማንያዘዋል ስለዚህች ግጥም ምንም ሳያውቅ ይኖራል።
   ጨካኝ ክፉና በአላማው ጽኑ ነው እንጂ አስተዋይ ስላልሆነ የሚያወራውን አያውቅም። ከአንድ ወር በፊት እንኳ የሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎችን ሰብስቦ “እኔ እኮ ለዚህ ግቢ የማልሆነው የለም ደጀ ሰላም ላይ ስለዚህ ጊቢ ተጽፎ በሁለት ሰዓት ውስጥ ያስጠፋሁ ሰው ነኝ” አለ አሉ። አይ ሞኞ እግረ መንገድህን ደጀ ሰላምን ማን እንደሚያዘጋጅ ጠቆምክ እኮ!! አሉላ ይኼን ሰምተሃል?

   Delete
 6. Who cares about this guy? Please only discuss the secrets and hidden agendas of mahibere kidusan aka mahibere seytan. Thanks.

  ReplyDelete
 7. yesew tarik sewn ayanitsim anam yeamilaken tarik bitaweru yishalal Egizihabiher Libona Yisiten Amen

  ReplyDelete
 8. we are surprised you side with Pentecostals even by bending the truth.

  ReplyDelete
 9. Ena min yetebese, who cares about personal life, ende-mender seet egele minamen malet haymanotgna liasble ayechilem. Werre alekebachu ende?

  ReplyDelete
 10. yerasua siaribat yesew tamasilalech.mikegnoch.Ende enaninte yent tut nekash mehon alebet endie.leboch?

  ReplyDelete
 11. ምንጊዜም የልጁ ስም "ማንያዘዋል" መሆኑን አትርሱ፡፡ ታዲያ ምን ያድርግ ስም የሰጠው ሌላ!! ስሙን ካልለወጠ በስተቀር መበጥበጡን መቼም አያቆምም  አራት ነጥብ

  ReplyDelete
 12. ere bezih be america columbus kidus gebriel church yemikadew ye ambagenenu yared gebremedhin hizbin yemekefafel zemarianin lela church kehedachu atzemirum bemalet ke kisu awtito demoz yemikeflachew yimesel churchun eyebetebete yale gleseb new mederek lay wengel yastemral tegbaru gin ye devil honual yihin min tilutalachehu? memenanin wede church mamtatit weyis mebeteb?

  ReplyDelete
  Replies
  1. what do you expect from mahbere seytan? mk?

   Delete
 13. maneyazewal welude seytan new. bedenbe new yemawekiw. wengelega nefse geday new.

  ReplyDelete
 14. ማህበረ ቅዱሳን እድሜው ያንድ ጎልማሳ እድሜ ቢይዝም የእድሜውን ያህል ለቤተክርስቲያን ያደረገው አስተዋጽኦ በአይን የሚታይ ነገር የለም:: የእድሜውን ያህል ወንጌልን በሽፍንፍን ሳይሆን በግልጽ እውነቱን ፍንትው አድርጎ ቢያስተምር ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስ ገልጦ የሚያስተምረው ሲያጣ ወደ ሌላ እምነት ድርጅት የገባውን ትውልድ ወደ እናት ቤተክርስቲያን መመለስ ይችል ነበር፡፡ ይህን ከማድረግ ይልቅ ማህበሩ ብቻ ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪና ከርሱ ሌላ ክርስቲያን የሌለ በማስመሰል፣ ከማህበሩ አባላት ውጪ ያለው ደግሞ ተከታይ፣ አድማቂ፣ የርሱ አጨብጫቢ እንዲሆኑ በጀሌነት ይጠቀምበታል::
  ማህበሩ ወንጌልን ከማስፋፋት ይልቅ ጎንበስ በርከክ እያለ አባቶችን መሸሸጊያ በማድረግ እጅ መንሻ በመስጠት አባቶችን በመያዝ ሐሳቡን እንዲያስፈጽሙለት በማቀድ የእርሱ ተገዢ እንዲሆኑ አድርጓል::

  ይህ በእንዲህ እንዳለ በገዳም የሚገኙ አባቶችን የተቀደደ ልብስ በማልበስ፣ አባቶችን በማዘዋወር፣ ፎቶና ቪዲዮ በመቅረጽ ውጪ ሀገር ላሉ አባሎቻቸው በገዳሙ ያሉ አባቶች ልብሳቸው በላያቸው ላይ አልቋል በማለት እርዳት ካሰባሰቡ በኋላ ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያኖች እውነት እየመሰላቸው ዶላሩን እየመዘዙ በተወካዮቹ በኩል ሲሰጡ እዚያ ያለው ተወካይ ደግሞ ሀገር ውስጥ ላሉት ብሩን ሲያስተላልፍ የማህበሩ የበላይ አመራሮች ቤታቸውን ይሰሩበታል፤ ንግዶቻቸውን ያስፋፉበታል፤ ከተረፈ ወደ ገዳሙ በመሄድ እራፊ ጨርቅ በማልበስ ብሩካን፣ ቅዱሳን እንዲሏቸው ያደርጋሉ:: ማህበሩ የሚጨነቀው ንግዱን በተቻለ መንገድ ለማስፋፋት ነው እንጂ ወንጌል ተሰብኮ፣ ህዝቡ ንስሀ ገብቶ፣ ቤተክርስቲያን ሳያውቁ ከውስጧ የወጡ ምዕመናንን እቅፍ ድግፍ አድርጋ እንድትይዝ አይደለም::

  ማህበሩ ከተመሰረተ ጀምሮ እግዚአብሔር የመረጠውን ሰባኪ ሲያስነሳ በተቃውሞ “የሚያስተምረው ትክክል አይደለም፤ ይህ አስተምህሮ ምንፍቅና ይታይበታል”:: በማለት አባቶችን በማሳሳት ቤተክርስቲያን እንዳያስተምሩ ያደርጋል:: ተከታይ ካላቸው ሰበብ ፈልጎ ስም በማጥፋት በህዝቡ ውስጥ አሉባልታ በመንዛት ያ አልሆን ካለው ደግሞ ሰበብ ፈልጎ በማሳሰር ካገር ብርር ብሎ እንዲጠፋ ያደረጉትን ቤት ይቁጠረው:: አባላቱ በዘመናዊ ትምህርት የተካኑ ቢሆንም ወንጌልን ማስተማር ግን የጸጋ ስጦታ ስለሆነ ማስተማርም አይችሉም:: ስብከትም ሆነ ዝማሬ ለዛው እና ስጦታው ከላይ ስለሆነ ላስተምር ብለው ቢነሱ ተረት ተረቱ ይበዛዋል:: ልዘምር ቢሉ የዝማሬ ለዛ ስለሌለው ስብከቱም ሆነ ዝማሬው ህዝቡን የሚለውጥና የሚያንጽ ስላልሆነ የሚሰማቸውን የሚያዳምጣቸውን ሲያጡ በውስጣዊ ምቀኝነት(ቅናት) ራሳቸውን ቅዱስ በማድረግ የዝማሬው የስብከቱ ገምጋሚ ደረጃ መዳቢ ሆነው ይቀርባሉ:: አንድ ወንጌል እንዲሰብክ እግዚአብሔር የመረጠው ሲነሳ ስብከቱን አይሰሙም ከሰሙም ቃላት ለመሰንጠቅ በትምህርቱ ላይ በንጹህ ስንዴ ላይ እንክርዳድ ለመዝራት ይሯሯጣሉ እንጂ በወንጌል ለመታነጽ ልባቸውን አይከፍቱም::

  ReplyDelete