Tuesday, February 12, 2013

እምነትና ምግባር ምንና ምን ናቸው?

“የሃይማኖትና የመልካም ሥራ ትርጓሜያቸው ይህ ነው፤ ሃይማኖት ለመጽደቂያ መልካም ሥራ የሃይማኖት መግለጫ ነው፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ መዳን የሚገኘው በእምነት ነው እንጂ በሥራ አይደለም ይላል፡፡ መልካም ሥራም የእምነት መግለጫ መሆኑን ይናገራል፡፡ ጥንታዊው የኢትዮጵያ እምነትም መዳን የሚገኘው በእምነት ነው፤ መልካም ሥራ ደግሞ የእምነት መግለጫ ነው የሚል ነበር። ነበር ለማለት የተገደድነው ዛሬ ይህን እውነት የሚቃረን ስብከት እየተሰበከ ስለሆነ ነው፡፡ አዋልድ መጻህፍት እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ለምኔ ያሉ የሚመስሉት ጸረ ወንጌል አቋም ያላቸውና ከእኛ በላይ ኦርቶዶክስ የለም የሚሉ ግለሰቦችና ማህበራት ይህን የወንጌል እውነት ሲቃወሙት ኖረዋል፡፡ በምትኩም መዳን የሚገኘው አዋልድ መጻህፍት በሚሰብኩት ስራ ነው እንጂ መጽሀፍ ቅዱስ በሚያስተምረው ወንጌል አይደለም እያሉ በግልጽ ይናገራሉ፡፡ እውነታው ግን ይህ አይደለም፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሴ በጣሊያን ወረራ ተሰደው እንግሊዝ በነበሩ ጊዜ በስደት የነበረችው ቤተክርስቲያን በ1931 ዓ.ም “የቤተ ክርስቲያን ጸሎት” በሚለ ርእስ ያዘጋጀችው፣ አሁንም ድረስ በቤተክርስቲያናችን የሚሰራበትና ብዙ ሰዎች ልብ ያላሉት መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሀፉ በቤተክርስቲያን የሚሰራባቸውን ልዩ ልዩ የጸሎት ስርአቶችን ይዟል፤ ቀጥሎ የቀረበው ግን የመዳንን መንገድ ያብራራል፡፡ በእርግጥም ሰው ይህን ዋና ነገር ካላስተዋለ ወደመዳን አይደርስም፡፡ ስለዚህ ሰው ሁሉ እንዲያነበው፣ እንዲያስተውለው፣ ራሱን እንዲፈትሽበትና እንዲድንበት ጽሁፉን ከዚህ ቀጥሎ እንዳለ አቅርበነዋል፡፡
 
“የጽድቅ መንገድ

“ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ከመምጣቱ አስቀድሞ እውነተኛ የጽድቅ መንገድ አልወቀም ነበር፡፡ ነገር ግን ዛሬ ሰማያዊ አባታችን እግዚአብሔር እውነተኛውን የጽድቅ መንገድ አሳየን፡፡ ይኸውም የጽድቅ መንገድ የተባለ አንድ ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ከሱ በቀር ሌላ ወደ ሰማያዊ አባታችን ወደ እግዚአብሔር የሚወስድ የለም፡፡ እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ የእውነትና የሕይወት መንገድ ነኝ በኔ በኩል ካልሆነ በቀር አንድም ወደ አብ የሚመጣ የለም ብሎ ተናግሮዋል፡፡ (ዮሐ. 14፥6)

“ስለዚህ እኛ ሁላችን ይህንን የማያሳስት እውነተኛውን የጽድቅ መንገድ ክርስቶስን ብቻ ይዘን ከሄድን ዘወትር እየናፈቅን አባታችን ሆይ እያልን ከምንጠራው ከሰማያዊ አባታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ሰማያዊት አገራችን ወደ መንግሥተ ሰማያት እንደርሳለን ዳግም በሥራችን እንጸድቃለን፤ መንግሥተ ሰማያት እንገባለን ብለን አንመካም፤ የምንጸድቅበት ሃይማኖታችን ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ ቀምበሬን በላያችሁ ተሸከሙ” ብሏል (ማቴ. 11፥28) እንዲህም ማለቱ በኔ ጽኑ ሲል ነው፡፡

“ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ጽድቅ በሃይማኖት ብቻ እንዲገኝ ሥራ በመሥራት እንዳይገኝ በጻፋቸው መልእክቶች ሁሉ ያስተምረናል፡፡ “ሰው ሥራ ሳይሠራ በሃይማኖት ብቻ እንዲጸድቅ እናውቃለን” ብሏል፡፡ (ሮሜ 3፥28) ከዚህም ቀጥሎ በ4ኛው ምዕራፍ በ4ኛና በ5ኛው ቁጥር የሚሠራ ሰው ዋጋው አይቆጠርለትም፤ እንዲያው እንደሚገባው ሠራ ይባላል እንጂ፡፡ የማይሠራ ግን ኀጢአተኛውን በሚያጸድቅ በእግዚአብሔር ቢያምን ማመኑ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል ብሏል፡፡ ደግሞ ይልቁንም በጣም የሚያስረዳ በኤፌሶን መልእክቱ “አምነን በጸጋው ድነናልና፤ እናንተም የዳናችሁ በእግዚአብሔር ቸርነት ነው እንጂ በሥራችሁ አይደለም፤ እኛም የዳን በሥራችን አይደለም ማንም የሚመካ እንዳይኖር ብሏል (ኤፌ. 2፥8-9) ዳግም ወደ ገላትያ ሰዎች በጻፈው በ2ኛው ምዕራፍ በ 21ኛው ቁጥር “የእግዚአብሔርን ጸጋ አልክድም የኦሪትን ሥራ በመሥራት የሚጸድቁ ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ ለከንቱ የሞተ ነዋ” ብሎ ተናግሮአል፡፡ ይህም ሰው ሁሉ በሥራው እንዳይጸድቅ በእግዚአብሔር ጸጋና በክርስቶስ ሞት እንዲጸድቅ ያስረዳል፡፡ ክርስቶስ መሞቱ ሰው በሥራው መጽደቅ የማይችል ስለ ሆነ ነው፡፡“ስለ መልካም ሥራ

“ሰው ሁሉ የሚጸድቀው በእግዚአብሔር ጸጋና በክርስቶስ ሞት በሃይማኖትም ነው እንጂ በሥራው ለመጽደቅ አይችልም ብለናል፡፡ ነገር ግን በሃይማኖት ብቻ እንጸድቃለን ስላልን የታዘዝነውን በጎ ሥራ አንሥራ ማለት አይደለም፡፡ እውነተኛው ሕያው የሚሆን ሃይማኖት ያለ መልካም ሥራ አይገኝም፡፡ ዛፍ በፍሬው እንዲታወቅ እንዲሁም ሃይማኖታችን በሥራችን ይታወቃል (ማቴ. 7፥16-21)

“ለሃይማኖታችን መልካም ሥራ መሥራት ያስፈልጋታል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ያዘዘንን ሥራ ሁሉ ሠርተን “እኛ ሥራ ፈቶች ሎሌዎች ነን፤ እናደርገው ዘንድ የሚገባንን አደረግን ማለት ይገባናል እንጂ በሥራችን ዋጋ እናገኛለን፤ እንጸድቃለን አንልም፡፡ ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እናንተ የታዘዛችሁትን ሁሉ አድርጋችሁ እኛ ሰነፎች ሎሌዎች ነን እናደርገው ዘንድ የሚገባንን አደረግን በሉ” ብሎ አስተምሮናል (ሉቃ. 17፥10) በጎ ሥራንም መሥራት የሚያስተምረን ሃይማኖት ነው፡፡

“እኛ መልካም ፍሬን ለማፍራት የክርስቶስ አትክልት ነን፤ መንፈስ ቅዱስን እንደ መስኖ ውኃ አጠጥቶናል፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበልን በኋላ መልካም ፍሬን ማፍራት ይገባናል፤ ነገር ግን መልካም ፍሬን ሳናፈራ ብንገኝ ተቆርጦ ወደ እሳት እንደሚወድቅ እንጨት እንሆናለን (ማቴ. 3፥10)

“እንደዚህ ያለውን መልካም ሥራ ሁሉ ክርስቶስ መንፈሱን ካልሰጠ በቀር ልንሠራው አንችልም፤ ባሕርያችን እጅግ ደካማ ነውና፤ ስለዚህ በክርስቶስ ብቻ መጽናት ያስፈልጋል፤ ያለሱም አንዳች ለማድረግ አይቻለንም ስለዚህም “ያለኔ አንዳች ማድረግ አትችሉም” ብሎ አስተምሮናል (ዮሐ. 15፥5)

“የሃይማኖትና የመልካም ሥራ ትርጓሜያቸው ይህ ነው፤ ሃይማኖት ለመጽደቂያ መልካም ሥራ የሃይማኖት መግለጫ ነው፡፡ መልካም ሥራ የሠራን እንደሆነ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆናችን ይታወቃል (ዮሐ. 15፥8)”

50 comments:

 1. many recent studies of the Greek word= pistis= have concluded that its primary and most common meaning was =faithfulness, meaning firm commitment in an interpersonal relationship.[11][12][13][14] As such, the word could be almost synonymous with "obedience" when the people in the relationship held different status levels (e.g. a slave being faithful to his master). Far from being equivalent to 'lack of human effort', the word seems to imply and require human effort. The interpretation of Paul's writings that we need to "faithfully" obey God's commands is quite different to one which sees him saying that we need to have "faith" that he will do everything for us. This is also argued to explain why James was adamant that "faith without works is dead" and that "a man is saved by works, and not by faith alone," while also saying that to merely believe places one on the same level as the demons (see James 2).

  ReplyDelete
 2. የእምነትን ምንነት አስፋፍታችሁ ስለገለጻችሁት የምግባርና መልካም ሥራን አስፈላጊነት በተመለከተ ፣ መጽሐፍ ከሚያስተምረን አሰፍራለሁ ፡፡ የመጽሐፍን ቃል ባታጐድሉ አስተያየት ለመስጠት ምንም ዕድል አይኖረኝም ነበር ፡፡ መልእክቱን ስለቆረጣችሁት ፣ የጐደለውን ለመሙላት ይኸው ፡፡

  አ/ ምግባር ማለት የእግዚአብሔር ሕግጋትን በአግባቡ መጠበቅና መፈጸም ፣ እግዚአብሔር እንድናደርግ የሚወደውን ደግነት ፣ ወንጌል እንድንፈጽም የሚያስተምረንን በጎነትና ፍቅር ሁሉ መከወን ነው ፡፡ የመጽሐፍ ቃልም “እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው ፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።” በማለት ይጠቀልለዋል ማቴ 7፡12 ፤ ሉቃ 6፡31
  ፡፡ አንዳችንም ብንሆን ክፉ እንዲገጥመን አንመኝምና ፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፡፡ እኛም እርስ በርሳችን በፍቅር እንድንሆን ይመክረናል ፡፡ “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።” ዮሐ 13፡35 ፡፡ “ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።” ሮሜ 13፡1ዐ ፡፡ ይኸም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ደግሞ ፣ የምግባር መገለጫ ነው ፡፡

  በ/ እርሱም (ጌታችንም ማለት) በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና። ቸር መምህር ሆይ፥ የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም። ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም። ትእዛዛትን ታውቃለህ፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አታታልል፥ አባትህንና እናትህን አክብር አለው። እርሱም መልሶ። መምህር ሆይ፥ ይህን ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ አለው። ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና። ይላል ማር 1ዐ፡17-21 ፡፡ እንግዲህ ርሱ ራሱ ጌታና ፈጣሪ የሆነው ምግባራችንን ከወደደልን እኛ ምን እንላለን ?

  ገ/ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ማቴ 25፡34-36 ፡፡ እንግዲህ ርሱ ራሱ ጌታችን መንግሥተ ሰማያት ትገቡበታላችሁ ብሎ ያስተማረውን በጎነት እኛ ስለምን ብለን እንክዳለን ?

  ደ/ በጽሁፋችሁ የሐዋርየው ጳውሎስን ትምህርት ከግራ ቀኝ እያመጣችሁ ስታስነብቡን ፣ ከሐዋርያው ያዕቆብ መጽሐፍ አንድ ቃል እንኳን ፣ በተለይም ምእራፍ ሁለት ሙሉ ቃሉ ስለ ምግባር አስፈላጊነትና እምነት ንጽጽር ሆኖ ሳለ አንድም ቃል አላስነበባችሁንም ፡፡ መጽሐፋችሁ ሉተር ወደ ጀርመንኛ የተረጎመው መጽሐፍ ቅዱስ ይሆን ?

  “Not surprising from a man who would alter Scripture, Luther did not believe in the inerrancy of Scripture either. Well known is his low esteem of the epistle of James (የያዕቆብ መልዕክትን). He called it an "epistle of straw (ገለባ መልዕክት)." In his opinion, it did not contain the gospel. In his translation of the Bible, Luther placed the epistle of James after Revelation, because he disliked it so much.”

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተባረክ ምእመን

   Delete
  2. father son & hollysprit peace of God be with you all i just want to say a little bit abt this blog ,my beloved friends always says now i see why he saied that cause all the time when i open this page the bloger post something anti eotc all the time he or she never say abt protestant ,in my belive this is completly their page but i learned a lot from those who trying to answers specially MEAMEN & i thanks both left & right for teaching me one or the other way as i saied they singing all arround additional books or gedelat yemogne lekeso meleso meleso & meamen geta abzeto yebarkeh ye enate mariam berket yederbeh balehebet yasenahe & again if you can pls contact me at saha2011@yahoo.com

   Delete
  3. I just say WAW! many times I explained my appreciation to you for your deep knowledge and teaching. Some of them were ignored by the admin. I hope you will recive this one...We are learning a lot from you...pls keep on teaching us...melkam memehir blenehla...thank you a lot. Egizer yibarkeh digil tiketeleh. I have no busniess in this bolg but I only come to read yours, more often!!!

   Delete
 3. ክርስቶስን ሳያውቁ፤ ህጉን ሳይጠብቁ፤ በዐመጻና በኃጢአት ሆነው የሞቱ የ40 ትውልድ ዘሮቼ ቢኖሩ እኔ የመነኩሴውን ጻድቅ ደጅ ስለረገጥሁ ብቻ እምርልሃለሁ ብሏል በተባለው ገድላዊ ዜና መሠረት አላስምራቸውም ማለት ነው? ሀገር ለሀገር የምዞረው እኮ በክርስቶስ የተገኘውን የጽድቅ ጸጋ በቂ ስላልሆነ ተጨማሪ መተማመኛ ለማግኘትና በሰማይ በፍርድ ቀን እነዚያ ጻድቃን እንዲከራከሩልኝ አስቀድሜ ያዘጋጀሁት ጠበብ ከላይ ባቀረብከው ትምህርት መሰረት ዋጋ የለውም ማለት ነው። እባክህን በፍርድ ወንበር እኔ የመረጥኩት ጻድቅ ስለእኔ እንዴት መከራከር እንደሚችል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አቅርበህ መልስ ስጠኝ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሀገር ለሀገር የምዞረው እኮ በክርስቶስ የተገኘውን የጽድቅ ጸጋ በቂ ስላልሆነ ተጨማሪ መተማመኛ ለማግኘት..

   Be eyesus sim, minew aba? Be kristos yetegegnaw ye tsedk tsega beki aydelem????

   Delete
  2. I am doing this not b/c what I get from Jessus is not enough but giving respect for those who are selected and blessed by him - if you know what I mean.

   Delete
 4. This the book written during Imperial Haile Selassie, as the Orthodox Christian we should accept the book and live with God.

  ReplyDelete
 5. I am happy to read all the discussion and it helps a lot to see how EOTC is well versed, righteous and firm in the belief of Jesus Christ, our Lord. I really understood how the protestant theology is self defeating, ill-articulated and extremely short of deep understanding about Jesus Christ, our Lord.

  I thank you abaselama. While you posted for spreading protestant ideas, this discussion rather served to preach the true belief and strengthen our understanding and belief in EOTC. It really answered a number of critical questions. Thank you once again. Of all, thank you for those who gave us the answers.specially "ምእመን"

  ReplyDelete
 6. Replies
  1. “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።” የሐዋ.ሥራ 13፥38-39
   “አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን፤ ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ … አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፤ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው። … ትምክሕት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቈጥራለንና። ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።” ሮሜ 3፥20
   “ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን ዐውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። … የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።” ገላ. 2፥16፡21
   “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።” ገላ. 3፥11

   Delete
  2. “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።” የሐዋ.ሥራ 13፥38-39
   “አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን፤ ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ … አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፤ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው። … ትምክሕት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቈጥራለንና። ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።” ሮሜ 3፥20
   “ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን ዐውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። … የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።” ገላ. 2፥16፡21
   “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።” ገላ. 3፥11

   Delete
 7. Replies
  1. “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።” የሐዋ.ሥራ 13፥38-39
   “አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን፤ ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ … አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፤ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው። … ትምክሕት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቈጥራለንና። ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።” ሮሜ 3፥20
   “ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን ዐውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። … የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።” ገላ. 2፥16፡21
   “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።” ገላ. 3፥11

   Delete
  2. AnonymousFebruary 13, 2013 at 12:42 PM ትክክል ነህ!ሰው በህግ ስራ(በሙሴም ሕግ) አይጸድቅም ! ነገር ግን faith የሚለው ቃል ትርጉም ያስፈልገዋል ያለበለዚያ ሃብታም እንዲጸድቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ማለፍ አለባት የሚለውንም biblical ቃል እንዳለ መቀበል ይኖርብናልና!እውነትኛ እምነት ምንድን ነው?For Orthodox Christians, justification by faith is dynamic, not static(long process). Faith is living, continuous, never static or merely a point in time. Faith is not something Christians experience only at one critical moment, expecting it to cover all the rest of their lives. True faith is not a decision; it’s a way of life. Characters of Faith: a. በፍቅር የሚሰራ እምነት =why?b/c= ገላ 5:6 በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።
   1ኛቆሮ 13;13 እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። 1ኛቆሮ 13;2- ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤

   5 የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤

   6 ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤

   7 ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።

   8 ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።It is not a surprise that true love is basically good works as bible says 1ኛ ዮሐ3;18 ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና(good work is true love) በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።1ኛ ዮሐ5:3ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።...continued

   Delete
  3. ...continued..second character2. የሚሰራ እምነት =why?b/c= ያዕ 2:17ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው። አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?

   21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?

   22 እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ @በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ@ ትመለከታለህን?“You see that a man is justified by works and not by faith only.” (Jam 2:24)

   23 መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ። 24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ። In english it clear“You see that a man is justified by works and not by faith only(በእምነት ብቻ ሳይሆን).” (Jam 2:24) 26 ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው። ....continue

   Delete
  4. ....protestants አንድ ዝነኝ መፈክር አላቸው ’ሃይማኖት አያድንም’ ፣ ’እኛ ሃይማኖትን አንሰብክም ’ ፣ ’ያለ ምንም ሃይማኖት እንዲሁ ጌታን በግሌ አምናለሁ …. ወዘተ the third character= ሃዋርያዊ እምነት=why ?b/c= ሉቃ 10:16 የሚሰማችሁ(ሃዋርያትን ነው) እኔን ይሰማል፥ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል። ገላ 1:8ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።

   9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። 20 ኤፌ2:20በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤

   21 በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤

   22 በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ። ማቴ 18:17 እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ። 2ጢሞ.4፡7 ሃይማኖቴን ጠብቂያለሁ 1ጢሞ 4፡2 በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንት ትምህርት እያዳመጡ ሃይማኖት ይክዳሉ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ.....

   Delete
  5. the fourth character እስከ መጨረሻው የሚጸና እምነት why?b/c ማቴ 24፥13እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል፡፡ «ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን(እስከ መጨረሻው የሚጸና እምነት ያገኝ ይሆንን)?» ሉቃ 18፥8፡፡እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።ዮሐ ራእይ 2:1014 የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤ዕብ3:14እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን።ዕብ3:6በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን።ዕብ6:11 conclusion =therfore,It is written, ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም።ዕብ 11:6 አዎ እውነት ነው በህግ ስራ ያለ እምነት አይጸደቅም ነገር ግን ቃሉ እንደዚህ ተቃንቶ ይነበብ!!!

   ‡ Without Sound Faith (Apostolic/ One/ Biblical & Traditional) it is impossible to please Him.
   ‡ Without Loving Faith it is impossible to please Him.
   ‡ Without Working Faith it is impossible to please Him.
   ‡ Without Faith that endures to the end it is impossible to please Him.

   Delete
  6. በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቈጥራለንና።....“ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ @በሕግ@ ሥራ እንዳይሆን ዐውቀን(A man is not justified by the works of the @law)፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። … የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።” ገላ. 2፥16፡21ይህ ምን ማለት ነው?መልሱ= የህግ ስራ እና ከእምነት የሚመነጭ መልካም ስራ የተለያዩ ናቸው ነው! መልካም ስራ ከላይ የተዘረዘሩትን ባህፘት(characterstics) ያሟላ መሆን ይኖርበታል በዋናነት ግን መልካም ስራ ባደረግን ቁጥር=“እናንተ የታዘዛችሁትን ሁሉ አድርጋችሁ እኛ ሰነፎች ሎሌዎች ነን እናደርገው ዘንድ የሚገባንን አደረግን ” (ሉቃ. 17፥10)ማለት ይገባናል!!! ለምን ብንል? ማንም በመልካምነቱ ወደ መንግስተ ሰማይ የመግባት ድፍረት የለውም፤ ምክኒያቱም ሁሉ ኃጢአትን አድርገዋልና፡፡ደኅንነነታችንን ለማግኘት የሚያስችል ፍጹም ሥራ ልንሰራ አንችልም፡፡ኃጢአት ከእግዚአብሔር ለይቶናል፡፡ ኢሳይያስ 59፡2፣ ‹‹ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።››፡፡ከእግዚአብሔር የለየን ኃጢአት ነው፡፡ ሮሜ 3፡23 እንዲህ ይላል፡ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ።‹እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።›› (ኢሳይያስ 53፡5-6)፡፡ሮሜ 5፡6-10 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና። ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤››፡፡ አዎ ሁሉ ነገር ከታረቁ በሁዋላ ነው ከርሱ ጋር ሳንታረቅ ያደረግነው ስራ ሁሉ ምን ይባላል=የህግ ስራ ይባላል

   Delete
 8. Replies
  1. “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።” የሐዋ.ሥራ 13፥38-39
   “አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን፤ ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ … አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፤ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው። … ትምክሕት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቈጥራለንና። ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።” ሮሜ 3፥20
   “ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን ዐውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። … የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።” ገላ. 2፥16፡21
   “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።” ገላ. 3፥11

   Delete
 9. Salvation is by the Grace of God alone. Our Lord died on the cross to save all humanity. That is why those who do not believe in this act on the cross will not be saved. So faith has to come first. In order for your faith to claim existence, it has to be manifested in your deeds. A man is justified by faith but righteousness must follow justification. You cannot be believing one thing and doing something that would contradict your belief. Faith is activated through our deeds.

  Many verses in the Holy Bible show the importance of works "For the Son of Man will come in the glory of His Father with His angels, and then He will reward each according to his works" (Mt 16:27).
  "Do not marvel at this; for the hour is coming in which all who are in the graves will hear His voice and come forth; those who have done good, to the resurrection of life, and those who have done evil, to the resurrection of condemnation" (John 5:28).

  Our Lord Jesus Christ showed us a glimpse of how judgment will be based on deeds. For He said, "Then the King will say to those on His right hand, "Come, you blessed of My Father, inherit the kingdom prepared for you from the foundation of the world for I was hungry and you gave Me food; I was thirsty and you gave Me drink; I was a stranger and you took Me in; 'I was naked and you clothed Me; I was sick and you visited Me; I was in prison and you came to Me" (Mt 25:34-36).

  The works of man are either good or evil. Evil works lead a person to perdition and makes him lose his salvation. But good works are necessary for salvation. Absence of good works shows that the faith is dead and fruitless. However, good works alone are not sufficient for salvation without faith, baptism and without the deserts of the blood of Christ. Salvation cannot be attained except through the blood of Christ..but works make one worthy of the deserts of this blood.

  A person cannot be saved by his striving alone, for the Lord Jesus Christ - glory be to Him –says, "Without Me you can do nothing" (Jn. 15:5). You cannot be saved then, by your own human arm (power) alone without God supporting you.. whatever striving or labor you may have. But grace would not save you by itself unless your will responds to it. In the words of St. John Chrysostom in this regard are, he says, "God does not want us to lie down on our backs and He gives us the Kingdom.. for grace does. not do everything alone".
  Grace is not a cause for laziness, carelessness and slackening.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለትምህርትህ አመሰግናለሁ ፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ

   Delete
  2. kale hiwot yasemaln @ewnt

   Delete
  3. ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ @ ምእመን and ewnt!!!

   Delete
 10. I am a regualr visitor of this site and comign here always to learn more epecially from people like "ምእመን" and others - Please don't get tired responding with the true teaching of my Lord Jessus - Tsegawun yabezalachihu.

  ReplyDelete
 11. ሐዋርያት “ወደ እግዚአብሔር መንግስት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” እንዳሉ:: የሐዋ. 14:22 የሰው ልጅ ይድን ዘንድ ከእርሱ የሚጠበቁትን ማድረግ ይጠበቅበታል::

  እንግዲህ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በዲያቢሎስ ምክር የምትመጣ የሲዖልን መንገድ ትተን በእርሱ ምክር የምትገኝ በገነት መንገድ ብንጓዝ እንደምንጠቀም አስተምሮ የፈለግነውን ለመምረጥ አልከለከለንም ማለት ነው:: ነገር ግን እዚህ ላይ አንዳንድ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ነገሮችን በመጥቀስና ልባቸው ያቀበላቸውን በመናገር የሰው ልጅ በድኅነቱ ውስጥ ምንም ዓይነት ድርሻ አይጠበቅበትም የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ:: ነገር ግን ይህ ሃሳባቸው የተሳሳተ ነው እስቲ እንደ ምሳሌ ጥቂቶችን እንመልከት::

  በመጀመሪያ የምናየው በጸጋው ድነናል የሚሉትን ክፍሎች ነው::
  እነዚህ ክፍሎች ሕገ እግዚአብሔርን አምዘግዝገው ጥለው “ድኅነት የሚገኘው በጸጋ ብቻ ነው” ይላሉ:: ይህ ግን የእግዚአብሔር ቃልና ትእዛዝ የሚቃወም የሐሰት ትምህርት ነው::

  አምላክ ሰውን ያዳነው የሰው ልጅ ሕግጋትን /ትዕዛዘ እግዚአብሔርን ፈጽሞ በመገኘቱ ሳይሆን እንዲህ በርኅራኄው በቸርነቱ በጸጋው ሊያድነው በመፈለጉ ነው:: ሰው በተሰጠው ነጻ ፈቃድ ተጠቅሞ አትብላ የተባለውን በልቶ ጸጋውንና ክብሩን ቢያጣ ተሰጥቶት የነበረውን ሙሉ ነጻ ፈቃድ ጎደሎ ቢሆንበት በበደሉ ተጸጽቶ ንሰሐ ቢገባ እግዚአብሔር የቀደመውን ሙሉ ነጻነቱን ሊመልስለት ተስፋ ሰጠው:: ሕይወትንና ሞትንም በፊቱ አኑሮ የፈቀደውን እንዲመርጥ ሥለጣንን ሊሰጠው ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ አዳነው::

  በዚህ ማዳኑ ውስጥ ታዲያ የድኅነቱ ተጠቃሚ የሆነው የሰው ልጅ ይድን ዘንድ ማድረግ የሚገባውን ሁሉ በማድረግ አሳይቶታል::

  በአብ በወልድ በመነፈስ ቅዱስ ማለትም በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በማመን በፍቅሩ እንዲኖር በባሕርይ ልጁ አስተምሮታል:: ዮሐ. 3:31-36:: ዮሐ. 5:24:: የሕይወትን መንገድ ከፍቶ “መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ ቢበድል ከበደሉ የሚነጻበትን የንስሐ በር ከፍቶለታል:: ማቴ.14:17:: ኃይልና ብርታትን አግኝቶ ዲያቢሎስን እንዲያሸንፍ ከእርሱ ጋር አንድ ሆኖ ይኖር ዘንድ ሥጋውና ደሙን ሰጥቶታል:: ዮሐ. 6:53-59::

  “እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ አዳነ” ማለት “ዕዳችን ተከፍሏል ድካማችን ተቃሏል የድኅነት መንገዱ ተከፍቷል” ማለት ነው:: በዚህ ነገር “እሺ” ብሎ ለመጠቀም “እምቢ” ብሎ ለመጎዳት ለሰው ልጅ ነጻ ፈቃድ ተሰጥቶታል:: እግዚአብሔር ሰውን ወደ በጎ ነገር/ወደ ድኅነት/ ይመልሰዋል እንጂ በግድ ጎትቶ አያመጣም:: ይህም “ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ”ባለው ይታወቃል:: ዮሐ. 14:15 ማነም የወደደ ትእዛዙን ጠብቆ የመጠቀም ያልወደደም ባለመጠበቅ ሊጎዳ ነጻ ፈቃድ አለው:: ጌታችን አልዓዘርን ከመቃብር ሲያስነሣ የመቃብሩን ድንጋይ ሰዎች እንዲያነሱ ሲያደርግ እርሱ ግን ሙቱን ጠርቶ አስነሳ:: ይህንን ማድረጉ ሰው በድኅነቱ ላይ የራሱ የሆነ ድርሻ እንዳለው ለማሳየት ነው::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ

   Delete
  2. ሰውዬው-- ሰው ለመዳን በአንዱ በእግዚአብሔር የባህርይ ልጁ አዳኝነት ማመን ብቻ በቂው ነው። ለመዳኛ የሚበቃና የሚሆን ሌላ ምንም ዓይነት ሥራ በዚህ ምድር ላይ የለም። በኢየሱስ አዳኝነት ያመነ ሰው ደግሞ ከአንድ አማኝ የሚጠበቀውን እምነት በሥራው ይገልጣል። ለምሳሌ መመጽወት የሚያድን ቢሆን ኖሮ ስንቱ ሙስሊም ዘካ እያለ ለድሆች በሚሰጠው ገንዘብ በዳነ ነበር። ነገር ግን ምጽዋት የመዳኛ መንገድ ሳይሆን በክርስቶስ አዳኝነት አምኖ እምነትን በሥራ የሚገልጹበት መሆኑ በስራ ይዳናል ለሚሉቱ በቂ አስረጂ ነው። አበ ብዙሃን አብርሃም የሚመካበት መልካም ስራ ነበረው። ነገር ግን የርሱ መልካም ስራ በእግዚአብሔር ፊት ምንም ነበር። አብርሃም ጻድቅ ተብሎ የተነገረለት በሰራው ስራ ሳይሆን እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል አምኖ በተቀበለ ጊዜ ነው።


   «እንግዲህ በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም። መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት» ሮሜ 4፤1-3
   የአብርሃም ጽድቁ ስራው ሳይሆን እምነቱ ነበር። ያ ማለት ግን አብርሃም ከጻድቅ ሰው የሚጠበቀውን አይሰራም ማለት አይደለም። በኦርቶዶክሳውያን አማኞች መካከል ያለው ችግር «ክርስቲያን ለድኅነት የሚያበቃው የሰራው ስራ ነው ወይስ በእምነት ስለዳነ በስራ የሚገልጸው ተግባር ነው» የሚለው ነገር ግልጽ አይደለም።
   ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ወደ ደማስቆ ሲሄድ ክርስቶስ አገኘው። ዓይኑ ታወረ፤ ማንነቱን ጠየቀ፤ የምታሳድደኝ እኔ ክርስቶስ ነኝ አለው፤ ወደሐናንያ ሄደ፤ የተናገረውን አመነ፤ ተጠመቀ፤ ከዚያም የእምነቱ መሰረት የሆነውን ክርስቶስን በሰውነቱ ተሸክሞ እስከሞት ድረስ እምነቱን በስራው ገለጸ። ሁሉም ሐዋርያት ለመዳን የሚያበቃ ምንም ስራ አልነበራቸውም። በእምነት ብቻ የጠራቸውን ተከተሉ። በዘመናቸው ደግሞ ያመኑበትን በስራቸው ገለጹ። ብዙዎቹ ክርስቶስ ማን እንደሆነ እንኳን እውቀት አልነበራቸውም። ነገር ግን የጸጋው ጥሪ እንዲያው የሚሰጥ በመሆኑ ክርስቶስ አዳኝ መሆኑን አምነው ጥሪውን እየሰሙ ተከተሉ። /ማቴዎስ ቀረጥ ሲቀርጥ፤ ጴጥሮስ ዓሳ ሲያሰግር/

   «በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል።
   እንግዲህ ምንድር ነው? እስራኤል የሚፈልጉትን አላገኙትም፤ የተመረጡት ግን አገኙት» ሮሜ 11፤6-7

   Delete
  3. ለAnonymousFebruary 13, 2013 at 7:28 PM
   ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ አብርሃም እንዲያ የተረዳውን ሐዋርያው ያዕቆብ ደግሞ እንዲህ ብሎታል፤
   "አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን? መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ። ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።" ያዕ 2፡21-24 ፡፡ ይህንን ትምህርት እንደምን አድርገህ ታስማማዋለህ? ሁለት ዓይነት ትምህርት በአንድነት ሊሰበክ አይገባም ፡፡

   Delete
  4. "ነገር ግን ምጽዋት የመዳኛ መንገድ ሳይሆን በክርስቶስ አዳኝነት አምኖ እምነትን በሥራ የሚገልጹበት መሆኑ በስራ ይዳናል ለሚሉቱ በቂ አስረጂ ነው።"what does that mean...???.eyalekk eko yalehu bezehm hone bezeya seram asfelagi newu aydel!!... esti and sewu be- kirstos ameno minim deg sera bysera ejena egrun atatefo bekemet yedenal woyes aydenem ????? yehen becha melselegn kezeya ante yemtlewun amegna letemek!!!

   Delete
  5. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !February 15, 2013 at 5:16 PM

   ምእመን

   I do agree that faith and work can not be separated. According to the scripture "Abraham believed God and called God's friend (wodagi), he also justified or strengthen his friendship by work, like ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ስላቀረበ. In my understanding if Abraham would't had faith ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው አያቀርብም ነበር. We Orthodox Christians use this reference to defense our religious from protestant, I doubt most have us don't have both. I said most us may be you have both, I didn't say any thing bad about you.


   Delete
  6. ለየተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !
   ደግሞ በአኖኒመስ ስም ጀመርክ ወይስ አቋማችን አንድ መሆኑን ለመግለጽ ብለህ መጣህ፡፡ ከላይ ርዕስ ሰጥቶ ያስነበበን ወገን ፣ "እምነት ብቻ" ወይም "Faith alone" የሚሉትን ሰዎች ትምህርት ሊያስተምረን ስለፈለገ ፣ በመልዕክትህ የሥራን አስፈላጊነት ብትጨምርበት የተሟላ ይሆን ነበር በማለት ምግባር የሌላት እምነት የሞተች ናት ተብሏልና ብዬ ለማስነበብ ሞከርኩ ፡፡ ከጸሐፊውና ከጥቂቶች በስተቀር አሁን ሁላችንም አንድ ቋንቋ እየተናገርን ነው ፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡
   ስለ መልዕክትህ አመሰግናለሁ ፤ ሰላም ሁንልኝ

   Delete
 12. Whatever we may try to interprete the Bible or other valuable works of scholars, I sincerely believe that this question of which comes first , faith/belief or deed does not make a lot of sense . To my understanding, faith without action/deed/living up to expectation practically are INSEPARABLE. It is very puzzling to say someone is faithful believer without shwoing his faith in practical terms. Faith without deeds/practice/action is just empty ,and deeds without faith is rootless. I am soory to say but I have to say that trying to see the two pillars as if one comes after another is nothing but mystification.

  ReplyDelete
 13. አባ ሰላማዎች የምትገርሙኝ እኛም ልንሳሳት እንችላለን የሚል እምነት የላችሁም ሁሌ ራሳችሁን እንከን አልባ አርጋችሁ ነው የምታቀርቡት ምእራባውያን ግን አሁን በድነት ላይ ያላቸውን አቋም faith alone doctrine እንደገና ገምግመው ስህተት መሆኑን እየተቀበሉ ነው!!! ኢንተርኔት ላይ = (new prespective on paul) = ብላችሁ ተመልከቱ For the past few decades, a paradigm shift in New Testament scholarship has led some researchers to question whether the church has rightly understood first-century Judaism and the apostle Paul. In the name of a “New Perspective on Paul,” certain men are calling for a reassessment of the traditional Pauline understanding of the doctrine of justification, the nature of good works, and other elements essential to the gospel of Jesus Christ. Prominent among these figures is N.T. Wright, bishop of Durham and theologian who in his voluminous writings is demanding a new reading of Paul, even claiming that the Protestant Reformers misunderstood the apostle.These accusations cannot be easily brushed aside, for they@ strike at the heart of our entire understanding of salvation.

  ReplyDelete
 14. please aba selama dont confuse us!“የሃይማኖትና የመልካም ሥራ ትርጓሜያቸው ይህ ነው፤ ሃይማኖት ለመጽደቂያ መልካም ሥራ የሃይማኖት መግለጫ ነው፡፡”in other words you are saying =Believer can have Assurance of heaven during this lifetime and has= Eternal Security!!!

  ReplyDelete
 15. continued....westerns also testifing now=MODERN TRANSLATIONS ARE DIFFERENT BIBLES!The TEXTUS RECEPTUS, original Greek text from which the Authorized King James Bible was translated, has been the target of textual critics since 1611. Yet copies of it substantially exist today without error. This is the Bible you can trust. destruction/corruption of manscruipts can be traced to 200 A.D., when there lived one of the world's foremost theologians whose name was Origen. Being a TEXTUAL CRITIC, he is supposed to have corrected numerous portions of the sacred manuscripts. Evidence to the contrary shows that he changed them to agree with his own human philosophy of mystical and allegorical ideas. Thus certain original MSS. became corrupt and it is evidently from this source the revised Bibles of this generation have come. Read pages 900-902, Vol. 16, 1936 edition Encyclopedia Britannica and you will see that Origen taught the "LOGOS" is "KTISMA," meaning the Lord Jesus Christ is a created being. Thus, he could easily omit Acts 8:37 and other texts which testify to Christ's deity.ONLY ONE BIBLE CAN BE THE WORD OF GOD

  It has been estimated that there are nearly one hundred versions of the Bible available in the English language today. However, this multiplicity of Bibles does not alter the fact that God has inspired and safeguarded one Bible. This one Bible is written in the Greek language in the New Testament and is called the Textus Receptus or Received Text. The Old Testament has been preserved in the Masoretic Text and is written in Hebrew. The Textus Receptus of the New Testament and the Masoretic Text of the Old Testament combine to give us the complete Word of God. The King James Version of the Bible stands alone as the one Bible in use today which has been faithfully translated from these God- given manuscripts. All of the modern versions are based wholly or in part on corrupt texts.....

  ReplyDelete
 16. continued....MODERN TRANSLATIONS ARE DIFFERENT BIBLES...The " Bibles" which are so prevalent today are as dependable as quicksand. They will vary even from printing to printing as the constantly changing whims of man directs. However, each new Bible will continue down the same path of confusion and error. You cannot produce good fruit from a rotten tree. ምሳሌ እንመልከት= New American Standard Bible
  Revised Standard Version
  Living New Testament
  Good News for Modern Man
  New English Bible
  Amplified New Testamen =John 6:69 -- Christ is omitted

  Acts 9:20 -- Christ is changed to Jesus

  Acts 15:11 -- Christ is omitted

  Acts 16:31 -- Christ is omitted

  Romans 1:16 -- Christ omitted
  Romans 16:24 -- entire verse about Christ emitted
  1 Cor. 5:4 -- Christ omitted twice

  1 PETER 2:2

  The King James Version:

  "As newborn babes, desire the sincere milk of the word, that ye may grow thereby." Good News for Modern Man:

  "Be like newborn babies, always thirsty for the pure spiritual milk, so that by drinking it you may grow up and be saved."New World Translation: (Jehovah's Witnesses)

  "And as newborn infants, form a longing for the unadultered milk belonging to the word, that through it you may grow to salvation."New American Standard Bible:

  "Like newborn babes, long for the pure milk of the word, that by it you may grow in respect to salvation."


  The wording may be slightly different in each of these new Bibles, but it should be obvious that they all have the same corrupt source. No amount of polish can correct an untrustworthy text.
  what a modern translations!?

  Modern translations are not just simply different versions of the King James Bible written in contemporary language. These perversions are different Bibles entirely. Their foundation is not the God-preserved Textus Receptus of the New Testament. Instead, they are based on contaminated, Christ-denying manuscripts which had been rejected by the early church fathers.

  This turning away from the true Bible to a wicked counterfeit is largely the work of humanistic scholarship. Men who call themselves textual critics have placed their thoughts and ideas above those of God and have presumed to improve upon that one Bible which has been given by God. One can only conclude that they have been so blinded by their compromise and delusions of self-importance that they forget God has already given us His Word. The duty of every believer today is to take the one Bible which God has given and proclaim its glorious message of salvation to a sin-sick world.

  "I marvel that ye are so soon removed from him that called you into the grace of Christ unto another gospel . . . As we said before, so say I now again, If any man preach any other gospel unto you than that ye have received, let him be accursed" (Galatians 1:6, 9). Almost 2000 years ago men were preaching another gospel no doubt from another Bible. However, never since the Bible was given has it been under such Satanic attack as it is in our generation. Humanistic scholarship has deviated from the Textus Receptus in about 6000 places. This has the same effect as questioning the inerrancy of the Holy Bible in 6000 places. Charles H. Spurgeon stated it very well when he said, "The craving to alter the Word of God is accursed. This is the crime of the present day. The Lord preserve us from it."....http://www.jesus-is-savior.com/Bible/which_bible_can_we_trust.htm ቀሪውን ራሳችሁ አንብቡት በነገራችህን ላይ ሉተርም ከዚህ ህጸጽ እጁ አለበት=ሉተር ወደ ጀርመንኛ የተረጎመው መጽሐፍ ቅዱስ

  “Not surprising from a man who would alter Scripture, Luther did not believe in the inerrancy of Scripture either. Well known is his low esteem of the epistle of James (የያዕቆብ መልዕክትን). He called it an "epistle of straw (ገለባ መልዕክት)." In his opinion, it did not contain the gospel. In his translation of the Bible, Luther placed the epistle of James after Revelation, because he disliked it so much.” እንዲል ምእመን!!!

  ReplyDelete
 17. I realy do not care about religen but please teach us from the holly BIBLE about Jesus Christ.I do not care about Protestant or ETHIOPIAN ORTHODOX only I do want learn the truth of Jesus Christ that is the only way to go to Heaven. It should not be a competation about RELIGEN ORTHODOX or PROTESTANT JESUS DIED for ALL HUMANBING.May the GOD almighty richely Blessed us.After all the most important thing is LOVE one ANOTHER.

  ReplyDelete
 18. For The article writer, Please before you write something refer the Old Churches teaching ( Orthodoxy or Catholicism).

  You are not writing about salvation or Bible. You are just pro Protestant and anti-Christ. We dont care What ever your motive is.Orthodoxy will witness for Jesus Christ is Lords of Lord, Kings of King, the Son and the Words of God , He is God the teaching Orthodoxy and Holy BIBLE.

  ReplyDelete
 19. For Anonymous February 14,2013 at 8:28am. how is going to help you for your salviation if the writer say Orthodox old Church or Catholicism? all we need is the truth it is not from this domination aor aother domination. I think it is our responsiblity to read the Holly Bible to understand first and seek other explanation to support our undersanding. We all need salvation regardles of race religen or color.

  ReplyDelete

 20. እምነትን በስራ መግለጥ ያድናል
  እርግጥ እናንተ የመጽሃፍን ሃሳብ በአንድ በኩል ስልምትመለከቱት ትሰታላችሁ::
   ስራ ብቻውን ያድናል አይባልም። ስራ ምን አልባት ወደ እምነት ሊያደርስ ይችል ይሆናል /ሐዋ 10 ቆርነሊዎስ/
   ሰውም በስራው ፍጹም ሊሆን አይችልም ሆኖም በተቻለው መጠን መልካም ነገር ማድረግ አለበት
   እግዚአብሔር ሐጢያተኞችን ይቀጣል።
  ሰው ለመዳን እምነት ብቻ እንጂ መልካም ስራ አያስፈልግም የሚሉ አካለት አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እምነት ያለ ስራ የሞተ ነው ይላል።
  ያዕ 2፡14 ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? 17 እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።26 ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።
  ሐጢያት የሚያደርጉ ሰዎች እንደማይድኑ
  ሮሜ 1፡32 እንደነዚህ (የተዘረዘሩ ሃጢያቶችን) ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም።
  ሮሜ 6፤ 23 ስለዚህ ሐጢያትን የሚያደርጉ ሁሉ ከሞት አያመልጡም።ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው
  ሮሜ 8፤ 6 እንግዲህ ስለ ስጋ ማሰብ ሞት ከሆነ በዚህ ዓለም የስጋ ስራ ወንድምን በመግደልና በልዩ ልዩ ሐጢያቶች ያሉ ሁሉ ሊድኑ ይችሉ ይሆንን?
  1ዮሐ 3፤ 5 ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ
  የእግዚአብሔርን ስም የሚጠሩ ሳይሆን ፈቃዱን የሚያደርጉ ይድናሉ።
  ማቴ 7፡ 21-23 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
  ማቴ 25፡ 32-42
  ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
  አምሰግናለሁ !!!
  “””””ምእመንን”””” ለማግኜት መጥሁና ይቺን Copy then paste አደረግኅት!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንኳንም እኔን ለማግኘት ስትል መጣህ ፡፡ ይኸው በሰበብ ብዙ አስተማርከን ፤ እጅ ለእጅ የመያያዛችን ጥቅሙና ምልክቱ እንዲህ ሁሉም የዕውቀቱን ማካፈሉ ፣ ያነበበውን ማጋራቱ ነው ፡፡ በጣም ደስ የሚል ማስረጃ ነው ፡፡

   ወንጌልን በምንም በምን እያሉ በየምክንያት ያጠኗታል ያለው ይኸን የኛንም ሥራ ይመስለኛል ፡፡ ያለ ርዕስ ቢሆን በግሌ በቀን ብዙ ገጽ አላነብም ፤ አንድ ሦስቴ ስላነበብኩት ፣ መጽሐፍትን ለማዛመድና ለመያያዝ በማለት ካልሆን ለመቀመጥ ትዕግስት አይኖረኝም ፡፡ ርዕስ ከሰጡኝ ግን ሙሉ የብርሃን ቀንና የጨለማ ሌሊትን ብቀመጥ አልሰለችም ፤ እህልና ውሃም እንኳን ትዝ አይሉኝም ፡፡ አባ ሰላማዎችን ተጣብቄም የቀረሁበት ምክንያት ለማንበብ ምክንያቴ ስለሆኑ ነው ፡፡ እንዲሁ ቀጥል ፤ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ሱሰኛ ትሆናለህ ፤ በበለጠ ትረዳዋለህ ፤ መልዕክቱ በገባህ ቁጥር ደግሞ የፈጣሪያችን ፍቅሩ ምን ያህል እንደሆነ ይገለጽልሃል ፡፡ ፍቅሩን እየተረዳህ ስትሄድም ፣ ቀስ በቀስ በህይወትህ እየተለወጥህ ትሄዳለህ ፡፡ በራሴ ገጠመኝ ያየሁት ነው ፡፡ ብዙ የባህርይ መታረቅ ፈጥሮልኛል ፡፡ ሙያዬና ጥበቤ ሌላ ሁኖ ሳለ ፣ አሁን ጊዜ ካገኘሁ ለማንበብ የምተጋበትና የምረካበት መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ፡፡ በተረፈ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የሚባል ሰው ከሌሎቹ ትምህርቶቹ በተጨማሪ የዮሐንስ ወንጌልን በየምዕራፍ እየሄደበት 44ኛው ሳምንቱን ጨርሷል ፡፡ የሚጠቅም ስለሆነ በ www.mekrezzetewahdo.org ገብተህ ተከታተለው ፡፡ መጽሐፍን ለመረዳት በጣም ያግዛል ፡፡ ተጨማሪ የኢኦተቤ ትምህርቶችን ታገኛለህ ፤ አሁን አሁን ደግሞ የሌሎች አስተማሪዎችንም ትምህርት እያከለ ስለመጣ ብዙ ይረዳል ፡፡ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ብትጎበኘው መልካም ነው ፡፡ ወደፊትም መጽሐፍን የሚያስተምሩንንና የምረካባቸውን ብሎጎች እጠቁምሃለሁ ፡፡

   ጌታ ይባርክህ ፤ ሰላምህንም ያብዛልህ

   Delete
  2. ምን ልበል ምእማን ብቻ ድንግል ትርዳህ ነዉ የምለው::በተረፈ አሁን ምክርህን ሰምቸ ይበልጥ ተጋሁ:: ይገርምሃል እኔም ሙያዬና ጥበቤ ሌላ:: አሁን ግን በየቦታዉ ዎንጌል ሲጣመም ሳይ ዎንጌልን ለማወቅ ይበልጥ አገረሸብኝ::አንተን የምሰለ ዎንድም ስለሰጠኝ ዎንጌልን አለቀቅሁትም::ስልሰጠኽኝ መረጃ ጠጣም አምሰግናለሁ!!!

   Delete
 21. ያን ያህል ከርእሱ ጋር ባይሔድም መልእክቱ ግን እርቁአል ማለት አይደለም::በተለይ አባሰላማን ለምሰሉ ጥሩ ትምህርት ይስጣል ብየ አምናለሁ::
  ድህነት በቅጽበት የሚካሄድ ወይስ እስከ ህይወት ፍጻሜ የሚሄዱት
  ድነሃል ? ወይስ?
  ይህን ጥያቄ ለክርስቲያን የሚጠይቅ ሰው እውነተኛ ኦርቶዶክስ አደለም:: ወይም ፕሮቴስታንት ነው አለበለዚያ ግን ባህሉ ወደ ፕሮቴስታንት ያመዘነ ነው:: መጠመቅህን እና ቅዱስ ሚስጢራትን ማድረግህን ችላ በማለት እምነትህን በተመለከት በጥርጣሬ ሊሞላህ እና የለፈው ህይወትህ በግብዝነት ያሳለፍከው በማስመሰል እንደገና እንድታምን የሚጠራህ በመሆኑ ነው:: ይህ ሰው ፍጹም ኦርቶዶክስ አደለም ነኝ ቢል እንኩዋ ንግግሩ ይከዳዋል::
  እንደዚህ ለሚጠይቅህ ሰው አዎ በመጠመቄ ከውርስ ሃጥያት ድኛለሁ ብለህ መልስ:: ይህ የመጀመርያው ድህነት በክርስቶስ ደም በኩለ የሆነ የታረቅንበት ካሳ የመክፈል ሃይል ባለው በደሙ የሆነ ነው:: የመጨረሻውን ድህነት በተመለከት የምናገኘው ግን "መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።" ኤፌ 6:12 እንደተባለው ይህን ጦርነት ስናሸንፍ ነው:: ስጋን እስከለበስን ደረስ ግን ይህ ውግያ ስለሚቀጠል ድነናል ማለት ከንቱ ነው:: "ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?" 1ኛ ጴጥ 4:18
  ሁሌም ሃጥያት ትሰራለህ የሃጥያት ደሞዝ ደግሞ ሞት ስለሆነ ሁሌም ለሞት የተጋለጥህ ነህ ስለዚህም ሁሌም ድህነት ያስፈልግሃል:: ከሃጥያትህ ሁሉ የሚያድንህ የክርስቶስ ደም ሁሌም ያስፈልግሃል:: ስለዚህም ሁሌ ንሰሃ መግባት መናዘዝ እና ስጋና ወደሙን መውሰድ ይገባሃል:: ድህነት ስለዚህ በየግዜው እየታደሰ የሚቀጥል ነው:: ሁሌም ስለርሱ ትጸልያለህ ንሰሃ በገባህ ና በተናዘዝህ ቁጥር ስጋና ደሙን በወሰድህ ግዜ ድህነት ታገኛለህ::

  እውነተኛው የኦርቶዶክስ መልስ ይህ ነው:: "እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ። "ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፥8
  Salvation in Orthodox view
  Pop HH Shenouda III

  ReplyDelete
 22. anonymous For on February 16,2013@10 pm and 10:16pm
  Please help me to understand what you mean when you said that “the truth answer
  According to Orthodox teaching not Jesus’ teaching”? What do you mean Ethiopian Orthodox not
  Following Jesus’ teaching? Please any one clarifies this for me if I misunderstand it. And also the Division
  Among Protestant and Orthodox I still not understand it the competition between those two religions.
  The most important I always thinke is to bring people to know Christ Jesus. So instead of division why we do not working
  For GOD. You know God loves everybody not only Orthodox or Protestant. At least let us agree with the common believe for the two of
  The religion. I do not think God will be pleased this is Orthodox or this is Protestant. This is not a Market we all need salivation.
  And we have to bring the one they don’t believe in Christ Jesus together. Selfishness has no places in God’s Eye.
  Jesus died on the Cross for the whole world
  Not only for Ethiopian Orthodox or Protestant. Let us focus on the main thing not always on the difference.Nobody will go heaven or hell because of you are Ethiopian orthodox or protestant. you only go to heaven if you know your saver The Lord Jesus Christ. pleas let us not waste our time by division.

  ReplyDelete
  Replies
  1. @AnonymousFebruary 18, 2013 at 12:48 PM

   This is the verse Colossians 2: 8 "See to it that no one takes you captive through hollow and deceptive philosophy, which depends on human tradition and the elemental spiritual forces of this world rather than on Christ." Basically don't let anyone deceive you and take you captive to the worldly matters. I think you kind of misunderstood the point he was trying to make. The question is not weather God only loves Orthodox and hates Protestants. It's obvious God loves the whole world and he died for our sins and transgression.
   Let me paraphrase his point. He asks "ድህነት በቅጽበት የሚካሄድ ወይስ እስከ ህይወት ፍጻሜ የሚሄዱት ድነሃል ?" As you continue reading you'll find salvation is a process. It's a whole life commitment. No doubt we're all saved by the blood of our Lord Jesus. But evil deeds will make us loose our salvation. Let me give you a simple analogy. What do we humans need to survive (live)? we need food, water, oxygen, sleep, shelter, clothes etc...Without oxygen, we can't survive by food and water alone. And without sleep, we can't survive by oxygen alone. Just as we need all this basic needs to survive, we need faith, repentance, baptism, receive Holy Communion and continue to do good deeds. That's why we orthodox Christians reject the "Faith Alone" doctrine. We are not in the place of God to say "protestants will go to hell". We're not in any condition to judge when we are sinners ourselves. One thing we know for certain is, the faith and beliefs we hold dearly are all transferred to us from the holy apostles themselves. We always testify in our prayers "We believe in one holy catholic and apostolic Church" so we ask the Protestants and others alike to come and join the true apostolic church our Lord Jesus Christ established. We condemn their teachings but we love them all. As St. Augustine said "the common Love of Christ unites all Christians."
   I suggest you read “Salvation in the Orthodox Concept” by Pope HH Shenouda III to better understand this matter
   God bless

   Delete
  2. ለAnonymous February 18, 2013 at 12:48 PM

   Ewnt ባስተላለፈው ላይ የሚታከል አስተያየት ነው ፡፡
   According to Orthodox teaching የሚለው አገላለጽ በየምክንያቱ የሚጠቀሰው ፣ ቤተ ክርስቲያናችን ከአብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የተለየ አምላክ ትሰብካለች ፤ በክርስቶስ ሞት መዳናችንን ትክዳለች በማለት ሳይሆን ፣ የመጽሐፍ ትርጓሜዋንና ትምህርቷን ብቻ የሚያመለክት ነው ፡፡ ይኸ በመጽሐፍ ትርጓሜ መከራከር ደግሞ ጥንት ለክርስትና እምነት የታገሉት አባቶች የጀመሩት እንጅ ፣ ዘመናችን የፈጠረው አዲስ ጉዳይ አይደለም ፡፡ ጥንት ድንግል ማርያም አምላክን አልወለደችም ፤ ኢየሱስ ፍጡር ነው ፤ መንፈስ ቅዱስ አገልጋይ ኃይል ነው እንጅ አምላክ አይደለም የሚሉትን የተሳሳቱ ትምህርቶች እንደተከራከሩበት ፣ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችን የምታስተምራቸውንና የምትሰብካቸውን ሁሉ ስህተት በማለት ለሚመጡብን መልስ መስጠታችን የአባቶች ልምድ ተቀጥላና አግባብ ነው ፡፡

   ኘሮቴስታንት ድንግል ማርያም ሰባት ልጆች አሏት ብለው ሲሉን ፣ እኛ ልጅዋ አንድ ነው ብለን የምናምንበትን ማሳወቅ እነርሱን መጥላት አይደለም ፤ በእምነትህ ብቻ ትድናለህ ብለው ሊሰብኩን ሲሉ ፣ ምግባርን የት ትታችሁት ብለን መጠቆማችን ራሳችንን መውደዳችን አይደለም ፡፡ ኢየሱስ ዛሬም የአብን ቀኝ እጅ ይዞ ተንበርክኮ ስለ እኛ ይማልዳል ሲሉን ስታችኋል ርሱ የሚፈርድ አምላክ ነው ብለን ስህተታቸውን ማሳወቃችን ፣ በቀና የሚገነዘብልን ካገኘን አንድም በቃላቸውና በአምልኮአቸው እንዲስተካከሉ እነርሱን ማስተማራችን ነው ፤ ሌላም ብዙ ምሥጢራትን ያልተረዱ ምእመናን በሚተላለፈው የተሳሳተ ትምህርት በዘፈቀደ እንዳይነዱ መረጃ መስጠታችን ነው ፡፡ የእነርሱም ዓላማ መንጋ ለማስኰብለል ስለሆነ ፣ ያንን አካሄድ ለመግታት የምናደርገው ትግል ነው ፡፡

   I do not think God will be pleased this is Orthodox or this is Protestant. ይኸም ትክክለኛ አባባል ነው ፡፡ ነገር ግን በአምልኮና በእምነት ተሳስታችኋል ብለው ሲወቅሱን ፣ አለመሳሳታችንን ማስረዳታችን ፣ ትክክለኛውን ሃይማኖት እንዲረዱት ለማገዝና ወደ አንድነት ለማምጣት መሆኑን ብትረዳው መልካም ነው ፡፡

   ሰላም ሁንልኝ

   Delete