Monday, February 18, 2013

የአባ ሳሙኤል አቤሴሎማዊ መንገድ

አቤሴሎም የዳዊት ልጅ ነው፡፡ የእህቱ የትዕማር በአባታቸው ልጅ በወንድማቸው በአምኖን መደፈር የእግር እሳት ቢሆንበትም፣ የሆዱን በሆዱ ይዞ ሁለት ዓመታትን በዝምታ አሳልፏል፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ግን በጎቹን ለማሸለት ባዘጋጀው በዓል ላይ አባቱን ዳዊትን አሳምኖ አምኖን በዝግጅቱ ላይ እንዲገኝ አደረገ። ከዚያም በወይን ጠጅ አስክሮ ራሱን ሲስት በአገልጋዮቹ አስገደለው፡፡ ከዚያም የእስራኤልን ምድር ለቆ ወደ ጌሹር ሸሸ፡፡ ሶስት ዓመታትንም በዚያ አሳለፈ፡፡

ዳዊት ከልጁ ከአምኖን ሞት ከተጽናና በኋላ ወደ አቤሴሎም ይሄድ ዘንድ ልቡ ናፍቆ ነበር፡፡ ይህን ያስተዋለው የዳዊት የጦር አለቃ ኢዮአብ አንዲት ብልህ ሴትን ተጠቅሞ አቤሴሎም ከኮበለለበት ወደኢየሩሳሌም እንዲመለስ ትልቅ ስራ ሰራ፡፡ ይሁን እንጂ ዳዊት ፊቱን እንዲያይ ስላልፈቀደለት አቤሴሎም ከአባቱ ጋር ሳይተያይ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ አቤሴሎም የንጉሡን ፊት ማየት አለብኝ ብሎ ወደኢዮአብ በተደጋጋሚ መልእክት ላከ፡፡ ኢዮአብ ግን አልሰማውም፡፡ ስለዚህ በእርሱ እርሻ አጠገብ የነበረውን የኢዮአብን እርሻ እንዲያቃጥሉ በማድረግ ኢዮአብን እንዲመጣ አስገደደው፡፡ ከዚያም ከንጉሱ ጋር እንዲያገናኘው አደረገ፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር አቤሴሎም የዳዊትን መንግሥት ለመገልበጥ እንቅስቃሴ የጀመረው፡፡ ታሪኩን ከመጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ ምዕራፍ 13-19 ላይ ማንበብ ይቻላል፡፡

ይህ የአቤሴሎም የመንግስት ግልበጣ ሙከራ እንቅስቃሴ አባ ሳሙኤል ፓትርያርክ ለመሆን ከመጀመሪያ እስካሁን ከተጓዙበት መንገድ ጋር የሚመሳሰል ገጽታ አለው፡፡ በመጀመሪያ አቤሴሎም ከኮበለለበት ተመልሶ ከሁለት ዓመት በኋላ የዳዊትን ፊት እንዳየ “በማለዳ ተነሥቶ በበሩ አደበባይ ይቆም ነበር አቤሴሎምም ከንጉሥ ለማስፈረድ ጉዳይ የነበረውን ሁሉ ወደ እርሱ እየጠራ። አንተ ከወዴት ከተማ ነህ? ብሎ ይጠይቅ ነበር። እርሱም፦ እኔ ባሪያህ ከእስራኤል ነገድ ከአንዲቱ ነኝ ብሎ ይመልስ ነበር። አቤሴሎምም። ነገርህ እውነትና ቅን ነው ነገር ግን ከንጉሥ ታዝዞ የሚሰማህ የለም ይለው ነበር።” (2ሳሙኤል 15፡2-3)፡፡

አባ ሳሙኤል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በነበሩ ጊዜ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ህንጻ በማሰራታቸውና አንዳንድ ለታይታ የዋሉ እንቅስቃሴዎችን ማድረጋቸውን ተከትሎ ጥቂት ጥቅመኞችን ከጎናቸው በማሰለፍ የሀገረ ስብከቱንና በየደብሩ ያለውን ገንዘብ ከሚበሉ “አምስቱ ከለባት” ጋር በመመሳጠር “ምን ዋጋ አለው ከፓትርያርኩ በኩል ጉዳይህን የሚሰማህ የለም” የሚል አይነት የማሳጣት ስራ ጀምረው እንደነበርና  እዩኝ እዩኝ ይሉ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

አቤሴሎም በየማለዳው ያደርግ የነበረውን ንጉሱን የማሳጣት ሥራ ቀስ በቀስ ወደላቀ ደረጃ ከፍ አድርጎታል፡፡ “ነገርና ክርክር ያለው ሁሉ ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ ቅንም ፍርድ እፈርድለት ዘንድ በአገር ላይ ፈራጅ አድርጎ ማን በሾመኝ? ይል ነበር።” (2ሳሙኤል 15፡4)፡፡ አባ ሳሙኤልም የፓትርያርኩ ረዳት መባላቸውን መነሻ በማድረግ ያለአቅማቸው ተሸክመውት የነበረው ረዳትነት አልበቃ ስላላቸው “ፓትርያርኩ አርጅተዋል፤ እርሳቸው ቡራኬ ብቻ እየሰጡ መቀመጥ ነው ያለባቸው ሌላውን ስራ እኔ መስራት አለብኝ” ማለትና ማስወራት ጀምረው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ ሌሎች ጉዳዮችን ቀስቅሶ ከአቡነ ጳውሎስ ጋር አጋጫቸው፡፡ አባ ሳሙኤልም በጉዳዩ ገፍተውበት አቡነ ጳውሎስ ማስተዳደር አልቻሉም፤ የሚለውን በጳጳሳቱ ዘንድ ሁሉ ለማሰራጨት በመሞከር ሲኖዶሱ ወገን ለይቶ እንዲራኮት እስከማድረግ የደረሰ ስራ ሲሰሩ መቆየታቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ይህ ወደፊት የሚያጭዱት ትልቅ ምርታቸው እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ሆኖም ይህ አባ ሳሙኤልን ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስነት እንዲነሱና ለተወሰኑ ወራት ሳይመደቡ እንዲቀመጡ አድርጓል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው የልማት ኮምሽን ሊቀጳጳስ ሆነው የተመደቡት፡፡

አቤሴሎም “ሰውም እጅ ሊነሣው ወደ እርሱ በቀረበ ጊዜ እጁን ዘርግቶ ይይዝና ይስመው ነበር። እንዲሁም አቤሴሎም ከንጉሥ ፍርድ ሊሰማ ከእስራኤል ዘንድ በሚመጣ ሁሉ ያደርግ ነበር አቤሴሎምም የእስራኤልን ሰዎች ልብ ሰረቀ።” (2ሳሙኤል 15፡4)፡፡ አባ ሳሙኤል በዚህ አቅጣጫ በግልጽም በስውርም ብዙ ስራ እንደሰሩ ይታወቃል፡፡ በተለይም ብዙ ገንዘብ በማፍሰስ ሚዲያን እየተጠቀሙ የአቡነ ጳውሎስ ተፎካካሪ መስለው እንዲታዩ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በዚህ በኩል ማቅ ባይፈልጋቸውም ለአላማው ማስፈጸሚያነትና አቡነ ጳውሎስን ስለተቃወሙለት እንደረዳቸው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ለአራት የተከፈሉት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከቶች ስራ አስኪያጆችና አንዳንድ በአዲስ አበባ አድባራት የሚገኙና ያለአንድ ከልካይ ከላይ እስከ ታች በጥቅም ተሳስረው የቤተ ክርስቲያንን ሀብትና ንብረት እየመዘበሩ የሚገኙ አምስቱ ከለባት/ውሾች/ የሚል ስም የወጣላቸው የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሀፊዎች፣ ሳብ ሹሞች፣ ቁጥጥሮች እና ገንዘብ ያዦች እያጨበጭቡላቸው ይገኛሉ፡፡ እነርሱ ምናቸው ይነካል?

ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ የስላሴ ኮሌጅ ተማሪዎች ቀጣዩ ፓትርያርክ እርሳቸው መሆን አለባቸው ብለው ተፈራርመዋል መባላቸው ነው፡፡ ይህ የሆነው እንዴት ነው? መቼም ከማንም በላይ አባ ሳሙኤል ከኤልቤቴል መንገሻ (ሚጡ) ጋር ስላላቸው ጾታዊ ግንኙነት እዚያው ሥላሴ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ዘወትር በአይናቸው የሚያዩት እውነት ነው፡፡ ሌላው ቢቀር እንኳን ይህን ማንነታቸውን እያወቁ ቀጣዩ ፓትርያርካችን እርሳቸው ናቸው ሊሉ እንዴት ይችላሉ የሚለው እያነጋገረ ነው፡፡ ብዙዎቹ ተማሪዎች አባ ሳሙኤል መጽሐፍ እንዳልጻፉና ሰዎችን እያጻፉ በስማቸው በማሳተም “ብዙ መጽሐፍ የጻፉ ጳጳስ” መባል እንደሚፈልጉና ፓትርያርክ ለመሆን ላላቸው ህልም እንደግባት መጠቀም እንደሚፈልጉ ከማንም በላይ ያውቃሉ፡፡ ሌሎችም በርካታ የሚጠቀሱ ችግሮች እያሉባቸው እርሳቸውን እንዴት ለፓትርያርክነት አጩ የሚለው ሊመለስ የሚገባው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡

በዚህ ረገድም አባ ሳሙኤል በአቤሴሎም መንገድ ተጉዘዋል ባይ ነኝ፡፡ አቤሴሎም የእስራኤልን ልብ እንደ ሰረቀ ያረጋገጠ በመሰለው ጊዜ ስእለት አለብኝና ሄጄ ላቅርብ ብሎ ንጉሥ ዳዊትን አስፈቅዶ ወደ ኬብሮን በመሄድ ለጊዜው የተሳካ የመሰለ መፈንቅለ መንግስት አካሄደ፡፡ ለመሳካቱ በኬብሮን ያሰማራቸው ሰላዮቹ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ “አቤሴሎምም በእስራኤል ነገድ ሁሉ የቀንደ መለከት ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ በሉ የሚሉ ጕበኞች ላከ።” የሚለው ቃል ለዚህ ምስክር ነው፡፡ (2ሳሙኤል 15፡10)፡፡ አባ ሳሙኤልም ምርጫው ባልተጀመረበትና ለፓትርያርክነት እጩ ሆነው ለመቅረብ መስፈርቱን ያሟሉ አያሟሉ ገና ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ቀጣዩ ፓትርያርክ እርሳቸው መሆናቸውን በእርግጠኝነት ማስወራታቸው የጤና አይደለም፡፡ ይህን የምለው ከዚህ ቀደም በዚሁ ድረገጽ ላይ ተዘግቦ እንዳነበብኩት የምርጫ ህጉን በልካቸው እንዲሰፋ ማድረጋቸውን ሳልዘነጋ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር የስላሴ ተማሪዎች አባ ሳሙኤልን መደገፋቸው በተላኩት ሰላዮች በኩል በቀረበላቸው የማባበያ ሐሳብ ተታለው፣ አንዳንዶቹም ባያምኑበትም ቀጣዩ ፓትርያርክ እርሳቸው ከሆኑ የተለየ ሐሳብ ባቀርብና ባልፈርም በበቀለኛው አባ ሳሙኤል ክፉኛ እመረዛለሁ ብለው ይሆናል የሚል ግምት አለኝ፡፡ አቤሴሎምን የተከተሉት ሁሉ ሴራውን በሚገባ የተረዱ አልነበሩም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሲመሰክር “የተጠሩትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአቤሴሎም ጋር በየዋህነት ከኢየሩሳሌም ሄዱ የሚሆነውንም ነገር ከቶ አያውቁም ነበር።”  ይላል፡፡ (2ሳሙኤል 15፡11)፡፡

ለአቤሴሎም ጊዜያዊ መፈንቅለ መንግስት መሳካት በዋናነት የረዳው ቀድሞ የዳዊት አማካሪ የነበረውና ምክሩ ጠብ የማትለው አኪጦፌል ከእርሱ ጋር ስለነበረ ነው፡፡ “አቤሴሎምም የዳዊት መካር የነበረውን የጊሎ ሰው አኪጦፌልን ከከተማው ከጊሎ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ አስጠራው። ሴራውም ጽኑ ሆነ ከአቤሴሎምም ጋር ያለ ሕዝብ እየበዛ ሄደ።” ይላል (2ሳሙኤል 15፡11)፡፡ ይህን በሰማ ጊዜ ዳዊት “አቤቱ፥ የአኪጦፌልን ምክር ስንፍና አድርገህ እንድትለውጥ እለምንሃለሁ አለ።” (2ሳሙኤል 15፡31)፡፡ ዛሬም አባ ሳሙኤል የሌላቸውን ሰብእና እየገነቡ ያሉት እንደአኪጦፌል ባሉ ቅጥረኞቻቸው በኩል መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ የስላሴ ተማሪዎችን ለማሳመን እስከመሞከር የደረሱት በአኪጦፌሎቻቸው በኩል ነው፡፡ እንደ እቅዳቸው ከሆነ ከየሀገረ ስብከቱ የሚመጡት መራጮች በስራ አስኪያጆች በኩል ለመያዝ ከፍተኛ ብር መድበው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
  
አባ ሳሙኤልን በአቤሴሎም መንገድ ውስጥ ከማሳየት እንውጣና ሌላው ሊነሣ የሚገባውን ጥያቄ ላንሳ፡፡ አባ ሳሙኤል በልካቸው እንዲሰፋ ባደረጉት መስፈርት መሰረት የፕትርክናውን መስፈርት ያሟሉ ይሆናል እንበል፡፡ ነገር ግን በሰብእናቸው ዙሪያ ሐሜት ያልሆኑትንና አገር ያወቃቸውን ጸሀይ የሞቃቸውን ለአንድ ጳጳስ ተገቢ ያልሆኑትን የሕይወት ችግሮች ሊያልፉ የሚችሉበት እድል በመስፈርቱ ውስጥ አለ ወይስ የለም? በዘሪሁን ሙላቱ የተጻፈባቸውን የጳጳሱ ቅሌት መጽሀፍ ዘሪሁንን ከመክሰስ በቀር አላስተባበሉም፡፡ ታዲያ ጉዳዩን በአንድ ራስ ሁለት ምላስ የሆነው ዘሪሁን በጳጳሱ ስኬት መጽሀፉ አስተባብሎላቸዋል ተብሎ ይታለፍ ይሆን? ከምሥራቅና ከሚጡ ጋር ስላላቸው ግንኙነት የማያውቅ የቤተክህነትና የቤተክርስቲያን አገልጋይ አይኖርም፡፡ መስፈርቱ እነዚህን ፋክቶች እንዴት ይመለከታቸው ይሆን? ሐሜት ነው ይል ይሆን? ወይስ ይህ ነጥብ የሌሎቹንም ጳጳሳት ችግር ስለሚቀሰቅስ “የውሾን ነገር ያነሣ …” በሚል በዝምታ ይታለፍ ይሆን?

አባ ሳሙኤል ጨካኝ፣ በቀለኛና አምባገነን መሆናቸውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በነበሩ ጊዜ በተግባር አስመስክረዋል፡፡ ስንቱን አገልጋይ ለችግር ዳርገውና የስንቱን ቤት በችግር ፈተው ያጉላሉበት፣ ብዙዎችን ለከፋ ረሃብና እንግልት የዳረጉበት ታሪካቸውን የችግሩ ሰለባዎችና በጊዜው በመገናኛ ብዙሃን ይፋ የሆኑ ዘገባዎችን የተከታተሉ ሁሉ የሚያስታውሱት ሀቅ ነው፡፡ አባ ሳሙኤል እኮ የአይንህ ቀለም አላማረኝም ብለው ከአንዱ ደብር ወደሌላ ተዛውረሃል ብለው ደብዳቤ ጽፈው ሲያበቁ፣ ከሄደ በኋላ ለተዛወረበት ደብር በሌላ ደብዳቤ እንዳትቀበሉት ብለው የሚጽፉ “አባት” ናቸው፡፡ በዚያ ወቅት ብዙዎች አቤት ቢሉም ሰሚ አጥተው የቤተክህነት በሮች ስለተዘጉባቸው ጉዳያቸውን ለሰብአዊ መብት ኮምሽን ያቀረቡበትና ኮምሽኑ በቤተክህነት ሰራተኞች አቤቱታ የተጨናነቀበት ጊዜ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አምባገነኑ አባ ሳሙኤል ባላቸው “ያለመከሰስ መብት” ለኮምሽኑ አቤቱታ ጆሮ ሳይሰጡ ተጠያቂም ሳይሆኑ ከአቡነ ጳውሎስ ጋር በመጋጨታቸው ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስነታቸው ተነሱ፡፡  ብዙዎች ግን አሁንም ድረስ እየተጉላሉ ይገኛሉ፡፡

ምን ይህ ብቻ አባ ሳሙኤል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በነበሩ ጊዜ ባዶነታቸውን ለመሸፈን በማደናገሪያነት ልሞክር ወይም ላድርግ ያላሉት አዲስ ነገር አልነበረም፡፡ ከሁሉም የማይረሳው “ቅዳሴ በኢንተርኔት ይቀደስ” በማለት ዘመናዊነት አይሉት መንፈሳዊነት ምእመናን ህያው ከሆነ ቅዳሴ እንዲወጡና በየቤታቸው በቴክኖሎጂ አማካኝነት “እንዲያስቀድሱ” ሙከራ አድርገው ነበር፡፡ ግን አልተሳካላቸውም፡፡

ከሁሉም በላይ ከብጤዎቻቸው በቀር አባ ሳሙኤልን ፓትርያርክ ሆነው ማየት ብዙዎቹ ጳጳሳት የሚቀበሉት እንደማይሆን ይጠበቃል፡፡ ቀድሞም ቢሆን አቡነ ጳውሎስን በመቃወም ሲኖዶሱን እስከ መከፋፈል የደረሰ ሴራ በመሸረብ ሚና ቢኖራቸውም ብዙዎቹ ጳጳሳት አባ ሳሙኤል ያን ያደረጉት ለቤተክርስቲያን ተቆርቁረው እንጂ ፓትርያርክ ለመሆን አስበው ነው የሚል ግምት እንዳልነበራቸው ይነገራል፡፡ ታዲያ አሁን ፓትርያርክ መሆን አለብኝ በሚል ከፍተኛ በጀት መድበውና ብዙ ሰላይ አሰማርተው አገሩን መቀስቀሳቸው የት ያደርሳቸው ይሆን? ሁሉም አባ ሳሙኤል ፓትርያርክ ይሆናሉ ሳይሆን ለፕትርክና የተዘጋጀውን መስፈርት ያሟላሉ ወይ? የሚል ጥያቄ ውስጥ ይገኛል፡፡ አባ ሳሙኤል እነዚህ ሁሉ እንከኖች እያሉባቸው መስፈርቱን ካሟሉ በትክክልም ቤተክርስቲያኗ ሰው የላትም ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም አባ ሳሙኤል የመረጡት የአቤሴሎም መንገድ የት እንደሚያደርሳቸው በቀጣይ የምናየው ይሆናል፡፡

መምህር ጣሰው
ከቤተክህነት        

12 comments:

 1. ፅጊቱ የአባ ሳሙኤል መሾም ላንቺና ለእጅጋየሁ ትልቅ መርዶ ነው። አላማችሁ ትናንት በአባ ጳውሎስ ሞት ተኮላሸ ነገ ደሞ በአቡነ ሳሙኤል የሬሳ ሳጥናችሁ ምስማር ይመታል። ደስ ሲል።

  ReplyDelete
 2. Ye CHELAMAW BUDEN(የጨለማው ቡድን) Gudachihu new Aba samulel Metubachihu.
  Kezihem belay malet Endemitichilu Yitaweqale. Kezih behwala Betekihneten Yematsidat zemecha Yijemeralena.
  Who ever will be the patriarich I am paraying to The Almighty to bless us through Him.
  May God blessed our beloved church.
  በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ
  በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ
  በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ

  ReplyDelete
 3. ke betekihinet???? Tehadisi ahunim betekihinet ale malet new????? ke paulosina ke ejigayehu gar tekebirachihual ekoo !! kezih behuala teterigachihu tiwetalachihu...wushoch !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Please @AnonymousFebruary 18, 2013 at 10:13 PM
   Why bark simply like a dog by hearing the others barking.
   What do you Know exactly by yourself about His Hollynes Abune Paulos's Beliefe.Except what was barked by others ????????
   or
   do you know what criteria can make one body among the Tehadiso group???????
   Do you think every person who is not thinking like you is Tehadiso???
   Please the above person and others barking guys...
   Let us come together to identify the Center of gravity to clear our beloved church from unwanted thinking and practices (not persons) b/c our Saviour Delivered his life for all us not only for Innocent ones.This is also the Core Mission of our Church (ነስሑ እስመ ቀርበት መንግስተ ሰማያት).
   If you think yourself as Chrstian please be Ethical.
   May The Almighty enlightened your eyes

   እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
   በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
   በእንተ ቅዱሳን መሐረነ ክርስቶስ
   Delete
 4. promotre of aba samuale are;1Chere Ababa 2Tadwose girima 3Eskender G.\kerstose.

  ReplyDelete
 5. ወይ መምህር ተብዬ አሁን እንደው ለቤተ ክርስቲያን ተጨንቀው ነውን?ወይስ የተለየ ስውር አላማ ይኖሮዎታል? አይጨነቁ የኛ አምላክ የፈቀደውን ይሹም። እኛ ግን ሀይማኖታችንን ይዘን ጠብቀን እንገኛለን።መልካምም ሆነ ክፉ ፓትርያርክ ይመጣል ይዬዳል።የኛ ሃይማኖት ተዋህዶ ከእግዚህአብሄር የተሰጠችንን አባቶቻችን ጠብቀው እንዳቆዩ እኛም የተዋህዶ ልጆች ለድህነታችን እንጠብቃታለን።ለናንተ ግን ልብ ይስጣችው

  ReplyDelete
 6. Abetu Egziabihier hoye kifu mikren afreseh ante yemertkewn melkam erenga siten

  ReplyDelete
 7. You are right he is poisenous snake

  ReplyDelete
 8. Ene Haymanoten keyire penet ehonalehu. Abba

  ReplyDelete
  Replies
  1. sewu newu eminetun newu sitiketel yenebrewu?

   Delete
 9. wey taso sentun neger taskew bakehe. berta lemanegaweme

  ReplyDelete
 10. ውድ አባ ሰላማ፦ ከዚህ ሁሉ ለምን ምርጫው በዕጣ አይሆንም የምትል ይቺን ጽሑፍ አግኝቼ ላክሁላችሁ። ማስፈንጠርያው እነሆ። አዜብ ነኝ ከዳላስ።
  http://www.ethiopianchurch.org/essay1/150-%E1%8D%93%E1%89%B5%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%88%AD%E1%8A%AD-%E1%89%A0%E1%8B%95%E1%8C%A3.html

  ReplyDelete