Thursday, February 21, 2013

የማኅበረ ቅዱሳን ስም የማጥፋት የቸከ ስልት በፓትርያርክ ምርጫ ዙሪያ

ከመምህር ታየ ከቤተ ክህነት
ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመሾም እየተዘጋጀች ባለችበት በዚህ ወሳኝ ወቅት አባ ሳሙኤል ራሳቸውን ለመሾም የምርጫ ዘመቻ የከፈቱ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ የ20 ጎረምሳ አባት የሆኑትን አባ ሉቃስንና መሰሎቻቸውን በመናጆነት አቅርቧል፡፡ ፓትርያርክ እንዲሆኑ የሚፈልገው ግን በዘረኝነት የሚታወቁትን አባ ማቴዎስን ነው፡፡ እርሳቸውን ለማሾም የሚከፈለውን ማንኛውንም መሥዋእትነት እከፍላለሁ ማለቱን ማኅበረ ቅዱሳን አካባቢ እየተናፈሰ ነው፡፡ ማህበሩ ዕጩ ፓትርያርክ እንዲሆኑ ያሰባቸውን ጳጳሳት ዝርዝር ታሪክ ባወጣበት በሀራ ዘተዋህዶ ድረገጹ ላይ ይፋ እንዳደረገው ዋና ፍላጎቱ አቡነ ማቴዎስ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን አቡነ ማትያስ ግን እንዲሆኑ ከቶም እንደማይፈልግ በዘወርዋራ መንገድ ገልጿል፡፡

በቅርቡ በሐራ ዘተዋህዶ ድረገጽ ላይ የማህበሩን እጩ አባ ማቴዎስን መልአክ አድርጎ ሲስላቸው «በአስተዋይነታቸው፣ ውጥረት በሚፈጠርበት ጊዜ ለማግባባት ባላቸው ተሰጥኦ፣ በተረጋጋ አመራራቸውና መንፈሳዊነት በተመላበት ሰብእናቸው ተለይተው ይታወቃሉ፡፡» ብሏል፡፡ ብፁዕ አቡነ ማትያስን ግን «ብፁዕነታቸው የሚነቀፍባቸው ነገር በአመራርና ለአስተዳደራዊ ችግሮች ፈጣን መፍትሔ በመስጠት ረገድ ይታይባቸዋል የሚባለው ዳተኝነት ነው፡፡» በማለት ሲጸርፋቸው፣ ይህን ክፍተት ሊሞሉ የሚችሉ አንድም እንከን የለባቸውም መልአክ ናቸው ሲል ያሞካሻቸው የማህበሩ እጩ አባ ማቴዎስ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡

ማህበሩ አንዳችም ሊተነፍስ ባይፈልግም ብፁዕ አቡነ ማትያስ በትምህርትም ሆነ በሰብእና ብዙ ሊነገር የሚችል ማንነት ያላቸው አባት ቢሆኑም አባ ማቴዎስን ክቦ አባ ማትያስን እያንኳሰሰ መግለጹ ድረገጹን ትዝብት ላይ ጥሎታል፡፡ ይህም የማይፈልገውን ሰው የሚያስጠላበት የተለመደ ስልቱ ነው፡፡ ከአቡነ ጳውሎስ ዜና እረፍት አንስቶ እስከ ምርጫው ዋዜማ ድረስ አቡነ ማትያስን በምእመናን ለማስጠላትና ተቀባይነት ለማሳጣት ስማቸውን ከወ/ሮ እጅጋየሁና ከመንግስት ጋር በማያያዝ መግለጹ የማህበሩ ፍላጎት ምን እንደሆነ ግልጽ ይመስለኛል፡፡ አዲሱ የማህበሩ ስውር ድረገጽ የሆነውና የሌላ በመምሰል ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ መከፋፈል እንዳለ አስመስሎ ባወጣው ዘገባ የማህበራዊ ድረገጾችን ጎራ የተቀላቀለው ሀራ ዘተዋህዶ ሳይውል ሳያድር የማን መሆኑንና ለምን አላማ እንደተጀመረ እያስመሰከረ ነው፡፡
አሁን ካሉት አባቶች ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው ብፁዕ አቡነ ማትያስ እንደሆኑ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ይህም ከትምህርታቸው፣ ከእድሜያቸው አንጋፋነት፣ ካላቸው ልምድ፣ በዘርና በገንዘብ ጉዳይ እንዲሁም አሁን ባለው የቤተክህነቱ ፖለቲካ ምንም ንክኪ የሌላቸው አባት መሆናቸው በብዙዎች ተመራጭ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ ሐራ ዘተዋህዶም ቢሆን የመጀመሪያውን የመመረጥ እድል የሰጠው ለእርሳቸው ነው፡፡ ይህም በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ለእርሳቸው ስለሆነ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ድረገጹ ስለእርሳቸው ሊገለጽ የሚገባ ብዙ ነገር እያለ ከእርሳቸው ጋር ተያይዞ ሊነሳ የማይገባውን የማጥላላት ዘመቻ ከፈተባቸው፡፡ ይህን ያደረገውም ብፁዕነታቸው በአቋም ደረጃ አይታዘዙኝም ብሎ ስለሰጋ ነው እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም፡፡

አቡነ ሉቃስም ቢሆኑ በ1986 ዓ.ም. እስኪመነኩሱ ድረስ ለጵጵስና ቀርቶ ለክርስትና የሚጠቀስ ሕይወት የሌላቸው መሆኑን የአብነት ትምህርት ቤት፣ የአዋሳም ህዝብ ሆነ የሩሲያ ትምህርት ቤት ቆይታቸው ይመሰክራል። በማኅበረ ቅዱሳን ፖለቲካ የተጠመቁና በአዋሳ ያላቸውን ቤትም ለማኅበሩ መገልገያነት ያከራዩ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን የ20 ዓመት ወንድ ልጅ ያላቸው መሆኑን እህቶቻቸው ሳይቀር በድፍረት የሚናገሩት ሀቅ ነው (እንደ አስፈላጊነቱ የልጃቸውን ፎቶ ማውጣት ይቻላል፡፡)። የጥንቱ አባ ኃይለ ስላሴ የዛሬው አባ ሉቃስ ለማኅበረ ቅዱሳን ባላቸው ታማኝነት የተነሳ የማኅበሩ ሁለተኛ ተመራጭ  ናቸው። ሀራ ተዋህዶ እንዲያ ቀባብታ እና አሽሞንሙና ያወጣቻቸው ለዚሁ ነው።

አቡነ ማቴዎስ ምንም እንኳ የሀዲስ ኪዳን መምህር ቢሆኑም እና እንደነ አባ ሳሙኤል እና አባ ሉቃስ የሚታሙበት የስነ ምግባር ችግር ባይኖርባቸውም በመምህርነት ችሎታቸው በቤተክርስቲያኒቱ ቋንቋ አይነ ላሕም ከሚባሉት ወገን የሚደመሩ ናቸው። የሸመደዱትን ከመድገም ያለፈ ምስጢር ጠንቅቆ የማስተማር ችሎታ እንደሌላቸው ይታወቃል። በዚያ ላይ በዘረኝነታቸው እና በቂመኝነታቸው ተወዳዳሪ የላቸውም። በዚህ ባህሪያቸውም ፈጽሞ ለአስተዳደር ስራ እንደማይመቹ አብረዋቸው የሰሩ ሰዎች ይናገራሉ።

ጨዋ ከሚባሉ ጳጳሳት ወገን የሚደመሩት አቡነ ያሬድም ቢሆኑ እድሚያቸው 45 ዓመት በመሆኑ ለምርጫው ብቁ አይደሉም።

አቡነ ገብርኤል ያለባቸው ዘርፈ ብዙ ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ አሁን ያወሩትን በዚያው ፍጥነት ስለሚክዱት ማንም ተስፋ የሚጥልባቸው ሰው አይደሉም።
አባ ሳሙኤልን ሃራ ተዋህዶ በአስተዳደር ችሎታቸው ብታመሰግናቸውም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ኋላም ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ በአስተዳደር በደል ምክንያት አራት ኪሎ ምን ያህል ትጨናነቅ እንደነበር የሚያውቅ ያውቃል። ባለትዳር የሆኑት የእኚሁ ጳጳስ ሚስት ሚጡ የተባለች ወጣት በአንድ ወቅት ለቅርብ ጓደኛዋ ፓትርያርክ መሆናችን እንደሁ አይቀርም በማለት አባ ሳሙኤል ከበፊት ጀምሮ የነበራቸውን ፓትርያርክ የመሆን ፍላጎት እንዳላቸው ጠቆም ማድረግዋ የሚታወስ ነው።

የሌላ ለመምሰልና ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ መከፋፈል እንዳለ አስመስሎ ባወጣው ዘገባ ወደማህበራዊ ድረ ገጽ የገባው ሀራ ዘተዋህዶ ብሎግ ሳይውል ሳያድር የማን መሆኑን እያስመሰከረ ነው፡፡ የሌሎችን አባቶች የትምህርት ሁኔታ በዝርዝር ገልጦ የብጹዕ አቡነ ማትያስን ግን ለማንሳት አለመፈለጉ ትምህርታቸውን ብገልጠው የህዝቡ ፍላጎት እሳቸው መሆናቸው አይቀርም ከሚል ፍርሃት የተነሳ ይመስላል። በትምህርታቸው እና በቋንቋ ችሎታቸው አሁን ካሉት አባቶች ሁሉ የላቁ መሆናቸውን ሰነዶች የሚያስረዱላቸው ብጹዕ አቡነ ማትያስ ሃራ ዘተዋህዶ ሊገልጸው ያልፈለገው ታሪካቸው ይህን ይመስላል።


ብጹዕ አቡነ ማትያስ ማን ናቸው?
ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከሁለት ዓመት እድሜያቸው ጀምሮ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያደጉ አባት ሲሆን፣ ያደጉበትም ገዳም ጭክ ኪዳነ ምህረት ይባላል፡፡ ገዳሙ የ1400 ዓመት ታሪክ ያለው ሲሆን መምህር ድሜጥሮስንና መምህር ኤስድሮስን የመሳሰሉ ሊቃውንት የወጡበት ገዳም መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይም ዮሐንስ ወንጌልን በልዩ ሁኔታ የተረጎሙት መምህር ኤስድሮስ ከዚህ ገዳም የተገኙ ፍሬ በመሆናቸው የገዳሙ አባቶች የትምህርቱን ስርአት ጥብቅ በማድረግ በርካታ አይነ ንሥር መምህራን የወጡበት ገዳም ሆኗል፡፡ ብፁዕነታቸው በመጀመሪያ ቅኔና ቅዳሴን የተማሩ ሲሆን፣ በ14 ዓመታቸው በቅኔ መምህርነት በማስመስከራቸው ወደ አክሱም ጽዮን ገዳም ቅኔ መምህር ሆነው ሄደዋል፡፡ አክሱም ገዳም እንደደረሱም ቅኔን እያስተማሩም ጎን ለጎን ጸዋትወ ዜማን በስርአቱ የዳዊትን የኢሳይያስን እና የነቢያትን ትርጓሜ በታላቅ ሊቅነታቸው ከሚታወቁት ከየኔታ ጌዴዎን ተምረዋል፡፡ ብፁዕነታቸው ቅኔን እያስተማሩ የየኔታ ጌዴዎን የቅኔ እውቀት ቢመስጣቸው ቅኔንም እንደ ገና ያስተምሩኝ ብለው ቅኔን ደግመው ተማሩ፡፡ ሐዲስ ኪዳንንም ደቡብ ጎንደር መካነ ኢየሱስ ከተባለ ስፍራ ከነበሩት የኔታ ገብረ ጊዮርጊስ ተማሩ፡፡ ብፁዕነታቸው የሐዲስ ኪዳን፣ የፍትሐ ነገሥትና የሃይማኖተ አበው ሊቅ ከመሆን አልፈው የሶስቱ ጉባኤ መምህር ናቸው፡፡ በዘመናዊ ትምርህትም የማስትሬት ዲግሪ ባለቤት ናቸው፡፡ በውጪ ቋንቋም በኩል ቤተክርስቲያናቸውን የሚያኮሩ  ዕብራይስጥ፣ ግሪክ፣ አረብኛና እንግሊዝኛ የሚናገሩ ናቸው፡፡

የኔታ ተክለ ማርያም በኋላ ብፁዕ አቡነ ማትያስ አራት አይና ከነበሩት እና ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት መካከል ባላቸው እውቀት እና ታላቅነት የዶክትሬት ማዕረግ ተሰጥቶዋቸው ከነበሩት ከዶክተር አየለ ሀዲሳትን ከልሰው ተምረው የሊቃውንት ትርጓሜንም ጨምረው ተምረዋል።

ከዶክተር አየለ ጋር ተያይዞ ስለብጹዕ አቡነ ማትያስ ይነገር የነበረ አንድ ታሪክ አለ። እንደሚታወቀው ሁሉ ቤተክርስቲያናችን ወንበር ሲዘረጋ የሚጀመረው በጸሎት ነው። ታዲያ ዶክተር አየለ ወንበር ዘርግተው በጸሎት እንዲጀመር ያዝዛሉ፡፡ በዚህ ጊዜም መምህር አቢይ የሚባሉ ካህን ጸሎቱን ሲጀምሩ ዶክተር አየለ “ዝም በል አንተ ደፋር ጳጳሱ እያለ አንተ ምን ያንቀዠቅዥሃል አሉዋቸው። እና የኔታ ተክለ ማርያም ጸሎቱን እንዲያደርጉ  አዘዙ። ታዲያ አቡነ ማቲያስ ጳጳስ በሆኑ ጊዜ ይህ የዶክተር አየለ ንግግር ትንቢት መሆኑ ታውቆ ብዙዎችን አስደምሞ ነበር ይባላል።

የኔታ ተክለማርያም በንጉሱ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ መጥተው በወቅቱ ከነበሩት ሊቃነ ጳጳሳት ልዩ መቀራረብን ፈጥረው ነበር፡፡ ሁሉም በሊቅነታቸው እና በመንፈሳዊነታቸው ይወዱዋቸው ነበር። በወቅቱም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እያገለገሉ በትርፍ ጊዜያቸው ዘመናዊ ትምህርትን ይማሩ ነበር። በኋላም በሶስተኛው ፓትርያርክ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት በወቅቱ ይሾሙ የነበሩት ኢጲስ ቆጶሳት እንደዛሬው ዝም ብሎ ከዋልድባ እየተነዱ መጥተው ሳይሆን  የቅዱሳት  መጻሕፍትን ትርጓሜ ጠንቅቀው መተርጎም የሚችሉ እና በጉባኤ ማስተማር የሚችሉ በስነ ምግባራቸውም የተመሰከረላቸው ሰዎች ስለነበሩ የሚመረጡት፣ ከነዚያ ውስጥ በስነ ምግባራቸው በጎንድር እና በሌላው አካባቢ ህዝብ ጭምር ተመስክሮላቸው የተመረጡ ምስጉን አባት ናቸው። እኚህ አባት በ1971 ዓ.ም. በወርሃ ጥር ከብዙ ሊቃነ ጳጳሳት አንዱ ሆነው የጵጵስናን ማዕረግ ተቀብለዋል።

በሊቀ ጵጵስና ከኢየሩሳሌም እስከ አሜሪካ ያገለገሉ ታላቅ አባት ሲሆኑ ጉዞዋቸው አልጋ በአልጋ አልነበረም። ብዙ ግፍ የደረሰባቸው ቢሆንም በታላቅ ትዕግስትና አርቆ አስተዋይነት አንድም ቀን ከአገር ውስጥ ሲኖዶስ አልተለዩም። ታዲያ እኚህን ታላቅ አባት ከገዳም እና ከአራት ኪሎ ተጠርተው በእጅ መንሻ ከተሾሙ ጳጳሳት ጋር ማወዳደር አስተዋይ ህሊና ላለው ሰው ሁሉ የሚያሳዝን ነው። ሆን ብሎ ትምህርታቸውንም አሳንሶ ትምህርት የሌላቸውን እነ አባ ሳሙኤልን በሊቅነት ለመጥራት መሞከር አያውቁኝ ብለሽ በተልባ ታሸሽ የሚለውን ተረት ያስታውሰናል።
ብርሃንን ከጨለማ ጋር አዋቂን ከአላዋቂ ጋር ለግል ጥቅማችን ስንል እያምታታን ይችን ቤተክርስቲያን ወደ አልተገባ አቅጣጫ ባንነዳት የተሻለ ነው። ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ የተነሳሁት እገሌ ይመረጥ ለማለት አይደለም። እገሌ ይመረጥ የሚል ሀሳብ ያላቸው ሰዎች የሚሸርቡትን ሴራ እንዲተዉና የሚፈልጉትን ክበው የጠሉትን ደግሞ አንቋሸው አላማቸውን ለማሳካት መንቀዥቀዣቸውን እንዲያቆሙ ለመንገር ነው። የዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ ለቤተክርስቲያን ከማንም በላይ የመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት እንደሚጠቅማት ያምናል። ስለዚህም ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር የተሻለውን ተስፋ ያደርጋል። ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን አባት የሚያስቀምጥ እግዚአብሔር ነውና ካህናቱና ምዕመናን ሁሉ ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን አባት እግዚአብሔር እንዲያስቀምጥ በጸሎት እንትጋ፡፡


11 comments:

 1. God bless you, let tell the truth.......

  ReplyDelete
 2. አዛኝ ቅቤ አንጓች፡፡ ድንቄም ለቤተ ክርስቲያን አሳቢ! ለማያውቅህ ታጠን፡፡ የለየልህ መናፍቅ፡፡

  ReplyDelete
 3. May I say Congra For YeChelamaw Buden????????
  But I hope God will destroy your Building like Senaor Ginb.
  እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር፡፡
  ‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ›› ---› ልክ ነው???
  እግዚአብሔር እናንተ በምትመርጡዋቸው አባት አድርጎ የፍቅር፣ የቅንነት፣ ለቤተክርስቲያን እድገት የሚያስብ እና የአስተዋይነት ልቦናን እንዲሰጣችሁ ጸሎቴ ነው፡፡
  ኦ ንጉሠ ሰላም ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላመከ ኃበነ ከመ ኢንትመአእ በፀር አላ ንትፋቀር በበይናቲነ፡፡
  ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን!
  ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን!
  ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን!

  ReplyDelete
 4. አባ ሰላማ በጣም እናመሰግናለን
  የአባታችንን ብጹዕ አቡነ ማትያስን ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ዕጩ ተወዳዳሪ አባቶቻችንን የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎች ከምርጫው በፊት ብታቀርቡ መልካም ነው፡፡
  ማህበረ ቅዱሳን ማለት የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ነው፤ ከማ/ቅዱሳን (ደጀ ሰላም፤ ሐራ ዘተዋህዶ….ወዘተ) ከሐሜትና ከስድብ በስተቀር ምንም መልካም ነገር አይገኝም፡፡

  ReplyDelete
 5. ስለ አባ ማትያስ ማውራት ለምን አስፈለጋችሁ ሁሉንም በእኩል ማስተናገድ ከተፈለገ አንዱን እየሰደቡ ሌላውን እያወደሱ አይደለም፡፡ ይህ ድረ ገጽ የእጅጋየሁ እጅ አለበት፡፡ ማንም የሚሰማችሁ የለም፡፡ስለ አባ ማትያስ ማውራት ለምን አስፈለጋችሁ ሁሉንም በእኩል ማስተናገድ ከተፈለገ አንዱን እየሰደቡ ሌላውን እያወደሱ አይደለም፡፡ ይህ ድረ ገጽ የእጅጋየሁ እጅ አለበት፡፡ ማንም የሚሰማችሁ የለም፡፡

  ReplyDelete
 6. U are doing wrong calculation. It is known Abune Matias will be next Patrica. So you want to make collstion between MK and Abune Matias at the begining. That will not never work. Your are so foolish some time.

  ReplyDelete
 7. Zare yemitestef ej nege tisebebesablech zare yemitnager andebetim endhihu. Yefetarin menor yemayamin sile kiristena ena kirstiyanoch liyaseb mechalum asgerami new. Ere lehilinachu enkuan nuru ??? Bekelachu eskemeche yihone ? Yihech merzama milasachu yederekech elet kalhone yihechin betekirstiyan mewugatachihun latakomu new ? Ebakachu temekeru !!!!!

  ReplyDelete
 8. ማቆች መቼን ይሉኝታ የላችሁም፡፡ ሀራ ዘተዋህዶ አባ ማትያስን አሳንሶ ሲያቀርብ እቹ ጳጳሱን አቡነ ማቴዎስን ግን እንከን አልባ አድርጎ ነው ያቀረበው፡፡ ሌላው ቀርቶ ከ5ኛ ክፍል አቋርጠው አሜሪካ የሄዱትንና የፓርኪንግ ሰራተኛ የሆኑትን አባ ሳሙኤልን የሌላቸውን የትምህርት ማስረጃ አሰማምሮ ሲያቀርብ ስለአባ ማትያስ ግን ምንም አላለምምንው ታዲያ ያን ጊዜ አባ ማትያስን በተመለከተ ጥያቄ አላነሳችሁ? አባ ሰላማ ያስተናገደው ጽሑፍ ነገሮችን ሚዛናዊ ከማድረግ አንጻር ተገቢ ነው፡፡ ሁልጊዜ እውነትን ለምን ትቃወማላችሁ? ለእናንተ ያልተስማማው ሁሉ ለእናንተ ትክክል አይደለም፡፡ ከዚያ ሌሎችን ትተቻላሁ፡፡ ይህ ተገቢ አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 9. መልከ ትፉን በስም ይደገፉ ነውና በቅዱሳን ስም የሚነግደው አቡነ ሰላማ ብሎግ፡-
  1. ቁጥር አንድ የመናፍቃን በሎግ ነው ፡፡
  2. በውሸቱ ከጥንተ ጠላታችን ዲያቢሎስ ይበልጣል /መላእክንትን ፈጠርኩ አችሁ የለ የመጀመጀመርያው የሃሰት አባት ሲሆነ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የኪያቢሎስ ታናሽ ወንድም ነው፡፡
  3. ሰው ሁሉ በተፈጥሮው እውነት ለመናገር እውነተኛ ህሊና ስኖረው አቡነ ሰላማ ብሎግ የውሸት ህሊና አለው ምክንያቱም አላማው እውነትን ማጥፋት ስለሆነ፡፡
  4. ማንኛውም ስው ቢዋሽ እንኳን 100ፐርስነተ በጭራሽ አይዋሽም ይህ በሎግ ግን 100ፐርሰንት በላይ ይዋሻል ምክያቱም ጥንተ ጠላታችን ዲያቢሎስ ፈጣሪ ትሆናላችሁ በሎ ሲምከራቸው እንኳን ፈጣሪ መሆን ሰው መሆንም ቀርቶ ነበር ፡፡ በቸርነቱ ቢመልሰንም፡፡
  5. ሐረግ ዘፍ ላያ ካልቆመ በስተቀር ከመሪት ከፍ አይልም በዙድጋፎች ይፈልጋል ፈፅሞ ብቻውን አይቆምም ፡፡ ይህ ብሎግም መሰሎቸሁን የዲያቢሎስ ቂያቆናት እየጠራ የውሸት ዘመቻ ተያይዞ ይገኛል
  6. ውሽታም ወደቀ ካሉት ተሰበርን ጨምሮያወራ ይሆናል አቡነ ሰላማ ብሎግ ግን ከሜዳ ተነስቶ ይዋሻል ፡፡
  7. ውሸታም በገጠመው ነገር ሊዋሽ ይችላል ይህ ብሎግ ግን እወነትን ከስሯ ለማጥፋት በእቅድ ወቅታዊ ነገሮችን እየጠበቀ ይዋሻል፡፡
  ወገን ……..ስለ እውነት
  እውነትን ብንጠላት
  በማስመሰል ብንሸሻት
  ብንሯሯጥ ልናጠፋት
  ከንቱ ድካም ሞኝነት
  መሰረቷን ለዘነጉት
  ዋሾ ተፍቶ እሷ ህያዊት፡፡
  መሰረቷ ፅኑ ነው
  ድካማችሁ ከንቱ ነው፡፡

  ReplyDelete