Saturday, February 23, 2013

አባ ሳሙኤል ዕጩ አለመሆናቸውን ተከትሎ ሲኖዶሱን ሲበጠብጡ ዋሉ

አባ አብርሃም መንግስት ጣልቃ ገብቷል ሲሉ የከሰሱ ሲሆን፣
«አቡነ ማትያስ በተሀድሶ ብሎግ ላይ ተወድሰዋልና ሃይማኖታቸውን እጠረጥራለሁ ተሀድሶ ይሆናሉ» ብለዋል፡፡

ስለራሳቸው ብዙ ያወሩትና ያስወሩት፣ በእርሳቸው ላይ ግን ብዙ የተወራባቸው፣ ድፍረት እንጂ እውቀት የሌላቸው (ትምህርት ከ7ኛ ክፍል እንዳቆሙ ይነገርላቸዋል፤ yes እና ok ነው የሚያውቁት)፣ ዓለማዊነት እንጂ መንፈሳዊነት የማይታይባቸው (ሌላውን ሁሉ ትተን እኔን ምረጡኝ ብሎ ዘመቻ ማድረግ በየትኛውም መስፈርት ዓለማዊነት ነው) ትእቢት እንጂ ማስተዋል የሌላቸው አባ ሳሙኤል እንኳን ፓትርያርክ ሊሆኑ በእጩነትም ለመቅረብ መስፈርቱን ስላላሟሉ በአስመራጭ ኮሚቴው በኩል ለምርጫው በእጩነት ሳይቀርቡ መቅረታቸው ዛሬ በተጀመረው ስብሰባ ላይ ተመልክቷል፡፡ ከ5 መቶ ሺህ ብር በላይ ቤተ ክርስቲያን በሶማሌና በአፋር ክልል ለልማት እንድታውለው በድጋፍ የተገኘውን ገንዘብ ስልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም ወጪ አድርገው ለምርጫ ቅስቀሳ ቢያውሉትም፣ ከተራ ተላላኪዎቻቸውና ጉቦ አቀባባዮቻቸው እስከ ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎች ብዙዎችን ገዝተውበት አስመራጭ ኮሚቴውን በጠቋሚ ብዛት ቢያጨናንቁትም (ከ9000 ጠቋሚዎች 7200ው የአባ ሳሙኤል ደጋፊዎች ናቸው) «መጠቆም መታጨት አይደለም» የሚለውን መርህ ይዞ የእጩዎችን የሕይወት ታሪክ ሲያጣራ ከቆየ በኋላ የኮሚቴውን ሥራ ብዙ ልቦለድ ታሪኮችን እየጨመሩ ለሀራ ዘተዋህዶ በማቀበል ድረጹን ስተው ያሳቱት የቅርብ ጊዜው የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆኑት የጭድ ተራው የመንደር ቀኛዝማች ኃይሉ ቃለ ወልድ ለአባ ሳሙኤል አድረው ፈቃደኛ ባይሆኑም አባ ሳሙኤል ለእጩነት መቅረብ አይችሉም ብሏል፡፡ ከተጠቆሙት መካከል 5ቱን ብፁዕ አቡነ ማትያስ  ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እና ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕን ለይቶ ለዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ ያቀረበ ሲሆን በአባ ሳሙኤልና በአባ አብርሃም ተቃውሞና በብዙሃኑ ጳጳሳት ድጋፍ እጩዎቹ አልፈዋል፡፡

አባ ሳሙኤልን በተመለከተ እስካሁን ሲነገርባቸው የቆየው የሕይወት ታሪካቸውና በምርጫው ዙሪያ እያደረጉ ስላለው እንቅስቃሴ በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ የወጣው ዘገባ ከባድ ተጽዕኖ እንዳሳደረባቸው እየተነገረ ነው፡፡ አባ ሳሙኤል በሰንደቅ ጋዜጣ ዘገባ ብዙ ደስተኛ እንዳልሆኑ ከዚህ ቀደም ልምዳቸው በመነሳት ጋዜጣውን ለመክሰስ እንደተዘጋጁ እየተነገረ ነው፡፡ በልቡ አቡነ ማቴዎስ እንዲመረጡለት የሚፈልገውና አስፈላጊውን መሥዋእትነት እከፍላለሁ ያለው፣ አባ ሳሙኤል በሚፈጥሩት ግርግር ተጠቃሚ መሆን ከተቻለም ጥቅሙን ለማስጠበቅ እየሰራ የሚገኘው ማህበረ ቅዱሳን በሐራ ዘተዋህዶ ድረገጹ የእርሳቸው ደጋፊ መስሎ እየቀረበ ነው፡፡ በተለይም ጋዜጦች እስካሁን በአብዛኛው ማህበሩን ደግፈውና ሚዛናዊ ሳይሆኑ የተሳሳቱ ዘገባዎችን እያወጡ ሲጠቅሙት እንዳልነበር የየካቲት 13ቱ ሰንደቅ ጋዜጣ ግን እውነታውን ይዞ በመውጣቱና አባ ሳሙኤል በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የምርጫ ዘመቻ ለማድረግ የፈጸሟቸውን ሙስናዎች በመዘገቡ ደስተኛ አለመሆኑን የሰንደቅን ጋዜጣ በተለመደው የማስጠላት ስልቱ ከፈረደባቸው ወ/ሮ እጅጋየሁ ጋር ለማያያዝ መሞከሩ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

ማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ውስጡን የሸዋን መንግስት ለመመለስ ለሚያደርገው ትግል ጵጵስናው ለታማኜና ለሸዋው ተወላጅ፣ የቀድሞውን የሸዋ ተወላጅ የአቡነ ማቴዎስን ስም በአጋጣሚ ይሁን ሆን ተብሎ ባይታወቅም ብቻ ስሙን ለወረሱት ለአሁኑ አቡነ ማቴዎስ መሰጠት አለበት ባይ ነው፡፡ ይህም የማህበሩ ስውር አመራሮች የሚታገሉለት ዋና አላማ ነው፡፡ ማህበሩ ይህን ጉዳይ በጥንቃቄ ይዞና እንደአባ ሳሙኤል ባለ የግንባር ሥጋ ተከልሎ እየሰራ ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያን ከዚህ የዘረኛነት ልክፍት መቼ ይሆን የምትወጣው? ሰውን በሰውነቱ በእውቀቱ በሥራውና በመሳሰለው መስፈርት መመዘን ትተን በዘሩ የምንመዝነውስ እስከ መቼ ይሆን? ለእኛ ሳይስማማን ሲቀርስ ተሀድሶ ነው ወይም መንግስት ከጀርባው አለ ማለትስ ምን ይሉታል?

በ16/6/2005 ከሰዓት በፊት በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አባ ሳሙኤልና አባ አብርሃም የአቡነ ማትያስን መታጨት በጽኑ ሲቃወሙ ውለዋል፡፡ ውለታ ቢሱ አባ ሳሙኤል አባ ማትያስን ይቃወማሉ ብሎ የጠበቀ ማንም አልነበረም፡፡ ያኔ ከአቡነ ጳውሎስ ጋር ተጣልተው ያለስራ ለዓመት ያህል በተቀመጡ ጊዜ ኢየሩሳሌም ሄደው ያረፉት አቡነ ማትያስ ጋ ነበር፡፡ አቡነ ማትያስ ለአባ ሳሙኤል የችግር ቀን ወዳጃቸው ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ በፕትርክና ቀልድ የለም የሚል ጠንካራ አቋም ያላቸው አባ ሳሙኤል አኚህን የክፉ ቀን ወዳጃቸውን በዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ መታጨታቸውን ተቃወሙ፡፡

ሌላው ሰሚውን ያስገረመው ነገር አባ ሳሙኤል የምርጫውን ኮሚቴውን ሪፖርት በመቃወም «የህዝብ ድምጽ አልተከበረምና መከበር አለበት» ማለታቸው ነው፡፡ አክለውም አገር ጥለው እንደሚሄዱ የተናገሩ ሲሆን ምናልባትም ከ7ኛ ክፍል አቋርጠው ወደአሜሪካ ሄደው ሳለ ከመማር ይልቅ በቤንዚን መቅዳት ስራ ላይ ተሰማርተው በነበሩባቸው ዓመታት ከኤርትራውያን ጋር በነበራቸው ቅርርብ ወደኤርትራው ሲኖዶስ ይገቡ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ያላቸው ወገኖች አሉ፡፡ ምክንያቱም የእርቁን ሂደት በማጨናገፉ ረገድ ትልቁን ሚና የተጫወቱት እርሳቸው ስለሆኑ ከአሜሪካው ሲኖዶስ ጋር አብረው ሊሰሩ የሚችሉበት እድሉ የጠበበ ነው፡፡

የአባ ሳሙኤል አጫፋሪ የሆኑት የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም ደግሞ «መንግስት በይፋ እጁን አስገብቶብናልና አቡነ ማትያስ የሚሾሙ ከሆነ እኔ ራሴን ከሲኖዶስ አገላለሁ» ማለታቸው የተሰማ ሲሆን፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ አባ አብርሃምን በመቃወም «መንግስትንና ቤተክርስቲያንን ምን ታነካካለህ? ስራው እየተሰራ ያለው እኛው በወከልናቸው ሰዎች ስለሆነ የመንግስት ጣልቃ ገብነት አለ ልንል አንችልም» ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም ራሴን አገላለሁ ማለታቸው ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን፣ አቡነ ማትያስን አስተዳደር አይችሉም ሲሉ ተቃወሟቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህንን ያሉትም ከሀራ ዘተዋህዶ የጫናቸውን በማራገፍ ነው ተብሏል፡፡ ይሁን እንጂ ብፁዕ አቡነ ማትያስ «ለመሆኑ የት ያውቁኛል? አስተያየት መስጠት ይችላሉ ክብር መንካት ግን ተገቢ አይደለም» ሲሉ  ምላሽ ሰጥተዋቸዋል ተብሏል፡፡ የሁለቱ ጎረምሶች ጳጳሳትን ቱግ ቱግ ማለት የተገዘነቡት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ይህን ስድብ አልሰማም ብለው ስብሰባውን አቋርጠው መውጣታቸው ተመልክቷል፡፡ የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃምም ሆኑ አባ ሳሙኤል እንደተናገሩት ራሳቸውን ቢያገልሉ ሲኖዶሱ ወደቀደመው ክብሩ ሊመለስ እንደሚችል የሚናገሩ አሉ፡፡ ሲኖዶስን የጭቅጭቅ አውድማ በማድረግ ደፍረው ያስደፈሩትና ዛሬ የተዋረዱበት እነርሱው ናቸው፡፡ ራሳችንን እናገላለን የሚሉት ማህበረ ቅዱሳን በስውር ብሎጎቹ ላይ ጠቆም እንዳደረገው ለሁለት የተከፈለችውን ቤተክርስቲያን ራሱን በመገንጠል ከሶስት የመከፍል እቅድ ሳይኖረው አይቀርምና የማኅበሩ ጳጳሳት ለመሆን ሳያልሙ እንዳልቀረ ግምት ተወስዷል፡፡ ለማንኛውም መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው፡፡

የጉድ ሙዳዩና የቅባት እምነት ተከታዩ አባ አብርሃም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን እርስዎም ተሐድሶ ነዎት ለማሸማቀቅ የተጠቀሙበትን ያረጀ ማስፈራሪያ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ላይም በመድገም «አቡነ ማትያስ በተሀድሶ ብሎግ ላይ ተወድሰዋልና ሃይማኖታቸውን እጠረጥራለሁ ተሀድሶ ይሆናሉ» ብለዋል፡፡ ይህን ሲሉም በተዘዋዋሪ ሊታመን የሚገባውና በሲኖዶስ ላይ እጩነቱ ሊጸድቅ የሚገባው በሀራ ዘተዋህዶ ላይ የተመሰገነው ጳጳስ ነው ማለታቸው እንደ ሆነ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ አቡነ ማትያስ ለዚህ ሁሉ ምንም ምላሽ አለመስጠታቸውን ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን ዜግነታቸውን መመለሳቸውን የሚያሳይ ደብዳቤ (አባ አብርሃም እኔ ይህን ማስረጃ አላምንበትም ብለው መሳቂያ ቢሆኑም) ማቅረባቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሁለቱ ጳጳሳት ንግግር ብዙዎቹ አባቶች ያዘኑ ሲሆን «እኛ እንደ ቤተክርስቲያን አባቶች አንተ ከእኔ ትሻላለህ ብለን እድሉን ለሌላው መስጠት እንጂ እኔ ልሁን ብለን ጭቅጭቅ ውስጥ መግባት አይገባንም» ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ከአባ ሳሙኤልና አባ አብርሃም ተቃውሞ በቀር አብዛኛዎቹ የሲኖዶስ አባላት የቀረቡትን እጩዎች ለፓትርያርክነት እንዲወዳደሩ ተቀብለው አጽድቀዋል፡፡

ሁሉም በቡድንም በግልም ሆኖ የየራሱን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ እየተንቀሳቀሰ ባለበት በዚህ ወቅት አንዱ ቡድን ሌላውን ቡድን ለመወንጀል ቢሞክርም የሁሉም ስራ ግን የየራሱን ሰው ፓትርያርክ አድርጎ ማስቀመጥ ስለሆነ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁሉም ለራሱ እንጂ ለቤተክርስቲያን እንደማያስብ ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን፣ ለስብከተ ወንጌል የሚተጋውን፣ ብልሹ አሰራሮችን ሙስናን፣ የዘመድ አዝማድ ሥራን፣ የጉቦን ሰንሰለት የሚበጣጥሰውን አባት እንዲያስቀምጥ በሁሉም አቅጣጫ ተገቢው ስራ ቢሰራና ከምንም በላይ ወደእግዚአብሔርም አብዝቶ ቢጸለይ መልካም ነው እንላለን፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከየካቲት 15 – 26 ድረስ ከተፈቀደላቸው ጥቂት ሰራተኞች በስተቀር በርካታ የቤተክህነት ሰራተኞችና ማንኛውም ባለጉዳይ ወደቤተክህነት እንዳይገባ እገዳ መጣሉን ከቤተክህነት አካባቢ የደረሰን ዜና ያስረዳል፡፡ ይህ እርምጃ የተወሰደው በፓትርያርክ ምርጫ ዙሪያ የሚፈጠሩ ግርግሮችንና በአባቶችና በሚመለከታቸው አካላት ላይ አላስፈላጊ ጫና ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ቡድኖችንና ግለሰቦችን ለመከላከል እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እርምጃው ይህን የተመለከተውን ደብዳቤ ለዘበኞቹ አለቃ የሰጠውን አቶ ተስፋዬ ውብሸትን ጨምሮ ለአንዳንዶች አመቺ አጋጣሚን እንደሚፈጥርላቸው እየተነገረ ነው፡፡ በዚህ ምርጫ አባ ሳሙኤልን ፓትርያርክ ለማድረግ ላይ ታች እያለ ያለው ተስፋዬ የአባ ሳሙኤል ከእጩነት መውጣት እንዳበሳጨው ውስጥ አዋቂ ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡

 19 comments:

 1. ቤተክርስቲያን ከዚህ የዘረኛነት ልክፍት መቼ ይሆን የምትወጣው? ዕናንተ ከገጸ ምድር ተጠራርጋቹ ስትጠፉ ብቻ ነው ቤተክርስቲያንዋ ከዘረኝነትና ከሙሰኝነት የምትጸዳው ፣
  በዕናንተ በኩል ዕኮ ኣልታወቀብንም ማለታ ነውቹ ነው ሞኝህን ፈልግ ቶፋ ሁላ፣ የክርስትና ስራ ዕየሰራን ነው ማለታችሁ ነው?ወይስ ፖለቲካ ?
  በበኩሌ ግን ከሁለቱም የላችሁበትም ምን ዓይነት ስራ ዕንደምትሰሩ ለምን ዓላማስ ዕንደምትጽፉ የምታውቁት ኣይመስልኝም በበኩሌ ግን የማቃጠር ስራ ነው የያዛችሁት ለማንኛውም ህዝቡ ንቅቶባችዋል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. We love Aba selama website, antena mesayochih (mk) duk belachu erasachun fogiru. Yemigermegn eko ketelachuhachew lemin temetalachu?yasgededachu sew ale? Endewim endante aynetu new more Web view yemisetachew, thanks

   Delete
  2. We love Aba Selama

   Delete
  3. R u a christian? Have u seen what u wrote?

   Delete

 2. አስመራጭ ኮሚቴው ያቀረባቸው አራት ሊቃነ ጳጳሳት ራሳቸውን ከዕጩነት አገለሉ
  አስመራጭ ኮሚቴው ለምልአተ ጉባኤው በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ተስኖት ውሏል
  ኮሚቴው በአምስቱ ዕጩዎች ላይ የተስማማበትን የውሳኔ ቃለ ጉባኤ ማቅረብ አልቻለም
  አብዛኞቹ ብፁዓን አባቶች በየሀ/ስብከታቸው የደኅንነት ወከባ እንደተፈጸመ ሪፖርት አድርገዋል
  መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ከኾነ እጁን ከቤተ ክርስቲያን ላይ እንዲያነሣ በአጽንዖት ተጠይቋል
  ብፁዕ አቡነ ማትያስን የተመለከቱ መረጃዎችን ለማድበስበስ ተሞክሯል
  በኮሚቴው ዋና ጸሐፊ እና በሕዝብ ግንኙነቱ መካከል የከረረ ልዩነት ተፈጥሯል
  ‹‹የኮሚቴው አካሄድ ሕጉን ሥርዐቱን ካልጠበቀ የማስተካከል የማረም የመጨረሻ ሓላፊነቱ የምርጫው ባለቤት የኾነው ቅ/ሲኖዶሱ ነው፤ አስፈላጊውን ውሳኔ መስጠት ይችላል፤ እኛ ያልነው ይኾናል፤ ሌላ ነገር አንነጋገር›› /የኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ/
  ‹‹የሚመረጠውን እያወቅን እኛ መናጆ ነን እንዴ!!›› /አራቱ ዕጩ ፓትርያሪኮች/
  ‹‹የሚሾማቸው አካል በቀጥታ በደብዳቤ ይሹማቸው [አቡነ ማትያስን] እንጂ በዚህ ዐይነቱ አካሄድ ላይ ፊርማችንን አስቀምጠን አንመርጥም፡፡›› /ብዙኀኑ የምልአተ ጉባኤው አባላት/

  ReplyDelete
 3. "ሁሉም በቡድንም በግልም ሆኖ የየራሱን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ እየተንቀሳቀሰ ባለበት በዚህ ወቅት አንዱ ቡድን ሌላውን ቡድን ለመወንጀል ቢሞክርም የሁሉም ስራ ግን የየራሱን ሰው ፓትርያርክ አድርጎ ማስቀመጥ ስለሆነ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁሉም ለራሱ እንጂ ለቤተክርስቲያን እንደማያስብ ግልጽ ነው፡፡"

  - እንዲህ እንደተባለው የቡድን ሥራ ውጤት የሚያናጋትና የሚቆጣጠራት ከሆነ ፣ መንፈስ ቅዱስ ፣ ክርስቶስ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ይመራል ፤ ይቆጣጠራል ፤ የሚባለው የአውደ ምህረት ትምህርትና ቋንቋ ብቻ ነው ማለት ነው?

  - ፓትርያርክ መሆን ማለት በተለይም በዚህ ዘመን እጅግ የሚያስፈራ (በበሰበሰ እንቁላልና ቲማቲም የሚያስደበድብ) መንፈሳዊ ሥልጣን መሆኑ እየታወቀ እንዴት ነው አባቶች እኔ መሆን አለብኝ ብለዋል የሚባለው? ምድራዊ ፈተና ፣ መከራ ፣ ጊዜያዊ ጥቅምንና ምቾችን በማሰብ ወይስ ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን ዘለዓለማዊ በረከትና ቅድስና በማለም ለመመረጥ ክርክር ያነሱት?

  በተረፈ በሚከተለው አድራሻ አቡነ ሳሙኤል ሰጡት የተባለው የቃለ መጠይቅ መልስ እውነት ቢሆን ተቃውሞአቸው አግባብነት የለውም የሚለኝ ሰው ይኖር ይሆን?
  http://dejebirhan.blogspot.com/2013/02/blog-post_3289.html

  Note: እኔ ማንም ተመረጠ ማንም በግል ህይወቴና እምነቴ ላይ ለውጥ አያመጣልኝም ፤ እንደ እኔ ምልከታ ቢሆን ፣ የሚሻለው የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነትንና ሰላምን ፣ የወንድሞች መግባባትን የሚፈጥር ፣ ቃለ ወንጌል ከአገራችንም አልፋ እንድትስፋፋ የሚተጋላት አባት ቢሰየምልን ነው ፡፡ ጥያቄ ያነሳሁት የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊ ስለሆንኩ ሳይሆን ነገርን ከምንጩ ወይም ከባለጉዳዩና ከባለቤቱ መስማት የተሻለ ሚዛናዊ ፍርድ ያሰጣል በሚል ምክንያት ብቻ ነው ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ‘ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ’ ነው፣ የአቡነ አብርሃም እዛም እዛም መሯሯጥ እናም የታወቁ የማቅ ተላላኪ መሆናቸው አሜሪካን ሳሉ ቤተክርስትያንን የማፍፈስ ተግባራቸው የስረዳል። ኦርቶዶክስን ለማጥፋት የሚሠሩ እና እርቅን ፈጽሞ የማይወዱ መሆናቸው የሥራ ታሪካቸው አረጋግጦባቸዋል። ስለዚህም የማቅ የጋራ ተጠቀሚው አቡነ አብርሃም ፊት ስለ እርቅ፣ ስለ ሰላም እና ስለ ፍቅር የሚያነሳ መለዓክ፣ ጳጳስ፣ መነኩሴ፣ ቄስ፣ ምዕምን፣ ወታደር ወይም ወንድ እንኳን አይገኝም። እስቲ ቤተክርስቲያንን ማመስ፤ ቆንጨራ ይዘው ምእምናኑን መቆራረጥና ማስለቀስ ትተው ምን አለ በፀሎት ቢተጉ፤ መልካም አስተዋጽኦ ቢያደርጉ፤ ከማቅስ የሚገኘው ስምና ጥቅማ ጥቅም ይቅርብኝ ብለው ወደ ቤተክርስቲያን ቢመለሱ!! እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ከፈተና ያወጣልናል። አሜን! እናምናለን እንታመናለን። ወስብኃት ለእግዚአብሔር!!!

   Delete
 4. Who is the writer? His mouth is full of insult (side bcha)

  ReplyDelete
 5. ለወራት ተከታተልኩዋቸሁ ዝባዝንኬ ብቻ ነው የምታውሩ ደሞ አባ ሰላማ ////// አባ ኢቲቪ ናችሁሁሁሁሁሁሁሁ/

  ReplyDelete
 6. አየ ጉድ እናቴ ጣጣሽ በዛ!!!

  ReplyDelete
 7. እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡፡ እውነቱን እንደዚህ እየተከታተላችሁ ዘግቡልን!!

  ReplyDelete
 8. this is very bad always you talk nonsense about the people . You are not practicing Christianity. Pls stop .

  ReplyDelete
 9. ለነ አባ እንቶኔ

  እመሰ አማን ጽድቀ ትነቡ...
  ይድረስ ለነ አባ እንቶኔ፦

  “ሰላም ለክሙ” እንዳልላችኍ፤ እንደ እኔ ያለ አንድ ምስኪን እንደ እናንተ ላሉ ታላላቆች ከታች ወደላይ ሰላምታ ማቅረብ የማይገባው መስሎ ስለሚታያችኍ፤ ላስቀይማችኍ አልሻምና ይቅርብኝ። “ሰላምክሙ ይብጽሐኒ” ብየ እንዳልማጠናችኍም፤ ስንኳን ለሌላ የሚተርፍ ለራሳችኍ የሚበቃ ሰላም እንደሌላችኍ እያየኍ የሌላችኍን ነገር በመለመን እንዳሳቅቃችኍ ኅሊናየ አይፈቅድልኝም። ስለዚህ የሰላምታን ነገር በዚሁ እንለፈው።

  ሰላምታውን በዚሁ ካለፍነው ዘንድ ነገሬን በቀጥታ ልጀምር። ከቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ባገኘኹት ላይ ተመርጉዤ። በሊቃውንት ቋንቋ እንድገልጠው ከፈቀዳችኹልኝ፦ ጳጳሳት አይደላችኍ? ከብሉይ ታሪክ ምሳሌ አምጥቼ ግሥ ልገሥሥላችኍ ነው።

  ርግጥ ነው ብዙዎቻችኍ ትርጓሜ መጻሕፍትን በወንበር ተምራችኋል ብየ አላስብም። እውነት ለመናገር ረ ከመካከላችኍ አንዳንዶቹ ተነሹን ከወዳቂ፥ እሚጠብቀውን ከሚላላው፥ በፍቅደት የሚነበበውን በውኅጠት ከሚነበበው በሚገባ ለይታችኍ ማወቃችኍን ስንኳ እጠራጠራለኍ። አዛኜን። ይኹን እንጂ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ እንዲሁም የዐጤ ኀይለ ሥላሴ ስም አጠራራቸው የተመሰገነ ይኹንና አቡኑ አእምሮ፥ ንጉሡ ገንዘብ ኾነው በረድኤተ እግዚአብሔር ያሳተሙትን የዳዊት አንድምታ ከመጽሐፍ መደርደሪያችኍ ፈላልጉና (ድንገት ለነ አቦይ መልእክት ስትፋጠኑ ጊዜ አላደርስ ብሏችኍ እስከዛሬ ያልገዛችኹት ከኾነም፤ ስንኳን አንድ መጽሐፍ አገር ምድሩን የሚገዛ ገንዘብ በየባንክ ቤቱ ስለሞላችኍ ዛሬውኑ ልካችኍ አስገዙና) የምገሥሥላችኍ ግሥ ተስማሚ መኾን አለመኾኑን አረጋግጡ።

  የምተኩረው በዳዊት መዝሙር ላይ ነው። በ57ኛው። ትርጓሜው የመቃብያንን ታሪክ ያስተርካል። ከታሪኩ አኹን የያዝነውን መዝሙር ለመረዳት የሚያሻው ክፍል፦ ስምዖን፥ እልፍሞስ፥ መባልስ የተባሉ ሦስት ንኡሳን ካህናት ለሹመት ሲሉ እስራኤልን የአሕዛብ ንጉሥ አንጥያኮስ እጅ እንዲያደርጋት መምከራቸውን፤ እሱ ስንኳ “አኹን የተናገራችኹትን ነገር ሳላስበው ውየ ዐድሬ አላውቅም። ነገር ግን እስራኤል ሰዎቹ ጽኑዓን ናቸው፤ አምባቸውም ጽኑ ነው ሲሉ እሰማለኍ። ፈጣሪኣቸውም ይረዳቸዋልና መቅረቴ ስለዚህ ነው እንጂ።” ቢላቸው፤ “እኛ ባወቅነ እናስገባኻለን። አንተም አመንኍ ብለኽ ዐዋጅ ነግረኽ ምስዋዕተ እሪያውን በዃላ በዃላ እያስጎተትኽ ላሙን በጉን በፊት በፊት እያስነዳኽ ና” ብለው መክረውት ኺደው የከተማዋን ቅጥር “ክፈቱልን” ያሏቸውን ይመለከታል። በዚህም ምክንያት "ፈጣሪየ የሃይማኖት አብነት ቢያደርገኝ የክህደት፥ የጥብዓት አብነት ቢያደርገኝ የፍርሃት፥ የበጎ አብነት ቢያደርገኝ የክፋት አብነት እኾናለኹን? አይኾንም" ያለው እውነተኛ ካህን አልዓዛር ሰባት ልጆቹ በሰይፍ ሲመቱ ሚስቱም በጡትና በጡቷ መኻል በኩላብ ተሰቅላ በሰይፍ ተቀልታለች። እሱም ይኽን ኹሉ እያየ ስንኳ ከጽናቱ የማይመለስ በመኾኑ በሰም የተጠማ የጋለ ብረት ምጣድ በራሱ ላይ ተደፍቶበት ተንጠቅጥቆ ሙቷል። በዚያኑ ጊዜ ከእስራኤል አራት ዕልፍ ዐብረው ዐልቀዋል፤ አራት ዕልፍ ተማርከዋል፤ አራቱን ዕልፍ ይሁዳ መቅብዩ እየተዋጋ ይዟቸው ወጥቷል። ስለዚህ በዚያን ጊዜ በሃይማኖታቸው የጸኑት ባባታቸው በመቃቢስ መቃብያን ተብለዋል። ዕጉሣን በስደት ጽኑዓን በምግባር ወበሃይማኖት ማለት ነው።

  መዝሙር 57ም በርእሱ “በእንተ መቃብያን” ይላል። መንፈስ ቅዱስ፦ ዳዊት በመቃብያን ተገብቶ እንዲናገር ያደረገው፤ ስለመቃብያን ያናገረው የትንቢት ቃል ስለኾነ። ስለዚህም መተርጉማኑ በትንቢት መልክ የተነገርውን መዝሙር ዃላ በመቃብያን ከተፈጸመው ታሪክ ጋራ አስማምተው እንዲህ ይተረጉሙልናል፦

  እመሰ አማን ጽድቀ ትነቡ፤

  ሦስቱ ካህናት (ስምዖን፥ አልፍሞስ፥ መባልስ) ከጽርእ ወጥተው “ክፈቱልን” አሉ። “እስካኹን ወዴት ኼዳችኍ ኖራችዃል” አሏቸው። “እናንተ ሥጋዊ ሹመትን ብትከለክሉን እኛ በደለኛ ለእግዚአብሔር ይካስ ብለን ጽርእ ወርደን አንጥያኮስን ያኽል ንጉሥ በሃይማኖት ወልደን በምግባር አሳድገን መጣን” አሏቸው። ነገራችኍ እውነት አይኾንም (አይመስልም) እንጂ፤ እውነትስ ተናግራችኍ እንደኾነ፤ ማለት፦ እንዲህስ አድርጋችኍ እንደኾነ፤

  ወርትዐ ትኴንኑ ደቂቀ እጓለመሕያው።
  የሰውን ልጆች በውነት በሚገባ ትገዛላችኍ…

  እስመ በልብክሙ ኀጢአተ ትገብሩ በዲበ ምድር።
  ነገር ግን በልባችኍ ዐስባችኍ በዚህ ዓለም ዕዳ የሚኾንባችኹን ሥራ ትሠራላችኹና በዚህ ምክንያት ይቀርባችዃል እንጂ።

  ወጽልሑተ ይጸፍራ እደዊክሙ።
  “የተፈተለ ከኹለት የተታታ ከሦስት” እንዲሉ፤ ከተፈተለ የተታታ እንዲጸና፤ እደ ልቡናችኍ ክዳትን ተንኮልን አጽንቷልና፤ በዚህ ምክንያት ይቀርባችዃል እንጂ፤ እንዲህስ ካደረጋችኍ የሰውን ልጆች በውነት በሚገባ ትገዛላችኍ። የሰው ልጆች እናንተም በውነት በሚገባ ለእግዚአብሔር ትገዛላችኍ።

  ተነክሩ ኀጥኣን እምማሕፀን
  ሦስቱ ካህናት ከሕግ ወጡ

  እምከርሥ ስሕቱ ወነበቡ ዐመፃ።
  ማሕፀንና ከርሥ አንድ ወገን፦ ከሕግ ወጡ። በልሳነ ሥጋ ሐሰት ተናገሩ።… እምነቱ ሳይኖር “ጽርእ ወርደን አንጥያኮስን ያኽል ንጉሥ በሃይማኖት ወልደን በምግባር አሳድገን መጣን” ማለታቸውን መናገር ነው።...

  ወመዐቶሙኒ ከመ ሕምዘ አርዌ ምድር።…
  በሰው የሚያመጡት መከራ እንደ እባብ መርዝ ነው።... አንድም… በራሳቸው የሚያመጡት መከራ እንደ እባብ መርዝ ነው።source… geez online

  ReplyDelete
 10. ለነ አባ እንቶኔ

  እመሰ አማን ጽድቀ ትነቡ...
  ይድረስ ለነ አባ እንቶኔ፦

  “ሰላም ለክሙ” እንዳልላችኍ፤ እንደ እኔ ያለ አንድ ምስኪን እንደ እናንተ ላሉ ታላላቆች ከታች ወደላይ ሰላምታ ማቅረብ የማይገባው መስሎ ስለሚታያችኍ፤ ላስቀይማችኍ አልሻምና ይቅርብኝ። “ሰላምክሙ ይብጽሐኒ” ብየ እንዳልማጠናችኍም፤ ስንኳን ለሌላ የሚተርፍ ለራሳችኍ የሚበቃ ሰላም እንደሌላችኍ እያየኍ የሌላችኍን ነገር በመለመን እንዳሳቅቃችኍ ኅሊናየ አይፈቅድልኝም። ስለዚህ የሰላምታን ነገር በዚሁ እንለፈው።

  ሰላምታውን በዚሁ ካለፍነው ዘንድ ነገሬን በቀጥታ ልጀምር። ከቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ባገኘኹት ላይ ተመርጉዤ። በሊቃውንት ቋንቋ እንድገልጠው ከፈቀዳችኹልኝ፦ ጳጳሳት አይደላችኍ? ከብሉይ ታሪክ ምሳሌ አምጥቼ ግሥ ልገሥሥላችኍ ነው።

  ርግጥ ነው ብዙዎቻችኍ ትርጓሜ መጻሕፍትን በወንበር ተምራችኋል ብየ አላስብም። እውነት ለመናገር ረ ከመካከላችኍ አንዳንዶቹ ተነሹን ከወዳቂ፥ እሚጠብቀውን ከሚላላው፥ በፍቅደት የሚነበበውን በውኅጠት ከሚነበበው በሚገባ ለይታችኍ ማወቃችኍን ስንኳ እጠራጠራለኍ። አዛኜን። ይኹን እንጂ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ እንዲሁም የዐጤ ኀይለ ሥላሴ ስም አጠራራቸው የተመሰገነ ይኹንና አቡኑ አእምሮ፥ ንጉሡ ገንዘብ ኾነው በረድኤተ እግዚአብሔር ያሳተሙትን የዳዊት አንድምታ ከመጽሐፍ መደርደሪያችኍ ፈላልጉና (ድንገት ለነ አቦይ መልእክት ስትፋጠኑ ጊዜ አላደርስ ብሏችኍ እስከዛሬ ያልገዛችኹት ከኾነም፤ ስንኳን አንድ መጽሐፍ አገር ምድሩን የሚገዛ ገንዘብ በየባንክ ቤቱ ስለሞላችኍ ዛሬውኑ ልካችኍ አስገዙና) የምገሥሥላችኍ ግሥ ተስማሚ መኾን አለመኾኑን አረጋግጡ።

  የምተኩረው በዳዊት መዝሙር ላይ ነው። በ57ኛው። ትርጓሜው የመቃብያንን ታሪክ ያስተርካል። ከታሪኩ አኹን የያዝነውን መዝሙር ለመረዳት የሚያሻው ክፍል፦ ስምዖን፥ እልፍሞስ፥ መባልስ የተባሉ ሦስት ንኡሳን ካህናት ለሹመት ሲሉ እስራኤልን የአሕዛብ ንጉሥ አንጥያኮስ እጅ እንዲያደርጋት መምከራቸውን፤ እሱ ስንኳ “አኹን የተናገራችኹትን ነገር ሳላስበው ውየ ዐድሬ አላውቅም። ነገር ግን እስራኤል ሰዎቹ ጽኑዓን ናቸው፤ አምባቸውም ጽኑ ነው ሲሉ እሰማለኍ። ፈጣሪኣቸውም ይረዳቸዋልና መቅረቴ ስለዚህ ነው እንጂ።” ቢላቸው፤ “እኛ ባወቅነ እናስገባኻለን። አንተም አመንኍ ብለኽ ዐዋጅ ነግረኽ ምስዋዕተ እሪያውን በዃላ በዃላ እያስጎተትኽ ላሙን በጉን በፊት በፊት እያስነዳኽ ና” ብለው መክረውት ኺደው የከተማዋን ቅጥር “ክፈቱልን” ያሏቸውን ይመለከታል። በዚህም ምክንያት "ፈጣሪየ የሃይማኖት አብነት ቢያደርገኝ የክህደት፥ የጥብዓት አብነት ቢያደርገኝ የፍርሃት፥ የበጎ አብነት ቢያደርገኝ የክፋት አብነት እኾናለኹን? አይኾንም" ያለው እውነተኛ ካህን አልዓዛር ሰባት ልጆቹ በሰይፍ ሲመቱ ሚስቱም በጡትና በጡቷ መኻል በኩላብ ተሰቅላ በሰይፍ ተቀልታለች። እሱም ይኽን ኹሉ እያየ ስንኳ ከጽናቱ የማይመለስ በመኾኑ በሰም የተጠማ የጋለ ብረት ምጣድ በራሱ ላይ ተደፍቶበት ተንጠቅጥቆ ሙቷል። በዚያኑ ጊዜ ከእስራኤል አራት ዕልፍ ዐብረው ዐልቀዋል፤ አራት ዕልፍ ተማርከዋል፤ አራቱን ዕልፍ ይሁዳ መቅብዩ እየተዋጋ ይዟቸው ወጥቷል። ስለዚህ በዚያን ጊዜ በሃይማኖታቸው የጸኑት ባባታቸው በመቃቢስ መቃብያን ተብለዋል። ዕጉሣን በስደት ጽኑዓን በምግባር ወበሃይማኖት ማለት ነው።

  መዝሙር 57ም በርእሱ “በእንተ መቃብያን” ይላል። መንፈስ ቅዱስ፦ ዳዊት በመቃብያን ተገብቶ እንዲናገር ያደረገው፤ ስለመቃብያን ያናገረው የትንቢት ቃል ስለኾነ። ስለዚህም መተርጉማኑ በትንቢት መልክ የተነገርውን መዝሙር ዃላ በመቃብያን ከተፈጸመው ታሪክ ጋራ አስማምተው እንዲህ ይተረጉሙልናል፦

  እመሰ አማን ጽድቀ ትነቡ፤

  ሦስቱ ካህናት (ስምዖን፥ አልፍሞስ፥ መባልስ) ከጽርእ ወጥተው “ክፈቱልን” አሉ። “እስካኹን ወዴት ኼዳችኍ ኖራችዃል” አሏቸው። “እናንተ ሥጋዊ ሹመትን ብትከለክሉን እኛ በደለኛ ለእግዚአብሔር ይካስ ብለን ጽርእ ወርደን አንጥያኮስን ያኽል ንጉሥ በሃይማኖት ወልደን በምግባር አሳድገን መጣን” አሏቸው። ነገራችኍ እውነት አይኾንም (አይመስልም) እንጂ፤ እውነትስ ተናግራችኍ እንደኾነ፤ ማለት፦ እንዲህስ አድርጋችኍ እንደኾነ፤

  ወርትዐ ትኴንኑ ደቂቀ እጓለመሕያው።
  የሰውን ልጆች በውነት በሚገባ ትገዛላችኍ…

  እስመ በልብክሙ ኀጢአተ ትገብሩ በዲበ ምድር።
  ነገር ግን በልባችኍ ዐስባችኍ በዚህ ዓለም ዕዳ የሚኾንባችኹን ሥራ ትሠራላችኹና በዚህ ምክንያት ይቀርባችዃል እንጂ።

  ወጽልሑተ ይጸፍራ እደዊክሙ።
  “የተፈተለ ከኹለት የተታታ ከሦስት” እንዲሉ፤ ከተፈተለ የተታታ እንዲጸና፤ እደ ልቡናችኍ ክዳትን ተንኮልን አጽንቷልና፤ በዚህ ምክንያት ይቀርባችዃል እንጂ፤ እንዲህስ ካደረጋችኍ የሰውን ልጆች በውነት በሚገባ ትገዛላችኍ። የሰው ልጆች እናንተም በውነት በሚገባ ለእግዚአብሔር ትገዛላችኍ።

  ተነክሩ ኀጥኣን እምማሕፀን
  ሦስቱ ካህናት ከሕግ ወጡ

  እምከርሥ ስሕቱ ወነበቡ ዐመፃ።
  ማሕፀንና ከርሥ አንድ ወገን፦ ከሕግ ወጡ። በልሳነ ሥጋ ሐሰት ተናገሩ።… እምነቱ ሳይኖር “ጽርእ ወርደን አንጥያኮስን ያኽል ንጉሥ በሃይማኖት ወልደን በምግባር አሳድገን መጣን” ማለታቸውን መናገር ነው።...

  ወመዐቶሙኒ ከመ ሕምዘ አርዌ ምድር።…
  በሰው የሚያመጡት መከራ እንደ እባብ መርዝ ነው።... አንድም… በራሳቸው የሚያመጡት መከራ እንደ እባብ መርዝ ነው።…

  ዘእንበለ ይትዐወቅ ሶክክሙ ሕለተ ኮነ።
  ይህ ቍጥቋጦ ምክራችኍ ሳይታወቅ ቀርካሃ ቀርካሃ ያኽል ኾኖ ተገኝ።…

  ከመ ሕያዋን በመዐቱ ይውኅጠክሙ
  …አለን አለን ስትሉ፤ በመዐቱ ያጠፋችዃል። አንድም… እንደ ዳታንና እንደ አቤሮን ነፍሳችኍ ከሥጋችኍ ሳትለይ ወደመቃብር ያወርዷችዃል

  ውጹኣን እምሕግ (ከሕግ የወጣችኍ) እነ አባ እንቶኔ ሆይ፦ ይህ እንዲህ ነው፤ የእናንተም ሕይወት በዚህ ግሥ ቢነገር መሥመር በመሥመር ቃል በቃል የሚስማማ ብዙ ዐተታ ተጎልጕሉ እንደሚወጣ ኾዳችኍ ያውቀዋል። ለጊዜው ዝርዝሩን እናቆየውና፦

  ይችን ቤተ ክርስቲያን ለሹመት ስትሉ መንግሥት ነን ብለው ለተቀመጡ ዐላውያን ጽሚተ/በጽሚት (በድብቅ በሹልክታ፥ በጥመት በቸልታ) ልታስረክቡ ተስማምታችኍ ስታበቁ ሕግ አክባሪ ሃይማኖተኛ ለመምሰል ደንብ ቅብርጥሶ እያላችኍ የማደናገሪያ ሽርጉድ ብታበዙ ዋጋ ቢስ መኾኑን ሌላ ማንም ሳይነግራችኍ ራሳችኍ አታውቁትምን? ይልቁንም ዓይናችኍ እያየ በምእመናን ላይ መከራን እንደእባብ መርዝ ማምጣታችኍ አይደለምን? በራሳችኍም ላይ እንጂ። የምእመናን መከራስ እንደመቃብያን ኹሉ ዋጋ ያለበት ነው። የእናንተ ግን…


  እናሳ? ከመካከላችኍ "ዮም አመ ሰምአ ቃሎ" (እስከ የካቲት ማርያም፤ ዛሬ የምትባል ዕድሜ ሳለችው) ከዚች ጠማማ መንገድ የሚመለስ የሃይማኖት ዐርበኛ ይኖር ይኾን? ልብ በሉ ጊዜው አጭር ነው። እናንተው አሳጠራችኍታ። ያለዚያ ግን… ሶበ ይውኅጠክሙ በመዐቱ (አለን አለን ስትሉ ያጠፋችኍ 'ለታ) ይሚቀርላችኍ፦ ሐቅየ ስነን ብቻ ይኾናል!!! geez online

  ReplyDelete
 11. 1) ቤተ ክሲያኗ ራሷን እየገደለች ነው።
  2) ማኅበረ ቅዱሳን በቅቶታል፤ ክዷል።

  ስለመጀመሪያው፦ እየኾነ ባለው፤ በትክክል ለመናገር፦ እንዲያው ዝም ብሎ በተገብሮ ወይም በደንቦብ (passively or neutrally) እየኾነ ሳይኾን እኛ በገቢር በኀቢር (actively, proactively) እየአኾንነው! ባለው ነገር፤ “መንግሥት እንዲህ አድርጎ፥ እገሌ እንዲህ ብሎ ነው እንጂ…” በማለት ከሓላፊነት የመሸሽ ዝንባሌ በተደጋጋሚ ታዝቤኣለኍ። ይኸውም ጥንት ለአዳምና ለሔዋን ያልበጀ (አዳም በሔዋን፥ ሔዋንም በእባብ ቢያሳብቡ ምክንያታቸው ዋጋ ቢስ ኾኖ “ወኮኑ ቀታልያነ ርእሶሙ” = "ራሳቸውን ገዳዮች ኾኑ" ያሰኛቸው) መኾኑን ሳስታውስ፤ አኹንም ቤተ ክሲያኗ በዋናነት እንመራሻለን በሚሏት የሲኖዶስ አባላት አማካይነት ራሷን ለምእመናን አሙታ ለዐላውያን ነገሥታት ለማኖር እየወሰነች በገዥ በተቃዋሚ ፓርቲ፥ በአቦይ እገሌ በአቶ እገሌ ማሳበብ የማይጠቅም መኾኑን ለመግለጥና ከተቻለ ይኽንን የዕብድ ውሳኔ ለማስቀልበስ በማሰብ ቢመርርም ሐቁን ግልጥ ፍጥጥ አድርጌ ተናግሬኣለኍ።

  ስለኹለተኛው፦ ለሥልጣኑ መደላደል (legitimacy) ከጉልበት በቀር፥ ያእምሮም የሕግም የሕዝብም የምንም መሠረት ማጣቱን የተረዳው የዐላውያን መንግሥት ብዙ አባላት ስላሉት ብቻ ሳይኾን፤ ቀና ቀናዎቹ የተዋሕዶ ልጆች የሚወዱትና የሚያከብሩት እንደኾነ በመገንዝብ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ትክሻ ለመታከክ በሚገባ ዐስቦና አስልቶ በዋልድባ ጉዳይ ላይ እንዲመራመር ሲፈቅድለት የምርምሩን ውጤት ሊቀበል ሳይኾን ስሙን ሊጠቀም መኾኑ ስለገባኝ፤ “ይኸ ማኅበር… በዕውቀትም ይኹን አለውቀት ነገ ተነገበስቲያ የጥፋት ኀይሎች መሣሪያ ኾኖ ‘ልማት ቅብርጥሴ’ በማለት ልባችንን ያደማው ይኾን?” ብየ ስጋቴን ገልጬ ነበር። ምኞቴም ጸሎቴም ግን “ስጋቴ ከንቱ ኾኖ እንደጉም በኖ እንዲጠፋ” ነበር። ይኹን እንጂ ሰሞኑን ማኅበሩ እያሳየን ባለው ተግባር ምኞቴ እንጂ ስጋቴ ጉም ኾኖ የሚጠፋ አይመስልም። ማኅበሩ ካንዴም ኹለት ሦስቴ ቃሉን በላኣ! ቃሉን በልቷልና፤ ይኽንኑ እየመረረኝም ቢኾን “ካደ” ብየ በተገቢው ኀይለ ቃል ካልገለጥኹት አባላቱን ባግባቡ እስደንግጦ ለራሳቸውም ለ"ታላላቅ ወንድሞቻቸው"ም ጥያቄ እንዲያነሡ የማያስችል ከመኾኑ በተጨማሪ እኔንም በበኩሌ “በከናፍረ ጉኅሉት ልበ ወበልብ” ከሚሸነግሉት የሚደምረኝ ኾኖ ተሰማኝ። “ስለዚህ በቅቶታል፤ ክዷል” ብያለኍ። ማኅበሩ እንዳልበቃውና እንዳልካደ በተግባር ያሳይና እኔን ውሸታም ያድርገኝ። ያን ጊዜ ለዋሸኹበት ንስሐ እገባለኍ።geez online

  ReplyDelete
 12. አባ ሰላማዎች የአሰቡን ወታደር አባ አብርሃምን ከሰው ቆጥራችሁ ይህን ኣሉ ማለታችሁ ያሳዝናል ሲጀመር እምነት የሌለው አብርሃም ተብዬው ስለ ቅዱሱ አባት አባ ማትያስ ለመናገር ብቃት የለውም ሌሎች ጳጳሳትም ብትሆኑ መናጆ መሆናችሁን ማወቃችሁም ትልቅ ነገር ነው በደፈናው ንጽህና የለንም ብትሉ የበለጠ እውነታ አለው ለሁሉም የነገው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ እንደ መሰግሉ አባ አብርሃም እና ሰዶማዊው አባ ሳሙዔል በምንም ነገር ተጠያቂ ያልሆኑ ታላቅ አባት መሆናቸውን የኢትዮጵያ ህዝብም ያውቃል ነጋሪም አያስፈልገውም አብርሃምና ሳሙዔልም ህይወታችሁ ከአባ ማትያስ ጋር ትልቅ ልዩነት ስላለው ከወዲሁ ቦታውን ከሳቸው ጋር መስራት ለሚችሉ ለቃችሁ ወደገዳማችሁ ሂዱ እንዳልል ገዳም አታውቁም ንስሃ ግቡ ብላችሁም የማይታሰብ ነው ከመርካቶ ራጉዔልና ከውጭ ተራድዖ የተመዘበረውን ገንዘብ ከነወለተ ማርያም ጋር ማገባደዱ ነው የሚጠቅመው ይየቀጥላል በነገራችን ላይ ለነገ ይቆየን=======ከውስጥ አዋቂ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቀጣዩ የወያኔ 'ፓትርያርክ ' አባ ማትያስ መሆን እንድሚችሉ ከውስጥ ኣዋቂው የተሠጠውን አስተያየት ማንም ሊጠራጠረው አይገባም። የወያኔን ውስጡን የሚያውቁት አባላቱ ስለሆኑ ማለቴ ነው። '' ሌሎች ጳጳሳትም ብትሆኑ መናጆ መሆናችሁን ማወቃችሁም ትልቅ ነገር ነው በደፈናው ንጽህና የለንም ብትሉ የበለጠ እውነታ አለው''??? ዋውውውውውውውውው! ወይ የዘረኝነት በሺታ !!ይገርማል ።

   Delete

 13. yesterday send message wher is it ? on

  ReplyDelete
 14. የቤትሕ ቅናት በላኝ
  የቤተክርስቲያኒትዋን እና ዘመናዊ እውቀት ከክህነት ጋር ያላቸው በዘመናዊና በመንፈሳዊ እውቀታቸው የተካኑና በስራቸው አምርቂ ውጤት የሚያሳዩ ሠራተኞች ከቤቱ ሳይጠፉ የተጣለባትን ተራ የስራ መደብ መወጣት ባለማቻልው ከአዲስ አባባ ዩኒበርስቲ የሴቶች ጉዳይ ቢሮ የተባረረችው እውቀት አልባ አጭር ቀሚስ ለባሽ በሆነችው ወ/ሮ ጽጌ ረዳ ዓለሙ የቤተክህነቱ ገንዘብ እየተመዘበረ ነው የቤተክህነቱ ሒሳብ በውጭ ኦዲተሮች ተመርምሮ አያውቅም የአሰራሩ ዘዴ በጣም ኃላ ቀር ከመሆኑም የተነሳ የድሮ ግብፃውያንና የፋርስ ባቢሎን ቀደምት የመጀመርያ ሂሳብ ጀማሪዎችት ካልመጡ በስተቀር ለማስራት የሚችል የሒሳብ ባለሙያ በዚች ከተማ የለም ይች ሴት ሒሳቡን ታዘምናለች ተብሎ በውሽሞችዋ ፕረፖጋንዳ ከፍተኛ ደመወዝ እየተከፈላት ለ3 ድፍን ዓመታት ሒሳቡ እንዳለ ዘግምተኛ የእድር የሂሳብ አያያዝ ተከትሎ እየሔደ ነው የሒሳብ ሪፖርት የሚባል ነገር አይታወቅም የሀብትና ዕዳ የሒሳብ ሚዛን አይታወቅም ግን አለቆችዋ ይወዱዋታል አንዳንዶቹ አብሮዋት ስለሚሰርቁ አንዳንዶቹ ስለሚያውቁዋት ነው በየምክንያቱ ቤተክህነት ለድግስ ዝግጅት ከሚያወጣው ከፍተና ወጪ አንድ ሁለተኛውን ገንዘብ ይች ሴት ተደራድራ ለራስዋና ለስራ ባልደረቦችዋ ታካፍላለች እስከ ከዚህ የተነሳ ሆዴ ይሉዋታል እስኪ አዲሱ አስተዳደር ምን ያደርግ ይሆን;

  ReplyDelete