Wednesday, February 27, 2013

ማኅበረ ቅዱሳን መራጮችን “ሎቢ” ሲያደርግ ዋለ

በ6ኛው የፓትርያርክ ምርጫ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ የሚገኘውና በወኪሎቹም በኩል ብዙም ያልተሳካለት ማቅ ለምርጫው አንድ ቀን በቀረበት ዕለት ከየአህጉረ ስብከቱ የመጡትን መራጮች በምግብ ቤቶቹ ምሳና እራት በመጋበዝ ለማኅበሩ እጩ ለአባ ማቴዎስ ድምጽ እንዲሰጡ እያግባባና “መንግስት ድምጽ ለአቡነ ማትያስ ስጡ ብሎናል በሉ” እያለ ባሰማራቸው ሰላዮቹ አማካይነት የማግባባት ስራ ሲሰራ መዋሉን የሎቢው ሰለባ ከሆኑት መራጮች አካባቢ የደረሰን ዜና ያመለክታል፡፡ ሎቢ ከተደረጉት መካከል አንድ የሀገረስብከት ስራ አስኪያጅ ሎቢ ሊያደርጋቸው ላሰበው የማቅ ሰው “እናንተ የምትሉት ነገር አልገጠመኝም፡፡ እናንተ በየድረገጹ ከምትሉት ውጪ ከመንግስት በኩል እገሌን ምረጡ የሚል ነገር አልሰማሁም፡፡ ደግሞስ መንግስት ፈጸመ ያላችሁትን ስህተት እናንተ በግልጽ ለምን ትደግማላችሁ? ስማ እኔ እገሌን ምረጡ ልል አልችልም፡፡ ሁሉም የሚመርጠውን ያውቃልና እናንተ ለምን አርፋችሁ አትቀመጡም” ማለታቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ማቅ በማግባባት ስራው በሃራ ድረገጹ አባ ማቴዎስ ትሁት መሆናቸው እንዲታይለት እርሳቸው ያልሆኑትንና ያላሉትን ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እጩነቱን አለመቀበላቸውንና “እንኳን ፓትርያርክ ልሆን ይቅርና ጵጵስናውም ከብዶኛል” ብለዋል እያለ እጅግ መንፈሳዊ አድርጎ ለማቅረብ በመሞከር የመራጮችን ቀልብ ለመሳብ ጥረት ቢያደርግም ብዙ የተሳካለት አይመስልም፡፡ የብዙዎች ምርጫ አቡነ ማትያስ እንደሆኑ እየተነገረ ነውና፡፡ እርሳቸውን ለመምረጥ ፍላጎት ያሳዩ መራጮች ተናግረዋል እንደሚባለው አቡነ ማትያስ በእድሜያቸው አንጋፋነት፣ በትምህርታቸው፣ በቋንቋ ችሎታቸው፣ ሌላው ሁሉ ቀርቶ በግርማ ሞገሳቸውና ከቤተክህነቱ ፖለቲካ ርቀው የኖሩ በመሆናቸው እንደሚመርጧቸው እየተናገሩ ነው፡፡ ምክንያቱም የአገር ቤቱ ሲኖዶስ በጎረምሶቹ ጳጳሳት ሲታወክ በመኖሩና በጳጳሳቱ መካከል ከፍተኛ መደፋፈር ስለሚታይ አሁን የሚያስፈልገው አዲስ ፊት ነው የሚል አቋም በብዙዎች እንደተያዘ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ማቅ የአቡነ ማትያስን ታሪክ በአንደኛ ተራ ቁጥር አስፍሮ ነገር ግን እጅግ እያድበሰበሰውና እየጨቆነው የአቡነ ማቴዎስን ታሪክ ግን መጨረሻ ላይ በማስፈርና አላስፈላጊ ዝርዝር ነገርን ሁሉ በመደርደር ከፍ አድርጎ ለማሳየትና አንባቢን ለማደናገር ጥረት እያደረገ መሆኑን፣ በሀራ ብሎጉ ላይ ስለ ዕጩዎች የሕይወት ታሪክ ህትመት ላይ ባወጣው ዘገባ ላይ ግልጽ አድርጓል፡፡ 

እንኳን ለጵጵስና ለፕትርክናም በማይመጥን የስነምግባር ችግር ምክንያት ከውድድሩ ውጪ የሆኑት አባ ሳሙኤልም የክፉ ቀን ወዳጃቸውን የአባ ማትያስን እጩ መሆንና የሚመረጡት እርሳቸው ናቸው የሚለውን ግምት በመቃወም “ለእኔ ድምጽ ልትሰጡ የነበራችሁ መራጮች አባ ማትያስን ሳይሆን አባ ማቴዎስን ምረጡ” የሚል የሎቢ ሥራ እየሰሩ መሆኑን አንዳንድ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ይህም በራሳቸው የምርጫ ዘመቻ ተይዘው በነበሩባቸው ሳምንታት ከማቅ ጋር ተቀዛቅዞ የነበረ ፍቅራቸውን ወደስፍራ ለመመለስና ለክፋት ስራ ለመተባበር እንደገና መነሳሳታቸውን ያመለክታል የሚሉ አሉ፡፡

በአስመራጭ ኮሚቴው ውስጥ በአንድ ሰው መወከል የነበረበትና ሌሎች ሁለት ወኪሎቹን ማለትም ባያብል፣ የግቢ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት አባል የሆነው ቀንደኛው ማቅ ሄኖክና የመንደር ቀኛዝማቹ አቶ ሀይሉ በድምሩ ሦስት ወኪሎች የነበሩት ማቅ በወኪሎቹ ደስተኛ አለመሆኑን ከማቅ አካባቢ እየወጡ ካሉ መረጃዎች መረዳት ተችሏል፡፡ በተለይም አቶ ባያብል ማቅ በስፋት የሚያስወራውን የመንግስት ጣልቃ ገብነት ማየት ስላልቻለ ግራ በመጋባቱና ማቅ የሰጠውን ተልእኮ ባለመወጣቱ ማቅ ጥርስ ውስጥ መግባቱ ተነግሯል፡፡ ማቅ የእርሱን ያልተሳካ መጠነ ሰፊ ጣልቃ ገብነት እንደጽድቅ ስራ በመቁጠርና መንግስትን በጣልቃ ገብነት በመክሰስ ቀጣዩ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከሆኑ በህዝብ እንዲጠሉ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ በስፋት ተያይዞታል፡፡ ይህም በአቡነ ማትያስና በማቅ መካከል ከመጀመሪያው ልዩነቶችን እንዳይፈጠር ተሰግቷል፡፡ ምንም ይሁን ምን አቡነ ማትያስ ማቅን እንደአቡነ ጳውሎስ እንደማይሸከሟቸው ግን ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡   

18 comments:

 1. Egziabher Lisanachihun Yizigaw. lela minim anilim. anedim ken melkam sira yemayitayachihuna haset bemefiter yetwoterachihu yeDiyablos yeGibir lijochi... Egziabher LeBetekiristiyan selam sil Lisanachihun Zegito leNiseha Yabikachihu.

  ReplyDelete
 2. tera yemender wore new yemtsifew

  ReplyDelete
 3. denbegna poletikegnoh nachehu mechem weregnoch!

  ReplyDelete
 4. ውይ የኛ ታማኝ ምንጮች!

  ReplyDelete
 5. negeregna neh!zimbleh atwolabed.

  ReplyDelete
 6. According to http://www.dejeselam.org/ online survey, Abune Matiwos is leading the race.

  ReplyDelete
 7. Why guys are obsessed with Abune Matias and doesn't like Abune Matiwos? any problem?

  ReplyDelete
 8. አይ የናንተ ነገር ባልበላዉም ጭሬ ልድፋው ሆነ እግዚኝብሔር ልቦና ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 9. amlak abune matyasen mertwal..lezich fews lemiyasfelgat betecrstiyan...ke mk blog lay new yesmahut i dont know if its true or false

  ReplyDelete
 10. pls always we speak a true

  ReplyDelete
 11. what a sad day for mahibere kidusan. To mahibere kidusan, this is what you get when you practice politics in the name of religion under the umbrela of the Ethiopian orthodox tewhdo church. Don't underestimate God; stay away from church since you have political agenda....

  mahibere kidusan, ask for forgiveness from God.

  ReplyDelete
 12. what is ማቅ? ማቅ ምን ማለት ነው? Does it stand for something?

  ReplyDelete
 13. ዉሸታም መሆን ምን ይጠቅማል፡፡

  ReplyDelete
 14. ኦርቶዶክሳውያን ብፁዕ አቡነ ማትያስን 6ኛ ፓትርያርካቸው አድርገው መረጡ፡፡ ምን ማለት ነዉ

  ReplyDelete
 15. our patriarch is abune merkorious

  ReplyDelete
 16. አማርኛ አታውቅም እንዴ?

  ReplyDelete