Saturday, February 9, 2013

"ማህበረ ቅዱሳንን" ያያችሁ!


በአንድም በሌላም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እምነት ተከታይ ሆኖ ራሱን "ማህበረ ቅዱሳን" በማለት የሚጠራ ነፍሰ ገዳይ ሳለ መንፈሳዊ ጭምብል አጥልቆ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሆነ ንዋያተ ቅድሳትና የተለያዩ ቅርሳቅርሶች ከዬ ገዳማቱና አድባራቱ እያደነ ከመዝረፍና ከመመዝበር አንስቶ ለዓላማው ያልተንበረከኩ ሊቃነ ጳጳሳት: ካህናትና ዲያቆናት በማሳደድና ነፍስ እስከ መግደል ድረስም የተሰማራ የጥቁር ራስ ስብስብ መሰሪ ድርጅት የማያውቅ ሰው ይኖራል የሚል እምነት የለኝም፡፡
በእርግጥ ማህበሩ በመላ ሀገሪቱ ባሰማራቸው ለዓመታት በስለላ የሰለጠኑ አባላቱና በተለያዩ የመንግስት የሃላፊነት ቦታዎች የተቀመጡ ግለሰቦች ጭምር በመጠቀም "ማህበረ ቅዱሳን የተቃቃመው ጥንታዊትና ሐዋሪያዊት የሆነችው የኢ//// ስርዓተ አምልኮ ለትውልድ ማስተላለፍ ነው፡፡ ዓላማውም አበው ትተውልን ያለፉት ትውፊት፡ ደንብና ስርዓት ጠብቆ ማስጠበቅ ነው።" ሲሉ በነጋ በጠባ ቁጥር ሳይታክቱ እንዲለፍፉ በማድረግ በሰራውና እሁንም ድረስ እየሰራው ባለ ፕሮፖጋንዳ "ማህበረ ቅዱሳን" ሲባል "ብዙዎቻችን" የምናወቀው ሃጢአት የማያውቃቸው፡ ቅዱሳን፡ ንጹሐንና የመላእክት ዘር ያለባቸው ንኡዳን አድርገን በመቁጥር ነው። እንግዲህ ይሄው ቀኑ ደረሰና "የቤተ ክርስቲያን ስርዓትና ትውፊት ጠብቆ ለማስጠበቅ የቆምኩ መንፈሳዊ ማህበር ነኝ" እያለ ሕዝብ ሲያደኖቅር ዓመታት ያስቆጠረ ድርጅት የሃይማኖት መሪዎች እየፈጸሙት ላለው ጥፋት ይሄው ጭራሽ መራጭና አስመራጭ ሆኖ በመሪ ተዋናይነት ተሰልፎ ሽርጉድ እያለ ይገኛል። (ስም ማጥፋት ወይንም ደግሞ ተራ ውንጀላ አይደለም እየተባለ ያለው ለማረጋገጥ ከተፈለገ የሚቀጥለውን ሊንክ በመጨቆን እውነቱን ሊያረጋግጡ ይችላሉ። http://www.ethiotube.net/video/24565/ETV-News--Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-Churchto- elect-its-6th-Patriarch-on-February-28--February-7-2013)
 

ውድ አንባቢ! በእርስዎ ቤት ስርዓት መጠበቅማለት ምን ማለት እንደሆነ ቃሉም እንዴት እንደሚተረጉሙት እርግጠኛ ባልሆነም በበኩሌ ግን፡
Ø  ስርዓት መጠበቅ ማለት ስርዓት ማፍረስ ከሆነ፤
Ø  ስርዓት መጠበቅ ማለት ቀነኖ መጠስ ከሆነ፤
Ø  ስርዓት መጠበቅ ማለት የቀደመውን እያፈረስክ አዲስ መስራት ማለት ከሆነ፤
Ø  ስርዓት መጠበቅ ማለት እንዳሻህ መሆን ከሆነ፤
Ø  ስርዓት መጠበቅ ማለት ለሕግ አለመገዛት ማለት ከሆነ፤
Ø  ስርዓት መጠበቅ ማለት የወደድከውን ማድረግ ማለት ከሆነ ቀድሞውንስ ትውፊት አክባሪ ስርዓት ጠባቂ/ጠበቃ ብሎ ማህበር ማቋቋም ለምን አስፈለገ? ብዬ እጠይቆት ዘንድ ግድ ብሎኛል። መቼም ስርዓት ሲጣስ፡ ቀኖና ሲፈርስና የአበው ትውፊት ሲዘነጋ የሕግ ያለህ! በማለት "ስርዓት ለመጠበቅ፤ የአበው ሐዋሪያዊ ግብር ለመዘከር እንዲሁም የቅዱሳን ትውፊት ለትውልድ ለማስተላለፍ የቆምኩ ነኝ ባይ ማህበር "ማህበረ ቅዱሳንን ያያችሁ!" በማለት ጮክ ብዬ ስጮክ አብረውኝ "ማህበረ ቅዱሳንን" ፍለጋ ለመውጣታቸው አልጠራጠርም፡፡ ነገሩ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የመታደግ ጉዳይ ነውና!

"ማህበረ ቅዱሳን ባይኖር ኖሮ እቺ ቤተ ክርስቲያን ድሮ ድምጥማጥዋ ጠፍታ ነበር" ለምትሉ ተሳላሚዎች "ቤተ ክርስቲያን" ከዚህም በላይ መበጣጠስ ነበረባት/አለባት ከሆነ ቁጭታችሁ "አልተሳሳታችሁም" ከማለት ውጭ በመላእክት ቋንቋም ቢሆን መግባባት ስለማንችል ፍርዱ ለአንባቢ ትቸዋለሁ። በተረፈ ይህ ሀገር የመበተን እንዲሁም ትውልድን የማኮላሸት ልዩ ተልኦኮ ይዞ የተነሳ ማህበር በየትኛው ህገ ደንብና ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሰረት ፓትሪያሪክ ለመሾም በሚቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ ሊገባ እንደቻለና እንደገባም ሌላ አዲስ አባባ በሚገኘው የክፋት ሁሉ ማከፋፈያ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አከባቢ የነገሰውን ስርዓት አልበኝነትና የተንሰራፋውን የውንብድና ድርጊት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። እዚህ ላይ ግልጽ ማድረግ የምፈልገው ነጥብ ቢኖር እንደው ስንዴውንና እንክርዳዱ መለየት ያቃተው ብዙሐኑ ሕዝብ በሚገባው መልኩ ለመግለጽ ተሞከረ እንጅ "ማህበረ ቅዱሳን" ዛሬ ይህን ቢያደርግ በግሌ ምንም የሚደንቀኝ አይደለም፡፡ እያደረገው ያለው ሁሉ የኢ////ያን ለማፈራረስ ይዞት የተነሳውን ዓላማ አንዱ ክፍል በመሆኑ ሲፈለግ በትክክለኛ ስፍራው መገኘቱ ለመግለጽ እወዳለሁ። "ማህበረ ቅዱሳን" ይህን ሲያደርግ ደግሞ በፓትሪያሪክ መርቆሬዎስ ለሚመራው በውጭው ዓለም ለሚገኘው ጉባኤ እያስተላለፈው ያለው መልእክትም እንስተዋለን የሚል እምነት የለኝም።


/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E- mail- yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America
February 8, 2013

34 comments:

 1. kinat new adel, patriarich kemimertut mekakel MK silalebet? ha ha ha , bikat newa. enante eko atafrum egna nebern megbat yalebn tilalachihu? If you get the chance I am sure you will choose to be patriarich "Kes Alemu Sheta"

  ReplyDelete
 2. Selam negn

  Selam hunulign. where she has gone?

  was she an artist created by Aba selamas? Relly I missed her.

  ReplyDelete
 3. "ውድ አንባቢ! በእርስዎ ቤት “ስርዓት መጠበቅ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ቃሉም እንዴት እንደሚተረጉሙት እርግጠኛ ባልሆነም በበኩሌ ግን፡
  ስርዓት መጠበቅ ማለት ስርዓት ማፍረስ ከሆነ፤
  ስርዓት መጠበቅ ማለት ቀነኖ መጠስ ከሆነ፤
  ስርዓት መጠበቅ ማለት የቀደመውን እያፈረስክ አዲስ መስራት ማለት ከሆነ፤
  የቀደመውን እያፈረስክ አዲስ መስራት ከሆነ፤
  ስርዓት መጠበቅ ማለት ለሕግ አለመገዛት ማለት ከሆነ፤
  ስርዓት መጠበቅ ማለት የወደድከውን ማድረግ ማለት ከሆነ"......What does that mean??? u or MK የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ለማፈራረስ የተነሳው???????? Bakachehu?? u have to write some thing fair!!!ቀነኖ መጠስ ,የቀደመውን እያፈረስክ አዲስ መስራት,ለሕግ አለመገዛት,የወደድከውን ማድረግ...this all ur activity over our church not by MK.

  ReplyDelete
 4. "እያደረገው ያለው ሁሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ለማፈራረስ ይዞት የተነሳውን ዓላማ አንዱ ክፍል በመሆኑ ሲፈለግ በትክክለኛ ስፍራው መገኘቱ ለመግለጽ እወዳለሁ።" Rebakeh? antes min eyserah yehon....yekidusanu sem sayker eyabteltelek aydel enda hyemtsefewu.Kalkes ante neh betkrsteyan eyfresek yalehewu.

  ReplyDelete
 5. ማኅበረ ቅዱሳን ለሚያከናውናቸው በጎ ሥራዎች ደጋፊዎች ነን:: በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በጠቅላላው ዓለም ማኅበሩ የሚያከናውናቸው ማሕበራዊ እና መንፈሳዊ ሥራዎች እናዳሉት የዐይን ምስክሮች ነን:: ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያናችን ብሎም ለሀገራችን ኢትዮጵያ የተማረውን ሀይል አስተባብሮ በመያዝ እግዚአብሐርን የሚፈራ እና ከሙስና የጸዳ ትውልድ እንደፈጠረም በሙሉ ልብ እንመሰክራለን:: እንዲሁም ደግሞ ምሁራኑ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በጉልበታቸው፣ በእውቀታቸው እና በገንዘባቸው በነጻ ቤተ ክርስቲያናቸውን ለማገልገል ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ደፋ ቀና ሲሉ በተለያዪ ቦታዎች እናውቃቸዋለን:: የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በብሔር፣ በፖለቲካ እና በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ሳይከፋፈሉ በአንድነት ሆነው ስለ እውነት ሲሰሩ አይተናል ሰምተናልም:: ስለዚህ ይህ ማኅበር ፍጹም የአገልግሎት ማኅበር ነው ብለን ብንናገር ማጋነን አይሆንብንም::

  የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች በተለያዩ ጊዜያት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ሲያካሄዱ ሰምተናል:: አሁንም እየሰማን ነው:: በተለይም በዚህ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚሳደቡ እኛ የምናውቃቸው ወደ አምስት ብሎጎች ተከፍተዋል:: በተቃራኒው ማኅበሩ ለሚካሄድበት የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ተመጣጣኝ ምላሽ ሲሰጥ አይታይም:: ከዚህ በፊት “ማኅበረ ቅዱሳንን ለምን ጠሉት” በሚለው ዘገባችን እንዳሳሰብነው አሁንም በድጋሚ ማኅበሩን ማሳሰብ የምንፈልገው ሐሰት ተደጋግሞ ሲነገር እውነት ይሆናል እንደሚባለው ማኅበሩ በተመለከተ የሚወጡ የሐሰት ውንጀላዎች በተቃራኒው ማሰተባበያ ቢሰጥባቸው የሚል እምነት አለን:: ማኅበሩን መጀመርያ የተሐድሶ መናፍቃን አሸበሪ በማለት ሲወነጅሉት ነበረ ይህንን የሐሰት ውንጀላ ተቀብለው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ክቡር መለስ ዜናዊ ከአሸባሪዎች ጋር በመደመር ዘልፈውታል:: ስለዚህ ለሚቀርቡ የሐሰት ውንጀላዎች ተመጣጣኝ ምላሽ ይሰጥባቸው እንላለን::
  ማኅበረ ቅዱሳንን ለመወንጀል ብቻ ተብለው ከተከፈቱ ብሎጎች አንዱ “የምንፍቅና ትምህርት እንይስፋፋ ብቸኛ ጠላታችን ማኅበረ ቅዱሳን ነው” የሚሉት አባ ሰላማ የተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ “ማኅበረ ቅዱሳን እና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አይተዋወቁም” በሚል የተለመደው የበሬ ወለደ የሐሰት ዘገባ ዛሬ አስነብቦዋል:: ለዚሁ ምላሽ ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ያገኘነውን የማኅበረ ቅዱሳንን የአመሠራረት ታሪክ የያዘ ጽሑፍ እንደሚከተለው አቅርበነዋል::
  ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? እንዴትስ ተመሠረተ?
  ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? እንዴትስ ተመሠረተ የሚለውን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት አጽራረ ቤተክርስቲያንና ዓላማቸውን ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱት ተላላኪዎቻቸው የውስጥ ዐርበኞች ማኅበረ ቅዱሳንን በሰው ውስጥ የጥላቻ መንፈስ እንዲያድር ከሚጣጣሩበት መንገድ አንዱ ማኅበሩ የሚጠራበትን ስያሜውን በማዛባት ነው የሚጀምሩት፡፡ ከዚህ አንጻር ማኅበረ ቅዱሳን ሲባል ምን ማለት ነው? የሚለውን ነገር ማብራራት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ስያሜው ላይ አጭር ትንታኔ በመስጠት ወደ ማንነቱና አመሠራረቱ እንለፍ፡፡
  የማኅበሩ ስያሜ
  አንዳንድ ሰዎች ስያሜውም ግራ ያጋባቸዋል፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው አባላቱ ለራሳቸው ያወጡት አስመስለው የሚነግሯቸው ሰዎች አሉና የዋሀኑ ግራ ቢጋቡ አያስደንቅም፡፡ ነገር ግን የማኅበሩ ስያሜ እኩያኑ ማኅበሩን ለማጥላላት ከሚጠቀሙት ፕሮ¬ጋንዳ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ ማኅበረ ሚካኤል «የሚካኤሎች ስብስብ»፣ ማኅበረ ማርያምም «የማርያሞች ስብስብ» ካልሆነ /እንዳልሆነ/ ማኅበረ ቅዱሳንም «የቅዱሳን ሰብስብ» አይደለም፣ ሊሆን አይችልም፤ ወይም ማኅበረ ጊዮርጊስን የመሠረቱ ሰዎች ራሳቸውን «ጊዮርጊሶች»ነን እንደማይሉት፤ እንዳልሆኑትም፣ ማኅበረ ቅዱሳንም ቅዱሳን ነን የሚሉ ሰዎች ስብስብ አይደለም፡፡ ይልቁንም ማኅበረ ማካኤል የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት፣ ተራዳኢነት የሚታሰብበት ማኅበር እንደሆነው ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳንም የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዐት ከመጠበቅና ከማስተማር በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርተ ሃይማኖት መሠረት የቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት እንዲሁም የቅዱሳን መላእክት ክብ ራቸው፤ ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ አማላጅነታቸውና በረከታቸው፤ በሰፊው እንዲታወቅና ትውልዱም የዚህ ተጠቃሚ እንዲሆን ትምህርት የሚሰጡበት ማኅበር ነው፡፡ ምእመናን በነዚህ ቅዱሳን አማላጅነትና ረድኤት እየታገዙ ለመንግሥተ ሰማያት እንዲበቁ ማድረግም ቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡
  ከዚህ የተነሣ የእነዚያ ብዙ ማኅበራት ኅብረት የሆነው ማኅበር የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ ጻድቃን ሰማዕታትና የቅዱሳን መላእከት ሁሉ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ማኅበረ ቅዱሳን ተባለ፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳን እንዴትስ ተመሠረተ?
  ዘመኑ የኮምዩኒዝም ርዕዮተ ዓለምና አስተሳሰብ የሰፈነበት፤ ስመ እግዚአብሔርን መጥራት አስቸጋሪ የሆነበትና ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሔድ እንደ ኋላቀርነት የሚቆጠርበት ዘመን ነበር 1977 ዓ.ም፡፡
  በተለይም በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ /ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች/ በሚገኙ ተማሪዎች ዘንድ ቃለ እግዚአብሔርን በግልጽ መነጋገርም ሆነ መሰማት የማይታሰብበት ወቅት ነው፡፡
  ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለይም በንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች እንዲያስተምሩ ከምዕራባውያኑ ሀገሮች መጥተው የነበሩ ሚሲዮናውያን የኑፋቄ ትምህርታቸውን ያሠራጩ የነበረውም በእነዚሁ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነው፡፡
  በዚህ ሁኔታ ትውልዱ በየአቅጣጫው በሚሲዮናውያኑ የኑፋቄ ትምህርት እንዲሁም በኮምዩኒዝም ርዕተ ዓለምና አስተሳሰብ እየተነጠቀ ከኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ እምነት የኮበለለበት ከቤተክርስቲያን የራቀበት ዘመን ነበር፡፡
  በዚህ ጊዜ ነው፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ዋናው ግቢ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ይከታተሉ የነበሩ አምስት ወጣቶች ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ በቅዱስ ገብርኤል ስም ተሰባስበው ጽዋ መጠጣት የጀመሩት፡፡ ይህ መንፈሳዊ እንቅስቀሴ በዚሁ ተወስኖ አልቀረም፡፡ በየሳምንቱ እሑድ በመንበረ ¬ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተክርስቲያን ግቢ በመጠለያ ሥር እየተሰባሰቡ በተደራጀ መልክ ባይሆንም መንፈሳዊ ትምህርት ይማሩ ጀመር፡፡ ከዚያም በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ ትምህርት መማር ቀጠሉ፡፡
  ይቀጥላል!!!

  ReplyDelete
 6. ክፍል 2
  እንዲህ የተጀመረው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች ዘንድ የተዳረሰበት አጋጣሚና ሁኔታ የተፈጠረው ደግሞ በዚሁ በ1977 ዓ.ም ነው፡፡ በወቅቱ በነበረው የመንግሥት ሠፈራ ፕሮግራም በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በሙሉ በመንደር ምሥረታና መልሶ ማቋቋም ዘመቻ ወደ ጋምቤላ፣ መተከል እና ፓ¬ዌ እንዲዘምቱ ተደረገ፡፡ በዘመቻው ወቅት ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየመጡ የተገናኙት የቤተክርስቲያን ልጆች ቃለ እግዚአብሔርን በመማር፣ በማኅበር ጸሎት በማድረግ እና ስለቤተክርስቲያን ጉዳይ በመወያየት ጊዜውን ተጠቀሙበት፡፡

  በዚህ ዓይነት የተጀመረው እንቅስቃሴ ከዘመቻው መልስ በ1978 ዓ.ም ተጠናከረ፡፡ ውስን የነበረው የተማሪዎች ቁጥርም ጨመረ፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ፣ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ ግቢዎች እስከ አርባ የሚደርሱ ተማሪዎች በምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ማኅበር አዳራሽ እየተገኙ ትምህርተ ወንጌል ይማሩ ነበር፡፡ የተማሪዎቹን ዓላማና ጥረት የተገነዘቡ አባቶች መምህራነ ወንጌልም በቅርብ ሆነው እየተከታተሉ ሲያስተምሯቸው ቆይተዋል፡፡

  በቀጣዩ ዓመት ከ1979 ዓ.ም እስከ 1980 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎቹ በተምሮ ማስተማር ማኅበር አደራሽ ከሚከታተሉት መንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር ጋር ይህ መንፈሳዊ እን ቅስቃሴ ተጠናክሮ በስፋት የሚቀጥልበትን መንገድ ይወያዩ ነበር፡፡ በወቅቱ ትኩረት ተሰጥቶት ውይይት ይደረግበት የነበረው ዐቢይ ጉዳይ ከመካከላቸው ሰባኪ ወንጌል ማፍራት ነበር፡፡ ለዚህም በተለይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት በቤተክርስቲያን አገልግሎት እየተሳተፉ በሰንበት ትምህርት ቤት ያደጉና በመጠኑም ቢሆን ልምድ ያላቸውን ተማሪዎች እንዲያስተምሩ ማድረግ አንድ መፍትሔ ነው፡፡ ለዘለቄታው ግን ከተማሪዎቹ መካከል በወቅቱ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የካህናት ማሠልጠኛ ገብተው እንዲሠለጥኑ ማድረግ የታመነበት መሠረታዊ ጉዳይ ሆነ፡፡

  ይህንኑ ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግ፤ አስቀድመው በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው ስለስብከተ ወንጌል ሥልጠና የወሰዱ፤ በወቅቱ የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እና የካህናት ማሠልጠኛው የበላይ ጠባቂ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር ይቀራረቡ በነበሩ ተማሪዎች አማካኝነት ግንኙነት ተደረገ፡፡

  እንዲሁም በ1980 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ግቢ ትምህርታቸውን ሊከታተሉ ከገቡት መካከል እስከ ሃምሣ የሚደርሱ ተማሪዎች በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብር ኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ተሰብስበው ይማሩ ጀመር፡፡ በዚሁ ዓመት በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎችም ተመሳሳይ መንፈሳዊ መርሐ ግብር ጀምረው ነበር፡፡

  በዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርታቸውን አጠናቀው በ1980 ዓ.ም ከተመረቁት ተማሪዎች ውስጥ በግቢ ቆይታቸው በቤተክርስቲያን ተሰባስበው መንፈሳዊ ትምህርት ሲማሩ የነበሩት የቤተክርስቲያን ልጆችም ለመጀመሪያ ጊዜ ተመረቁ፡፡ የምረቃው መርሐ ግብር የተካኼደው በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ማኅበር አዳራሽ ነው፡፡ በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮሰ ካልዕ ከጋር ሌሎችም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተው፤ ተመራቂዎቹ ተማሪዎች ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እንዲተጉ አስተምረው ባርከው መርቀዋል፡፡

  ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር በተደረገው ግንኙነት መሠረት በዚሁ ዓመት ከተመረቁት መካከል ዐሥራ ሁለት ተመራቂ የቤተክርስቲያን ልጆች በዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው በክረምቱ ወራት፤ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ እምነት፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ትውፊት እንዲሁም የስብከት ዘዴ ሲማሩ ከረሙ፡፡ ሥልጠናውን የተከታተሉት ተማሪዎች ተመርቀው ከገዳሙ ሲሔዱ፤ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮሰ ካልዕ፤ «ከዚህ ስትወጡ ተበትናችሁ እንዳትቀሩ አደራ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎታችሁ እየተገናኛችሁ መወያያ ይሆናችሁ ዘንድ መሰባሰቢያ አብጁ» በማለት፤ ተመራቂዎቹ በጽዋ ማኅበር ስም በመሰባሰብ፣ በሚሔዱበት ቦታ ሁሉ ስብከተ ወንጌልን እንዲያስፋፉ፣ በየዓመቱም በዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እየተገናኙ ስለ ዓመቱ የአገልግሎት ቆይታቸው ሪፖርት እንዲያቀርቡና እንዲወያዩ አሳስበው አሰናበቷቸው፡፡

  ተመራቂዎቹ የቤተክርስቲያን ልጆች የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕን አባታዊ ምክርና መመሪያ አልዘነጉም፡፡ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ «ማኅበረ ማርያም» በሚል ስያሜ የጽዋ ማኅበር መሠረቱ፡፡ በአዲስ አበባና በዙሪያው በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በዓውደ ምሕረትና ሌሎች መርሐ ግብሮች ቃለ እግዚአብሔርን እያስተማሩ በየወሩ እየተገናኙ ስለአገልግሎታቸው ይወያዩ ነበር፡፡ በዓመቱ መጨረሻም በዝዋይ ተገኝተው ሪፖርት አድርገዋል፡፡ በ1981 ዓ.ም ክረምት ለሁለተኛ ዙር ሥልጠና በምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ተምሮ ማስተማር ማኅበር እና በግቢ ገብርኤል ዓምደ ሃይማኖት አዳራሾች ይማሩ ከነበሩት መካከል ዐሥራ ሁለት ተማሪዎች ተወክለው በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ በአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ አማካኝነት ሥልጠና ተሰጠቷቸዋል፡፡
  በዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች መንፈ ሳዊ እንቅስቃሴው እየተጠናከረ ቀጥሎ በተለይም በ1982 ዓ.ም በብዙ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ተዳረሰ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ፋኩልቲዎች፤ በጥቁር አንበሳ ሕክምና ፋኩልቲ፣ በልደታ ሕንፃ ኮሌጅ፣ በደብረ ዘይት እንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ እንዲሁም በጅማ ጤና ሳይንስ፣ በዓለማያ ዩኒቨርሲቲ፣ በወቅቱ በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ ወዘተ ተስፋፋ፡፡ በዓመቱ የክረምት ወራት ከየዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጆቹ የተውጣጡ አርባ አምስት ተማሪዎች ዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው ሥልጠና ወስደዋል፡፡ በሥል ጠናው በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ከሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ አርባ የሚደርሱ ተማሪዎችም ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ ሥልጠና ወቅት ነበር ባልታሰበ ሁኔታ ታላቅ ኃዘን የደረሰው፤ ብፁዕ አቡነ ጎርጎር ዮስ ካልዕ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ነዐረፉ፡፡
  በ1983 ዓ.ም በወቅቱ በነበረው መንግሥት በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ ወታደራዊ ሥልጠና እንዲወስዱ ሲታዘዝ፤ በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጆችና ተቋማት የሚማሩ አሥራ አንድ ሺሕ ያህል ተማሪዎች በብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ እንዲገቡ ተደረገ፡፡ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆቹ ግቢዎች ተጀምሮ ቀስ በቀስ የተስፋፋው መንፈሳዊ እንቅስቃሴም የበለጠ የሰፋበትና የተጠናከረበት ጊዜ ሆነ፡፡ ተማሪዎቹ ቀን ከሚሰጣቸው ወታደራዊ ሥልጠና መልስ ማታ ማታ እየተገናኙ መንፈሳዊ ትምህርት መማር በጋራ መጸለይ ጀመሩ፡፡ መንፈሳዊ ትምህርቱና ጸሎቱ በኅብረት የሚካኼደው በወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፑ በሚገኝ በሌላ አገልግሎት ያልተያዘ አዳራሽ /ኬስፖን/ ውስጥ ነበር፡፡ ትምህርቱ ከዚህ ቀደም በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው በሠለጠኑ እና ሌሎችም በቤተ ክርስቲያን ትምህርትና አገልግሎት በቆዩ ተማሪዎች እየተሰጠ በየቀኑ ምሽት መርሐ ግብሩ ሳይታጎል ለሁለት ወራት ቀጥሏል:፡ በዚህ ጉባኤ እስከ አምስት መቶ የሚደርሱ ተማሪዎች ያለማቋረጥ ይከታተሉ ነበር፡፡
  ይቀጥላል::

  ReplyDelete
 7. ክፍል 3
  በወቅቱ በብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ ካምፕ ለወታደራዊ ሥልጠና የገቡት ተማሪዎች ማታ ማታ እየተሰበሰቡ በአንድነት ከሚያደርጉት ጸሎት እና ከሚማሩት የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በተጨማሪ፤ በአካባቢው ወደሚገኘው ብላቴ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እየተደበቁም እያስፈቀዱም በመሔድ ምስጢራተ ቤተክርስቲያንን ይሳተፉ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰባሰቡት ተማሪዎች ኅብረት እየጠነከረ መንፈሳዊ እንቅስቃሴው እየሰፋ መጣ፡፡ እነዚህ የቤተክርስቲያን ልጆች በወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፕ በነበሩበት ጊዜ የ1983 ዓ.ም የእመቤታችንን የልደት በዓል /ግንቦት ልደታ/ ለጸሎትና ለመንፈሳዊው ትምህርት በሚሰበሰቡበት አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል፡፡

  በብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ ካምፕ የነበረው የተማሪዎቹ ወታደራዊ ሥልጠና የሁለት ወር ቆይታ በመንግሥት ለውጥ ምክንያት ሊበተን ግድ ሲሆን፤ ተማሪዎቹ በወታደራዊ ካምፑ ቆይታቸው የነበረው መንፈሳዊ እንቅስቃሴና ኅብረታቸው ዕጣ ፈንታ አሳሰባቸው፡፡ ይህ መንፈሳዊ አንድነት እንዴት መቀጠል እንዳለበት ተነጋገሩ፡፡ ከብዙ ውይይት በኋላም ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ በየዩኒቨርሲቲና ኮሌጆቻቸው ሲመለሱ በቅዱስ ሚካኤል ስም ተሰባስበው ቤተክርስቲያንን ለማገልገል በመስማማት ቃል ገብተው ተለያዩ፡፡

  በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ዕረፍት ዓመታዊ መታሰቢያ ላይ የተገኙ ደቀመዛሙርትና መምህራን ነሐምሌ 22 ቀን 1983 ዓ.ም፤ በወቅቱ የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ የገዳሙና የካህናት ማሠልጠኛው የበላይ ጠባቂ በነበሩበት በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገብርኤል ሰብሳቢነት ጉባኤ ተደርጎ ነበር፡፡ በጉባኤው ላይ «በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ተምራችሁ በማኅበረ ማርያም የታቀፋችሁ፣ በየቦታው ያላችሁ፣ በገዳሙም የምትኖሩ መነኮሳት እንዳትበታተኑ በአባታችን ስም ማኅበር አቋቁሙ» በማለት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ሐሳብ አቀረቡ፡፡ በሐሳቡ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ለጊዜው «የዝዋይ ደቀመዛሙርትና መምህራን ማኅበር» በሚል ስያሜ እንዲጠራ ተወስኖ ማኅበር ተመሠረተ፡፡
  ከዚህ ቀደም በ1981 ዓ.ም በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም በተምሮ ማስተማር ማኅበር እና በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት የሚማሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች ጉባኤ አንድነት በመፍጠር የተጠናከረ እንቅስቃሴ ባያደርግም «ማኅበረ እስጢፋኖስ» የሚባል ማኅበር መሥርተው ነበር፡፡ ከዚያ በኋላም ቢሆን እንቅስቃሴአቸው የተጠናከረ ባይሆንም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ፋኩልቲ ተማሪዎች «ማኅበረ ሥላሴ» በሚል ስያሜ፤ በሌሎችም ፋኩልቲዎችና ኮሌጆች ግቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች በተለያዩ ቅዱሳን ስም በሰየሟቸው ጽዋ ማኅበራት ተሰባስበው ነበር፡፡
  በጥር ወር 1984 ዓ.ም በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው «ማኅበረ ሚካኤል» የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ አጽድቆ አመራሩንም መርጧል፡፡ ሆኖም በቅዱሳኑ ስም ማኅበር መሥርተው የተሰባሰቡት አባላት፤ «ዓላማቸው፣ አገልግሎታቸውም ሆነ ታሪካቸው አንድ ነው፡፡ ለምን አንድ ስያሜ ይዘው በአንድነት አይንቀሳቀሱም?» የሚል ሐሳብ በውስጣቸው እየተነሣ በተለያዩ አጋጣሚዎች በጉዳዩ ሲወያዩበት ቆይቷል፡፡
  በዝዋይ ለተመሠረተው ማኅበር ስያሜ ለመስጠት አዲስ አበባ በብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቤት በዚሁ ዓመት በየካቲትና መጋቢት ወራት በተካኼደው ስብሰባ ላይ ሐሳቡ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት፡፡ በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል «ሁላችሁም የያዛችሁት አገልግሎት የቅዱሳን ክብር የሚገለጽበት ነው፡፡ ስለዚህ የማኅበራችሁም ስም 'ማኅበረ ቅዱሳን' ይባል፡፡» በማለት ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት፤ የ«ማኅበረ ማርያም»፣ «ማኅበረ ሚካኤል» እና «የዝዋይ ደቀመዛሙርትና መምህራን ማኅበር» ተዋሕደው የሁሉም ማኅበራት የጋራ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ተመሠረተ፡፡

  አባላቱም መንፈሳዊ አገልግሎታቸው የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሥርዓትና መዋቅር ጠብቆ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ዕውቅና ማግኘት እንዳለበት አምነው፤ «በጠቅላይ ቤትክህነት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ሆነን እናገልግል» በማለት መተዳደሪያ ደንባቸውን ይዘው ወደ መምሪያው ጽ/ቤት ቀረቡ፡፡ በዚህ ዓይነት ማኅበረ ቅዱሳን ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቷ መዋቅር ዕውቅና አግኝቶ ግንቦት 2 ቀን 1982 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር መደራጀቱ ይፋ ሆነ፡፡
  አመስግናለሁ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እስኪ የማኅበሩን መስራቾች ስም ጥራ!!!! ለምን ትደብቃቸዋለህ? ስም የለሾች መናፍስት ናቸው እንዴ? አንተ ባትጠራቸው እኛ እናውቃቸዋለን። ሰው ሊገድሉ የጦር ማሰልጠኛ ገብተው ሲያበቁ ግን የአትግደል መፈክር ሰልጣኝ ሲሆኑ አይገርምም........... ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ
   ምናለበት ከማሰልጠኛ ከተበተኑ በኋላ መንፈሳዊ ለመሆኑ ፈለጉ ብለህ ብትዋሽ ይሻል ነበር። በእርግጥ «የእናት ሀገር ወይም ሞት» ወታደሮች ወደመንፈሳዊነት ተለውጠው ማኅበር ቢያቋቁሙ አያስገርምም። ችግሩ ወታደሩ ማኅበር እስከዛሬ ድረስ ብዙ ደም ማፍሰሱንና የሚቃወመውን ሁሉ ሲያሳድድ መኖሩ ነው። ከአዲስ አበባ እስከ አዋሳ፤ ከዲላ እስከ ሐረር ስንቱን ደበደበ? ስንቱንስ አካለ ስንኩል አደረገ? ስንቱንስ አሳደደ? ዛሬ ዛሬማ ሚሊየነር ሆኖ ወደንግዱ ዓለም ገብቶ መድረኩን በሰው ኃይል፤ በገንዘብ አቅም ተቆጣጥሮት ይገኛል። የናዝሬቱ ማኅበር ዛሬ ላይ ፓትርያርክ ለማስመረጥ ስሙ ሲጠቀስ እንደአንድ የመንበረ ፓትርያርክ የመምሪያ ክፍል ሊቆጠር በቅቷል። ቤተክህነቱን ከተቆጣጠረ የቀረው ምንድነው? ቤተ መንግሥቱን ነው? አያያዙን አይቶ ያንንም መገመት ይቻላል። አፍንጫው ስር የሚደረገውን የማየት አቅም የሌለው ኢህአዴግ ለዓይኑ ጥራት ካሮት እንዲበላ እንመክረዋለን። ያለበለዚያ በእንቁላሉ ጊዜ ያልቀጣውን ልጅ የማኅበረ ቅዱሳን ሀረካት ቪዲዮ ቢሰራ እንደቀልድ የሚቆጠርበት ዘመን ይመጣል። በጥቅሉ ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ ማኅበሩ እንደሚያምነው በወታደሮችና ብዙዎች እንደሚያውቁት በድንግልና ገርሳሾች የተመሰረተ ቡድን መሆኑን ታሪክ የሚናገርበት ቀን ይኖራል።

   Delete
  2. ወንድማችን በጣም ጥሩ ገለጻ ነው እናመሰግናለን፡፡
   “ማህበረ ቅዱሳን” የተባለበትን ምክንያት ሰምተናል፤ እስኪ “ማህበረ ሰይጣን” የተባለበትን ምክንያት ደግሞ ንገረን፡፡

   Delete
  3. kale Hiwot Yasemaln.

   Delete
  4. AnonymousFebruary 9, 2013 at 10:27 PM ምን እንደዘማዊ ስት ታስካካለህ !!! Lebona yisteh beyalehu.esti man endegedele negeregn? mechem egzeabhefr beftereleh andebet endeflegeh haset tenageraleh aydel.bakeh telachan kewusteh asewota.Betkrstiyan kalzerefeku beleh tekelalelohal meselegn endewu ayen yawota wushet tewashaleh.esti negeregn MK man gedele???? man asegdele???? lebona yesteh beyalehu bedegami.

   Delete
  5. February 9, 2013 at 10:27 PM
   ቂቂቂቂቂቂ በሳቅ አለች ልጅቱ
   “ማህበረ ቅዱሳን የድንግልና ገርሳሾች ቡድን ነው”
   ወንድማችን ይህንን ጉዳይ ያነሳኸው የማ/ቅዱሳን አባላት በተክሊል ስለሚያገቡ ነው ወይስ………
   ጉዳዩ ተጣርቶ ይቅረብ

   Delete
 8. አይ አቶ ሙሉጌታ አሁንም ከመጮህ አላረፍክም፡፡ በርታ ወዳጄ ያንተ ጩህት ማህበሩን አጠነከረው ተዋቂነቱንም አገነነው እንጂ አልጎዳውም፡፡ ስለዚህ ከጥልበት አይንህ እያየ እሱ ሲያብብ እናንተ ትጠፋላቹ፡፡

  ReplyDelete
 9. አይ ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል ትገርማለህ:ትገርማለህ እግዚአብሂር ልቦና ይስጥህ ብለናል::

  ReplyDelete
 10. Aye///////// mahebere seytan, Getaa yifaredachhu..

  ReplyDelete
 11. ዘላኖችና ዝልሎች የተዘለኑበትና የተዘለሉበት ዘመን በመሆኑ ምንም ይተብተብ ምን ማነንም አያሳምን
  ያባ ሰላማ ተከታዮችና አንባቢዮች ግን ትግላችሁ ከረቂቁ ሳይሆን ከግዙፉ ዓይን አውጣ ጋር ስለሆነ
  ቀን ተሌት ልትተጉ ይገባል። መንገዳቸው ዘወርዋራ ነገራችው ደንጎርጓራ የሆኑ የዘመኑ ልጆች አስገንዛቢው
  ግንዛቤውን በልባቸው እስቲሽጥባቸው አይመለሱም ያው ናቸው።

  ReplyDelete
 12. Ato MK ehdehone wedefit yiramedal ante gin titefaleh. nisiha gebiteh bitimeles yishalihal. endiyawu ke misetu commentoch ayigbahim

  ReplyDelete
 13. ende ene yared g/medhin yalut nachew be mahbere kidusan sim tesebisibe ye dirjitun sim yemistefut

  ReplyDelete
  Replies
  1. yared gebremedhin man new?

   Delete
 14. mahibere kidusan hone orthodox hulum and nachew! betekrisriyanua yetsafechiwun mahiberu yiteregumewal!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቀልደኛ ነህ አቦ!! ማቅ የጻፈውን ቤተክርሰቲያን እንድትተሮግም ያስግድዳታል ብትል አይሻልም?ወዴት ነው እውነቱን የምትሸው?

   Delete
 15. mahbere Erkusan cancer of the church ( Neqersa)

  ReplyDelete
 16. Egziabher bezih hulu wuste yemiseraw sira ejig wubena dink new. Yehulu geta kiristos melkam eregna abat yisten
  Amen

  ReplyDelete
 17. I never knew what MK was I thank you for explaining yourselef what MK is.So therfore MK has nothing to do with the believe or to be part of Ethiopian Orthodox church there Doctrin is out of God. it is a party group or camponey. Why MK has to claim to be Ethiopian Orthodox they donot even believe in Gods only they blieve in Angels that is not Ethiopian Orthodox church believe.Ethiopian Orthodox believes God the father and the son and Holy sprite. I hope people not following the wrong thing God help us please from wrong believe.

  ReplyDelete
 18. ማቅማ ወደ ገደል እየሮጠ እኮ ነው!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ha ha ha ha...ante kedemeh gedel gebeteh yele ende! esti ante mejemeria ke gedelu wuta ena tinish ende Tewhado lijoch or MK asibeh mut!!

   Delete
 19. ማህበረ ቅዱሳን ባይኖር ኖሮ እቺ ቤተ ክርስቲያን ድሮ ድምጥማጥዋ ጠፍታ ነበር

  ReplyDelete
  Replies
  1. God bless you (February 11,2o13 at 10
   ;20 PM)

   Delete
 20. Mahiberun lakak minfiknachun ezawa manafikan gar adarash wust chafiru mahaberu minfikinachun endatizeru enkifat honabachu? Mahiberun benante yehaset wunjala kesiraw ayistaguagolim Egzire mahaberun kakifu yitebikilin

  ReplyDelete
 21. ማህበረ ቅዱሳን በማርጫው የእርሱ አሻንጉሊት ጳጳሳት ፓትሪያርክ ሆነው እንደማይመረጡ ሲያውቅ ጊዜ እርቁ ይቅደም ማለት ጀመረ እርቁም እንደማይሳካ ሲረዳ ደጀ ሰላም በተባለች ምላሱ ጦርነትን ቀሰቀሰ ህዝቡ አንተን አንሰማህም ሲሉት አሁን በስተመጨረሻ ሐራ ዘተዋህዶ በተባለች ምላሱ ቅዱሳን አባቶችን/መነኮሳትን/ እየተሳደበና እየተራገመ ይገኛል፡፡
  ማህበረ ቅዱሳን ምስኪን፤ የ 20 ዓመታት ልፋትህ ሁሉ ከንቱ ሊሆን ነው
  ጳጳሳት በሙሉ ቂም ይዘውብሃል፤ ከምርጫው በኃላ ዋነኛ ስራቸው አንተን ማስወገድ ነው፡፡
  ማቅ እኔ ለአንተ አዘንኩልህ
  ወንድሜ ድካምህ ሁሉ ከንቱ ሊሆን ነው
  የከንቱ ከንቱ
  ማህበሩ ከመፍረሱ በፊት ለ 3 ወራት ሰላሳ ሰላሳ ብር የከፈልኩትን መዋጮ ከነወለዱ 100 ብር አድርጋችሁ መልሱልኝ አደራ

  ReplyDelete
 22. For the writer, you always acuse mk and write against the saints of the church and you are hate the canon of the church, but you use it to insult the mk. God return your heart to the beloved church and serve like mk. Sidib leseytan new. Chirstian aysadebim yimerkal enji. Lemin ke Getachin Iyesus Chirstos anmarim!

  ReplyDelete
 23. ere bakachehu lemin arifachihu sile geta fikir ,sile andinetachin atawerume.

  ReplyDelete
 24. "ማህበረ ቅዱሳን ባይኖር ኖሮ እቺ ቤተ ክርስቲያን ድሮ ድምጥማጥዋ ጠፍታ ነበር" ለምትሉ ተሳላሚዎች "ቤተ ክርስቲያን" ከዚህም በላይ መበጣጠስ ነበረባት/አለባት ከሆነ ቁጭታችሁ "አልተሳሳታችሁም" ከማለት ውጭ በመላእክት ቋንቋም ቢሆን መግባባት ስለማንችል ፍርዱ ለአንባቢ ትቸዋለሁ።
  አዎ በእርግጥ መግባቢያ ቋንቋ የለንም መቼም ደግሞ በዚህ ሁኔታ አንግባባም::ክብራችን በነዉራችን የሆነ ክብርን እንደ ነውር የቆጠርን እውነተን ለመደበቅ የምንጥር ነገር ግን የማንችል ሕያዋንን ለመግደል የተዘጋጀን ነገር ግን ከሕያው አምላክ ጋር መታገል መሆኑን ያልተረዳን, የመጨረሻ እጣ ፈንታችን ከእውነት ራሳችንን ማራቅ አድረገን የወሰንን እኛ የማህበረ ቅዱሳን ባላንጣዎች እውነተኛ ክርስቶስን ትተን ዘመናዊ ክርስቶስን የምናመልክ ዘመን ያፈራን የኢ/ኦ/ት/ቤ ልጆች ነን የምንል የቀደመችዋ ተዋህዶን ትተን ዘመናዊ ተዋህዶን የሰራን እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ጠላቶች ወዮልን ወዮታ አለብን:: በዚች አለምስ የኛ መሳሳት አልበቃ ብሎን የዋሃንን እያሳሳትን እውነትን እየደበቅን ሕያዋንን እያሳደድን እንኖራለን::በኋላ እውነት ሲገለጥ ያሳሳትናቸው ነፍሳችውን ከኛ ሲጠይቁን ሕያዋን ሲፈርዱብን ማንን እንከሳለን?ማህበረ ቅዱሳንን ወይስ ራሳችነን ወይስ አለምን ወይስ ማንን?በልዓም የመርገም ልምዱ ነበረው ነገር ግን የተቀደሰውን እስራኤልን መረቀው እንጂ አረገመዉም, የሚጠብቀው ሕያው አምላክ ነበርና::ዛሬ የረገምናቸውን የማህበረ ቅዱሳን አገልጋዮች እግዚአብሔር ይተብቃችዋልና ነገ ከእግራቸው በታች ወድቀን እንድንማልዳቸው እንገደድ ይሆናል::ደግሞስ እንኳን ከፎከረ ከወረወረ ያድን የለ እንዴ የኛ አምላክ!
  እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን ,የጠፉትን ይፈልግልን አሜን!!!

  ReplyDelete