Friday, March 8, 2013

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 11
በግንቦቱ 15/2004 የሲኖዶስ ስብሰባ በሕገወጥ መንገድ ከተወገዙት ማኅበራት መካከል አንዱ ቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር ነው፡፡ በማኅበሩ ላይ ኑፋቄ ተብለው የቀረቡትና ማኅበሩ ተጠርቶ ሳይጠየቅ የተወገዛባቸው ሁለት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡

“ሀ. የገሃነም ደጆች አይችሏትም የተባለችው የሰማያዊ መንግሥት ባለሙሉ ሥልጣን ጥሪዋን በመዘንጋቷ በራሷ ችግር ተይዛ ባልታዘዘችበት መንገድና ባልተወከለችበት ስፍራ በመጠመዷ የንስሐ አዋጅ ማድረግ አቅቷታል፡፡ ታላቋ የእግዚአብሔር መንግሥት ዛሬ የደረቁ አጥንቶች የመሉባት ሸለቆ ሆናለች’ በማለት ቤተክርስቲያንን ይዘልፋል፡፡’ በሃይማኖት ቁሙ፣ 13ኛ ዓመት እትም ቁ. 3 ገጽ 1”

እንደተባለው ቤተክርስቲያን ትልቅ አሸናፊነት የተሰጣትና ጌታ በገሃነም ደጆች ላይ ያሰለጠናት በምድር ላይ የእግዚአብሔር መንግስት ወኪል ናት፡፡ ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያን ይህን ተልእኮዋን በመዘንጋቷና ባልተጠራችበት አላማ በመሰማራቷ ከላይ የተገለጹት ነገሮች አልደረሱባትም ብሎ ሊያስተባብል ማን ይችላል? ቤተክርስቲያን በዘመናት ሁሉ በውስጧ ስለተፈጸመው ኃጢአትና በደል፣ አንዳንዶች በግልጽ ስለፈጸሙትና ዛሬም እንኳን እየፈጸሙ ስላለው የግፍ ሥራ ንስሐ ስትገባ አልታየም፡፡ ከጥንት እስከ ዛሬ “ቤተክርስቲያን አትሳሳትም፤ የምንሳሳተው እኛ ነን” በሚለው የተላሎች ብሂል ስለታሰረች ተሳስቻለሁ ብላ በአደባባይ ንስሐ መግባት በሚገባት ጉዳይ ላይ እንኳን ንስሐ አልገባችም፡፡ ቤተክርስቲያን ማለት እኛው አይደለንም ወይ? እኛ ደግሞ የምንሳሳት ነን፡፡ ስለዚህ የሰዎች ስብስብ የሆነችው ቤተክርስቲያን አትሳሳትም እንዴት ይባላል? ምናልባት አባባሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት ትክክል ነው፤ በእርሱ ላይ የተመሰረተው የአበው ትምህርትም እውነት ነው ለማለት ተፈልጎ ከሆነ ያን ግልጽ ማድረግ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ግን ትናንትም ዛሬም ቤተክርስቲያን ልትሳሳት ትችላለች፡፡

ከሁሉ በፊት አማኞችን መናፍቃን መናፍቃንን አማኞች ስትል የኖረች ቤተክርስቲያን የንስሐ አዋጅ ልታውጅ ይገባታል፡፡ አጼ ዘርዐ ያዕቆብን ጻድቅ፣ አባ እስጢፋኖስንና ተከታዮቹን መናፍቃን ብላ የፈረጀች ቤተክርስቲያን ንስሐ ልትገባ ይገባታል፡፡ ብዙ አይናማ ሊቃውንቷን በያዙት እውነተኛ ትምህርት ምክንያት በሕገወጥ መንገድ እያወገዘች ከአንድነቷ ስትለይና ስታሳድድ የቆየችና ያለች፣ በዚህ በሠለጠነ ዘመንም በዚሁ ሥራዋ የገፋችበት ቤተክርስቲያን ንስሐ ልትገባ ይገባታል፡፡ ዛሬ በየስፍራው ብዙ የአመጽ ሥራ ዘረኛነት፣ ጉቦ፣ ብልሹ አሠራር የሰፈነባት ቤተክርስቲያን ንስሐ ልትገባ ይገባታል፡፡ በአጠቃላይ የወንጌልን እውነት የምታወግዝ የሐሰት ትምህርትን የምትድገፍ፣ ወንጌላውያን ልጆቿን የምታባርር፣ ፀረ ወንጌል አቋም የያዙትን ግን የምታከብር ቤተክርስቲያን በእውነት ንስሐ ልትገባ ይገባታል እንጂ እንዴት ንስሐ ግቢ እባላለሁ ብላ፣ ንስሐ ግቢ የሚለውን መልእክት እንደ ኑፋቄ መቁጠርና ማውገዝ ባልተገባትም ነበር፡፡

ነቢዩ ሕዝቅኤል በምዕራፍ 37 ያየው ራእይ ስለደረቁ አጥንቶች ይናገራል፡፡ “የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ አጥንቶችም በሞሉባት ሸለቆ መካከል አኖረኝ። በእነርሱም አንጻር በዙሪያቸው አሳለፈኝ እነሆም፥ በሸለቆው ፊት እጅግ ብዙ ነበሩ፥ እነሆም፥ እጅግ ደርቀው ነበር። እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን? አለኝ። እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁ። እርሱም እንዲህ አለኝ። በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው። እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ። ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል። እነሆ፥ ትንፋሽን አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ። ጅማትም እሰጣችኋለሁ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ በእናንተም ላይ ቁርበትን እዘረጋለሁ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ ስናገርም ድምፅ ሆነ፥ እነሆም፥ መናወጥ ሆነ፥ አጥንቶችም አጥንት ከአጥንት ጋር ተቀራረቡ። እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ጅማት ነበረባቸው ሥጋም ወጣ ቁርበትም በላያቸው ተዘረጋ፥ ትንፋሽ ግን አልነበረባቸውም። እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስም። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ፥ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ እነዚህም የተገደሉት በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው በል አለኝ። እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ ትንፋሽም ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ፥ እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ። እርሱም እንዲህ አለኝ። የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው እነሆ። አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል ፈጽመንም ተቈርጠናል ብለዋል። ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ፥ መቃብራችሁን እከፍታለሁ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ፥ ወደ እስራኤልም ምድር አገባችኋለሁ።” ቁጥር 1-12፡፡

እነዚህ የደረቁ አጥንቶች የእስራኤል ቤት መሆናቸው ተብራርቷል፡፡ በኃጢአታቸው ምክንያት ተላልፈው ተሰጡ፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር መቃብራችሁን እከፍታለሁ አላቸው፡፡ ይህ የተነገረላቸው “አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ተቆርጧል” ብለው ያሉበትን ሁኔታ ስላመኑና ንስሐ ስለገቡ ነው፡፡ የእነርሱ ችግር መፍትሔ አገኘ፡፡ መፍትሔ ያጣው የእኛ ችግር ነው፡፡ ትልቁ ችግራችን ደግሞ ጥፋታችንን አለማመናችንና ንስሐ አለመግባታችን፣ ዘወትርም በእግዚአብሔር ፊት የሌለንን ማንነት እንዳለን አድርገን በውድቀታችን መኩራታችን፣ የሚያሳፍረውን ነገር የኩራት ምንጭ አድርገን መመልከታችን ነው፡፡

በእነዚህ ሁሉ ስህተቶች ተጠላልፋ የምትገኝ ቤተክርስቲያን በውስጧ የያዘቻቸው ብዙዎቹ አባላት መቼም ሕያዋን ናቸው ቢባል መቀለድ ይሆናል፡፡ ጌታ ለሰርዴስ ቤተክርስቲያን በላከው መልእክት “ሥራህን አውቃለሁ ሕያው እንደ መሆንህ ስም አለህ ሞተህማል።” (ራእይ 3፡1-6) ብሎት ነበር፡፡ እኛንስ ዛሬ ከዚህ የተሻለ በሕያው ቃሉ ከዚህ ውጪ ምን ሊናገረን ይችላል? አባቶች እንዲህ ያለውን እውነት ከሚያወግዙት ይልቅ ቢጋፈጡትና ራሳቸውን ቢፈትሹበት ቤተክርስቲያን ወደ ትክክለኛው መንገድ ትደርስ ነበር፡፡ ስለዚህ ዛሬም ለንስሐ የተሰጠ ቀን ነውና በንስሐ ወደጌታ እንመልስ፡፡ ከዚህ ቀደም አባቶቻችን ስለሠሩት ኃጢአት ዛሬም እየሠራን ስላለው ኃጢአትና ግፍ ንስሐ እንግባ፤ የዚያን ጊዜ የደረቁ አጥንቶቻችን ሥጋ ይለብሳሉ፤ በጅማት ይታሰራሉ፤ ቆዳም ይለብሳሉ የሕይወት መንፈስ እፍ ይባልባቸውና ሕያዋን ይሆናሉ፡፡ 

“ለ. የእለት ውዳሴ ማርያም ማድረስ ጸሎትን ፈጽሞ አይተካውም” በማለት በእመቤታችን አማላጅነት የምንማጸንበትን የቤተክርስቲያናችን የጸሎት መጽሐፍ በመቃወም ጽፏል፡፡ ገጽ 8”
በዚህ በሁለተኛው ነጥብ የተባለው ምንድነው? ውዳሴ ማርያም ጸሎትን አይተካውም ነው የተባለው እንጂ ጽሑፉ የጸሎት መጽሐፉን አልተቃወመም፡፡ ታዲያ እርሱ የተቃወመውን ነገር ወደጎን ትቶ ወደራስ ሐሳብ መሳብ ምን ይባላል፡፡ ለመሆኑ ውዳሴ ማርያም ጸሎትን ይተካል ወይ?

ጸሎት ምንድነው? ጸሎት ወደእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ የልብ መሥዋዕት ነው፡፡ የልብ መሥዋዕት ከሆነም ማርያምን የሚወድስ ድጋም ጸሎትን ሊተካ አይችልም ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡ ልብ እንበል ጸሎት ወደእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ወደሌላ ፍጡር አይቀርብም፡፡ ጸሎት የአምልኮት መገለጫ ስለሆነ አምልኮትም የሚቀርበው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሊመለሱ የሚገባቸው ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነርሱም ምን ብለን ነው የምንጸልየው? ጸሎት የሚቀርበውስ ወደማነው? የሚሉ ናቸው፡፡ ሁለተኛው አስቀድሞ ተመልሷል፤ ጸሎት ወደሌላ ፍጡር አይቀርብም፤ ወደእግዚአብሔር ብቻ ነው የሚቀርበው፡፡ የመጀመሪያው ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ ምን ብለን ነው የምንጸልየው? የሚል ነው፡፡

በቅድሚያ ከቀረበው ተቃውሞ አንጻር በውዳሴ ማርያም ወደእግዚአብሔር መጸለይ ይቻላል ወይ? ብለን ብንጠይቅ መልካም ሳይሆን አይቀርም፡፡ ውዳሴ ማርያም ምስጢረ ሥጋዌውን፣ ነገረ ድኅነትን በውስጡ እንደያዘ ቢታወቅም አብዛኛው ክፍል ግን ማርያምን ነው የሚያወድሰው፡፡ እመቤታችን ማርያም ትውልድ ሁሉ በጽዕት ይሉኛል ብላ ተናግራለች፡፡ ይህ ማለት ግን ውዳሴ ማርያም ተደርሶልኝ ወደእኔ ይጸለይበታል ማለቷ እንዳልሆነ ማወቅ ይገባናል፡፡ የጌታ እናት በመሆኗና ለዚህ ታላቅ ክብር በመመረጧ “ከዛሬ ጀምሮ” ካለችበት ጊዜ አንሥቶ ያለው ትውልድ ሁሉ የጌታ እናት በመሆኗ ለእርሷ ያለውን አክብሮት ይገልጻል ማለት ነው፡፡ 

አንዳንዶች በውዳሴ ማርያም የምንጸልየው ወደእግዚአብሔር እኮ ነው ቢሉም ማርያምን እያወደሱ ወደእግዚአብሔር ሊጸልዩ አይችሉም እንላለን፡፡ ለአበበ እየተናገሩ ሰማህ ከበደ ለአንተ እኮ ነው እያወራሁ ያለሁት እንደማለት ነውና፡፡

ወደእግዚአብሔር የምንጸልየው ምን ብለን ነው? ጌታ “እንጸልይ ዘንድ አስተምረን” ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ “ውዳሴ ማርያም ድገሙ” አላላቸውም፡፡ አባታችን ሆይ ብላችሁ ጸለዩ ነው ያለው ሉቃስ 11፡1-4፡፡ ለዚያውም አመቤታችን ሆይ የሌለውን አባታችን ሆይ እንደ ሆነ ልብ እንበል፡፡ ታዲያ ጌታ ካስተማረን ወጥተን ጸሎት ውዳሴ ማርያም ነው ብለን ለመከራከር ምን አነሳሳን? እርግጠኛ እንሁን ይህ እመቤታችንን መናቅ አይደለም፡፡ ፈጽሞ!! የጌታን እናት ማን ሊንቅ ይችላል? እርስዋን የሚንቅ ክርስቲያን አይደለም፡፡ ነገር ግን ከተጻፈው በማለፍና እግዚአብሔር ያላለውን ከራሳችን ጨምረን ማርያምን እናከብራታለን ማለትም ዘበት ነው፡፡

ስለዚህ ጸሎት ከልባችን ተጨምቆ የሚወጣ የሕይወታችን ልባዊ መሻት፣ የሕይወታችን ልባዊ ምስጋና፣ የሕይወታችን ልባዊ ልመና፣ የሕይወታችን ልባዊ ንስሐ፣ ስለሌሎችም የሚቀርብ የሕይወታችን ልባዊ ምልጃ የተካተተበት ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ መሥዋዕት ነው፡፡

የጽሑፍ ጸሎቶች በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የተለመዱ ቢሆንም ጸሎት ከልብ የሚመነጭ የሕይወት ጭማቂ እንጂ በጽሑፍ የሚቀርብ ማመልከቻ አይደለም፡፡ ልጅ አባቱን በሚችለው ቋንቋ እንደችሎታው ተናግሮ ይለምነዋል እንጂ በማመልከቻ አይጠይቀውም፡፡ አባቱም የልጁን ጥያቄ እንጂ ጥያቄው የቀረበበትን የቋንቋ ውበት አይመለከትም፡፡ ተኮላትፎም ቢሆን ብቻ አባቱን ይለምን አባቱ የልጁን ልመና ይሰማል፡፡ እንደፈቃዱም ምላሽ ይሰጠዋል፡፡

ጸሎት ይኸው ብቻ እንጂ የተጻፈውን መድገም አይደለም፡፡ አሕዛብ በመናገራቸው ብዛት የሚሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደእነርሱ በከንቱ አትድገሙ ተብሏልና ውዳሴ ማርያምን በመድገም ጸልየናል ማለት እንደአሕዛብ በከንቱ መድገም ነው፡፡ ደግሞም የጸሎቱ አድራሻ ማርያም እንጂ ጌታ አይደለም፡፡ ስለዚህ አባቶች ሆይ ስሕተትን እያረማችሁ ብትሄዱ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አይደለም፡፡ ስሕተትን አንግሣችሁ እውነትን ብታወግዙ ሰውን እንጂ እግዚአብሔርን ደስ እንዳላሰኛሁ እወቁት፡፡

ይቀጥላል

  

22 comments:

 1. I do not blame our fathers the problem was most of them they do not read properly and alwayes they follow the culture or tradation not clearley understund the BIBLE the problem now is the young generation know how to read and understand but they want continiue the same way.Even if they understand the BIBLE how our LORD JESUS teach the disaple how to pray LUKE 11:1-4. The BIBLE is our gadince to leaern to correcect ourself to open our eyes and our minds so we do not want continue blindely let us open our eyes and mind and read the BIBLE learn from it.There is no one place in the BIBLE that The Lord Jesus mention about to follow his mother or pry to her.Where did all the ethiopian Orthodox prayto Mary came from it is false teaching.Please follow the LOrd prayer.I am sorry if I offend any body.May GOD help us to open our eyes and mind. God bless us all.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Kezih wist Min Asqemetachu Enante Kemtamnubet Bet Lemin Athedum Yesew Ljie Eko Nesa Yehone Mebt Alew Yefelegewum Yemamen Ena Yemamlek. Gin Bezyaw Layim Degmo Yesew Mebtim Endhu Makber Endalebet Gils new. Enam Ye Tewahedo Ljoch Sathonu Yehonachu meslachu Lemin Rasachu Shtachu Tqemetalachu? Tinsh Hlinachu Ayweqsach hum wey? Yeset were Hulye Endhu Endawerachu Menor bcha new yetefeqedelachu? Yesew Ljoch hewot Yemyanis Message Min Ale And qen post Btadergu Abaselamawoch. Hulye Yabatoch Sim Matfat Yebetekiristian Sim Mawared Hez Kehzb Maleyayet Ttachu Min new wede Meshaf Kidus Btmelesu

   Delete
  2. "The problem now is the young generation knows how to read and understand but they want continue the same way"
   You hit it right on the nail brother. The term "ignorance is a bliss" really applies to our young generation. I agree with your input; we shouldn't be bound to manmade tradition and culture. Knowledge is power. The problem is we have knowledge but most of us from adolescence were "intoxicated" with fairy tales and now we want to still keep our old ways & habits. It's like teaching an old dog new tricks. To clean up all the mess, it certainly takes time and we ought to strive and toil to saves souls by the grace of God. But I want to reiterate one main thing you missed. We orthodox Christians don't regard the Virgin Mary (and all the saints) as divine by no means. We ask her (and all the saints) to pray for us because they are alive in heaven. The original definition of pray is to "beseech, ask, or petition" and has nothing to do with worship. So in this sense, asking (praying) to saints to pray (ask) for you before God is not a worship. In fact, scripture tells us it "pleases God". It's the same as asking someone to pray for you on your behalf.
   Romans 15: 30 "I appeal to you, brothers, by our Lord Jesus Christ and by the love of the Spirit, to strive together with me in your prayers to God on my behalf"
   God bless

   Delete
  3. Shame on you. Correct your spelling and grammer first then you will blame the fathers who earned more than one degree as incompetent to read and understand the bible.

   Delete
 2. ena wudase mariam sindegim eko abatachin hoy enilalen jal! tadia yihe tselot ayadergewum????

  ReplyDelete
  Replies
  1. wegen, yetesafewin anbebewital weyest endemeselot meterter new? "Abatachin hoy" yemilew tselot ke wedase mariyam new yetegegnew weyes ke meshaf kidus? mejemeriya astewilu

   Delete
 3. Great Article!

  ReplyDelete
 4. የሚያሳፍር ሲኖዶስና የሊቃውንት ጉባዔ ነው

  ReplyDelete
 5. you are teaching liberalism, the church is preaching religion!

  ReplyDelete
 6. who ever write the article God bless you such a true stetment.Jesus is Lord of Lord.

  ReplyDelete
 7. ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ፣ እግዚአብሔርን ማመስገን መለመን፣ መጠየቅ፣ መማለድ፣ መማፀን ነው፡፡ ጸሎት ከእግዚብሔር ጋር ያለን የመገናኛ ምልክትና የግንኙነታችን ማጽኛ ነው ፡፡ ጸሎት ኀብረትን ፣ ምስጋናን ፣ ስግደትን ፣ ንስሓን ፣ ልመናን ፣ ምልጃን ሁሉ ያጠቃልላል ፡፡

  ጸሎታችን በአጠቃላዩ በሦስት መልክ ይከፈላል፡-
  1. ጸሎተ አኰቴት - እግዚአብሔር ስላደረገልንና ለሌሎች ወገኖችም ስለፈጸመው ሁሉ ምስጋናን ማቅረብ
  2. ጸሎተ ምህላ - እግዚአብሔር እንዲፈጽምልን የምንፈልገለውንና የፈቃዱን መለመን
  3. ጸሎተ አስተብቊዖት - ስለ አንድ ጉዳይ ሱባኤ ገብቶ የእግዚአብሔር ፈቃዱና ኀብረቱን የሚጠጠየቅበት ነው

  የጸሎት ጊዜያታችን
  ቤተ ክርስቲያን በቀን ውስጥ ሰባት ጊዜ መጸለይ እንደሚገባ ወስናለች ፡፡ መዝ 118/119፡164 ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 14 ቁ. 545 ፡፡ ለደንብ ያህል እንዲህ ቢባልም ፣ በተግባር የተለመደው ግን እንደ ጾማችን ሁሉ ፣ አብዝቶ መጸለይም (መወትወት) ጠቃሚ እንደሆነ ትመክራለች ፤ ሕይወታችንንም በሙሉ ከእግዚአብሔር ጋር እንድናቆራኝና የየዕለቱና የየሰዓቱ እያንዳንዱ እርምጃችን በርሱ ፈቃድ ይሆንና ይፈጸም ዘንድ እንድለምን ፣ በየጊዜው እንድንጠይቅም ታስተምራለች ፡፡

  መጪው ጊዜ የጾም ወራት ስለሚሆንና ማወቁና መተግበሩ ስለሚጠቅመን ሰባቱን የየዕለት የጸሎት ጊዜያት እጠቅሳቸዋለሁ ፡፡ (የሰዓት አቆጣጠሩ እንደ አገራችን ነው)
  1. ጸሎተ ነግህ (ጠዋት ከመኝታችን ስንነቃ ፣ ከጠዋቱ 11-12 ሰዓት)
  2. ጸሎተ ሠለስት (ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት)
  3. ጸሎተ ቀትር (ከቀኑ ስድስት ሰዓት)
  4. ጸሎተ ተሰዓተ ሰዓት (ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት)
  5. ጸሎተ ሰርክ (ከቀኑ 11-12 ሰዓት)
  6. ጸሎተ ንዋም (የመኝታ ጊዜ ጸሎት)
  7. ጸሎተ መንፈቀ ሌሊት (የእኩለ ሌሊት ጸሎት)

  የጸሎት ዓይነቶች
  ለየቀኑ የተከፋፈሉ ሁነው አባቶች በየዕለቱ የሚጸልዩአቸው ከአሥራ አምስት በላይ የሚሆኑ የጸሎት ዓይነቶች አሉን ፡፡ እነርሱም የዘወትር ጸሎት ፣ ውዳሴ ማርያም ፣ ይዌድስዋ መላእክት ፣ አባታችን ሆይ ፣ አንቀጸ ብርሃን ፣ ውዳሴ አምላክ ፣ የሙሴ ጸሎት ፣ የሃና ጸሎት ፣ የሕዝቅያስ ጸሎት ፣ የምናሴ ጸሎት ፣ የዳንኤል ጸሎት ፣ መዝሙረ ዳዊት ፣ የእንባቆም ጸሎት ፣ የእመቤታችን ጸሎት ፣ የዘካርያስ ጸሎት ፣ የስምዖን ጸሎት ፣ እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ ናቸው ፡፡
  ዝርዝር የየዕለት ክፍፍሉንም በድረ ገጽ መፈለግና መመልከት ይቻላል ፡፡

  - ከነዚህ ውስጥ ጸሃፊው ያተኰረው ሙሉ ቀኑን ስንጸልይ የምንውለው አንድ ውዳሴ ማርያምን ብቻ ይመስል የተቸው በቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና የተሰየመውን ነው ፡፡ ምክንያት ምን ይሆን ብባል እኛ ኢትዮጵያውያኖች የድንግልን ማርያምን አማላጅነት ፣ ከሌሎች አብልጠን ስለምናምን ፣ ያንን እምነት ለመገዝገዝ ወይም ለመሸርሸር በማቀድ የፈጸመው መስሎኛል ፡፡

  እኔ በራሴ የመሃይም ዕውቀት የሚሰማኝን ሳይሆን በብዙዎቻችን ዘንድ በወንጌል አርበኝነት የሚታወቁት አባ ወልደ ትንሣኤ ፣ በትምህርታቸው መሃል ስለ ውዳሴ ማርያም ምንነት የመሰከሩትን ብቻ ቃል በቃል እጠቅሳለሁ ፡፡ “ውዳሴ ማርያም ማለት ለአስተዋለው ሰው የተተረጐመ ወንጌል ማለት ነው ፡፡ ውዳሴ ማርያም ማለት ከሌሎቹ ሁሉ ጸሎቶች የተለየ ፣ የተተረጐመ ወንጌል ማለት ነው ለሚገባው ሰው ፤ እንዲያው ዝም ብሎ በልማድ ብቻ ለሚያስብ ግን ውዳሴ ማርያምን የሚንቁም አሉ ፤ ግን የተተረጐመ ወንጌል ነው ፡፡” ብለው ነበር ፡፡
  … ይቆየን

  ReplyDelete
 8. ክፍል ሁለት
  - ሌላው “ጸሎት ወደሌላ ፍጡር አይቀርብም፤ ወደእግዚአብሔር ብቻ ነው የሚቀርበው፡፡” የተባለው የቅዱሳንንና የጻድቃንን አማላጅነት ለመሞገት የቀረበ ሥውር ቃል ነው ፡፡ እኛ ግን አባቶች እንዳስተማሩን አማልዱን ፣ ተራዱን ብለን ለቅዱሳንና ለጻድቃንም ሁሉ እንጸልያለን ፡፡ ፈራጁን አምላክ አማላጅ የሚሉ ወገኖች ግን ይህን ሃቅ ለመቃወም የተለያየ ስልትና ዘዴ ፈጥረው ዛሬም ይሞክሩናል ፡፡

  - ጸሐፊው “አንዳንዶች በውዳሴ ማርያም የምንጸልየው ወደ እግዚአብሔር እኮ ነው ቢሉም ማርያምን እያወደሱ ወደእግዚአብሔር ሊጸልዩ አይችሉም እንላለን፡፡ ለአበበ እየተናገሩ ሰማህ ከበደ ለአንተ እኮ ነው እያወራሁ ያለሁት እንደማለት ነውና፡፡” የሚለውን ሳነበው ለራሴ አዘንኩ ፡፡ ንጽጽርና ሊያመሳስሉት የማይገባውን ፈጣሪ ከአንድ አበበና ከበደ ግለሰብ ችሎታ ጋር አወዳድሮ ፣ የምንጸልየውን አይረዳውም እያለን ነው ፡፡ እግዚአብሔር ኩላሊትና ልብን ይመረምራል (መዝ 7፡9 ፤ ኤር 2ዐ፡12) የተባለውን የአምላክ ክህሎቱን መካድ ካልሆነ በስተቀር ጸሎታችን በስሙ ካልሆነ አይረዳውም ማለት ስህተት ነው ፡፡ በዚህ ዓለም አካሄዳቸውን ከርሱ ጋር ያደረጉ ቅዱሳንና ጻድቃን ሁሉ ፣ ከርሱ ተለይተው አይኖሩምና ጸሎታችንን በየትኛውም መንገድ ብናደርገው ርሱ በዋናነት ይመለከተዋል ፡፡

  በንባብ ካገኘሁት ጠቃሚ ቃልም ለማካፈል ፡፡
  ከላይ እንደተዘረዘረው ብዙ መጽሐፍትን ለማንበብና ለመጸለይ ለማንችል ወገኖች ፣ አንዳንድ አባቶች የሚከተለውን ሥርዓት ይመክራሉ ፡፡ “አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ ሃይማኖት፣ ሰላም ለኪ /ስለ ውዳሴ ማርያም ፈንታ/፣ አቡነ ዘመሰማያት፣ አንድ ከመዝሙረ ዳዊት /መዝሙር 150/ በመዝሙረ ዳዊት ፈንታ/ በመጨረሻም አቡነ ዘበሰማያት ማድረስ ብንችል መልካም ነው ። ጸሎተ ሃይማኖት የህይማኖት መግለጫ በመሆኑ እንጸልየዋለን። በመካከል ሰላም ለኪ በመድገማችንም የውዳሴ ማርያም በረከት ይደርሰናል። መዝሙረ ዳዊት 150 ስናደርስ ደግሞ ሁሉንም መዝሙራት የደገምን ያህል ይሆንልንና የዳዊቱን በረከት እናገኛለን፡፡ ይህንን ሁሉ ማድረስ ካልተቻለን ግን ቢያንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን አቡነ ዘበሰማያት ብለን ከቤታችን ልንወጣ ይገባናል። አጭር ጸሎት ከሥፍራ ሥፍራ ሊለያይ ይችላል፡;ዘጠኝ ሰላም ለኪ፣ አስራ ሁለት አቡነ ዘበሰማያት በገዳማት ያሉ አበው ያደርሳሉ።”

  በጊዜ እጥረት ተሳቦ “በየእለቱ አንድ አቡነ ዘበሰማያት ብቻ መድገም ግን ከስንፍና እንዳይሆን” ፍርሃታቸውንም ይገልጻሉ ፡፡

  “ጸሎት ስናደርስ የጸሎታችን መነሻ (መጀመሪያ) አቡነ ዘበሰማያት ነው፡፡ በመካከል ጸሎት አቋርጠን (ስለ አስቸኳይ ነገር) ከሰው የምንነጋገርበት ጉዳይ ቢገጥመን በአቡነ ዘበሰማያት ማሰር ተገቢ ነው፡፡ በአቡነ ዘበሰማያት አስረን የገጠመንን ጉዳይ ፈፅመን እንመለሳለን፡፡ ከዚያም አቡነ ዘበሰማያት ብለን ካቆምንበት እንቀጥላለን። ጸሎታችንን በአቡነ ዘበሰማያት ሳናስር በመሃል እንዳሻን እንዳናቋርጥ አበው ያስተምሩናል፡፡

  የመዝሙረ ዳዊትን በተመለከተ የሚመከረው ሌላው አማራጭ አጭር ጸሎት ደግሞ ለዕለቱ የተመደቡትን የጸሎት መዝሙሮች በችግር ምክንያት መጸለይ ካልቻልን ቢያንስ አንድ ንጉሥ (አሥር መዝሙሮችን) ማድረስ እንደሚገባ መምከራቸው ነው ፡፡

  ከጸሐፊአችን ቃልም “ጸሎት ከልብ የሚመነጭ የሕይወት ጭማቂ እንጂ በጽሑፍ የሚቀርብ ማመልከቻ አይደለም፡፡ ልጅ አባቱን በሚችለው ቋንቋ እንደችሎታው ተናግሮ ይለምነዋል እንጂ በማመልከቻ አይጠይቀውም፡፡ አባቱም የልጁን ጥያቄ እንጂ ጥያቄው የቀረበበትን የቋንቋ ውበት አይመለከትም፡፡ ተኮላትፎም ቢሆን ብቻ አባቱን ይለምን አባቱ የልጁን ልመና ይሰማል፡፡ እንደፈቃዱም ምላሽ ይሰጠዋል፡፡” የሚለው ጠቃሚ ቃል ነው ፡፡ እግዚአብሔር የቋንቋ ብልሃታችንንና የሃይማኖት ዕውቀት ሊቅነታችንን በጸሎታችን ውስጥ አካትቶ አይመዝነውም ፡፡ መሃይሟ እናቴ በእምነት ከእኔ የጠነከረች ነገር ግን በወንጌል ማነብነብ የኔን ቁራጭ የማትሆነው በጸሎቷ ከእኔ የተሻለ እንደምትሆን አምናለሁ ፡፡
  መልካም ንባብ
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 9. ቃለ ህይዎት ያሰማልን ምእመን!!! እግዚአብሔር በጤና ይጠብቅልን::

  ReplyDelete
 10. “አባታችን ሆይ ብላችሁ ጸለዩ ነው ያለው ሉቃስ 11፡1-4፡፡ ለዚያውም አመቤታችን ሆይ የሌለውን አባታችን ሆይ እንደ ሆነ ልብ እንበል፡፡…..”ለሚለዉ

  ሰላም ላንተ ይሁን::ቦታዉ አንድ ላይ ባይሆንም (ጥቅሱ ያለበት ለማለት ነዉ) ይህም ጽሎት እኮ ነዉ::አሁን ጥያቄው ይጨመር አይጨምር ሳይሆን መሆን ያለበት ፍጽም መጽሃፍ ቅዱሳዊ ነዉ ዎይ ነዉ::ይህ ደግሞ ቅዱሳን አባቶች በምንፈስ ተመርተዉ ያስተላለፍልን ጽሎት ነዉ::አሁን እስቲ ምጽሃፍ ቅዱሳዊ መሆኑን እንምልከት :-
  “እመቤቴ ቅድስት ማርያም ሆይ በመላኩ
  በቅዱስ ገብዔል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ
  በሃሳብሽም ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል
  ነሽ ያሸናፊ የ እግዚአብሔር እናት ሆይ
  ላንችቺ ሰላምታ ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ
  ተልይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽ
  ፍሬ የተባረከ ነዉ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ
  ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነዉና
  ከተዎደደዉ ልጅሽ ከጌታችን ከመድሃኒታችን
  ከእየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን
  ሃጥያታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ ለዘለአለሙ አሜን::”
  +++ይህ ሁሉ ቃል በቃል ከመጽሃፍ ቅዱስ የተገለበጠ ነዉ:-
  ”መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።”ሉቃ.1:27
  ሉቃ.1:41-42
  41 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥
  42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

  አሁን ከላይ ያየነዉ ጸሎት ሙሉ በሙሉ በዚህ 3 ጥቅሶች ዉስጥ ያሉ ናቸዉ::ታዲያ ፍጽም መጽሃፍ ቅዱሳዊ ከሆነ ችግሩ ምን ላይ ነዉ???ምስጋና እንደሚያስፈልጋት ደግሞ ገብርዔል ከሰማይ ኤልሳቤጥ ከምድር ምስክር ናቸዉ::ከላይ ያየነዉ ጸሎት በራሱ ምስጋና ስለሆነ:: በትዉልድ ሁሉ እንደምትመሰግን እራሱዋ ነግራናለች::”እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል”ሉቃ.1:48:: ይህ ቃል ድንግል ማርያም ምስጋና እንደሚገባት በግልፅ ቃል ይነግረናል::ለዚያ ነዉ የምናመሰግናትም::እመቤታችን የከበረች ፍጡር ናት::አንዳንዶች ማርያም ፍጡር ናትና ለፍጡር ድግሞ ምስጋና አንሰጥም ይላሉ::መፅሐፍ ቅዱስ ግን ይህን ሃሳባቸውን ከንቱ ያደረግባቸዋል::በመዝሙር 32:1 ላይ እንዲህ ብሎ ቃሉ ይንግረናል :- <>::ሳጠቃልልህ ዋናው መጽሃፍ ቅዱሳዊ መሆኑ ነዉ::በተረፈ እባካችሁ አሁን ለይቶላችኀልና እዚያዉ ሉተሪያዋኑን ብትቀላቀሉ መልእክቴ ነዉ::::አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
 11. My friend, first distinguish between ''tselot'' and ''mesgana''. Awo emebatachin mesgana yegebatal getan seleweledech, kidest selehonech, Ye melekot maderiya selehonech. Gen mesganana tselot leyunet alew. ''abatachin hoy'' yemilew kal be kal tselot new. Gen ''emebatachin hoy'' yemilew beminim mekniyat tselot libal aychilim. mesgana endehone gin minim tirtir yelegnim. mecheresha lay ''ke getachin ke medhanitachin ke eyesus kristos zend yekiran lemegnilin'' yemilew becha new tselot. Meshaf kidusawi lemehonu menim tirtir yelewim. Gin meshaf kidusawi hone malet tselot new ayasbilewim. Selezih eyastewalu yenageru

  ReplyDelete
 12. ድንግል በሥጋ ወድንግል በህሊና የሆነችውን ፥ ቅድስት፥ ወላዲት አምላክን ምሥጋና አይገባትም የሚል ሰው በምንም መመዘኛ ክርስቲያን ነው ሊባል አይገባውም። አምላክ እራሱ ከሴቶች ሁሉ እርሷን መርጦ 9 ወር ከ5 ቀን በማሕፀኗ አድሮ እናቱ ያደረጋትን እመ-ቤት የሚቃልል የልጇ ወዳጅ ከቶውንም ሊሆን አይችልም! ፀረ ማርያም ማለት ፀረ አማኑኤል ማለት ነው ፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ለወላዲት አምላክ ከአምልኮት በስተቀር ሁሉንም አይነት ምሥጋና ይገባታል ብለው ያምናሉ ፤ እግዚአብሔር ይመስገን እኔም አንዱ ነኝ። በአማልጅነቷም በጽናት እናምናለን!

  ReplyDelete
 13. The problem is Jesus say” I am the only way the truth and the light.” And we have to pray to him to him alone what is the hard thing to understand. It is better to pray to the father GOD in Jesus name. There is no place that Jesus tells his disciple to pray to the Angel or Mary. We as a Christian know Mary we have to honor her and respect her. But if Jesus says he is the only way why we do not obey his commandments?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከላይ የጽሁፉ አቅራቢ የፈጸሙትን ዓይነት የስያሜ ግድፈት (በመጨረሻ ለማስረጃ አቅርቤዋለሁ) እዚህም "We as a Christian know Mary" እና "honor her and respect her." በማለት ስለተደገመ ፣ በቀልድ እንዳንለማመደው ለመማማር ያህል ይህን አስተያየት ለመጻፍ ተነሳሁ ፡፡

   አንዳንዶቻችን ሥራዬ ብለን ባናተኩርበትና ባንጠነቀቅም ቢያንስ ከስሟ ቀደም ብሎ የሚጻፍ ፣ ሊነጠል የማይገባው (ቅድስት - Saint ፣ ድንግል - Virgin ፣ ሲሆን በአንድነት ቅድስት ድንግል ወይም የጌታ እናት - mother of Jesus) የሚሉ በቤተ ክርስቲያንና በክርስቲያን ወገኖች ዘንድ የምትታወቅበትና የምትለይበት የስም ማዕረግ አላት ፡፡ ለእኔ ርሷን ማክበር ማለት ከዚህ ይጀምራል ፡፡ መልአኩ አክብሮ በሚያስደነግጥ ሰላምታ ያበሠራትን የጌታችንን እናት እኛ በንግግራችንም ሆነ በጽሁፋችን ሳናስበው ልናቃልላት አይገባም ፡፡ አንዳንድ ጐበዝ ደፋሮች መጽሐፍን በመረዳት ችግር ፣ ከዕጮኛዋ ተዳራች ፣ ተዋለደች ማለትን አልፈው ፣ አሁን አሁን ደግሞ “እህታችን ማርያም” ሲሉም ሰምቻለሁ ፡፡ ይኸኛውም ጉዞ ወደዚያው እንዳያመራ ስለፈራሁ እንድናርመው በመፈልግ እንደ አስተያየት አነሳሁት ፡፡

   ጸሐፊው በነጠላ ያስቀመጧቸው አስረጅ ቃሎች ፡-
   - “… አብዛኛው ክፍል ግን ማርያምን ነው የሚያወድሰው፡፡”
   - “… ቢሉም ማርያምን እያወደሱ ወደ እግዚአብሔር ሊጸልዩ አይችሉም እንላለን፡፡”
   - “… እርግጠኛ እንሁን ይህ እመቤታችንን መናቅ አይደለም፡፡” (መካሻ ብየዋለሁ)
   - “… ከራሳችን ጨምረን ማርያምን እናከብራታለን ማለትም ዘበት ነው፡፡”

   አንድ የታወቁ የአባ ሰላማ ብሎግ ከታቢ “ውዳሴ ማርያም የተባለው መጽሐፍ የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ድርሰት ነው። በዚህ ድርሰት ውስጥ ምስጢረ ሥላሴን፣ ምሥጢረ ሥጋዌን በጠቅላላው ነገረ መለኮትን ልንማርበት እንችላለን። ድርሰቱ ድንግል ማርያም ከጌታ የተሰጣትን ክብር በማድነቅ ጠለቅ ያለ ሥነ መለኮታዊ ምስጢር ያስተምራል። ውዳሴ ማርያም ከሚለው ስያሜ ይልቅ ነገረ መለኮት የሚል ስያሜ ቢሰጠው ለያዘው ሐሳብ በጣም ቅርብ ይሆናል። ቅዱስ ኤፍሬም ይህን ድርሰት ሲደርስ በራሱ ነገረ መለኮትን መተርጎሙ ስለሆነ የቅዱስ ኤፍሬም ሥነ መለኮት ትርጉም ሊባልም ይችላል።” በማለት በዚሁ ብሎግ ቀደም ብለው ጽፈዋል ፡፡ ርሳቸው የማይስማሙበት ሊቃውንቱ የሚጠቀሙበትን የትርጉም መጽሐፍ ስለሆነ ምንም አልልም ፡፡ የዛሬው ጸሃፊ ግን ይኸን ከቤቱ ያለውን መግለጫ እንኳን ሳይመረምር ነው ማርያም የምትወደስበት የጸሎት መጽሐፍ ነው በማለት የደመደመና ለመቃወም የሞከረው ፡፡

   ምናልባት ይኸን መጽሐፍ የመጠቀም ወይም የመፈተሽ ዕድሉ ከሌለ ፣ የቅዱስ ኤፍሬም የጸሎት መጽሐፍ ዋና መልዕክት እኚህ የዚህ ብሎግ ታዋቂ ጸሃፊ እንደገለጹት ሆኖ ፣ በእያንዳንዱ ማሳረጊያ ላይ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” ማለትም “ቅድስት ሆይ ለምኝልን” የሚል የተማጽኖ ቃል ያስገባል ፡፡ ይህም ርሷን በአማላጅነቷ አብሮ ተጠቀመበት እንጅ ሌላ በመስቀል የሞተልንን አዳኝ የሚተካና የሚያሳንስ መልዕክት አልገለጸበትም ፡፡

   በተረፈ ጥቂት የጸሎት መጽሐፍትን ለማግኘት ሊያገለግሉ ስለሚችሉ የሚከተሉትን አዳራሻዎች ፈልጌ አምጥቻለሁ ፡፡ መጽሐፍቱን የማየት ዕድሉ ያልነበራችሁም በመፈተሽ ሰበብ ብታነቧቸው ለወራቱ ተስማሚ ናቸውና ተጠቀሙበት ፡

   1. ለየዕለቱ የተከፋፈለው የሳምንቱ ጸሎት ዝርዝር
   - http://sfikirbet.wordpress.com/tselot/
   - http://tewahedo.org/yesamentutselote.pdf

   የተወሰኑ የጸሎት መጽሐፍትን ለማግኘት
   1. ውዳሴ ማርያም ፣ አንቀጸ ብርሃንና ይዌድስዋ መላእክት በግዕዝና አማርኛ
   - http://sfikirbet.files.wordpress.com/2011/12/wedase_meriyam-geez-amh.pdf

   2. የነቢያት ጸሎት በአማርኛ
   http://sfikirbet.files.wordpress.com/2009/06/tslote-nebyat.pdf

   መልካም የጸሎትና የጾም ወራት

   Delete
  2. አሜን !!!እናምሰግናለን ምእመን !!!

   Delete
 14. የተፈጠረ ፍጡር ትልቁን ፈጣሪ የሆነውን አየሱስ ኣይከልልብህ

  ReplyDelete
 15. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete