Thursday, March 28, 2013

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 12

በግንቦት 15/2004 «ውግዘት» ስማቸው ከተካተተው መካከል «የእውነት ቃል አገልግሎት» አንዱ ነው፡፡ በዚህ አገልግሎት ላይ የግንቦቱ ሲኖዶስ ቃለ ጉባኤው ያሰፈረው «ኑፋቄ» ብሎ ያቀረባቸው ነጥቦች የሚከተሉት ሲሆኑ መጽሐፍ ቅዱስንና መሰረት አድርገን ኑፋቄ የተባሉት ነጥቦች ኑፋቄ መሆን አለመሆናቸውን እንመረምራለን።


«ሀ. ወልድና መንፈስ ቅዱስ አማላጆች ናቸው ይላል» በማለት ጽፏል፡፡የእውነት ቃል መጽሔት 2001 ዓ.ም እትም  ቅጽ 5 ቁጥር 22»

በአማላጅነት ዙሪያ ቤተ ክርስቲያናችን የምታራምደው አቋም ከመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ፈጽሞ የራቀና በሰው ሐሳብ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ምንም እንኳን «ወልድና መንፈስ ቅዱስ አማላጆች ናቸው» የሚለው አነጋገር «አማላጆች ቅዱሳን እንጂ ኢየሱስ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ አይደሉም» ተብሎ ሲነገረው ለኖረ ህዝብ የሚከብድ መስሎ ቢታይም ወልድና መንፈስ ቅዱስ አማላጆች የተባሉበትን ምክንያት ከመጽሐፍ ቅዱስ መመልከቱ ተገቢ ነው እንጂ እርሱን ሳያገናዝቡ ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ማውገዝ የክርስቶስ ነኝ ከምትል ቤተክርስቲያን ከቶ አይጠበቅም፡፡
 
ኢየሱስ ሰው ሆኖ የመጣው በሞቱ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ነው፡፡ ይህንንም በዚህ ምድር ላይ እያለ በመጸለይና አንድ ጊዜ በመሞት ፈጽሞታል፡፡ አንድ ጊዜ የፈጸመው የማስታረቅ ስራ እስከዘላለም ያገለግላልና በእርሱ በኩል አምነው የሚመጡት ሁሉ ይታረቁበታል፡፡ ይህም በስሙ በመጸለይ የሚከናወን እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ጌታም በስሜ ብትለምኑ አብ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል ብሏል፡፡ «በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። … በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤ እናንተ ስለ ወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋልና።» ዮሐንስ 16፡23-24፡26-27፡፡ ስለዚህ የክርስቶስ ምልጃ የምንለው በስሙ የምናቀርበውን ልመና ነው እንጂ ዛሬ በክርስቶስ ስም ስንለምን እርሱ በዚህ ምድር ሳለ ያደርግ እንደነበረው እየወደቀ እየተነሳ አብን ይለምነዋል ማለት እንዳልሆነ መገንዘብ አለብን፡፡ መንገዱ እኔ ነኝ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ ሊመጣ አይችልም የሚለው ቃልም ያለእርሱ ድኅነትን ማግኘት፣ ወደእግዚአብሔር መድረስም ሆነ ጸሎትና ልመና ማቅረብ የማንችል መሆኑን ያሳያል፡፡ ዮሐንስ 14፡6፡፡

እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ በልጁ በኩል ስለፈጸመና ሰውና እግዚአብሔር በመካከለኛነቱ ስለታረቁ ሌላ ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት መንገድ የለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው መካከለኛ አንድ እርሱም ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ያስተምራል፡፡ 1ጢሞቴዎስ 2፡5-6፡፡ ከዚህ ውጪ ሌሎችን መካከለኛ አድርጎ ማቆም የእግዚአብሔርን አሰራር መቃወም ነው የሚሆነው፡፡ ቅዱሳን በዚህ ምድር ይማልዱ የነበረው፣ ወደእግዚአብሔርም ይቀርቡ የነበረው እግዚአብሔር በሰጣቸው ሞገስ እና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንጂ በራሳቸው አልነበረም፡፡ በተለይም በሀዲስ ኪዳን በኢየሱስ መካከለኛነት በኩል ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት ያስነብበናል፡፡ ጸሎትን ምስጋናን ልመናን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንዲቀርቡ የታዘዘውም ከላይ የተመለከትነውን የጌታችንን ትምህርት መሰረት በማድረግ ነው፡፡
·        «እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማች አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።» ሮሜ 1፡8
·        «ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።» (ሮሜ 5፡11)
·        «በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።» (ሮሜ 7፡25)
·        «እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥ ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።» (ሮሜ 16፡25-27)
·        «ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።» (ኤፌ. 5፡20)
እነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ምስጋና ምልጃና ልመና ማቅረብ እንዳለብን የሚያስተምሩ ናቸው፡፡ የኢየሱስ መካከለኛነትም የሚገለጠው በዚህ  መንገድ ነው፡፡

ስለመንፈስ ቅዱስ ምልጃ የተጻፈው በሮሜ መልእክት ምእራፍ 8 ቁጥር 26 - 27 ላይ ነው «እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤  ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።» ይህ ክፍል እንደሚገባን መጸለይ የማንችለውን መንፈስ ቅዱስ ድካማችንን በማገዝና በመርዳት እንደሚማልድልን ያስረዳል፡፡ እኛን ለመርዳትም መንፈስ ቅዱስ ሊነገር በማይቻል መቃተት እንደእግዚአብሔር ፈቃድ ይማልድልናል፡፡

መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ ወደሰማይ ማረግ በኋላ ወደዚህ ምድር የመጣው ኢየሱስን ተክቶ ቤተክርስቲያንን ለመምራት ቅዱሳንን ለማገዝና ለመርዳት ነውና በማይነገር መቃተት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለቅዱሳን ይማልዳል ቢባል ትክክል ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሚመሰክረው ይህንኑ ነውና፡፡ ይህን እውነት መቀበል ከእኛ የኖረ ልማድ ጋር ስለማይስማማና እኛ በፈቃዳችን አማላጆች አድርገን ያስቀመጥናቸው ያንቀላፉ ቅዱሳን ስራ የሚፈቱና ስፍራ የሚያጡ ስለሚመስለን ግን የመንፈስ ቅዱስን ምልጃ እናስተባብላለን፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ለማረም ከመሞከር ይልቅ የራሳችንን የተሳሳተ አስተምህሮ ብናስተካከል አይሻለንምን? ሲኖዶስ ይህን እውነት ያወገዘው ሐሰትን ለማንገስ ፈልጎ እንጂ ሌላ ምክንያት አይኖረውም፡፡ ለራስ ወግና ልማድ ሲባል መጽሐፍ ቅዱስን ከማረም ይልቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ወግና ልማድን ማረም ከሲኖዶስ ይጠበቅ ነበር፡፡ ነገር ግን አልሆነም፡፡    

«ለ. በሰው ሥርዓት የተመሰረቱት ሰባቱን አጽዋማት በመጾም ለጌታ የሚቀርብ አምልኮ ከንቱ አምልኮ ነው፡፡» በማለት በእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ በተመሰረቱት አጽዋማት የምናቀርበውንና የምንፈጽመውን ሥርዓተ አምልኮ ከንቱ በማለት ዋጋ እንደሌለው አድርጎ ያጣጥላል፡፡ የእውነት ቃል መጽሔት መስከረም 1995 ዓ.ም እትም»

ጾም ሰው ራሱን አዋርዶ ወደአምላኩ ለመጸለይ ሲፈልግ የሚያከናውነው የመንፈሳዊ አምልኮ ክፍል ነው፡፡ ሰው የሚጾመው ራሱን በአምላኩ ፊት ለማዋረድና የእርሱን ረድኤት ለመፈለግ ነው እንጂ ያለፈና በተለይም ደግሞ ከእርሱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለውን ታሪክ ለመዘከር መሆን የለበትም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እንድንጾም ታዘናል፡፡ ነገር ግን ሰባት አጽዋማት ተቆጥረው አልተሰጡንም፡፡ መጾም ያለብንም የራሳችንን ጾም እንጂ ሌሎች የጾሙትን ደግመን እንድንጾም አልታዘዝንም፡፡ ከዚህ አንጻር ሰባቱ አጽዋማት ቤተክርስቲያናችን የደነገገችው እንጂ ሲኖዶሱ እንዳለው «በእግዚአብሄር ፈቃድና ትእዛዝ» የተመሰረቱ ለመሆናቸው አንድም ማስረጃ ማቅረብ አይችልም፡፡

ታላቁን የጌታን ጾም ጨምሮ ሌሎቹም አጽዋማት ታሪክን መዘከሪያ እንጂ የእኛ ጾም አይደሉም፡፡ ሰባቱ አጽዋማት ሌሎች በራሳቸው ምክንያት የጾሟቸው ስለሆኑ የእኛ ሆነው መቆጠር አይገባቸውም፡፡ እኛ መጾም ያለብን የራሳችንን ጾም ነው፡፡ የራሳችንን ጾም በግልም ሆነ በማህበር መጾም ይገባናል፡፡ ይህም ጊዜ ጠብቀን፣ ጾም ገባ ጾም ወጣ በሚል የምግብ ለውጥ በማድረግ ብቻ ሳይሆን ልዩ ልዩ ጉዳዮች በገጠሙንና የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ በሚገባን ጊዜ ሁሉ በየጊዜው እየጾምን ልንጸለይ ይገባል፡፡ ሰባቱን አጽዋማት መሠረት ያደረገው አምልኮአችን ብዙ የሚጎድሉት መንፈሳዊ ነገሮች የሉትምን? በጾም ወራት የምግብ ለውጥ ከማድረግ በቀር ብዙው ሰው መች ይጸልያል? ደግሞስ በቅበላውና በፋሲካው ስለሚበላው ስጋና ስለሚጠጣው የአልኮል መጠጥ፣ ስለሚረግጠው ዳንኪራ እንጂ በጾሙ ወራት ስለሚያከናውነው መንፈሳዊ ተግባር መቼ ያስባል? ለዚያስ መቼ ራሱን ያዘጋጃል? በዚሁ በሰው ስርአት በተመሰረተ ጾም የራሱን ጾም መጾም ትቶ ሌሎችን በጾም በሉ ብሎ የሚከስና የሚሰልል አይደለምን? ታዲያ ይህ በሰው ስርአት እየተፈጸመ ያለ አምልኮ ከንቱ አይደለም ማለት ይቻላል? ስለዚህ በሰው ስርአት የተመሰረተውንና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይስማማውን ስርአታችንን ሁሉ ቆም ብለን ልንፈትሽ ይገባል እንጂ በሆነው ባልሆነው የውግዘት ሰይፋችንን መምዘዝ የለብንም፡፡

ይቀጥላል     


14 comments:

 1. ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካችንና አባታችን ነው ሰባቱን አጽዋማት ጠብቀን፣ራሱን አዋርዶ በመጸለይ በስርአት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን አምልኮ ለመኖር እግዚአብሔር ይርዳን የቅዱሳን ምልጃ አይለየን

  ReplyDelete
 2. Abatoch bereba barebaw tinsh neger hulu Yewugzet seyf memzez yelbachewum bemstewal megaz elebachewu

  ReplyDelete
 3. ያባ ሰላማ ታሪክ ዘጋቢ እንዲያ ነው ልክ ልኩን መንገር ቢሰማ ባይሰማ ንግር ወኢታርምም!
  ሰው የሚወደው ሰው ሠራሽ የሆነውን እንጂ ቁምነግሩን መች ያስወድደዋል አይጣል ነው፤
  ከእግዜር ሳይሆን ከሰው ምስጋና የሚፈልግ ወልገድጋዳ ትውልድ ለማውገዝ ባድ ዘመድ አይለይም
  ዮሓ 5.44-45 ሾላ በድፍኑ እንዲያው ቅዱስ እንዲያው ጻድቅ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ‹‹ሊበሉ ያሰቧትን አሞራ ዶሮ ናት ይሏታል›› ሆዳቸው አምላካቸው ነው ተብሎ አንዴ ተጽፎላችኋል

   Delete
 4. Valuable info. Fortunate me I found your web site by chance, and
  I'm shocked why this accident did not came about earlier! I bookmarked it.

  my blog post: kredit ohne schufa ohne bonität

  ReplyDelete
 5. Hurrah, that's what I was looking for, what a material! existing here at this website, thanks admin of this website.

  Here is my homepage ... seo experts london

  ReplyDelete
 6. What a beautiful article! Please teach us more and more. All our life was following the tradition and culture of Ethiopian orthodox religion. We thank God now they are people understand the bible clearly so we get a chance to learn the truth meaning of the bible. Thank you! Thank you! God bless you richly. Please do not stop writing; you are helping a lot of us.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Abet abet whats is the beauty of this article. I am sure you are penete and that is why you think this article is valuable since it is out of orto.teaching and near to yours. that is why we chase tehadiso that is why we say they are anti-chruch....that is why we say they should we washed from the chruch......

   Delete
 7. If this is Tahedeso's teaching so be it. An excellent piece of work. Simple and to the point. Honestly I was detestful on other guys work of clarity. Please bring it on this kind od discussions.

  ReplyDelete
 8. For the person wrote April 1, 2013 at 9:38pm.”Abet abet what is the beauty of the article”? To begin with who are you to tell anybody what is the beauty of the article? Do you know everybody have a right to like article or not to like? Second “that why we chase theadiso”. Who do you think you are? To chase theadiso and who is theadiso? If anybody teaching from the bible is that what you call anybody? I thought Theadiso teaching is wrong teaching? Now you are telling me the the people who teach from the Bible which is the right Gospel of Jesus Christ are Theodiso? “They should be washed from the church.” From which church? Or whose church? Who are you? It is Ethiopian church so everyone have a choice if you do not like the perfect and right teaching you have a choice to leave yourself. But in any circumstance you have no any right to chase or washed anybody. God have mercy on you. It is ok to learn from the bible that is our foundation and the truth doctrine. Take advantage to know to learn and to be saved and to have eternal life. The bible clearly teaches you if you read it right. Please read your bible. May God richly bless you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. They are modern day sheeps. We should pray for them so God may open their heart

   Delete
  2. Man @ April 1, 2013 at 4:21 P.M, thank you for the note. You said a lot but let me pick few. "From which church? Or whose church?", my answer is very short, the should be washed from orthodox tewahdo church. Why because, the chruch is not for all it is for those who respect its rule and regulation, it is not for those who doesn't know rules, so that who dance, jump, fail, speaks odds etc..all on behalf of Jesus (though I don't agree at all). As you wrongly said, Ethiopian ortodox church is not for all, especially who have hidden ajenda under umberela of gospel. "But in any circumstance you have no any right to chase or washed anybody", of course we have! those who are within but with hidden ajenda are being washed and that will continue. Didn't you hear what happen to Ashenafi and many other that I may bore if I list all here? Didn't you? the same will be done on others. It is possible and should be! You said "you have no right" but I tell you it is right and shall continue. If you say the church is wrong and should be reformed (tehadiso), what are you doing under the Church? go and find your right church. It is ok to learn bible but it should not be the way that tehadiso or protestant interpreted it. You are working to create useless people with no moral and tradition ...just to rehearse the name jesus here and there...But I tell you that is not enough....I hope you know what is happening in Europe and America!! Selam!

   Delete
 9. really a very nice and valuable lesson. pls keep up of posting this kind of true lessons.

  ReplyDelete
 10. haymanotegna hono behassetna betradition kemenor ewinetin awiko medan yishalal.

  ReplyDelete