Tuesday, March 5, 2013

ክሽፈት እንደ ማኅበረ ቅዱሳን በ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ

(ይህችን ጽሁፍ ለአንባቢ እንድትመች ከፓትርያርክ በዓለ ሲመቱ ዜና ለይተን ለብቻዋ አስቀምጠናል)
“ክሽፈት” የሚለው ሰሞነኛ ቃል የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መጽሐፍ ርዕስ ሆኖ በየጋዜጣውና በየመጽሔቱ ትልቅ የመወያያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ መጽሐፉ በኢትዮጵያ ያልከሸፈ ነገር የለም፤ ያልከሸፈ ነገር ቢኖር ኢትዮጵያውያን ለውጭ ወራሪዎች ያላቸው የጋራ አቋም ወይም ኢትዮጵያዊ ወኔ ብቻ ነው ይላል፡፡  እኛም ክሽፈት በሚለው ቃል ማኅበረ ቅዱሳንን መፈተሽ ወደድን፡፡ ከአቡነ ጳውሎስ ህልፈት በኋላና ከምርጫው ጋር በተያያዘ ሁሉም ከሽፎበት ያልከሸፈበት አንድ ነገር ብቻ የቀረ ይመስለናል፡፡ እርሱም በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ኮታ ማግኘቱና በባያብል ሙላት መወከሉ ብቻ ነው፡፡ ክሽፈቶቹ ምን ምን ናቸው? ለሚል ጠያቂ እነሆ ክሽፈቶቹ፦

ክሽፈት አንድ
ያገለግሉኛል ይተባበሩኛል ይረዱኛል ብሎ ተሯሩጦ አቃቤ መንበር ያደረጋቸው ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ባልተጠበቀ ሁኔታ ፊታቸውን ገና ከማለዳው ነበር ያዞሩበት፡፡ በዚህ ምክንያት አቃቤ መንበሩን መለወጥ አለብን ለማለት የዳዳቸው እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡

ክሽፈት ሁለት
ለእርሱ በሚመች መልኩ የምርጫ መስፈርት አውጥቶ ለደጋፊዎቹ ጳጳሳት ቢሰጥም ውድቅ ተደረገበት፡፡ ለምሳሌ፦
·        የዜግነት ጉዳይ (ይህ ደንብ አቡነ ማትያስን ለማግለል ሲባል የገባ ነው)
·        መነኮሳትም እጩ ይሁኑ ብሎ ያለው ተቀባይ አላገኘም፡፡ (ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ከዚህ ቀደም እንደ ዘገበው በገዳማቱ ለዘመናት የመለመላቸውና በሐሳቡ ያስቀመጣቸው ፓትርያርኮች  ሳይካተቱለት ቀርተዋል፡፡ በነገራችን ላይ ያረጋል አበጋዝ እስካሁን ሚስት ያላገባው ለፕትርክና ተመልምሎ ነው የሚል ነገር ማኅበሩ አካባቢ በሰፊው ሲናፈስ ነበር፡፡ ሁኔታው ከተመቻቸው በቶሎ መንኩሶ ለፕትርክና እንዲወዳደር ታስቦ ነበር ማላት ነው፡፡)
·        ፕትርክናው በዕጣ ይሁን የሚለው የማኅበሩ ሐሳብ ሰሚ አላገኘም፡፡

ክሽፈት ሦሰት
በዚህ መንገድ የፕትርክናው ተስፋ እየተመናመነ የመጣ ሲመስለው ማቅእርቅ ይቅደምበማለት ለፍፎ ነበር፡፡ የማቅ አንዱ አሳፋሪ ተግባር ይህ ነው፡፡ 20 ዓመት ሙሉ ዝም ብሎ ተቀምጦ አሁን የእርሱ ፍላጎት ስላልተሟላና እቅዱ ስላልተሳካ እርቅ ይቅደም ማለቱ ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ እርቅ መቅደም አለበት ብለው ስለእርቅ የተናገሩትን እነአባይነህ ካሴን እስከማገድ ደረሰ፡፡ በዚህ ተግባሩም አንዳንድ አባላቱማቅ እየኖረ ያለው /ቤቱ እንዳይዘጋ ብቻ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንን ትቷታልእያሉ ነው፡፡ ይህ ለማቅ ክሽፈት ነው፡፡

ክሽፈት አራት
ከቅርብ ወዳጆቹ አንዱ አቡነ ቀሌምንጦስ የማደራጃ መምሪያ የበላይ ሀላፊ ሊቀጳጳስእስከዛሬ ሳናውቅ ነው ከማኅበሩ ጎን የቆምነውብለው አባ ሠረቀ ብርሃንንና የማደራጃ መምሪያ ሰራተኞችን ይቅርታ መጠየቃቸውና ከአንድ አባት የሚጠበቅ ተግባር ማከናወናቸው ማቅም አዘውትሮ ስማቸውን ማጥፋቱ የማቅ አስገራሚው ክሽፈት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ክሽፈት አምስት
የቤተክህነት የመምሪያ ሃላፊዎችን G8 አማካኝነት በተለይ የትግራይ ተወላጆችን ወደሌላ በማዘዋወር ለምርጫ ድምጽ ያላቸውን መምሪያዎችን እርሱ በሚፈልጋቸው ሰዎች ለማስያዝ ሞክሯል፡፡ ይሁን እንጂ ገና ከጠዋቱ የልብ ወዳጁና ወደመምሪያ ሃላፊነት ያስመጣው ሊቀትጉሃን /ጊዮርጊስ ዳኜ ወንጀል ሰርቶ ሸዋሮቢት ወረደበት፡፡ ከዚህ የበለጠ ምን ክሽፈት አለ?
  

ክሽፈት ስድስት
ምርጫውን ሌላ አቅጣጫ ለማስያዝ የሞከረውና በልዩ ልዩ መንገድ አልታዘዝ ባይነትን እያሰፈነ የመጣው ማቅ አቡነ ናትናኤል ብርቱ ደብዳቤ ጽፈው መንግስት ጣልቃ እንዲገባና ስርአት እንዲያሰፍን በመጠየቅ በቤተክህነት ውስጥ የተደራጀ ቡድን መኖሩን፣ በዚህ ቡድን ውስጥ የቤተክርስቲያን ባለስልጣናት መኖራቸውን (ከአራዳ ክፍለ ከተማ ሥራ አስፈጻሚነቱ በግምገማ የተባረረው እስክንድር ገብረ ክርስቶስና አደገኛ ቦዘኔዎች ያሉበት ጣሊያን ሰፈር ተወልዶ ያደገው ተስፋዬ ውብሸት) ተገልጿል፡፡ በዚህ መሰረት ለመንግስት የተጻፈውን ደብዳቤ ተከትሎ ቤተክህነት ውስጥ የተጀመሩ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች መገታታቸው ማቅ ያሰበውን ግርግር ሳያሳከ ከሽፎበታል፡፡

ክሽፈት ሰባት
ይህን ተከትሎ የቲዎሎጂ ማኅበር ተብዬው ሰብሳቢ አቶ ማንያዘዋል አበበ የማኅበሩን /ቤት ተገን አድርጎ ግቢውን በወንጌል ሳይሆን በወሬ ሲንጥ ከርሞ አሁንም በሱና በማህበሩ በኩል ማቅ ሊጠቀም ሲል በአቃቤ መንበር ናትናኤል አማካኝነት ከጥር 3/2005 . ቤተክህነት ግቢ ዝር እንዳይል መደረጉ እሱን እያሉ በሰበብ ይገቡ የነበሩት፦
1. የቤተክህነቱን ግቢ ብላክ ማርኬት ያደረገው ዶላር መንዛሪውና ከህገወጦች ጋር ተመሳጥሮ ኮንደሚኒየም አሻሻጭ የሆነው ኃይለማርያም
2. የስምአጽድቅ አዘጋጅና የሁለተኛው ሐመር የዕንቁ መጽሔት አምደኛ የሆነው ታደሰ ወርቁ
3. የዋልድባን ጉዳይ መነሻ በማድረግ ህዝብንና መንግስትን ለማጣላት በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይምላጭ ቢያብጥበሚል ርእስ አሸባሪ ጽሑፍ የጻፈውናበዓላትየተሰኘ መጽሐፍ ጽፎበዓላት በገበሬዎች ኮንፍረንስ በመንግስት ሚዲያ ልፈፋ አይሻሩምበማለት ኋላቀርና ፖለቲካዊ አቋሙን ሃይማኖትን አስታኮ መጻፍ የሚወደው ብርሃን አድማስ፣
4. በጥንቆላ፣ በገንዘብ ዝርፊያ፣ በአስገድዶ መድፈር በተደጋጋሚ በማቅ ሸንጎ የተከሰሰው ህሩይ ባየ፣ የማንያዘዋል እጣ ይደርሰናል ብለው ቤተክህነት ግቢ ውስጥ አይደለም በቤተክህነት አካባቢ ዝር ሲሉ አለመታየታቸው ለማቅ ሌላው ትልቅ ክሸፈት ነው፡፡

ክሽፈት ስምንት
ማቅ በአስመራጭ ኮሚቴው ውስጥ በውክልናም በስውርም ያስገባቸው ባያብል ሙላት፣ የማኅበሩ ፈንድ አሰባሳቢውና በዘንድሮው የመስቀል በዓል ላይ በቶቶት ክትፎ ቤት በተደረገው የበዓል ዝግጅት ላይ ሲደንሱ የነበሩት የጭድ ተራው የመንደር ቀኛዝማች ሃይሉ  እና የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጣቶችን ለአድማ፣ ለረብሻ ሲያሰማራ የነበረውና በማቅ ሰዎች ተጽፎ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ስም ለሲኖዶስ ቀርቦ የነበረውንና ብዙ ሊቃውንት እንዲወገዙ ጥየቄ የቀረበበትንና ውድቅ የተደረገውን የክስ ፋይል ካቀረቡት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የማቅ ሰዎች መካከል አንዱ ሄኖክ ቢኖሩም ምንም ሳይሰሩለት መበተናቸውና በተለይ ብዙ የተማመነበት ባያብል ምርጫው ትክክለኛና ፍትሐዊ መሆኑን በሚዲያነጻ መሆናችንን የሚያረጋግጠው እግዚአብሔርና ኅሊናችን ነውበማለቱና ሀራ ዘተዋህዶን ስለሐሰተኛ ዘገባው በጎን በመውቀሱ ማቅ በመጨረሻው ላይ ያጋጠመው ትልቅ ክሽፈት ሆኖ ተወስዷል፡፡

ክሽፈት ዘጠኝ
ቀደም ብሎ ለፓትርያርክነት ባጫቸው አቡነ ሉቃስ ላይ እምነት ማጣቱና ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የልጅ አባት መሆናቸውና ከአብነት ትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ራሽያ የለመዱት ሰዶማዊነት ነገ ሌላ መዘዝ ያመጣብኛል በማለት እሳቸውን ተወት በማድረግ፣ ፊቱን ትክክለኛ እጩው ወደሆኑት ብሄረተኛ የአንኮበር ፖለቲካውን (መንግስትና ፕትርክና ከሸዋ) የሚያራምዱለትን አባ ማቴዎስን እጩ ውስጥ ቢያስገባም ሊመረጡ ባለመቻላቸው ማቅ ዋናውን ክሽፈት ለማስተናገድ ተገዷል፡፡

ክሽፈት አሥር
ስለምርጫ አጠቃላይ ሁኔታ ግንዛቤ ለማስጨበጥ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ ከሚጠበቀው በላይ ባጓተተውና ከአቡነ ጳውሎስ ህልፈት በኋላ “ፕትርክናው ዘንድሮ ከእኔ አይወጣም” በሚል ቅዠት ከሚገባው በላይ ባፋጠነው ህንጻ ላይ የጠራው የአድማ ስብሰባ በጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጁ መታገዱ ክሽፈት ነው፡፡ክሽፈት አሥራ አንድ
ማቅ ለተሐድሶ እንቅስቃሴ ማጥፊያ በማለት ከየባለሀብቱ በየአዳራሹ በሰበሰበው ገንዘብ ያደራጃቸውና መንፈሳዊ ህይወታቸውንና ሰብእናቸውን ሳይገነባላቸው ቤተክርስቲያን ደክማ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች አስመርቃ ክፍለሃገር ብትመድባቸውም ተልእኳቸውን ንቀውና ጠቅጥቀው በማቅ የሻይ ቡና በጀት ቀኑን ሙሉ በቱሪስት ሆቴል ውለው ማታ ወደየአውደ ምሕረቱ “ለማስተማር” የሚበተኑትና ወንጌልን ሳይሆን ስድብን፣ ትችትን፣ ዘለፋን፣ ተረትን ሲሰብኩ የኖሩት በተለምዶ የቱሪስቱ ቡድን ተብለው የሚጠሩት በማቅ የተገባላቸው የፀረ ተሃድሶ ጥምረት ቢሮ መከፈት ከሽፎ የዘወትር መዋያቸው ቱሪስት ሆቴል በመዘጋቱም ይህን ተከትሎ እርስ በርስ በመከፋፈል (ባለመተማመን) ቡድኑ (ጥምረቱ) በመበተኑ፣ ማቅም ትኩረቱን ወደ ምርጫው በማድረጉ የትነው ያላችሁት? ስሎ ስላልፈለጋቸው ልዩነታቸው ሰፍቷልና ማቅ የደረሰበት ሌላው ክሽፈት ነው፡፡ ዛሬ የቱሪስቱ ቡድን አባላት 99% የሚውሉት ለየብቻቸው ሲሆን፣ ሁሉም ቤልኤር፣ ቀበና አካባቢ ከተከራዩአቸው ቤቶች ባለመራቅ አንድን ሻይ ቤት ከአንድ ቀን በላይ ባለመጠቀም አቋም ፀንተው ታይተዋል፡፡ ይህ ለማቅም ለቡድኑ አባላትም ሌላው አሳዛኝ ክሽፈት ነው፡፡

ክሽፈት አስራ ሁለት
የሀገር ውስጥ እና መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የማቅ አባላት (በላቸው፣ ኤፍሬም፣ መስፍን፣ ብርሃጉ ጐበና) ከአ.አ ማዕከል ጋር በፓትርያርኩ ምርጫ የተነሳ በሀሳብ መከፋፈላቸውና ይህን ፖለቲካዊ አቋማቸውን ተከትሎ የውስጥ ልዩነት እየሰፋ መሄዱን ማወቅ ተችሏል፡፡ ይህስ ክሽፈት አይደለም?
  
ክሽፈት አስራ ሶስት
ማቅ ዘወትር ሲዘምትባቸው የነበሩት ዘማሪያን፣ ማቅና አባላቱ የዜማ ሊቅ ሳይሆኑ መዝሙራቸውን የተሐድሶ ነው በማለት በየዐውደ ምሕረቱ ሲያሳጧቸው የነበሩ ዘማሪያን “አለው ነገር” በሚለው አልበማቸው ምድራችንን በመሸፈናቸው የማቅ ዘመቻ መክሸፉን ያስተዋልንበትስ አጋጣሚ ቢሆን ሌላው የማቅ ክሽፈት አይደለም?

ክሽፈት አስራ አራት
ማቅ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ሲጓጓለትና ሲንገበገብለት የነበረው በፓትርያርክነት ደረጃ ቤተክርስቲያኒቱን ብሎም ሀገሪቱን ለመቆጣጠር (የአንኮበር ፖለቲካን ለማራመድ) የፓትርያርክነቱን ማዕረግ ለራሱ ወገኖች ቢቻል ከገዳም ካልሆነም ከሸዋ ጳጳሳት (ለምሣሌ እንደ አቡነ ማቴዎስ) ያሉትን እዚህ ለማስቀመጥ ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ ከምንግዜውም በላይ በበጀት፣ በመወቅራዊ አሰላለፍ፣ በምክር፣ የራሱን የህግ ባለሙያዎች ረቂቅ ህግ እንዲያዘጋጁ በመመደብ ወዘተ በከፍተኛ ሁኔታ ሲሳተፍ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የካቲት 21/2005 ዓ.ም ምኞቱ ሳይሳካ፣ ሕልሙ ሳይተረጐም፣ የዘራው ሳያፈራ እጩው ተሸንፈው ማቅ ፓትርያርክነት እያማረው ቀረ፡፡ የካቲት 24/2005 ዓ.ም ቀንም ብፁእ አቡነ ማትያስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተብለው መንበረ ፕትርክናውን ተረከቡ፡፡ ከአቡነ ጳውሎስ ህልፈት በኋላ እስከ ስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ካደረጋቸው ወሳኝ እንቅስቃሴዎች አንድም ሳያሳካ ሁሉንም በሚቻል ሁኔታ በክሽፈት ደምድሟል፡፡

ክሽፈት እንደ ማህበረ ቅዱሳን!

15 comments:

 1. ha ha ha! Yekeshefu sile kishfet binageru kelimdachew silehone enadenkalen.

  ReplyDelete
 2. ክሽፈት የናንተ ውሸት እንጅ የማቅ እንዳልሆነ እናንተም በሚገባ ታውቁታላችሁ። ማቅ እንደ እናንተ በወሬና በሰብቅ ጊዜውን እንድማያሳልፍ ይህንንም በሚገባ ታውቁታልችሁ። ለወሬ የለውም ፍሬ ነውና እናንተ በየቀኑ እየቀለላችሁ ማኅበሩ ግን ለቤተ ክርስቲያን ተገን እየሆነ እንደሆነ ዲያብሎስም ያውቃል። ኑሮአችሁ በዚሁ ስለሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም ስለሆነም መቼም እንደናንተ ሀሳብ ከሆነ ፕሮፓጋንዳ ሲደጋግም እውነት ይመስላል ብላችሁ ይሆናል ነገር ግን በየጊዜው በምታናፍሱት የሀሰት ዘመቻ ከእግዚአብሔር ፍጹም እየራቅችሁ መሄዳችሁ በጣም ያሳዝናልና ወደ ልባችሁ ተመለሱ። ልባችሁ እያወቀ የምታደርጉት ነገር ሁሉ ትግሉ ከራሳችሁ ኅሊና ጋር እንጂ ማንንም እንደማትጎዱ በእርግጠኝነት ለመናገር እችላለሁ። የማኅበሩ አባል ባልሆንም ስለማኅበሩ በሚገባ አውቃለሁ። ለንባብ ባታበቁትም ካነበባችሁት በቂ ነው። መልካምን ተመኙ በሆነ ባልሆነም እራሳችሁን የታሪክ ተጠያቂ ባታደርጉ መልካም ነው።

  ReplyDelete
 3. ere endekiristian tsafu

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ere bakihe, Woro bela, asemesay krestiyan, ye-Betekrestiyanachn telat hulu, tegeletachu.

   Delete
 4. manewe yehenene hulu bemistere yenegerachehu? anebesochu eko nachehu bertu teberatu!!!edegu temenedegu!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. yih aynet mistir aybalim mikniyatum hulgize yemitlutnna yemtdegmutin dawit new yemtzebezibut maferiyawoch

   Delete
 5. enanete nachuh wana keshafi

  ReplyDelete
 6. ክሽፈት እንደ ማህበረ ቅዱሳን! becha sayhone weredatem chemer new becha fetari lebona yestachew mk ማህበረ ቅዱሳን yehe adegega bozena yetesebesebebat maheber seraw yeareyos nebesegeday nebesebela becha new sewoche kezihu awera letetenakeku yegebale

  ReplyDelete
 7. ለማህበረ ቅዱሳን /የዝንጀሮ መንጋ/
  ኢህአዴግ በ 20 ዓመታት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ሸወዳችሁ……አባ ሳሙኤል እና አባ አብረሃም የኢህአዴግ በትር ሆነው ሲያገለግሉ ቆዩና በመጨረሻ ተጣሉ…….”እባቡን ግደል በትሩን ወደ ገደል”
  አባ ሳሙኤል እና…….እርቅ አያስፈልግም እያሉ ሲጮሁ የነበሩ ሁሉ……የኢህአዴግ በትር መሆናቸውን አላወቁም ነበር፤
  ታሪክ ተደገመ……..ያሳዝናል……እኔ ግን ደስ ብሎኛል፡፡

  ReplyDelete
 8. የዋልድባን ጉዳይ መነሻ በማድረግ ህዝብንና መንግስትን ለማጣላት በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ “ምላጭ ቢያብጥ” በሚል ርእስ አሸባሪ ጽሑፍ የጻፈውና “በዓላት” የተሰኘ መጽሐፍ ጽፎ “በዓላት በገበሬዎች ኮንፍረንስ በመንግስት ሚዲያ ልፈፋ አይሻሩም” fitun tsefto afun kefto anagerewu alu yenta endih satasibut yanagrachihu enji menfesqdus tinantim zaream yanagral

  ReplyDelete
  Replies

  1. ተሃድሶዎች ሆይ!!! እንደምን አላችሁ እግዚአብሄር ያስተምራችሁ!!! የከሸፋችሁት እኮ እናንተ ናችሁ!!!
   እናንተ ባልቴቶች፡- ባልቴቶች ስል (በመንደር የሚገኙ ህጻናትን የሚጠብቁትን፣ወጣቶችን የሚያስተምሩ ከጥፋት የሚገስጹትን፣የታመሙ የታሰሩ የሚጠይቁትን፣ያዘኑ የሚያጽናኑትን በበጎ ነገር ተጠምደው በመንደሩ የሚውሉትን ወዘተ… አዛውንቶች ሳይሆን ) አረቄ እየቃረሙ ካንዱ ቤት አንዱ ቤት ወሪ የሚያመልሱትን፣ባልና ሚስት ለመጨቃጨቅ ምክንያት የሚሆኑትን የመንደሩን ሴቶች ወሪ በማመላለስ የሚበጣብጡትን ሥራ ፈት ባልቴቶች ማለቴ ነው፡፡ ለመሆኑ እስከመቼ በአሉ አሉ ወሬ ተጠምዳች አባ እገሌ፣መምህር እገሌ ሊቀትጉሃን እገሌ ወዘተ… እንዲህ ሆኑ እንደዚያ ሆኑ እያላችሁ የስጋ ወሪ በማውራት ትውላላችሁ፡፡ አንድ እውንት ልንገራችሁ ተጋድሎአችሁ ሁሉ ከደምና ከሥጋ ጋር ነው ስለ ሥልጣን ነው ወዘተ… እናንተ በክሽፈት ጹሁፋችሁ የጠቃቀሳችኋቸው ሰዎች የሚጋደሉት በእናንተ ላይ አድሮ ቤተክርስቲያንን ሊያተራምስ ከሚፈልግ መንፈስ ጋር ነው፡፡ ሌላ እውነት ልንገራችሁ በሚስጢራተ ቤተክርስቲያናችን፣ በሥርዓተ ቤተክርስቲያንችን መኖር ስለአቃታችሁና ለሥጋችሁ ስለምትኖሩ ይህችን ሥርዓት ለምፍታት ለማላላት ትታገላላችሁ ለፍሬ ሳይሆን ለገለባ ትደክማላችሁ፤ ተዋህዶ እምነታችን ቤተክርስቲያናችን የታነጸችው በመድኃኒታችን በአለት ላይ ነው፣ ሥርዓቷም የተመሠረተው በመንፈስ ቅዱስ ቅኝት በሃዋርያት ተጋድሎ ነው፣ ከዛም በኋላ ቅዱሳን አባቶቻችን የቅርቦቹን እንኳን ላስታውሳችሁ እና ብፁአቡነ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ፣አቡነ ጎርጎሪዮስ፣አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ ማቲዎስ፣አቡነ ኤልሳ ወዘተ… ስንቱን ልጥራላችሁ መሠረቷን አጽንተው ዛሬ እናንተ በክሽፈት ጹሁፋችሁ የምታነሳሷቸው የመንፈስ ልጆቻቸውን ወልደው ነው የሞቱት እናንተ እኮ የምታጣጥሏቸው እኒህ ወንድሞች እነ ዳግማዊ ጳውሎስወጴጥሮስ መሆናቸውን ልባችሁ ያውቃል እውነት የሚናገሩ እውነትን እውነት የሚሉ ስለእውነት እሥር ቤት የተወረወሩ የተሰደዱ ናቸው፡ እንደ እናንተ ዘፈን አይሉት መዝሙር የሚዘመረው ስለስጋዊ ፍቅር ይሁን ስለመንፈሳዊ ፍቅር የማይገባ ወጣቱን ግራ የሚያጋባ መዝሙር በየመንገዱ የመኪና ላይ ንግድ ሲያካሂዱ አይደለም የታሰሩት እንደ ሃዋርያት እውነትን በመናገራቸው እውነትን በመስበካቸው እንጂ፡ መድሃኒታችንን አይሁድ ሊሰቅሉት ሲፈልጉ ክሱን እንደአበዙበትና በይሁዳ አመላካችነት በሌሊት ሰዎች ሳይሰበሰቡ እንደያዙት ሁሉ የእኝህም ሰው እስር እንዲሁ ነው በእናንተ መሰሎች አጋፋሪነት በአፈና መያዛቸው ምን ይነግራችኋል ወንጀል ቢኖርማ በግልጽ በህጋዊ መንገድ ይታሰሩ ነበር፡፡ እስከመቼ ትዋሻላችሁ ልጆቻችሁ ብዙ ዋጋ እንዲከፍሉ ስለምን እዳ ታበዙባቸዋላችሁ፡፡
   ሌላ እውነት ልንገራችሁ እናንተ መናፍቃን ሆይ!!! የቤተክርስቲያናችን ጾመ ሠርዓት፣ጸሎት፣ስግደት እና ሥጋን ማድከም የከበዳችሁ እኛ እና እናንተ አንድነት የለንምና ከቤተክርስቲያናችን ጓሮ ውጡ ሥርዓቷን መበረዝ አይቻላችሁምና ሂዱ ለራሳችሁ ተቋም ፍጠሩ ሥርዓታችሁንም መሥርቱ ለሥጋችሁ እንደሚመቻችሁ አድርጋችሁ ገንቡ ብሉ፣ ጠጡ ፣ስከሩ አመንዝሩ ለብቻችሁ ግን ከግቢያችን ውጡ!!! እግዚአብሔር ያስተምራችሁ!!!
   ወስብሐት ለእግዚአብሄር

   Delete
 9. ፕትርክናው በዕጣ ይሁን የሚለው የማኅበሩ ሐሳብ ሰሚ አላገኘም፡፡
  this phrese alone tells us how isMahibere kidusan. how can it recomend if the association has an intension to put one father as Patriarch...... EGZIABHERE YEFEKEDEWEN ABAT YISTEN MALET TILK MENFESAWINET NEW KORAHUBACHER
  ORHER WHICH TELL ME AS MAHIBERE KIDUSAN STANDS FOR THE TRUTH
  ማቅ “እርቅ ይቅደም” በማለት ለፍፎ ነበር
  “በዓላት በገበሬዎች ኮንፍረንስ በመንግስት ሚዲያ ልፈፋ አይሻሩም”
  “ነጻ መሆናችንን የሚያረጋግጠው እግዚአብሔርና ኅሊናችን ነው”
  KORAHUBACHUH

  ReplyDelete
  Replies
  1. እእ.. ወዴት ወዴት.. ይቺ ይቺ እንኳን ነጭ ውሸት ናት፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን እግዚአብሄር ይስጣቸው ለናንተ ብሎግ ጥሩ እርስ ፈጥረውለካቺሁአል፡፡ ብሎጋቺሁን እንዲህ ብትሉት ያዋጣችኋል መክሸፍ እንደ አባሰላማ ብሎግ ወይም ነጭ ውሸት በነጻ እናስነብባለን በጣም ውሸታሞች ናቺሁ:: ስለምረት አብ የጻፋችሁትን ሳነብ ነው የታዘብኳችሁ ሰፈሬ እኮ ኮተቤ እያቄም ወሐና ቤ/ክ አጥብያ ነው፡ ዝም ብላቺሁ በሬ ወለደ ትላላችሁ እንዴ; ለምን ይዋሻል፡፡ በጓደኛየ አማካኝነት ነበር ወደ ብሎጋቺሁ የተቀላቀልኩት አሁን ግን ከዛሬ ጀምሮ ቻው ቻው ውሸታም አልወድም እግዚአብሄር ልቦና ይስጣችሁ፡፡ የገባባቺሁን የውሸት መንፈስ በፀበል ካልሆነ በምክር የሚለቃቺሁ አይመስለኝም፡፡

   Delete
 10. wetam werede.....
  betekiristan yemtfersew be
  mahbere "kidusan"new.

  ReplyDelete