Monday, March 11, 2013

የሊቀ ጳጳሱ የሲሚንቶ ሽያጭ ቅሌት

በከፋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የዋሻ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ሥራ ከተጀመረ 4 ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ ይህ የአካባቢው ምዕመናን አስተዋጽኦና በበጎ አድራጊዎች እርዳታ እየታነፀ የሚገኘው ቤተክርስቲያን በአስተዳዳሪውና የህንፃ አሰሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ የገንዘብ ምዝበራ ተካሂዶበታል በሚል በተደጋጋሚ ክስ ቢቀርብበትም ሀገረ ስብከቱ አባ ሕዝቅኤል ክሱን እየሸፋፈኑና የሕዝበ-ክርስቲያኑን ጥያቄ በማፈን በልመና የሚሰበሰበው ገንዘብ እንዲመዘበር ሽፋን ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

በአባ ሕዝቅኤል ፍርደ-ገምድልነት የተከፉ የአካባቢው የሀገረ ሽማግሌዎች በሰኔ ወር 2ዐዐ4 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ቀርበው ጉዳዩን ለብፁዕ ውቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ያስረዳሉ፡፡ ለገንዘቡ መመዝበር እንደ ምክንያትም እንደ ሽፋንም የሆኑት የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባ ሕዝቅኤል መሆናቸውንም ያስረዳሉ፡፡ ፓትርያርኩም አጣሪ ወደ ሀገረስብከቱ በመላክ የሀገር ሽማግሌዎቹ አቤቱታ አግባብነት መሆኑን፣ በህንፃ ቤተ-ክርስቲያኑ ምክንያት የተመዘበረ ገንዘብ መገኘቱን ወዘተ በመገንዘብ የደብሩ አስተዳዳሪ ከቦታቻው እንዲታገዱና የሒሳብ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ፡፡ “የበላ ዳኛ የወጋ መጋኛ” እንዲባል ይህን እንዲያስፈፅሙ የታዘዙት የሀገረስብከቱ ሊቀጳጳስ አባ ሕዝቅኤል የብፁዕ ወቅዱስን ማለፍ ተገን በማድረግ ትዕዛዙን ሳያስፈፅሙ፣ ሒሳቡም እንዳይመረመር ሲከላከሉ ቆይተው አስተዳዳሪውን ወደ ሥራው እንዲመለስ በማድረግ የሕዝበ-ክርስቲያኑን ልፋት ከንቱ ያደርጉታል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የደብሩ አስተዳዳሪ በአባ ሕዝቅኤል ፊርማና ቲተር በተፃፈ ደብዳቤ 36ዐ ኩንታል ሲሚንቶ ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለዋሻ ሚካኤል ህንፃ-ቤተክርስቲያን ማስፈፀሚያ በሚል ምክንያት ይገዛና ሲሚንቶውን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አየር በአየር እንዲሸጥ ይደረጋል፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሆነባቸው የአካባቢው ተወላጆችና የሀገር ሽማግሌዎች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ክስ ይመሰርታሉ፡፡ አባ ሕዝቅኤልም ክሱ እንዲቋረጥና በቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ዳኝነቱ እንዲታይ ፍርድ ቤቱን ይጠይቃሉ፡፡ የአካባቢውም ምዕመናን በሊቀጳጳሱ ላይ እምነት እንደሌላቸው በመግለፅ የስርቆሽ ወንጀሉ በፍርድ ቤቱ እንዲታይ ይማፀኑና ክሱ መሰማት ቀጥሎአል፡፡ በሒደቱም በዋሻ ሚካኤል ስም የወጣው ሲሚንቶ አላግባብ ተሸጦ ለግለሰቦች ጥቅም መዋሉን ያረጋገጠው የከፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአባ ሕዝቅኤል ሸሪክ በመሆን ቤተክርስቲያኑን ሲያስመዘብሩ የቆዩትን የዋሻ ሚካኤል የደብር አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባተ ሃይሌን በ6ወር እስራትና በ2ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ማክሰኞ የካቲት 26 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ይወሰናል፡፡ በዚህ ፍትሃዊ ውሣኔ የተደናገጡት የደብሩ አስተዳዳሪ በብስጭትና በቁጭት “ወይኔ አባተ ሲሚንቶውን ሸጠው የወሰዱት ጳጳሱ አቡነ ሕዝቅኤል ናቸው እኔ ለእንጀራ ብዬ ጉድ ሆንኩ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸውንም አባ ሕዝቅኤልን እንዲያነጋግሩ እንደላኩና በሽያጩ ገንዘብ ለቤተሰባቸው የማይሰጥ ከሆነ ሲሚንቶውን ሊቀጳጳሱ አሸጠው ገንዘቡን ኪሣቸው መክተታቸውን አጋልጣለሁ ብለዋል፡፡

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ ነውና በሲሚንቶ ሽያጭ ያልታመኑ አባ ሕዝቅኤል ፓትርያርክ መሆን የነበረብኝ እኔ ነኝ እያሉ፤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የፓትርያርክነት ምርጫ አኩርፈው ቤት ውለዋል፡፡

“ተመስገን ነው እንጂ ሰው ባያሌው ታሞ
ያማረሩት እንደሁ ይጨምራል ደግሞ” እንዲባል የፓትርያርክነት ሹመቱን ሀዘን ሳይጨርሱት የሲሚንቶ ክስ ሊመጣባቸው መሆኑን ለአባ ሰላማ ከአካባቢው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፡፡

9 comments:

 1. Bebezu yaltamene...............

  ReplyDelete
 2. አባ ማትያስ ሲሾሙ ኣባ ህዝቄኤል አኩርፈው ቤት በማዋላቸው የበቀል እርምጃ እንደሆነስ ማን ያውቃል? በዚህ ሥርአት ውስጥ ምንም የሚታመን ነገር የለም። "ጦርነትን ማሸነፍ ብቻም ሳይሆን መፍጠርም እንችላለን '' ብለውናል እኮ።

  ReplyDelete
 3. I wonder if Mahibere Kidusan has anything to do with this. Please do more research for us about this evil political organization. thank you.

  ReplyDelete
 4. May be MK behid of this reducless issues to share the big bucks or money. thanks aba selama..........

  ReplyDelete
  Replies
  1. kefuwech nachehu ye betecrstian telatoch!!!!!!!!

   Delete
 5. ጾም ማለት ለተወሰኑ ሰዓታት ከእህል እና ከውሃ (ጥሉላት መባልዕትን ጾሙ እስኪፈጸም ፈጽሞ መተው) እንዲሁም ለተወሰኑ ጊዜያት ከሥጋ ፈቃዳት መከልከል ነው።። ስለዚህ መጾም ማለት በጾም ወቅት የምግብ ዓይነትን መለወጥ ብቻ ሳይሆን የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ነው።። የሥጋ ፍላጎት የዓለምን ምኞት መፈጸም ሲሆን ይህን ነገር የምንገታው ደግሞ ራሳችንን በጾም በመግዛት ነው። ”ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ- ነፍሴን በጾም አስመረርኋት” መዝ. 68፥10 እንዲል። ታሪካቸው በትንቢተ ዳንኤል ተጽፎ የምናገኘው ሦስቱ ወጣቶች በንጉሥ ቤት እየኖሩ የተሻለ ነገር መመገብ ሲችሉ እግዚአብሔርን ስለ መውደድ ብለው በንጉሡ ቤት ከሚዘጋጀው ማለፊያ ምግብ ይልቅ ጥራጥሬን መመገብ መረጡ። ትን ዳን. 1፥8-16። በተጨማሪም እንደ ዮሴፍ እግዚአብሔርን በመፍራት ምክንያተኝነትን በመተው ከኃጢአት መጾም ነው:፡ ዮሴፍ ኃጢአቱን ለመሥራት የእመቤቱን ፈቃደኝነትና የእርሱን ወጣትነት እንደ ምክንያት አላቀረበም። ነገር ግን ፈጣሪውን ዘወትር በፊቱ በማድረጉ ከኃጢአት ለመጾም ችሏል። ዘፍ 39፥7-13;: ስለዚህ ጾም ማለት እያለንና ማድረግ እየቻልን ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ነው።

  ReplyDelete
 6. Thanks abaselama if it is real . By theway I am not supprised whatever they do what we call "The church Father" . Be honest how many real church fathers do we have from synod member ? u can answer for youself. Our church need to have father like Abuna Shenoda the one he protect church from their enemies & he sacrified his life for the sake of safity for his spirtual childern , brothers, sisters etc.
  I can say father like him holy father and the synod lead by such a father l can say Holy Synod. But when u come to us our church u knew it what happend it look like poletics rally . I am not forget coptic church is well organise than us

  ReplyDelete
 7. Abune Hzkiel ejig tewaredu
  yekefawn kahn eji nestew hedu

  ReplyDelete
 8. tekulawoch atasesitu

  ReplyDelete