Thursday, March 14, 2013

"ሰባኪው" ምሕረተአብ ከኮተቤ ኢያቄም ወሃና ቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት በስካር ቅሌት ወረደ

ዐቢይ የተባለው የጌታችን ጾምን ደግመን በምንጾምበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ ጾሙ ትውፊትን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በልማድ መጾማችን እንደተጠበቀ ሆኖ ዋናው ጾም ከመብል መጠጥ ብቻ ሳይሆን ከኃጢአት መጾሙ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ይሁን እንጂ በጾም ወራት ስለምናከናውነው መንፈሳዊ ተግባር ከማሰብና ከመጨነቅ ይልቅ ለ54 ቀናት ከምንለየው ስጋና ሌሎችም የጥሉላት ጋር የመጨረሻ ስንብት ለማድረግ ለቅበላ የምናደራው የሥጋ ገበያ አይሎ ስለሚታይ ጿሚዎች ሳንሆን ስጋን ናፋቂዎች እያስመሰለን ነው፡፡ ፍትሐ ነገሥታችን በጾም ወቅት ሥጋንና ሌሎቹንም የጥሉላት ምግቦች ብቻ ሳይሆን የሚያሰክር መጠጥንም እንድንጾም ያዝዘናል፡፡ ነገር ግን ማን ሰምቶ? እነ ሆድ አምላኩ ለመብልና ለመጠጥ እንጂ ለጾም አያደሉም፡፡ አድልዉ ለጾምን ሳይሆን አድለዉ ለሆድን ነው የሚያስቀድሙት፡፡ በተለይም ቤተክርስቲያን በዝክርና በተዝካር ሰበብ በአልኮል መጠጥ የተሞላች ስለሆነች መጠጥ የሚበረታታባት ቤት ሆናለች፡፡
አንዳንድ ወጣቶች አልኮልን ትተው በሻይና በለስላሳ መጠጥ የጽዋ ማኅበር ይጠጡ በነበረባቸው በ1980ዎቹ ዓመታት፣  ጠላና ጠጅ ከጽዋ ማሕበር ለምን ቀረ? በሚል እንዲህ ያለው አካሄድ የተሐድሶ ነውና ንቁ እየተባለ ይሰበክ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ መጠጥ የኦርቶዶክስነት ምልክት ተደርጎ እንዲታሰብ እስከማድረግ ደርሰዋል፡፡ የማይጠጣ ተሐድሶ ነው እያሉም በመጠጥ ጉዳት እንጂ ጥቅም ኪሳራ እንጂ ትርፍ እንደማይኖር የተረዱና መጠጥ አንጠጣም ያሉ አንዳንድ አገልጋዮችን  ሲያሳድዱና ስማቸውን ሲያጠፉ እንደኖሩና አሁንም በብዙ ስፍራዎች እያሳደዱ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ጠጪዎቹ እንዲህ የሚያደርጉት ለምንድን ነው ቢባል የማይጠጡት አገልጋዮች ሕይወት ስለሚኮንናቸውና ህሊናቸው ስለሚወቀስ ነው፡፡ እኛን ካልመሰሉ መናፍቃን ተሐድሶዎች ናቸው ብለው ያስባሉ፡፡
ከሰሞኑ ስለ ትክክለኛው መናፍቅ ምሕረተአብ (እንዳሻው) የወጣው ዘገባ የዚህ አንዱ ማሳያ ነውና እንድታነቡት ጋብዘናል፡፡
ምንጭ፡- http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com
"ሰባኪው" ምሕረተአብ ከኮተቤ ኢያቄም ወሃና ቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት በስካር ቅሌት ወረደ

"ከእኔ በላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰባኪ ለአሣር"!! ባዩ ምሕረተአብ አሰፋ (እንዳሻው) በትላንትናው ዕለት በስካር ምክንያት መስበክ አቅቶት ከኮተቤ ኢያቄም ወሃና ቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት መውረዱን ከዚያው አካባቢ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

የኮተቤ ኢያቄም ወሃና ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ጉባዔ አዘጋጆች ምሕረተአብ በተለይ ከአንድ ዓመት ወዲህ በሚያሳየው ከመንፈሳዊነት የራቀ ባህርይ አንጻር እርሱን መጋበዝ አለብን ወይስ የለብንም በሚል ሃሣብ ለሁለት ተከፍለው እንደነበር የገለጹልን ምንጮቻችን፣ በመጨረሻም ይገኝ ተብሎ ቢወሰንም በትላንትናው የቅበላ በዓል ላይ በጊዜ ተገኝቶ ስለጾም ያስተምራል ተብሎ ሲጠበቅ፣ አርፍዶ ከምሽቱ 100 ሰዓት ላይ ከመጣ በኋላ ጭራሹን መቆም አቅቶት እየተንገዳገደ በተንተባተበ ምላስ ". . . ቡታጀራ ሄጄ አሁን መመለሴ ነው፡፡ ይቅርታ!! ለዛሬ ላስተምራችሁ አልችልም፤ ሌላ ጊዜ መጥቼ በሰፊው እንማራለን" ማለቱ ተገልጿል፡፡ ከዚያም እንደ ስድስት ወር ጨቅላ ሕፃን በሰዎች ተደግፎ መውረዱ ታውቋል፡፡

በሁኔታው ያፈሩና የተሸማቀቁ ምዕመናንና የጉባዔው አዘጋጆች "እንኳን መጥተህ ልታስተምር ከዚህ በኋላ በሌላ አጥቢያም ስታስተምር ብናይህ ወየውልህ" ማለታቸውን ምንጮቻችን አረጋገጠዋል፡፡ ከዚህም በላይ አንዳንዶች እዚያው ሊጠፈጥፉት ተጋብዘውበት የነበረ ቢሆንም በሌሎች ገላጋዮች ጥረት መትረፉ ታውቋል፡፡

ምሕረተአብ (እንዳሻው) ቀደም ሲል በአዲሱ ሚካኤል ተገኝቶ "የእነ አሸናፊ መኮንንን መጻሕፍት ለቃቅመን እዚህ ግቢ እናቃጥላለን" እያለ ሰባክያንንና ዘማርያንን በስም እየጠራ ሲረግምና ሲያስረግም ማምሸቱን በዚሁ ብሎጋችን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

የትላንትናውን ትዕይንት የታዘቡ ሌሎች አካላትም ምሕረተአብ ከወደ አልኮል አካባቢ እንደማይጠፋ እና ፉት ማለት እንደሚወድ የገለጹ ሲሆን፣ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ጥር ወር ላይ አዋሬ አካባቢ በሚገኘው ኮከብ አዳራሽ ሠርግ ላይ ተገኝቶ አልኮል ሲቀመቅም መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ በኋላም ዘማሪ ዲያቆን ዕዝራ ወጥቶ ሲዘምር አልኮል ባመጣው ግፊት ተነሳስቶ ወደ መኪናው ሮጦ ሽጉጥ ነገር አውጥቶ "እናታችሁን እንዲህ ትሁንና ከተሃድሶ ጋር እየሠራችሁ ነው እንዴ ያላችሁት"? ብሎ በእነ ዘማሪ ሰማኸኝ ምሥጋናው፣ ዘማሪ እስጢፋኖስ (ቄሴ)፣ አሸናፊ አበበ እና በዘማሪ ዳግማዊ ላይ መፎከሩን ገልጸውልናል፡፡ ከዚያም አንዱ ታዛቢ ተነስቶ "እናትህ እንዲህ ትሁን የሚለውን ስድብ እንድተው አንተ ነበርክ እኮ ያስተማርከኝ፡፡ ዛሬ ከአንተ አንደበት ይህንን ስሰማ በጣም አዝናለሁ" ብሎ በብስጭት እንደተናገረው በስፍራው የነበሩ ሰዎች ያስታውሳሉ፡፡ ኋላም "እንዳሻው" እጁ በፖሊስ ተይዞ ጣቢያ ያደረ ሲሆን አልኮሉ ሲበርድለት አማላጅ ልኮ መታረቁንና ፋይል ማዘጋቱን፣ ነውሩን ለመሸፈንና ዕርቁን ፍጹም ለማድረግም ጥግሸት ሆቴል ወስዶ ተበዳዮችን ምሣ መጋበዙን ውስጥ ዐዋቂ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡

ምሕረተአብ (እንዳሻው) ራሱን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠባቂ እና የ"ማኅበረ ቅዱሳን" አገልጋይ አድርጎ ቢሾምም ምግባሩ እንደሚያሳየው አገልግሎትንና ቤተክርስቲያንን ከማሰደብ አልተመለሰም፡፡ አንዳንድ የዋሃን "አማኝ ነኝ" ባዮች "ጴንጤ" ላለመባል የግድ አልኮልን ሲዳፈሩ ይታያል፡፡ ይሁን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈውም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀኖና እንደሚያዘውም ቤተክርስቲያናችን አልኮል መጠጣትን አታበረታታም፡፡

ምሕረተአብ (እንዳሻው) ሌሎችን ከመስበኩ በፊት ከመጽሐፍ ቅዱስ አልኮልን ከሚመለከቱ በርካታ ክፍሎች ውስጥ አንዱን ከፍቶ እንዲያነብና አስቀድሞ ራሱን እንዲሰብክበት ቀጥሎ ያለውን መልዕክት እናስተላልፍለታለን፡፡

"ዋይታ ለማን ነው?
ኃዘን ለማን ነው?
ጠብ ለማን ነው?
ጩኸት ለማን ነው?
ያለምክንያት መቁሰል ለማን ነው?
የዓይን መቅላትስ ለማን ነው?
የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን?
የተደባለቀ የወይን ጠጅን ይፈተኑ ዘንድ ለሚከተሉ አይደለምን?
ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት፡፡ በቀላ ጊዜ መልኩም በብርሌ ባንጸባረቀ ጊዜ እየጣፈጠም በገባ ጊዜ በኋላ እንደ እባብ ይነድፋል፡፡ እንደ እፉኝትም መርዙን ያፈስሳል፡፡
ዓይኖችህ ጋለሞታን ያያሉ፤ ልብህም ጠማማ ነገርን ይናገራል፤ በባህር ውስጥ እንደተኛ ትሆናለህ በደቀልም ላይ እንደተኛ፡፡
መቱኝ ያውም አልተሰማኝም፤
ጎሰሙኝ አላወቅሁም፤
መቼ እነሣለሁ? ደግሞ ጨምሬ እሻታለሁ ትላለህ"፡፡

ምሣሌ 23 ፡ 29:35
ወንድማችን ምሕረተአብ (እንዳሻው) ሆይ!!
እግዚአብሔር ከብጥብጥና መለያየት መንፈስ እንዲያርቅህና ከአልኮል መዳፍ ውስጥ መንጭቆ እንዲያወጣህ፣ እንደገናም ሰው አድርጎ እንዲሠራህ ዘወትር እንጸልይልሃለን፡፡

     

94 comments:

 1. እስኪ እናንተ የሰው ነውር ከማውጣት ወንጌልን ልቀቁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yama Yewegu Neber Gin Altadelum Ye Abaselama Blog Yetekefetechew Endhu Yesew Sim Lematfat new Enji Ewunetengna Yehonewun Ye Egzeabher Qal Lemastelalef Aydelem. Lbona Ystachew Amlak.Ewunetengnoch Christianoch Bhonu Nuro Endh Aynet Sira Ayserum neber Gin Manafqi Men gzem bhon menafq new

   Delete
  2. ምነው ወገን ሁሉ እንዲህ ሆነ፣
   እንደ ቸኮለው ጅብ ፈጠነ፣
   እከተማ ውስጥ መነነ፣
   በሁሉም ነገር ባከነ፣
   የእግዜርን ትቶ የሰጠነ፡፡
   እንኪያ ሰላምቲያ
   በምንቲያ
   በጻድቃን
   ምን አለ በጻድቃን፣
   የቤተክርስትያን ጠላት ማህበረ ቅዱሳን።
   ጠይቀኝ፣
   እሽ! የቤተክርስቲያን ልጆች እንዳይታረቁ ጥረት የሚያደርግ ማነው?
   ማህበረ ቅዱሳን ነው።
   ሊቃውንቱና ካህኑ እንዳይታረቁ ደፋ ቀና የሚለው ማነው?
   ማህበረ ቅዱሳን ነው።
   መምህራንንና መዘምራንን ያለ ዳቦ ቅጥያ ስም የሚሰጥ ማነው?
   ቅጥረኛው ማቅ ነው።
   አገርም ቤተክርስቲያንም አንድ እንዳይሆን የመከፋፈል ተልእኮ ያለው ማነው?
   ቅጥረኛው ማቅ ነው።
   ገዳማት እንዲደፈሩ በር የከፈተውና የመክፈት ተልእኮ ያለው ማነው?
   ቅጥረኛው ማቅ ነው።
   የመጨረሻ ጥያቄ፣
   ከመለስካቸው መልሶች አንድ እንኳን እንዴት አልተሳሳትክም?
   በደንብ ተግቸ ስለማጠና እና የቤተክርስቲያን ልጅ ስለሆንኩ፤
   እንዲሁም የተወሰኑትን በተግባር ስለማውቃቸው ነው።

   Delete
 2. ጉድ በል ጎንደር!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 3. አንተ ማን ነህና ስልሰዉ ሃጥያት ትናግራለህ!!! ልቦና ይስጥህ!!!

  ReplyDelete
 4. he used to oppose Mahibere Kidusan, and now MK is celebrating because they think they got him. However, there are so many teachers, professors, and so many professionals who oppose the evil political organization, MK (Mahibre kidusan).

  ReplyDelete
 5. hahahahaah nege demo manenwe sekere metlute

  ReplyDelete
 6. ዋናው የቤተ ክርስቲያናችን ድክመት
  ከዲያቆን ሰባኪ ቄስ ጳጳስ ድረስ አብዛኛዎቹ ያልተማሩ
  በወንጌል ያልታነጹ መንፈሳዊ ባሕርይ የማይታይባቸው መሆናቸው ነው
  ለወንጌል ሃዋርያነት መጠራት ብቃት ላላቸው ነው
  የነ ቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት ብቻሳይሆን ሕይወታቸውም ያስተምረናል
  -ድንኩዋን እየሰፋ እጁ ባፈራው ነበር እየኖረ ያገለገለው
  የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 20
  33 ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤
  34 እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ።
  35 እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።
  36 ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ።

  ዛሬ የምናያቸው ረጅም ቀሚስ ለብሰው የወርቅ መስቀል አንጠልጥልው
  ገንዘብ የሚሰበስቡ ናቸው
  ማነው መምህርህ ማነው ያደቆነህ ያቀሰሰህ ብሎ ማን ይጠይቀቸው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዋናው የቤተ ክርስቲያናችን ድክመት ከዲያቆን ሰባኪ ቄስ ጳጳስ ድረስ አብዛኛዎቹ ያልተማሩ
   በወንጌል ያልታነጹ መንፈሳዊ ባሕርይ የማይታይባቸው መሆናቸው ነው

   Idiot persons analysis. How dare you say? what about you? "Yanebebu yetemerameru" pentewochim kemtilachew sewoch yeteshale migbar ayitaybachewum.

   Delete
  2. አንተ ማን ነህ ስለ እነሱ አለመማር የምትናገረው ለምን ይዋሻል ይሄ ብሎግ የፕሮቴስታንቶች መሆኑ ግልፅ ነው ሁላችንም እናውቃለን እኔ መፅሐፍ ቅዱስ ውሸትን የፈቀደበት ቦታ ብታሳየኝ ደስ ይለኛል እስልምናና ፕሮቴስታንቶችን አንድ ከሚያደርጋቸው ነገሮች ውስጥ ሁለቱም ስለ ሐይማኖታቸው ውሸታሞች መሆናቸው ነው መምህር ምህረቴብ ለሙስሊሙም ለ መናፍቁም መልስ ስለሚስጥ ነው ይህ ሁሉ የ ሃሰት የክስ ወንጀል የቀረበው ለነገሩ የዲያቢሎስ ስራ እኮ የሃሰት ክስ ይዞ በጌታ ፊት መቅረብ ነው ስለዚህ ስራች ሁ ነው

   Delete
  3. አንተ ማን ነህ ስለ እነሱ አለመማር የምትናገረው ለምን ይዋሻል ይሄ ብሎግ የፕሮቴስታንቶች መሆኑ ግልፅ ነው ሁላችንም እናውቃለን እኔ መፅሐፍ ቅዱስ ውሸትን የፈቀደበት ቦታ ብታሳየኝ ደስ ይለኛል እስልምናና ፕሮቴስታንቶችን አንድ ከሚያደርጋቸው ነገሮች ውስጥ ሁለቱም ስለ ሐይማኖታቸው ውሸታሞች መሆናቸው ነው መምህር ምህረቴብ ለሙስሊሙም ለ መናፍቁም መልስ ስለሚስጥ ነው ይህ ሁሉ የ ሃሰት የክስ ወንጀል የቀረበው ለነገሩ የዲያቢሎስ ስራ እኮ የሃሰት ክስ ይዞ በጌታ ፊት መቅረብ ነው ስለዚህ ስራች ሁ ነው

   Delete
  4. diablos mechiem deg sra serto ayawkm.... ewnetm kesu betam yerkech nat ahunm enante rasachu mermru engi sew lay atkesru

   Delete
 7. Egna sewun anketelim. Geta Eyesusin enji. Hatiyat yelelebet Mihereteabin yiwgerew.

  ReplyDelete
 8. ይህ እንግዲህ የናንተ የዓብይ ጾም ወንጌል መሆኑ ነው!!! ዘ ይገርም አለ!!1

  ReplyDelete
 9. men yetebes? yarasachehun htyat lemen atayum? weyolachehuuuuu?

  ReplyDelete
 10. Please don't kill your to talk bad things about others. Use your website to teach bible.

  ReplyDelete
 11. ለቤተ ክርስቲያን መቆማችሁን በዚህ ነው እንዴ የምታሳዩት
  በጣም ታሳዝናላችሁ
  እኛ የሰውን ሐሜት ከመስማት ወንጌል መስማት እንመርጣለን
  ዓላማችሁንም እናውቃለን
  ምዕመኑን ግራ ለማጋባት ብዙ ባትደክሙ
  እባካችሁ በራሳችሁ እና በሌሎች ሕይወት ላይ አትቀልዱ
  ያላችሁት እውነት ከሆነም እንደተባለው ኃጢኣት የሌለበት ምሕረተ አብን ይውገረው

  ReplyDelete
 12. Kentu yesim matfat zemecha! Sew mehonun eresachut? Tesastom kehone wekash alew kesu yeminfeligew kale e/r nw

  ReplyDelete
 13. እንደዚህ ዓይነት የገለሰብ ከመልቀቅ ብትቆጠቡ ጥሩ ይመስለኛል በራስህ ላይ ያለ ጉድፍ ሳትመለከት የወንድምህን ጉድፍ አትይ ተብለዋል እግዚአብሄር ይጠይቀው አስተማሪ ወንጌሎችን ብትለቁ ጥሩ ነው ለብሎጋችሁ

  ReplyDelete
 14. Who in the right mind support drinking and teaching? If it is true he is not a good role model to the Ethiopian orthodox believer it is wrong it is bad. We have to condom this kind of character. The most important things is it true? If it is true it is wrong we do not have to defend him because he is orthodox or MK it does not matter who he is his character is wrong. It does not matter whether he orthodox or protestant what he does is wrong. Whoever supports this drunken person not helping him but you hurting him. After all GOD is watching everybody. We might hide from human but not from GOD. So let us pray, God to help us to do the right thing and guide us to the right direction. May the Lord Jesus help us all.We all are sinner but God alwyes ready to help us if we admit our problem.

  ReplyDelete
 15. http://www.youtube.com/watch?v=4S7Ayc-eHYg

  ReplyDelete
 16. Great mind discuss ideas, moderate mind discuss events,Little mind discuss people. Libona yistilin

  ReplyDelete
 17. Who ever this dikon is, if it is true that he was drunk we should condem him as someone said in the above. He can not be good example of his church. Those of you who defended him will be asked one day and you will be punished for it. When people tell the truth we get something from it. Lets pray for orthodox church.

  ReplyDelete
 18. እውነተኛው ማን ይሆን? የእግዚብሔር መንግሥት ግን በሰብቅ አትወረስም እግዚብሔር ማጣቀሻ አይፈልግም ማንነታችን ያወቀዋል ‹ኢትኰንኑ ከመ ኢትትኰነኑ›

  ReplyDelete
 19. ይህ ሰው የሐይማኖት ጉዳይ ጠበቃ ነኝ ብሎ የሰውን ስም ሲያጠፋ የሚኖር ሰው ነው፡፡ የምህረተአብ ሐይማኖት ሰውን መክሰስ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ እንዲህ ያለው አሳች ምን አይነት ሰው እንደሆነ መግለጥ ስህተት የለውም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. menafik gena taleksaleh memhir mihiretab yasabidachihual banda pente hula

   Delete
 20. enkuan sekere!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 21. Who in the right mind support drinking and teaching? If it is true he is not a good role model to the Ethiopian orthodox believer it is wrong it is bad. We have to condom this kind of character. The most important things is it true? If it is true it is wrong we do not have to defend him because he is orthodox or MK it does not matter who he is his character is wrong. It does not matter whether he orthodox or protestant what he does is wrong. Whoever supports this drunken person not helping him but you hurting him. After all GOD is watching everybody. We might hide from human but not from GOD. So let us pray, God to help us to do the right thing and guide us to the right direction. May the Lord Jesus help us all.We all are sinner but God alwyes ready to help us if we admit our problem.

  ReplyDelete
 22. ዋናው የቤተ ክርስቲያናችን ድክመት
  ከዲያቆን ሰባኪ ቄስ ጳጳስ ድረስ አብዛኛዎቹ ያልተማሩ
  በወንጌል ያልታነጹ መንፈሳዊ ባሕርይ የማይታይባቸው መሆናቸው ነው
  ለወንጌል ሃዋርያነት መጠራት ብቃት ላላቸው ነው

  ReplyDelete
 23. i think most of the comment above yetesafew be mahebere kidusan degafiwoch new....when mahbere kidusan(mahbre seytan }sem siyatefa dem siyafes menem asteyayet yemayset hulu yenesu balegewoch sineku yinchacahlu...

  ReplyDelete
 24. http://www.youtube.com/watch?v=v5xMPKzhKuQ

  This is just a search for drunk pastor, your bosses. Watch and learn. If you need there is a bunch of them on YouTube.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህ ማለት ታድያ ምህረተአብ ትክክል ነው ማለት ነው? ነገ ደግሞ እነርሱ 3 ቢያገቡ እሱም 3 ያግባ? ምነው ጃል ጴንጠዎች ያደረጉት ሁሉ እኛ እናድርገው ማለት እኮ በተዘዋዋሪ እነርሱን ትክክል ማድረግ ነው፡፡ እውነተኛ ክርስቲያን የምህረተአብን ስህተት ስህተት የፓስተሮቹንም ስህተት ስህተት ነው ማለት ያለበት፡፡ ምክንያታዊ ሆነህ የቀረብክ አልመሰለኝም፡፡ እንዲህ ያለ እምነት ዝቅጠት ነው፡፡ በጣም ያሳዝናል፡፡

   Delete
  2. በጣም ተሳስተኃል:: ምህረተአብ ያድርግ አያድርግ ምንም ማስረጃ የለህም:: ያለው የሚጠሉት የመናፍቃን ክስ ብቻ ነው:: እነሱን ለማመን ደሞ በጣም ከባድ ነው:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አለቆቻችሁ እንዴት ሰክረው እንደሚዘባነኑ አሳየውህ:: ለኔ እናንተ የተካናችሁበት ለጌታ የምታደርጉት ውሽት እና የሰው ስም ማጥፋት ነው የእምነት ዝቅጠት ማለት::

   Delete
  3. menafikn mamen kebad new bicha lemin tilaleh 100% wushetam nachew engi pastor ebabun tidnalachihu bilo asbelachew endezih new yemenafik kirsina

   Delete
 25. ምናለ ለኑሯቸው ጥንቁቅ ያልሆኑ ሰባኪዎቻችን እንዲታረሙ ቢደረግ? የምህረተአብ ስራ ተሸፍኖ ከሚቀር ይልቅ እንዲጸጸትበትና በቀጣይ ራሱን እንዲያስተካክል ሌሎቹም ራሳቸውን ቆም ብለው እንዲያዩበት ይህ ጽሑፍ መውጣቱ ጥሩ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ግን ከዚህ አቅጣጫ ነገሩን ማየት የቻልን አልመሰለኝም፡፡ ወንጌል እኮ በዚህም መንገድ ይሰበካል፡፡ እኛ መስማት የምንፈልገው ወንጌል ነው ያለችሁ ሰዎች በጽሑፉ ውስጥ የወንጌል መልእክት የለም ብላችሁ ታስባላችሁ? እባካችሁ እናስተውል፡፡ አለባብሰን ከማለፍ ይልቅ እንደዚህ ባለው መድረክ መተራረም ቢቻል ጥሩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 26. የመጽሐፍ ቃል ስለ ወይን ጠጅ ምን ይላል ?

  1. የወይን ጠጅ ለመባረክ ምክንያት እንደሆነ የሚያስረዳ
  ይስሐቅ ማለት የያዕቆብና የዔሳው አባት ነው ፡፡ የዚህ ዓለም ጉዞውን ማጠናቀቁን በተረዳበት ሰዓት ልጁን ዔሳውን ሊባርከው ፈልጐ ፣
  ”ይስሐቅም። ከልጄ አደን እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አቅርብልኝ አለ። አቀረበለትም፥ በላም፤ የወይን ጠጅ አመጣለት፥ እርሱም ጠጣ።” ዘፍ 27:25 ፡፡ በዔሳው ምትክ ምግብና መጠጡን ያቀረበለት መባረክን አጥብቆ የሚሻው ያዕቆብ ስለነበረ በዔሳው ስም እንደተባረከ ታሪኩ ሰፍሯል፡፡

  2. የእግዚአብሔር በረከትና ጸጋ ውጤትም እንደነበር
  እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል ከምድርም ስብ የእህልንም የወይንንም ብዛት ይስጥህ፤ ዘፍ 27:28 …

  3. ለእግዚአብሔርም የሚቀርብ ቁርባን ስለመሆኑ
  - የመጠጡም ቍርባን የወይን ጠጅ የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ ይሁን። ዘሌ 23:13

  - የኢን መስፈሪያ ግማሽ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለህ።ዘኍልቍ 15:10

  - (ሳሙኤል) ጡትም በተወ ጊዜ ከእርስዋ (ከሐና) ጋር እርሱንና አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣችው ሕፃኑም ገና ታናሽ ነበረ። 1ኛ ሳሙ 1፡24

  4. ጌታችንም የወይን ጠጅን መጠጣቱን ስለመንገሩ
  - የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እነርሱም። እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች። ማቴ 11:19

  - መጥምቁ ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላ የወይን ጠጅም ሳይጠጣ መጥቶ ነበርና። ጋኔን አለበት አላችሁት። የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጥቶአልና። እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ አላችሁት። ሉቃ 7:33-34

  5. ጌታችን ለሌሎች ወገኖችም ወይን ጠጅን እንዲጠጡት ስለማቅረቡ
  ሀ - በቃና ዘገሊላ ሠርግ ላይ ፣ ጌታችን ውኃውን ወደ ጠጅ በመቀየር ሰዎች እንዲጠጡት አድርጓል ፤ ዮሐ 2:7-1ዐ

  ለ - ለደቀ መዛሙርቱም በተለየ ደግሞ የመጨረሻውን የፋሲካ እራት ባበላበት ምሽት
  - ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ። ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር ከዚህ ከወይን ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣውም።ማቴ 26፡27 – 29 ፤ ሉቃ 22፡17-18 ፤ ማር 14፡23-25

  6. ወይን ሊጠጡ የማይገባቸው ተብለው በመጽሐፍ የተለዩ ወገኖች
  - (እግዚአብሔር ለአሮን) እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን ነገር ሁሉ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤ ዘሌ 10:9፤

  - ካህናቱም ሁሉ በውስጠኛው አደባባይ ሲገቡ የወይን ጠጅ አይጠጡ ፡፡ ሕዝ 44፡21

  - አሁንም ተጠንቀቂ (የማኑሄን ሚስት ማለትም የሳምሶንን እናት) የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ።መሣፍ 13፡4 እርሱም እነሆ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አሁን የወይን ጠጅ የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ አለኝ ብላ ተናገረች። መሣፍ 13፡7

  - (የሬካባውያን ልጆች) እነርሱ ግን እንዲህ አሉ። የወይኑን ጠጅ አንጠጣም፥ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እንዲህ ብሎ አዝዞናልና። እናንተና ልጆቻችሁ ለዘላለም የወይን ጠጅ አትጠጡ። በምትኖሩባት ምድር ላይ ብዙ ዘመን እንድትኖሩ፥ በዕድሜአችሁ ሙሉ በድንኳን ውስጥ ተቀመጡ እንጂ ቤትን አትሥሩ፥ ዘርንም አትዝሩ፥ ወይንም አትትከሉ፥ አንዳችም አይሁንላችሁ። ኤር 35፡6-7 ፡14

  - (መጥምቁ ዮሐንስ) በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤ ሉቃ 1፡15
  ይቆየን ....

  ReplyDelete
 27. ክፍል ሁለት
  7. የወይን ጠጅ ስካር ልብን ይነሳልና የተከለከለ ስለሚሆንበት ማስረጃ ፡-
  - ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ዕራቁቱን ሆነ። የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ (ለሴምና ያፌት) ነገራቸው። ዘፍ 9: 20-22 ፡፡ ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ። ዘፍ 9:24 ፤ ካሉት ጥቂት ልጆች ከነዓንን ባሪያ ይሆን ዘንድ ረገመው ፡፡

  - (ከሎጥ ሴት ልጆች ፣ ታላቂቱ ታናሽቱን) ነዪ አባታቻንንም የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፥ ከአባታችንም ዘር እናስቀር። በዚያችም ሌሊት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታላቂቱም ገባች፥ ከአባትዋም ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት። እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፤ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፥ ከአባታችንም ዘር እናስቀር። አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታናሺቱም ገብታ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። ዘፍ 19: 32-35

  - የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል፥ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል በዚህም የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም። ምሳሌ 2ዐ፡1

  - ግልሙትናና የወይን ጠጅ ስካርም አእምሮን ያጠፋል ፡፡ ሆሴ 4፡11

  - እናንተ ሰካራሞች፥ ነቅታችሁ አልቅሱ እናንተም የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉ፥ ዋይ በሉ። ኢዮኤል 1፡5

  8. የሐዋርያው ጳውሎስ ምክር ፡-
  - ልጄ ለሚለው ለጢሞቴዎስ የሰጠው ምክር "ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፥ ወደ ፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ።" 1ኛ ጢሞ 5:23

  - ሥጋን አለመብላት ወይንንም አለመጠጣት ወንድምህም የሚሰናከልበትን አለማድረግ መልካም ነው። ሮሜ 14:21

  - መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤ ኤፌ 5:18

  - እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥1ኛ ጢሞ 3:8

  - እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤ ቲቶ 2:3

  መደምደሚያ
  ሰዎች በዕውቀትም ይሁን ባለማወቅ ፣ ከጥፋት የማናመልጥ ፣ ፈጣሪን በየዕለቱ ምግባራችንና ሥራችን ከማሳዘን የማናርፍ በመሆናችን ፣ በደከምንና በሰነፍን ቁጥር ስህተታችንን እንድናውቀው መመካከሩ አግባብና መልካም ነው ፡፡ ይወገር ፣ ይገደል እስካልተባለ ድረስ ፣ እውነትም እንደተባለው ፣ "በተለይም እግዚአብሔርን ማገልገል ሲገባው ሳለ ፣ በስካር ምክንያት ሳይፈጽም ከቀረ" እንዲታረም በማለት ፣ በአደባባይ ሳይሆን በቅድሚያ በግል መውቀስና መገሠጽ ክርስቲያናዊ አሠራር ይሆናል ፤ ማቴ 18፡15-17 ፣ ሉቃ 17፡3 ፡፡ ያንን ሳይሞክሩ ወዲህ ወደከፍተኛው ሥፍራ (ወደ ህዝብ) አቅርበውት ከሆነ ግን መጽሐፍ የሚያዘውን አልተገበሩትም በማለት ልንከራከር እንችላለን ፡፡ ሌላው እንደቀረበልን አቤቱታ ያለን ስህተት ፈጽሞ ከሆነ ፣ መጀመሪያ የርሱንም አቋምና መግለጫ በመጠየቅ (ምላሱ የተሳሰረበትንና የተንገዳገደበትን ምክንያት አጣርቶ ለማወቅ ሲባል ፣ በስካርም ከሆነ ደግሞ በስህተቱ ተጸጽቶና አዝኖ ከሆነ) አብሮ ማቅረብ ሁላችንንም (ስለ ንስሓ)ያስተምረን ነበር ፡፡ ብዙ ጉዳት ፣ ጠኔ ፣ረሃብና ድካም ሲበዛና ከመጠን ካለፈም ያሰክራልና የተንገዳገደውን ሁሉ ሰክሮ ማለት ትክክል አይመስለኝም ፡፡ በተረፈ በደፈናው ህዝብን ማስተማር የሚገባውን ሰው እንኳን ሰከረ ፣ ቢሰክርስ ምናለበትም ማለት አያስኬድም ፤ መልሶ እኛኑ ያስወቅሳል ፡፡

  ከመንጋው አንዱ እንኳን ቢሆን እንዲጠፋ የአምላካችን ፈቃድ አይደለምና ማቴ 18፡14 ፣ ሰዎች የሚታነጹበትን መንገድ ሁልጊዜም እየፈለግን እንማማር ፤ ከጥላቻ የፈለቀ ሳይሆን ፣ መጽሐፍ የሚያዘውን አግባብ ያለው ወንድማዊ ምክርም እንስጥ ፡፡

  ReplyDelete
 28. ኣይ አባሰላማ በቃ ይህ ነው ስራቹህ እግዚአብሔር ይቅር ይበላቹህ

  ReplyDelete
 29. betam tasazinalachiw

  ReplyDelete
 30. FIND ONLY UR WEAKNESS BEFORE GOING TO OTHERS....

  ReplyDelete
 31. አይጣል ነው!አሁን ማን ይሙት የመ/ ቤት ሠካራም ቢመክሩት ይሰማ ይመስላችኋል?
  ኧረ ምንም!አባባል እንስማ(ተመክሮ ልብ ተፍቆ ጥርስ)አይሆን እንዲያው ድካም እንጂ፤

  ReplyDelete
  Replies
  1. befor u see the others u must think for ur seve

   Delete
 32. It is too shameful. Majority of EOTC preachers have ethical problem. Look, mk fake deacon and priest invaded in our church to destroy the ancient part of regulation. Human nature is not perfect, but such like Meherteab those element paid by mk to demolish the real rule of church. To find out solution, the key point is to demolish the master mind of those group called himself MK from the road map of our church. Moreover here is fake priest in Atlanta, ERGETKULA(mk) no formal education at all, just he was kenjiet cadere in 2005 election in Addis and former solder of DERG. The other shame part is one fat priest he seems like over weight eating junk ,pork and others. He called him self KESIS GIRMA , which is one son with out marriage his x girl name was WOLTMARIAM, she will be ready to speak out in the public. On the contrary he Girma married other woman and serving still in EOTC. Additional, Tebate and Zelebanose are suffering from HIV. ABASELAMA,you are the choice of true eotc that is no voice at church. Please lets working hard to clear this church with real reform to drive in wright direction. Long live for Abaselama death to mk.

  ReplyDelete
 33. Yenezerfen mezmur ebakachihu yezefagnochin mezmur atadamtu neber yalew ahun degmo ersu sekro sigegn min mebal endalebet alawqim

  ReplyDelete
 34. ከላይ በጣም የሚበዛው አስተያየት የተሰጡት ያው በማህበረ ቅዱሳን ጭፍን ደጋፊዎችና አባሎች መሆኑ
  ጥርጥር የለውም። የሆነው ሆኖ በጣም የሚገርመውና የሚያስተዛዝበው ግን፤ ይህ የሰይጣን ማህበር ስም
  ሲያጠፋና ሲያጣላ፣ እንዲሁም ሲከፋፍል፣ የሰው ደም ሲያፈስ አስተያየት ያልሰጠ ሁሉ አሁን የእናንተው
  ጉድና የድርጅታችሁ አባል ወይም ደጋፊ ብልግናና መጥፎ አርአያነት ሲገለጥ ትንጫጫላችሁ። እረ
  እናስተውል//// ሌሎች እውነተኛ ክርስቲያኖችን ግን በየቀኑ የዚህ /የማቅ/ አባልም ሆነ ጭፍን ደጋፊ
  ስማቸውን በሃሰት ስታጠፉና በድንጋይ ስትወግሩ ግን አይታያችሁም። ጌታችንን ግን ማታለል አይቻልም
  የእያንዳንዳችንን ልብ ያውቃል። ዳሩ ይህን የሚያስተውል በእግዚአብሔር የሚያምን ክርስቲያን ነው
  እንጂ፤ ለማቅ ለአስመሳይ ክርስቲያኑ ምን ይከብደዋል/ አታምኑ ፤ የሰይጣን ቡችላ ጥርቅም።

  ReplyDelete
 35. ከላይ በጣም የሚበዛው አስተያየት የተሰጡት ያው በማህበረ ቅዱሳን ጭፍን ደጋፊዎችና አባሎች መሆኑ
  ጥርጥር የለውም። የሆነው ሆኖ በጣም የሚገርመውና የሚያስተዛዝበው ግን፤ ይህ የሰይጣን ማህበር ስም
  ሲያጠፋና ሲያጣላ፣ እንዲሁም ሲከፋፍል፣ የሰው ደም ሲያፈስ አስተያየት ያልሰጠ ሁሉ አሁን የእናንተው
  ጉድና የድርጅታችሁ አባል ወይም ደጋፊ ብልግናና መጥፎ አርአያነት ሲገለጥ ትንጫጫላችሁ። እረ
  እናስተውል//// ሌሎች እውነተኛ ክርስቲያኖችን ግን በየቀኑ የዚህ /የማቅ/ አባልም ሆነ ጭፍን ደጋፊ
  ስማቸውን በሃሰት ስታጠፉና በድንጋይ ስትወግሩ ግን አይታያችሁም። ጌታችንን ግን ማታለል አይቻልም
  የእያንዳንዳችንን ልብ ያውቃል። ዳሩ ይህን የሚያስተውል በእግዚአብሔር የሚያምን ክርስቲያን ነው
  እንጂ፤ ለማቅ ለአስመሳይ ክርስቲያኑ ምን ይከብደዋል/ አታምኑ ፤ የሰይጣን ቡችላ ጥርቅም።

  ReplyDelete
 36. ከላይ በጣም የሚበዛው አስተያየት የተሰጡት ያው በማህበረ ቅዱሳን ጭፍን ደጋፊዎችና አባሎች መሆኑ
  ጥርጥር የለውም። የሆነው ሆኖ በጣም የሚገርመውና የሚያስተዛዝበው ግን፤ ይህ የሰይጣን ማህበር ስም
  ሲያጠፋና ሲያጣላ፣ እንዲሁም ሲከፋፍል፣ የሰው ደም ሲያፈስ አስተያየት ያልሰጠ ሁሉ አሁን የእናንተው
  ጉድና የድርጅታችሁ አባል ወይም ደጋፊ ብልግናና መጥፎ አርአያነት ሲገለጥ ትንጫጫላችሁ። እረ
  እናስተውል//// ሌሎች እውነተኛ ክርስቲያኖችን ግን በየቀኑ የዚህ /የማቅ/ አባልም ሆነ ጭፍን ደጋፊ
  ስማቸውን በሃሰት ስታጠፉና በድንጋይ ስትወግሩ ግን አይታያችሁም። ጌታችንን ግን ማታለል አይቻልም
  የእያንዳንዳችንን ልብ ያውቃል። ዳሩ ይህን የሚያስተውል በእግዚአብሔር የሚያምን ክርስቲያን ነው
  እንጂ፤ ለማቅ ለአስመሳይ ክርስቲያኑ ምን ይከብደዋል/ አታምኑ ፤ የሰይጣን ቡችላ ጥርቅም።

  ReplyDelete
 37. ብዙዎች ስለማኅበረ ቅዱሳን በምንጽፋቸው ጠጣር መልዕክቶች በጣም ሲያዝኑ እንመለከታለን። በኢሜል ወቀሳና ከዚያም ሲያልፍ ስድብ የሚልኩልን አሉ። በጽሁፎቻችን ውስጥ ማኅበሩን ነካ ባደረግን ቁጥር የሚያማቸውና ጸያፍ አስተያየቶችን የሚሰጡንም አጋጥሞናል። አንዳንዶች ስለማኅበረ ቅዱሳን የምንጽፋቸውን እውነትነት አላቸው ብለው እንደሚቀበሉን ሁሉ ተቃራኒውን አመለካከት እንደተለየ ሃሳብ ቆጥረን በአክብሮት እኛም ስንቀበላቸው ቆይተናል። ወደፊትም እንደዚሁ! የሃሳብ ልዩነት በዱላ ማስገደድ እስካልተቀላቀለበት ድረስ ለበጎ ነው እንላለን። እኛ የሚታየንና እውነት ነው ብለን የተቀበልነው ነገር ለእነርሱ እንደስህተት ቢቆጠር አያስገርምም። እኛም ያላየንላቸው የእነርሱ እውነት ሊኖር እንደሚችል አስበንላቸው ተቃራኒ ሃሳባቸውን እናከብራለን። በዚሁ መንገድ የሁለት ወገን እሳቤን ተቀብለን ወደተነሳንበት ርዕሰ ጉዳይ እናምራ።
  ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ተመሠረተ? ብለን የዓመታቱን መታሰቢያ የልደት ሻማዎችን ለመለኮስ ወይም አስልቺ የሆነውን የልደት ትረካ በመዘብዘብ ጊዜ ለማባከን አንፈልግም። ግብሩን ለመናገር ጥያቄዎችን እንጠይቅና እንመርምር።


  ፩/ ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱ የእውቀት ገበታ ነው ወይ?


  ማኅበረ ቅዱሳንን እንደምናየው በጠለቀ ደረጃ ባይሆንም በተወሰነ መልኩ በቤተ ክህነቱ የአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ ያለፉ ሰዎችን ለመያዝ ሞክሯል። አብዛኛው ግን የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ያቃጠላቸው እንደሆኑ የሚናገሩ የሰንበት ት/ቤት አባላትን ያቀፈና ዘግየት ብሎም ከሰንበት ት/ቤትም ሆነ ከፈለገ ሕይወት ት/ቤት ቅርበት ያልነበራቸውን ለመያዝ የሞከረ እንደሆነ ይታወቃል። ይህንና ይህንን የመሳሰሉ ሰዎችን ይዞ እየተጓዘ እዚህ የደረሰው ማኅበር በነማን ምን ሰራ? ምንስ አበረከተ? የሚለውን ልክ ስንመለከት ማኅበሩ እንዳዋቀሩት ሰዎች የማንነት ደረጃ አለኝ የሚለውን የእውቀት ልክ ከነድርጊቶቹ እንመዝናለን እንጂ ዝም ብለን በጥላቻ አንፈርጅም።


  ከዚህ አንጻር ማኅበሩ ሌላውን የሚመለከትበት ዓይን ራሱን ባዋቀረበት አቅምና ባለው የእውቀት ልክ ሳይሆን ነገሮች እየገጠሙ ስለተጓዙለት ብቻ ራሱን የቤተ ክርስቲያኒቱ የእውቀት ገበታ አድርጎ ማስቀመጡ አስገራሚ ይሆንብናል። በማኅበረ ቅዱሳን ሠፈር ራስን በማሳበጥ የእውቀትና የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት አብጠርጥሮ የማወቅ ችግር እንደሌለ ትልቅ ሥዕል አለ። መድረክ ላይ ቆሞ የማስተማር እድልና የእውቀት ጥማት ባላቸው ብዙ ምእመናን ጉባዔ ላይ ተገኝቶ የመናገር እድል በመግጠሙ ብቻ ማኅበሩ የእውቀት ርካታ የማካፈል ብቃት እንዳለው አድርጎ ራሱን አግዝፎ ማየቱን ስናይ ይገርመናል። ብዙዎቹን የማኅበሩ አንጋፋ ተናጋሪዎቹን ትምህርት በአካልና በድምጽ ወምስል መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች የማየት እድሉ ነበረን። አንዳንዶቹ የእውቀት ሳይሆን የንግግር ችሎታ ያላቸው ናቸው። አንዳንዶቹ የእውቀትም፤ የንግግር ችሎታ የሌላቸው ነገር ግን እድል የከነፈችላቸውና የሰው ወፍ የሚረግፍላቸው ስለሆኑ ብቻ መምህራን መሆናቸውን ለራሳቸው የነገሩ ናቸው። አንዳንዶቹ እውቀት ያላቸው ቢሆኑም ነገር ግን እውነቱን በማጣመም ልክፍት የተያዙ ጠማማዎች ሲሆኑ አረፋ እየደፈቁ ለጉባዔ ሲናገሩ ከማንም በላይ የደረሱበትን እውቀት የሚያስተምሩ ይመስላቸዋል። ሌሎቹም እውቀቱ እያላቸው ለማስተማር የማይፈልጉ ጥገኞች/Parasitic/ ሆነው ተጎልተዋል። ከምንም ከምኑም ውስጥ የሌሉ ነገር ግን ክፋትና ሴራ በመጎንጎን የተካኑ የጥፋት መንፈስ ያሰገራቸው ሰዎችንም ተሸክሟል።


  እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ባሉበት ማኅበር ውስጥ በተለየ መደብ በቅንነት፤ በየዋህነትና በእምነት የተሰለፉ አያሌዎች ደግሞ የማኅበሩ ቀኝ እጅ ሆነው እያገለገሉ መገኘታቸው እውነት ነው። አለማወቅ በራሱ ችግር ቢሆንም ቅኖችና የዋሃን ከማኅበሩ ጋር በመቆማቸው የማኅበሩ ድክመት እንደጥንካሬ በመቆጠሩ ብቻ ቅን ማኅበር ነው ሊሰኝ አይችልም።  የቱንም የሰው ሰልፍ ቢሸከም ራሱን ለማቆየት ሌላውን እስካልተጫነ ድረስ ለእኛ ጉዳያችን አልነበረም። ችግሩ የሚነሳው በቤተክርስቲያን ውስጥ ራሱን የእውቀት የመጨረሻ ጥግ አድርጎ ማስቀመጡና ሁሉ ሊመገበው የሚገባው የእውቀት ማእድ በእጁ እንዳለ የሚያስብበት መንገድ ነው ተቀባይነት የማይኖረው።
  ማኅበረ ቅዱሳን ካሰባሰባቸው ሰዎች ዓይነትና ደረጃ አንጻር ስንመዝነው ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮና የተግዳሮቶች ልክና መጠን ጋር በፍጹም መቀራረብ የማይችል ስብስብ ነው። ራሱን ያስቀመጠበትን ስፍራ የሚለካው በቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ድክመቶችና የስብከት ደረጃ እያደገ አለመሄዱ፤ ጥቅመኝነት እያየለ በመምጣቱ የተነሳ ድምጹ የተሰማለት ማኅበር ለመሆን በመብቃቱ እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱ የእውቀት ገበታ ለመሆን ቀርቶ ራሳቸውን ማዳን የቻሉ ሰዎች ስላሉበት አይደለም።

  ReplyDelete
 38. የስብስቦቹን ማንነት ለማሳየት እንደተሞከረው ሁሉ አጋጣሚው የፈጠረላቸውን አጋጣሚ ተጠቅመው ያዳበሩትን የንግግርና ሰው ፊት ቆሞ የመናገር ዓይ ነጥላቸውን የመግፈፍ ብቃት ካልሆነ በስተቀር ቤተክርስቲያኒቱ ከ፬ኛው ክ/ዘመን እስከ ፲ኛው፤ ከዚያም ከ፲ኛው እስከ ፲፭ው ክ/ዘመን ድረስ ያለውን ከዚያም እስከ ዕሥራ ምዕት መባቻ ድረስ ያለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን እድገቶች፤ ጉድለቶች፤ እንከኖችና ተግዳሮቶች በመተንተን ምን ቀረን? ምንስ ሞላልን? ለማለት ብቃት ያለው አይደለም። በተለይም ወንጌልን ከስሙና ከማነብነቡ በላይ አውቀው የሚኖሩበት፤ ኖረውበትም የሚያውቁት ስለመሆኑ እንዲሁም አምልተው፤ አስፍተው ካስተማሩ አበው መምህራንና ከቃለ ሐዋርያት ጋር የጠለቀ ቁርኝት እንዳላቸው ምስክር የሚሰጥባቸው አይደሉም። ይልቁንም ይህ ነገር ጆሮአቸውን ስለሚያሳክካቸው ትውፊትና ባህል ላይ ሙጭጭ ብለው መጣበቅ የሚወዱ መሆናቸውን እናውቃለን። ተረትና ምሳሌ የሚጥማቸው፤ እንደረበናተ አይሁድ የማይኖሩበት የሙሴ ሕግ የሚያቃጥላቸው፤ ትንኝን የሚያጠሩ ናቸው። ወንጌልን፤ ከስሜት ቴኦሪ ለይተው ማየት የማይችሉ በመሆናቸው አውቀናል ብለው ባስቀመጡት ከረጢት ውስጥ ሁሉም እንዲገባላቸው የሚፈልጉ ናቸው። የማኅበሩ ሰዎች ከፍተኛው የእውቀት ጣሪያ ላይ ስለደረሱ ቤተ ክርስቲያኒቱን የመጠበቅና በዚያ እውቀታቸው ልክ እንድትራመድ የማድረግ ትልቅ የምኞት ተስፈኞች ስለሆኑ ሌላውን አፈንጋጭና ሴረኛ አድርገው መፈረጅ ይቀናቸዋል። ራሳቸውን እንደፈጥኖ ደራሽና እንደቀድሞ አዋቂ አድርገው ስዕላቸውን አግዝፈው በማስቀመጥ ተመልሰው በማየት ብቁ ነን በማለት የሚኩራሩ ናቸው። ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለተናዊ እድገትና ጥበቃ ሁሉም አባል መሰለፍ ያለበት እንደመሆኑ መጠን ማኅበረ ቅዱሳንም እንደማኅበር ለዚህ ዓላማ መቆሙ በመልካም ጎኑ ቢታይ ችግር የለውም።
  ጥያቄው የሚነሳው ግን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ምሉዕ ከሆነ የእውቀት ማዕድ ያልዋለበትን ቦታ ራሱን አስቀምጦ ሁሉም በኔ በኩል ይለፍ የሚለው አባዜ ግን አቅሙን የማያውቅ አድርጎታል።

  መናፍቅና ተሀድሶ ብሎ ዘወትር የእርግማን አፉን የሚከፍትበት ጽጌ ስጦታውን በየመድረኩ እያነሳ እድሜውን ሙሉ ሲያላዝን አያፍርም። ስንት ዓመት ሙሉ የሚያወግዘውን ሰው፤ ማኅበሩ አለኝ ከሚለው የእውቀት ጎተራ ውስጥ እየሰፈረ ጽጌን ለመመለስ የ፴ ደቂቃ መድረክ ቢጠየቅ ግን ሊያገኘው በጭራሽ አይፈልግም። ቤተ ክርስቲያኒቱ ጽጌን አውጥታ ከጣለችና ከረሳች ቆይቷል። ማኅበሩ ግን መባነኑ ሁሉ የሚታየው ጽጌ በሚባል መንፈስ ነው። ወይ ጽጌ ከእውቀት ማጣት የተነሳ ጠፍቷል፤ አለያም ማኅበሩ ከእውቀት ማጣት የተነሳ ጽጌን አጥፍቷል። ከሁለት አንዱ ሊሆን የግድ ነው። ነገር ግን ማኅበሩ እድሜውን ሙሉ ጽጌ፤ጽጌ ሲል መኖሩ የእውቀት ጉደለቱን እንጂ ሙላቱን አያሳይምና ሁሉም በኔ ማረጋገጫ ይለፍ የሚለው አዋቂነቱ መዳኛ የሌለው በሽታ ነው። ጽጌ እያሳመነ አስክዷል እያሉ ከማላዘን ይልቅ መንጋ ሁሉ አባል ያለው ማኅበር ተሰብስቦ የአንዱን የጽጌ ያህል አሳምኖ ሰው መመለስ ለምን አቃተው? የሌለ እውቀት ከየት ይመጣል።


  ስናጠቃልል በንዑስ ርዕሳችን ያነሳነውን ጥያቄ ደግመን እንቋጨው። ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱ የእውቀት ገበታ ነው ወይ? ብለን እንጠይቃለን። በብዙ አስተማሪ ተብዬዎቹ አንደበት የምንሰማቸው ትምህርቶች ጆሮን የሚሞሉ ከመሆን አልፈው በልብ ሰሌዳ ላይ ተጽፈው የሚቀሩ አይደሉም። ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱ የእውቀት ገበታ መሆን ይቅርና ተምሮ ለመረዳት ብዙ ዘመን የሚፈጅበት የሰነፍ ተማሪዎች ስብስብና ለማወቅ የእልከኝነት መንፈስ ጠፍንጎ ያሰራቸው ሰዎች የሞሉበት ሥፍራ ነው።


  አንድ ጥሩ ማስረጃ እንናቅርብ። ወደመቀያየም ሳይደርስ በፊት ቀንደኛ የማኅበሩ አባልና በእውቀት ያይደለ ባለእድለኛ ተናጋሪ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ሳን ጆሴ/ ካልፎርኒያ በሚገኘው ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገኝቶ ሴቶች በወር አበባ ወቅት ስላላቸው የርኩሰት ጉዳይ በጉንጩ ከሞላው እውቀት ውስጥ ቆንጥሮ የሚያቀርብ መስሎ ለመታየት ሞክሮ ነበር። ሴቶች ቤተ ክርስቲያን መግባት የተከለከሉት ወር አበባቸው እንደርኩሰት ስለሚቆጠር ሳይሆን ባንድ ቤተ መቅደስ ሁለት ደም መፍሰስ ስለሌለበት ነው ሲል ተደምጧል።። ፍትሐ ነገሥት የተባለው የጥንቱ የሕግ መጽሐፍ ይሁን የቤተ ክርስቲያኒቱ ኦሪታዊ አስተምህሮ እንደሚያስረዳው ግን ሴት በወር አበባዋ ወቅት ምንም ዓይነት አስተማማኝ መከላከያ ብትጠቀምም መግባት አትችልም የሚለው ጥንታዊውን ሕግ ተከትሎ ክርስትና ለማስነሳት ወንድ ከሆነ ፵ ቀን፤ሴት ከሆነች ፹ ቀን እንኳን ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከአጸዱም መግባት የምትከለከለው ከርኩሰቷ እስክትነጻ የሚያዘውን የዘሌዋውያን ፲፪፤፪-፮ ሕግ ለመፈጸም እንጂ ሌላ የአዲስ ኪዳን ሕግ ስላለ አልነበረም። የወለደች ሴት እስከ ሰማንያ ቀን ድረስ የሚፈሳት ደም ስለሌለ ከርኩሰት ጋር ካልተያያዘ በስተቀር የዳንኤል ስለሁለት ደም መቅደስ ውስጥ አይፈስም የሚለው ትረካ ዋጋ የሌለው ፈጠራ ከመሆን ያለፈ አይደለም።

  ReplyDelete
 39. አንድም የኦሪቱ ጥቅስ መቀመጡ ስህተት ይሆንና የዳንኤል አዲስ ትምህርት ተቀባይነት ይኖረዋል አለበለዚያም ቤተ ክርስቲያን ያስቀመጠችው ስለመንጻትና አጸድ የመግባት የክልከላ ሕጎች መሠረት የማኅበረ ቅዱሳኑ ሊቅ የዳንኤል ተረት ውድቅ ይሆናል። እንግዲህ እነዚህ ናቸው የማኅበረ ቅዱሳን የእውቀት ጥግ መምህራንና ሌላውን ለመመዘን የቤተ መቅደሱ ሚዛን ነን ብለው ራሳቸውን አስቀመጡ። ከየት የተገኘ ትምህርት ነው? ብልን ጊዜና ወቅት አሰልጥኖ ካስቀመጣቸው ዐውደ ምሕረት የተፈበረኩ በመሆናቸው ብቻ የቤተ ክርስቲያኒቱ የእውቀት ሙላት አድርገው ራሳቸው ሰየሙ እንላለን። የእነብርሃኑ አድማስንና የሌሎቹን ዘራፍ ትምህርት ሰምተን ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና የልብ ምኞታቸው ጋር እያዛመድን ብናስቀምጥ እጅግ የሚዘገንን ነገር እንሰማለን። ምናልባትም ሌላ ጊዜ በማስረጃ አስደግፈን እንመለስበት ይሆናል።


  2/ ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ የማነው?


  ማኅበረ ቅዱሳን ራሱን የቤተ ክርስቲያኒቱ የእውቀት ሙላትና ጥግ አድርጎ በማስቀመጡ የተነሳ ያለው ጉድለትና እክል ለብዙዎች ውድቀትና የድጥ ጉዞ ምክንያት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሌላው ችግር ራሱ ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው ድርጅት የማነው? የሚለው ጥያቄ ግራ ያጋባናል። ሲቋቋም ጀምሮ ማኅበሩን ቤተ ክርስቲያን ያስፈልገኛል ብላ ያቋቋመችው አይደለም። ራሱ የሕይወት ታሪኩን በሚተነትንበት መድረክ ሁሉ የተቋቋመው በራሱ ትግልና ጥረት እንጂ በቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ውሳኔ አይደለም። ይህንን ትልቅ ጉድለት ለመሸፈን በእነ የጉድ ሙዳዮች በኩል የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥቅም የሚጎዳ፤ ማኅበሩን ደግሞ መንትያው እንደሞተበት የአንበሳ ግልገል የእናቱን ጡት ያለተቀናቃኝ እየጠባ እንዲፋፋ ያደረጉበትን ሕግ አስጸድቀው ማውጣታቸው ካልሆነ በስተቀር ቤተ ክርስቲያን ፈልጋ የተከለችው አይደለም። እሱም ቢሆን የሚለው ቤተ ክርስቲያን ተከለችኝ ሳይሆን የዳቦ ስሜን አቡነ ገብርኤል አወጡልኝ ነው። ከዚህ አንጻር ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የተቋቋመ፤ ያቋቋሚዎቹ መሳሪያ ነው ማለት ነው። ይህ ግልጽ እውነት መሆኑ እርግጥ ነው።


  በአንድ ወቅት አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅና አለኝ ካልክ የሂሳብ ምርመራ እናድርግልህ ቢሉት በጉድ ሙዳዮች በኩል አመቻችቶ ራሱ ያዘጋጀውን መተዳደሪያ ደንብ ጠቅሶ ራሴን ደስ ባለኝ የንስሐ አባቴ በኩል አስመርምሬአለሁ ሲል መመጻደቁ አይዘነጋም። የተቋቋመበትን ዓላማ የሚጻረር ስለሆነ ሰርስረውና ፈርፍረው አባ ሠረቀን ከፊት ለፊታቸው ነቅለው ለመጣል ችለዋል። ከፊታቸው ያለውን ስጋት ገለል ማድረግ ከቻሉ በኋላ በአባ ሠረቀ ብርሃን ላይ ሲወርድ የነበረው የተሐድሶ የስድብ አፍ ወደአፎቱ ተመልሷል። አሁን እንዲያውም የአባ ሠረቀ ብርሃን ጉዳይ ተረስቷል። በተፈገለበት ሰዓት የተጠቀሙበት የክስ ፋይል አገልግሎቱ እንዳበቃ ወዲያው ተዘጋ። ምናልባት አባ ሠረቀ ብርሃን አንድ ቀን ወደአስጊ ሥልጣን ማማ ላይ ብቅ ሲሉ ያኔ ደግሞ የተወለወለው የማኅበሩ ሠይፍ ከአፎቱ ሲመዘዝ እናይ ይሆናል።


  የማኅበሩን ገንዘብ እስኪበቃቸው የተጠቀሙበት እንዳለ ይወራል። የተወራውን ደግሞ ውሸት ነው እንዳንል የሚያደርገን የቤተ ክርስቲያኒቱን የሂሳብ ምርመራ እንደጦር የሚፈራበት መንገድ ነው። ምን ያለበት ዝላይ አይችልም እንዲሉ ሆኖ ማኅበሩ ውስጠ ምስጢሩን ከፍቶ የማይሰጠውና የማያስጠናው የተቋቋመው ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ያቋቋሚዎች የግል መሣሪያ በመሆኑ ምክንያት ነው። በጥቅሉ ማኅበረ ቅዱሳን የማንም ሳይሆን የራሱ የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ንብረት ነው። ንብረትነቱ ግዘፍ ነስቶ የሚንቀሳቀሰው ግን ክፍቱን ባገኛት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለተጠለለ ነው። ከዚያ ባሻገር የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አካል ሆኖ አያውቅም። መሆንም አይፈልግም። ቤተ ክርስቲያኒቱ የማኅበሩን አጠቃላይ ካፒታልና አቅም ታውቃለች? ማን ቢነግራት!


  3/ የማኅበረ ቅዱሳን ዓላማ ምንድነው?


  ማኅበረ ቅዱሳን የእውቀቱ ደረጃና የማንነቱ ነገር በራሱ ተነስቶ ለራሱ የቆመ መሆኑን በሁለት ነጥቦች አይተናል። ሦስተኛውና የመጨረሻው ነጥባችን ማኅበረ ቅዱሳን የሚጓዘው የት ለመድረስ ነው? የሚለውን ጥያቄ በማንሳት በማኅበሩ ላይ ያለንን ጥንቃቄ የተሞላበትን የምልከታ ጥያቄ ማንሳት ግድ ይሆንብናል።
  እናስ የማኅበረ ቅዱሳን ዓላማ ምንድነው? በእውቀት ያልበሰለ፤ የራሳቸውን ስሜትና ማነብነብ እንደእውቀት የሚቆጥሩ፤ መድረኩን በመቆጣጠራቸው ጠበቃ መሆን የቻሉ በሚመስላቸው ሰዎች መሞላቱን ካየን ዘንድ የቤተ ክርስቲያኒቱን የአስተምህሮ ጉድለት ወይም ችግር ለማሟላት ነው ብለን የምንጠብቀው ነገር አይኖርም፤ ያ ማለት ግን የሚመስላቸው የዋሃን የሉም ማለት አይደለም። የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደር ለማረ’ቅ ነው ወይስ ለመተካት? ይህን ግምት በብዙ ትንታኔ ማረጋገጥ ቢቻልም ከምኞትና ገቢር ሩቅ መሆን የተነሳ ፍላጎቱ ቢኖርም ማኅበሩን ብዙም የሚያስጉዝ ስላለሆነ እንዲህና እንዲያ እያልን አንደክምበትም። ይልቅስ ትኩረት እንድንሰጥ የሚያደርገን አንድ ነገር እናንሳ።


  ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ እንደተፈላጊ ምርጥ እቃ ራሱን ሰይሞ ይህንን ሚዛን እያስጠበቁ ሁኔታዎች ከአቅም በላይ ሆነው መጓዝ እስካልከለከሉ ድረስ አብሮ መሄድ የሚለው ሚዛን የሚደፋ ይመስለናል። ይህንንም ከታዋቂ ሰዎች፤ ከምሁራን፤ ከካህናት፤ ከሥራ አስኪያጆችና ከአስተዳዳሪዎች አባላትን ማሰለፍ ከቻለና ምልምል ጳጳሳትን ካደራጀ ኅልውናውን ማስጠበቅ እንደማይከብደው የሚረ’ዳ ማኅበር ነው። ይህንን ለማድረግ ካልሆነ በስተቀር የቤተ ክርስቲያኒቱን አባላት የራሱ አባል አድርጎ መመልመል ባላስፈለገም ነበር። የቤተ ክርስቲያኒቱን አባላት ተቀምጠው ካገኘበት የቤተ ክርስቲያኒቱ መድረክ ላይ ለራሱ ዓላማ ከመመልመል ውጪ ማኅበረ ቅዱሳን የየትኛውንም የሌላ ሃይማኖት ሰዎች ሰብኮ በመወለጥ አባል የማድረግ ብቃት የለውም። እንዲያውም የማኅበረ ቅዱሳን ወከባና ስለላ ሰልችቷቸው፤ የቤተክርስቲያንም አቋም እየመሰላቸው የኮበለሉ ብዙ ሺዎች ናቸው።


  ReplyDelete
  Replies
  1. where did u got a time to wrote this nonsense

   Delete
 40. የማይመቹትን ሰዎች ሲዘምትባቸው አይተናል። የተመቹትን ደግሞ እስከነ ጉዳጉዳቸው ለመሸከም የማይጸየፍ መሰሪ መሆኑንም አስመስክሯል። አባ ፋኑኤልን ሲዘምትባቸውና ለጉድ ሙዳዮች «የወይን አበባዬን» ሲዘፍንላቸው ታዝበናል። ሰሞኑን ደግሞ ዛሩ የተነሳበት ሆኖ ዘፈኑን ወደእርግማን ለመቀየር ፈልጓል። አባ ቀሌምንጦስንም ካስቀመጠበት የእንቧይ ካብ ላይ ለመናድ ዳር ዳር ብሎም ነበር። ያዝ ለቀቅ ማድረግ ጠቃሚ ስልት መሆኑን ያውቅ ይሆናል።
  ከቤተ ክርስቲያኒቱ ትልቁ የአገልግሎት ማማ ይልቅ ቁልቁል ወርደው የተራ ማኅበር አባላት ከሚሆኑ ጳጳሳት ድሮስ ምን ሊገኝ ነበር? ወትሮም «ውረድ ሲዋረድ» ይባል የለ!
  ከዚህ ውጪ ማኅበረ ቅዱሳን፤ የማኅበሩ ቀንደኛ አባላትና አመራሮች የግል ተቋም እንጂ ቤተ ክርስቲያን የምታዘውና የምትናዝዘው የንስሐ ልጇ አይደለም። ነኝ የሚልበትን አንድም አስረጂ ማቅረብ አይችልም። ነው ብሎ የሚመሰክርለት አንድም የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አካል የለም።


  ማጠቃለያ፤


  ማኅበረ ቅዱሳን ከተራ ቁጥር አንድ እስከ ሦስት ድረስ ባሉት ጥያቄዎች ዙሪያ ማለትም የእውቀቱን ልክ በራሱ ሚዛን የሚለካበትን ትምክህት ሳያራግፍ፤ የማን ንብረት መሆኑንና ማን ሊያዘው እንደሚችል በተግባር ሳያረጋግጥ፤ በዚህ አካሄዱም የት ሊደርስ እንዳሰበና ዱካውም በየት እንደሚያልፍ ሳይገለጽና እዚያም እንዴት እንደሚደርስ? መንገዱን ካላሳየ በስተቀር መሰሪ ድርጅት፤ የቤተ ክርስቲያኒቱም ጠንቅ ነው ማለታችንን አንተውም። የምደግፈውንና የማንደግፈውን እንደወርቅ ባብለጨለጨ ልባሱ ሳይሆን የምንለካበት ሚዛን የቤተ መቅደሱ የንጹሕ ዱቄት መስፈሪያ ቆሮስ ውስጥ አስገብተነው ብቻ ይሆናል። ሌሎች በራሳቸው ሚዛኖች ለክተው ይህንን ሚዛን ተቀበሉት ቢሉን ሚዛናችሁ ልከኛ አይደለም እንላለን።
  የንስሐ እድሉን ቢጠቀምና ለእውነት ነገር ዳግመኛ ራሱን ቢሰራ ይበጀው ነበር። ሁላችንም አብረነው በቆምን! ለዚህ የተዘጋጀ ማንነት ስለሌለው እድሉን ለጥፋት እያባከነ በመገኘቱ እናዝናለን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የማህበረ ቅዱሳን ከሳሽ፦
   እስኪ ለግንዛቤ ይረዳን ዘንድ አንተ ካልታረመች ከምትላት ቤተ ክርስቲያን የምትቀበለው ትምህርትና ጴንጤዎቹ የማይቀበሉት ትምህርት አለ? ትገልፅልን? አንተን ኦርቶዶክስ ነኝ ያስባለህ ምንድነው።

   ስለ ታቦት ያለህ አመለካከት?
   ስለ ኢየሱስ ያለህ አመለካከት?
   ስለ ነገረ ድህነት ያለህ አመለካከት?
   ስለ ማሪያም ያለህ አመለካከት?
   ስለ መላዕክት ያለህ አመለካከት?
   ስለ ፃድቃን ሰማዕታት ያለህ አመለካከት?

   ከጴንጤ የሚለይህ ምንድነው?
   አንድስ ከሆነ ለምን እነሱ ጋር አትሄድም?
   እዚህ እስከዛሬ የዘበዘብከው ያንተ ትምህርት ከኔ የተለየ ነው። (ከፅጌ- የአባ ሰላማ ሃሜተኛና ስም አጥፊ ፅጊቱ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ አውቃለሁ።) ስለዚህ ከኦርቶዶክስ የተለየህበትንና እንድትታረም ልዮነትህን እንደፃፍክ ከጴንጤ እምነት ጋር ያለህን ልዮነትና አንድነት ትገልፅልን? ግንዛቤ ማለት ይሄ ነው። አውቃለሁ ይህን ከመመለስ ይልቅ አንድ ቃል ፈልገህ ታዟዙራታለህ። ቀጥታ መመለስንማ መቼ አስተማሩህ። ችክ ብለህ ፈሪሳዊያን ጌታን በውሸት ለቄሳር እንደከሰሱትና ስልጣንህን ሊነጥቅህ ነው እንዳሉት አንተና የምንፍቅና ድርጅትህም ለ20 ዓመታት ትከሳለህ፤ትከሳላችሁ።

   Delete
  2. አንባቢ ከላይኛው ጽሁፍ ንባብ ጐን አንጻራዊ መረጃ እንዲያገኝ በማለት

   http://sfikirbet.files.wordpress.com/2011/12/mk-about-tehadeso-new.pdf

   የማኀበረ ቅዱሳን አባልም ሆነ ደጋፊ አይደለሁም ፤ ተሐድሶ ከሚባሉትም እንደዛው የራቅሁ ነኝ ፡፡ መረጃ ከአንድ ወገን ብቻ ከሆነ የሰዎችን የህሊና ፍርድ ሊያዛባ ስለሚችል ግብዣው ቀርቧል ፡፡ ምኞቴ ግን ቤተ ክርስቲያን የልጆቿን ሰላም አግኝታ መንፈሳዊ ተልእኮዋን ብቻ እንድትወጣ ማየት ነው ፡፡ ትምህርቷን እያነሱ ሊያጠቋት ሲነሱ ዕውቀትና ክህሎቱ ባይኖረኝም ለመከላከል ጥረት አደርጋለሁ ፡፡

   Delete
  3. you are really a researcher. you advised as that fast is free backbite ------- but you back bite Mihretab, MK Aba Samuel etc. You believe that only faith in Christ is enough in you dogma that is why you do not worry for your personality, good works.

   Delete
 41. በጣም የሚገርመው መምህር ምህረተ አብን የምት ሳደቡበት የም ታሳድ
  ዱበት ምክንያት ስታጡ የሐሰት የክስ መዝገባች ሁን ገለጣች ሁ ጽሁፋች ሁ ከ እርኩስ መንፈስ (የቅናት) መንፈስ መሆኑን ከ አጀማመሩ ያስታውቃል መምህር ግን ዛሬም ነገም እውነትን ይናገራል የጨላምውን የዲያቢሎስን ስራ ይገልጣል እናንተም ተሰብስባች አልቅሱ ለመልካም ስራ ያልታደለ አእምሮ ለተንኮል ወደር የለውም እናውቃለን እነማን እንደሆናች ሁ ይሄንን የሐሰት ክስ ያቀረባች ሁት አላነበባች ሁትም እንጅ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሏል ሁሌም ጠላታችን ዲያቢሎስ የክስ መዝገብ ሲያዘጋጅ ፡ ሁሌም የ ሐሰት ክስ ይዞ ሲቀርብ ነው የምናየው ለመምህር ምህረተ አብ ያለንን መልካም ፍቅር እና አክብሮት የማንም ተራ ወሬ ሊያጠፋው አይችልም ወሬኞች ያውሩ ዋጋቸውን የሚሰጣቸው አምላክ አለ

  ReplyDelete
 42. kenante mehal andem hatiat yelelebet binager neber teru "kesashochesh yetalu" yale amlak degefo kewedekebet yansaw kedmo neger awde meheret lay weteto enditay yaregut nachew mewekes yalebachew

  ReplyDelete
 43. እኔ ግራ የገባኝ አንድ ነገር አባ ሰላማ የኦርቶዶክስ ብሎግ ነው ወይስ የጴንጤ፣

  ReplyDelete
  Replies
  1. Bezu neger gera gebtohal!

   Delete
  2. ኸረ እኛም ግራ ገብቶናልኸረ እኛም ግራ ገብቶናል

   Delete
 44. memhir mhereteab is one of the ethiopian orthodox tewahido church preacher,and he has good personality,behavior.
  ABA SELAMA DO NOT BE JEALOUS,before you wright something about MHIRETEAB or others make up your mind and deeply see your self ok!

  ReplyDelete
  Replies
  1. you accept anything mk feeds you but when it's aba selama, you have a problem? friend, it's you that needs to reevaluate your hypocrisy. Did you say anything when mk falsely accused the beloved aba weldetensae? so hypocrite

   Delete
 45. Enante eko be Noah zemen bitnoru noro ende kam betsadiku Noah lay betesalekachihubet neber. Yigermal!

  ReplyDelete
 46. eziyaw bemenderachehu.......benante chikichik egna muslimoch men ageban?.....................,gin gin ...,mekniyatawi lemehon mokru.

  ReplyDelete
 47. መምህር ምህረቴብ ለሙስሊሙም ለ መናፍቁም መልስ ስለሚስጥ ነው ይህ ሁሉ የ ሃሰት የክስ ወንጀል የቀረበው ለነገሩ የዲያቢሎስ ስራ እኮ የሃሰት ክስ ይዞ በጌታ ፊት መቅረብ ነው ስለዚህ ስራች ሁ ነው

  ReplyDelete
 48. I think Mihreteab(Endashaw)has a right to drink any sort of alchol, what is shame is when he tries to reach with this grave personality.

  ReplyDelete
 49. ሲዲውን እየቸበቸበ ኢትዮፅያውያንን ለማጋጨት የሚፍጨረጨር እኩይ

  ReplyDelete
 50. በመጀመሪያ ከአንድ ኦርቶዶክ ተዋህዶ እንዲህ አይነት ነገር ሊፈጠር አይገባም፡፡ ይሁን እንጂ ሆኖም ከሆነ እንኳንስ የቤታችንን ልጅ ይቅርና ሌላ ከውጭ ያለን ሰው ገበና ማውጣት ከክርስቲያን አይጠበቅም፡፡ መ/ር ለብዙዎች መልስ በመስጠት ቤታችንን ያስከበረ ነው፡፡ ቢጠጣና ቢሰክር ሌላም ቢያደርግ እርሱ ከሰው ወገን ወይንም ድግሞ ከስጋና ደም የተሰራ አይደለምን ማንስ ፍጹም ሰው አለ? እንደልቤ የተባለው ንጉስ ዳዊት እንኳን እኮ በሃጢያት ወድቋል፡፡ ትልቁ ነገር ልቡ ወደ አምላኩ መሆኑ ነው መ/ሩ ሰከረ በተባለበት ሌሊት ካምላኩ ጋር ያደረገውን ግንኙነት እኛ ምን እናውቃለን? ፍርድስ /ቅጣት/ ቢገባው ከጌታው ነው እንጂ እኛ የሱን ስም ብናጠፋ ጣጣው ለኛ ነውና እስኪ ባካችሁ የማንንም ስም አታንሱ ህይወት የሆነውን ነገር አስተምሩ ለናንተም ህይወት ለኛም መዳኛ ይሆንልናል፡፡ ይህ ስራ ለናንተ መጥፊ እንጂ መልሚያ አይሆንም እ/ር የመረጠውን ማንም ሊያነሳው አይችልም፡፡ እ/ር ልብ ይስጠን አምን፡፡

  ReplyDelete
 51. very bad action for our religious

  ReplyDelete
 52. hey?the one who write this article,you are hailey sided in one direction,pls make a faire and balanced news,why you hate mk and the spritual teacheres who supporte the aim of mk,pls pray for your selfe!!!

  ReplyDelete
 53. be tam yasazenal ens yemegermaghn lemenden naw benanta batekerstiyanchne yemterbeshaw yewandemeghn gudefe kemawtatgh befete bemejmeria yeraseghn gudefe awta bewnte yegha tekorqarnet ydelem

  ReplyDelete
 54. continue on this taking information because it disturb
  the other.

  ReplyDelete
 55. ስለ ምህረተ አብ ካነሳቸሁ ላይቀር ቅሬታየን እንድትጠይቁልኝ እፈልጋለሁ፤
  ሚስጥራዊዉ ቡድን በሚል ባሳተመው ቪሲዲ በብዛት የጠቀሳቸው ጥቅሶች ከመጽሀፍ ቅዱስ የሉም የት መጡ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እባካችሁ አትልፉ፡ ይህ ብሎግ የማን እንደሆነ እናውቃለን። አንዱን ጣታችሁን ወደ ምህረተአብ ስትጠቁሙ ሌላው ወደ እናንተ እንደሚያመለከት አትዘንጉ። የተዋህዶ ሃይማኖታችን በመናፍቃን ስብከት አትፈርስም። መናፍቃኖች

   Delete
  2. እባካችሁ አትልፉ፡ ይህ ብሎግ የማን እንደሆነ እናውቃለን። አንዱን ጣታችሁን ወደ ምህረተአብ ስትጠቁሙ ሌላው ወደ እናንተ እንደሚያመለከት አትዘንጉ። የተዋህዶ ሃይማኖታችን በመናፍቃን ስብከት አትፈርስም። መናፍቃኖች

   Delete
 56. ወቸው ጉድ! ዘንድሮ ቤ/ክ ከቃሉና ከመንፈሱ ርቃ በስርዓትና ወግ ተጥለቅልቃ ጉልበት አጥታ ደክማ (መድሃኒአለም አንተ ታደጋት) ጉድ በጉድ ኪሳራ በኪሳራ ሆናለች! ምነው እግ/ርስ ዝም አለን? ቤቱ እንዲህ ሲቆሽሽና ሲዝረከረክ? ምናልባት እግዚአብሔርን ከቤቱ ገፍተነው አስወጥተነው ይሆን እንዴ? ምናልባት ለክብራችንና ለምቾታችን ተሸንፈን የልባችንን ደጅ ዘግተነበት በደጅ ቆሞ እያንኳኳ ይሆን እንዴ? እሰቲ እያንዳነዳችን አንድ ጊዜ ቆም ብለን እናስብ እናስተውል ፡፡ እስቲ የምር እግ/ርን እንፈልገው ፤ወደ ቃሉ ፊታችንን እናዙር፤ ለመንፈሱ እንሸነፍ ሁሉን በሚችል ብቻውን እውነተኛ አምላክ በሆነ በእግ/ር ፊት በፀሎት እንሁን የምህረቱን ብዛት የቸርነቱን ልክ እናስተውል (ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው ርኅራኄው አያልቅምና።ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ታማኝነትህ ብዙ ነው።ሰቆቃዌ ኤርሚያስ 3፣23-24 እንደሚል ቃሉ)ወቸው ጉድ! ዘንድሮ ቤ/ክ ከቃሉና ከመንፈሱ ርቃ በስርዓትና ወግ ተጥለቅልቃ ጉልበት አጥታ ደክማ (መድሃኒአለም አንተ ታደጋት) ጉድ በጉድ ኪሳራ በኪሳራ ሆናለች! ምነው እግ/ርስ ዝም አለን? ቤቱ እንዲህ ሲቆሽሽና ሲዝረከረክ? ምናልባት እግዚአብሔርን ከቤቱ ገፍተነው አስወጥተነው ይሆን እንዴ? ምናልባት ለክብራችንና ለምቾታችን ተሸንፈን የልባችንን ደጅ ዘግተነበት በደጅ ቆሞ እያንኳኳ ይሆን እንዴ? እሰቲ እያንዳነዳችን አንድ ጊዜ ቆም ብለን እናስብ እናስተውል ፡፡ እስቲ የምር እግ/ርን እንፈልገው ፤ወደ ቃሉ ፊታችንን እናዙር፤ ለመንፈሱ እንሸነፍ ሁሉን በሚችል ብቻውን እውነተኛ አምላክ በሆነ በእግ/ር ፊት በፀሎት እንሁን የምህረቱን ብዛት የቸርነቱን ልክ እናስተውል (ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው ርኅራኄው አያልቅምና።ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ታማኝነትህ ብዙ ነው።ሰቆቃዌ ኤርሚያስ 3፣23-24 እንደሚል ቃሉ)

  ReplyDelete
 57. lalublta ena letefate yetkefete Yemnafekan blog!!

  ReplyDelete
 58. እናንተ ደደቦች ፤መናፍቆች፤መጀመሪያ ስሌራሳችሁ እወቁ በቅዱሱ ዻዻስ ስም አትንፈቁ...............we don t believe u .

  ReplyDelete
 59. ewenet enanete kerestiyanoche nachehu? ewenetegna kerestian yerasungudefe sayetrege yelela gudefe ayawerame bregete mehereteab btame teru sebaki nwe ysenetune mnafeqe afe yaseyaz egnaneme kemeteratere ymlsne anedebete retue sebaki newe egziabehere yaglegelote zmenune yabezalete. enanet gene yehenene tsehufe badebabaye mawetatachehu esune lemasetemar sayehone hayemanotachenen lemanequasheshena lemenafeqane asalefachehu lmesetet newe lesu asebachehu bihonema adebabay kemawerate yeleq mmeherune kuche aderegachehu yathefawene thefate bmnegre ksehetetu enedimelese badergachehu nebre ahuneme bihone gene esu sewe bemehonu tefate athefa lezaweme yalachehute ewenete kehon amelakachenene yeqereta yetyeqale leke sewochune mesa gabezo yeqereta teyequal enedalachehute ?enanetese?ene lenegeru yetsafewene sewe sasebewe anedeme balefewe teru aderego melsachewene kesetachewe menafeqoche anedu aleyame lemene bletegne belo yeqena aberote yemibla sebaki yaganenewe weri yemeselegnale keweche telate yebelete yemigodawe yewesete telate newena.

  ReplyDelete
 60. betame tasazenalachehu

  ReplyDelete
 61. haimanot gin alachihu?

  ReplyDelete
 62. ምነው ሰድባቹ ለሰዳቢ አሳልፋቹ ሰታቹሁን᎐᎐᎐᎐

  ReplyDelete
 63. ምነው ሰድባቹ ለሰዳቢ አሳልፋቹ ሰታቹሁን ስለማምላክ

  ReplyDelete
 64. Filflu he is stand-up comedian ..

  ReplyDelete
 65. ይህ ጦማር ዋነኛ አላማው የቤተክርስቲያንን ጉድፍና ገመና ለጥጦና አጋኖ በማቅረብ ማህበረሰባዊ ተቀባነቱአን ማሳጣት ይሆን?

  ReplyDelete
 66. enante menafkoch ,alamachihu yitawekal, lemn kemahibere kidusan ras lay atwerdum yerasachihun ,chigir satawuku silesew silemn taweralachihu,enawukachihualen kehadiwoch nachihu ,yaltederege tederege eyalachihu yemtaweru asmesay tekulawech ,silerasachihu bicha nuru,enante tesastachihu sewun lemasasat yetechiberebere website bemetekem yemtadergut seytanawi sira beegziabher bicha sayhon besewechim zend yitawekal ,abetu egziabher yikir yibelachihu

  ReplyDelete
 67. kesash hulu tera nachu zero menafek nachu የማህበረ ቅዱሳን ከሳሽ፦
  እስኪ ለግንዛቤ ይረዳን ዘንድ አንተ ካልታረመች ከምትላት ቤተ ክርስቲያን የምትቀበለው ትምህርትና ጴንጤዎቹ የማይቀበሉት ትምህርት አለ? ትገልፅልን? አንተን ኦርቶዶክስ ነኝ ያስባለህ ምንድነው።

  ስለ ታቦት ያለህ አመለካከት?
  ስለ ኢየሱስ ያለህ አመለካከት?
  ስለ ነገረ ድህነት ያለህ አመለካከት?
  ስለ ማሪያም ያለህ አመለካከት?
  ስለ መላዕክት ያለህ አመለካከት?
  ስለ ፃድቃን ሰማዕታት ያለህ አመለካከት?

  ከጴንጤ የሚለይህ ምንድነው?
  አንድስ ከሆነ ለምን እነሱ ጋር አትሄድም?
  እዚህ እስከዛሬ የዘበዘብከው ያንተ ትምህርት ከኔ የተለየ ነው። (ከፅጌ- የአባ ሰላማ ሃሜተኛና ስም አጥፊ ፅጊቱ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ አውቃለሁ።) ስለዚህ ከኦርቶዶክስ የተለየህበትንና እንድትታረም ልዮነትህን እንደፃፍክ ከጴንጤ እምነት ጋር ያለህን ልዮነትና አንድነት ትገልፅልን? ግንዛቤ ማለት ይሄ ነው። አውቃለሁ ይህን ከመመለስ ይልቅ አንድ ቃል ፈልገህ ታዟዙራታለህ። ቀጥታ መመለስንማ መቼ አስተማሩህ። ችክ ብለህ ፈሪሳዊያን ጌታን በውሸት ለቄሳር እንደከሰሱትና ስልጣንህን ሊነጥቅህ ነው እንዳሉት አንተና የምንፍቅና ድርጅትህም ለ20 ዓመታት ትከሳለህ፤ትከሳላችሁ።

  ReplyDelete
 68. ከፕሮቴስታንት /ከተረፈ ንስጥሮሳዊያን ፍሬ ነገር አይገኝም እንኳን በሎጋችሁን አየሁት በጣም ትገርማላችሁ ትክክለኛን ሰው በቀር ሰይጣን እንዴት ይወዳል፡፡እናንተም ስለሰው ብታወሩ ሰውንም ብታጥላሉ ብታሙም እረሱ ግን ከመጀመሪያው እግዚአብሔር ከናቱ ማህፀን የመረጠው ምርጥ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅ ነው፡፡ ምንም በሉ ምንም እርሱ ሰማያዊ ነው !!!!!!!!

  ReplyDelete
 69. hare lemehonu enante eneman nachu talaku abatachnin ye mtsadebu? titawekalachu enante tehadso sithonu lemn orvtgodox nent ilalachu? megemera beyazacht yeflsfina hnymanot emenubet

  ReplyDelete