Sunday, March 17, 2013

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ነው ከተቃውሞው በስተጀርባ የአባ ሳሙኤል እጅ አለ


የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎች ከሰሞኑ የተቃውሞ ድምጽ እያሰሙ ሲሆን በ5/7/2005 ዓ.ም አርብ እለት ጥቁር ቀሚሳቸውን ለብሰው በጠቅላይ ቤተክህነት በር ላይ ተሰልፈው መታየታቸውና ወደውስጥ ሳይገቡ በመቅረታቸውም ወደኮሌጃቸው ተመልሰው ለተወሰነ ጊዜ ተማሪም ሆነ ሰራተኛ እንዳይገባ ሲከለክሉ እንደነበር ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ፡፡ ተማሪዎቹ በኮሌጁ ብልሹ አስተዳደር ምክንያት ከአቡነ ጳውሎስ ዘመን ጀምሮ በኮሌጁ ውስጥ ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ያሏቸውን ችግሮች መሰረት አድርገው የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የቆዩ ሲሆን ጥያቄዎቻቸው ሙሉ በሙሉ ሳይመለሱ እስካሁን ዘልቀዋል፡፡ ከሰሞኑም አዲስ ተቃውሞ መቀስቀሱ እየታየና እየተሰማ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ እስካሁን ሳይሰተካከሉና ሲንከባበሉ የቆዩ አስተዳደራዊ ችግሮችና የምግብ አቅርቦት ጉዳይ ሲሆን ከካፌ ምግብ አቅራቢዎች እስከ ዲኑ አቡነ ጢሞቴዎስ ይነሱልን የሚል ጥያቄ እንደአዲስ ማንሳታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
 
በዚህ በጾም ወቅትና ስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከተመረጡና ከተሾሙ ከጥቂት ቀናት በኋላ ተቃውሞው መነሳቱ ከጉዳዩ በስተጀርባ የሌሎች እጅ እንዳለበት ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ መኖሪያቸውን በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ያደረጉትና ከማንም በላይ ማንነታቸው ከኮሌጁ ተማሪዎች ያልተሰወረው አባ ሳሙኤል በምርጫው ሰበብ በአቤሴሎማዊ እጃቸው የስላሴ ኮሌጅ ተማሪዎችን ወደራሳቸው በመሳብ ከፍተኛ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ቢከፍቱም ለመታጨት እንኳን ሳይበቁ በጊዜ መሰናበታቸው የሚታወስ ሲሆን በምርጫው ቅስቀሳ ወቅት ለተማሪዎቹ ውስጥ ለውስጥ ቃል ገብተውላቸዋል እየተባለ የሚነገረው አንዱ ነገር እርሳቸው ፓትርያርክ ሆነው ቢመረጡ አባ ጢሞቴዎስን ከዲንነት አነሳላችኋለሁ የሚል እንደነበር ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ ከእጩነት በጊዜ መሰናበታቸው የታሰበውን ሁሉ መና ቢያስቀረውም ለክፋት የማይተኙት አባ ሳሙኤል ፕትርክና ቢያመልጠኝም በቀጣዩ ግንቦት የስራ ዘመናቸውን በሚጨርሱት በአባ ፊልጶስ ምትክ ቀጣዩ ስራ አስኪያጅ ሆኜ ብመረጥ ብዙ ነገር እሰራላችኋለሁ በሚል ተማሪዎቹ በአባ ጢሞቴዎስ ላይ እንዲነሳሱ አድርገዋል ነው የተባለው፡፡ በአባ ሳሙኤልና በአባ ጢሞቴዎስ መካከል ልዩነቶች እየሰፉ የመጡት በስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ላይ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች አባ ጢሞቴዎስ አባ ሳሙኤልን ለፓትርያርክነት ብቁ አለመሆናቸውን በመጥቀስ “አንተ እኔ አላውቅህም? 50 ዓመት እንኳን መቼ ሞላህና ነው 50 ዓመቴ ነው የምትለው?” ብለው በመናገራቸውና ለአቡነ ማትያስ ሙሉ ድጋፍ በመስጠታቸው አባ ሳሙኤል ጥርስ ነክሰውባቸዋል ተብሏል፡፡
የአባ ሳሙኤል ዋና አላማ የስላሴ ተማሪዎችን ከአዲሱ ፓትርያርክ ጋር ማጋጨት ሲሆን ለዚህም መረማመጃ ለማድረግ ተማሪዎቹን በመጀመሪያ በአባ ጢሞቴዎስ ላይ ማነሳሳት ነው ተብሏል፡፡ በነማንያዘዋል የሚመራውና የማቅ መጠቀሚያ የሆነው የቲዎሎጂ ምሩቃን ማህበር ከስላሴ ኮሌጅ ግቢ እንዲወጣ በመደረጉ ከአባ ጢሞቴዎስ ጋር መጋጨቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በዚህ አጋጣሚ ብድር ለመመለስ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለዚህም አንዱ ማሳያ ሰሞኑን በማቅ ሳንባ የሚተነፍሰው የቴዎሎጂ ምሩቃን ማህበር ተብዬው ሰዎች ከአንዳንድ ተማሪዎች ጋር መመካከራቸው ነው ይላሉ ምንጮቻችን፡፡ ማቅ የስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን የተሀድሶ መፈልፈያ ነው በሚል ኮሌጁን የማዳከምና ስሙን የማጥፋት ስራ ከቀድሞ ጀምሮ እየሰራ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በኮሌጁ ውስጥ “ጨዋ” አባላቱን በተለይ በማታው መርሀግብር በመሰግሰግ መምህራንን የማሸማቀቅና እከሌ አያስተምረንም፤ እንደዚህ ያለ ትምህርት ለምን እንማራለን፣ ወዘተ በሚል ኮሌጁን የማወክ ስራ በመስራት ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ አንዳንድ ተማሪዎችም እኩይ አላማውን ስላልደገፉና ስለተቃወሙ በማሳደድና ስማቸውን በማክፋት ብዙ ግፍ ሲፈጽምባቸው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

የአሁኑን የተማሪዎቹን ጥያቄ አስመልክቶ አባ ጢሞቴዎስ የምግብ ቤቱን ኃላፊ በማንሳት ጊዜያዊ ምላሽ ለመስጠት መሞከራቸው ሲታወቅ “ምግባችሁን እየተመገባችሁ እየተማራችሁ ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ” ቢሏቸውም ተማሪዎቹ ጥያቄዎቻችን በሙሉ አልተመለሱም በማለት በተቃውሟቸው መግፋትን መርጠዋል፡፡ ተማሪዎቹ ቀድሞ አባ ሳሙኤልን የሚቃወሙ በተግባራቸው የሚንቋቸውና ቦታ የማይሰጧቸው እንደነበሩ የሚናገሩት ምንጮች በአሁኑ ወቅት የአባ ሳሙኤል ተባባሪ መሆናቸው ብዙዎችን አስግርሟል፡፡

ከሁሉም በላይ በዚህ የጾም ወቅትና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተሾሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ ጾሙ ከገባ አንድም ቀን አስቀድሰው የማያውቁት አባ ሳሙኤል በተማሪዎቹ ችግር ታከው ተቃውሞውን ማነሳሳታቸው ሰውዬው ምን ያህል ችግር ፈጣሪ እንደሆኑ ያሳያል ይላሉ ታዛቢዎች፡፡ ሁሉም ጳጳሳት በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ቤት ያላቸው ቢሆንም አባ ሳሙኤል ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር ስለተጣላሁ ይጎዱኛል ብለው ምክንያት እያደረጉ ወደዚያ ቤት እንዳልገቡና በስላሴ ኮሌጅ መኖርን እንደመረጡ የሚታወቅ ነው፡፡ ከእርሳቸው ህልፈት በኋላም ከዚያ ለመውጣት ያለመፈለጋቸው ምክንያቱ በብዙ ነገር ነጻ ለመሆን ነው ይላሉ የኮሌጅ ግቢ ኑሯቸውን የሚከታተሉ ምንጮቻችን፡፡ በተለይም ቀጣዩ ፓትርያርክ እኔ ነኝ በማለት በስፋት ባስወሩ ሰሞን የስላሴ ኮሌጅ ግቢ ኬክ በጫኑ መኪናዎች ይጨናነቅ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ይህም የሙስናውን መዋቅር ለመዘርጋት የፈለጉ ጥቅመኞች እንኳን ደስ አለዎ በሚል ኬክ ይዘው ይመጡ ስለነበር ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ነገሩ በዚሁ ከቀጠለ ከአባ ጢሞቴዎስ ጋር ያለው ልዩነት ሊሰፋ ስለሚችል ከስላሴ ኮሌጅ ግቢ እንዲወጡ ሊደረግ እንደሚችል የሚገምቱ አልጠፉም፡፡      

     

26 comments:

 1. ምነው ወገን ሁሉ እንዲህ ሆነ፣
  እንደ ቸኮለው ጅብ ፈጠነ፣
  እከተማ ውስጥ መነነ፣
  በሁሉም ነገር ባከነ፣
  የእግዜርን ትቶ የሰጠነ፡፡
  እንኪያ ሰላምቲያ
  በምንቲያ
  በጻድቃን
  ምን አለ በጻድቃን፣
  የቤተክርስትያን ጠላት ማህበረ ቅዱሳን።
  ጠይቀኝ፣
  እሽ! የቤተክርስቲያን ልጆች እንዳይታረቁ ጥረት የሚያደርግ ማነው?
  > ማህበረ ቅዱሳን ነው።
  ሊቃውንቱና ካህኑ እንዳይታረቁ ደፋ ቀና የሚለው ማነው?
  > ማህበረ ቅዱሳን ነው።
  መምህራንንና መዘምራንን ያለ ዳቦ ቅጥያ ስም የሚሰጥ ማነው?
  > ቅጥረኛው ማቅ ነው።
  አገርም ቤተክርስቲያንም አንድ እንዳይሆን የመከፋፈል ተልእኮ ያለው ማነው?
  > ቅጥረኛው ማቅ ነው።
  ገዳማት እንዲደፈሩ በር የከፈተውና የመክፈት ተልእኮ ያለው ማነው?
  > ቅጥረኛው ማቅ ነው።
  የመጨረሻ ጥያቄ፣
  ከመለስካቸው መልሶች አንድ እንኳን እንዴት አልተሳሳትክም?
  > በደንብ ተግቸ ስለማጠና እና የቤተክርስቲያን ልጅ ስለሆንኩ፤
  እንዲሁም የተወሰኑትን በተግባር ስለማውቃቸው ነው።

  ReplyDelete
 2. the news is not a news but a lobby.

  ReplyDelete
 3. ay bariyaw~ nefisih yimaral? korto ketil!!!

  ReplyDelete
 4. ምነው ወገን ሁሉ እንዲህ ሆነ፣
  እንደ ቸኮለው ጅብ ፈጠነ፣
  እከተማ ውስጥ መነነ፣
  በሁሉም ነገር ባከነ፣
  የእግዜርን ትቶ የሰጠነ፡፡

  ጥያቄና መልስ፡
  እሽ! የቤተክርስቲያን ልጆች እንዳይታረቁ ጥረት የሚያደርግ ማነው?
  መልስ፤ ማህበረ ቅዱሳን ነው።
  ሊቃውንቱና ካህኑ እንዳይታረቁ ደፋ ቀና የሚለው ማነው
  መልስ፤ ማህበረ ቅዱሳን ነው።
  የከፋፍለህ ግዛን የቤተክርስቲያን አፋኝ የዱርዬ ቡድን ስብስብ ማን ነው?
  መልስ፤ ቅጥረኛው ማቅ ነው።
  አገርም ቤተክርስቲያንም አንድ እንዳይሆን የመከፋፈል ተልእኮ ያለው ማነው?
  መልስ፤ ቅጥረኛው ማቅ ነው።
  ገዳማት እንዲደፈሩ በር የከፈተውና የመክፈት ተልእኮ ያለው ማነው?
  መልስ፤ ቅጥረኛው ማቅ ነው።
  የመጨረሻ ጥያቄ፣
  ከመለስካቸው መልሶች አንድ እንኳን እንዴት አልተሳሳትክም?
  መልስ፤ በደንብ ተግቸ ስለማጠና እና የቤተክርስቲያን ልጅ ስለሆንኩ፤
  እንዲሁም የተወሰኑትን በተግባር ስለማውቃቸው ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. lemin gin hule silesew hatyat taweralachihu, ebakachihu befird endatiwodku tetenkeku.

   Delete
 5. The evil political and business organization mahibere kidusan has something to do with this. MK is eager and trying so hard to create violence, disturbance and sadness in our church. Mahibere Kidusan is trying to contorol both the church and the government while pretending to be standing for the church. MK is trying to fulfill its objectives; install a government from Shewa, in Ethiopia. The good thing is the government is well aware of MK's dirty tactics and ignorant roles in our church internal affairs. MK will fall like babilon. Believe me and you will see this pretty soon.

  ReplyDelete
 6. By the way the evil Mahibere Kidusan has began to collect money from orthodox christians in the US in the name of teachers or fathers in our churches in Ethiopia. MK has been showing exhibition in Seattle in the names of fathers or teachers. Unfortunately, none of the fund will go to the poor teachers in Ethiopia. For example, MK collected thousands of dollars in the name of Waldiba several months ago; however, only 1% of the collected money was given to Waldiba discriminately.

  ReplyDelete
 7. yigerimal sewiyew betam yamachewal?

  ReplyDelete
 8. "The good thing is the government is well aware of MK's dirty tactics and ignorant roles in our church internal affairs."-----
  By saying this do you really believe the Government is good for our church?????
  Medhanialem ayenachehun yegletlachehu

  ReplyDelete
  Replies
  1. By saying this do you really believe MK is good for our church?????
   Medhanialem ayenotin yegletilot

   Delete
  2. I am not MK .To tell you the truth I heard a lot about Mk some bud and a lot of good things.The more I get a chance to know them I feel like I wish I have devotion and strength to my religion like them.When I say this it is from the bottom of my heart.

   Delete
  3. MK's cons far more outnumber their pros. I wouldn't call that a "good thing for our church". If you're truly sincere about your faith, MK should never be part of your vocabulary. You don't need the approval of some lunatic group to be devout to the Orthodox Church. You should read for yourself and follow on the footsteps of the great orthodox fathers before us, not some phony wannabes

   Delete
 9. ከላይ ከተዘረዘሩት የቀረ ጥያቄ አለኝ
  ጥያቄ፡ የተሐድሶ መናፍቃን ውጋትና የእግር እሳት ማን ነው?
  መልስ፡ ማቅ
  ጥያቄ እንዴት አወቅህ?
  መልስ፡ ከ abaselama ብሎግ የዘወትር ምኞትና ጸሎት!!

  እውነትኛ ሠላም ይስጣችሁ
  ታ.ው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጥቅመኛ እና ንፍቀኛ አውቆ ኣበድ ጥያቄ ማውጣት አይችልም። ጥያቄው ከመልሱ ጋር ካልተዛመደ የክፍሉ ልጅ በሙሉ ይወድቃሉ። ታዲያ እንደዚህ ያለ ሁሉን የሚጠልፍ አስተማሪ ውሎው ከ ስድስት ኪሎ በታች ከ አራት ኪሎ አካባቢ በላይ ሲሆን አዳሩ የተመቸው ቦታ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ከላይ የተጠየቁት እና የተመለሱት በቀላሉ እና ግልጽ በሆነ መንገድ የተዘጋጄ ስለሆነ፤ ሌላ ጥያቄ ሳትጨምርበት ስለ ማቅ ማወቅ የምትፈልገውን ከእርሱ ላይ አጥኑ፡፡ አመሰግናለ!!

   Delete
 10. http://michaelyemane.blogspot.ae/2013/03/1.html

  ReplyDelete
 11. MK has never been devoted to the church. Trust me, there are other insiders (hidden) individuals who are ruling MK from the back seat. MK contributes nothing to our church. They have collected donations, funds, and name it; but none of that money goes to the church. They will contribute may be one percent of what they collect and keep the rest of it in Swiss Bank.

  If MK had no other agendas besides religion, do you think they need to accumulate that much wealth in foreign banks?

  If MK is standing for our church, should MK trade and collect the profit for themselves rather than the individual church they are abusing?

  If MK is standing for our church, should their attempt to disintegrate our church be their number one priority?

  If MK had true intentions in the affairs of our church, do you think MK should lie and let our holy fathers fight against each other?

  I will tell you next. I have more.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ረባክህ ጥላቻ የሰይጣን ነው ወንድም/እህት::አሁን እንዲህ ነደህ ነድህ ምን ታታርፋለህ??? ማህብረ ቅዱሳን እንደሆን መልካም ስራ እይሰራ እንደሆን ስራዉ ይምሰክራል::ከላይ እርእሱ ሌላ ቢሆንም ያለቦታዉ ይህን በማንሳትህ ፍጽም ጥላቻ እንዳለህ ያሳያል::ይህ ደግሞ ክርስቶስ አይወደውም::እናም እባክህ አስተዉል/ይ::

   Delete
 12. Thank you for your advice.This is how I see it.MK follows the steps of our beloved fathers the orthodox tewahido teachings unlike Tehadiso who r following the foot step of Luther.I read my bible myself .When I said the devotion I see the faith and acts on most MKS.As our lord MEdhanialem Eyesus Christos said faith and doings are expected from us.
  When I read this aba selama blog what I understood is a blind hate for MK.which is against being christian.Christos said yemiteluachehun Wededu.
  Medhanialem ke chifen telacha yawetan ,yawetachehu.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I didn't tell you to follow aba selam blog nor Luther. All I said is, read the bible daily and pray. Differentiate between truth from falsehood & always condemn false. Even if that means condemning your current thought. The only way you can know if something is false is by studying the bible, reading early church fathers' commentaries (like haymanote abew)& many other writing by early pious fathers. You assume MK follows the footsteps of our beloved "fathers", but when you read the early church father testimonies, you will be greatly shocked by MK's ideologies (I know I did). MK condemns anyone that speaks the truth (ex. Aba weldetensae and many other scholars of the church). MK encourages you to follow what you been thought from childhood, but what if what you been told from young age is wrong or skewed? St John in his epistle says "Beloved, do not believe every spirit, but test the spirits to see whether they are from God" So I tell you, test every spirit and don't be fooled. Set yourself free by the word of God. MK tells you what you already know & what you want to hear. But the word of God and the orthodox father's testimonies are far from that.

   Delete
 13. I am just an ordinary Tewahedo Church follower. I can say about me reasonably educated Ethiopian. Now I come to believe Mahibre Kidusan is becoming a nested area for some kind of cult. Some of their leaders are seen always strifing to get a lime light of attention.Their rehotorical skill swade many to follow them. Many of their followers turned out to be vigilantes who attack others for having diffrent opinion from their leaders.I have witnessed this in Dallas St.Michael Church and St. Mary Church of Irvin Texas. the same would be true in all churchs from east to west coast. One of their diciples and his spouse were secretely aggitating the youth choirs to incite protest @ Debre Selam Medanealem of Houston so the church would fell under MK. The board members foiled thier attempt at its infantile stage. Soon both fleed to Dallas.

  ReplyDelete
 14. Long before I know MK is existed ,one of my protestant cousin told me that You orthodox Christians are changing to protestant bz listen to Aba Woldetnsae sebket.I started to listen and I came to understand that in between the nice sebket he add something unorthodox.Recently I heard myself when he said I wish all Ethiopia orthodox christians become like TAMRAT LAYNE?what does that mean????convert to protestant?????? and also he said all of you have protestant relatives look how God bless them the only people who are not blessed are Ethiopian orthodox people.BEDFRET he said Ethiopia has 80,000,000 ERESA so there is no need to send human remain to Ethiopia.When I tell you this is not something I heard from somebody else.Even those old Ethiopian religious books like DERSANAT,GEDELAT he said has to be studied again which I believe he is against our beloved old Ethiopian orthodox teachings.My grand father use to pray every morning and read dersane Michael what is wrong with it???Even when he call GOD he always say YENE MEDHANIALEM.But the tehadeso people thought unless we pray protestant style WE don,t know Christos en.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I smell hate.. a bitter hate & ignorace. You had fabricate lies rather than to accept the truth. Why are you afraid of the truth? Who are you to judge Aba weldetensae? What's your education in the church? It's seems you can't even comprehend a simple sentence nevertheless to critic a true scholar of our church. A typical blind sheep of MK.

   Delete
  2. My brother or sister I didn't hate, judge or fabricate anything.If you have Aba Weldetnsae conntact ask him directly.He said it in public.My education in the church is I am learning everyday as YeEgziabher kale is Yehiwotachen MENCHE.About my sentence comprehension that is not the issue.The issue is what kind of teaching in our Church.Is it ok My priest tell me to be LIKE TAMERAT LAYNE?????I know he used to be a true scholar is he still ????Focus on the teaching rather than personality.I am trying to be God's sheep .

   Delete
  3. Forget about tamerat Layne, it's obvious your mind is already preoccupied with politics and worldly materials. Ripping something out of context won't help your narcissistic image neither. Is the ''tamerat Layne saying'' your only problem with Aba? I don't think so. If it was, you'd have said to yourself ''oh jeez maybe I misunderstood him''. But you come up here & tell me to call and ask him? What a joke! Why don't you ask Aba and let us all know what a moron you feel like afterwards. That's why I considered you a hater, hater for the truth. Your main agenda is hidden beneath this false ''tamirat Layne'' accusation. Come out of your shell and say what you have to say. Most probably won't be something we haven't heard before; same old same old

   Delete
 15. ጎበዝ ኸረ የምን ጉድ ነው! የቤተ ክርስቲያን ገመናችን ላደባባይ አትንዙት

  ReplyDelete
 16. eyandahdh akibr abake wemek sibal eyale astemareh amlakachin enant bemefekaker mefthe mefeleg eng sletesadebk mnm yelem ahun alem bitefa ahun yetenagerew andebth mnyhonal?awe sratoa eyetefana adis srat eyewta new ymnastewlew bemanew yewtaw?"ewnet lezelalem tnoralch"tiyakewoch lenante.

  ReplyDelete