Saturday, March 23, 2013

በሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎችና በአስተዳደሩ መካከል ያለው ችግር አልተፈታም

ፍስሐ ጽዮን፣ ዘላለም፣ ፋዘር ጆሲና ማቅ ምን እያደረጉ ነው?
የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎች ትምህርት ካቆሙ ቀናቶች የተቆጠሩ ሲሆን በኮሌጁ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙት ፍስሐ ጽዮን ደሞዝና ዘላለም ረድኤት፣ እንዲሁም የኮሌጁ ዲን አባ ጢሞቴዎስ ካልተነሡ ትምህርት አንጀምርም በሚል አቋማቸው እንደጸኑ ሲሆን ኮሌጁም በበኩሉ እስከ 12/7/2005 ዓ.ም ድረስ ትምህርት ካልጀመሩ በፖሊስ ከኮሌጁ እንዲወጡ እንደሚያደርግ በማስታወቂያ አስታውቋል ተብሏል፡፡

እነዚህ ስማቸው የተጠቀሰው የኮሌጁ ኃላፊዎች በርካታ ችግሮችን በኮሌጁ ተማሪዎች ላይ ሲፈጥሩ የቆዩ መሆናቸው ሲታወቅ በተለይም ፍስሐ ጽዮን ደሞዝ የማቅ ወኪል በመሆንና በጥቅም በመተሳሰር ኮሌጁን ለማቅ ሰዎች መጠቀሚያ በማድረግና እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆችን ተሀድሶ መናፍቅ እያስባለ እንዲባረሩ ሲያደርግና ለማቅ ብሎግ ለደጀሰላም ወሬዎችን በማቀበል ሲሰራ መቆየቱን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ፍስሀ ጽዮን በተለይም ማታ የሚማሩ የማቅ ሰዎች የሚያቀርቧቸውን መሰረተ ቢስ ክሶች በመቀበልና ጉዳዩን በማራገብ መምህራንን ከማስቀየር ተማሪዎችን እስከማስባረር ደርሶ የማቅን ጥቅም በማስጠበቅ ይታወቃል፡፡ ኮሌጁ በቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ ሳይሆን በማቅ ተረታተረት እንዲመራ ለማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ ድጋፍ አየሰጠ እንደሚገኝም ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡

ዘላለም ረድኤት የተባለው በኮሌጁ ውስጥ የሚሰራ ሰውም በተማሪዎች ላይ ልዩ ልዩ ጫና በመፍጠርና የግል ጥቅሙን በማሳደድ የሚታወቅ ሲሆን በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደሌሎቹ መምህራን አንድ ክፍል ቤት የተሰጠው ቢሆንም ኮሌጁ ለትምህርት ማስፋፊያ ተብሎ የተገነባውን ሕንጻ ለንግድ ስራ ሲያከራይ እርሱም አንድ ክፍል አፓርትመንት በ4 ሺህ ብር ተከራይቶ ለፈረንጆች በማረፊያነት በዶላር እያከራየ የሚጠቀም ሆኗል፡፡ በተለይም የአፓርትመንቱ ነዋሪዎች ኮሚቴ ሰብሳቢ መሆኑም ለኪራይ ሰብሳቢነቱ እጅግ ጠቅሞታል ተብሏል፡፡ ኮሌጁ ሕንጻ ያስገነባው ትምህርቱን ለማስፋፋት ቢሆንም ለቤተክርስቲያን የሚበጃትን ሳይሆን ጊዜያዊ ጥቅማቸውን ማሳደድ የሚቀናቸው የኮሌጁ ኪራይ ሰብሳቢ ባለስልጣኖች ህንጻውን በሙሉ በማከራየት ገንዘብ ወደማጋበስና የኮሌጁን የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ጫና ወደማሳደር አዘንብለዋል፡፡ ለምሳሌ የኮሌጁ ላይብራሪ ከተማሪዎቹ ካፌ ጋር የተያያዘና ምቾት የሌለው ክፍል ሲሆን ተማሪዎች ጥራት ያለው አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም፡፡ አዲስ በተሰራው ህንጻም ሆነ በኪራዩ ተማሪዎች አመጠቀማቸውና የኮሌጁ ኑሮ ማሽቆልቆሉ በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ ስለዚህ ለቤተክርስቲያን የሚያስብ አካል ካለ የኮሌጁ አስተዳደር ወደንግድነት የቀየረውን የኮሌጁን ህንጻ በከፊል እንኳ ለኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲያውለውና የተማሪዎችን ችግርም እንዲያቃልል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

እነዚህ ሁለት ግለሰቦች የራሳቸውን ጥቅም በማሳደድ ተማሪዎች ላይ አስተዳደራዊ በደል እየፈጸሙ በመሆናቸው በተማሪዎቹ በኩል ይነሱልን የሚል ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ፋዘር ጆሲ ከተባለው ህንዳዊ መምህር ጋር ባላቸው ግንኙነት እከክልኝ ልከክልህ እየተባባሉ በመጠቃቀምና የኮሌጁ መምህራንና ተማሪዎችን ጥቅም በማስቀረት በደል እየፈጸሙ መሆናቸውን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ይናገራሉ፡፡ ፋዘር ጆሲ በወር 25 ሺህ ብር የሚከፈለው ሲሆን ለኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የሚከፈለው ግን እጅግ ያነሰ በመሆኑ በተማሪዎችና በመምህራን በኩል በክፍያው ላይ ተቃውሞ የሚቀርብ ሲሆን እንዲያስተምር የተደረገውም ዶግማን ነው፡፡ በዚህ በኩል ማቅ ዶግማን  ፋዘር ጆሲ እንዲያስተምር እንደሚፈልግና በወኪሎቹ በኩል ይህን እንዳስፈጸመ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ማቅ ከፈትኩት ባለው የጸረ ተሀድሶ ዘመቻ የህንድን ተሞክሮ ለማቅረብ በዋቢነት የተጠቀመው ይህን ሰው በመሆኑ ሰውዬው በማቅ መንደር ከፍተኛ ተቀባይነት አለው፡፡ ከዚህ የተነሳና ማቅ በአገራችን ሊቃውንት ዘንድ የሚታወቁ ዶግማዊ ጉዳዮች እንዳይነሱና የተማሪዎች አይን በወንጌል እውነት አንዳይገለጥ በማሰብ የዶግማ ትምህርትን ከፋዘር ጆሲ ውጪ ማንም እንዳያስተምር ያደረገው ኮሌጁን ለመቆጣጠር ካለው ሕልም የተነሳ ነው ተብሏል፡፡ ፋዘር ጆሲ በአገራችን በኦርቶዶክስ ውስጥ ያሉትን የቅባት የጸጋና የካራ ባህለ ትምህርቶችንና ሌሎችንም አወዛጋቢ አስተምህሮዎችን ምንነት እንደማያውቅ እየታወቀ ዶግማ እንዲያስተምር መደረጉ ከአገራችን ሊቃውንት ዶግማን የሚያስተምር ጠፍቶ ነወይ የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ፋዘር ጆሲም ለተዋለለት ውለታ በማታው ፕሮግራም ከሚማሩ የማቅ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ወደ መምህርነት እንዲመጡ ለማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

ፍስሐ ጽዮንና ዘላለም ህንድ አገር ስኮላርሺፕ እንዲያገኙ በማድረግ ለዋለላቸው ውለታ ሁለቱ ግለሰቦች ለፋዘር ጆሲ በኮሌጁ ውስጥ ከፍተኛ ሽፋን እንደሚሰጡት የገለጹት ምንጮች ከዚህ ቀደም ለ4 ወር ሳያስተምር 100 ሺህ ብር እንዲከፈለው አድርገዋል፡፡ እርሱም ከአባ ጢሞቴዎስ ጀምሮ በየደረጃው ከ100 ሺህ ብሩ ላይ ስላካፈለ ተቃውሞ ቢነሳበትም እስካሁን የነካው የለም፡፡ በምርጫ 97  ወቅት በተማሪዎች መካከል መከፋፈልን በመፍጠርና ተማሪዎችን ከአስተዳደሩ ጋር በማጋጨት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ይላሉ ታሪኩን የሚያስታውሱት፡፡ ግለሰቡ እንዳይባረር ኮሌጁ ያለዝግጅት የማስተርስ ፕሮግራም እንዲጀምር ከፍተኛ ስራ እንደሰራም ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ኮሌጁ ከፍተኛ የትምህርት ጥራት ችግር እንዳለበት እየተነገረ ባለበት ሁኔታ የማስተርስ ዲግሪ እንዲጀመር መደረጉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል ይላሉ ታዛቢዎች፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ፋዘር ጆሲ ቦሌ ላይ ሬስቶራንት መክፈቱም ታውቋል፡፡ ከዚህ አንጻር የሰውዬው አላማ በቤተክርስቲያን መነገድ መሆኑን አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡

15 comments:

 1. በባለፈው አባ ሳሙኤል ናቸው ብላችሁ ነበር። ዛሬt ደግሞ አባ ጆሲ። ጥላቻና መረጃን መለየት አታውቁም እንዴ? ልቦና ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 2. The primary goals of MK (mahibere Kidusan) aka Mahibere seytan are as follows....

  1. To promote violence, disturb peace, dishonor our church fathers those who oppose its evil ideas.

  2. To nurture and nourish those poor students in our church so that they are founded and built under the ideology of evil MK. Why? This is a long term goal; to completely control the church and government.

  3. By doing these, MK is destroying our church by creating hawkish environment in our church so that church program participants would violate the country's laws because those people will be forced to think that the government is meddling in the church affairs.

  4. MK owns stores that sell products that are useful in our church services. These stores are strategically located next to each church found in the cities of Ethiopia. Before the creation of MK's stores, each church used to sell church products so that the church is benefited. Unfortunately, right now all the profits and sells go to MK. One of the primary concerns of MK is to collect as much money as possible from the mouth of our church.

  I will bring more tactics uses by MK in the near future.

  ReplyDelete
 3. Problem: Mahibere Kidusan

  Solution: Take out those MK members who are trying to disintegrate the college and the church.

  Immediate action should be taken right away; otherwise, MK will try to take the advantage of disturbance in the prominently known peaceful college.

  ReplyDelete
 4. "ከዚህ አንጻር የሰውዬው አላማ በቤተክርስቲያን መነገድ መሆኑን አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡"

  Mk is also making money in the name of the church as well....

  ReplyDelete
 5. You were blaming the student for your previous article as tools of Abba Samuel. When that is not working you are falsely alleviating MK.
  Can't you pass a day without saying for every thing that goes is wrong in Ethiopia by making Mk responsible. Evey body in Ethiopia understood that you driven by your spritual Father are trying to instigateat disturbance in EOTC that was our Memher taug us under the title of " Yebeteh kenat yeblagnael " i Addis Ababa
  God has given us Melekam Ernga! Your days are numbered with grace of God. Please repent before it is too late !

  Peace and progress for EOTC with grace of God!

  ReplyDelete
 6. Hi guys, it is fasting season. Why u don't write something constructive.

  ReplyDelete
 7. እገዚያብሄር ምን ይሰራል ሁሉንም እንደየስራው ይሰጠዋል ለተንንኮል ነጠላቸውን ንጠልጥለው የሚሮጡትን ያጋልጣል ገና ገና ምን አይተው የህ አይበቃም የሐፍረት ሸማ ይከናነባሉ ሰው ሁሉን አውቆ ይህች ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ወንጌል አትሰብክም ሲሉ የነበሩ አባቶች የወንጌል እውቀት የላቸውም እያሉ ሲያዋርዱ የነበሩትን መናፍቃን ባዋረዱና ትክክለኛውን መንገድ ባሳወቁ በቅናት ለስማቸው ቆሙ በእነሱ ያደረ ዲያቢሎስ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲንን ሊበትኑ ተነሱ ለቤተክርስቲን ሳይሆን ለስማቸው ቆሙ ናቸው ማህበር ማህበር በደንብና በህግ ተቁሞ የራሱን ስራ ይስራ ወነወጌሉን ለወነወጌል ገበሬ ይልቀቁ ቢሮ ተቀምጠው ባስተዳደር ተቀምጠው በብእራቸው የሰው ፋይል ይደልዙ ይሰርዙ ወነወጌልን ለባለቤቱ ይተዉት ከምንገዱ ዞር በሉ እንማርበት እናንተ የራሳችሁ ጉዳይ አድመኝነት ፣ ጠብ፣ ክርክር ዋጋ ያስከፍላል፡፡
  እገዚያብሄር ሆይ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ አሜን!!!!!

  ReplyDelete
 8. ማህበሩ እነደ መንግስት ሆነ ፈነጨ ማንም ሳያውቀው ወደፊት ምርጫ ቦርድ ያስመዝግብ ድርጅቱን ከዚያም ያገኛታል ራሱን ይመርምር ግድቡን ባያልፍ ጥሩ ነው፡፡
  አስተኳሽ ኆኖ መቀጠል አይቻልም ጦር ሜዳውን መቃኘት ነው፡፡
  እገዚያብሄር ሆይ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ አሜን!!!!!

  ReplyDelete
 9. የፅጌ አሉባልታ።

  ReplyDelete
 10. Some of the comment may be it's true info. but i didn't accept all yemata temari mk's membere.so,why u tried all z time u critize night student .i remmeber that in my batch appretiated by all.
  secondly,we must use z new building for z college education.And also ,there was no outstanding teacher in HTC except father josi.so we have to ask for z quality edu.
  pls try to idetify first z fact before posting .

  ReplyDelete
  Replies
  1. please don't talk to much. you guys don't know the college problem it is like "afencha sineka ayene yalqesal"newoo. please I leanred at college 5 years our college life was very good.

   Delete
 11. አሁንም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ''ቅባት ፥ ፀጋና ካራ '' የሚባሉ መናፍቃን አሉ እንዴ ? በተቋም ደርጃ ማለቴ ነው ። ካሉ የት ?

  ReplyDelete
 12. Hey Mulugeta ahuneme ke seheteteh atemarem maheber kedusan semune bemateleshet yemiwodeke maheber ayedelem everybody knows MK what it doing.MK is one of the eye of the EOTC whether you believe or not. It will do more and more to expose those who are tehadeso,afekare neway,and asemasayoche...

  ReplyDelete
 13. Why don't the synod in the USA open a theological college? This would have strengthened both the church and the synod. So many people would have joined the college and the church would have benefited from it. Please, tell them to open a college instead of trying to build huge cathedrals or fight against each other. Abuna Melchizedek are you listening me?

  Please, open college and organize Ethiopians for the scholarship. That will do a miracle!

  ReplyDelete
 14. We were hoping the Ethiopian orthodox was guiding to the right direction which is the pure gospel of Jesus Christ, but now we see unnecessary groups of member, company under the name of Ethiopian orthodox religion when it will be over? Let us follow the truth Gospel of Jesus Christ. Please MK Members You can be a MK member but does not mix with the Christian’s believe. If it Christianity the Bible is clear it is only about God the father the son and the Holy Spirit Nothing else. So why are you under the name of the religion? Your believe is not clear if you are believe in so many thing it is not Christianity. Christians means follower of Christ. As someone said let the farmer do his farm land, let the merchant do merchandize let the dispel teach the Gospel of Jesus Christ. As the Bible said on (Corinthians 1:22-27)22 For the Jews require a sign, and the Greeks seek after wisdom:
  23 But we preach Christ crucified, unto the Jews a stumbling block, and unto the Greeks foolishness;24 But unto them which are called, both Jews and Greeks, Christ the power of God, and the wisdom of God.25 Because the foolishness of God is wiser than men; and the weakness of God is stronger than men.26 For ye see your calling, brethren, how that not many wise men after the flesh, not many mighty, not many noble, are called:27 But God hath chosen the foolish things of the world to confound the wise; and God hath chosen the weak things of the world to confound the things which are mighty

  ReplyDelete