Sunday, March 3, 2013

ጥንቆላ - በሀገራችን ፣ በቤተ ክርስቲያናቸን እንዲሁም በእያንዳንዳችን ላይ ሊኖረው የሚችለው ተጽዕኖ

ክፍል ሁለት
ባለፈው ጽሑፌ ጥንቆላ ምን እንደሆነ ጥቂት ለማሳየት ሞክሬያለሁ፤ በሰፊው ግን አልገለጥሁትም። የሰይጣንን ክፋት በሰፊው ከመግለጥ የእግዚአብሔርን ደግነት አጉልቶ መግለጥ ይሻላል የሚል እምነት ስላለኝ ነው። ነገር ግን ወገኖቼ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ጥንቆላን እንደቀላል ልማድ በማየት በጨለማው ገዢ ሥር ሲወድቁ እያየሁ ስለማዝን እውነታውን ለማሳየት ምክሬያለሁ። ዛሬ ደግሞ አንዳድ መናፍስት ጠሪዎችና ደጋሚዎች የሚያጠምቁበትን ዘዴ ከአንድ ደብተራ ጓደኛዬ ያገኘሁትን ምስጢር በጥቂቱ መግለጥ እሞክራለሁ።
አስማቱ በመስቀል፤ በጣት ቀለበት እና በመቁጠሪያ ሊሠራ ይችላል። በመስቀል ቅርጽ እንዲሁም በመቁጠሪያነት ለድግምቱ የሚያገለግሉ እጸዋት ሁለት ናቸው። አንደኛው አርግፍ የሚባል ሲሆን ሁለተኛው ጠንበለል ይባላል። እጸዋቱ በደጋማ ሥፍራዎች ይገኛሉ። በትክል ድንጋይና በሰከላ በብዛት ይገኛሉ። የአስማቱ ባለሙያዎችም ከላይ በጠቅስሁአቸው ቦታዎች አሉ። በተለይ አርግፍ የሚባለውን እንጨት በአካባቢው ያሉ ገበሬዎች እየጠረቡ ለሕጻናት ከሰይጣን እና ከቡዳ ይጠብቃል እያሉ ባንገታቸው ያደርጉላቸዋል።
 ይህ እንጨት የማይሰራበት አስማት የለም ይባላል፤ ሰዎችን ለክፉዎች አሳልፌ እንዳልሰጥ ሁሉን ከመግለጥ እቆጠባለሁ። ለማጥመቅ ሲጠቀሙበት ግን የሚያደርጉትን መናገር ግድ ሆኖብኛል። እንጨቱን ሲቆርጡት የሚደግሙት አላቸው። ሰባት ቀን ሲደግሙ ቆይተው የዶሮ ወይም የሰው ደም ቀብተው ይቆርጡታል። ቅጠሉን በአዲስ ሸክላ[ውሃ ወይም እህል ያልነካው] ዘፍዝፈው አርባ ቀን ከደገሙበት በኋላ ዋናው ለማጥመቅ የተዋረሰው ግለሰብ ይጠመቅበታል። አጥማቂው አርባ ቀን በተደገመበት ውሃ ሲጠመቅ መናፍስት ያለ ከልካይ በብዛት እንደሚያድሩበት ይነገራል።
 ግንዱን ወይም ሥሩን መቁጠሪያ አድርጎ ወይም በመስቀል ቅርጽ ሊይዘው ይችላል፤ ወይም በሰውነቱ ትከሻውና ግንባሩ አካባቢ ሊያስቀብረው ይችላል። በአንድ ገመድ ውስጥ የሚገኙ መቁጠሪያዎች ሁሉ አንድ ዓይነት ወይም የተደገመባቸው እንጨቶች ላይሆኑ ይችላሉ። ከነዚያ መቁጠሪያዎች መካከል አንዷ ወይም ሁለቱ ጠጠሮች የተደገመባቸው ናቸው። መቁጠሪያ ከሄትም ተገዝቶ አንድ ወይም ሁለት የተደገመባቸው ጠጠሮችን በገመዱ ውስጥ መጨመር ይቻላል።
 ሌላው በብር ቀለበት ተደግሞ እጣት ላይ ወይም ክንድ ላይ ሊታሰር ይችላል። በእግዚአብሔር ጥበቃ ሥር ያልተገኘ ማንኛውም ሰው ሁሉ የዚህ አስማት ሰለባ ሊሆን ይችላል። መናፍስቱ ከሰውየው ላይ እየወረዱ እርሱ በሚያጠምቀው ሰው ላይ እያደሩ ይቀልዳሉ። ቡዳ ነኝ ብሎ ጮኾ ከወጣ በኋላ በሌላ ጊዜ አይነ ጥላ ነኝ ይላል። በሌላ ጊዜ የደብተራ ድግምት ነኝ ሊል ይችላል። እራሱን እየቀያየረ ድራማ ይሰራል። ዛሬ ጩኾ ወጥቶ ከሆነ ነገም ተመልሶ ይጮሓል። ይህን ለማረጋገጥ ትንናንትና ጮኾ ወጣለት የተባለውን ሰው በማግስቱ ተከታትሎ ማየት ነው። ተመልሶ ሲጮህ ታገኙታላችሁ። ሰይጣን ሰይጣንን አያወጣውም በገዢ ጋኔንና በተገዢው ጭፍራ የሚከናወን ስምምነት ነው እንጂ። አንዳዴ የስጋ ሕመም ያለበት ሰው በጋኔኑ ሥር ከወደቀ የርሱ ማደሪያ ከሆነ በኋላ ከሥጋ ሕመሙ ሊፈወስ ይችላል። መንፈሱ ታሥሮ ሥጋው ነጻ ሊወጣ ይችላል ማለት ነው። ለምሳሌ በራስ ምታት፣ በአእምሮ ጭንቀት፣ በእበጥ፣ በሽባነት እራሱ ከመታቸው በኋላ ታዋቂ ወደ ሆነ ነባር ጠንቋይ ሄደው እንዲለማመጡት መስዋእቱን እንዲያደርጉ እንዲሰግዱለት ያደርጋል፤ በሽተኛው ሥጋው ይፈወሳል መንፈሱ ግን ይታሠራል። የሰይጣን አገልጋይ ለመሆን ቃል ይገባል፤ በዚህ ጊዜ በህብረተ ሰቡ ቋንቋ ሰከነለት ይባላል። እርሱም በተራው ታዋቂ ጠንቋይ ይሆናል። ብዙ ጠንቋዮች በሽተኛ የነበሩ ናቸው  ሁሉም የሰከነላቸው አሩሲዋ እመቤት ዘንድ ከሄዱ በኋላ ነው ይባላል። እነርሱን ብትጠይቁአቸው ይህን እውነት አይክዱም።
 ሥርዓቱ ይለያይ እንጂ አጥማቂዎችም የሚያደርጉት ይህንኑ ነው። ምዕመናን ግን ባለማወቅ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው ይላሉ። ይህ አባባል እውነት አይደለም። ዛሬ በወረራ መልኩ አጥማቂ ነን የሚሉ ሰዎችን ብናስተውል የማጥመቅ ጥንቆላ የተማሩ እንጂ በእግዚአብሔር የተመረጡ አይደሉም። አጥማቂው ግርማ ቦሌ ጎርጎርዮስ ብሎ ቤተ ክርስቲያን ከፍቶ ሲያጠምቅ ሄጄ ጎብኝቸዋለሁ። በዚያን ጊዜ የርሱ ረዳት የነበሩ ሁለት ግለሰቦች ዛሬ ታዋቂ አጥማቂ ሆነዋል። በተለይ አንዱ የኤምባሲ ሹፌር ሆኖ የኖረ ምንም መንፈሳዊ እውቀት ያልነበረው ነው። የግርማ ረዳት ሆኖ ከቆየ በኋላ በቆይታው ለግርማ የነበረውን ገቢ ሲመለከት አስማቱን ከግርማ ተምሮ አጥማቂ ሆኗል። ዲቁናውንም ቅስናውንም ባጭር ጊዜ ውስጥ ተቀብሎ ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ በማታው ክፍለ ጊዜ መማር ጀምሮ ነበር። በኋላ  ይድራስ ጊዮርጊስ በሰባኪነት ተመድቦ ብዙ ሰው በክሏል። ከዚያም ወደ ፉሪ ሥላሴ ተዛውሮ በዚያ እያጠመቀ ታዋቂ አጥማቂ ሆነ፤ ከዚያም አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጥንቆላ ተከሶ ከሥራ ታገደ፤ እንዳያጠምቅም ማስጠንቀቂያ ተሰጠው። ዛሬ በትንሣኤ ዘጉባዔ ማተሚያ ቤት ይሠራል።
 የፈረንሳይ ኪዳነ ምህረት አጥማቂ ወጣት ተስፋየ የማጥመቅ ጥንቆላ የተማረው ከግርማ ነው የሚል ግምት አለኝ። ሙያው ተለግሶታል፤ ግርማ ልጁን ሀብት ሰጥቶ ጎጆ እንደሚያወጣ መልካም አባት ልጆቹን ጎጆ ማውጣቱ ነው። የጠንቋይ አገልጋይ ሆነው የቆዩ ግለሰቦች ከጥቂት ጊዜ ባኋላ አስማቱን ወርሰው እራሳቸውን የቻሉ አጥማቂዎች ይሆናሉ።
 ባሕታዊ ፍቅረ ማርያም የተባለው አጥማቂ የደብረ ሊባኖስ የቆሎ ተማሪ ነበር። የአባቱ ዛር አርፎበት ከታመመ በኋላ ወዴት እንደ ደረሰ ሳይታወቅ አጥማቂ ሆኖ ብቅ አለ። በአዲስ አበባ ቶታል አካባቢ ዳግማዊት ጻድቃኔ ማርያም ብሎ ማንም ጳጳስ ያልባረከው ቤተ ክርስቲያን ከፍቶ ሲያጠምቅ ቆይቷል። በርካታ ሕዝብ ወደ እርሱ እየሄደ በመጠመቅ የረጅም ጊዜ በሽታ ተሸክሟል። ይህ አጥማቂ ሰዎች የተጠመቁበትን ውሃ ካጠራቀመ በኋላ መልሶ በማጠጣት ግፍ የሠራ የኢትዮጵያ ጠላት ነው። በኋላ አንዳድ የእግዚአብሔር ሰዎች ባካሄዱት ጠንካራ ጸሎትና ተቃውሞ ሥፍራውን እንዲለቅና ወደ ዱከም እንዲሰደድ ተደረገ። ቤተ ክህነቱ ባቀረበበት ክስ ሁለት መቶ ሃያ አምስት ሺህ ብር ጉቦ ከፍሎ ነጻ ወጥቷል። ዛሬ ቤተ ክርስቲያኒቱን ቤተ ክህነቱ ተረክቦ እያስተዳደራት ይገኛል። ባሕታዊው ግን በዱከም እያጠመቀ ትልቅ ባለሀብት ሆኖ በርካታ አውቶቢሶችን ገዝቷል፤ የርሱ መኪኖች ወደ ግሸን ለሚሄዱ ተሳላሚዎች አገልግሎት ሲሰጡ፤ የባሕታዊው መኪኖች እየተባሉ የታቦት ያህል ሲከበሩ ተመልካቻለሁ።
 ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የጠንቋይ አጥማቂዎችን ቀጥረው ሲያሠሩ የወንጌል ሰባኪዎችን ግን ያሳድዳሉ። ይህ ከባድ የቤተ ክርስቲያን ሙስና ነው እላለሁ። አቶ ግርማ የእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ጠንቋይ ነው። በነገራችን ላይ አብያተ ክርስቲያናቱ አጥማቂዎችን የሚቀጥሩበት ምክንያት ቤተ ክርስቲያኑ ገንዘብ ሲቸግረው ነው። ሕንጻ ጀምሮ ከሆነ ማስጨረሻ ሲያጣ፣ ለካህናቱ ደሞዝ ለመክፈል ሲቸገር፣ ወይም በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ገንዝብ ፈላጊ የማፍያ ቡድን ሲኖር ነው። ጠንቋዩ ሲቀጠር ከቢሮ ሰራተኞች ጋር በፐርሰንት ሊከፈለው ውል ከፈጸሙ በኋላ ነው። አጥማቂ እንደማነኛውም አገልጋይ በደሞዝ ሊቀጠር ከቶ አይችልም። በአስማት ከሚያመጣው ገንዘብ በፐርሰንት ይከፈላዋል እንጂ። ዛሬ አጥማቂዎች ባለፎቅና ባለ መኪና የሆኑት በደሞዛቸው ነው ብሎ የሚያስብ ካለ ያው የተጠመቀና በመንፈሱ የታሰረ ማስተዋሉ የተወሰደበት ነው።
 ይህን ሁኔታ ማጋለጥ ለምን አስፈለግ?
የጌታ ቃል ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት 1ቆሮ 5፥14፤ ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ ይልቁንም ግለጡት እንጂ ስለሚል። ኤፌ 5፥11፤ ይልቁንም ኢትዮጵያዊ ወገናችንን ስለምንወድ ከዚህ ክፉ የአጋንንት ሥራ እንዲጠነቀቅ ለማድረግ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ በውስጧ የያዘቻቸውን አደገኛ ጠንቋዮች እንድትለይና እራሷን እንድታጸዳ ለማሳሰብም ነው። ቤተ ክርስቲያን ሰላሟ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚሰብኩ ደቀ መዛሙርትን እያወገዘች ጠንቋዮችን ግን በከፍተኛ ገንዝብ ቀጥራ ትገኛለች። በግፍ የሚሰበሰበው ገንዘብ ሰላሟን ነስቷታል፤ ወንጌልን ይዛ ድሃ ብትሆን ይሻላት ነበር። ሰላሟ ክርስቶስ ነውና።
 የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተ ሰቦች፦
ቤተ ክርስቲያናችን ተሃድሶ ያስፈልጋታል። ብዙ ቆሻሻ የሆኑ የአጋንንት ሥራዎች፤ የሥጋና የደም ትምህርቶች፤ ልዩ ልዩ ባዕድ አምልኮዎች እንደ ልማድ ሆነው ይዘወታራሉ። እነዚህ ሁሉ አጸያፊ ነገሮች ንጹሕ በሆነው በእግዚአብሔር ቃል እየተመረመሩ መወገድ አለባቸው። ይህ ባይሆን ግን ጥፋታችን ሩቅ አይደለም። የመስቀሉን ነገር አጉልተን በመግለጥ ጠላታችንን ከእግራችን በታች እንጣለው።      
በክርስቶስ ያመለጥሁ ደብተራ ነኝ

48 comments:

 1. የአቡነ ማትያስ የመጀመርያ ስራ መሆን የሚገባው በቤተ ክርስትያኗ ስም ብሎግ እና ሚድያ ከፍተው ምንፍቅናቸውን የሚዘባርቁ ተኩላዎችን በህግ ማስዘጋት ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስንቱን የክርስትና ብሎግ በክስ ይዘልቁታል ብለህ ነው? እንዲያው ንደድ ቢልህ ነው እንጂ እንኳን በስመ ክርስትና በክህደትም ቢሆን ኢንተርኔት የነጻ ሃሳብ ማንጸባረቂያ ስልት መሆኑን አታውቅምና አፍህን በትልቅ ዳቦ ዝጋ። ይልቅስ ከዳቦ በተረፈ ጭንቅላትህ መድኃኒቱን ልንገርህ። ንጹሁን የቃል ወተት ለሕዝቡ አቅርብ። አልቀበልም ካለ ፍርዱ በራሱ ነው። ከዚያ ባሻገር ገመናህ እንዳይገለጥ ገመና ገላጮችን ለመዝጋት በመሞከር የሚያኮራ አስተምህሮ ስለሌለህ አፍ ይዝጉልኝ ማለትን መረጥህ። ከፍርሃት ወደ ብርታት፤ እውነት እንዳይገለጥ ከመመኘት ወደ ወንጌል ቃል እንድትመለሱ አንተንና ቢጤዎችህን እግዚአብሔር ይርዳችሁ። አሜን በል!!!!!

   Delete
 2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !March 3, 2013 at 12:11 PM

  Please watch (tekulaw manew?)

  http://www.youtube.com/watch?v=o0I1QCs1ZkA
  http://www.youtube.com/watch?v=jTdi5_gsINU
  http://www.youtube.com/watch?v=pvqrz68xnuc
  http://www.youtube.com/watch?v=SkMC7MAz4_M

  Thank you, በክርስቶስ ያመለጥሁ ደብተራ ነኝ  ReplyDelete
  Replies
  1. ለመሆኑ የኘሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ያዘጋጁት ዘገባ መሆኑን ልብ ብለኸዋል ወይስ ያለ ዕውቀት ጋበዝከን?

   Delete
  2. አይ ምእመን እስቲ ተዎኝ አዉቆ ነዉ::ምእመን ሰላም ብያልሁ::የተሰቀለዉ ብዙ ግዜ ከምትጽፈዉ ከአመላካከትህ ተንሰቼ በግልጽ ፕሮቴስታንት እንደሆንክ ከዚህ በታች በሰጠሁት አስተያየት ፈርጄህ ነበር::እንዲያዉም ከጊዜ ዎደ ጊዜ የምትሰጠዉ አስተያየት ወደ ስህተት እይመራህ እንደሆን እና ከቻልክ አስተያየት ከመስጠት እንድትቆጠብ ነግሬህ ነበር::ነገር ግን ለካ ግምቴ ትክክል ሆኖ ዛሬ በግልጽ የፕሮቴስታን የሆነ ምስል ለጠፍክልን::ለመሆኑ ማስታዎቂያ ለሰራህበት ስንት ከፈሉህ??? በተረፈ ባክህ ከቻልክ አባቶች የሰሩትን ድንበር ለማፍረስ አትታገል መልእክቴ ነዉ::ለእነሱም ለአዘጋጆቹ ዘምዶችህ እስቲ ይህንኑ መልክት አስተላልፍልኝ::በተፈ ሁለት ነገር መናፍቁ በቪዲዮዉ ላይ ካነሳቸዉ እስቲ እንመልክት::
   1/ከእግዚአብሔር ሌላ ስግደት እሚባል ነገር የለም ነዉ የሚለዉ::ለዚህም ማስረጃ ብሎ ያቀረበዉ በራእይ የተጠቀሰዉን ህይለቃል ነዉ::ይኽዉም ራእ.22:8 ::
   8 “ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
   9 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።”
   እስቲ ይህን እንደሚከተዉ አስረዳለሁ ካልገባህ ደግመህ ጻፍልኝ የተሰቀለዉ:: ቨዲዮዉን እንዳመጣህ ቃሉን እስቲ ለነሱም በመዉሰድ ብትተባብረኝ::ጽሁፉ እንዲህ ይነበባል::
   ኢያ. 5 ፡14 “ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ” ለመልአኩ:: ራእ. 22:8 “በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ” እርሱም፦ እንዳታደርገው አለዉ::ካንተ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ አለዉ ::ለምን? ፕሮቴስታንት ዎንድሞች ራእ.22:8ን ይዘዉ ለመልአክት አይሰግደም ይሉናል ::ሚስጥሩ ምንድን ነው? ለኢያሱ የተገለጠ መልአክ ስህተተኛ ነበር? ለምን አትስገድልኝ አላለውም? ለዮሐንስ የተገለጠውስ ለምን አትስገድልኝ አለ? ሁለቱም ጋ መላዕክት ናቸው ሁለቱም ሰዎች ሰግደዋል አንዱ መልአክ ኢያሱ ሲሰግድለት ምንም አላለም ሌላኛው መልአክ ግን ዮሐንስ ሲሰግድለት አትስገድልኝ አለው።እስኪ ይህን ፕሮቴስታንት ዎንድሞች በምን ያስማሙታል? ለመሆኑ ቅዱስ ዮሐንስ እና ኢያሱ ዛሬ እኛ ካለን እውቀት ያነሰ እውቀት ስላላቸው ነው የሰገዱት? እዉነት ለመናገር ኢያሱ እና ቅዱስ ዮሐንስ በዚያን ጊዜም ቢሆን ለማን መስገድ እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ።”እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።” ኢያ. 24:15 ያለ ኢያሱ ሆነ ፍቁረ እግዚእ (የጌታ ወዳጅ የተባለ) የስላሴ ሚስጥ አስፋፍቶ የጽፈ(ዮሐ.1:1) ሰማያዊዉን ህይዎት በራእይ መልእክቱ ይሳየን:: ምድራዊ ሞትን ያልሞተ::ክብሩ እጅግ የበዛ ዮሐንስ ፈጽሞ የአምላክን ክብር ለመልአክ አሳልፈዉ አይሰጡም።ዮሐንስስ መልአክ መሆኑ ጠፍቶት ነው? እንዲህ እንዳንል ከፍ ብሎ ባሳየኝ በመልአኩ እግር.. ይላል:: ዮሐንስ አንድ ግዜ ብቻ አይድለም ለመልአኩ የስገደለት ቀደም ብሎ በራእ. 19:10 ሰግዶለታል:: እንዴት ሁለት ገዜ ተሳስቱአል ይባላል? ለነገሩ አልኩ እንጂ ሶስተኛም ቢያገኝዉ ይስግድለታል ምክንያቱም ዮሐንስ ክርስትያንዊ ግዴታዉን እየተዎጣ ነዉና :: ስለዚህ ለመልአክ የሚሰገደው የአክብሮት ስግደት መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል ።ነገር ግን ዮሐንስ በክብሩ ታላቅ ስለሆነ መልአኩ እኔም እኮ ባርያ ነኝ አትስገድልኝ ብሏል።የተሰቀለዉ አንተን ለማስረዳት እንዲያዉ ለፋሁ እንጂ ስግደት እንኳን ለመልአክ ለሰውም ይሰገዳል።ዘፍ.23፡12 “አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ ...”ዘፍ. 23፡ 7 “አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም፥ ለኬጢ ልጆች፥ ሰገደ።”ዘጸ. 18፡7 “ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ፥ ሰገደም፥ ሳመውም...”ይልብሃል:: አብርሃም ለኬጢ ልጆች የአክብሮት ለእግዚአብሔር የአምልኮ ስግደት እንደሚያስፈልግ ጠንቅቆ ያዉቃልና ።አብርሃም የአምላክን ክብር ለሰው አሳልፎ የሚሰጥ አይነት ደካማ ሰውአይደለም(እነደዚህም ዓይነት ስህተት አይሰራም):: ሠላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን
   2/ ሌላዉ ያነሳዉ” በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታልበዘሁ” የሚለዉን ሃሳብ ባማንሳት ኦርቶዶክስ ተሳስታለች ይላል::ግን ሁሌም የመጽሃፍን ግማሽ ይዘው ሰለሚጉዋዙ ለምስ እንደተባለ ለየቱ የምጽሃፍ ቅዱስ ክፍል እንደ ተነግረ የማያስተዉሉ ናቸዉ::ራእ.22:18:: ነገር ግን ይህ የተነግረዉ ለራእይ ዮሃንስ ብቻ ሲሆን::እርሱ ግን መልእክቱን የሚያሰተላልፈዉ ግልሰብ ለምጽሃፍ ቅዱስ አድርጎ ሲያዎራ የነበረ ስለሆነ ተሳስቱዋል ወንድም የተሰቀለዉ አንተም አብርህ አትሳሳት ምክሬ ነዉ::
   ሌላዉ ብዙው የተለምደዉ ዎቀሳ ነዉ::ደመልሽ ግርማን ሰዉ አስደበደቡ ሲሉ ሰምቻለሁ::መምህር ዘበነንም እንዲሁ ያዉ ጉዳቸዉን እያዎጣ ስላስችግራቸዉ ይምሰለናል ፎቶዉን በምስሉ በፖሊስ እንደሚፈለግ ዎንጀለና ሲያመለሱት ነበር::
   ማሳሰቢያ:ይህን ሃሳብ ያሰፈርኩት ካየሁት ቪዲዮ ክፍል ሁልት መሆንን ይታዎቅልኝ::ሌላዉን ለማየት ግዜ አልነበረኝም::

   Delete
  3. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !March 10, 2013 at 10:01 PM

   That is fine, if we cannot see "how devil is playing in our territory" while our counter part can able to see that and giving us a lesson is not bad. I had seen like that ምእመን. Melkama yesome geze yehonele, Egezehabreh holachenenm Keranione yemenmelektebetn ayen yesten.

   Take care!

   Delete
  4. "Melkama yesome geze yehonele, Egezehabreh holachenenm Keranione yemenmelektebetn ayen yesten."ልዚህ ሃሳብህ እኔም አሜን በያለሁ::እንዲህ በመንፈስ ብንመራረቅ ነዉ ሚሻለዉ:: የተሰቀለዉ ሰላሙ ይብዛልህ::አብዝቼ ስለዎቀስኩህ ይቅርታ::ብዙ እንዳንሳሳት እና የምንዎዳትን ቤት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለባእድ እንዳንሰጣት በማሰብ ነዉ::

   Delete
 3. Endezih aynetun mewagat sigeba ke wendmochachihu Mak (MK) gara min atalachihu? Degmom eko yenesun sim matifat strategy "ye cheke" eyalachihu rasachihum "ye cheke" strategy tiketelalachihu. Wushetamoch.

  ReplyDelete
 4. እግረ መንገዳችንን የወንጌል ቃል እንድንማርበት እጠቅሳለሁ፡፡

  “ከዚህም በኋላ ጋኔን ያደረበትን ዕውር ዲዳም ወደ እርሱ አመጡ፤ ዕውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪናገር ድረስ ፈወሰው። ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና። እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ። ፈሪሳውያን ግን ሰምተው። ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ። ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው። እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም። ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፥ እርስ በርሱ ተለያየ፥ እንግዲህ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች? እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች። ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል። ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም። በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።” ማቴ 12 : 22-32

  ጥያቄዎቼ ይከተላሉ ፡-
  1- እንዲህ ጌታችን ካስተማረን ቃል ውጭ የሆነ ፣ ሰይጣን ሰይጣንን ያስወጣል ፣ አጋንንት አጋንንትን ያስለቅቃል ፣ ዲያብሎስም የመፈወስ ችሎታ አለው የሚለው ትምህርት ከየት ወገን የመጣ ነው ?

  2- የቤተ ክርስቲያን ክህነትን በእርግጥ ከተቀበሉ ፣ ምስጢረ ንስሐ ማለት ስለሌሎች በደል ወይንስ ስለራስ ድክመት መናዘዝና ይቅርታን መጠየቅ የሚያስተምረን ? ምናልባት በደብተራነትዎ የአባይ ጠንቋይን ሙያ ተገልግለውበት ከሆነ ፣ ስምዎን እንደ መሪጌታ ሙሴ በግልጽ አስቀምጠው ፣ የሠሩበትን ሥፍራና ያገለገሉትን ህዝብ ጠቅሰው ይቅር በሉኝ ማለት እንጅ እነ እገሌ መኪና ገዙ ፣ ፎቅ ገነቡ ማለትዎ ንስሐ ሆኖ ስላልተሰማኝ ነው የምስጢረ ንስሐ ጥያቄዬ ወይንስ በዚህ ዘመን የቤተ ክርስቲያን የንስሐ ትምህርቱም ተቀይሮ ይሆን ?

  3- ከአለፈ መግለጫዎ ለመጥቀስና አብረን ለማየት ፡- “ብዙውን ጊዜ አማኞች ለመምሰል የአላህን ወይም የእግዚአብሔርን ስም ያነሳሉ (ጠንቋዮቹን ማለትዎ መሰሎኛል)። እንዲህ የሚያደርጉት ብዙዎች ደንበኞቻቸው ከእስልምና ወይም ከክርስትና የመጡ ስለሆኑ ይመስላል። ኢየሱስ የሚለውን ስም ግን ተሳስተውም እንኳ አይጠሩትም።” የሚል መልካም ቃል በመግቢያዎ አስነብበውናል ፡፡ እኒህ የሚከሷቸው ግለሰብ (ደመላሽ ግርማ) በኢንተርኔት የተለቀቀ ትምህርታቸውና ተአምራቸው በኢየሱስ ስምና በቅዱሳን ጭምርም እንደሆነ አይተናልና ቃልዎን ለማስማማት ምን ልበለው ? ወይስ ጽሁፍዎትን ያርሙታል ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !March 4, 2013 at 7:48 AM

   ምእመን

   You said: "እኒህ የሚከሷቸው ግለሰብ (ደመላሽ ግርማ)"
   ምእመን- I think, your ደመላሽ ግርማ replaced the old or small devil spirit you inherited from your family by the big one. You are lost!

   Delete
  2. So with their view the name" Egziabher " is lesser than" Eyesus" ha ha ha.

   Delete
  3. ሰላም የተሰቀለው
   ለቀናት ተጠፋፍተን ስለከረምን በጣም ናፍቀኸኝ ነበር ፡፡ መቼም ያንተ ክርስትና ረጋ ብዬ ሳስባት በእጅጉ ታስጨንቀኛለች ፡፡ ምንም ህይወት የሌላት የስም ብቻ ስለምትሆንብኝም አዝናለሁ ፡፡ እንደ ወገን ወዲህ ደግሞ እንደ አንድ ወንድም የምመክርህ ፣ ለመጻፍ ስትነሳ መጀመሪያ እንድትጸልይ ነው ፤ ሰይጣን ወደሚፈልገው መሥመር እንዳይወስድህ ይረዳህ ይሆናል ፡፡ ለማስተማር የምትፈልገውን ደግሞ ለይተህ በትክክል አስቀምጠው ፡፡ የዲያብሎስን ቋንቋና ወግ እየተጠቀምህ ኢየሱስን እከተላለሁ ብትለኝ አንተም ልታሳስተን የምትታገል ልዝብ --- ነህ ማለት ነው እላለሁ ፡፡ ብበድል እንኳን ለማስተማር ስትል ቃላት ምረጥ ለማለት ስለፈለግሁ ነው፡፡

   ልብ በል ፤ ከጻፍኩት ውስጥ የወንጌሉ ቃል እንዳለ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተቀዳ ነው ፡፡ ሌላው ጸሐፊው ቢመልሱልኝ በማለት የቀረበው ደግሞ ጥያቄ ነው ፡፡ የተጠየቀው ጥያቄ አግባብ አይደለም የምትልበት መግለጫ ካለህ ፣ ምክንያትህን አስረዳኝ እንጅ “your ደመላሽ ግርማ replaced the old or small devil spirit you inherited from your family by the big one. You are lost!” በማለት አጥንት የሚሰብርና ጋብቻ የሚከለክል የዋልጌ ነገር አታምጣ ፡፡ ስታስበው በዚህ ጽሁፍህ እኔን የሚያንጽ ምን አንዳች ነገር አስቀምጠሃል ? በዛ ላይ ደግሞ የሚያስተናግዱንን ሰዎች መድረክም መልክ አታሳጣባቸው ፡፡ በሥርዓት ልዩነታችንን ፣ እምነታችንን ፣ አቋማችንን ብናስተላልፍ ሰዎች ከአንተም ከእኔም ሆነ ከሌላው ወገን ቃል ብዙ የሚመለከቱት አለ ብዬ አምናለሁ ፡፡ ስለ ጌታ ብለህ አደብ ግዛ ፡፡ የቋንቋ ጀማሪ ይመስል ያለመጥፎ ቃል አይቋጭልህም ፡፡ ልጅ ሆነን እያጫወቱ ቃላት ሲያስተምሩን ንፍጣም ፣ ድዳም .. ይሉን ነበር ፡፡ ጽሁፍህን ሳነበው ያ ዘመን ነው ትዝ የሚለኝ ፡፡

   በተረፈ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲያ እንደማታስተምርና እንደማታሰለጥን እያወቁ ፣ ርሷኑ ተወቃሽና በደለኛ አድርገው እናድሳታለን ይሉናል ፡፡ ጸሐፊው ራሳቸው እንዲያስተምሩን በማለት በጥያቄ አቀረብኩት እንጅ ፣ ቤተ ክርስቲያን ካህናቷን ጠንቁሉ ፣ ስራሥር ማሱ ፣ ቅጠል በጥሱ ፣ መተት ድገሙ ወይም ጻፉ እያለች እንደማታስተምር ልቦናቸው ያውቃል ፡፡ እውነት ሆኖ ቢሰማቸው እንኳን የግለሰቦችን ድክመትና ስህተት ፣ የምታራምደው የዕለት ግብሯ አድርገው መለጠፋቸው ፣ የተላኩ ቅጥረኛ ስለሆኑ ብቻ ነው ማለቱ ይቀለኝ ነበር ፡፡ ነካክተህ ሳልፈልግ አስባልከኝ ፡፡

   Delete
  4. "የተሰቀለዉ" እስቲ ማስረጃህ ምንድን ነዉ::ዝም በሎ ጠፍተሃል ተኮንነሃል በቃ ያልሆነ ምክንያት::ክርስቲያናዊ ያለሆነ አነጋገር ::ቆይ እኔ እምለዉ አንተም እንደሰዎቹ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ተጣልተህ ነዉ ዎይስ እዉነቱ ተጋርዶብህ???

   Delete
  5. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !March 5, 2013 at 8:56 AM

   ምእመን

   ለቀናት ተጠፋፍተን ስለከረምን በጣም ናፍቀኸኝ ነበር , Thank you, sir.
   መቼም ያንተ ክርስትና ረጋ ብዬ ሳስባት በእጅጉ ታስጨንቀኛለች -- Don't worry about me! I am for Jesus.

   ለመጻፍ ስትነሳ መጀመሪያ እንድትጸልይ ነው-- Thank you for your advice, I do pray. I will always condemn the devil spirit, nothing will stop me. Jesus is in my blood. Not your (ደመላሽ ግርማ)
   ልብ በል ፤ ከጻፍኩት ውስጥ የወንጌሉ ቃል እንዳለ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተቀዳ ነው-- Don't you know that Satan even can forward a bible references, I will not consider you a christian being you are citing several bible references, for your deceptive comments and protecting the false prophet your ደመላሽ ግርማ.

   በተረፈ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲያ እንደማታስተምርና እንደማታሰለጥን እያወቁ ፣ ርሷኑ ተወቃሽና በደለኛ አድርገው እናድሳታለን ይሉናል

   Our church needs reform, the church should be bible based and get ride of all ጠንቁላ.

   Delete
  6. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !March 5, 2013 at 9:16 AM

   AnonymousMarch 5, 2013 at 3:55 AM

   ቆይ እኔ እምለዉ አንተም እንደሰዎቹ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ተጣልተህ ነዉ ዎይስ እዉነቱ ተጋርዶብህ???
   Who is ማህበረ ቅዱሳን?
   እዉነቱ ተጋርዶብህ? if you have Lord Jesus the truth will leave with you forever.I have Lord Jesus, by his grace and faith I am born and created again therefore I have a place in the heaven.

   Read bible!

   Delete
  7. “Don't worry about me! I am for Jesus.” ምስክርነትህን አልጠላውም ፤ ነገር ግን ቃሉ ብቻውን ከሆነ ፍሬ የለውም ፤ ሕይወት የለውም ፤ አቅመቢስና ደካማ ነው ፤ የሞተ እምነት ነው ፡፡ ቢቻልህ ክፉውን መንፈስ በጌታ ስም ገስጸህ ዛሬውኑ ተገላገል ፡፡ የስንፍና ቃልና ምግባር ከከናፍርህና ከጽሁፍህ መሃል ሳይለይህ የጌታ ተከታይ ነኝ እያልክ አታስክረኝ ፡፡ ጌታችን እንዳንተ ዓይነት አንድም ተከታይ አልነበረውም ፡፡ ወይስ ክርስትናንና ክርስቲያኖችን ለማሰደብ የተነሳህ ወገን ትሆን ? አሁን አንድ መንገደኛ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ይሰዳደባሉ ብሎ ለማስረጃ ቢቆጥርህ ምን ይሰማሃል ? እባክህን የወንጌል ቃል በየትም በምንም ቢሆን እንማርበታለን የምንለውን መድረክ መልኩን አትቀይረው ፡፡

   “Don't you know that Satan even can forward a bible references,” የብሉይን መጽሐፍ እንደሚያውቅ አውቃለሁ ፡፡ ያንንም ለፈተናና ስግደትን ለመቀበል ሲል ጠቃቀሰው እንጅ ፣ ምእመን ጌታችንን እንዲከተሉ ለማስተማር አይደለም ፡፡ እኔም የመጽሐፍን ቃል መጥቀሴ ጌታ ያስተማረንን ተከተሉ ፣ እንከተል ለማለት እንጅ ፣ ስገዱልኝ ፣ በእኔም አምልኩ ለማለት እንዳልሆነ ሁላችሁም ትረዱታላችሁ ፡፡

   “I will not consider you a Christian” ለእኔም አንተ ግልባጩን ስለሆንክብኝ ነው የተጨነቅሁና የተቸገርኩት ፡፡ እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ ከአባባልህ ስመዝንህ የክርስቲያንነት እጣቢው እንኳን አልፈሰሰብህም ፡፡ ቢቻልህ አሁንም ጊዜው አልመሸም ፤ ራስህን ለመቆጣጠርና ለማሸነፍ ታገለው ፡፡ የስሜታችን ተገዥዎች ከሆንን መንፈሳዊ ጉዞአችን ይደክማል ፤ ይረክስብናል ፡፡

   አንድ ጸሃፊ በእምነት ገና ትኩስ በነበርንበት ዘመን ፣ ጌታን ያገለገልነው እየመሰለን ለማሳመን ያልፈጠርነው ብልሃትና ያልሞከርነው ዘዴ ፣ ከዛ አልፎም ያልወቀስነው ሰው አልነበረም ፡፡ ኋላ ላይ ክርስትናችን እየገባንና እየሰከንን ስንመጣ ፣ ሩጫችን ሁሉ ከንቱና ውሸት መሆኑን ተገንዝበን ፤ ዛሬ ሌሎች እኛ ባለፍንበትና በሮጥንበት እንዳይመላለሱ ብዙ እንመክራለን ፡፡ ነገር ግን ያንኑ የኛኑ አካሄድና ሩጫ የሚደግሙ እያየን ብናስተምርም ሰሚ አላገኘንም የሚል ነገር አካፍለውን ነበር ፡፡ ያንተውን ግን እንደርሳቸው እንኳን ለመገንዘብ በዛብኝ ፡፡ እሰከ ዛሬ ያልተሳደብክበትን ጽሁፍ ለይተህ እስቲ ቁጠረው ፡፡ ከአንድ ወይም ከሁለት አይዘልም ፡፡ አንተም እንደማታቆም ነግረኸኛል ፤ እኔም ደግሞ እንዲህ በማድረግህ አንገቴን አልደፋም ፤ የማደርገውንም አላቆምም ፤ የመንግሥተ ሰማያቱን ነገር እንኳን እንዳንተ መናገር ባልደፍርም ጌታ ትዕግሥቴን ይመለከትልኛል ብዬ እጽናናለሁ ፡፡ በሃሳቤ በአንዳቸውም ላትስማማ ትችላለህ ፤ያም ቢሆን እንኳን አለመስማማትህን የምትገልጸው በስድብ ቃል አይሁን እላለሁ፡፡ አንባቢዎችን አንዳች አያስተምረንምና ፡፡

   “I will always condemn the devil spirit” ይኸም ዓላማህ አያጣላንም ነበር ፤ ነገር ግን እንደ አሁኑ ይዞታህ ከሆነ ቅዱሱን ከርኩሱ የመለየት አቅም ያለህ አልመሰለኝም ፡፡ ያም ስለሆነ ነው እኔን አልፈህ እስከ ቤተ ሰቦቼ የሚደርስ ቃል የመዘዝከው ፡፡ ክፉ መንፈስ ለራሱ ሰላም የለውም ፤ ሌሎቹንም እንዲሁ ሰላማቸውን ይነሳል ፤ በመቃብር ያረፉትን እንኳን ሳይቀር እንዲሁ ይናደፋል ፡፡

   ራስክን ብታንጽበት በማለት ተጻፈ እንጅ ብቻህን እንድትጨፍር እተውልህ ነበር ፡፡ ከላይ እንደ ገለጽኩት እንደ ጳውሎስ በጌታ የመመካት ያህል መመካት ቢያስፈልገኝ ኖሮ ፣ ያለዕውቀት እኔም አፌን የፈታሁት በጸያፍ ቃል ነበር ፤ ጌታችን ከአፍ የሚወጣ ያረክሳል (ማቴ 15፡11 ና18) ብሎ ስላስተማረን ፣ በጌታ ስም የታሠረ ሁኗልና ከእንግዲህ አልጠቀምበትም ፡፡

   በተረፈ መምህር ግርማ የሚፈውሱት በኢየሱስ ስም መሆኑን በድረ ገጽ የተለቀቁት ትምህርቶቻቸው ያስረዳሉና ፤ ጸሃፊው ደግሞ በክፍል አንድ ጽሁፉ ፣ አጋንንት ሳቢዎችና ጠንቋዩች ቢሞቱ እንኳን የኢየሱስን ስም አይጠሩም ብሎን ስለነበረ ፣ ያንን እንዲያስታውስ ቃሉን ጠቅሼ ፣ ማረም የሚፈልገውን ቃል እንዲያስተካክል በጥያቄ መልክ ማቅረቤ ክፉ አልመሰለኝም ነበር ፡፡ አንተ እንደምን ተረድተኸው እንዳስቆጣህ ቆሜም ሆነ ተቀምጨ ባስበው አልመጣልኝም ፡፡ ያቀረብኳቸውን ሦስት ጥያቄዎች ተመልክተህ ሃሳብ ካለህ በሥርዓቱ አካፍለኝና በዛ ዙሪያ እንወያይ ፡፡

   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
  8. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !March 6, 2013 at 7:02 AM

   ምእመን

   Bechelema lemetgotwe, geta eyesuse berhanuen yegeltehe.

   Delete
  9. አይ የተሰቀለዉ እስካሁን ካየኅቸዉ ያንተ ግን ትለያለህ ::
   if you have Lord Jesus the truth will leave with you forever? ስለቃሉ እዉንት ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም::ግን እዉንት “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።”ዮሐ.14:15 ያለ አምላክ አንተ እከተለዋለሁ እያለክ የምትነግረን አምላክ ከ10ቱ ትዛዛት ውስጥ ተሳደቡ የሚል ይገኝበት ይሆን??? ስትሳደብ ስለሰማውህ በዬ ነዉ::
   “I have Lord Jesus, by his grace and faith I am born and created again therefore I have a place in the heaven.”
   አደራ በዚህ ዘመን ብዙ እየሱስ አለና የድንግለ ማርያም ልጅ እየሱስ መሆኑን አረጋግጥ ምክሬ ነዉ::
   ለመሆኑ የግል አዳኝህ ነዉ እንዴ ??? “I have a place in the heaven….”አልክ አየህ አሁን በግልጽ ፕሮቴስታንት መሆንህን አሳዎቅክ:: ምክንያቱም እነሱ ናቸዉ እንደዚሁ በባዶ የሚኮፈሱ:: ድነናል :ገብተናል: ጽድቀናል :ይዘነዋል ያበዛሉ:: ሞያ በልብ ነዉ አለ ያገሬ ሰዉ::ለመሆኑ ሰምተኽዉ ታዉቃለህ ይህን አባባል::መጽሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም እንዳትለኝና እንዳልስቅ::ስልህ ክርስትና ፈጽመህ የበቃህ በትሆንም እንዲህ የምትመፅደቅባት ስላልሆነች::Read bible!” ብለህ አንባቢ መሆንህን የገለጽከዉ አንተ ቅዱስ ጳውሎስ እኔ ገና እንዳልዳንሁ እቆጥራለሁ /ያንን ለማግኘት እንደክማለን/ “ፊሊ 3፡11-14 “አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ። ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።”ሲል አልሰማህ ይሆን::ብዙ ሰርተዉ እነ ቅዱስ ጳውሎስ ገና አልያዘነዉም ሲሉ አንተ ደግሞ በባዶ መንገስተ ሰማያት ገብተህ ትዋኛለህ:: አይ አንተ ትገርማለህ::ከዘያ ሁሉ እስቲ የግል አዳኝህን ሰው ተናግረህ እንድታሳምን ቃሉን ያድልህ ዘንድ ለምነዉ::በተረፈ ምእምን ብዙ መክሮሃልና ተግብረዉ::እዉነት ለመቀበል አትፍራ ::እንደመሸንፍ አትቁጠረዉ::ሰላም ሁንልኝ

   Delete
  10. የተሰቀለው የተመኘህልኝ ቢሆንልኝ አሜን ፣ አሜን ፣ አሜን ብያለሁ ፡፡ ርሱ ለሁላችንም ብርሃኑን ይግለጽልን ብትል ደግሞ የበለጠ ያስተሳስረን ነበር ፡፡ ለእኔ ያበራውን ለአንተም ጭምር ካላበራልህ አሁንም አንድ መሆን ስለማንችል ለማለት ፡፡

   Delete
  11. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !March 6, 2013 at 11:21 AM

   ምእመን
   ከ10ቱ ትዛዛት ውስጥ ተሳደቡ የሚል ይገኝበት ይሆን??? ስትሳደብ ስለሰማውህ በዬ ነዉ:: Do you expect me to say you "good job" for your Antichrist comments posting in this blog. Any one who read my comment probably getting mad on my statement, because ምእመን's comments more or less based biblical. Satan is not coming by his won name, he came politely and prudently before he reveal him self. ምእመን, how can I consider you as a christian? you are worshiping ግርማ, you also said that he is your ደመላሽ ግርማ. Thus, you and me are in two different path. I worshiping Lord Jesus, based on your comment you worshiping your ደመላሽ ግርማ. let me explain like this " your traveling in dark, I am traveling in light.'

   If you want to travel in the light and to get the life after death, ask Lord Jesus to reveal the truth.

   Delete
  12. ለየተሰቀለው
   ወንድሜ አሁንስ ሳስብህ በስሜ የደገሙብህ መሰለኝ ፡፡ አስተያየት የጻፈልህ ሌላ ታዛቢ ወገን ሆኖ ሳለ ፣ መልስ የሰጠኸው ግን አሁንም ለእኔ ነው ፡፡ ፍቅር ይሁን ጥላቻ ይህን የሚያሰራህ ወይም አማርኛ የመረዳት ችግር አልገባኝም ፡፡ ቢያንስ በመጨረሻ ማሳረጊያው ምእመን ብዙ መክሮሃል የሚል የሦስተኛ ወገን አባባል ሠፍሮልህ ነበር ፡፡

   “Do you expect me to say you "good job"” ከአንተም ሆነ ከሌላ ምስጋናንና ሙገሳን በመፈለግ ስሜት ሁኜ አልጽፍም ፡፡ ማቴዎስ በቅዱስ ወንጌሉ ይኸን በተመሳሰለ ጉዳይ ጌታ ያስተማረውን ቃል በምዕራፍ ስድስት ከቁጥር አንድ እስከ ስድስት እንዲሁም ቁጥር በ16 እና 17 የሚለውን ተመልከተው ፡፡ የአንተ የምድራዊ ምስጋና ማብዛት ፣ ምናልባት ለእኔ የሚታደለውን የሰማዩን ሊቀንስብኝ ይችላልና አለማመስገንህን አልቃወመውም ፡፡ መልካም አይደለም የምልህ ስትቃወም የምትቀላቅላቸውን ጸያፍ ቃላቶችን ብቻ ነው ፡፡ ከእኔም አልፈው ቤተሰብ ነክ ሲሆኑ ያሙኛል ፡፡

   አንድ “ልቤ ሁነኝ” የተባለን ሰው ፣ ሰው አይደለህም ለማለት ስትፈልግ በቀላሉ ሰው አይደለህም በለው ወይም የማይሆንበትን ምክንያት አስረዳው እንጅ ፣ አጋሰስ ፣ አህያ ፣ ደደብ የሚሉ ቃላትን ፣ የእንስሳነት ባህርዩን ይገልጻሉ በማለት አትቀላቀል ማለቴ ነው ፡፡ ሌላው እንድትረዳልኝ የምፈልገው ደግሞ በስድብና በዱላ የምቀናበት ዘመን ከዛሬ ሃምሳና ስድሳ ዓመት በፊት ማብቃቱን ነው ፡፡ አሁን እኔን በመስደብ ጐብጨም ከሆነ አታቀናኝምና በከንቱ አትድከም ፡፡

   “ምእመን, How can I consider you as a christian? you are worshiping ግርማ”, አሁንም የክርስቲያንነትን መታወቂያ አዳዩ አንተ አይደለህምና ካለሙያህ አትግባ ፤ በደረጃህ ሁንልን (ለትምህርት ያህል ማቴዎስ 23፡5-7 እንድታነብ ተጋብዘሃል)፡፡ በተረፈ መምህር ግርማን እናምልክ ፣ እንስገድላቸው የሚል ነገር በጽሁፌ አልተጠቀምኩም ፡፡ ይኸን ዓይነት ችግር በሰዎች ላይ ሲያዩት ፈረንጆቹ አሉሲኔሽን ይሉታል ፡፡ በአማርኛ የቁም ቅዠት የምንለውን መሰለኝ ፡፡

   “he is your ደመላሽ ግርማ” አሁንም ይኸን ስያሜ ቀደም ሳስቀምጥ ፣ ካልዘነጋኸው ምክንያቴን ገልጨ ነበር ፡፡ ከቤተ ክርስቲያናችን ኑ ትድናላችሁ ተብለው በሃሰት ስብከት የተነዱትን መንጋዎች ወደ ቤተ ክርስቲያናችን በመመለሳቸው (ቀላል መ)፣ ሥራቸውን ለማወደስ የምጠቀምበት ቃል ነው ፡፡ በኮምፒዩተር ስክሪን ሲሠሩ ከማያቸው ውጭ አላውቃቸውም ፡፡ እኔም ቢሆንልኝ እንደ ርሳቸው የተበተኑትን ባፈልስና ብሰበስብ ደስ ይለኝ ነበር ፡፡ ነገር ግን ይህን ስጦታ እኔ አልታደልኩትም ፡፡

   ለመሆኑ አፍንጫን ሰንገው ፣ ጉሮሮ አንቀው እያስጨነቁ ሲያሻቸውም ተነባብረው እንደ አህያ በሜዳ እያንደባለሉ እንፈውሳለን የሚሉትን ፣ በዘመቻ የመጋደምና የማጋደም ልምምድን የሚያሰለጥኑ ሰባኪዎችንና አስመሳዮችን በኢየሱስ ስምና ኃይል ነው ብለህ ከተቀበልክ ፤ የመምህር ግርማ በኢየሱስና በቅዱሳን ስም መፈወስ ለምን አመመህና ከሰይጣን ሥራ ጋር አቆራኘኸው ? አሁንም እንኳን ሚዛናዊ ፈራጅ ባለመሆንህ ታሳዝነኛለህ ፡፡
   እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ፤ ይቅር ይበለን ፡፡

   Delete
  13. .....ከ10ቱ ትዛዛት ውስጥ ተሳደቡ የሚል ይገኝበት ይሆን??? ስትሳደብ ስለሰማውህ በዬ ነዉ::....የሚለዉ
   የተሰቀለው ባክህ አትቀላቅል እስከ አሁን ምእመንን ከሌላዉ ለመለየት እንኩአን አልቻልክም::አንተ ብዙ ሳታዎራ ጽሁፉ የምእመን ሳይሆን የኔ ነዉ::አስተያየትህን ለኔ አድርገዉ::
   "If you want to travel in the light and to get the life after death, ask Lord Jesus to reveal the truth.'
   "አይ አንተ ለዚያ ነዉ የምትሳደበዉ....."የብርሃንና ጭለማንም ልዩነት አታዉቅም ማለት ነዉ::ብርሃን:እዉንት ማለት ክርስቶስ ነዉ ክርስቶስ ደግሞ ትሁት ነዉ:የሰላም አምላክ ነዉ:መልካም እረኛ ነዉ:መንጋዉን ለመበተን እንዳንተና እንደ አባሰላማዎች ጥረት አያደርግም:: ሁሌም ፍቅር ነዉ::በፍቅር ነዉ የሚገዛ::

   Delete
  14. የተሰቀለው እኔ እኮ በጣም ትገርመኛለህ አማርኛ አንብበህ በእንግሊዝኛ ትጽፋለህ::እንዲያዉ ቃሉ አልመጣ ሲልህ በእንግሊዝኛ ልትሸፍነዉ እያሰብክ ይሆን???ነዉ ያዋቂነትህ መገለጭ ይሆን::ነዉ ያዉ የባእድ ሃገር የአማርኛ ቃላቶችህን ወሰደብህ::ሃሰት የሚናገር የክርስቶስ ይሆን ይሆን? ይህን እስቲ አንተ ምልሰዉ? መቼም ምእመን ደመላሽ ግርማን አመልካቸዋለሁ ሲል አልሰማንም ለማለት ነዉ::እንዲያዉ ከየት አመጣኽዉ::ያልተጽፈ እንደምታነብ እንኩዋን ብዙ ገዜ አይቼሃለሁ::በተረፈ እባክህ ባዎራህ ቁጥር በጣም እይሳተክ ሰለሆነ ዝም ብትልስ::ሰላም ሁንልኝ

   Delete
 5. እውነት ነው
  ደብተራዎች/ጠንቋዮች/ ከቤተ ክርስቲያን ካልወጡ ሰላም ሊኖር አይችልም፡፡
  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተሃድሶ ያስፈልጋታል፡፡

  ReplyDelete
 6. kentu wunjela.mesrat siyakit qinat

  ReplyDelete
 7. የመስቀሉን ነገር አጉልተን በመግለጥ ጠላታችንን ከእግራችን በታች እንጣለው።

  ReplyDelete
 8. menafikan hoy tenkuay degimo kemech wodih new begeta sime seyitanin yemiyaswota?

  ReplyDelete
 9. Praise God for His mercy for those Debteras who are willing to confess under His feet. May God Open the eyes of all our people so that our Orthodox Church can be renewed and comeback to its ORGINAL DOCTRINE,which was began by the first leader, Aba Selama many years ago.

  I really wish to see my mother church to be the right Bride of Jesus Christ. This is my daily prayer with faith in Him. Many thank.

  Your sister,

  In the love of God,

  Selam

  ReplyDelete
 10. ምእመን እንደምን አለህ ዛሬም እንደተለመደዉ በከፊል ገልብጬ መጥቻለሁ::የባለፈዉ ምክርህን እየተግበርኩት ነዉ::ክርስትና እንዲህ ነዉ አንዱ ላንዱ የሚያስብበት::ሰላሙ ይብዛለህ:: ከቻልክ በኢሜል አድራሻዬ “orthodox_1212@yahoo.com”ብለህ ብትጽፍልኝ ደስታዉን አልችለዉም::
  ጽሁፉ ከጉዳዩ ጋር አይሔድም ካላችሁ የሚሔደዉን እየመረጣችሁ አንብቡት እኔ ሳቀናብረዉ ሌሎች ሙሉ ሃሳቡን እንዲያነቡት ብዬ ነው::
  በሰውኛ ሲታሰብ በጣም ከባዱ ተአምር የሞተ ሰው ማስነሳት ነው። ቅዱስ መጽሐፍ ላይ ያሉ አባቶቻችን የሞቱ ሰዎችን አስነስተዋል።በእነሱ ላይ ይሰራ የነበረ መንፈስ ቅዱስ ዛሬም እንደሚሰራ ካመንን ዛሬም አባቶቻችን ከሙታን ቢያስነሱ የታመሙ ቢፈውሱ ከፋቱ ምን ይሆን::መቼም እናዉቃለን ሰይጣን ሰዉ ሲታሰር እንጂ ሰዉ ሲፈታ አይዎድም::እናንተም ከዚያዉ ከአባታችሁ ናችሁና መቼ በሰዉ መፈዎስ ትደሰታላችሁ::ታዲያ የደም መላሻችን(ምእመን እንዳለዉ) አባ ግርማያን ያሁሉ ጉድ በክርስቶስ ስም ለዚያዉም የሰይጣንን ሴራ ከምጽሃፍ ቅዱስ እያጣቀሱ ቢፈዉሱ ምን ይሆን ክፋቱ:: ለምንስ ይገርመናል? እስቲ ከመጽሃፍ ቅዱስ አባቶች የስሩትን ልዩ ልዩ ተአምር እንመልከት :-

  በብሉይ ኪዳን

  ==>ኢያሱ ጸሐይን አቆመ።(ኢያ.10፣13) ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ።
  ==>ሶምሶን የመኳንንቱን ቤት አፍርሷል።(መሳ.16፣30) ምሰሶቹን በሙሉ ኅይሉ ገፋ፥ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመኳንንቱም በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ።
  ==>ኤልያስ ሰማይን ለጉሟል ደግሞም መልሶ ዝናብ እንዲዘንብ አድርጓል።(1ኛ ነገ18፣41-45) ከጥቂትም ጊዜ በኋላ ሰማዩ ከደመናውና ከነፋሱ የተነሣ ጨለመ፥ ብዙም ዝናብ ሆነ፤
  ==>አልያስም ኤልሳዕም የዮርዳኖስን ባሕር ከፍለዋል(2ኛ ነገ.2፡8 2፣19)
  ==>አልያስ በሰራፕታ የባልቴቷን ቤት በበረከት ሞልቷል።(1ኛ 17፣14) በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋ አይጨረስም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አይጎድልም።
  ==>አልያስ የሞተ ልጇን አስነስቷል።(1ኛነገ 17፣22) እግዚአብሔርም የኤልያስን ቃል ሰማ፤ የብላቴናው ነፍስ ወደ እርሱ ተመለሰች፥ እርሱም ዳነ።
  ==>ኤልሳዕም ለሱነማዊት ሴት በረከት ሰጥቷል የሞተ ልጇንም አስነስቷል(2ኛ ነገ 4 1-35 ) መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ።ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ፤ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕፃኑ ላይ ተጋደመ፤ ሕፃኑም ዓይኖቹን ከፈተ።
  ==>ኤልሳዕ ንዕማንን ከለምጹ አንጽቶታል።2ኛ ነገ 4፣42-44 በባህር የሰጠመውን መጥረቢያ በውሃ ላይ እንዲሳፈፍ አድርጓል። 2ኛ ነገ 6፣6
  ==>ኤልሳዕ የደቀመዝሙሩን ዓይነልቡና ተከፍቶ መላዕክትን ለማየት እንዲበቃ አድርጓል።(2ኛ ነገ 6፡17) የሶርያውን ሰራዊት አይናቸው እንዲታወር አድርጓል።
  ==>ኤልሳዕ በተቀበረበት ቦታ የወደቀ የሞተ ሰው ከሞት ተነስቷል።ከሞተ በኋላ እንኳ ሙት አስነስቷል።(1ኛ ነገ 13፣21) ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፥ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት፤ የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ።
  ==>ሰለስቱ ደቂቅ ከሚነድ እሳት ውስጥ ምንም ሳይሆኑ ወጥተዋል።(ዳን3፣23)
  ==>ዳንኤል ከአናብስት ጉድጓድ በሰላም ወጥቷል።(ዳን 6፤22) መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፥ እነርሱም አልጐዱኝም አለው።
  ==>ዮናስ በአሳአንበሪ ሆድ 3 መዓልት 3 ልሊት ቆይቶ ምንም ሳይሆን ወጥቷል።(ዮና 2፣1) ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ።

  በሐዲስ ኪዳን

  ==>ጴጥሮስ ጣቢታን ከሞት አስነስቷል።(ሐዋ.9፣40) ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።
  ==>ጴጥሮስ ሃናንያና ሰጲራ እንዲሞቱ አድርጓል።(ሐዋ.5፣5-10) ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም…. ያን ጊዜም በእግሩ አጠገብ ወደቀች ሞተችም
  ==>ጴጥሮስና ዮሐንስ ሽባውን ተርትረዋል/ፈውሰዋል/።(ሐዋ 3፣2-11)
  ==>ጳውሎስም አውጤኪስን ከሞት አስነስቷል።(ሐዋ20፣9) ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፥ አቅፎም። ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ አላቸው።
  ==>ጳውሎስ እባቢቱ እንዳልጎዳቸው ምንም ሳይሆን እዳራገፋት ይናገራል።(ሐዋ.28፣5) እርሱ ግን እባቢቱን ወደ እሳት አራገፋት አንዳችም አልጐዳችውም፤
  ==>የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላው ይፈውሳቸው ዘንድ ድውያንን ያሰልፉ ነበር።(ሐዋ 5፣ 15) ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።
  ==>ፊሊጶስ ከጃንደረባው ዓይን በመንፈስ ተነጥቆ እንደተሰወረ መጽሐፍ ይነግረናል።(ሐዋ.8፣39)

  እንግዲህ ከላይ በጥቂቱ የተመለከትነው በብሉይም በሐዲስ ኪዳንም የነበሩ አባቶቻችን ታላላቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራት ሲያደርጉ ነው። ታዲያ በእነዚያ ዘመናት ሁሉ ታላለቅ ድንቅ ተአምራትን እንዲያደርጉ ሲያደርጋቸው የነበረ መንፈስ ቅዱስ ዛሬ እየሰራ መሆኑን የምናምን ከሆነ ለምን የገብረመንፈስ ቅዱስ ፣የአቡነተክለሃይማኖት ፣የእነ ቂርቆስ ኢየሉጣን ድንቅ ተአምራት መቀበል አቃተን?ሰለስቱ ደቂቅ ከእሳት ምንም ሳይሆኑ መውጣታቸውን ካመኑ ለምን የቂርቆስ እና ኢየሉጣ ከፈላ ውሃ ምንም ሳይሆኑ መውጣት ይጎረብጣቸዋል? ለኢያሱ ግዑዝ ፍጥረት ጸሐይ ታዝዛ ከቆመች ለአቡነገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብርቱ አናብስቱ መታዘዛቸው ምን ያስገርማል? የኤልሳዕ አጽም ሙት ካስነሳ ፤በሕይወት የነበሩ አባቶቻችን ሙት ማስነሳታቸው ምን ያስገርማል?1ኛ ቆሮ.12:4-10 “የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው………ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ….”ይሰጠዋል:: ስለሚል የደመላሻችን አባ ግርማም ጸጋም ስጦታ ይህ መሆኑ ነዉ::ከዘህ አካያም ሳየዉ የደም መላሻችን አባ ግርማ በጣም ቀላሉ ተአምር በእግዚአብሔር እርዳታ ሰሩ እላለሁ::ቢቀናችሁ እና ጽጋዉን ቢያድላችሁ እናንተም ሰይጣንን ታስራላችሁና እባካችሁ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንጋጭ እላለሁኝ::ሃይሌ ገ/ስላሴ እንኩአን ይቻላል ሲል አልሰማችሁም::እየቀልድሁ አይደለም ክርስትና ደግሞ ከዚህ በላይ እምናምነዉ ስለሆነ ነዉ::እናንተ ደግሞ መጽሃፍ ታዉቃላችሁ አማኝ ተብላችሁ የምትጠሩ ናችሁና እባካችሁ የመንፈስ ቅዱስን ስራ ከዲያቢሎስ ለዩ:: ለመለየት ድንግል ትርዳችሁ ነዉ የምለዉ::መቼም ብታቃልላትም እርሱ አተዋችሁምና::

  ጌታችንም እኮ ያለው(ዮሐ.14፤ 12) እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።
  ታዲያአባ ግርማ ካመኑ ምን ማድረግ ይሳናቸዋል? እኛም እኮ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ታሪክ እንድንተርክ ሳይሆን እንድንኖረው ነው የሚጠበቅብን። ቅዱስ ጴጥሮስ ሙት ካስነሳ ፣እኛም ሕይወታችንን ብናስተካክል ፍጹም ክርስቲያኖች ብንሆን በቅዱስ ጴጥሮስ ላይ የሰራ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ ይሰራልና ሙታን ማስነሳት እንችላለን።ስለዚህ አባቶቻችን ምንም ዓይነት ተአምራት ቢፈጽሙ በእነርሱ አድሮ ስራ የሚሰራ መንፈስ ቅዱስ ነውና ሊሆን አይችልም የሚስብል ነገር አይኖርም።

  ሠላመ እግዚአብሔር አይለየን::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጽናቴ ብየሃለሁ ፤ ሰላምህ ይብዛ ፡፡
   ዮሐንስ በኤልሳቤጥ ማህጸን እንደጨፈረ ፣ ጽሁፍህን ሳነበው ልቤ በደረቴ ውስጥ ሲጨፍር ተሰማኝ ፡፡
   አስረጅ ስለሆነው ትምህርት በበኩሌ አመሰግናለሁ ፡፡

   Delete
  2. kale hiwot yasemalin .Bezu temarkudg.

   Delete
  3. እግዚአብሔር ይስጥልን: ጸጋውን ያብዛልን::

   Delete
 11. ....."የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተ ሰቦች፦
  ቤተ ክርስቲያናችን ተሃድሶ ያስፈልጋታል። ብዙ ቆሻሻ የሆኑ የአጋንንት ሥራዎች፤ የሥጋና የደም ትምህርቶች፤ ልዩ ልዩ ባዕድ አምልኮዎች እንደ ልማድ ሆነው ይዘወታራሉ። እነዚህ ሁሉ አጸያፊ ነገሮች ንጹሕ በሆነው በእግዚአብሔር ቃል እየተመረመሩ መወገድ አለባቸው። ይህ ባይሆን ግን ጥፋታችን ሩቅ አይደለም። የመስቀሉን ነገር አጉልተን በመግለጥ ጠላታችንን ከእግራችን በታች እንጣለው።" rebakeh???? mejmreya ante ena gbrabroch tadesu wodaja.ke-orthodox gudf atwotam!!!

  ReplyDelete
 12. ሰላም የተሰቀለው
  ለቀናት ተጠፋፍተን ስለከረምን በጣም ናፍቀኸኝ ነበር ፡፡ መቼም ያንተ ክርስትና ረጋ ብዬ ሳስባት በእጅጉ ታስጨንቀኛለች ፡፡ ምንም ህይወት የሌላት የስም ብቻ ስለምትሆንብኝም አዝናለሁ ፡፡ እንደ ወገን ወዲህ ደግሞ እንደ አንድ ወንድም የምመክርህ ፣ ለመጻፍ ስትነሳ መጀመሪያ እንድትጸልይ ነው ፤ ሰይጣን ወደሚፈልገው መሥመር እንዳይወስድህ ይረዳህ ይሆናል ፡፡ ለማስተማር የምትፈልገውን ደግሞ ለይተህ በትክክል አስቀምጠው ፡፡ የዲያብሎስን ቋንቋና ወግ እየተጠቀምህ ኢየሱስን እከተላለሁ ብትለኝ አንተም ልታሳስተን የምትታገል ልዝብ --- ነህ ማለት ነው እላለሁ ፡፡ ብበድል እንኳን ለማስተማር ስትል ቃላት ምረጥ ለማለት ስለፈለግሁ ነው፡፡

  ልብ በል ፤ ከጻፍኩት ውስጥ የወንጌሉ ቃል እንዳለ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተቀዳ ነው ፡፡ ሌላው ጸሐፊው ቢመልሱልኝ በማለት የቀረበው ደግሞ ጥያቄ ነው ፡፡ የተጠየቀው ጥያቄ አግባብ አይደለም የምትልበት መግለጫ ካለህ ፣ ምክንያትህን አስረዳኝ እንጅ “your ደመላሽ ግርማ replaced the old or small devil spirit you inherited from your family by the big one. You are lost!” በማለት አጥንት የሚሰብርና ጋብቻ የሚከለክል የዋልጌ ነገር አታምጣ ፡፡ ስታስበው በዚህ ጽሁፍህ እኔን የሚያንጽ ምን አንዳች ነገር አስቀምጠሃል ? በዛ ላይ ደግሞ የሚያስተናግዱንን ሰዎች መድረክም መልክ አታሳጣባቸው ፡፡ በሥርዓት ልዩነታችንን ፣ እምነታችንን ፣ አቋማችንን ብናስተላልፍ ሰዎች ከአንተም ከእኔም ሆነ ከሌላው ወገን ቃል ብዙ የሚመለከቱት አለ ብዬ አምናለሁ ፡፡ ስለ ጌታ ብለህ አደብ ግዛ ፡፡ የቋንቋ ጀማሪ ይመስል ያለመጥፎ ቃል አይቋጭልህም ፡፡ ልጅ ሆነን እያጫወቱ ቃላት ሲያስተምሩን ንፍጣም ፣ ድዳም .. ይሉን ነበር ፡፡ ጽሁፍህን ሳነበው ያ ዘመን ነው ትዝ የሚለኝ ፡፡

  በተረፈ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲያ እንደማታስተምርና እንደማታሰለጥን እያወቁ ፣ ርሷኑ ተወቃሽና በደለኛ አድርገው እናድሳታለን ይሉናል ፡፡ ጸሐፊው ራሳቸው እንዲያስተምሩን በማለት በጥያቄ አቀረብኩት እንጅ ፣ ቤተ ክርስቲያን ካህናቷን ጠንቁሉ ፣ ስራሥር ማሱ ፣ ቅጠል በጥሱ ፣ መተት ድገሙ ወይም ጻፉ እያለች እንደማታስተምር ልቦናቸው ያውቃል ፡፡ እውነት ሆኖ ቢሰማቸው እንኳን የግለሰቦችን ድክመትና ስህተት ፣ የምታራምደው የዕለት ግብሯ አድርገው መለጠፋቸው ፣ የተላኩ ቅጥረኛ ስለሆኑ ብቻ ነው ማለቱ ይቀለኝ ነበር ፡፡ ነካክተህ ሳልፈልግ አስባልከኝ ፡፡

  ReplyDelete
 13. በክርስቶስ ያመለጥከው ደብተራ- የመምህር ግርማ ትምህርት ላይ አንተና ደብተራ ጓደኛህ ብቅ በሉና ጠንቋይ ማን እንደሆነ ትረዳላችሁ፡
  በክርስቶስ አመለጥኩ ብለህ የለ አትፍራ ።

  ReplyDelete
 14. haha...haha..."enies awksh alehu lemayawksh tategn"alu.
  Haha...haha.."Yeabayen wede emaye lekek"alu
  Gebresedo,ጥንቆላ yenante gbr huno eyale mnew?mnew? Smlemades new endie haha...haha...New yegbr guadegn lemggnt egna bcha adelenem lelawm tenquay nache new lemalet? Taktikawi yewgia slt kerachu endie? ጥንቆላ ሰይጣን ljoch huna chu sal mnew aferachu endie bemgbarachu? New antawkm blachihu?.
  Haha...haha.."gdshn besemash gebiya balwetash"alu
  Menew blogachihun"ABA SELAMA"Slachihu kdusan yehunachhu meselachu?haha...haha...gud belegoner ale yagerasew!
  Ere smu ema yenatebitie ABA JIB kemayawkut ager hido"lemekmch koda antflegn "ale alu
  Ok! Lechat,lemechferia,belabet lemsrat, BIRR tefa endie Ke aleqochachihu" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን"protestant"tehadeso"lemdreg yewese dachihut"WL OR SMMNET" keshef endie ,ketqola yemigegnew birr anese endie? Protestant sihunu kemigegnew gentzeb? Gar sinetsatser
  New BE ABAYT BALAT BAHTAWI MESLO LBSN AWLKO alem lttefanew eyalu keyewhu hizbekrstan Genzeb mesebsebu slekernew?haha...haha...
  Ykrta TYAQI ALEGN "BELOGACHUN ABASELAM SAYHON MEBAL YALEBET"ABA SEDOM"NEW kenant gibrgar yemihad
  Yihnew ena haha...haha...Saymadru mastemar kyet ameta chihut haha...haha.....ጥንቆላን/ ሰይጣንን ክፋት/ erasachu stseru nurachu hizbn statallu nurachhu mnew ahun
  "TNQOLA GOJNEW"ባለፈው ጽሑፌ ጥንቆላ ምን እንደሆነ
  ጥቂት ለማሳየት ሞክሬያለሁ፤
  በሰፊው ግን አልገለጥሁትም።
  የሰይጣንን ክፋት በሰፊው ከመግለጥ የእግዚአብሔርን
  ደግነት አጉልቶ መግለጥ ይሻላል የሚል እምነት ስላለኝ ነው። ነገር"mnmalet new ?yegzihabhirn degnet kmalet ylk yegnzebn dfgne btn ykelal enantzmtawkuet genzebn new ena

  ReplyDelete
 15. "መናፍስት ጠሪዎችና ደጋሚዎች የሚያጠምቁበትን ዘዴ ከአንድ ደብተራ ጓደኛዬ ያገኘሁትን ምስጢር በጥቂቱ መግለጥ እሞክራለሁ።" ያን ሁሉ ዝባዝንኬ ቁጭ ተብሎ በምናብ የተተበተበ ሙሆኑን ያሳያል

  ReplyDelete
 16. ክፍል አንድ
  በተቻለ መጠን የሰዉ አስተያየት ባታስቀሩ እያለኩ ባለፈዉ ስላልዎጣ በድጋሚ ታዎጥዋት ዘንድ እማፅናለሁ::አምሰግናለሁ::
  ምእመን እንደምን አለህ ዛሬም እንደተለመደዉ በከፊል ገልብጬ መጥቻለሁ::የባለፈዉ ምክርህን እየተግበርኩት ነዉ::ክርስትና እንዲህ ነዉ አንዱ ላንዱ የሚያስብበት እና የምትደጋገፍበት::ሰላሙ ይብዛለህ:: ከቻልክ በኢሜል አድራሻዬ “orthodox_1212@yahoo.com”ብለህ ብትጽፍልኝ ደስታዉን አልችለዉም::
  ጽሁፉ ከጉዳዩ ጋር አይሔድም ካላችሁ የሚሔደዉን እየመረጣችሁ አንብቡት እኔ ሳቀናብረዉ ሌሎች ሙሉ ሃሳቡን እንዲያነቡት ብዬ ነው::
  በሰውኛ ሲታሰብ በጣም ከባዱ ተአምር የሞተ ሰው ማስነሳት ነው። ቅዱስ መጽሐፍ ላይ ያሉ አባቶቻችን የሞቱ ሰዎችን አስነስተዋል።በእነሱ ላይ ይሰራ የነበረ መንፈስ ቅዱስ ዛሬም እንደሚሰራ ካመንን ዛሬም አባቶቻችን ከሙታን ቢያስነሱ የታመሙ ቢፈውሱ ከፋቱ ምን ይሆን::መቼም እናዉቃለን ሰይጣን ሰዉ ሲታሰር እንጂ ሰዉ ሲፈታ አይዎድም::እናንተም ከዚያዉ ከአባታችሁ ናችሁና መቼ በሰዉ መፈዎስ ትደሰታላችሁ::ታዲያ የደም መላሻችን(ምእመን እንዳለዉ) አባ ግርማያን ያሁሉ ጉድ በክርስቶስ ስም ለዚያዉም የሰይጣንን ሴራ ከምጽሃፍ ቅዱስ እያጣቀሱ ቢፈዉሱ ምን ይሆን ክፋቱ:: ለምንስ ይገርመናል? እስቲ ከመጽሃፍ ቅዱስ አባቶች የስሩትን ልዩ ልዩ ተአምር እንመልከት :-

  በብሉይ ኪዳን

  ==>ኢያሱ ጸሐይን አቆመ።(ኢያ.10፣13) ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ።
  ==>ሶምሶን የመኳንንቱን ቤት አፍርሷል።(መሳ.16፣30) ምሰሶቹን በሙሉ ኅይሉ ገፋ፥ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመኳንንቱም በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ።
  ==>ኤልያስ ሰማይን ለጉሟል ደግሞም መልሶ ዝናብ እንዲዘንብ አድርጓል።(1ኛ ነገ18፣41-45) ከጥቂትም ጊዜ በኋላ ሰማዩ ከደመናውና ከነፋሱ የተነሣ ጨለመ፥ ብዙም ዝናብ ሆነ፤
  ==>አልያስም ኤልሳዕም የዮርዳኖስን ባሕር ከፍለዋል(2ኛ ነገ.2፡8 2፣19)
  ==>አልያስ በሰራፕታ የባልቴቷን ቤት በበረከት ሞልቷል።(1ኛ 17፣14) በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋ አይጨረስም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አይጎድልም።
  ==>አልያስ የሞተ ልጇን አስነስቷል።(1ኛነገ 17፣22) እግዚአብሔርም የኤልያስን ቃል ሰማ፤ የብላቴናው ነፍስ ወደ እርሱ ተመለሰች፥ እርሱም ዳነ።
  ==>ኤልሳዕም ለሱነማዊት ሴት በረከት ሰጥቷል የሞተ ልጇንም አስነስቷል(2ኛ ነገ 4 1-35 ) መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ።ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ፤ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕፃኑ ላይ ተጋደመ፤ ሕፃኑም ዓይኖቹን ከፈተ።
  ==>ኤልሳዕ ንዕማንን ከለምጹ አንጽቶታል።2ኛ ነገ 4፣42-44 በባህር የሰጠመውን መጥረቢያ በውሃ ላይ እንዲሳፈፍ አድርጓል። 2ኛ ነገ 6፣6
  ==>ኤልሳዕ የደቀመዝሙሩን ዓይነልቡና ተከፍቶ መላዕክትን ለማየት እንዲበቃ አድርጓል።(2ኛ ነገ 6፡17) የሶርያውን ሰራዊት አይናቸው እንዲታወር አድርጓል።
  ==>ኤልሳዕ በተቀበረበት ቦታ የወደቀ የሞተ ሰው ከሞት ተነስቷል።ከሞተ በኋላ እንኳ ሙት አስነስቷል።(1ኛ ነገ 13፣21) ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፥ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት፤ የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ።
  ==>ሰለስቱ ደቂቅ ከሚነድ እሳት ውስጥ ምንም ሳይሆኑ ወጥተዋል።(ዳን3፣23)
  ==>ዳንኤል ከአናብስት ጉድጓድ በሰላም ወጥቷል።(ዳን 6፤22) መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፥ እነርሱም አልጐዱኝም አለው።
  ==>ዮናስ በአሳአንበሪ ሆድ 3 መዓልት 3 ልሊት ቆይቶ ምንም ሳይሆን ወጥቷል።(ዮና 2፣1) ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ።

  ይቀጥላላ…

  ReplyDelete
 17. ክፍል ሁለት

  በሐዲስ ኪዳን

  ==>ጴጥሮስ ጣቢታን ከሞት አስነስቷል።(ሐዋ.9፣40) ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።
  ==>ጴጥሮስ ሃናንያና ሰጲራ እንዲሞቱ አድርጓል።(ሐዋ.5፣5-10) ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም…. ያን ጊዜም በእግሩ አጠገብ ወደቀች ሞተችም
  ==>ጴጥሮስና ዮሐንስ ሽባውን ተርትረዋል/ፈውሰዋል/።(ሐዋ 3፣2-11)
  ==>ጳውሎስም አውጤኪስን ከሞት አስነስቷል።(ሐዋ20፣9) ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፥ አቅፎም። ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ አላቸው።
  ==>ጳውሎስ እባቢቱ እንዳልጎዳቸው ምንም ሳይሆን እዳራገፋት ይናገራል።(ሐዋ.28፣5) እርሱ ግን እባቢቱን ወደ እሳት አራገፋት አንዳችም አልጐዳችውም፤
  ==>የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላው ይፈውሳቸው ዘንድ ድውያንን ያሰልፉ ነበር።(ሐዋ 5፣ 15) ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።
  ==>ፊሊጶስ ከጃንደረባው ዓይን በመንፈስ ተነጥቆ እንደተሰወረ መጽሐፍ ይነግረናል።(ሐዋ.8፣39)

  እንግዲህ ከላይ በጥቂቱ የተመለከትነው በብሉይም በሐዲስ ኪዳንም የነበሩ አባቶቻችን ታላላቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራት ሲያደርጉ ነው። ታዲያ በእነዚያ ዘመናት ሁሉ ታላለቅ ድንቅ ተአምራትን እንዲያደርጉ ሲያደርጋቸው የነበረ መንፈስ ቅዱስ ዛሬ እየሰራ መሆኑን የምናምን ከሆነ ለምን የገብረመንፈስ ቅዱስ ፣የአቡነተክለሃይማኖት ፣የእነ ቂርቆስ ኢየሉጣን ድንቅ ተአምራት መቀበል አቃተን?ሰለስቱ ደቂቅ ከእሳት ምንም ሳይሆኑ መውጣታቸውን ካመኑ ለምን የቂርቆስ እና ኢየሉጣ ከፈላ ውሃ ምንም ሳይሆኑ መውጣት ይጎረብጣቸዋል? ለኢያሱ ግዑዝ ፍጥረት ጸሐይ ታዝዛ ከቆመች ለአቡነገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብርቱ አናብስቱ መታዘዛቸው ምን ያስገርማል? የኤልሳዕ አጽም ሙት ካስነሳ ፤በሕይወት የነበሩ አባቶቻችን ሙት ማስነሳታቸው ምን ያስገርማል?1ኛ ቆሮ.12:4-10 “የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው………ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ….”ይሰጠዋል:: ስለሚል የደመላሻችን አባ ግርማም ጸጋም ስጦታ ይህ መሆኑ ነዉ::ከዘህ አካያም ሳየዉ የደም መላሻችን አባ ግርማ በጣም ቀላሉ ተአምር በእግዚአብሔር እርዳታ ሰሩ እላለሁ::ቢቀናችሁ እና ጽጋዉን ቢያድላችሁ እናንተም ሰይጣንን ታስራላችሁና እባካችሁ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንጋጭ እላለሁኝ::ሃይሌ ገ/ስላሴ እንኩአን ይቻላል ሲል አልሰማችሁም::እየቀልድሁ አይደለም ክርስትና ደግሞ ከዚህ በላይ እምናምነዉ ስለሆነ ነዉ::እናንተ ደግሞ መጽሃፍ ታዉቃላችሁ አማኝ ተብላችሁ የምትጠሩ ናችሁና እባካችሁ የመንፈስ ቅዱስን ስራ ከዲያቢሎስ ለዩ:: ለመለየት ድንግል ትርዳችሁ ነዉ የምለዉ::መቼም ብታቃልላትም እርሱ አተዋችሁምና::

  ጌታችንም እኮ ያለው(ዮሐ.14፤ 12) እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።
  ታዲያአባ ግርማ ካመኑ ምን ማድረግ ይሳናቸዋል? እኛም እኮ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ታሪክ እንድንተርክ ሳይሆን እንድንኖረው ነው የሚጠበቅብን። ቅዱስ ጴጥሮስ ሙት ካስነሳ ፣እኛም ሕይወታችንን ብናስተካክል ፍጹም ክርስቲያኖች ብንሆን በቅዱስ ጴጥሮስ ላይ የሰራ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ ይሰራልና ሙታን ማስነሳት እንችላለን።ስለዚህ አባቶቻችን ምንም ዓይነት ተአምራት ቢፈጽሙ በእነርሱ አድሮ ስራ የሚሰራ መንፈስ ቅዱስ ነውና ሊሆን አይችልም የሚስብል ነገር አይኖርም።

  ሠላመ እግዚአብሔር አይለየን::

  ReplyDelete
 18. Who u r speak in chelema? rasachun gletu ewnet yelelebet neger hulu be hubue lemin mefetsem tfelgalachu. Tewegzachuhal, tehadsowoch atasfelgunm betekrstianachin be hulet egrwa komalech melake menkorat Girma Wendmu tsegachew yabzaln

  ReplyDelete
 19. እውነት ነው
  ደብተራዎች/ጠንቋዮች/ ከቤተ ክርስቲያን ካልወጡ ሰላም ሊኖር አይችልም፡፡
  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተሃድሶ ያስፈልጋታል፡፡

  ReplyDelete
 20. "The whole evangelical apologetics movement is dangerous in my opinion. Trying to prove the veracity of the Christian Faith by human reason alone is an exercise in futility. It's good to defend the Faith and give reasons for the hope that we have, but attempts to reduce Christianity to logical syllogisms and systematic proofs ultimately create idolatous caricatures of the Divine rather than proving the existence of the Divine Creator. If you search the Scriptures merely with your own mind then you will find confusion and contradiction, and you will be led to heretical ideas. But if you search the Scriptures guided by the mind of the fathers, then you will find Christ and you will be led to eternal life." Selam, +GMK+

  ReplyDelete
 21. Lehulachnm egziabher Mastewal na tibebun ystea,Besewoch lay bemefred endayferedbnm rasachnn enmermr.

  ReplyDelete
 22. እግረ መንገዳችንን የወንጌል ቃል እንድንማርበት እጠቅሳለሁ፡፡

  “ከዚህም በኋላ ጋኔን ያደረበትን ዕውር ዲዳም ወደ እርሱ አመጡ፤ ዕውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪናገር ድረስ ፈወሰው። ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና። እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ። ፈሪሳውያን ግን ሰምተው። ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ። ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው። እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም። ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፥ እርስ በርሱ ተለያየ፥ እንግዲህ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች? እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች። ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል። ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም። በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።” ማቴ 12 : 22-32

  ጥያቄዎቼ ይከተላሉ ፡-
  1- እንዲህ ጌታችን ካስተማረን ቃል ውጭ የሆነ ፣ ሰይጣን ሰይጣንን ያስወጣል ፣ አጋንንት አጋንንትን ያስለቅቃል ፣ ዲያብሎስም የመፈወስ ችሎታ አለው የሚለው ትምህርት ከየት ወገን የመጣ ነው ?

  2- የቤተ ክርስቲያን ክህነትን በእርግጥ ከተቀበሉ ፣ ምስጢረ ንስሐ ማለት ስለሌሎች በደል ወይንስ ስለራስ ድክመት መናዘዝና ይቅርታን መጠየቅ የሚያስተምረን ? ምናልባት በደብተራነትዎ የአባይ ጠንቋይን ሙያ ተገልግለውበት ከሆነ ፣ ስምዎን እንደ መሪጌታ ሙሴ በግልጽ አስቀምጠው ፣ የሠሩበትን ሥፍራና ያገለገሉትን ህዝብ ጠቅሰው ይቅር በሉኝ ማለት እንጅ እነ እገሌ መኪና ገዙ ፣ ፎቅ ገነቡ ማለትዎ ንስሐ ሆኖ ስላልተሰማኝ ነው የምስጢረ ንስሐ ጥያቄዬ ወይንስ በዚህ ዘመን የቤተ ክርስቲያን የንስሐ ትምህርቱም ተቀይሮ ይሆን ?

  3- ከአለፈ መግለጫዎ ለመጥቀስና አብረን ለማየት ፡- “ብዙውን ጊዜ አማኞች ለመምሰል የአላህን ወይም የእግዚአብሔርን ስም ያነሳሉ (ጠንቋዮቹን ማለትዎ መሰሎኛል)። እንዲህ የሚያደርጉት ብዙዎች ደንበኞቻቸው ከእስልምና ወይም ከክርስትና የመጡ ስለሆኑ ይመስላል። ኢየሱስ የሚለውን ስም ግን ተሳስተውም እንኳ አይጠሩትም።” የሚል መልካም ቃል በመግቢያዎ አስነብበውናል ፡፡ እኒህ የሚከሷቸው ግለሰብ (ደመላሽ ግርማ) በኢንተርኔት የተለቀቀ ትምህርታቸውና ተአምራቸው በኢየሱስ ስምና በቅዱሳን ጭምርም እንደሆነ አይተናልና ቃልዎን ለማስማማት ምን ልበለው ? ወይስ ጽሁፍዎትን ያርሙታል ?

  ReplyDelete
 23. አባ ሰላማ
  የስምህ ማማር እንደወንድሞቻችን እስላሞች ስም ብቻ መሆንህ ያሳዝናል
  ዛሬ እስላሞች የሚያደርጉት ይህን ነው በህዝባቸው ላይ ውዝምብር መፍጠር
  እውነቱን ሃሰት አድርጎ ማቅረብ
  ታዲያም አንተ ያደረከው ከዚህ የከፋ የዲያብሎስ ነህ፣
  ውድ ክርስቲያን ወንድሞቸ ዛሬ ለቤቱ ቅርበት አለን የሚሉት የ አባ ሰላማ አይነቶች ቤታችንን እንዴት እንደበጠበጧት ልንገነዘብ ይገባል ፣ በመጨረሻው ዘመን እርኩሱ መንፈስ በቤተመቅደሱ ስታዩት ስዐቱ እንደደረሰ እወቁ ፣ ይላል ዛሬ በቤተክርስቲያናችን የምናየው
  1 ለህዝብ ደህንንተ ግድ የሌላቸው
  2 የገንዘብ ጥመኞች
  3 ኑሯቸው ትምህርታቸው አስተዳደራቸው ለራቸው
  4 ምንም አይነት ፍርሃ እግዚአብሄር የሌላቸው
  5 እንደፈሪሳዊያን ፕሮቶኮል ብቻ
  ታዲያ እነሱን የሚነካ ካለ ውግዝ ከመአርዮስ ይባላል ባጠቃላዩ የውግዘት ዘመን ብቻ ሁነናል
  ታዲያ መነሻየ በአባ ግርማ ወንድሙ የተጻፈውን አይቸ ነው
  በውነቱ እኒህን አባት ከሰይጣን ነው ማለት ያሳዝናል
  በመቁጠሪያ በቀለበት ላይ ይሰራል ያልከው ይገርማል ከሁሉም ቅንብርህ ምርጡን አጋንንትን ያማከርክ ሳይሆን አይቀርም
  1 መቁጥሪያ ፣ በዚህ በስደት ያለነው ሰወች አንተ የምትለውን አይነት (ከመሃል አንድ ፍሬ ከተጨመረበት) ያልከው አይደለም የምንጠቀመው ያለን ከዚህው የምናገኘውን መቁጠሪያ በመግዛት ፣ቅዱስ፣ዒልሻዳይ ፣አዶናይ፣ ጸባዖት፣ያህዊ፣እየሱስ ክርስቶስ፣አማኑዔል፣ወልደ እግዚአብሔር፣ወልደ ማርያም
  በዚህ ስም ባርከን ስንቀጠቅጠው ከዲያብሎስ ወጥመድ እንድንበታለን
  2 በመስቀል ላይ ግን ምታት አለ ያልከው የሚያሳዝን ነው መስቀል ትልቁ የሰይጣን መቀጥቀጫ ሳለ የዲያብሎስ መሳቢያ ነው ስትል አፈርኩ ላንተ
  እኔ እራሴ ያየሁትን ልመስክርላችሁ አዲስ አበባ ሽንቁሮ ሚካዔል የሚባል ገዳም አለ በዚያ ጸበል ቦታ አጋንንት በቅዱስ ሚካዔል ስም ሲለፈልፉ የሰማሁትን ፣አባ ግርማ ወንድሙን ያስቆማቸው እራሱ ሰይጣን ባሴረው እንደሆነ ፣ለምን እያቃጠለ ስለፈጀን ሲሉ ሰምቻለሁ
  ታዲያ ከሰይጣን ቢሆን በዚህ ቅዱስ ቦታ ስማቸው አይነሳም ነበር፥ ወገኖቸ ለሁላችንም ማስተዋልን ይስጠን ....

  ReplyDelete
 24. አንድ በሙቅ ውሃ ውስጥ ገላውን የሚታጠብ ሰው ሀገሩ ሙሉ በረሃ ይመስለዋል!!!!! ስለዚህ አንተም በድሮ ጊዜ የነበረህን የደብተራነት ታሪክ እየቆሰቆስክ የሌሎቹን ስም ታጠፋለህ፡፡ ቤተ-ክርስቲያናችን ተሃድሶ ሳይሆን የሚያስፈልጋት እንዳንተ አይነቱን ለምን እኔ ብቻ የሚሉትን ጠርጎ ማስወጣት ነው የሚበጃት!!!!! በውኑ አባ ግርማ አጋንንት የሚያስወጡት በተደገመበት መቁጠሪያ ከሆነ ለምን የደብተራውን ስራ ይቃወማሉ!! የይልቅ ስለሌላ ከማውራት የራስህን አጽዳ!!!!

  ReplyDelete
 25. tehadsom menafikm muslimim lalam lelam yflsifna emnetoch slemn new ortodoxn bicha lemetal yemitagelu?

  ReplyDelete
 26. የተድላና ፈንጠዝያ ትንቢት ጥንቆላ ነው፡-
  ወፋፍራም ፓስተሮቹ እነጆሹዋና ዳዊት ጠንቋዮች ናቸው!
  -በሚስዮናውያን ላይ የነበረ የቅኝግዛትና የባርነት መንፈስ፤
  -በመናፍቃን ላይ ያለ የ666ና የግብረሰዶማዊነት አሰራር…
  ወደጥልቁ ይውረድ!

  ReplyDelete