Monday, March 4, 2013

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ተፈጸመ

6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የተመረጠት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዓለ ሲመት የካቲት 24/2005 ዓ.ም. የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮችና ሊቃነ ጳጳሳት፣ የልዩ ልዩ ሃይማኖት አባቶች፣ ክቡር አቶ አባ ዱላ ገመዳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ፣ የፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ተወካይ፣ የአዲስ አበባ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል፡፡ ቅዱስነታቸው ሥርአተ ሲመታቸው ከተፈጸመ በኋላ ባደረጉት ቃለ መሐላዊ ንግግር በክርስቶስ ትምህርት ላይ የተመሠረተውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርትን ጠብቀው ለማስጠበቅ እንደሚተጉ፣ የሁሉም አባት እንደመሆናቸው ምእመናንንና ምእመናትን ያለአድልዎ በቅንንት በታማኝነትና በትህትና እንደሚያገለግሉ የገለጹ ሲሆን፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የጎደለውን ለመሙላት የጠመመውን ለማቅናትና አባጣ ጎርባጣውን ለማስተካከል ብልሹ አስተዳደርን ለማቃናት ከቅዱስ ሲኖዶስ ብዙ እንደሚጠበቅና ለዚህም እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡

የፈሪሳውያን ጥርቅም የሆነውና ከቤተክርስቲያን አባቶች በላይ እናውቃለን የሚለው፣ በቤተክርስቲያኗ የአስተዳደር ክፍተት ተጠቃሚ ለመሆንና ምርጫውን ለማዘግየት ሲሰራ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን በስውር ብሎጎቹ በዓለ ሲመቱ የካቲት 24 መሆኑን የተቃወመ ሲሆን፣ ምክንያቱ ደግሞ ቀኑ ወደፊት በአቢይ ጾም ውስጥ የሚውልበት ዓመት ስለሚኖር በጾም በዓለ ሲመት መከበር የለበትም የሚል “ትንኝ የማጥራት” ቅስቀሳ ቢያደርግም ሰሚ አላገኘም፡፡

ክሽፈት እንደ ማኅበረ ቅዱሳን በ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ
“ክሽፈት” የሚለው ሰሞነኛ ቃል የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መጽሐፍ ርዕስ ሆኖ በየጋዜጣውና በየመጽሔቱ ትልቅ የመወያያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ መጽሐፉ በኢትዮጵያ ያልከሸፈ ነገር የለም፤ ያልከሸፈ ነገር ቢኖር ኢትዮጵያውያን ለውጭ ወራሪዎች ያላቸው የጋራ አቋም ወይም ኢትዮጵያዊ ወኔ ብቻ ነው ይላል፡፡  እኛም ክሽፈት በሚለው ቃል ማኅበረ ቅዱሳንን መፈተሽ ወደድን፡፡ ከአቡነ ጳውሎስ ህልፈት በኋላና ከምርጫው ጋር በተያያዘ ሁሉም ከሽፎበት ያልከሸፈበት አንድ ነገር ብቻ የቀረ ይመስለናል፡፡ እርሱም በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ኮታ ማግኘቱና በባያብል ሙላት መወከሉ ብቻ ነው፡፡ ክሽፈቶቹ ምን ምን ናቸው? ለሚል ጠያቂ እነሆ ክሽፈቶቹ፦

ክሽፈት አንድ
ያገለግሉኛል ይተባበሩኛል ይረዱኛል ብሎ ተሯሩጦ አቃቤ መንበር ያደረጋቸው ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ባልተጠበቀ ሁኔታ ፊታቸውን ገና ከማለዳው ነበር ያዞሩበት፡፡ በዚህ ምክንያት አቃቤ መንበሩን መለወጥ አለብን ለማለት የዳዳቸው እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ክሽፈት ሁለት
ለእርሱ በሚመች መልኩ የምርጫ መስፈርት አውጥቶ ለደጋፊዎቹ ጳጳሳት ቢሰጥም ውድቅ ተደረገበት፡፡ ለምሳሌ፦
·        የዜግነት ጉዳይ (ይህ ደንብ አቡነ ማትያስን ለማግለል ሲባል የገባ ነው)
·        መነኮሳትም እጩ ይሁኑ ብሎ ያለው ተቀባይ አላገኘም፡፡ (ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ከዚህ ቀደም እንደ ዘገበው በገዳማቱ ለዘመናት የመለመላቸውና በሐሳቡ ያስቀመጣቸው ፓትርያርኮች  ሳይካተቱለት ቀርተዋል፡፡ በነገራችን ላይ ያረጋል አበጋዝ እስካሁን ሚስት ያላገባው ለፕትርክና ተመልምሎ ነው የሚል ነገር ማኅበሩ አካባቢ በሰፊው ሲናፈስ ነበር፡፡ ሁኔታው ከተመቻቸው በቶሎ መንኩሶ ለፕትርክና እንዲወዳደር ታስቦ ነበር ማላት ነው፡፡)
·        ፕትርክናው በዕጣ ይሁን የሚለው የማኅበሩ ሐሳብ ሰሚ አላገኘም፡፡

ክሽፈት ሦሰት
በዚህ መንገድ የፕትርክናው ተስፋ እየተመናመነ የመጣ ሲመስለው ማቅ “እርቅ ይቅደም” በማለት ለፍፎ ነበር፡፡ የማቅ አንዱ አሳፋሪ ተግባር ይህ ነው፡፡ 20 ዓመት ሙሉ ዝም ብሎ ተቀምጦ አሁን የእርሱ ፍላጎት ስላልተሟላና እቅዱ ስላልተሳካ እርቅ ይቅደም ማለቱ ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ እርቅ መቅደም አለበት ብለው ስለእርቅ የተናገሩትን እነአባይነህ ካሴን እስከማገድ ደረሰ፡፡ በዚህ ተግባሩም አንዳንድ አባላቱ “ማቅ እየኖረ ያለው ጽ/ቤቱ እንዳይዘጋ ብቻ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንን ትቷታል” እያሉ ነው፡፡ ይህ ለማቅ ክሽፈት ነው፡፡

ክሽፈት አራት
ከቅርብ ወዳጆቹ አንዱ አቡነ ቀሌምንጦስ የማደራጃ መምሪያ የበላይ ሀላፊ ሊቀጳጳስ “እስከዛሬ ሳናውቅ ነው ከማኅበሩ ጎን የቆምነው” ብለው አባ ሠረቀ ብርሃንንና የማደራጃ መምሪያ ሰራተኞችን ይቅርታ መጠየቃቸውና ከአንድ አባት የሚጠበቅ ተግባር ማከናወናቸው ማቅም አዘውትሮ ስማቸውን ማጥፋቱ የማቅ አስገራሚው ክሽፈት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ክሽፈት አምስት
የቤተክህነት የመምሪያ ሃላፊዎችን በG8 አማካኝነት በተለይ የትግራይ ተወላጆችን ወደሌላ በማዘዋወር ለምርጫ ድምጽ ያላቸውን መምሪያዎችን እርሱ በሚፈልጋቸው ሰዎች ለማስያዝ ሞክሯል፡፡ ይሁን እንጂ ገና ከጠዋቱ የልብ ወዳጁና ወደመምሪያ ሃላፊነት ያስመጣው ሊቀትጉሃን ሀ/ጊዮርጊስ ዳኜ ወንጀል ሰርቶ ሸዋሮቢት ወረደበት፡፡ ከዚህ የበለጠ ምን ክሽፈት አለ?
  
ክሽፈት ስድስት
ምርጫውን ሌላ አቅጣጫ ለማስያዝ የሞከረውና በልዩ ልዩ መንገድ አልታዘዝ ባይነትን እያሰፈነ የመጣው ማቅ አቡነ ናትናኤል ብርቱ ደብዳቤ ጽፈው መንግስት ጣልቃ እንዲገባና ስርአት እንዲያሰፍን በመጠየቅ በቤተክህነት ውስጥ የተደራጀ ቡድን መኖሩን፣ በዚህ ቡድን ውስጥ የቤተክርስቲያን ባለስልጣናት መኖራቸውን (ከአራዳ ክፍለ ከተማ ሥራ አስፈጻሚነቱ በግምገማ የተባረረው እስክንድር ገብረ ክርስቶስና አደገኛ ቦዘኔዎች ያሉበት ጣሊያን ሰፈር ተወልዶ ያደገው ተስፋዬ ውብሸት) ተገልጿል፡፡ በዚህ መሰረት ለመንግስት የተጻፈውን ደብዳቤ ተከትሎ ቤተክህነት ውስጥ የተጀመሩ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች መገታታቸው ማቅ ያሰበውን ግርግር ሳያሳከ ከሽፎበታል፡፡

ክሽፈት ሰባት
ይህን ተከትሎ የቲዎሎጂ ማኅበር ተብዬው ሰብሳቢ አቶ ማንያዘዋል አበበ የማኅበሩን ጽ/ቤት ተገን አድርጎ ግቢውን በወንጌል ሳይሆን በወሬ ሲንጥ ከርሞ አሁንም በሱና በማህበሩ በኩል ማቅ ሊጠቀም ሲል በአቃቤ መንበር ናትናኤል አማካኝነት ከጥር 3/2005 ዓ.ም ቤተክህነት ግቢ ዝር እንዳይል መደረጉ እሱን እያሉ በሰበብ ይገቡ የነበሩት፦
1ኛ. የቤተክህነቱን ግቢ ብላክ ማርኬት ያደረገው ዶላር መንዛሪውና ከህገወጦች ጋር ተመሳጥሮ ኮንደሚኒየም አሻሻጭ የሆነው ኃይለማርያም
2ኛ. የስምአጽድቅ አዘጋጅና የሁለተኛው ሐመር የዕንቁ መጽሔት አምደኛ የሆነው ታደሰ ወርቁ
3ኛ. የዋልድባን ጉዳይ መነሻ በማድረግ ህዝብንና መንግስትን ለማጣላት በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ “ምላጭ ቢያብጥ” በሚል ርእስ አሸባሪ ጽሑፍ የጻፈውና “በዓላት” የተሰኘ መጽሐፍ ጽፎ “በዓላት በገበሬዎች ኮንፍረንስ በመንግስት ሚዲያ ልፈፋ አይሻሩም” በማለት ኋላቀርና ፖለቲካዊ አቋሙን ሃይማኖትን አስታኮ መጻፍ የሚወደው ብርሃን አድማስ፣
4ኛ. በጥንቆላ፣ በገንዘብ ዝርፊያ፣ በአስገድዶ መድፈር በተደጋጋሚ በማቅ ሸንጎ የተከሰሰው ህሩይ ባየ፣ የማንያዘዋል እጣ ይደርሰናል ብለው ቤተክህነት ግቢ ውስጥ አይደለም በቤተክህነት አካባቢ ዝር ሲሉ አለመታየታቸው ለማቅ ሌላው ትልቅ ክሸፈት ነው፡፡

ክሽፈት ስምንት
ማቅ በአስመራጭ ኮሚቴው ውስጥ በውክልናም በስውርም ያስገባቸው ባያብል ሙላት፣ የማኅበሩ ፈንድ አሰባሳቢውና በዘንድሮው የመስቀል በዓል ላይ በቶቶት ክትፎ ቤት በተደረገው የበዓል ዝግጅት ላይ ሲደንሱ የነበሩት የጭድ ተራው የመንደር ቀኛዝማች ሃይሉ  እና የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጣቶችን ለአድማ፣ ለረብሻ ሲያሰማራ የነበረውና በማቅ ሰዎች ተጽፎ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ስም ለሲኖዶስ ቀርቦ የነበረውንና ብዙ ሊቃውንት እንዲወገዙ ጥየቄ የቀረበበትንና ውድቅ የተደረገውን የክስ ፋይል ካቀረቡት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የማቅ ሰዎች መካከል አንዱ ሄኖክ ቢኖሩም ምንም ሳይሰሩለት መበተናቸውና በተለይ ብዙ የተማመነበት ባያብል ምርጫው ትክክለኛና ፍትሐዊ መሆኑን በሚዲያ “ነጻ መሆናችንን የሚያረጋግጠው እግዚአብሔርና ኅሊናችን ነው” በማለቱና ሀራ ዘተዋህዶን ስለሐሰተኛ ዘገባው በጎን በመውቀሱ ማቅ በመጨረሻው ላይ ያጋጠመው ትልቅ ክሽፈት ሆኖ ተወስዷል፡፡

ክሽፈት ዘጠኝ
ቀደም ብሎ ለፓትርያርክነት ባጫቸው አቡነ ሉቃስ ላይ እምነት ማጣቱና ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የልጅ አባት መሆናቸውና ከአብነት ትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ራሽያ የለመዱት ሰዶማዊነት ነገ ሌላ መዘዝ ያመጣብኛል በማለት እሳቸውን ተወት በማድረግ፣ ፊቱን ትክክለኛ እጩው ወደሆኑት ብሄረተኛ የአንኮበር ፖለቲካውን (መንግስትና ፕትርክና ከሸዋ) የሚያራምዱለትን አባ ማቴዎስን እጩ ውስጥ ቢያስገባም ሊመረጡ ባለመቻላቸው ማቅ ዋናውን ክሽፈት ለማስተናገድ ተገዷል፡፡

ክሽፈት አሥር
ስለምርጫ አጠቃላይ ሁኔታ ግንዛቤ ለማስጨበጥ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ ከሚጠበቀው በላይ ባጓተተውና ከአቡነ ጳውሎስ ህልፈት በኋላ “ፕትርክናው ዘንድሮ ከእኔ አይወጣም” በሚል ቅዠት ከሚገባው በላይ ባፋጠነው ህንጻ ላይ የጠራው የአድማ ስብሰባ በጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጁ መታገዱ ክሽፈት ነው፡፡

ክሽፈት አሥራ አንድ
ማቅ ለተሐድሶ እንቅስቃሴ ማጥፊያ በማለት ከየባለሀብቱ በየአዳራሹ በሰበሰበው ገንዘብ ያደራጃቸውና መንፈሳዊ ህይወታቸውንና ሰብእናቸውን ሳይገነባላቸው ቤተክርስቲያን ደክማ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች አስመርቃ ክፍለሃገር ብትመድባቸውም ተልእኳቸውን ንቀውና ጠቅጥቀው በማቅ የሻይ ቡና በጀት ቀኑን ሙሉ በቱሪስት ሆቴል ውለው ማታ ወደየአውደ ምሕረቱ “ለማስተማር” የሚበተኑትና ወንጌልን ሳይሆን ስድብን፣ ትችትን፣ ዘለፋን፣ ተረትን ሲሰብኩ የኖሩት በተለምዶ የቱሪስቱ ቡድን ተብለው የሚጠሩት በማቅ የተገባላቸው የፀረ ተሃድሶ ጥምረት ቢሮ መከፈት ከሽፎ የዘወትር መዋያቸው ቱሪስት ሆቴል በመዘጋቱም ይህን ተከትሎ እርስ በርስ በመከፋፈል (ባለመተማመን) ቡድኑ (ጥምረቱ) በመበተኑ፣ ማቅም ትኩረቱን ወደ ምርጫው በማድረጉ የትነው ያላችሁት? ስሎ ስላልፈለጋቸው ልዩነታቸው ሰፍቷልና ማቅ የደረሰበት ሌላው ክሽፈት ነው፡፡ ዛሬ የቱሪስቱ ቡድን አባላት 99% የሚውሉት ለየብቻቸው ሲሆን፣ ሁሉም ቤልኤር፣ ቀበና አካባቢ ከተከራዩአቸው ቤቶች ባለመራቅ አንድን ሻይ ቤት ከአንድ ቀን በላይ ባለመጠቀም አቋም ፀንተው ታይተዋል፡፡ ይህ ለማቅም ለቡድኑ አባላትም ሌላው አሳዛኝ ክሽፈት ነው፡፡

ክሽፈት አስራ ሁለት
የሀገር ውስጥ እና መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የማቅ አባላት (በላቸው፣ ኤፍሬም፣ መስፍን፣ ብርሃጉ ጐበና) ከአ.አ ማዕከል ጋር በፓትርያርኩ ምርጫ የተነሳ በሀሳብ መከፋፈላቸውና ይህን ፖለቲካዊ አቋማቸውን ተከትሎ የውስጥ ልዩነት እየሰፋ መሄዱን ማወቅ ተችሏል፡፡ ይህስ ክሽፈት አይደለም?
  
ክሽፈት አስራ ሶስት
ማቅ ዘወትር ሲዘምትባቸው የነበሩት ዘማሪያን፣ ማቅና አባላቱ የዜማ ሊቅ ሳይሆኑ መዝሙራቸውን የተሐድሶ ነው በማለት በየዐውደ ምሕረቱ ሲያሳጧቸው የነበሩ ዘማሪያን “አለው ነገር” በሚለው አልበማቸው ምድራችንን በመሸፈናቸው የማቅ ዘመቻ መክሸፉን ያስተዋልንበትስ አጋጣሚ ቢሆን ሌላው የማቅ ክሽፈት አይደለም?

ክሽፈት አስራ አራት
ማቅ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ሲጓጓለትና ሲንገበገብለት የነበረው በፓትርያርክነት ደረጃ ቤተክርስቲያኒቱን ብሎም ሀገሪቱን ለመቆጣጠር (የአንኮበር ፖለቲካን ለማራመድ) የፓትርያርክነቱን ማዕረግ ለራሱ ወገኖች ቢቻል ከገዳም ካልሆነም ከሸዋ ጳጳሳት (ለምሣሌ እንደ አቡነ ማቴዎስ) ያሉትን እዚህ ለማስቀመጥ ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ ከምንግዜውም በላይ በበጀት፣ በመወቅራዊ አሰላለፍ፣ በምክር፣ የራሱን የህግ ባለሙያዎች ረቂቅ ህግ እንዲያዘጋጁ በመመደብ ወዘተ በከፍተኛ ሁኔታ ሲሳተፍ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የካቲት 21/2005 ዓ.ም ምኞቱ ሳይሳካ፣ ሕልሙ ሳይተረጐም፣ የዘራው ሳያፈራ እጩው ተሸንፈው ማቅ ፓትርያርክነት እያማረው ቀረ፡፡ የካቲት 24/2005 ዓ.ም ቀንም ብፁእ አቡነ ማትያስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተብለው መንበረ ፕትርክናውን ተረከቡ፡፡ ከአቡነ ጳውሎስ ህልፈት በኋላ እስከ ስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ካደረጋቸው ወሳኝ እንቅስቃሴዎች አንድም ሳያሳካ ሁሉንም በሚቻል ሁኔታ በክሽፈት ደምድሟል፡፡

ክሽፈት እንደ ማህበረ ቅዱሳን!28 comments:

 1. ay abaselamawech hulum yawerachihut betekaraniw new yemanebew endih slachihu ye mk abl hogn sayhon enanten kefriachihu slawekuachihu new nsa nsa nsa gibuuuuuuuuu mk mn madreg endalebet yakal eskahunm le betekrstiyan zeb hono yemiyageleglen mk new

  ReplyDelete
 2. ከዋናው ርእስ ስር በንዑስ፤ «ክሽፈት እንደማኅበረ ቅዱሳን!» የሚል ቢገባ ጽሁፉን ሳቢና ገላጭ ያደርገዋል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. BETAM YEWEREDE ANENEGAGER NEGERU YEBETEKIRTIAN TELAT SEYTAN BENATE ADRO SILEMINAGER AYSIGERIMIM

   Delete
 3. ክሽፈት እንደ አባ ሰላማ። በሐዋርያት የተጀመረው የእጣ ማውጣት ስርአት ይፈፀም በማለቱ እንደ ክሽፈት ቆጠራችሁት?

  ReplyDelete
 4. God bless you guys.it's so bad failured to MK. if you do bad things to somebody, you will get bcak to you.......this is good lessen to every evil peoples and group. thanks aba selama for your truth assessment..........

  ReplyDelete
 5. ማህበረ ቅዱሳን የሚዘጋበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡ የሄ የዝንጀሮ መንጋ/ማህበር/ ካልተበተነ ቤተ ክርስቲያን ሰላም አታገኝም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Mignot ayikelekelim, temegn. if MK is from the will of God, nobody touches it. You are trying your best to get MK in trouble with the new Patriarck and the government.

   MK go ahead with your job, let others talk and you do your job.

   May God bless Ethiopia

   Delete
  2. ማቅ ተላላኪ እና አጥፊ የደህንነት ቅጥረኛ ድርጅት ነው። እውነት ነው፤ ማቅ ፊት የእርቅ ወሬ አይወራም። ማቅ መጥፋት ሳይሆን ቢደመስስ ወይም እንደተነገረለት ብን ቢል አገሪቱም ሀይማኖቱም በነፃነት፣ በፍቅር፣ በመከባበርና በናፈቅነው አንድነት እንመረቅን ነበር።

   Delete
 6. Satwku yemtistifu nachihu

  Yihn hulu le enat 'Kishfet' bilachihu yetsafachihut ewnet MK adrgot kehone, ewntim lebetkirstian tenkro endesera yemiyasy new. Mikniyatum 80% kirstianu yahun yepatric mirch yemgnst ej endalebt yawkal. Silzih benat zegab mesert MK yihn sitagl nebr malt new. Welkldone MK

  ReplyDelete
 7. መቶ አለቃ ያረጋል አበጋዝMarch 5, 2013 at 3:48 AM

  ክሽፈት እንደ ማኅበረ ቅዱሳን በቁጥር አይገለጽም የአቶ ዳንዔል ክብረት : የአቶ አሉላ: እና የአቶ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም....... የሰይጣን ማህበሩ የሰጣቸውን ተግባር አለመፈጸማቸው ክሽፈት ቢቻ ሳይሆን ክስረት እና ውድቀት ነው:: ባጠቃላይ ግን ማቅ አፈር ልሶ እንደ ኮብራ እባብ በአዲስ ተንኮል ብቅ ከማለት የውንብድና ስራውን በማቆም ቢያንስ ንስሃ እንዲባ ቢመከር ይሻላል

  ReplyDelete
 8. Teru eyeta new abawoch EGZIABHER yemisanew neger yelem Yegermachehual yemetetsefut bemulu ewenetegna negr bemehonu Egziabeher Yerdacehu balehubet hager mk yemibalu sim atfiwoch alu lenesu akahed yebetkerseteyanu astedadarina mezemeran selaletemechuachew bagegnut agatami ye egziabeher kal yemisebekebetn awedemihert yemesadebeyana yemasamecha eyadergu yewha yehonu miemenanen bemerzachew eyebekelu neger gin Egziabeher negr alew enesu yebtekiresteyan lijochn eyasadedu yikir yebelachew Egziabehr gin hulun astekakele

  ReplyDelete
 9. Yemk abalat betekrstian yetemeseretechbetn Wana
  Alama bemezengat ye and tinish mahber buchila bemehon
  Eyaterameswat yalut mebawan betikikil yemaysgebu abalat
  Ahunm sir sedew yalu bemehonu akahedachew tifat slemihon
  Mikir mestet yasfeligal.

  ReplyDelete
 10. From what I read we need MK to our beloved church bz they stand for truth.thank you aba selama you tried to accuse MK but you tell us their good stand .

  ReplyDelete
 11. አባ ሰላማ እግዚአብሔር አብዝቶ አብዝቶ ይባርካችሁ። እንዴት ያለ ግሩም ፅሁፍ ና ስኬታማ የሆነ የማቅ ክሽፈትን የሚያበስር በአስተዋይ ክርስቲያኖች የተገመገመ፣ የተገለፀ፣ ፅሁፍ ነው። የሰይጣንን ተንኮልና የቤተክርስቲያናችንን የጠላት ሥራ፤ በመንፈስ ቅዱስ ረቂቅ ሥራ የገለፀ። አቤት አቤት የሰይጣን ክሽፈት// ገና ገና ይገለጣሉ። በጨለማው መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ፤ በክርስቶስ ብርሃን ይገለፃሉ። ሃሌሉያ።  ReplyDelete
 12. ክሽፈት እንደ አባ ሰላማ!!

  ReplyDelete
 13. እናንተ አባ ሰላማዎች እንደ ዘሪሁን ሙላቱና እንደ ጽጌ ስጦታው ሞራል አልፈጠረባችሁም ማለት ነው እሱ ናቸው ውሽት በማውራት አቋማችን በመከያየር የሚታወቁት ። ስለዘህ እናንተ ወይ እነሱን ናችሁ ወይም የነሱ ቢጤ ነሰችሁ ማለት ነው ።

  ReplyDelete
 14. kibie atetachihugn Mk'n endih enawardew enji mechem alitechalem. bayihon besidib enimokir.

  ReplyDelete
 15. አባ ሰላማዎች እንደምትሉት በእውነት ማኅበረ ቅዱሳን የሸዋን መንግሥት ለመመለስ ከሆነ የሚታገለው እናንተስ የትግራዮችን መንግሥት ለመጠበቅ ነው እየታገላችሁ ያላችሁት ? ለመሆኑ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሸዋ ልጆች ብቻ ናቸው እንዴ ? ከመላው ኢትዮጵያ የሚወለዱ አባላት ያሉት መስሎይ ? በርግጥ የወያኔ አባል ለመሆን ትግሬ መሆን ግድ ነው ። የወያኔ አገልጋይ ለመሆን ግን የሚጠይቀው ህሊናንም ሆነ ክርስትናን ሺጦ ሆድን አስፍቶ ለሆድ መገዛትን ብቻ ነው የሚጠይቀው። ''አሌ ሎሙ እለይትቀነዩ ለከርሶሙ !'' እንዳለው። እኔ የነአባ ሰላማን ተልዕኮ ለማወቅ በጣም ተቸግሬአለሁ። አንዳንዴ ከምርጫ በፊት እርቀ ሰላም ይቅደም የሚለውን የብዙኃኑን ሃሳብ የሚጋሩ የሚመስል አቋሞች ያሏቸው መስለው ይታዩ ነበር። በስደት ያለውን ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚደግፉም መስለው የሚታዩበት ሁኔታ አለ። በሌላ በኩል ደግሞ አሁንም ሆነ ከአባ ማትያስ ምርጫ በፊት አባ ማትያስ እንዲመረጡና የወያኔ አባት ሁነው መመረጣቸውን ደግሞ ሲደግፉ እናያለን። የት ላይ ነው አባ ሰላማውያን የቆሙት? ባንድ እውነታ ላይ ሁለት እውነቶች ሊኖሩ ይችላሉ ? ነገረ መለኮትን በተመለከተ ድርሳናቱንና ገድላቱን የሃይማኖት መረጃ አድርገን አንቁጠራቸው የሚለውን ሃሳባቸውን እኔም እጋራለሁ። 'ክርስቶስ ነው አማላጃችን' የሚለውን የጴንጤዎችን ቲዎሎጅ ስለሚቀበሉ ይህን እምነታቸውን ግን አልጋራም። ስለዚህ የኔ ጥያቄ የሚሆነው እነአባ ሰላማ እነማን ናቸው ? ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Aba Selama, Tikekelegna Kerestiyanoch nachew.
   Not poletician.

   Delete
 16. አይ kebede Bogale?
  "ነገረ መለኮትን በተመለከተ ድርሳናቱንና ገድላቱን የሃይማኖት መረጃ አድርገን አንቁጠራቸው ?" አልህ?
  እና የምን መረጃ ናቸው? የፓሊስ?የአቃቤ ሕግ?
  አዋልድ፣ገድላትና ድርሳናቱ የወንጌል መረቅ (የወንጌል ልጆች) መሆናቸውን አጠፋኸው?
  እስከ ዛሬ ስለ አባ ሰላማ አለማወቅህ ረቀውብህ አልመሰለኝም። እንዲህ አንተ ከፍለህ የምታምነውን ስለደገፉ ይሆን ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወገኔ ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የነገረ መለኮት መመሪያዎቿና መረጀዎቿ 81ዱ መጽሐፍቶቿ ናቸው እንጅ ከዘመናት በኋላ በአንዳንድ ደረስያን የተደረሱት ድርሳነ መላእክት፥ ገድለ ሰማዕታትና ገድለ ቅዱሳን በነገረ መለኮት ላይ ለሚነሳ ጥያቄ እንደ ማስረጃነት አይቀርቡም። ሌላው ቢቀር ግንቦት 21 ቀን 1870 ዓ.ም ቦሩ ሜዳ (ወሎ) በአፄ ዮሐንስና በያኔው ንጉስ ምኒልክና ተክለሃይማኖት ዳኝነት በአንድ በኩል በነአለቃ ኪዳነ ወልድ ፥ አለቃ ተክለ ሥላሴና መላከ ብርሃን ወልደ ዮሐንስ፤ በተቃራኒ በአለቃ ሀብተ ወልድ ፥ አለቃ ውቤ ፥ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስና አለቃ ቤተ ሌዊ መካከል ስለተደረገው የ3 ልደትና 2 ልደት ክርክር ታሪክ ብታነብ መልካም ነው። በዛን ጊዜ ከ3 ልድተ አማኝ ተከራካሪዎች መካከል አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ ''ደብረ ብርሃን ውስጥ ከሚገኝ ተአምረ ማርያም ላይ ተጽፎ አንብቤ አለሁ'' በማለታቸው ''ከምታስተምረው ከዐራቱ ጉባኤ ውስጥ አጣህና ከተአምረ ማርያም መረጃ ትጠቅሳለህ'' ተብለው በውርዴት እንደተሸነፉ የሚያስርዳውን ታሪክ ተረዳ። ስለዚህ አዋልድ መጻሕፍት መቸውንም ለሃይማኖት ክርክር ማስረጃ ሁነው ቀርበው ተቀባይነት ያገኙበት ጊዜ በታሪክ መዛግብት ውስጥ አይገኝም። ''ከመጠምጠም መማር ይቅደም'' አበው።

   Delete
  2. YEHAWARIYAT SIRA(GEDLE HAWARIYAT AYDELEMN?).GEDLAT KEMETSHAF KIDUS AYTEBABERUM BILEH TAMNALEH? 81 yemtlachewunm eko pentewochu(tehadsowochu) aykebelutm .Endalkew begedlatu lemayamn metshaf kidus masreja adrgeh litteks tichilaleh.lemiyamn gin wudase amlakin,wudase kidusanin,melka melkun,dirsanatunina gedlatun bititeks sihtet aydelem(new weys begedlatuna dirsanatu tiritare alebh?).yaba giyorgis metshafe mistir,yemelake birhan admasu jenbere kokuha haymanot yenegere melekot masreja aydelum?

   Delete
  3. አትሳሳት ወገኔ፥ ግብረ ሓዋርያትን የጻፈው ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው እንጅ አፄ ዘራ ያዕቆብ ወይም አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አይደሉም ። ከ4ቱ ወንጌል እና ከመልዕክታቱ ጋር እኩል ነው። ስለሆነም አዋልድ ተብለው ከሚጥሩት ጋር ሳይሆን የዶግማ መጻሕፍት ከሚባሉት ጋር የሚቆጠር ነው። ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ በኢትዮጵያ ነገሥታትና በእዛቸው ሥር የነበሩ አባቶች የደረሷቸው መልካ መልኮች፥ ድርሳናትና ገድሎች በነገረ መለኮት ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች በማስረጃነት ቀርበው አያውቁም። እነዚህን ድረሰቶች የሃይማኖት ማስረጃዎች አይደሉም የሚሉትን ከሆነ መንፍቃን እያላችሁ የምትጠርዋቸው ተሳስታችኁኣል። ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት የበለጠ ለማወቅ ከፈለግህ ''ሃይማኖት አበው '' እየተባለ የሚታወቀውን መጽሐፍ አንብብ። በዚያ ውስጥ የተዋሕዶ መምሕራን እነቅዱስ ቄርሎስ (380-444ዓእ)፥ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ (-454)፥ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (347-407ዓእ)እና ሌች አባቶች የጻፉትን የብሉይና ሓዲስ ሀተታ በሰፊው ተመልከት። ድርሳናቱን፥ መልካመልኮቹን፥ ገድላቱን በግልህ ያዛቸው እንጅ ለስብከተ ወንጌል አትጠቀምባቸው። እንደ ዶግማ መጻሕፍት አድርገህ አትቁጠራቸው። ከዚህ ሌላ ስለ ኦርቶዶክስ ክርስትና የምልህ አይኖርም። ከአክብሮት ጋር ፤ እሁከ ከበደ ዘውእቱ ስምአ ጽድቅ ወተላዌ ፍኖቶሙ ለአበዊነ ሐዋርያት።

   Delete
 17. "ድርሳናቱን፥ መልካመልኮቹን፥ ገድላቱን በግልህ ያዛቸው እንጅ ለስብከተ ወንጌል አትጠቀምባቸው።"?
  አይ ከቤ
  የቆምሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል አሉ አበው።
  ጥሩ ይብቃን ከዚህ ሌላ የምትለውም ስለሌለ

  ReplyDelete
 18. sewoch yihinin seytan atanagrut zigut and niftam endezih ale bilachihu atimelusulet

  ReplyDelete