Saturday, March 9, 2013

ፍሬ-አልባ ጩኸት

Read in PDF
አንሰ እቤ አምግዕዝየ ኵሉ ሰብእ ሐሳዊ ውእቱ!
(የዳዊት መዝሙር 115)
መስፍን ወልደ ማርያም
የካቲት 2005

አቶ ዳንኤልን አላውቀውም፤ ለካ ብዙ ጭፍሮች ያሉት ሰው ነው፤ በጣም ተንጫጩለት፤ የሎሌ ነገር ሆነና ጩኸታቸው አንድ ነው፤ ጉዳዩን ጭራሽ አያውቁትም፤ ያንገበገባቸው መሪያቸው መነካቱ ነው፤ ለሎሌዎቹ መልስ መስጠት ባልተገባ ነበር፤ ነገር ግን ያደረጉት ትክክል መስሎአቸው እንዳይኩራሩና በያዙት የመክሸፍ መንገድ አንዳይቀጥሉ አንዳንድ ነጥቦችን ላብራራላቸው ፈለግሁ፤ ውጤት ይኖረዋል ብዬ ሳይሆን ለኔው ለራሴና ለማኅበረሰባችን ጤንነት ነው፤ ራሴን ከአቶ ዳንኤል ጭፍሮች ለመከላከል ፈልጌ እንዳይመስል፤ አትኩሮት በጉዳዩ ላይ እንዲሆን ለመሞከር ነው።

አንዳንዶቹ ዲያቆን የሚል ቅጽል ባለመጨመሬ ሆን ብዬ መስሎአቸዋል፤ ባለማወቅ ነው፤ ራሴን ተጠራጥሬ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ከፈትሁና የማውቀውን ነገረኝ፤የተካነ፣ ምሥጢር ያየ፤ ቀዳሽ የሚል፤ በዚህ መስፈርት እኔም ዱሮ ዲያቆን ነበርሁ፤ ዛሬም ይህንን የሚያሙዋሉ ወጣቶች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚልዮን ባይሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ይኖራሉ፤ በዚያ ላይ እኔ እንደማውቀው ዲያቆን ሦስት ደረጃዎች ሲኖሩት የዲያቆኖች አለቃ ሊቀ ዲያቆናት ይባላል፤ አቶ ዳንኤል ሊቀ ዲያቆናትም አልሆነም፤ የአቶ ዳንኤል ዲያቆንነት የቱ ዘንድ እንደሚወድቅና ምን ማለትም እንደሆነ አላውቅም፤ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም እንዲህ ያለማዕርግ መስጠት ጀምራ እንደሆነና ለነማን እንደምትሰጥ አላውቅም፤ እኔ ዱሮ የማውቀው ዲያቆን የቅስና ሥልጣን (በምድር ያሰራችሁት በሰማይም የታሰረ ይሆናል፤) ሲያገኝ መምሬ መባሉን ነው።

ወደ ተነሣሁበት ጉዳይ ልግባ አንድ መጽሐፍ አሳተምሁ፤ አውቃለሁ የሚለው አቶ ዳንኤል ተነሥቶ ስለ መጽሐፉም ስለሌላ ሌላም የማያውቀውን ጻፈ፤ ስድስት የግድፈት ነጥቦችን ለቅሜ በማስረጃ እያስደገፍሁ የማያዳግም መልስ ሰጠሁት፤ ይህንን ያደረግሁበት ምክንያት ጭፍሮቹ እንዳሉት ሥራዬን አትንቀፉት በማለት በመታበይ አይደለም፤ ማናቸውም ሥራ አደባባይ ሲወጣ መነቀፉ አይቀርም፤ ስሕተትም አይጠፋም፤ አንድ ሰው በአንድ የአገር ወይም የማኅበረሰብ ጉዳይ ላይ ሲጽፍ ወይም በአደባባይ ሲናገር ራሱን ማጋለጡ ነው፤ የአቶ ዳንኤል ጭፍሮች ይህንን የማያውቁትን ጉዳይ ለእኔ ለማስተማር መከጀላቸው ጨቅላነታቸውን ያሳያል፤ በእኔ ላይ ባወረዱት ውርጅብኝ እንኳን ጉድጓድ ቆፍረው ራሳቸውን ቀብረው ነው፤ እውነተኛ ማንነታቸውን ደብቀው ነው፤ እነዚህ ጭፍሮች ስለመጋለጥ የሚያውቁት የለም፤ ስለዚህም ጉርጓድ ውስጥ ተቀብረው ስለማያውቁት ነገር መጮሁ የመጀመሪያው ስሕተታቸው ነው፤ ለነገሩ ስሕተት አይደለም፤ ወኔ-ቢስነት ነው።
እነዚህ ሁሉ ጭፍሮች ለጩኸት ከመጠራራታቸው በፊት መጽሐፉን ለማንበብና የክርክሩ መነሻ የሆኑትን ነጥቦች ለመጨበጥ አልሞከሩም፤ ወደው አይመስለኝም፤ ንዴታቸውን ለመግለጽና ግዳይ ለመጣል ስለቸኮሉ ለእነሱ ችሎታ የሚቀልለውን
‹‹የአንተ አሽከር፣ የአንተ ቡችላ፣
ኩፍ ኩፍ ይላል እንደጉሽ ጠላ!
በማለት በአደባባይ አቅራሩ፤ የችሎታ ማነስና ችኮላ ተለውሶ ያንን ጫጫታ አስከተለ፤ ገና ይቀጥላል፤ ባገኙን ቦታ ሁሉ ይህንን ጀብዱአቸውን ሊገልጹልኝ የሞከሩም አሉ፤ ከመሀከላቸው አንድም አንኳን ጉዳዩን ለመገንዘብና በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሞከረ አለመኖሩ የአስተሳሰብ ደረጃቸውን በግልጽ ያመለክታል፤ የሁሉም ዘገባ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ነው።
§  ከመሀከላቸው ስለመጽሐፉ የተናገረ አንድም የለም፤
§  ከመሀከላቸው አንድም ሰው አቶ ዳንኤል ስለ ጻፈው የተናገረ የለም፤
§  መጽሐፉን ሳያነቡና የአቶ ዳንኤልን ጽሑፍ ሳያነቡ እንዴት ብለው እኔ በጻፍሁት ብቻ እንደዚያ ያለ የንዴት ጫጫታ ማሰማት ቻሉ?

ለጭፍራዎቹ በመጽሐፉና በአቶ ዳንኤል ጽሑፍ መሀከል ምንም ግንኙነት እንዳላዩበት ግልጽ ነው፤ ሊያዩበትም አይችሉም፤ ስለዚህ የእውቀት ጉድለታቸውን በንዴት ተኩት፤ እነሱው ራሳቸው የተገነዘቡትን የእውቀት ጉድለታቸውን እያጋለጡ ስለመጽሐፉ ለመናገር ወኔ አላገኙም፤ የኢትዮጵያውያን ባህላዊ ማምለጫና መብለጫ በሆነው የብልጣ ብልጥ ዘዴ ተጠቅመው በእነሱ ግምት እነሱን ከፍ እኔን ዝቅ አድርገው ለማሳየት ሞከሩ፤ ጭፍሮቹ በሙሉ እውቀቱ ስለሌላቸው መጽሐፉን ረሱት፤ ስለዚህም ራሳቸውን የሥነምግባር ሊቃውንት አደረጉና ትንሽነታቸውን ወደ በላይነት ለመለወጥ ጣሩ፤ ይህ ብልጣብልጥነት እንደማያዋጣ ስለገባቸውና የእውቀታቸውንም ጎዶሎነት ስለተገነዘቡ ማንነታቸውን ሳይገልጹ ስማቸውን ደብቀው በአደባባይ ደነፉ፤ ደስ አላቸው፤ አስደሰቱ፤ ‹‹ያንን ፕሮፌሰር ነኝ ብሎ የሚኮፈስ ሰውዬ ልክ ልኩን ነገርነው! ልኩን እንዲያውቅና ከእኛ የማይሻል መሆኑንም ነገርነው!›› አንዳንዶቹ የእውቀት ደረጃቸውን አዘቅት ሲያወርዱ ከመስፍን ጋር ፕሮፌሰርነትንም አብረው ይኮንናሉ! አይ ፕሮፌሰርነት! እንዲህ ከሆነ ይቅርብን! እያሉ ዘላበዱ።
ተመካክረው የተነሡት በእነሱ ሚዛን ስለመስፍን ወልደማርያም ምግባረ -ብልሹነት ለዓለም ለመንገር ነው፤ አዋጃቸውን እንቀበለው፤ ስለመስፍን ወልደማርያም አንድ እውቀት ያስጨብጠናል፤ ዋናው ጉዳይ ግን መስፍን ወልደማርያም አይደለም፤ ዋናው ጉዳይ መጽሐፉ ነው፤ እንግዲህ ስለመጽሐፉ ምንም የማያውቅ ሰው ስለመስፍን ወልደማርያም መናገር የሚችለው ስንት ገደሎችን ዘልሎ ነው? ሁሉም ያሉት መስፍን ወልደማርያም ለአቶ ዳንኤል የሰጠው መልስ ስድብ ነበር የሚል ነው፤ ነገር ግን ከመሀከላቸው አንድም ሰው ስድቡ ምን እንደነበረ አልተናገረም፤ አንዴም ደህና አድርጎ ያላነበበውን ደጋግሜ አንቤዋለሁ ብሎ ሐሰት የተናገረን ሰው ሐሰት ተናግረሃል ማለት፣ የማያውቀውን አውቃለሁ ብሎ የተናገረ ሰውን አታውቅም ማለት፣ የማያውቀውንና ያልሆነውን ነገር ሲለጥፍብኝና የተናገረውን መልሶ ምሥጢር በማድረጉ የደብተራ ተንኮል ማለት፣ ለእኔ ስድብ አይደለም፤ እውነትን መናገር፣ ወይም ፈረንጆች እንደሚሉት አካፋን አካፋ ብሎ መጥራት ነው፤ ማሰብ የሚችል ሰው ለተናገርሁት ማስረጃ እንዳይጠይቀኝ ማስረጃዎቼን ሁሉ ቁልጭ አድርጌ አቅርቤአለሁ፤ እንዲያውም ትልልቅ ግድፈት የምላቸውን ነገሮች አልገባሁባቸውም፤ እዚያ ብገባ የበለጠ አንጫጫ ነበር፤
ከጭፍሮቹ አንዱም እንኳን መጽሐፉን ያነበበ አይመስለኝም፤ ከጭፍሮቹ አንዱም እንኳን በአቶ ዳንኤል ጽሑፍ ውስጥ ምንም እንከን አላዩም፤ ሊያዩም አይችሉም፤ ከስድብም አልፎ ወንጀል ሊለጥፍብኝ ሲከጅለውም አልታያቸውም፤ ወንጀልን በሰው ላይ መለጠፍ አላዋቂነት፣ ተንኮል፣ ውሸት ቢባል ስሕተቱ ምኑ ላይ ነው? እውነት ከማይከበርበት ቤት የወጡ ጭፍሮች እውነትን አላዩም ብሎ መውቀስ ባይቻልም አለማየታቸውን መናገር ግን ተገቢ ነው።
የአቶ ዳንኤል ጭፍሮች የመጽሐፉን ቁም-ነገር መጨበጥ ስላቃታቸው የሥነ-ምግባር ጉድለት የመሰላቸውን የመመጻደቅ ስብከት አወረዱት፤ ነገራቸው ሁሉ እንደ አህያ መልክ አንድ ዓይነት ነው፤ ራሳቸውን አፋፍ ላይ እኔን ደግሞ ገደል ውስጥ ጨምረው እንደናዳ ሊያወርዱብኝ ሞከሩ፤ ከጭፍሮቹ መሀል አንድም እንኳን እሱም ራሱ ሆነ ጓደኞቹ የጻፉት የምግባረብልሹነት መግለጫና ማረጋገጫ መሆኑን የመገንዘብ ችሎታ ያለው አልተገኘም፤ በነዚህ ጭፍሮች የማሰብ ችሎታ እውነት መናገርን እንደስድብ ከመውሰዳቸው በላይ እነሱ ግን ለመሳደብ ልዩ ፈቃድ ያላቸውና የሥነምግባር ደረጃቸውም የተለየ ነው፤ እነሱ ሲሳደቡ የሥነምግባር ብልሽት አይታያቸውም! እውነትን በደረቅ ቋንቋ ከመስማት ይልቅ ውሸትንና ተንኮልን በለስላሳ ቋንቋ መስማት የሚበልጥባቸው ጭፍሮች አቶ ዳንኤል ለተናገረው ዓይኖቻቸውን ሸፍነው እኔ በሰጠሁት መልስ ላይ ማተኮራቸው ያጋደለ የሆዳምነት ሚዛናቸውን በገሀድ ያሳያል፤ ውሸት የተናገረን ውሸታም ማለት፣ ተንኮልን የሸረበን ተንኮለኛ ማለት ትክክል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእውነት የተራበ፣ ለእውቀት የተራበ ሆኖ ለብዙ ሺህ ዓመታት ባለህበት ሂድ ሲል የኖረው በእንደነዚህ ያሉ የእውነትና የእውቀት ጸር የሆኑ ጭፍሮች እየታገተ ነው።
ሳያውቁት የመክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ ዋናውን መልእክት በተግባር አሳዩ፤ እውነትንና እውቀትን (ሁለቱን መለየት አይቻልም፤ እውነትን የማይቀበል እውቀትን አያገኝም፤ እውቀትን የማይቀበል እውነትን አያገኝም፤) አርክሰው እነሱ ጨዋነት የሚሉትን አወጁ፤ አንዱ በማያሻማ መንገድ ገልጦታል፤ መስፍን ኃይለማርያም ነኝ የሚል እንዲህ አለ፤ ‹‹ከእርስዎ ምሁራዊ ስድብ የዳንኤል ክብረት ጨዋዊ መሃይምነት በእጅጉ ይሻላል፡፡›› ይህ ሰው እሱና ጓደኞቹ በያዙት ሚዛን ‹‹ስድብ›› ያሉትን ተቀብሎ ከመታረምና ወደእውነትና ወደእውቀት መንገድ ከመግባት ይልቅ ‹‹ጨዋዊ መሃይምነትን›› መርጦ ለመኖር መወሰኑ ያሳዝናል፤ የዳንኤል ክብረትን አስመሳይነት፣ ደፋርነት፣ አላዋቂነትና ተንኮል በማያሻማ ቋንቋ ለመግለጥ የወሰንሁት በእንደዚህ ያሉ ምስኪን ‹‹ጨዋዊ መሃይሞች›› ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ገምቼ ልከላከልላቸው ብዬ ነበር፤ ተመችቶናል ስላሉ እግዚአብሔር ያውጣቸው፤ ሌሎች ሕመሙ እንዳይጋባባቸው ይጠንቀቁ!

በመጨረሻ በእውቀት ጉዞ ይሉኝታ፣ መግደርደር፣ መሸፋፈን፣ ማድበስበስ፣ መቀላመድ፣ የተጠሉና የእውቀት ጸር በመሆን የሚፈረጁ ዝንባሌዎች ናቸው፤ ሀ ማለት ሁለት ነው፤ ለማለት ሦስት ነው፤ ከተባለ ሀ+ለ አራት ነው ሲል የተጻፈውን አላነበብህም፤ ወይም አልገባህም፤ ስለዚህም መልስህ ልክ አይደለህም ማለት መማር ለፈለገ ነውር አይደለም፤ እውነትንና እውቀትን ለማራመድ መንገዱ ይህ ነው፤ የተገነዘበው ይራመዳል፤ እውነትን የሚፈራው ወደኋላ ይቀራል፤ መክሸፍ ማለት እንዲህ ነው።

28 comments:

 1. በእውነት ደስ ይላል፡፡ ዕድሜ ይስጥልን፡፡ ፕሮፌሰር ከዚህ የበለጠ የሚጽፉበት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ በስተርጅና ዲቁና እንዲሉ በስተርጅና ዲያቆን የተባለውን ሰው እንዲህ ማረም፣ በሁለት ኮፊያ የሚንቀሳቀስን ሰው አድራሻ መስጠት ተገቢ ነው፡፡ መምህር ኤስድሮስ እንዳሉት ከመሃይም አትጣላ ደጋፊው ብዙ ስለሆነ ያሸንፍሃል የተባለው ይኸው ደረሰ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንስ በጀሌዎቹ መናፍቃን ብሎ ከፈረጃቸውና ይወገዙልን ብሎ ካቀረባቸው ሰዎች መካከል አንዱ እኒህ ፕሮፌሰር አይደሉምን? የማኅበሩን ዓላማ ነው ያንጸባረቀው፡፡ አገራችን ግን በእነዚህ ጥራዝ ነጠቆች፣ ራሳቸውን በቀቡ ሊቃውንት መሳዮች መወረሯ ያሳዝናል፡፡ አለመማር ኃጢአት አይደለም፡፡ ደንቁርናን ዕውቀት ብሎ መኖር ግን ምንኛ ያሳዝናል፡፡ ወገኔ ፍረደኝ፡፡ ዛሬ እንኳ እውነት እንነጋገር እውነት ብንነጋገር የሚመለስ ብዙ ቁጣ አለ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ትክክል

   Delete
  2. እውነት ነው። ፕሮፌሰሩእንዳሉት ሰው ያለው ነገር ወይም ያለበት ደረጃ ሲነገረው የማይቀበል ከሆነ የሚጣላው ከራሱ እንጂ ከማን ጋር ይሆናል?

   Delete
  3. እውነት ነው ፕሮፌሰር ቃለ ህይወት ያሰማልን። የምሁር አባት ትልቁ ኃላፊነት የእውቀት ጨቅላ ልጆቹን እያመማቸውም ቢሆን ገርፎ ማስተካከልነውና።

   Delete
  4. It is very True, I like It. Legebaw hulu mastewalen seteual. Endante yale 10 sewoch ankuan binoru, abet endeat tiru neber? Let us make a different in peoples life, to be posetive like above. God bless you.

   Delete
  5. አሳቤን ስለተባበራችሁ እውነትን ለመፍረድ ስለጨከናችሁ አመሰግናለሁ፡፡ የማንም ክብር ቢነካ አልሻም፡፡ እውነት ግን እውነት በመባሉ ደስ ይለኛል፡፡ ፕሮፌሰር በውሸትና በአረመኔነት የተቀመመውን ታሪካችንን ፍርጥ አድርገው ከተገሩን ከእኛ ከካህናት ደግሞ ንስሐን መስበክ ይገባል፡፡ በአህያ ቆዳ የተሠራ ቤት ጅብ የጮኸ ዕለት ይፈርሳል እንዲሉ በሐሰት የደረትነውን ታሪካችንን ትተን ነጻ የሚያወጣውን እውነት እንያዝ፡፡ አገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል እንዲሉ ማኅበረ ቅዱሳን የአገር ማርጀት ምልክት ነው፡፡ እግዚአብሔር በእነርሱ የሚሠራውን ክፉ ገስጾ ወንድሞቻችንን ገንዘብ ያድርግልን፡፡ ዓለም ኃላፊ ነውና እባካችሁ እናንተ ልጆች በጭካኔ የሃይማኖት ካባ በደረበ አረመኔነት እስከ መቼ ለዚህ አገርና ቤተ ክርስቲያን የቤት ሥራ ትሆናላችሁ? በወጣትነት ያኔ ተሳሳታችሁ ዛሬም በጎልማሳነት ለምን ትበድላላችሁ? ክርስቶስ የሞተለትን ለምን እንዲህ ታሳድዳላችሁ? የበደለ ካለም እናስተምር ማለት ሲገባ እናባር ለምን ትላላችሁ? ሰላም እንደሌላችሁ እርግጠኛ ነን፡፡ ንስሐ ግቡ....

   Delete
 2. Thank you professor, the majority of the reader understood you. Please forget this cynical person, he is know by his copycat, all his articles copy and paste. God Bless You Professor.

  ReplyDelete
 3. እምቢ ብሎ ከቤታችን ካልወጣ፣
  ምን አለ ታድያ ለማቅ ስም ብናወጣ፣
  ለሞሶሎኒ የልጅ ልጅ፣
  ለዚህ ሸለታም የድንገት ምጥ ውራጅ።
  ወገኑን በድንጋይ ደብዳቢ፣
  እውር ፈረስ ጋላቢ፣
  ትልቅ ትንሹን ተሳዳቢ፣
  የዳቢሎስ አጃቢ፣
  ማቅ ማጂራት መችው ሰድቦ ለሰዳቢ፣
  ባለ ውቃቢ ነው ድቤ ደብዳቢ፣
  ስድ አደግ የእናት አባቱን ገበና ገላቢ።

  ReplyDelete
 4. fire alba profesor
  madeg yalchalnew leka endersewo aynet profeseroch eyastemarun new. areju ende? erjina bicha ayimeslegnm Jaju? min ale arfew yetetala biastarku. ayimognu yih tiwld yersewon yahl fidel baykotirm ahun sasbew kersewo yetshal yigebawal. min waga alew bersewo emnet lelaw ayigebawum. YAsaznal! yesew mecheresha!!

  ReplyDelete
 5. ፕሮፌሰር በቃዎት:: ጊዜው ያለፈበትና በዘመን ያረጀ አስተሳሰብን አንፈልግም:: የእናንተ ትውልድ ከአስተሳሰቡ ጋር አርጅትዋል:: እኛ አዲስ ትውልድ ነን:: በመሰለን የመራመድ መብት አለን::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ታላቅህን አክብር። እናት አባቱን የሰደበ ሽማግሌን የነቀፈ እሱ ይሙት ብሎ በመጽሐፉ ተፈርዶበታል። እሄም የድሮ ነው ካልክ ይህ መድረክ ያንተ አይደለም፤ እናም አይመለከትህም፣ ዉጣ። ደግሞም ሽማግሌን ጠይቁ ስለሚል ማቆች ደግሞ ይህን ስለካዳችሁ ዉጡ። ሃይማኖቱንም አገሩንም ዘርምንም ለማጥፋት እየደከማችሁ ነው።

   Delete
 6. አይ የናንተ ነገር ዳንኤል፥ ማቅ ሲባል ስማቸው ሲነሳ ምንም ነገር ለማገናዘብ እድሉን እንኳ ሳታገኙ ዘው ብላችሁ ትነከራላችሁ። እናንተ ማለት ልክ የበሬ ወንድ ፍሬው ከአሁን አሁን ወደቀልኝ እያለ ለሃጩን እያዝረበረበ እንደሚከተል ውሻ ናችሁ። የሚወድቅ ፍሬ የለም። ትናንት እኮ የስም ማጥፋታችሁ አካል አንዱ የሚያጠነጥነው ማቅና ፕሮፍ መስፍን ላይ ነበር። በዛ የምርቃና ፅሁፋችሁ አቡነ መስፍን ያላችኋቸው መስፍን ዛሬ ዳንኤል ስለ ተቻቸው የፃፉትን ስድብ ስታገኙ ምራቅ ባፋችሁ ሞላ እና አቡንነታቸውን ረሳችሁት። ትናንት ማቅን አቋቋሙ ያላችሁትን አውቃችሁ ዘነጋችኋት። እኛ አንረሳም። እናንተ ዛሬም የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ ናችሁ። ሁሉንም ያገኛችሁትን ጭቃ ሁሉ እየወረወራችሁ ነው። እስካሁን የወረወራችሁት አልተሳካምና አሁንም ከመወርወር ወደኋላ አትሉም። የወረወራችሁት ጭቃ እስከሚለጠፍ። አንድ ነገር እንዴት አንዴ ደጋፊ አንዴ ተቃዋሚ መልሶ ደጋፊ ከዛ ተቃዋሚ ማድረግ ይቻላል? ለናንተ ይቻላል። ምክንያቱም ጭቃ ውርወራ ላይ ናችሁና።

  ReplyDelete
 7. ደብተራ ስድብ ነው ወይስ ማዕረግ?

  ReplyDelete
 8. አሁንም ፕሮፌሰር ስድብ የሚቀናቸው በመሆኑ ከዚህ ሁኔታ ይታረሙ ቢባል እንኳ እድሜው ረዘም ያለ በመሆኑ በጣም አስቸጋሪ ነውና አይቶ ማለፉ መልካም ነው። የሆነ ሆኖ በአንዳንድ ጽሁፋቸው እርግጥ ብዙ ዘለፋ ይበዛዋል። የዲቁናውን ጉዳይ ሲያነሱ ለምን አቶ እንዳሉ ሲያብራሩ ዲያቆን ብሎ ወደ ላይ ከፍ ማለት እንጂ እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ ለኔ ግልጽ አይደለም ያሉት ዳንኤል ክብረት ወደ ላይ በክህነቱ ከፍ ማለት ምንም የሚያግደው የለም ከዛም ባለፈ የወንጌል ገበሬ ነው። እርስዎ ፕሮፌሰር ግን የተቀበሉትን የዲቁና መዓርግ በአግባቡ ተጠቅመው ወደ ትልቅ ደረጃ ባለማድረስዎ ተጠያቂነቱ በርስዎ ይብሳል። እርስዋ ያልሰጡትንም ሲመተ ክህነት እርስዎ ሊሽሩት መብት ስለሌለዎ ይህን ልብ ያድርጉ ስለሌላው ጉዳይ ምንም ቢሉ ስለማይመለክተኝ ብዙም ክብደት አልሰጠውም። ልበ ሰፊ ሆኖ መወያየትም ሆነ መተራረም ግን ከብዙ ስሕተት ያድናልና በዚህ ላይ በርቱ እላለሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወገኔ ፕሮፌሰሩ ዲያቆን ነኝ ብለው አታለው አያውቁም፡፡ ዳንኤል ግን ዲያቆንና አቶን እየለዋወጠ ስለሚጠቀም ነው፡፡ ዲያቆን የሕጻንነት ማዐርግ ነው፡፡ "በስተርጅና ዲቁና" እንዲሉ ከነተረቱ

   Delete
 9. I like to say thank you for professor Mesfin positive and educated comment. I proud you.Please keep continue to give us kind of this good assessment. We have alot fales writters on this planet and in our country too. we need more knowledgeable peoples like you to share us.
  we love you Professor...................
  G.

  ReplyDelete
 10. እኔ የሚገርመኝ አቡነ ማትያስ መሾማቸው አይደለም እንዲያውም ካሉት አባቶች በአቋም የተሻሉ ናቸው፡፡ በእን በኩል ምንጫው የእግዚአብሔር እጅ ያለበት ሌሎቹ ሊቃነ ጳጳሳት ትምህርት የሚማሩበትን መንገድ የሚያመቻች ነው፡፡ ምክንያቱም አቡነ ጳውሎስን ሁሉም ፈርቶ አባ ገነን ሆነው ቤተክርስቲያኗን ሲመዘብሩና ሲያስመዘብሩ ዝም ጭጪ ሲሉ እርሳቸው በሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ በአምባ ገነንነታቸው፣ በገንዘብ ብክነት፣ በሃይማኖታቸው ወዘተ ይናገሩ ይጣሉ የነበሩት እርሳቸውና እርሳቸው ብቻ ነበሩ፡፡ ይህም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ናቸው በእኔ አመለካከት ጀግና እላቸው ነበር፡፡ አሁን ካሉት ከዓላማቸው ፈሪ የሆኑ፣ ለምን ጳጳስ እንደሆኑ ዓላማቸውን ያልተረዱ፣ ግራና ቀኛቸውን ሳያውቁ የሚወዘወዙ፣ እንደ ቦይ ውሃ በነዷቸው የሚነዱ፣ ለደቂቃ ወጥ አቋም የሌላቸው፣ እንደ ሕጻን ልጅ በየደቂቃው የሚያኮርፉ፣ ሁሉ ጌዜ ብሶት የሚያወሩ ብቻ በተሰበሰቡበት ከእርሳቸው የተሻለ አለ ብየ አላምንም፡፡ ለዚህ ነው ዝም ብለው መርጠው ዝም ብለው የሾሙት፡፡
  እኔ የገረመኝ መሾማቸው ሳይሆን ለቤተክርስቲያን ጠበቃ ነኝ፣ ከእኔ በላይ ለአሳር፣ ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ የሚለው፣ ዘመናዊ አሥተዳደርና ለውጥ በቤተክርስቲያን አመጣለሁ ብሎ ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና የሚለው ሥውር የመንግሥት አሥተዳደርን በመደገፍ የመንግሥትን፣ የእነ ንቡረ እድ ኤልያስና የእነ አባ ሠረቀ ባለሟልና ተዋናይ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ሌላ ሊያስመርጥ ደፋ ቀና ሲል ከርሞ ከተሾሙ በኋላ ከዮድ አቢሲንያ ክትፎ ይዞ፣ አመራሩና አሥፈጻሚው ከሌላ ጊዜ ለየት ባለ አለባበስ ሔደው እንኳን ደስ ያለዎት በለዋል፡፡ ይገርማል ይኽ ሹመት ሳይሆን አገልግሎት፣ ሰማእትነት፣ አስተማሪነት፣ ሓላፊነት ስለሆነ መባል ያለበት ‹‹ያስችለዎት›› ነው እነርሱ ግን ሔድው እንኳን ደስ አለዎት አሉ ታዲያ ይህ አይገርምም ይገርማል፡፡ ‹‹በልጅነቱ የመነኮሰ ሰልሞ ይሞታል እንደሚባለው›› ማኅበሩ በትውልድ ተወቃሽ፣ በየዋሃንና በቅንነት ትክክለኛ ዓላማ ያለው መስሎአቸው ለሚከተሉት ኣባላቶቹ አስነዋሪ፣ በየዋኅነት ገንዘባቸውን ለሚሰጡ ምዕመናን አሳፋ ሥራ የፈጸመበት፣ እውነተኛ መሥሎ ሥውር ደባውን በቤተክርስቲያን ያሴረበት፣ የክፋትና የተንኮል እጁን የጫነበት ወቅት መሆኑ ትዝብትና ጥርጣሬ ውስጥ፣ ሃይማኖታዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ርምጃ የሚሔድበት መሆኑን ፍንትው አድርጎ አሳይቷል፡፡ ለመንግሥትም ታማኝ አገልጋይ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
  የእውነት አምላክ፣ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን አባቶቻችን ረድኤትና በረከት፣ በየገዳማቱ፣ በየአድባራቱ፣ በየጫካው፣ በየ ትምህርት ቤቱ ያሉ አባቶቻችን ጸሎት ቤተክርስቲያንን ምዕመናንን ይጠብቅልን አሜን፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ይፋረድልን፡፡
  ዛሬም ሆነ ወደፊት ቀጥተኛ የሃይማት አባት እግዚአብሔር እንዲሰጠን ገዳማት ውስጥ በዓት አጽንተው ለተቀመጡ አባቶች ማሳሰብ ነው፡፡

  ReplyDelete
 11. ፕሮፌሰሩ ምን እያስተማሩን ነው ? እርሳቸው የእውቀት ሁሉ የበላይ ፈጣሪ መሆናቸውን ካመኑ ለምን ወርደው ካንድ ''የማያውቅ ደንቆሮ ''ብለው ከናቁት ሰው ጋር ወርደው ተራ ስድብና አተካራ ገጠሙ? በዚህ ሁኔታ ማን ነው ወርዶ የሚታየው ? ማነውስ ከፍ ብሎ እንዲታይ የሆነው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከአለቃው የጭፍራው እንዳይሆንብን እስቲ የጻፉትን እናንብብ፡፡ ዛሬም መጽሐፍ በከቨር ማውገዝ አይበቃንም ወይ? ይህ እኮ የግንቦቱ የአውጋዦች ሲኖዶስ ጠባይ ነው? የቆላ ቄስ ይመስል ደርሶ ግዝት የመሃይም ሥራ ነው

   Delete
 12. Professor Mesfin is respected intellectual in Geography of Ethiopia, although he writes also on issue of politics and history. He is known to raise controversial issues and defends his thought arrogantly. He justifying his arrogance and polemics by saying he is defending the truth.

  What we are saying is you should be polite and modest when arguing with other people to sell your taught.

  ReplyDelete
 13. ለእኔ ለማስተማር መከጀላቸው ጨቅላነታቸውን ያሳያል፤

  ReplyDelete
 14. ፕሮፌሰር የሚለውን የትምህርት ደረጃ ማዕረግ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኜ የማውቀው የእርስዎን ስም በየሚዲያው ስሰማ ነበር፡፡ በተለይ በ80ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ይታተሙ በነበሩ መጽሔቶች እና ጋዜጦች ላይ ሃሳበዎን በድፍረት እና በትጋት ያካፍሉ ስለነበር ከእርስዎ ጋር የተደረጉ ቃለመጠይቆች እና የመሳሰሉትን ለማንበብ እድሉ ነበረኝ፡፡ የምስማማባቸውን ሃሳቦችዎንና አስተያየቶችዎን እንደማደንቅልዎት ሁሉ የማልስማማባቸውን አስተያየቶች እና ሃሳቦችዎንም ሳከብርልዎት ኖሬያለሁ፡፡ በጣት ከሚቆጠሩ የአደባባይ ሙሁራኖቻችን (ዳንኤል እንዳለው) አንዱ መሆንዎን ሁልጊዜም ቢሆን በአክብሮት አስታውሳለሁ፡፡
  የዚህ አስተያየት ምክንያት የሆነውን መጽሐፍዎን በሚገባ አንብቤዋለሁ (አላነበብከውም ! ደንቆሮ፣ ውሸታም… ካላሉኝ) መጽሐፍዎን በተመለከተ ዳንኤል ክብረት (ዲያቆን ያላልኩት እንደእርስዎ በመገበዝ ማእረጉ አይገባውም በሚል ሳይሆን እርሱም ከስሜ በፊት ማዕረጌን ቀጽላችሁ ካልጠራችሁኝ ብሎ ስላማያውቅ ነው) የሰነዘረውን አጭር አስተያየትም በደንብ አንብቤዋለሁ ! በእውነት አንብቤዋለሁ ! እርስዎ የተከበሩት ፕሮፌሰር ለዳንኤል የጻፉት መልስ ግን በእውነት እጅግ ጨዋነት የጎደለው፣ በተለይ ከእርሰዎ የማልጠብቀው ስለነበር ከልብ አዝኜብዎታለሁ፡፡ ስድብ የተቀላቀለበት በሰከነ አእምሮ ያልተጻፈ ብቻ ሳይሆን የእርስዎን አዋቂነት በዳንኤል አላዋቂነት ለማስመስከር የሚሞከረ ነበር የሚመስለው፡፡ (ዳንኤል እርስዎ እንዳዋረዱት አላዋቂ ነው ብዬ ብቀልቀበልልዎት )
  የአሁኑ ይባስ ! አሁን ደግሞ የጭቃ ጅራፍዎ ከዳንኤል ወደ የዋሃን አስተያየት ሰጪዎች ዞሮ ‹‹ ጭፍራዎች ›› ከሚል ቅጽል ጋር በጅምላ መናጆ ሆነው ተዋርደዋል፡፡ ምነው የተከበሩ ኣባቴ ! እንደው ትንሽ አልከበደዎትም ወይንስ ከስምዎ የቀደመው ማዕረግዎ እና ዕድሜዎ ከበደዎት እና ሰው ሁሉ ትንኝ መሰለብዎ ! አንድ ሰው ማዋረድ ፣ ማንኳሰስ ተገቢ አይደለም ብለው አስተያየት የሰጥዎትን ሁሉ ይግረማችሁ ብለው ‹‹የምን አንድ ሰው! እናንተስ ብትሆኑ›› ብለው በአንድ ሙቀጫ አስገብተው ወቀጧቸው !
  ከተሳሳትኩ እታረማለሁ እድሜዎ 82 ዓመት አካባቢ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ እድሜ ሲደረስ ትልቁ ዳቦ ሊጥ ይሆናል እንዴ ! ‹‹ካረጁ አይበጁ›› የሚለው የቆየው የማኅበረሰባችን ተረት በእርስዎ በኣባቴ እንዳይደርስብዎት እመኛለሁ ! የእኔ አዲወሱ ትውልድ (ዕድሜዬ 35 ነው) ከእናንተ ከአባቶቻችን ዘለፋን፣ ማዋረድን .. ሳይሆን ሃሳብን በሃሳብ መሞገትን፣ ሰውን ሁሉ ከነልዩነቱ ማክበርን፣ በሰከነ ሁኔታመነጋገርን መማር እንፈልጋለን፡፡ የምታስተምሩን ነገር ከሌላችሁ ግን የእስልምናው ቅዱስ ቁራን እንደሚለው ‹‹ ደግ ነገር መናገር ካቻልክ ዝም በል››

  ReplyDelete
  Replies
  1. You smell like Daniel Kibret. Probably you are daniel. Don't get mad when you are told the truth not the fiction by the Professor Mesfin W/Mariam. Try to face the truth!! Peolple like you will never learn from mistakes. Go for it.

   Delete
 15. እውቀትና እውነት አይገኙም እንጂ ቢገኙ እንዴት መልካም ነበር፤
  ጲላጦስም ጠይቆ መልስ አላገኘም መልስ ቢገኝ ማቅና ሌላውም አፋቸውን ይይዙ ነበር
  ዳሩ ግን ምን ይደረግ!

  ReplyDelete
 16. የዕውቀትና የዕውነት ስንኳን ፊታቸው ኋላቸው አልታየም፤ ሙሴ ብቻ ለመረዳት ሙከራ አደረገ
  በድግዝግዝታ ተላልፈውለታል እናም ኋላን እንጂ ፊትን አላየም፤ስለሆነም የዘመናችን ተፈላሳፊዎች እንደ
  ወፍጮ መጅ በስተኋላ(ሆድና ጀርባ)ሆኖ በነገር አካሄድ አንዱ ሌላውን መከካት መገርደፍ መሠለቅና
  ማድቀቅ ካልሆነ በስተቀር ዕውነት+ዕውቀትና ሰውና ሰው ሆድና ጀርባ ናቸው። ቅንነትና መቻቻል ግን
  ሰምና ወርቅ ነበሩ በማን ይተግበሩ ሁሉም ተገዳደሩ!

  ReplyDelete
 17. professer u are right ewerferse galabe they do not need to read,I read many of professor article they are good according to my knowledge these who are hodam, banda they can not see,small minds discuss people....

  ReplyDelete
 18. Have you read Daniel's ' Mist Efeligalehu Article' and Judy Brady’s famous Essay “I Want a Wife.”? Then you know him.

  ReplyDelete