Tuesday, April 9, 2013

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 13

«የእውነት ቃል አገልግሎት» ላይ የግንቦቱ (ግንቦት 15/2004 ዓ/ም) ሲኖዶስ ቃለ ጉባኤው ያሰፈራቸውና «ኑፋቄ» ብሎ ካቀረባቸው ነጥቦች መካከል ቀጣዮቹን ነጥቦች መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርገን ኑፋቄ የተባሉት ነጥቦች ኑፋቄ መሆን አለመሆናቸውን እንመረምራለን።

 

«ሐ. የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ (ሥልጣነ ክህነት) ለጴጥሮስ ብቻ እና ለተወሰኑት ተተኪ ነን ባዮች የተሰጠ አይደለም» በማለት ከሐዋርያት ሲያያዝ የመጣውን የቤተክርስቲያናችንን ሥልጣነ ክህነት በመቃወም ጽፏል፡፡ የእውነት ቃል መጽሔት ሰኔ 2003 ዓ.ም እትም  ገጽ 11»

«መ. ለጴጥሮስ የተሰጠው የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ ሥልጣነ ክህነት አይደለም፡፡ በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፡፡ በምድር የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሆናል የሚለው ሀይለ ቃል ኃጢአትን እንደሚያስተሰርይ አያሳይም በማለት ጽፏል፡፡  እውነት ቃል መጽሔት ሰኔ 1993 እትም ገጽ 13»

ቤተክርስቲያናችን የእግዚአብሔርን ቃል ለራሷ በሚመቻት መንገድ በመተርጎም ከምትጠቀምባቸው ጥቅሶች መካከል ከላይ የተጠቀሱትና እንደ ብሉይ ኪዳን ሁሉ በአዲስ ኪዳን ለተወሰኑ ሰዎች ክህነት ተሰጥቷል የሚለው ይገኝበታል፡፡ በፊደል «ሐ» የተጠቀሰው ከእውነት ቃል መጽሔት ላይ ሙሉ በሙሉ የተጠቀሰ አይመስልም፡፡ የሚፈለገው ክፍል ብቻ ተቆርጦ የወጣ ነው የሚመስለው፡፡ ይሁንና በቀረበው ላይ ተመስርተን ጉዳዩን ስንመረምረው ለጴጥሮስ የተሰጠው የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ ስልጣነ ክህነት ነው ወይ? በፍጹም አይደለም፡፡
 
በአዲስ ኪዳን ያለው አንድ ሊቀካህናት ብቻ ሲሆን በእርሱ ሥራ የጸደቁ ምእመናን ሁሉ ደግሞ ካህናት ናቸው፡፡ ይህን የአዲስ ኪዳን ትምህርት ወደጎን ትቶ ስልጣነ ክህነት የተሰጣቸው የተወሰኑ ሰዎች ናቸው ብሎ ማሰብ የኋሊት ወደ ኦሪት ስርአት መመለስ ነው የሚሆነው፡፡

ኢየሱስ ስለእርሱ ማንነት በጠየቀ ጊዜ ጴጥሮስ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ መመለሱን ተከትሎ «ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።» (ማቴ 16፡17-19)፡፡ ይህ በምንም መንገድ ስልጣነ ክህነት የሚል ስያሜ የሚሰጠው አይደለም፡፡ ስልጣነ ክህነት ለማለት የሚያስችል ምክንያትም የለም፡፡ «የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።» የሚለው ምንም እንኳ በዚህ ስፍራ ለጴጥሮስ የተነገረ ቢሆንም በምዕራፍ 18 ላይ ግን አንዱ ሌላውን ቢበድል በመጀመሪያ ለብቻው እንዲወቅሰው፣ እርሱን ካልሰማው በምስክር ፊት እንዲወቅሰው፣ በምስክሮች ፊት እንቢ ካለ ግን ለቤተ ክርስቲያን እንዲነግራት፣ ቤተ ክርስቲያንን አልሰማ ካለ ግን ያ ሰው እንደ ቀራጭና አረመኔ እንዲቆጠርና ከቤተክርስቲያን እንዲለይ ጌታ አስተምሯል፡፡

ከዚያም «እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።» (ማቴ 18፡18) በማለት ለጴጥሮስ የተናገረውን ለቤተ ክርስቲያን ሰጥቶ እናገኛለን፡፡ ይህም የሚያሳየው ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ያለች የእግዚአብሔር መንግስት ወኪል በመሆኗ እርሷ ከላይ የተጠቀሰውን አይነት ጉዳይ ይዛ በትክክለኛው መንገድ ያሳለፈችውን ውሳኔ መቀበል እንደሚገባ ነው፡፡ አልቀበል የሚል አካል ቢኖር ቤተክርስቲያን በምድር ብታስረው (ብታወግዘው ወይም ብትለየው) በሰማይ የተወገዘ ይሆናል፤ ብትፈታው ደግሞ የተፈታ ይሆናል የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠው፡፡ ታዲያ ለቤተክርስቲያን የተሰጠ የማሰር የመፍታት ስልጣን ለተወሰኑ ሰዎች የተሰጠ  ስልጣነ ክህነት ነው ማለት እንዴት ትክክለኛ ነገር ይሆናል፡፡ ይህ አተረጓጎም ሊበሏት የፈለጓትን ጅግራ ዶሮ ናት እንደማለት ይቆጠራል፡፡

ስልጣኑ ለቤተክርስቲያን ተሰጠ ሲባልም ጉዳዩ ተግባራዊ የሚሆነው በቤተክርስቲያን መሪዎች በኩል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህ ግን የእኛ ቄሶች ኃጢአትን እንዲናዝዙ ስልጣን ባይሰጣቸውም ሀጢአትን ሳይናዝዙ መስቀል ባሳለሙ ቁጥር ያልታሰረውን ሰው ሁሉ «እግዚአብሔር ይፍታህ» የሚሉትን በጭራሽ አያሳይም፡፡ ስለዚህ ጉዳይም የተነገረ አይደለም፡፡ እስኪ በየትኛው ክፍል ነው በዚህ ስልጣን ሐዋርያት ኃጢአትን ያስተሰረዩት? ስለዚህ ማሰርና መፍታትን ኃጢአትን ከመናዘዝና ከማስተስረይ ጋር ማያያዝ ስህተት ነው፡፡

የአዲስ ኪዳን ካህናት ምእመናን ሁሉ ናቸው፡፡ «እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤» 1ጴጥ 2፡9
«ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።» ራእ. 1፡5-6

ከእነርሱ መካከል ደግሞ ለቤተክርስቲያን መሪነት የተሾሙ አሉ፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሹመት ክህነት ተብሎ እነርሱም ካህናት ተብለው በአንድም ስፍራ አልተጠሩም፡፡ ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ወዘተ ተብለው ነው የተጠሩት፡፡ ይህን ከክህነት ጋር በማያያዝ ስልጣነ ክህነት ማለት መሰረት የለውም፡፡  ስለዚህ ዘመናት ያስቆጠረውን የተሳሳተ ትምህርት በእግዚአብሔር ቃል ማረም እንጂ እውነትን ማውገዝ ከሲኖዶስ አይጠበቅም፡፡

ይቀጥላል

25 comments:

 1. minm ayasaminim. Ewunet mels teftobachihual.

  ReplyDelete
  Replies
  1. endante aynetu be chefin lemigwazew, minim neger bihon ayasaminim

   Delete
 2. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ፤ አሜን ፡፡

  ካህን የሚለውን ቃል ዲያቆን ፣ ቄስ ፣ ደብተራ ፣ በቤተ ክሲያን የአምላክ አገልጋይ ፣ አምላክን የሚቀድስ ፣ የሚያወድስ የሚዘምር ፤ ሳታት ቋሚ ፣ አወዳሽ ፣ ቀዳሽ በማለት ደስታ ተክለወልድ ተርጉመውታል ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትም ደግሞ “በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሆኖ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ሰው ይለዋል፡፡ የአገልግሎታቸውንም ዓይነት ሲገልጽ መሥዋዕትን በመሠዋትና ጸሎትን በመጸለይ ይፈጽማል ፡፡” ይላል ፡፡

  በብሉይ ኪዳን ሥርዓት አሮንና ተከታዮቹ የኰርማና ሙክት መስዋዕትን ደም እየረጩ ኃጢአትን ሲያስተሠርዩ ነበር ፡፡ በሐዲስ ኪዳን ዘመን ግን ኢየሱስ ዘለዓለማዊ መስዋዕታችን ሆኖ ስለቀረበ ፣ ኃጢአትን በሙክት ደም የማስወገድ ሥርዓት ተሽሯል ፡፡ ጸሎትና ምልጃን የማድረሱ ግልጋሎት ፣ እግዚአብሔርን የማመስገኑና የመለመኑ ፣ ሰዎችን የማስተማሩና በሥርዓት የመምራቱ ደንብ ግን በሐዲስም ስላልተቋረጠ የካህናት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ አላበቃም ፡፡

  ሐዋርያው በሥጋና በደም ጥበብ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነት የተረዳውን በመመስከሩ ፣ ከሰዎች መሃል እግዚአብሔር ለአገልገሎት የሚፈልጋቸውና የሚረዳቸው ሰዎች እንዳሉ የሚያስተምረን ቃል ነው የተነገረው ፡፡ ይህን በመመልከቱም ጌታችን ሥልጣነ ክህነቱን ፣ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል፤” (ማቴ 16፡17-19) በማለት መረጠውና ሹመቱን አበሠረው ፡፡ ካቶሊኮች ይኸን የተሰጠ ሥልጣን ምድራዊ አፈርና ድንጋይ በሚል ትርጉም ፣ በጴጥሮስ አጽም ላይ ቤተ ክርስቲያን አንጸው ፣ ክርስቶስ የፈቀዳት ቤተ ክርስቲያን ይህችኛዋ ብቻ ናት ፤ ጳጳሳቸውንም የክርስቶስ ብቸኛ ምድራዊ ወኪል ፣ አድራጊና ፈጣሪ በማለት ከቃሉ ውጭ ይኩራሩበታል ፡፡

  ከተጠቀሰው የሥልጣነ ክህነት ቃል በተጨማሪ ፣ ጌታችን ይህንኑ የሰጠውን የኃላፊነት ድርሻ ለሐዋርያው ሲያጠናክርለት “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው። ደግሞ ሁለተኛ። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው። ሦስተኛ ጊዜ። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። ሦስተኛ። ትወደኛለህን? ስላለው ጴጥሮስ አዘነና። ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ኢየሱስም። በጎቼን አሰማራ፤” ዮሐ 22፡15-17 በማለት ምእመናንንም እንደየፈርጃቸው በአደራ ተሰጥቶት ተቀብሏል ።

  አሁንም በመጨመር ካህናት በዚህ ምድር የማሰርና የመፍታት ቃልን ብቻ ሳይሆን በሚመጣው ዓለምም እንኳን ያላቸውን ሥልጣን “እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ ፤” ማቴ 19፡28 በማለት አስረድቷቸዋል ፡፡ ጳውሎስም “በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን?” 1 ቆሮ 6፡3 ይለናል ፡፡


  የኘሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ደግሞ በደረቅ ቋንቋ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ነው ፣ ካህናት የምንባለውም እኛ ምእመናን ነን በሚል የተሳሳተ ትርጉም ተመርተው ፣ አንዳንዶች ለምሣሌነት የሚያዘጋጁትን ኩኪስ (ስጋወ ደሙ በማለት) እንኳን ሳይቀር እንደ አይሁዳውያን የገበታ ቂጣ በነፍስ ወከፍ እየተቧጨቁ እንደሚካፈሉ ሰምቻለሁ ፡፡ የበላይና የበታች የሚልን ደረጃ ሽረው ሁሎችም ባራኪና ቀዳሽ ፤ ፈዋሽና ተርጓሚ በመሆን ስህተትን በየራስ ተዳርሰውታል ፡፡

  እንደ መጽሐፍ ቃል ከሆነ ግን ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ነው (ዕብ 4፡14-15) የምንለው መስዋዕቱና መስዋዕት አቅራቢው ለዘላለም የማይሻር ፣ የማይለወጥ ካህን ሁኖ (ዕብ 6፡2ዐ) በመቅረቡ ነው እንጅ ፣ ዛሬም በእኛ መካከል እየተዘዋወረ በመስቀል ላይ ስለተሰዋው ልጅህ ስትል ማረን እያለ ጸሎታችንን ሊመራልን አይደለም ፤ ጸሎታችንን ተቀባዩ አንዱ ርሱ ነውና ፡፡ ስለሆነም ይህነን ጊዜያዊ ምድራዊ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲያስፈጽሙ ሥልጣነ ክህነት በሐዋርያው በኩል በመስጠቱ ፣ ርሱን ወክለው ልመናና ምልጃን ከምእመናን ጋር እንዲያቀርቡ ፣ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶችንም በአግባቡ እንዲፈጽሙና እንዲያስፈጽሙ ፣ ሕዝብን እንዲያስተምሩ ፣ እንዲገስጹ ሥልጣን ሰጥቷል ፡፡

  እኛ ምእመናን ካህናት ስንባልም በስጋና በውሃ ስለተወለድን ሳይሆን ፣ በክርስቶስ አምነን ለሌላ ወገን መስክረን ስናስተምርና አንዲትም ብትሆን የጠፋች ነፍስን የማትረፍ ሥራ ስንሠራ ወይም ራሳችንን እግዚአብሔርን ደስ እንደሚያሰኝ ቅዱስ መሥዋዕት አድርገን በሙሉ ልባችን ማቅረብ ስንችል ብቻ ነው (1 ጴጥ 2፡9 ፤ ዕብ 13፡15 ፤ 1 ጴጥ 2፡5) ፡፡ ሙሴን ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ እንዳለው ዓይነት /ዘጸ 7፡1/ ፤ ባይገባንም ፣ ምእመናን የምንሰጠው ሹመት ለማለት ፡፡

  በተረፈ ጸሐፊው በመቀጠል የራሳቸውን መልዕክት ሲያርቁት ወይም ሲያስተካከሉት “ከዚያም «እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።» (ማቴ 18፡18) በማለት ለጴጥሮስ የተናገረውን ለቤተ ክርስቲያን ሰጥቶ እናገኛለን”፡፡ ይህን አባባል እውን ብለን ብንቀበል እንኳን ፣ በዚህ አገባብ ቤተ ክርስቲያንም ማለት ጣራና ግድግዳ አለመሆኑን ራሳቸው “ጉዳዩ ተግባራዊ የሚሆነው በቤተክርስቲያን መሪዎች በኩል” ነው በማለት አብራርተውታል ፡፡ ታድያ እኛስ እንደ መጽሐፍ ቃል ካህናት ያስራሉ ፤ ይፈታሉ ፤ በማለት ቀሳውስቱንና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ናቸው በማለታችን ለየት ያለ ትርጉም ለመስጠት ዛሬ ለምን አስፈልጓል ?

  ወስብሐት እግዚአብሔር

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምእመን እንደምን አለህ እግዚአብሔር ይምስገን እኔ ደህና ነኝ::ውድ ወንድም አንድ በጣም ወስጤ ያስጬነቃት ጥያቄ አለኝና አባካችሁ እባክህ እግዚአብሔር በገለጽልህ መጠን ገላግለኝ እላለሁ::ወድ ወንድም በዚህ መልኩ ጥያቄ መጠየቅ ትክክለኛ አካሄድ እንዳልሆነ አዉቃለሁ ነገር ግን ያለሁበትም ቦታ አባቶችን ማግኜት ስለማያስችለኝ ነዉና ከታላቅ ይቅርታ ጋር ሃሳብህን አካፍለኝ ወንድም::

   1/በመጽሃፍ እየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ብዙ ቦታ ተጽፋል::ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ መባልና እግዚአብሔር ነው ማለት የተለያዩ ናቸዉ የሚሉት የተካራካሪዎች ሃሳብ ውድቅ ይሆን ዘንድ እንድትመልሱልኝ ይሁን::
   2/ስለ ክርስቶስ አምላክነትም እንዲሁ በዚያው በመጠኑ ብትጽፉልኝ ደስ ይለኝማል::አምሰግናለሁ ወንድም!!! እንዲሁም ለአባሰላምዎች ጥያቄዬን በማድረሳችሁ አመሰግናለሁ::

   Delete
  2. ቃለህይወት ያሰማልኝ ማለቴን በመርሳቴ ይቅርታ ይደረግልኝ::ለዚህ ድንቅ የሆነ ት/ት እግዚአብሔር ይስጥልን!!!

   Delete
  3. ሰላመ እግዚአብሔር ለሁላችንም ይብዛልን ፡፡ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ ፡፡

   ወንድሜ ማንነቴን በመለያ ስሜ ያስታወቅሁ ስለሆነ እንደ ልቤ ሃሳቤን እገልጻለሁ ፡፡ እንዲያ ማድረጌ ደግሞ ስህተት ስፈጽም ቢያገኙ ሊቃውንቱ ደፍረው እንዲያስተምሩኝ በመፈለግ ነው ፡፡ እንዲያ ዓይነቱ ሰውም እስከሚገኝ መጽሐፍትን በግሌ በማንበብ ፣ አቅሜ የሚችለውን ያህል እታገላለሁ ፡፡ ሞኝና መሃይም ምንም አይፈራምና እንደሚሉት ቢጤ ፣ በንባብ ካገኘሁት በመነሳት ነው በድፍረት አስተያየቴን የምሰጠው እንጅ ፣ በሥርዓቱ ተምሬና ተክኜበት አይደለም ፡፡ እንደ ከብት በነዱኝ እንዳልሄድና መቀላቀል እንዳይመጣብኝ ግን ፣ ሃይማኖቴን በሥርዓቱ ለመረዳት ዘወትር የሁሎችንም በመፈተሽ ለመማር እጥራለሁ ፡፡ ስለዚህ ማስተማሩና ማስረዳቱም ቢሆን ከአቅሜ አኳያ የኔ ችሎታና ሥራ አይደለም ማለት ነው ፡፡ ቢሆንም በሥርዓቱ የሚያስተምረን ሰው እስከምናገኝ ድረስ ያለኝን ግንዛቤ ስለጥያቄህ በአጭሩ ለማካፈል እሞክራለሁ ፡፡ በተረፈ እግዚአብሔር በጐደለው ስለሚሞላበት በግሌ ብዙ አልጨነቅም ፡፡

   1. በቅድሚያ የአምላክን የልጅነትንና የአባትነት ነገር ለመረዳት ከሰውኛ ቋንቋና አስተሳሰብ መውጣት ያስፈልገናል ፡፡ ምክንያቱም ፈጣሪአችንን በሰው ልክ ፣ በሰው ልማድና ህግ መመዘኑና መተርጐሙ ስህተት ስለሚያመጣብን ነው፡፡ ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነው ስንል ከተዋሕዶ በኋላ እንጅ እምቅድመ ዓለም በነበረው አገኛኘቱ አይደለም ፡፡ ስለዚህም ጥያቄህን ለመመለስ ወልድን በሰውነቱ አንመዝነውም ማለት ነው ፡፡

   እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን አንድ አምላክ ብለን እናምናለን ፤ በስም ደግሞ አብ ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ እንላለን ፡፡ በስም እንዲህ ሦስት ያልናቸውን አሁንም በአካል ፣ በግብርና በኩነትም ሦስት ናቸው እንላለን ፡፡ ቀጥለንም የወልድና የመንፈስ ቅዱስ መገኛቸው አብ ነው ፤ በግብራቸው ደግሞ አብ ወልድን ይወልዳል ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰርጻል ፡፡ ወልድም ከአብ ይወለዳል (ይገኛል) ፤ መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ከአብ ይሰርጻልና ሠራፂ (የወጣ) ይባላል ፡፡

   ልብ ብለህ ቃሉን ከተመለከትከው በቅድሚያ መገኛ ያልነውን ፣ ግብራቸውን በየራሳቸው ስንከፋፍል መውለድና ማስረጽ ፣ መወለድና ሠራፂ በሚል ቃላት ተካናቸው ፡፡ ይህም ማለት ተወለደ ስንል በሰውኛ ቋንቋ ሳይሆን ከአብ ዘንድ (ጋር) ተገኘ ማለታችን ነው ፡፡ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ከአብ ተለይተው ያልነበሩበትና የማይኖሩበት ዘመን ስለሌለ ፣ አብ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ወልድም አለ ማለት ነው ፤ መንፈስ ቅዱስም እንደዚሁ (ለማስረዳት ቃልን አስገባሁ እንጅ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ነበር በዚያኛው ዘመን አይባልም ፤ ቅድመ ዓለም የነበረው ፣ ዓለምን አሳልፎ ለዘለዓለም ይኖራልና ፡፡ መግለጫዬ በጊዜ አለመቀዳደማቸውን ብቻ ለማስረዳት ነው )፡፡ ይህ አለመቀዳደም ደግሞ እኩልነታቸውን ያመለክታል ፡፡ በማስገኘትና በመገኘት ምክንያት አንዱ ከአንዱ አልቀደመም ፤ አንደኛውም ከሌላው አልበለጠም ፡፡ ሦስቱም ትክክል ናቸው ፡፡

   ሌላው ማስተዋል ያለብን ፣ ወልድን የእግዚአብሔር ልጅ ነው ስንል ግብሩን ፣ የመወለድ ወይም የመገኘት ባህርዩን ለማመልከት እንጅ ፣ እንደ ሰው ልማድ እንደ ህጻን አንሶ ፣ አብ እየታቀፈ አሳድጐታል ማለታችን አይደለም ፡፡ ልጅነቱን አብ ልጄ በማለት መስክሮለታል (በማቴ 3፡17 ፣ 17፡5) ፡፡ ምድራዊ አስረጅ ደግሞ መጥምቁ ዮሐንስ ነውና (ዮሐ 1፡34)የእግዚአብሔር ልጅ ለማለት አናፍርም ፡፡

   2. ከላይ ያጐለዳደፍኩትን በመጠኑ መረዳት ከቻልክልኝ አሁንም እንደዛው እቀጥላለሁ ፡፡ አብን እግዚአብሔር ነው ካልን ፣ ከአብ የሚተካከልም እግዚአብሔር ብቻ ነው ፤ ስለዚህም ወልድም እግዚአብሔር ነው ፤ መንፈስ ቅዱስም እግዚብሔር ነው ማለታችን ነው ፡፡ አስረጃችን እግዚአብሔር ዓለምን በፈጠረበት ጊዜ ሁሉ ይጠቀም የነበረው ቃሉን መሆኑ ነው ፡፡ "እንዲህ ይሁን" ባለ ሰዓት ሁሉ ነገሮች ሆነዋል ፤ ያ ዓለምን የፈጠረበት ቃል ፣ ወልድ የምንለው ነው ፡፡ ዮሐንስም “ሁሉ በእርሱ ሆነ ፤ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም” በማለት የወልድን ፈጣሪነት ይገልጽልናል (ዮሐ 1፡3) ፡፡ ስለዚህም ወልድ ፈጣሪም ነውና አምላክ እንለዋለን ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም ይህንኑ በአጭር ቃል ሲገልጽ “ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ” (ዕብ 1፡2) ይለዋል ፡፡ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 2፡9 “የማይለይ ምክር ፣ እርሱ በአንዲት ፈቃድ ከአባቱ ጋር ሰማያትን ፈጠረ” ይላልና የፈጠረንን አምላካችን ማለታችን ትክክል ነው ፡፡ አብ ፣ ወልድና መንፈስ ቀዱስ በመለኰት ፤ በኃይል ፣ በሥልጣንና በፈቃድ አንድ ስለሆኑም ደግሞ አምላክ ያሰኛቸዋል ፡፡

   “ሰውም ቢሆን ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ፤ ሥጋዊ ልደትን ለመወለድ የመጣ ቀዳማዊ እርሱ ለመወለድ ከአዳም የተገኘ መዋቲ ሥጋን ነሣ (ገላ 4፡4)፡፡ ሰው የሆነው እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው ፡፡ አስቀድሞ በነቢያት የታወቀ በሐዋርያትም የተሰበከ (ዮሐ 1፡ 46 ፤ ሮሜ 9፡5 ፤ ሥራ 1፡8) ፡፡ ሰዎች ሁሉ የሚያምኑበት ፣ በእግዚአብሔር አብ ምስክርነት የተገለጠ ፤ ከመላእክት የተመሰገነ (/( 2፡13-14) ፡፡” ሃይማኖተ አበው 3፡15-16

   አምላክነቱን የሚገልጽ በጣም አጭሩ መልስ ያለው ደግሞ በዮሐንስ ወንጌል 1፡1 ላይ የተጠቀሰው ነው ፡፡ “በመጀመሪያ ቃል ነበረ ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ፡፡” በማለት አስተካክሎ ወልድ አምላክ ወይም እግዚአብሔር እንደሆነ ይገልጠዋልና ነው ፡፡

   በተረፈ ሰፊውን ትምህርት ፣ ምሥጢረ ሥላሴ በሚል ርዕስ የተዘጋጁ ጽሁፎችን ባገኘህበት ሁሉ ብታነብ ከኔ የተሻለ ያስረዱሃል ፡፡ ያበላሸሁትንም ያቀኑልሃል ፡፡

   ለምሣሌ “እግዚአብሔር አብ ወልድን ከባሕርዩ (ከዓላዌው) እምቅድመ ዓለም ስለ ወለደው አብ (አባት) ተባለ ፡፡ ወልድም ከአብ ባሕርይ ስለ ተወለደ (ስለ ተገኘ) የአብ ልጅ ተባለ፡፡” ይላል ፡፡ ቀጣይ ንቡቡን በሚከተለው አግኝ
   - http://ethiopianorthodox.org/amharic/mystery/pdfs/trinity.pdf

   ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ተጨማሪ የንባብ አድራሻዎች
   - http://ethiopianorthodox.org/amharic/tiyakenamelse/qanda/eyesus.pdf ከገጽ 3ዐ - 32
   - http://www.mekrezzetewahdo.org/index.php?option=com_k2&view=item&id=182:ምስጢረ-ሥላሴ-በመጋቤ-ሐዲስ-ሮዳስ-ታደሰ-የሰዋስወ-ብርሃን-ቅዱስ-ጳውሎስ-መንፈሳዊ-ኮሌጅ-የዶግማ-መምህር&Itemid=148

   ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ እግዚአብሔር ይርዳህ ፡፡

   Delete
  4. ትንሽ ተጨማሪ ማብራሪያ
   “The sun is a ball of fire.” ይኸ ቃል የፀሃይ ክበቧን ያመለክታል ፤ በጭጋጋማ ቀን ወይም ደመናማ ቀን ፀሃይ ስትወጣ ብትመለከት የተሰቀለች ቀይ ኳስ መስላ ነው የምትታየን ፡፡ አባቶች ይኸን ክበበ ፀሃይ በአብ መስለውታል ፡፡ ፀሃይ ደግሞ ብርሃንና ሙቀት ትሰጠናለች ፡፡

   “The Sun produces light.” ይኸም ፀሃይን ባየን ጊዜ የሚፈነጠቀውን ብርሃን ለማለት ነው ፡፡ ፀሃይ በክበቧ ከታየችን ብርሃኗ ሁል ጊዜም አለ ፡፡ ይኸኛውን ደግሞ በወልድ ይመስሉታል ፡፡ ፀሃይን ፀሃይ የሚያሰኛትና ከሌላው የሚለያት ብርሃኗ ጭምር ነው ፡፡ ፀሃይ ከእይታችን ዘወር ስትል ጠለቀች እንላለን ፤ ብርሃኗም አይታየንም ፡፡ ያ እንደሚሆን ሁሉ ግን ወልድ የማይኖርበትና የሚኖርበት ጊዜ አለ ማለት አይደለም ፡፡ ምሳሌውን በትክክል ለመረዳት በሃሳብ ከፀሃይ መቶ ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል ፡፡

   “The Sun produces heat.” ይኸኛውም ፀሃይ በፈነጠቀች ወቅት የሚሰማን ሙቀትን ለማለት ነው ፡፡ ይኸም ከላይ እንደተባለው ከፀሃይ ተለይቶ የቀረበት ጊዜ የለም ፡፡ አባቶች በመንፈስ ቅዱስ ይመስሉታል ፡፡ ፀሃይ ባለችበት ሰዓት ሁሉ ሙቀቷም አይታጣም ፡፡ እነዚህ ምሳሌዎችን ያስታወስኳቸው አንዱ ከሌላው አይቀድምም የሚለውን ለመረዳት ቆንጆ ምሳሌ ስለሚሆኑልን ነው ፡፡ የማለዳ ፀሃይና የቀትር ፀሃይ ሙቀታቸው አንድ አይደለም ፤ እንዲያ መሆኑ ግን መንፈስ ቅዱስም አነስና ጠንከር የሚልበት ሰዓት አለ ማለት አይደለም ፡፡

   ***** ከመጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን አምላክነት ለሚጠራጠሩ ሰዎች መልስ የሚሆኑን ማስረጃ ቃሎች
   - ለወልድ መለኮት የባህርይ ንብረቱ መሆኑ ፡፡ ቆላ 2፡9
   - ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደሆነ መገለጹ ፡፡ ዮሐ 1፡1፡14 ፤ ፊልጵ 2፡6
   - አይሁዶች ሊገድሉት ይፈልጉ የነበረው ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ አምላክን የባሕርይ አባቴ ነው በማለቱ ስለሆነ ፡፡ ዮሐ 5፡18
   - እግዚአብሔር በብሉይ ራሱን እንደገለጸው ሁሉ (ዘጸ 3፡14)፣ ኢየሱስ “እኔ ነኝ” በማለት ራሱን ገልጿል ፤ ዮሐ 8፡24፡58
   - ሰዎች ለአምላክ ብቻ እንደሚደረገው በአምልኮ ሰግደውለታል ፡፡ ማቴ 2፡2፡11 ፣ 14፡33 ፣ 28፡9
   - በሰዎች ጌታ ፣ አምላክ ፣ አዳኝ ተብሏል ፡፡ ዮሐ 2ዐ፡28 ፤ ቲቶ 2፡13
   - ለአምላክ ብቻ እንደሚቀርበው ዓይነት ጸሎትም ወደርሱም ቀርቧል (ነፍሴን ተቀበል)፡፡ ሥራ 7፡59 ፤ 1 ቆሮ 1፡2
   - በቀላል አመክንዮም ብንመለከተው የሰው ልጅ ሰው ነው ፤ የእንስሳም ልጅ እንስሳ ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ደግሞ እግዚአብሔር ነው የሚሆነውና የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅን እግዚአብሔር እንለዋለን ፡፡ ማር 1፡1 ፤ ዮሐ 2ዐ፡28 ፤ ዕብ 1፡8
   - አምላክ በመሆኑ ሁሉን ነገር አስቀድሞ ያውቃል ፡፡ ዮሐ 21፡17
   - አምላክ በመሆኑ ቅዱስ ነውና ፤ ኃጢአትንም ፈጽሞ አላደረገም ፡፡ 1 ጴጥ 2፡22 ፤ ዕብ 4፡15 ፡፡ እኛ ቢያንስ ከአዳም የወረስነው በደል ነበረብን ፡፡
   - የዘላለምን ሕይወት መስጠት የሚችል አምላክ የሆነ ብቻ ነውና ርሱም እንደሚሰጠን መስክሯል ፡፡ ዮሐ 1ዐ፡28 ፣ 17፡2
   - በሞት ላይ ሥልጣን ያለው አምላክ ብቻ ነው ፤ በራሱ ሥልጣን የከረመ ሙትን አስነስቷል ፤ ለራሱም በሦስተኛ ቀን ከሙታን መሃል ተለይቶ ተነስቷል ፡፡ ሌሎች ሙትን ቢያስነሱ በርሱ ስም ነው ፡፡ ማለትም በነርሱ ውስጥ ሥራ የሠራ ርሱ ነው ፡፡

   አንዳንዶች በተዋሕዶ የከበረ አካሉን በመዘንጋት ለምን ጸለየ ፣ ለምን ተራበ ፣ ለምን አለቀሰ ፣ ለምን አምላኬ ብሎ ጸለየ ብለው በመጠራጠር ይጠይቃሉ ፡፡ ያ ሰነፍ መሆናቸውን በአዋጅ መግለጣቸውን ያሳያል እንጅ የባሕርይ ምሥጢሩን ተረድተውት አይደለም ፡፡ ስለዚህ አብረን እንዳንጠፋ እንጠንቀቅ ፡፡

   እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን

   Delete
  5. ”ለቅኖች ምስጋና ይገባል”።እንዳለ ቅዱስ መጽሃፍ በእውነት በቅንነትና ታናሽ ነዉ ብልህ ሳትንቀኝ በታላቅ ትህትና እና ትጋት ልብ የሚያረሰርስ በሃሴት የሚያስፈደድቅ መልስህን ስለላክልኝ በእዉነት ምስጋናዬ ከልብ ነዉ::እግዚአብሔር የአገልገሎት ዘመንህን ይባርክልክ ወንድም ምእመን::አዉቃለሁ ኦርቶዶክ ለጥያቄ ሁሉ መልስ እንዳላት ነገር ግን መልስ የሌለ እየመሰለን በዘመኑ ማእበል እንዳንዎሰድ ልንጠነቀቅ ይገባል::ለዚህም ነዉ ለውሳኔ ከመፍጠናችን በፊት አባቶችን መጠየቅ እንዲሁም ሰለ ቤተ እምናታችን በቂ እዉቀት እንዲኖረን ልንተጋ የሚገባዉ::እግዚአብሔር ሰላሙን ያብዛልን:በቀደመች እምነታችን ለዘላላም ይጠብቀን::በምህረቱ ይጎብኜን አባቶችን በጤና ይጠብቅልን::አሜን

   Delete
  6. ስለ ምስጋናህ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ፤ እንድትረዳልኝ ያደረገ ርሱ እንጅ የጻፍኩት ለኔም እንኳን በቀላሉ የሚገባኝ አይደለም ፡፡ ምክንያቴም በእምነት ሲሆኑ ብቻ መረዳት የሚችሉት ትምህርት ስለሆነና ፣ ቤተ ክርስቲያናችንም ምሥጢር ብላ ስለምትገልጸው ነው፡፡

   በተጨማሪም ላሳስብህ የምፈልገው ሰዎች የራሳቸውን መጽሐፍ ቅዱስ እያስነበቡ እንዳያሳስቱህ እንድትጠነቀቅ ነው ፡፡ እነርሱ የራሳቸውን መጽሐፍ አውጥተው ሊያስረዱህ ወይም ሊከራከሩህ ሲፈልጉ ፣ አንተም በራስህ መጽሐፍ ቅዱስ ለመመለስ መሞከር አለብህ እንጅ ፣ የተጻፈ ስላስነበቡህ ብቻ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል እንዳትልላቸው ነው ፡፡

   መጽሐፍ ቅዱሱን የየድርጅቶቻቸውን ዓይነትንና ፍላጐት ለማሟላት ሲባል በራሳቸው ልክ መቀየራቸው በማስረጃ ተረጋግጧል ፡፡ ለምሳሌም ጾም የሚልን ቃል ደምስሰው ፣ ጸሎት ብቻ እንጅ ጾም አያስፈልግም ይሉሃል ፡፡ በዮሐንስ ወንጌልም ላይ "ቃል እግዚአብሔር ነበረ" የሚለውን መልአክ በሚል ቀይረዋል ፡፡

   ከዚህም ለየት የሚለው ብልሃታቸው ደግሞ ኃይለቃሉን ቀንጭበው በመተርጐምና በማሳፋት የራሳቸውን ዶክትሪን ሊያሳምኑ መታገላቸው ነው ፡፡ ለእንደነዚህ ዓይነቶቹ መፍትሄ የሚሆነው ፣ ቢያንስ ኃይለቃል ያመጡበትን ምዕራፍ በሙሉ ሳያነቡና መልዕክቱን ሳይረዱ የማንንም ትምህርት እውነት አለማለት ነው ፡፡ ከተቻለ ቀደም ካለ ምዕራፍ ጀምሮ ቀጣዩንም ጨምሮ በማንበብ መረዳት ይጠቅማል ፡፡ ለእኔ አዲስ ትምህርት በሙሉ ውሸት ነው ፤ ሰዎች በምን ልሥራ ሲፈላሰፉ የሚፈጥሩት የትርጉም ልዩነት ውጤት ስለሆነ ፡፡

   እግዚአብሔር እንደነዚህ ዓይነቶቹን በቃሉ የሚያሳፍር አባት ካልሰጠን በስተቀር ብዙ የዋሃንን ፈተና ውስጥ ያስገባሉ ፡፡ አሁን እንደምናየው ብዙውን እውነት የተረዱ አባቶች ተመልካች ሁነዋል ፡፡ እንደ ጥንቱ ስለሃይማኖት ጥብቅና ቆሞ የሚሞግት አላገኘንም ፡፡ እነርሱን ተክቶ የሚታገለው ፣ ሃይማኖቱ የገባው የነርሱ ተከታይ ወጣትና ተራው የእኔ ብጤ ምእመን ብቻ ነው ፡፡

   ስለሁሉም ምስጋናዬ ይድረስህ ፤ እግዚአብሔርም ይመስገን ፡፡

   Delete
  7. in the name of father son & hollysprit thy peace up on us amen my blessed brother meamen as I told you I always waiting your answer & its wonderful that's how our church teach so u always make me know new thing God bless you but I ask you to change our mail address that to ask you a lot of question &to do something good together I know u might be busy but just once wright to my mail & make happy here is my address saha2011@yahoo.com thank you in advance God be with you always

   Delete
  8. አሜን አሜን አሜን ይሁንልን ይደረግልን ወንድም ምእመን::ምክርህ እጀግ ያጽናናል እጅግም ያስተምራል እናም ገንዘቤ አድርጌዋለሁ::ደግሞም በዚህ ዘመን እንደ አሸን ሃስተኛ ነቢያት በበዙበት እንደበግ ልንነዳ አይገባም ጥንቃቄም ማድረግ ያለብን ሰአት ነዉና ሃሳብህ ሃሳቤ ነዉ:: በበኩሌ ምእመን በጸፍክ ቁጥር እንማራለንና ደግመህ ደግመህ ጸፍልን እንላለን::ይገርምሃል ወንድም ምእመን አንዳንዴ ተቃዋሚ ሲኖር ጥሩ ነዉ መሰልኝ የተቃዋሚ ብሎጎች ከተክፈውቱ ጀምሮ የሚቀርቡ የመልስ ጽሁፎች እየተባዙ ብዙ ሰዎችን ብዙ ቦታ ሲያስተምሩበት በማየቴ እኔ በበኩሌ ብዙም አልጎዱንም እላለሁ:: እንዳልከዉ እዉቀቱ ያላቸዉ አባቶች ብቅ እያሉ ቢያስተምሩን ደግሞ ጠቀሜታው እጅግ የጎላ ነዉ እላለሁ::እግዚአብሔር ይርዳን::አምሰግናለሁ በድጋሚ!!!

   Delete
 3. I started reading the article with an open mind, hopping to get some information. The argument is very shallow and unconvincing, in some wayd there is contradition

  ReplyDelete
 4. ለአስተያየት ሰጪዎች ማህበረ ቅዱሳን
  እኛም እንደአንተና እንደ አማራው የሰሜኑ ነፍጠኛ ወንጌል ይዣለሁ ባይ ወንጌልን እናቃወም ነበር ዛሬ በኢትዮጵያ ብዞዎች የአንተን ስህተተኛ መንገድ ትተው ወደ መዳኛው ወንጌል ከዛም ሲያልፍ ወደ መጥፊያው የእስልምና ቁርዓን እየገቡ ነው አንተ የሚታይህ ታቦት ላይ ያለውን ህዝብ መውጣት ነው ነገ ስንቱ ይከዳል ምክንያቱም ጸሎት ስግደት ለአንድ ጌታ ስላሴ ብቻ ነው የስግደት ሁለት ለወም አንድ ብቻ ጸሎትን የሚሰማ 1እዬ ለሚጠፉት ለነሱ አስብ ይህ ወንጌል ባጣማሚዎች ተጣሞ ባቅኝዎች ሊቃና ሲል ተቃዎሞ በየጊዜው ይደርስበታል እኔ የምልህ ለምን ወንጌልን አትሰብክም ለምን ወደ ደቡብ አትወርድም ያጠመካቸው የታሉ ቢጠመቁም መች ጸኑ ምክንያቱም ለአንተ ወንጌል የአባቱቼን እያልክ ዘርኝነትን መስበክ
  አቤሶ ከወለጋ

  ReplyDelete
  Replies
  1. zeregnaw,we know you well.ye oromon hizb, orthodox ye Amhara, ye Tigre haymanot new eyalachihu, you changed this poor people to protestantism. Not by preaching gospel rather by using the current ethnic based discrimination. Nothing special in your post. salvation is not about ethnicity, it is all about being human. Avoid this local thinking. Don't you know westerns, who are majorily protestants are rapidly changing to Godless people (Paganism).If it as you said, nothing different with orthodox.It is due to modernization to change to other denominations not the problem of orthodox church. errrrr bel, there are more than 50 million people in Ethiopa who are orthodox including oromo & SNNP. And the fashion to change to pente is already has finished.

   Delete
 5. We cannot change the truth the Bible is true. Let us open our heart and mind so that God can help us to see through. I thank God we have reference to read which is the bible let us stop blind lead the blind. This article is very informative may God richly bless you whoever writes this article.

  ReplyDelete
 6. Whoever wrote on April 9,2013 at 11:44 “minm ayasaminim ewunet mels teftobachihual”If you have an answer why do not you bring it and teach others. If you do not want to hear the truth how do you learn? What is the truth in your side is it out of the bible or other? May God open your heart.

  ReplyDelete
  Replies
  1. እስቲ አንተ መሃይሙ አስተምረን …የከሸፈ ብሎግ ይሉሃል ይሄ ነው… ሁሉም ነገር በሬ ወለደ … እረ ልብ ግዙ(ከቄራ)

   Delete
  2. See above the response of MIEMEN. Again read the pop shinoda III book, which is called "priesthood". which gives response to the claims of protestants on it.please search on Google pop shinoda III, then priesthood. I said not blindly but b/c I read that & others. Translating biblical statements is not as such simple as we think. okay, in what way the aba selama translations can be taken as a truth? who set them as standards? I believe in the spirit who dwells in Pop shinoda & other orthodox father but not in aba selamas.Sorry, i.e my problem

   Delete
 7. Tebareku yeh ewnet new lebachenen yemigezaw kirsotosn zewor aderegew kahen nen lemilu lene gen yezelalem kahen geta new. Tsegawen tabezalchu

  ReplyDelete
 8. This is not convincing article. The person who wrote this article is useless. Better to go to the protestants who don't question if a pastor tells them anything.

  ReplyDelete
 9. «የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።» የሚለው ምንም እንኳ በዚህ ስፍራ ለጴጥሮስ የተነገረ ቢሆንም በምዕራፍ 18 ላይ ግን አንዱ ሌላውን ቢበድል በመጀመሪያ ለብቻው እንዲወቅሰው፣ እርሱን ካልሰማው በምስክር ፊት እንዲወቅሰው፣ በምስክሮች ፊት እንቢ ካለ ግን ለቤተ ክርስቲያን እንዲነግራት፣ ቤተ ክርስቲያንን አልሰማ ካለ ግን ያ ሰው እንደ ቀራጭና አረመኔ እንዲቆጠርና ከቤተክርስቲያን እንዲለይ ጌታ አስተምሯል፡፡

  minun ke min agenagnachihut? pa pa pa... yegna ye metsihaf kidus terguamiwoch

  ReplyDelete
 10. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ፤ ለምን ከጴንጤ ቆስጤዎች ጋር አተካራ ትገጥማላችሁ? አንድ አይነት እምነት ከሌለን ሰዎች ጋር መከራከር አይገባንም። ሥልጣነ ክህነት የለም ከሚሉን ጋር ምን አይነት ኅብረት ነው የሚኖረን? ማንነታቸውን እኮ ግልጽ እያደረጉ ነው ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ የተማርከውንና የምታውቀውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ብታስረዳን ይጠቅመናል እንጅ ፣ እነርሱ የአማኞችን ሃሳብ ለመበታተንና እምነትን ለማዳከም ፣ ብሎም ለማስኮብለል መጽሐፍን በሌሎች መንገድ እየተረጎሙ ሲያስነብቡን መልስ አለመስጠት ትክክል አይደለም ፡፡ በመወያየታችን ከነርሱም መሃል እንኳን እውነትን የሚማሩ አልጠፉም ፡፡ ምክንያቴም ከዚህ ቀደም ኢየሱስ ሥጋዊ አካሉን ይዞ ስላረገ እየጸለየ ከአብ ያማልደናል ብለው የጻፉትን ፣ አሁን አሻሽለው በስሙ ነው የሚማለደው ማለት ችለዋል ፡፡ የኢየሱስን የአማላጅነት ትምህርት የተውት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ስለተከራከርናቸው ነው እንጅ ከራሳቸው ተነስተው አይደለም ፡፡ አሁን ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ተነስተውበታል ፡፡ ጌታችን ግን በመንፈስ ቅዱስ ላይ ስህተትን መናገር ይቅርታ የለውም ብሏልና መጠንቀቁ ለሁሉም ይበጃል ፡፡ በወቅቱ ከሌላ ሰው ጋር በውይይት ላይ ስለነበርሁ ፣ የጊዜ እጥረት ምክንያት ሆኖ ፣ በዚህ ርዕስ አስተያየቴን ሳላካፍል አለፈብኝ ፡፡ የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርት በሥርዓቱ የምታውቁት ፣ ከቻላችሁ በየምክንያት አስተምሩን ፤ ለምእመናን ትጥቅ ማስታጠቅ ስለሚሆንልን ፤ መቅረዝን ከያዙ በኋላ ከጋን አያኖሩትምና ፡፡ ስለዚህም ዓይነታቸውን አውቀናልና ተብሎ እጅ አጣጥፎ ዝም ማለቱ መጨረሻው ጥሩ አይደለም እላለሁ ፡፡

   Delete
  2. ውድ ወንድሞች እንደምን አላችሁ!!! መቼም ያለንበት ዘመን ምን ያህል አስከፊ እና በተለይ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የተጀመረዉ የዳቢሎስ ዘመቻ ለናንተ ለወንድሞቼ የተደበቀ ነዉ አይባልም ምክንያቱም ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ሁለታችሁም ወንድም ቦጋለም ወንድም ምእመንም የሰጣችሁት መልስ የማያዳግም እንደነበር ያለፈ ስራችሁ ይመሰክራል::ትውልድም ይዘክረዋል::::እናም ምን አልባት ለየላቸዉ ብለን መልስ መስጠት አቆምን ማለት እጅግ አደጋ አለዉ::ብዙዎቻችን እዉቀቱ የለንም እናም በመማር ላይ ላለነዉ ወንድሞቻችሁ የናንተ እና መሰል የአባቶች ት/ት ማለት የማዳንና ያለማዳን ጉድይ ነዉ::ወንድሞች እኔ ከንቱው ፍጥረት እንኩዋን ምንም አይነት የቤተክርስቲያን ት/ት የሌለኝ በአለማዊ ት/ት ጥየዉ ነግ ጠዋት ለምሄደዉ ደፋ ቀና ስል የኖርኩ ስሆን አሁን ቢያንስ በዚህ ብሎግ ላይ የወጡ ትምህርቶችን በማንበብ ለመናፍቅ የሚሆን መልስ በከፊል እንድታጠቅ አድርጋችሁኛልና ለስራችሁ አምላክ ይክፈላችሁ እላለሁ::እናም አሁን ምእመን ባለዉ ሃሳብ ብንስማማና እዉነት እዉቀቱ ያላቸዉ ሊቃወንቱም ወደምንፍቅና አራማጅ ብሎጎች ብቅ እያሉ የዳቢሎስን ስራ ያፍር ዘንድ መልካም ነዉ::ነገር ግን ምን አልባት ወድ ወንድሞች ሁለታችሁንም ጽህፋችሁን ብዙ ግዜ አንብቤያለሁ እግዚአብሔር ይምሰገን መጽሃፍ የመረዳት አቅማችሁ እጅግ መልካም ነዉና ለምእመናን ጥያቄ የሚመልስ አንድ ብሎግ ብትከፍቱልን የሚል ታላቅ አድራ ልጭንባችሁ ተገድጃለሁ::ይህን ልል የተገደድሁት ከማንበብ በተጬማሪ ያ ትሁት ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ እንዳለዉ ሚስጥርን የሚገልጡ ትርጋሜውን የሚነግሩን አባቶች ስለምታስፈልጉን ነዉ::እናም እስቲ ወድ ወንድም ቦጋለ እና ወድ ወንድም ምእመን ሃሳባችሁን በዚህ ዙሪያ ጀባ ብትሉኝ ስል በትህትና በክርስቶስ ስም እጠይቃለሁ::ሰላም እግዚአብሔር አይለየን::   Delete
 11. Peace to all the follower of Jesus Christ! This website is very helpful website because we can write all our opinion. But one thing let us stop to criticize one another; instead let us explain what we understand from the bible. Reading the Bible is not difficult .when we seeking for God and read the Bible it reveal to us so please let us read the bible before criticizing anybody. This is not a matter of which groups we are in. believe and have eternal life is a matter of life and death. We all going to die one day and we will be judge by GOD. Let us prepare and understand what can take us to heaven when we die. And teach other the truth. But it should be from the Bible. How many of us read the bible let us question ourselves? Because when we read the bible it opens our eyes to love one another and respect others. First of all if we clam ourselves we are Christians we should do what Christ thought us. Even when his dispel asked him who will have eternal life He told them the one who is humble himself. He said have child heart. Love one another and the Bible said live with peace with everyone not by saying my religion is better than the other religen. As we all Christian let us lead by example of Jesus Christ. Think about his love. He died for the whole world. May God richly bless you.

  ReplyDelete