Monday, April 1, 2013

ማኅበረ ቅዱሳን መዳናችን መቀደሳችን በግብረ መንፈስ ቅዱስ መፈጸሙን ያምናል?

መጽሐፉ በውስጡ የያዛቸውን በርካታ እውነቶች ማኅበሩ እንደማያምን ይታወቃል፡፡ ሳያምንበት ታዲያ በስሙ እንዴት ሊያሳትመው ቻለ? የሚለው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አላገኘም፡፡ ማኅበሩ መጽሐፉ ብዙ ፈላጊ እንዳለው እያወቀና አሮጌ ተራ ላይ ዋጋ ሰማይ መድረሱን እየሰማ በድጋሚ ሊያሳትመው ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ከዚህ ይልቅ አሳትሞ ያሰራጨውን ሰዎች እያነበቡ “እንዳይሳሳቱበት” ሰብስቦ አብዮታዊ እርምጃ ቢወስድበት ደስ ባለው፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን አሳታሚነት ለንባብ የበቃው የታላቁ ሊቅ የሊቀ ጉባኤ አባ አበራ “ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት” መጽሐፍ ከታተመ 10 ዓመታት አልፈዋል፡፡ ማህበሩ መጽሀፉ የያዘውን እውነት በአንድም በሌላም መንገድ ሲቃወመው እንደኖረ አይካድም፡፡ ታዲያ የማያምንበትን መጽሐፍ ለምን አሳተመ? ካመነበትስ ይህንኑ እውነት ያመኑትን የቤተክርስቲያን ልጆች ተሀድሶ መናፍቅ እያለ ለምን ያሳድዳቸዋል? እስኪ በተጠቀሰው መጽሐፍ ከገጽ 176-178 ላይ የመንፈስ ቅዱስን ስራ በተመለከተ የሰፈረውን እናካፍላችሁ፡፡
መዳናችንና መቀደሳችን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ይፈጸማል
የጸጋ መስጫ መንገድ የተላኩት ልኡካን ናቸው ቢባልም ልኡካኑን ሁሉ የሚልከው እሱ ባለቤቱ ስለሆነ የጸጋ ሁሉ ምንጭና መገኛ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ልኡካን መሳሪያዎች ናቸው፡፡ የክርስቶስ ጸጋ ለሰዎች ሁሉ የሚሰጠውና የሚታደለው፥ የድኅነት ጸጋና በረከት ተካፋይ መሆን የሚቻለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ረድኤት ነው፡፡ ወደ ክርስቶስ የሚመጣም ሆነ የሚያምን ሁሉ በቅድሚያ “ከእግዚአብሔር የሰማ የተማረም” በጸጋውም የተጠራ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ነው ጌታችን “አልቦ ዘይክል መጺአ ሀቤየ እመ ኢሰሐቦ አብ” ያለው (ዮሐ. 6፣44-45 ትርጓሜውን ተመልከት)፡፡ ይህም ማለት የላከኝ አባቴ በሀብት ስቦ በረድኤት አቅርቦ ካልሰጠኝ በኔ ማመን የሚቻለው የለም ማለት ነው፡፡ ታዲያ ይህን በውል ያልተረዱ አንዳንድ ሰዎች ያለጸጋ እግዚአብሔር ማለት ያለ መንፈስ ቅዱስ ጸጋና ረድኤት በራሳቸው ዕውቀትና ፈቃድ፥ ኃይልና ውሳኔ ብቻ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ፥ ጌታና አምላክ መሆኑን የሚያምኑ ስለ መሰላቸው የመዳንንና የመጽደቅን ጸጋ ማግኘት በግል ጥረታቸው ብቻ የተፈጸመ የግል መብታቸው እንደ ሆነ በትምክሕት ያስባሉ፤ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ሐሰት ነው፡፡ ማንም ሰው ቢሆን በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር ኢየሱስን ጌታና አምላክ ነው፤ እርሱም በስጋ የመጣው ክርስቶስ ነው ማለት አይችልም (1ቆሮ. 12፡3 1ዮሐ. 4፡2)። ማንም ሰው ይህን ካላመነና ካልመሰከረ ደግሞ ሊድን አይችልም፡፡ ስለዚህ ለማመን ልቡናችንን የሚያነሣሣ ካመንና ከተጠመቅን በኋላ በእምነት ለመኖር የሚያጸናንና የሚያጽናናን እርሱ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ስለ በጎ ፈቃድ መፈለግንና ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና ፊልጵ. 2፡13፡፡  እንግዲህ በክርስቶስ የተገኘው የመዳን ጸጋ ሁሉ በእያንዳንዱ አማኝ ልቡና ውስጥ እውን የሚሆነው በተግባርም የሚተረጐመው በመንፈስ ቅዱስ ረቂቅ ጥበብና ሥራ ነው። ይህን ረቂቅ የእግዚአብሔር መንፈስ ዓለሙ ፈጽሞ የማያውቀው ቢሆንም አማኞች ግን በውስጣቸው ስለሚኖር ያውቁታል (ዮሐ. 14፥17)፡፡

እንግዲህ የእግዚአብሔር መንፈስ የምሥራቹን ቃል እንድንሰማና እንድናምን ይረዳናል፤  በጥምቀትም ሥርየተ ኃጢአትን አዲስ ሕይወትን የጸጋ ልደትን ይሰጠናል፤ እንደ ሥጋዊ ልደታችንና እድገታችን በመንፈሳዊ ሕይወታችንም ቀስ በቀስ በጸጋው እንድናድግ ያበቃናል፡፡ መንፈስ ቅዱስም ይህን ከፈፀመ በኋላ ሥራውን በዚህ አያቆምም፡፡ ይህ የመንፈስ ቅዱስ የመጀመሪያ ሥራ ይሆናል፡፡ ገና በውኃና በመንፈስ ቅዱስ አዲስ ልደት አግኝተው በክርስቲያናዊ ሕይወታቸው ካላደጉት ከንኡሰ ክርስቲያንነት ጀምሮ ወደ ከፍተኛ ደረጃና ማዕረግ እንዲደርሱ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስ የአማኞቹን ልቡና ያነሣሣል፡፡ በክርስቶስ ጸጋ አምኜአለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ምን እሆናለሁ በማለት አዲስ አማኝ ያለ አግባቡ ራሱን በራሱ በመሸንገልና በመደለል፣ በሐሰት በሚያባብል ስሜት ተነሣሥቶ እንዲያው በከንቱ እንዳይዘናጋና እንዳይዝናና ያስጠነቅቀዋል፤ “የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ” ተብሎአልና 1ቆሮ 1ዐ፡12፡፡ ከዚህም ጋር መንፈስ ቅዱስ የሰውን ድካሙን ያውቃልና ከፈቃዳተ ሥጋ ጋር መንፈሳዊ ተጋድሎ እንዲያደርግ እንጂ በቸልተኝነት እንዳይኖር ያተጋዋል፡፡ የኃጢአት ዝንባሌውንም በመዋጋት ከፈተናም ሁሉ እንዲድን ተግቶ እንዲጸልይና እንዲጾም ያደርገዋል፡፡ ከበደልና ከክፉ ነገሮች ዓለምንም ከመውደድና ከመምሰል ራሱን እንዲለይ በማድረግ ወደ ቅድስና ኑሮ ይመራዋል፡፡ እንግዲህ በዚህ ሁኔታ የአማኙን መንፈሳዊ እድገት ከፍ በማድረግ በሕይወቱ ውስጥ የመንፈስ ፍሬዎች እንዲያፈሩ ይሆናል፤ መንፈስ ቅዱስ በገለጸለት እውነት እየተመራ በመንፈስ ይኖራል፤ በመንፈስም ይመላለሳል ገላ. 5፡22-25፡፡

እንግዲህ ሰዎች በክርስቶስ በማዳን ሥራው አምነው እንዲድኑና እንዲጸድቁ እንዲቀደሱም በክርስቲያናዊ ሕይወታቸውም እንዲጸኑ ካደረገ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ስራውን በመቀጠል የዳኑትንና የተቀደሱትን ደግሞ ለበለጠ ሥራና አገልግሎት ያዘጋጃቸዋል፡፡ ለእነርሱ ልዩ ልዩ የአገልግሎት ጸጋ ማለት የማስተማር፣ ትንቢት የመናገር፣ ተኣምራት የማድረግና የመሳሰሉት ስጦታዎችን በማደል አሕዛብን አሳምነው እንዲያጠምቁና እንዲያድኑ በማድረግ የራሱ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ተባባሪዎች ይሆናሉ እንጂ ያለ ጸጋ ስጦታ እንዲሁ አይተዋቸውም፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንደ ወደደ ለሁሉምና ለእያንዳንዱ የጸጋን ስጦታ በማደል ልዩ ልዩ የመንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲያበረክቱ ያደርጋቸዋል፡፡ በተለይም ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን የፈጸመውን ተአምራትና ድንቅ ሥራ፣ ያስተማረውንም የወንጌል መልእክትና መልካም ዜና ሁሉ የሚሰብኩና ድህነተ ጸጋውንም ለሁሉም የሚያዳርሱ የተመረጡ መሣሪያዎች በሆኑ ሰዎች አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ሥራውን ያካሂዳል፡፡ ስለዚህ ነው በመንፈስ ቅድስ የተላኩ ልኡካን የምሥራቹን ቃል መስበክ፣ ማሳመንና የመዳንን ጸጋ ማስተላለፍ የሚችሉት፡፡ እነርሱ የመዳናቸውንና የመንጻታቸውን ጸጋ ከመንፈስ ቅዱስ ተቀብለውና የእርሱም ማደሪያ በመሆን ለሌሎች ደግሞ የኃጢአት ሥርየትና የመዳን ጸጋው መስጭያ ምክንያት መሣሪያ ወይም መንገድ እንዲሆኑ ብቃትን ከላኪያቸው አግኝተዋል፡፡

11 comments:

 1. very nice article may God richely bless you.

  ReplyDelete
 2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !April 1, 2013 at 9:16 PM

  Very thoughtful article, RIP Aba Aberra.

  ReplyDelete
 3. This is true Orthodox Theology but I don't think mk leaders understand this.The target of mk is the issue of membership, if you are not their memebr, they mayn't accpet whether you are Orthodox or not.

  ReplyDelete
 4. I do not even know the way I finished up here, however I assumed this put up was once great.
  I don't know who you're but certainly you're going to a well-known blogger in case you are not already. Cheers!

  My web page ... free work from home jobs for moms

  ReplyDelete
 5. Discussion like this will broaden our horizon. I wish some of us are refrained from labeling others and open our mind
  to seek out the truth.
  Bless you !

  ReplyDelete
 6. I like what Mahibre Kidusan do when it comes to restoring the country side churchs and monastries. I give them top credit, but their attitudes towards people like the writer above would put them in the bottom of any standard you put. Proffessor Mesfin has said it enough.

  ReplyDelete
 7. MK is evil. Unfortunately, 95 percent of its members don't know that MK has hidden political and business agenda. The good thing the eyes of those 95 percent innocent MK members are opening and beginning to see the true and hidden agendas of MK, which is to control the church and install a government from Shewa.

  ReplyDelete
 8. እናንተ ተደናግራችሁ ሰውን ለማደናገር የምትጥሩ .................. የአባ አበራ ጽሑፍም ይሁን የማህበረ ቅዱሳን አስተምህሮ ልዩነቱ የቱ ላይ ነው? የተጻፈውን በራስ መንገድ መተርጎምና የጽሑፉ ይዘት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 9. who tells you MK is opposed this fact,don't be foolish men, this is pure tewahedo teaching. we dont work for salivation but we become a liar if we don't have a work after salivation.so liar is satan. if you have abraham's faith were is abraham's work in your life

  ReplyDelete
 10. ሰይጣን ክፉ መልእክቱን ወደ ሰዎች የሚያደርሰዉ በአብዛኛዉ በዉስወሳ (በጉትጎታ) አማካኝነት ይሁን እንጂ ጥቂት ሊባሉ በማይችሉ ሁኔታዎች ደግሞ የተለያዩ ነገሮችን ተመስሎ በመግለጥ እኩይ መልእክቱን ያስተላልፋል ፡፡ ሰይጣን ሰዉ ተመስሎ መገለጥ ይችላል ፡፡ ድምጽ በማሰማት ብቻ ይገለጣል ፡፡ እንግዳ የሆነ አቋም እና መልክ ይዞ ሊገለጥ ይችላል ፡፡ መላእክት ወይም ቅዱሳን ናቸዉ ተብለዉ የተሳሉ ምስሎችን ተመስሎ ይገለጣል ፡፡ ወይም ከመናፍስት ዓለም የመጣሁ ነኝ ፤መንፈስ ነኝ ፤ መንፈስ ቅዱስ ነኝ በማለት እራሱን ይገልጣል ፡፡
  ሰይጣናት በቀጥታ በመንፈስ በመገለጥ ሰዎችን ሊያነጋግሩ ይችላሉ ወይም በቀጥታ ባይገለጡም ለዚሁ ጉዳይ ባዘጋጁት ሰዉ ዉስጥ በመግባት በሰዉዬዉ ቋንቋ እና ምላስ ይናገራሉ ፡፡ የዛር ፈረስ ፤ወልይ ፤ባለ አዉሊያ ፤ጠንቋይ ፤አጉሪ ፤ በመንፈስ ቋንቋ /በልሳን እንናገራለን የሚሉ የተሳሳቱ እምነት አራማጆች ለሰይጣን ምላስ በመሆን ያገለግላሉ ፡፡ ሰይጣን በእነዚህ ሰዎች ዉስጥ በማደር በማይታወቅ ወይም በሚታወቅ ቋንቋ ይናገራል ፡፡
  መላእክቶችን ፤ነብዮችን ፤ጻድቃንን አማላጅ አድርገዉ ለሚይዙ ሰዎች መላእክ ፤ነብይ ወይም ጻድቅ ነኝ በማለት ሰይጣን ይገለጥላቸዋል ያነጋግራቸዋል ፡፡ ሰዎቹ ያ ያነጋገራቸዉ አካል መላእክ ወይም ጻድቅ ወይም ነብይ እንደሆነ ያምናሉ ፡፡ እዉነታዉ ግን መላእክ ወይም ጻድቅ ወይም ነብይ ነኝ ብሎ የቀረባቸዉ እርሱ ሰይጣን ነዉ ፡፡ በአንድ ጻድቅ ስም የተሰየሙ በተለያዬ ቦታ የሚገኙ የእምነት ቤቶች ይኖራሉ ፡፡ በአንዱ እምነት ቤት የሚገለጠዉ ጻድቅ በሌላዉ እምነት ቤት ከሚገለጠዉ የተለዬ ነዉ ፡፡ ደብተራዎች በተለያዩ የአስማትና የጥንቆላ መጽሐፍት ዉስጥ የሚገኙትን ትርጉማቸዉ የማይታወቁ ስሞችን የመላእክት ወይም የእግዚያብሄር ስሞች ናቸዉ ይላሉ ፡፡ እዉነታዉ ግን የሰይጣናት ስሞች ናቸዉ ፡፡

  ReplyDelete