Sunday, April 14, 2013

የአቶዎቹ ስፖንሰርሺፕ ጥያቄ አነጋጋሪ ሆኗል

Read in PDF
በጥቅምት 2004 ዓ.ም. የሲኖዶስ ስብሰባ ከተነሱት ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋናው ቤተክርስቲያኒቱን በቅጡ የማያውቋት ትምህርቷም የሌላቸውና በቤተ ክህነቱ አስተዳደር ቦታ ላይ የተቀመጡ አቶዎች ጉዳይ እንደ ነበር ይታወሳል፡፡ ያን ተከትሎም አቶ ተስፋዬ ከምክትል ስራ አስኪያጅነት ቦታ እንዲነሳ የተደረገ ቢሆንም አቡነ ፊልጶስ ቤት ገብቶ እግራቸው ላይ ወድቆ በማልቀስ ከዚህ ጉድ አውጡኝ አሊያ የት እደርሳለሁ ብሎ ተማጽኖ በአባ ፊልጶስ ጥያቄ ዳግም እንዲመለስ መደረጉን ምንጮቻችን ያስታውሳሉ፡፡ ከተመለሰ በኋላ እርሱ ብቻውን ኢላማ እንዳይሆን በማሰብ የእርሱ ቢጤ አቶዎችን በተቻለው ሁሉ ቦታ ቦታ አስያዘ፡፡ ከዚያም ከአባ ሳሙኤልና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በማበር የቤተክርስቲያኒቱን ሊቃውንትና መምህራን ወንጌል ሰባኪዎችንም ማሳደዱን በተለይም በደቡብ ክልል ማቅ በእውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች የተነጠቀውን እስትራቴጂክ ቦታ ለማስመለስ ስልጣኑን ተጠቅሞ የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ ሲታገል መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከተለያየ አቅጣጫ ጫና ውስጥ እየወደቀ የሚገኘውና በአባ ፊልጶስ ቢሮ በርካታ ከሙስና ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ደብቋል እየተባለ የሚወራበትና በሙስና ወንጀል ስለሚጠረጠር ኦዲት ሊደረግ ነው የሚባለው ተስፋዬ እና ግብረ አበሩ እስክንድር እህል ውሃቸው ከቤተክህነቱ ሳይቋረጥና አዲሱ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስተዳደር  ሳይጠናከር በፊት በተለመደ የሙስና መንገድ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ለመሰብሰብ ለአብያተ ክርስቲያናት የበተኑት ደብዳቤ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ “እስፖንሰር እንድታደርጉልን ስለመጠየቅ ይመለከታል” በሚል ርእስ የተበተነው ደብዳቤ አቶዎቹ ስለቤተክርስቲያን ምንነት የማያውቁና ማንን ስፖንሰር መጠየቅ ማንን ደግሞ ተባበሩኝ ማለት እንዳለባቸው እንኳን ያለዩ ጨዋዎች መሆናቸውን ያሳበቀባቸው ሆኗል፡፡ እንደ ደንቡ እስፖንሰር የሚጠየቅ ባእድ አካል እንጂ ቤተክርስቲያን አልነበረችም፡፡ ቤተክርስቲያን ግን የጉዳዩ ባለቤት ስለሆነች ስራው የራስዋ በመሆኑ ተሳትፎ ነበር መጠየቅ የሚገባት፡፡ አቶዎቹ ግን ልባቸው ገንዘቡ ላይ ስለሆነ አጠያየቁንም አላወቁበትም፡፡ ስህተታቸው የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡
በደብዳቤው ላይ የቀረበው ሐተታ እንደሚያሳየው ቤተክርስቲያን እስካሁን በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በመንፈሳዊ ዘርፎች ያከናወነቻቸውን ዋና ዋና ተግባራት በተገቢው መንገድ ስላላስተዋወቀች መጽሔቱን ማዘጋጅ እንዳስፈለገ ያትታል፡፡ ይህ በራሱ ያለፈውን የአቡነ ጳውሎስን አስተዳደር ቤተክርስቲያንን ከማስተዋወቅ አንጻር የሰራውን ስራ ሁሉ ገደል የሚጨምር ነው፡፡ ቤተክርስቲያኗ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን ከመቼውም ጊዜ በላይ በዓለምአቀፍ ደረጃ መታወቋ የማይካድ ሀቅ ሆኖ ሳለ አቡነ ጳውሎስም የዓለም አብያተ ክርስቲናት ምክር ቤት ፕሬዚደንት እስከመሆን ደርሰው ሳለ ይህን ሁሉ በዜሮ አባዝቶ ቤተክርስቲያኗን አቶዎች እንስተዋውቃታለን ብለው መነሳታቸው ለመዝረፍ ካልሆነ በቀር ምንም ትርፍ እንደሌለው ይታወቃል፡፡ 112 ገጽ አለው ለተባለው መጽሔት “ደረጃውን የጠበቀ” ህትመት ለማሳተም ለየአብያተ ክርስቲያነቱ እስፖንሰር ሁኑን የተባለው ገንዘብ ደረጃ ወጥቶለት የነበረ ሲሆን አማካዩን 20 ሺህ ብር ብንይዝና 50 አብያተ ክርስቲያናት መክፈል ቢችሉ እንኳን ሊገኝ የሚችለው ገቢ በጥቂቱ 1 ሚሊየን ብር ይሆናል፡፡ ታዲያ ይህ ገንዘብ በዚህ መልክ ለህትመቱ ሊውል ይችል ነበር የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡  ይህ ሁሉ ሀተታ በመጽሔቱ ስም ዳጎስ ያለ ገንዘብ ለማግኘት ነው፡፡ በግንቦቱ ሲኖዶስ በአጀንዳነት ሊነሱ ከሚችሉ ጉዳዮች መካከል የእነዚህ አቶዎች ጉዳይ መሆኑን ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” እንደሚባለው ሙስናዊ ተረት እስካሁን የበላነው አልጠቀምንም ግንቦት ላይ ሳንጫር ቶሎ ቶሎ ብለን እንብላ ነው ነገሩ፡፡

12 comments:

 1. እግዚአብሔር ይመስገን ማጅራት መቺዎቹ ተስፋዬ ውብሸት እና እስክንድር ገብረክርስቶስ እንዲሁም ከመፅሄቱ ጀርባ የቆመው ሴሰኛው መጋቢ ምስጢር ተደረሰባቸው፡፡

  ReplyDelete
 2. እነዚህ ከንቱዎች ቤተክርስቲያንን ቀለዱባት አይደል?

  ReplyDelete
 3. ወይ ጉድ !!!!!!! አሉ አባ ባሌ ተሰማ

  ReplyDelete
 4. መኑ ውእቱ ገብር ኄር፣ ታማኝ አገልጋይ ማን ይሆን?
  http://www.ashenafimekonen.blogspot.com/2013/04/blog-post_12.html#more

  ReplyDelete
  Replies
  1. ራሱስ መች ታማኝ አገልጋይ ነበር፤ ጥሩ ነጋዴና ኪራይ ሰብሳቢ እንጂ። ኪሱን ለመሙላትና ምንፍቅናውን ለመዝራት በአባ ጳውሎስ ሳይታክት ይገለገል ነበር እንጂ። በውዳሴ ከንቱ ሲጥላቸው “ቤተ ጳውሎስ” ብሎ ብሎግ ከፍቶ ነበር። ሲሞቱበት፣ ቁርጡን ሲያውቀው ተረቱን በስሙ መፃፍ ጀመረ። ባይወገዝ ኖሮ ቤተ ማቲያስን ይከፍት ነበር። መጀመሪያ ራስህ ታማኝ አገልጋይ ሁን።

   Delete
  2. kemiqnubet andu anete nehe meselegne, aye??? mk yezeraw enkerdad? daru yete ygebahal ye-Tsega setota. wanaw menafeqs ante alawaqiw. kkkkkkkkk....

   Delete
  3. Anonymous April 15, 2013 at 7:48 PM... you sound just like the brothers of Joseph in the bible. It's not healthy to have so much hate & envy. Don't worry about Ashenafi, he's in good hands with the good shepherd Jesus (i know how much you hate this name). Worry about yourself; save yourself from the wrath of God

   Delete
  4. @ Anonymous April 15, 2013 at 11:56 PM
   እንዴት ነው ነገሩ። የአንተን አባባል በቀጥታ ብንጠቀምበት አባ ሰላማ ስም የሚያጠፋው አንተ እንዳልከው “ aba selama sound just like the brothers of Joseph in the bible. It's not healthy to have so much hate & envy. Don't worry about Tesfaye and Eskinder” ብልህ ምንድነው የሚገባህ። ስሜት ይሰጣል? ለአባ ጳውሎስ ሃውልት ሲሰራላቸው አብሮ አልነበረ እንዴ? ይገባዎታል እርስዎ “ሰማዕት ዘእምበለ ደም ኖዎት ሲላቸው አልነበረ እንዴ?

   However, you just sound like Judah. You are trying to sell this church for 30 Bucks like Judah. About Jesus name, oh man, unlike you (who know Jesus yesterday) I know Jesus and like him since i was kid so don't assume. You don't know me.
   እኔም እልሃለሁ ለኔ አትጨነቅ። ይልቅ በውሸት ለምትሰቃየው ነፍስህ እረፍት ስጣት። ከዚህች በ፴ ብር ልትሸጣት የምታስማማትን ቤተ ክርስቲያን ክፉ እጅህን አንሳላት። ከዛ ለራስህ ከጌታ ቁጣ ትድን ዘንድ ተጨነቅ።

   አሁንም እላለሁ፦ አባ ማቲያስ በነካ እጅዎት ሌሎች ሞሳኝና መናፍቅ ቅጥረኞችን ከቤተ ክርስቲያናችን ያስወጡልን።

   Delete
  5. Anonymous April 16, 2013 at 4:46 PM... I touched a nerve there didn't I? the only sense you had left.
   First off, I'm not a scavenger like you who study the in & outs of a person. Get a life
   Second, I don't care about your Aba paulos and what Ashenafi did for him during his office. My concern is only about the spiritual things.
   Third, If you know Jesus you wouldn't have so much hate for your own brother.
   "But I tell you that anyone who is angry with a brother or sister will be subject to judgment." Mt. 5:22

   Yes, you sound just like the brothers of Joseph. Yes, save yourself from the wrath of God

   Delete
 5. እናንተስ መች ታማኝ ወሬኛ ሆናችሁ ባለፈው የፓትሪያሪኩን የህይወት ታሪክ የያዘ መጽሄት ሊያሳትሙ ሲሉ ተገዱ አላችሁን ዛሬ ደግሞ ያቤተክርስቲያንን ታሪክ ነው ትላላችሁ
  አይ ገብርሄርነት/ታማኝነት/
  ቁጥር1 ውሸት በህዝብ ግንኙነት መምሪያው ስም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሕይወት ታሪክ ዙሪያ 112 ገጽ ጋዜጣና መጽሔት አዘጋጅተናልና እስፖንሰር ሁኑን ብለው ለስድስት አብያተ ክርስቲያናት ደብዳቤ ከጻፉና ገንዘብ ለመሰብሰብ አሰፍስፈው ባሉበት ሁኔታ በስማቸው ሊነገድ መሆኑን መረጃ የደረሳቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ሃላፊ በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገሪማ ፊርማ የእነእስክንድር ደብዳቤ እንዲታገድ አዘዋል፡፡ብላችሁ አስናበባችሁን
  አሁን ደግሞ ይህንን ትላላችሁ

  በደብዳቤው ላይ የቀረበው ሐተታ እንደሚያሳየው ቤተክርስቲያን እስካሁን በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በመንፈሳዊ ዘርፎች ያከናወነቻቸውን ዋና ዋና ተግባራት በተገቢው መንገድ ስላላስተዋወቀች መጽሔቱን ማዘጋጅ እንዳስፈለገ ያትታል፡

  ReplyDelete
 6. አቶዎቹ በሌብነት አጀንዳ ላይ
  አቶ ተስፋዬ ውብሸት የኢሕአዴግ አባል ነው፡፡ ድርጅቱ ራሱን ማፅዳት የሚችል ከሆነ አሁኑኑ ያፅዳ፡፡ ሌባ ተይዞ ልማት የለም፡፡ ነገ ለማሟያ ምርጫ ወይም ለፓርላማ ብሎ ካመጣው የሚዋረደው ድርጅቱ ነው፡፡ ተስፋዬማ ውርደት ቀለቡ ሆኖ እፍረት ርቆታል፡፡ የሚያደርገው ጫማ እና አልባሳት እንዲሁም ውሎው በሕዝብ እየታየ ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በስሙ የሚመዘብረውን ያጋልጠዋል፡፡ አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ ከቀበሌ በኢሕአዴግ ተባሮ የመጣ ቤተክርስቲያኒቱን ለዝርፊያ የተጠጋ በአባቱ አማካይነት የማያልቅ ሀብት ውስጥ የተዘፈቀ ነው፡፡ ይህ 11ኛን ክፍል ያላጠናቀቀ መሐይም በምን እውቀቱ የኢ.ኦ.ተ.ቤ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንደሆነ የሚያውቁት በሚንበለበል ባዶ ምላሱ የተታለሉት አቡነ ጳውሎስ ብቻ ነበሩ፡፡ አቶ ሰለሞን ካሳዬ ከአዲስ አበባ ምክር ቤት በኢህአዴግ ተባሮ የመጣ እለት በእለት ሕዝበ ክርስቲያኑን እየመዘበረ የሚገኝ ሌላው ዓይናውጣ ወሮበላ ነው፡፡ ከዚያ ቤት እጅጋየሁ በየነን ያበረረ አምላክ ምነው እነዚህን የቀን ሌቦች ችላ አላቸው፡፡ ቢያንስ ኢሕአዴግ ለዚህ ጊዜ ብቻ ቤተክርስቲያኒቱን ተጠግተው የሚመዘብሩ ኃይሎችን በማስወገድ ቤተክርስቲያኗን አይተባበርምን፡፡ እግዚአብሔር ከሌባ የፀዳች የእምነት ቤት ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. TO THE HOLY PATRIARCH,
   Your holiness,
   At first we members of a Ethiopian management group would like to congratulate you to assume the highest and blessed office in all standards. We hope your office take every action to bring the church administration back to normal. For this matter you need to remove all unnecessary individuals who are always intended for their own specific concerns.
   To that effect you need to check the human resource system and assign concerned people to rearrange who is most relevant and who is not. Other than that your journey will be dangerous.
   We want you to serve all your time with honor and respect,
   God bless you

   Ethiopia Management group

   Delete