Friday, April 26, 2013

የሺ ፍልጥ ማሠሪያው ልጥ

ከአባ ዕዝራ ዘደቂቀ እስጢፋኖስ
ሀራ ዘተዋህዶ የተሰኘው አፍቃሬ ማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ በApril 19, 2013 ባወጣው ጽሁፍ እንደተለመደው በርካታ በሀሰት የተሞላ የፈጠራ ወሬ አስነብቧል፡፡ ከዚያም ባለፈ ቤተክርስቲያንን በዘረኛ ፖለቲካው ለመከፋፈል በዘረኝነት የተለወሰ መርዙን ረጭቷል፡፡ የትግራይ ተወላጆች የግቢውን አመራር ሙሉ በሙሉ እንረከበዋለን፡፡ ከዚህ በኋላ ቤተ ክርስቲያን በትግራዎች እንጂ በአማራ አትመራም፡፡” ብለዋል በማለት ዘረኛ አመለካከቱን እግዚአብሔርን ሳይፈራ ሰውንም ሳያፍር በገሃድ ተናግሯል፡፡

የማቅ ሰዎች ፈሊጥ የጐደላቸው በመሆናቸው በሃይማኖት ሽፋን የሚያራምዱትን ፖለቲካ በቅጡ የተረዱት አይመስልም፡፡ ፖለቲካን ለማራመድ ቅድሚያ ፖለቲካን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ በጭንጫ ላይ የበቀለ ሣር ፀሐይ ሲወጣ እንደሚጠወልግ እነርሱም እንደዚያ ከመሆን አያልፉም፡፡  ዘርን ጠቅሶ ማንቋሸሽና አንዱን ወገን ከሌላው ወገን ጋር ለማጋጨት ቤተክርስቲያንን መጠቀሚያ ማድረግ ለቤተክርስቲያንና ለአገር አስባለሁ ከሚል ወገን አይጠበቅም፡፡ ለራስ የሚተርፈው ኪሳራም ቀላል አይሆንም፡፡

“የእሳት ልጅ አመድ” እንዲሉ ከጽንፈ ቀላይ የወጡ የአጋንንት ጥርቅም ጊዜ ያለፈበትን ዘውድ በተስፋ አንግበው በጨለማ የሚጓዙ ጭላንጭሎችን ማንነት ገሐድ ለማውጣት ብዙ መድከም አያስፈልግም፡፡ እንደውጫሌው ውል፣ እንደ አድዋው ጦርነት አካልን ሸጠው ለሥልጣን መቋመጥ ልማዳቸው ነው፡፡ “ድኃ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ አይድንም ነበር” እንዲሉ አይሆንላቸውም እንጂ ዛሬ ሳይሆን ከድብ ፀር ከዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ጀምሮ እስከ ፋሽስት ደርግ ድረስ “አሳውን ለማጥፋት ባሕሩን ማድረቅ” በሚል የትምክህት ፍልስፍና ይዘው መጓዝን ስራዬ ብለው ይዘውታል፡፡ ይህ ጊዜ ያለፈበት ፍልስፍናቸው ነው፡፡ ይህ የአጋንንት ጥርቅም የሆነ ማሕበር በአካሄዱ ሰውን ግራ ማጋባቱን ሥራዬ ብሎ ቢቀጥልም ከወሬ ያለፈ ፋይዳ ግን አይኖረውም፡፡ ካለፈው አይማርም አመራሮቹ አብዳን ናቸው፡፡ ባለፈው ታሕሣሥ 4/2ዐዐ5 ዓ.ም. በ5ኛውና በ6ተኛው ፓትርያርክ ላይ የማጥላላት ዘመቻቸውን ሲገልፁ “ምዕመናን ቅዱስ አባታችን ብለው በሙሉ ልብና በፍቅር የሚታዘዙት አባት ይፈልጋሉ” እንዳላሉና “ቤተክርስቲያን ዕንቁላልና ቲማቲም የሚወረወርበት ሌላ ፓትርያርክ አያስፈልጋትም በማለት እንዳልተቃወሙ ሁሉ አሁን ግን “ጅብን ሊወጉ በአያ ይጠጉ” እንዲሉ መተተኛ አካሄዳቸው አይታወቅ መስሎአቸው ከመንግሥት ባለሥልጣን ጀምሮ የቤተክርስቲያን ሰዎችን በመጠቃቀስ የተለመደውን መርዛማ የስም ማጥፋትና ከፋፋይ ዘረኛ ዘመቻቸውን አውጀዋል፡፡ እነዚህ አብዳን ርኩሣን መናፍስት እኩያን አጋንንት ከፋፋዮች ዘረኞች ትምክህተኞች ተኩላዎች ቀሳጢዎች በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጥላ ስር ተጠግተው ባካበቱት መጠን የለሽ የዘረፋ ገንዘብ አብጠው ተመልሰው ቤተክርስቲያኒቱን ትግሬ አማራ ወዘተ እያሉ ለመከፋፈልና ብሎም ለመበጣበጥ ሥራዬ ብለው ተነስተዋል፡፡ እስኪ ይህ አማራና ትግሬ የሚለው ፖለቲካ በምን መስፈርት ነው ሃይማኖታዊ ሊሆን የሚችለው? ቤተክርስቲያን ሁሉን ያቀፈች አሐቲ አይደለችምን?

እነርሱ ግን ከሥረ መሠረታቸው ስለሚታወቁ የሚያልሙት ስልጣን አይሆንላቸውም እንጂ ፕትርክናውም ሆነ ሥርወ መንግሥቱ የት እንደ ተመሠረተ ሳያውቁ ቀርቶ አይደለም፡፡ ዛሬ የበግ ለምድ ለብሰው ታሪክን በታሪክ ለመተካት ሆነ ብለው ቢታትሩም እውነተኛውንና መሰረታችን የሆነውን ታሪክ ሊያጠፉት አይችሉም፡፡ እውነተኛውን ታሪክ ዛሬ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ያለው ትውልድ ያድሰዋል እንጂ አያፈርሰውም፡፡ ለእነርሱ ግን አጉል መሮጥ መላላጥ ይሆንባቸዋል፡፡ ኧረ ለመሆኑ የትግራይ ተወላጆች የግቢውን አመራር እንረከበዋለን ያሉት መቼ ነው? ከዚህ በኋላ ቤተክርስቲያን በትግራይዎች እንጂ በአማራ አትመራም ያሉትስ መቼ ነው? እንዴትስ እንዲህ ይታሰባል? እንዲህ ያሉት ህዝብን ከህዝብ በማበጣበጥ ትርፍ እናገኛለን ብለው ከሆነ ተሳስተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቁንም የኦርቶዶክስ አማኝ አብሮ የኖረና በዚህ ርካሽ ፖለቲካ የሚነዳ አይደለም፡፡

እነዚህ ማህበረ እኩያን መለስ ብለው ታሪክን ከባለታሪኮች ቢያጠኑ መልካም ነበር፡፡ ከሣቴ ብርሃን ሰላማ ነገሥተ አክሱም አብርሃ ወአጽብሃ ወገን ሣይለዩ አገር ሳይከፍሉ ከየት ተነሥተው እስከ የት እንደደረሱ ታሪክ ዘግቦታል፡፡ ታሪክ ደግሞ ይወረሳል እንጂ ሊረሳ አይገባውም፡፡ የሺህ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ እንደሚባለው ፍቅርን እንጂ መለያየትን በመስበክ የሚመጣ ትርፍ የለም፡፡ ለነገሩ መንጋ ዝንብ ቢሰበሰብ መሶብ አይከፍትምና ሐሳባችሁ አይሳካም፡፡ ለማንኛውም ቤተክርስቲያንን የፖለቲካ አውድማ አታድርጓት፡፡ በስውር ከምትንቀሳቀሱ የሃይማኖት ለምዳችሁን አውልቁና በተኩላዊ ፖለቲከኛነታችሁ ተሰለፉ፡፡

11 comments:

 1. Endya Endya New Enje Kezelabedu Ayqer Dehna Adrgo New Mezelabed Alu. Zern Kezer Manekakes Ena Yeswun Sim Matfat Kenante Belay Alewey? Eski Yesafachut Meles Blachu Anbbut Enkwan Hay Manot Lnorachu Qerto Siweram Yesemachu Atmesilum Min Ale And Qen Sile Ewunet Tenagrachu Btalfu. Mesheim Negam Yaw Mahbere Kidusan new Yenante Yeaf Mefchachu. Yliq Yemayadrubet Bet Ayameshubet Endetebalew Begze Wede Wegenochachu Paster Daniel, Paster Tolesa < Paster Dawit Mehed New Yalebachu. Bebete Kiristian Sim Menegedu Yqirbach. Manim Yetewahdo Lji Yehone Hulu Enanten Yemayawq Yelem Ende Enante Aynun Bezer Ena Bep[oltica Yeteshefene Kalhone Beqer

  ReplyDelete
 2. Thank you brothers for your great words.we love you for your telling us the truth and realistic intellectualism. MK today went down in the hell. Thanks for Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Almighty God. Truth is truth every time with our doubt..................

  ReplyDelete
 3. ለተጠየቃችሁት የሀሰት ዘገባ/የፓትርያሪኩን ታሪክ የያዘ መፅሄት እንዳይታተም ታገደ/ላላችሁት መልስ መስጠት እንጂ ለተፃፋበችሁ እውነት መልስ ለማስመሰል የድህረገፁን ስም ለአርእስት መጀመሪያ መጠቀም አንባብያንን አያሳምንም ተአማኒነት ያሳጣችኋል።

  ReplyDelete
 4. I don't expect much from the evil MK.

  MK pretended a religious organization while trying to fulfill its political agendas.

  The holy synod should remove the letters EOTC from MK's name. This political organization doesn't belong in any church.

  MK also collects money in the name of Gedamat, fathers, churches and you name it. None of that money goes to Gedamat, fathers or churches. MK deposits all of its money in multiple foreign owned banks outside Ethiopia.

  Lots of MK members are getting frustrated by the actions taken by the leaders of MK. And many of these members are leaving the organization and helping the church directly.

  MK never gives any funds to churches. This is the bottom line. So if you are a member of MK and leave the evil organization and directly support the church.

  MK sprays hatred in our church. MK promotes violence in churches. If you have noticed, many of the churches outside Ethiopia who had lost peace, many MK members are fully participants.

  ReplyDelete
 5. nice one i like aba selama

  ReplyDelete
 6. ማህበረ ቅዱሳን ካላላችሁ ሃሳብ አይመጣላችሁም ምናፍቅ ሁሉ

  ReplyDelete
 7. አይ "አባ" አዝራ ደቂቀ ጋኔን ቢባሉ ይሻላል በስድብ ተመርቀው/ተረግመዋል ይገርማል ይህ ሁሉ ትጋት አንዲት ቤ/ክ ለማዳክም ቢቻል ለማትፋት ከንቱዎች!

  ReplyDelete
 8. Wonderful eyita newu, "leban leba kalalut Gebto yifetefetal" newuna, dege adregachhuwal.
  God Beless this writer.

  ReplyDelete
 9. አንተ ደግሞ ፍጹማ ማስተዋል ያልተሰጠህ ነህ
  ሰው ሁሉ ካንተ የበለጠ አናላይዝ ያደርጋል፡፡ ስለሚጻፈው ነገር ሁሉ
  አንተ ብቻ የምትረዳ ሌላ ሰው የማይገባው ይመስልህል? እንደነንትና…
  እሳቸው እንዲህ ብለው ነበር አሉ አለ እንጂ እኔ አልኩ አለህ
  ፓለቲካ ዘር ቅብርጥሴ በማላት ከህዝብ እና ከመንግስት ጋር
  ማህበረ ቅዱሳንን ያጋጨህ መስሎህ ነው፡፡ መሠረተ ትምህርት ብቻ
  የተማረችው እኛ ሠፈር ያለቸው ብርቄ ልብስ አጣቢዋ ከአንተ የበለጠ
  አናላይዝ ታደረጋለች፡፡ ስለዚህ ማንም አይሰማህም፡፡

  ReplyDelete
 10. ገና የማቅ ተንኮል ይጋለጣል፡፡

  ReplyDelete