Sunday, April 28, 2013

ሆሳዕና በአርያም ለወልደ ዳዊት

እናንት መኳንንት በሮችን ክፈቱ የክብር ንጉሥ ይግባ
ሆሣዕና ከጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ ጌታችን በተነገረው ትንቢት መሠረት በአህያ ላይ ተቀምጦ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ የሚታሰብበት በዓል ነው፡፡ በዓሉን ቤተክርስቲያን በሚታይ ትእምርት የምታከብረው ቢሆንም ትእምርቱ የሚወክለውን እውነት ግን ቦታ ሰጥታዋለች ማለት አይቻልም፡፡ በሆሣዕና ዕለት ቅዳሴው የሚጀመረው ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ነው፡፡ ቀዳሾች ሥጋ ወደሙን ከቤተልሔም ይዘው ወደመቅደስ የሚገቡት  እንደወትሮው በምሥራቁ በር ሳይሆን በወንዶች መግቢያ ነው፡፡ መዘምራን በቀኝና በግራ ሥጋ ወደሙ የያዙትን ቀዳሾቹን አጅበው እየዘመሩና ምንጣፍ እያነጠፉ ይገቡና ቅድስቱ ላይ ቆመው፣ በመዝሙረ ዳዊት “እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ። ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? እግዚአብሔር ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ እግዚአብሔር ነው፥ በሰልፍ ኃያል።” (መዝ. 23፡7-8) የሚለውን ክፍል ዲያቆኑና ቄሱ ሕዝቡም እየተቀባበሉ ያዜማሉ።

ዲያቆኑ “አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት (እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ)” ይላል
ቄሱ ከመቅደስ ሆኖ “መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት (ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?) ሲል ይጠይቃል።
ዲያቆኑም “እግዚአብሔር አምላከ ኃያላን ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት (ይህ የክብር ንጉሥ የኃያላን አምላክ እግዚአብሔር ነው)” ብሎ ይመልሳል፡፡
በዚህ ጊዜ ቄሱ “ይባእ አምላከ ምሕረት ይባእ ንጉሠ ስብሐት (የምሕረት አምላክ ይግባ፤ የክብር ንጉሥ ይግባ) ይልና መጋረጃው ተከፍቶ ቀዳሾቹ ሥጋወደሙን ይዘው ወደመቅደስ ይገባሉ፡፡

ይህ ትእምርታዊ ሥርዓት እጅግ ደስ ይላል፡፡ ሥርዓቱ የሚያመለክተው እውነታ ተግባራዊ ካልሆነ ግን ትእምርቱና ሥርዓቱ ብቻውን አይበቃም፡፡ ከትእምርታዊ ስርዓቱ ባሻገር የመቅደሱ መጋረጃ ብቻ ሳይሆን የምእመናን ልብ ሊከፈትለት የሚገባው የምሕረት አምላክና የክብር ንጉሥ በእያንዳንዳችን አንቀጸ ልብ (የልብ ደጅ) ላይ ቆሟል፡፡ ለሆሳዕና “ይግባ” ተብሎ የመቅደስ መጋረጃ ቢከፈትም፣ ዘወትር ግን በቤተክርስቲያን እርሱ ብቻ እንዳይነግሥ ክብሩ ለሌሎች እየተሰጠ ቀድሞ ከምኩራብ እንደተባረረ ዛሬ ደግሞ የእርሱ ሙሽራ ከሆነችው ቤተክርስቲያን በልዩ ልዩ ስልት ተመሳሳይ ዕጣ እየገጠመው ይገኛል፡፡

ቤተክርስቲያን የማንም አይደለችም፤ የክርስቶስ የብቻው ሙሽራ ናት፡፡ ይሁን እንጂ እንደሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዛሬ ያለችው ቤተክርስቲያን በገዛ ደሙ የዋጃትንና ቤዛ የሆነላትን ሙሽራዋን ክርስቶስን ተለይታው እንደሚዜ ከሚቆጠሩት ጋር (“ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።” ዮሐ. 3፡29 የተባለውን ማጣቀስ ይቻላል) በፍቅር በመክነፍ ሙሽራዋን እያስቀናችው በሯን ዘግታበት ይታያል፡፡  ነገር ግን ወረት የለሹ የፍቅር አምላክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እርሱን ከውስጧ አስወጥታ ሌሎችን እያወደሰችና እያመለከች ብትተወውም ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን “እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።”  (ራእ. 3፡20) እንዳለ፣ ዛሬም ለእኛ ቤተክርስቲያን ተመሳሳይ መልእክት እያስተላለፈ ነው፡፡ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን “ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም” ስትል ጌታን ጭምር እንደተወችውና ከውስጧ እንዳስወጣችው ግልጽ ነው፡፡ ጌታም በደጅ መቆሙንና የሚከፍትለትን እየጠበቀ መሆኑን ነው ለቤተክርስቲያኗ የተናገረው፡፡ ዛሬስ ጌታ በቤተክርስቲያናችን አለ ወይ?

ስለዚህ በሆሳዕና ዕለት የሚታየው ትእምርታዊ ሥርዓት የመጨረሻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ በመጋረጃው መከፈት የተገለጸው ትእምርት የእያንዳንዱ አማኝ ልብ እንዲከፈት በማድረግ ወደእያንዳንዱ አማኝ ልብ ጌታ እንዲገባና በውስጡ እንዲኖር በመደረግ ምሳሌው ከአማናዊው መገናዘብ አለበት፡፡ ዛሬ ጌታ የሚገኘው በልባችን ውስጥ ነው ወይስ በደጅ? በልባችን ውስጥ ያለውስ ማነው? “ዛሬም አለሽ ከልቤ?” ያለው ዘማሪ ማን ነበር?

ስለዚህ አባቶቻችንን ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ምእመናንም ሁላችሁ እባካችሁን የልባችሁን በር በደጅ ቆሞ ለሚያንኳኳው ጌታ ክፈቱለት፡፡ በትእምርት ያሳያችሁትን ሥርዓት በተግባርም የልባችሁን በር በእምነት በመክፈት የክብርን ንጉሥ ወደልባችሁ አስገቡት፡፡ እርሱ ብቻ በልባችሁ ላይ ይንገሥ፡፡ በልባችሁ ሌላ የምታነግሡት አይኑር፡፡ ከእርሱ በቀር አዳኝ፤ ከእርሱ በቀር ጌታ፣ ከእርሱ በቀር መሓሪ የለምና፡፡ ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ  ክርስቶስ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።” (ዮሐ. 14፡23) ያለውን ቃል እናስብ፡፡ በቅድሚያ ጌታን መውደድ አለብን፡፡ ጌታን መውደዳችን ደግሞ ቃሉን በመጠበቃችን ይታያል፡፡ እንዲህ ካደረግን የአብና የወልድ የመንፈስ ቅዱስም ማደሪያ እንሆናለን፡፡ ታዲያ ስንቶቻችን ጌታን ወደ ልባችን ለማስገባት ተዘጋጅተናል?

ምልከቱ ጌታን መውደዳችን ነው፡፡ ቃሉን በአክብሮት መቀበልና ለእርሱ ትልቅ ስፍራ መስጠት ዋናው ነገር ነው፡፡ እኛ ግን እኮ ለመጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ ባለመሆንና ለባህላችን በሚስማማ መንገድ እስከመተርጎም ደርሰን ለጌታ ያለን ፍቅር ምን ያህል የወረደ እንደ ሆነ አሳይተናል (በ2000 ዓ.ም. የታተመው መጽሐፍ ቅዱሳችን ለዚህ ምስክር ነው፡፡ “ስለእናቱ ምልጃ” ብለን ለዮሐንስ 2 የሌለ ርእስ የሰጠነው ለቃሉ ሳይሆን ለልማዳዊ ትምህርታችን ታማኝ በመሆን አይደለምን?)፡፡ ነገር ግን ጌታን እንወደዋለን ወይ? ለጌታ ያለን እውነተኛ ፍቅር ለቃሉ በመታዘዝ የሚለካ መሆኑ ባይካድም፣ ብዙዎቻችን ግን ኢየሱስ የእኛ እንዳልሆነና የሌሎች እንደሆነ እስከማሰብ ደርሰንና “የእኛ” እና “የእነርሱ” ኢየሱስ እያልን አንዱን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደመክፈልና በፈጠርነው ቡድንተኛ ስሜት ለእርሱ ያለንን ጥላቻ እየገለጽን እንደሆነ በልዩ ልዩ መንገድ ስንገልጽ ኖረናል፡፡ ከሰይጣን ባላነሰ ሁኔታ ኢየሱስ የሚለው ስም ሲያስበረግገን ነው የኖረው፡፡ መጽሐፍ ግን “ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን።” (1ቆሮ. 16፡22) ይላል፡፡ ዲያቆኑ በቅዳሴ ጊዜ የጳውሎስን መልእክት ከማንበቡ በፊት የሚያሰማው ዐዋጅም ይኸው ነው፡፡

ስለዚህ የወደደንን ጌታ ከመውደድ የበለጠ ነገር ስለሌለ ቡድንተኞች ሲግቱን የኖሩትን እርግማን እምጪ ክፉ መርዝ ልንተፋና እነርሱ የሚሉንን ሳይሆን መጽሐፍ የሚለንን በመቀበል እስከሞት የወደደንን ጌታ ልንወደው፣ የልባችንን በር ልንከፍትለትና በውስጣችን እንዲኖር ልንፈቅድለት ይገባል፡፡

በዚህ የሕማማት ሳምንትም ትእምርታዊ የሆኑ ልዩ ልዩ ሥርዓቶችን በመጠበቅ ላይ ብቻ ከምናተኩር ልናስበው የሚገባውን የሕማማቱን ጌታ ብቻ በማሰብ እርሱ ስለእኛ መዳን የከፈለውን ክቡር ዋጋ እያሰላሰልን በፍቅሩ ገመድ ልንታሰርና እስከመጨረሻውም ልንከተለው፣ እርሱን ብቻ በእኛ ላይ ጌታ እና አዳኝ አድርገን ልንሾመው፣ ሁለንተናችንንም ልናስረክበው ይገባል፡፡ አሊያ ሥርዓት ፈጻሚዎች ብቻ ሆነን መቅረታችን ነው፡፡ ሥርዓት ብቻውን ደግሞ ወደዘላለም ሕይወት አያስገባንም፡፡
“እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ። ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? እግዚአብሔር ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ እግዚአብሔር ነው፥ በሰልፍ ኃያል።” (መዝ. 23፡7-8)

7 comments:

 1. “ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን።” demo yemin ergiman new? sew mebit yelewum ende?

  ReplyDelete
  Replies
  1. seyitan becha new geta eyesusin yemaywed, selezih seytan demo yeteregeme new. erso seytan newot?

   Delete
  2. men we are tired of your " teret teret" .Open your eyes and read our books ,specially Kidus Bible. Then your suggestion willnot be senseless and useless.

   Delete
 2. woy gud, yegna "medhanialem " ke "Eyesus" bemn yansal? Eyesus kalalachihu atamnum teblen ke seytan gar yetenetsatsernew? This is orthodox church trend to call either Lord, saviour Jesus christ or Medhanialem, Amanuel etc rather than " Eyesus" only. Nothing special how we call him, rather God wants our devotion.In bible usually peter, John called him " Getachin, medhanitachin Eyesus christos like what orthodox says. Rather paul every where says Eyesus. There is also d/c among apostles in calling him.yihe ye tsidk na kunene megelecha adelem. negeru pentewoch Eyesus kale tsadk, medhanialem kale yemayamn endeza new yemtasibut. poor people.

  ReplyDelete
 3. God bless you who wrote the article.
  If anybody have a problem with this article he should ask himself if he a true follower of Christ.
  It is ok if someone is not a Christian he can argue with this article otherwise there is no ways anyone claim a Christian and have a problem with this article. The name of Christian came from the follower of Christ. Do we believe the Ethiopian orthodox is follower of Christ or Christian? For long time we never know the Name of Jesus Christ as if we afraid to call his name but know thank God we read the Bible and the whole Bible is talk only about Jesus Christ especially the new testament the whole thing is about Christ. God the father the son and Holy Spirit help us to open our heart

  ReplyDelete
 4. The name of Jesus is above of all name.His name has a power.Do not be afiead to call the name Jesus.Jesus Jesus Jesus above all. Thank you.

  ReplyDelete
 5. gata eyesus yebarekeh yehen yetafke sew ewnet new medan be Jesus bech new

  ReplyDelete