Monday, April 29, 2013

አባ አብርሃም እና ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ ያለውን የሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ

                        ምንጭ፡- http://awdemihreet.blogspot.com/
 በማኅበረ ቅዱሳን አይዞህ ባይነት የአሜሪካውን ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል አላስረክብም ብለው የነበሩት አባ አብርሃም የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ፡፡ ይህ በቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ፊርማ የወጣው እና አድራሻውን ለአባ አብርሃም ያደረገው ደብዳቤ እንዳስታወቀው አባ አብርሃም ሀገረ ስብከቱን በዝውውር ለቀው ከወጡ በኃላ የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት አላስረክብም ማለታቸው ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡
አባ አብርሃም ቤተክርሰቲያን አንዲት መሆንዋን መረዳት ከብዷቸው እና እሳቸውን ለማዘዝ ሙሉ ስልጣን ያለውን ቅዱስ ሲኖዶስ ተጋፍተው ላለፉት ሁለት አመታት የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት አላስረክብም በማለት በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሽፍታ ሠራዊት ማስፈራቸው አስገራሚ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ እኚህ ጉድ አያል ቅበት የሆኑት ጳጳስ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሳካው እሺ ብሎ በመታዘዝ መሆኑ ከዲቁና እስከ ጵጵስና ድረስ አለመረዳታቸው በብዙዎች ዘንድ የሚያስተዛዝብ ሆኗል፡፡
በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ለምን ተዘዋወርኩ በሚል ሂሳብ የሲኖዶሱን ውሳኔ አላከብርም ቁልፍም አላስረክብም በማለት የመጀመሪያው የሆኑት አባ አብርሃም ቁልፍ ላለመስረከብ እና የሲኖዶሱን ውሳኔ ላለማክበር እንደ ምክንያት የሚያቀርቡዋቸው ቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ካረፉም በኃላ በተተኪው ፓትርያርክ በአቡነ ማትያስ ጊዜም ቋሚ ሲኖዶሱ ሕገ ወጥነታቸውን ጠቅሶ ቁልፍ እንዲያረክቡ መወሰኑ በፊትም ሆነ አቡን የቤተክርሰቲያንን ውሳኔ ተጋፍተው በሙሉ ስጋዊ አቋም ላይ ያነበሩትም ሆነ ያሉት አባ አብርሃም መሆናቸውን ስለሚገልጽ ውሳኔው አባ አብርሃምን ትልቅ ኃፍረት ያከናነበ  ሆኗል፡፡
የአባ አብርሃም የልብ ወዳጅ  የሆኑት እና እንደ አባ አብርሃም ሁሉ በተለይ ለማኅበረ ቅዱሳን “ቅዱስ” አባት የሆኑት አባ ኤዎስጣቲዎስ የሲኖዱሱን ውሳኔ ተጋፍተው እምቢኝ አሻፈረኝ በማለት በማኅበረ ቅዱሳን አይዞህ ባይነት ሚናው ያልለየ ሽፍትነት ጀምረው የነበረ ቢሆንም መጨረሻቸው ግን ውርደት መሆኑን ሰሞኑን ከሚማሩነት ትምህርት ቤት የተባረሩበት ምክንያት አስረጅ ሆኗል፡፡ አባ አብርሃምም ከአባ ኤዎስጣቴዎስ የተሻለ ሰብዕና ባይኖራቸውም ዘግይተውም ቢሆን የሲኖዶሱን ውሳኔ በከፊል ለማክበር መወሰናቸው እንዲህ ካለው ውርደት ሸሽጓቸዋል፡፡ አሁንም ውሳኔውን ሙሉ በሙሉ ለማከበር ካልወሰኑ እና ሀገረ ስብከቱን ያስወረሩትን የድርጭት መንጋ አስወግደው ቁልፉን ለአቡነ ፋኑኤል ካላስረከቡ እሳቸውም ቀጣይ ውርደት እንደሚገጥማቸው ብዙዎች የሚስማሙበት ሀቅ ነው፡፡
አባ አብርሃም ከተነሱ በኃላ የሲኖዶሱን ውሳኔ እና የደብዳቤ ልውውጦች የሚዳስሰውን ዝርዝር ታሪክ ወደፊት እናቀርባለን፡፡

12 comments:

 1. Hale Luya, Hale Luya, Hale Luya.

  ReplyDelete
 2. The End of MK is coming pretty soon

  ReplyDelete
 3. elelelelelelelle

  ReplyDelete
 4. አውደ ምህረት እንኳን ደህና መጣሽ ባለሁበት አካባቢ ላሉ የማቅ ሰዎች ምን ያህል ሕመም እንደነበርሽ አውቃለሁ፡፡ ተመልሳችሁ ስራ መጀመረችሁ ደስ ያሰኛል፡፡ በርቱ በርቱ በርቱ

  ReplyDelete
 5. አሁን አቅርቡት እንጂ! የምን ማዋል ማሳደር ነው?

  ReplyDelete
 6. አይ የቤተ ክርስቲያን ጉድ ብዛቱ፤ ለመሆኑ ማንን ይሆን ሽፍታ ብለህ የምትጠቅስ "በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሽፍታ ሠራዊት ማስፈራቸው አስገራሚ ሆኖ ሰንብቷል" ያልከው ማንን ነው? አባቶቻችን ከጥንት በመንፈስ ቅዱስ በመመራት የቤተ ክርቲያናችንን ሕግ ወስነው የሰጡን ቃለ አዋዲ ይከበር፤ የቤተ ክርቲያናችንን ቀኖና እና መዋቅር ይጠበቅ ብሎ በቆራጥነት የቆመን ምዕመን "ሽፍታ" አልከው?
  በሀገረ ስብከቱ መንበር ላይ ያሉ ሊቀጳጳስ ወደ ሌላ ሀገረ ስብከት በቅዱስ ሴኖዶስ ትዛዝ ሲቀየሩ ተተኪው አባት በቅዱስ ሴኖዶስ ትዛዝ ወደተላኩበት ሀገረ ስብከት መንበር ጵጵስና አይደለምን መግባት ያለባቸው? ታዲያ አቡነ ፋኑኤል የገቡት ወደ ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን አይደለም ወይ የገቡት::
  ምዕመናን በጉጉት እየጠበቃቸው ካለበትና በኢትዮጵያ ቅዱስ ሴኖዶስ ስር በሚተዳደር አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንኳን ገብተው ቅዱስ ሴኖዶስ የላከኝ ኣባታችሁ እኔ ነኝ ከዛሬ ጀምሮ አብረን እንሰራለን ያሉት የልም፤ ይልቁንስ ቃለ አዋዲን በመጣስ በኢትዮጵያ ቅዱስ ሴኖዶስ ስር በሚተዳደሩ ቤተ ክርስቲያናትን የሰብካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላትን ወደ ገለልትኛ ቤተ ክርስቲያን ለቃለ አቃዲ ከማይታዘዙ የቤተ ክርስቲያን ቦርድ አባላት ጋር ለስብሰባ ነው የጠሩ::
  አቡነ ፋኑኤል ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ አንድም ቤተ ክርስቲያን በቃለ አዋዲ የሚመራ በአሜሪካ ምድር የለም ብለዋል ያ ትክክል አይደለም፤ ወደ መንበራቸው ሳይገቡ ምን አይተው ይህንን አሉ። ሌላው ወደ መንበረ ጵጵስናው ላለመግባት ያቀረቡት ምክንያት የተቀበለኝ የለም የሚል ነው። እርሳቸውን የላካቸው ቅዱስ ሴኖዶስ ነው፤ የላካቸውም የአቡነ አብረሃምን ሀገረ ስብከት (የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢውን ሀገረ ስብከት) በመረከብ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያሉትን ምዕመናን እንዲጠብቁ እና በገለልተኛ ስም ቅጡን ያጡትን ካህናትና ምእመናንን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ስር እንዲገቡ እንዲያደርጉ ነው። የሆነው ግን የተገላቢጦሽ ነው፤ ታዲያ ሽፍታው ማን ይሆን፤ አባታቸውን የሚጠባበቁ ልጆች ወይስ የቅዱስ ሴኖዶስን ትዛዝ ያላከብረና ወደ ልጆቹ አልመጣም ያለ አባት???
  ብዙ የምለው ነበረኝ ግን ለቅዱስ ሴኖዶስ ልልከው ስለፈለኩ እዚህ ላይ ላቁም።
  አባ ሰላማዎች ቅዱስ እግዚአብሔር ሰላምን እንድትሰብኩ ብርታቱን ይሰጣችሁ። እኔ የምትጠሉትና የምትፈሩት ማህበር ማ.ቅ አይደልሁምና እንዳሳሳቱ እባካችሁ።
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Aye------------mk gena gena maheberun alawukewum belehe yemitikedebet kene yimetal. Eyadere eyewale mk tenkoluna kefu seraw eyetegelete simeta yigebahal. ahun enkuan ye-Egziabeherne sewoch lematalel yesetekewu asteyayet mataleya newu. libona yistehe.

   Delete
 7. ልብ ምን ይመኞል አሉ መጀመሪያ የጠቀሰካችው አባት ሴኖዶሰን ይቀበላሉ
  ዉ ይ?

  ReplyDelete
 8. ጊዜና እድሜውን ይስጠን እንጂ እንደ አባ ኤወስጣጤወስ ቅሌት፤ አቡነ ፋኑኤልም የሙስናና ከቤተ ክርስቲያን ንብረት ጋር የተያያዘ ቅሌት በቅርቡ በኢንተርኔት ይለቀቃል። ምናልባት ቅዱስ ሴኖዶስ ሁኔታውን ተገንዝቦ ተግሳጹን ይሰጣቸዋል ብለን እንጠብቃለን። ቤተ ክርስቲያን በጣም ብዙ መንፈሳዊ አስተዳደር ብልሽትን ለማጽዳት ከብፁዕ አቡነ ማትያስ ትልቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ትጠብቅባቸዋለች።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Seytan mk alekelet, aba abrehamm kengedihe ayigegnum.
   Abune Fanueal gene the true Father selehonu geta yitebkachewal. seme lematfatma enaneten man yikedemachual. Menem betelu menem, esachew ewunetegna Abat nachew. Seytanochen Egziabeher yigesesachu.

   Delete
 9. ha ha ha Mahibere Kidusan mechem mechem behone ayefersem mekneyatum esum betekrestiyan selehone . betam azenalehu endasekayachu awkalehu medre tehadiso hula Mahibere kidusan ye betekrestiyan zeb new!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete