Thursday, April 4, 2013

አቶ ደስታ በጉቦ ቅሌትና ሊቀጳጳስን በመሳደብ ከሀላፊነቱ ተነሳ

በአቡነ ህዝቅኤል ላይ ክስ መስርቷል

አለችሎታው ለማቅ በነበረው ቅርበት ብቻ የምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጸሀፊ ሆኖ የተመደበው አቶ ደስታ በጉቦ ቅሌትና ሊቀጳጳስ አቡነ ህዝቅኤልን በስልክ “ባሪያ” ብሎ በመሳደብ ከሥራው ሀላፊነት መነሳቱ ተገለጸ፡፡

ደስታን በቅርበት የሚያውቁት የሊቀ ህሩያን ያሬድ ከበደው የሚይዙትን መኪና በማጠብ የቤተክህነት ስራ መጀመሩን ይገልጻሉ፡፡ ወደቤተክህነት ግቢ ለመግባት ምክንያት የሆነውም ለድግስ የሚሆን ጐላ ብረት ድስት ተሸክሞ መምጣቱ ነበር፡፡ በዚህ አጋጣሚ እግሩን ያስገባው አቶ ደስታ ቀስ በቀስ ወደቢሮ ስራ በመዘዋወር በሰበካ ጉባኤ መምሪያ ውስጥ ስራ አግኝቶ የልደት፣ የጋብቻ ….. ሰርተፌኬት ለማሰራት የሚመጡትን ገንዘብ መቀበል ጀመረ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ  ማህበረ ቅዱሳን በቤተ ክህነት ውስጥ የሚፈልጋቸውን ደብዳቤዎች በህገ ወጥ መንገድ ከመዝገብ ቤት እያስወጣ የደጀ ሰላምን ጽሁፎች ለሚያዘጋጀውና አሁን ወደሀራ ለተገለበጠው ለአሉላ ጥላሁን አዘውትሮ መስጠት መጀመሩንና ለዚህም የማኅበሩ ዋና ጸሀፊ አቶ ሙሉጌታ የኪስ ገንዘብ ይመድብለት እንደነበር ምንጮች ይገልጻሉ፡፡

ገንዘብ ካገኘ ምንም ከማድረግ ወደኋላ የማይለው ደስታ የቀድሞው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ቆሞስ ሠረቀ ብርሃንን ማህበሩ ሲከሳቸው ምስክር ሆኖ የቀረበው ተመሳሳይ አላማ ካለው ከህሩይ ባየ ጋር እንደነበር ይታወሳል፡፡ በጊዜው ዳኛው ለአቶ ደስታ ጥያቄ ሲያቀርቡ “ማህበረ ቅዱሳን በምን ስር ነው የሚገኘው?” ብለውት ነበር፡፡ አቶ ደስታም “በሲኖዶስ ስር ነው” ብሎ ዋሸ፡፡ ዳኛውም ደንቡን ሲመለከቱ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር ነበር የሚለው፡፡ የሀሰት ምስክር ይህ ነው፡፡

ከዚያ በመቀጠል ደስታ ገንዘብ ተከፍሎት በማኅበሩ አዘጋጅነት በስሙ “የሰባኪው ህጸጽ” የሚል ውጤት አልባ መጽሐፍ በእነ መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ ላይ ያጻፈ ሲሆን፣ ደስታ መጽሐፉን ሊጽፈው ቀርቶ ስሙን መጻፍ እንኳን እንደሚከብደው እየታወቀ ማኅበሩ ግን ለርካሽ አላማው ግለሰቡን ተጠቀመበት፡፡ ስሙ የጠፋው መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ ክስ መስርቶ መጽሐፉ ሳይሰራጭ ታግዶ ደስታም በወቅቱ ታስሮ በ5 ሺህ ብር ዋስ መፈታቱ የሚታወስ ነው፡፡ የዋስትናውን ብር የከፈለው ማህበሩ ነበር፡፡ ክሱ ቀጥሎ ደስታ ጥፋተኛ ተብሎ ሲበየንበት እዚያው አራዳ ምድብ ችሎት ላይ የአዞ እንባ አፍስሶ ዳኛውን ተንበርክኮ በመለመን የልጅ አባት እንደሆነ በማስረዳት እስራቱ በ2 ዓመት ገደብ ተለውጦለት ተፈታ፡፡

ከዚህ በኋላ ደስታ ሰከን ቢልም ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ ማኅበሩ በጣሊያን ሰፈሩ ዱርዬ በተስፋዬ ውብሸት አማካኝነት ቤተክህነቱን ሲያምሱት እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለአራት ሲከፈል ቀድሞ ለሰራው ውለታ የምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፀሀፊ ሆኖ በተስፋዬ ውብሸት አማካኝነት ተቀጠረ፡፡ ደብዳቤ እንዴት እንደሚጽፍና እንደሚመራ ሳያውቅ ፈፅሞ መጻፍ የማይችል ሆኖ ሳለ ይህን ቦታ ማግኘቱ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል፡፡ በዚሁ ሀገረ ስብከት ተመድበው የሚሰሩና ከእርሱ ጋር ፈፅሞ  የማይነጻጸሩና ብቃት ያላቸው ሰራተኞች ነበሩና፡፡
ለምሳሌ፦ መምህር ባህሩ  በቴዎሎጂ ዲፕሎማ፣ አሁን ለዲግሪ እየተማረ ያለና በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው፡፡
              መምህር አሉላ በቴዎሎጂ ዲግሪ ያለው
              መምህር ሀይሉ ጉተታ በቴዎሎጂ ዲግሪ ያለው
ወዘተ እያሉ ጨዋውን ደስታን ፀሀፊ አድርገው ማስቀመጣቸው ቤቱ ሰው የሌለበት መሆኑን ከማሳየቱም በላይ ማህበሩ ጉዳዩን ያስፈፅምለት እንጂ እምነቱን እንኳን እንደማይጠይቅ በጠንቋዩ ህሩይ ባየ ማየት ይቻላል፡፡

ደስታ ይህን ቦታ ከያዘ ጀምሮ አይን ያወጣ የገንዘብ ዝርፊያ ውስጥ ነበር የገባው አስቀጥራችኋለሁ እያለ ከተለያዩ ሰዎች የወሰደው ገንዘብ ሰማይ ሲደርስ ነበር፡፡ ደስታ የተጋለጠው ገንዘብ የወሰደበት አንድ ሰው አቡነ ህዝቅኤል ቢሮ ቁጭ ብሎ ለደስታ ከደወለና ላውድ ላይ አድርጎ “እንዲያው ሊቀጳጳሱ እሺ ይሉ ይሆን?” ሲለው ደስታም “ምን ይሄ ባሪያ እያለ መስራት አልቻልንም” ሲል አቡነ ህዝቅኤል ከሰሙ በኋላ ነው ተብሏል፡፡ ሌሎች ሶስት ሰዎችም 15 ሺህ ብር ተቀብሎናል በማለት አሁን ክስ ሲያቀርቡ ወዲያው ከቦታው ላይ እንዲነሳ ተወስኖበታል፡፡

ሌላው አስቂኙ ድራማ የደስታ የግል ማህደር ሲታይ ምን እንደተማረ የት እንደ ተማረ ስንተኛ ክፍል እንደ ሆነ ካለመገኘቱ በላይ አንድ ነገር ብቻ ተገኝቷል፡፡ የሶስት ቀን ሴሚናር መካፈሉን የሚገልጽ መረጃ፡፡ ደስታ ፍፁም አለመማሩ የሚታወቀው የራሱን የመልክ ቀለም እንኳን ሳያውቅ አቡነ ሕዝቅኤልን ባሪያ ብሎ መሳደቡ ነው፡፡ ምክንያቱም ቀለም ማወቅ መማርን አይጠይቅም ነበርና - ማየት ካልተሳነ በቀር፡፡

አምላክ ሁሉንም በየጊዜው እየገለጠው ነው እንጂ ማህበረ ቅዱሳን በእነዚህ አሳፋሪ ሰዎች መጠቀሙም ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ለምን ብለው ስለማይጠይቁና እንደፈለገ ስለሚጋልብባቸው ነው፡፡ ለምን ለማለት መማር ማወቅን ይጠይቃል፡፡ ለነገሩ እነሱ ባያፍሩ ሌሎች ያፍሩላቸዋል፡፡ የሀገራችንም ተረት “ሞኝ ባያፍር ዘመዶቹ ያፍራሉ” አይደል የሚለው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሃላፊነቱ መነሳቱን ተከትሎ ደስታ በአቡነ ህዝቅኤል ላይ ክስ መመስረቱ ተሰምቷል፡፡ በጋጠ-ወጥነት የኖረና ያደገ ሰው ተግባሩ አይለቀውምና ደስታ ክስ በመመስረት ለአቡነ ሕዝቅኤል መጥሪያ ይዞ በመምጣቱ ብዙዎችን አሳዝኖአል፡፡ ከሃላፊነት መነሳትና ወደሌላ ክፍል መቀየር በእርሱ አልተጀመረምና “ደህና አድርጌ ከምግጥበት ቦታ ለምን ተቀየርኩ” በሚል ክስ መመስረቱ የሰውዬውን ማንነት ይበልጥ ግልጽ አድርጓል፡፡

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከየአድባራቱ እሱን የተመለከቱ ክሶች ሲበረክቱባቸው ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ዝርዝር አድርገው ጥፋቱን በደብዳቤ የላኩ ሲሆን፣ ይህን ደብዳቤ አቶ ተስፋዬ ውብሸት ለደስታ መስጠቱን እና ደስታም ክስ ለመመስረት መብቃቱ ታውቋል፡፡

በደህንነት ስም ተስፋዬ ያሰማራቸው ግለሰቦች አቡነ ሕዝቅኤልና አቡነ ፊልጶስን ያነጋገሩ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ እነዚህ ኪራይ ሰብሳቢ ደህንነት ነን ባዮች በማያገባቸውና በማይመለከታቸው ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡ በዚህ አይነት ነገ ቅዳሴው በእነ እገሌ ካልተቀደሰ ላለማለታቸው ምን ዋስትና አለ ሲሉ ታዛቢዎች ይጠይቃሉ፡፡ ይህን ተከትሎ በአቡነ ህዝቅኤል ጥሪ አንድ የደህንነት ሃላፊ ጠቅላይ ቤተክህነት የመጣ ሲሆን በዚህ ጊዜ ተስፋዬ ያሰማራው ደህንነት ነኝ ባይ ቅጥረኛ የት እንደደረሰ አልታወቀም ይላሉ ምንጮች፡፡

አቡነ ሕዝቅኤል እና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በአቶ ደስታ ቅያሬ ላይ የተነጋገሩ ሲሆን ፓትርያርኩ በቂ መረጃ ስለቀረበላቸው ቅያሪውን አምነው ነገር ግን በጾም ባይቀየር ጥሩ ነው ሲሉ የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ይሁን እንጂ አቡነ ሕዝቅኤል “ደስታ ተቀምጦ የሰውን ሀዘን ከማባባስ በዚህ ወቅት መቀየሩ የብዙዎችን እንባ ያብሳል” ሲሉ መልሰውላቸው በዚሁ ተስማምተዋል፡፡

እንደታማኝ ምንጮቻችን ከሆነ ተስፋዬ ውብሸት ደስታን ተሯሩጦ የምዕራብ አዲስ አበባ ጸሐፊ ያደረገበት ምክንያት ደስታ በሙስናና በጉቦ ከሚያገኘው ገቢ ላይ 5 ከመቶ ለእሱ ፈሰስ እንዲያደርግ ስምምነት አድርገው ነበር፡፡ ክሱን ተከትሎ አቡነ ሕዝቅኤል የጣሊያን ሰፈሩን አደገኛ ቦዘኔ ተስፋዬን እቤታቸው በመጥራት “እስከ ዛሬ ድንጋይ አስወረወርክብን አሁን የምንፅፈውን ደብዳቤ እያወጣህ ታስከስሰናለህ” በማለት የወቀሱት ሲሆን፣ “ሲኖዶስ አንስቶህ ሳለ እኛ መልሰን ማስቀመጣችን ትክክል አልነበረም ማለት ነው” ሲሉት “አሁኑኑ እለቃለሁ” በማለት መመለሱ ታውቋል፡፡

አቶ ደስታ ከውሻ ጋር ታግለውና ለፍተው ተምረው ስራ ለመቀጠር ከሚቀርቡት ካህናት ዲያቆናትና መሪጌታዎች ላይ በጭካኔ ጉቦ በመቀበል ቅሌት ከሃላፊነቱ ተነስቶ ወደ ጳውሎስ ኮሌጅ በጸሐፊነት ቢሄድም የኮሌጁ ማህበረሰብ ደስታን አንቀበልም በሚል ከአሁኑ ተቃውመውታል ተብሏል፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት በዚሁ ኮሌጅ ለመማር ሲሞከር ምንም ዓይነት እሱነቱን የተመለከተ መረጃ ስለጠፋ ብዙ ታላላቅ አባቶችና ጳጳሳት፣ አሁን ድረስ በታላላቅ ቦታዎች በአስተዳዳሪነት የተመደቡ አለቆች የወጡበትን ትምህርት ቤት ምንም የትምህርት ደረጃ የሌለውን ደስታን ተቀብሎ ማስተማር ኮሌጁን ማዋረድ መሆኑን ተገንዝበው አልተቀበሉትም፡፡ አሁን ይባስ ብሎ እርሱን በጸሐፊነት መላካቸው ለኮሌጁ ካላቸው ዝቅተኛ ግምት ጋር ይያያዛል ይላሉ፡፡

በተዘፈቀበት የጉቦ ቅሌት ነገ ክስ ቢመጣበት መውጫ የሌለው ደስታ ጩኸቴን ቀሙኝ በማለት እስከ ዛሬ ተደርጐ የማያውቀውን በጥፋቱ ወደፈለጉት ቦታ ማዘዋወር መብታቸው የሆኑ ኃላፊዎችን ለመክሰስ መጥሪያ ማምጣቱ አጠያያቂ ሆኗል፤ የቤተ ክህነት ሠራተኞች ሌሎችም ጳጳሳት አቡነ ሕዝቅኤል እንደወሰዱት ዓይነት ፈጣን እርምጃ በሙስና በተሠማሩት ላይ ቢወስዱ መልካም እንደሆነ እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡

በተለይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ከመንግሥት አላማና ተግባር ውጭ በካድሬነት ስም እየበጠበጡና እያጣሉ ያሉትን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊውን አቶ እስክንድርንና እርሱ እየተጠቀሙበት ያለውን አቶ ተስፋዬን ተገቢ የሆነ እርምት ሊወሰዱባቸው ይገባል እያሉ ነው፡፡


9 comments:

 1. Kerestos berehan bemehonu, bechelema yemiserawun ye-mk ne yediyabilosn sera eyegelete yehedal. Temesgene yegna Geta tageso,tageso, siyametaw endihe newu. mk(ms) lebe yistachehu.

  ReplyDelete
 2. Desta malte besewe enba elelta yemiyasema kenetu sew new. enkuwan tenesa!!

  ReplyDelete
 3. ine imilewu inanitem christian tibalalachihu? christinas min malet newu? hule and aynet wore, Medihaniyalem yirdachihu. Ere hizib iyetefa newu sibiket sibeku yehe ayawatam. Egizabiher libonachihun yimelisewu.

  ReplyDelete
 4. Ere Wisht abzachihu, MK hone sew yimemdib? Bedenb bota yizal belunga

  ReplyDelete
 5. MK is evil. Unfortunately, 95 percent of its members don't know that MK has hidden political and business agenda. The good thing the eyes of those 95 percent innocent MK members are opening and beginning to see the true and hidden agendas of MK, which is to control the church and install a government from Shewa.

  ReplyDelete
 6. for those of you who said this website belongs to Menafikan,
  Then, what the hell are you doing searching on this site?

  This website reveals the true faces of evil MK, which is trying to disintegrate our church.

  ReplyDelete
 7. thanks Anonymons( at 1:07pm). what are you guys doing here if you're really beleive this web is belongs to protestant. I bet you are " weregna" or don't know what you are standing for.

  ReplyDelete
 8. enantem thadson eyasfafachehu ena ewnetengawan orthodox lemafres yemtfelgut genzeb slaggnachhu new eko new kabatchhu diablos bearopwian bekul yemtaggnut ena yesus nege nsehaun gebto tetsetsto litew ychelal hatiatnewna ynetsal yenant wed esat siol yemiasorewr krstosn kemskel yemayley new

  ReplyDelete
 9. if u think this blog is ye menafkan atanbebut I think mk nachu yemetanbebut'..."zare yetgnaw gudachen tesafe?? "eyalachu...amlak en danel kesereten ena mk n ystagselen

  ReplyDelete