Sunday, April 7, 2013

ደብረ ዘይት

ምንጭ፦ የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ ቅዳሜ መጋቢት 28 2005 ዓ.ም (http://www.ashenafimekonen.blogspot.com/)
የዐቢይ ጾም አምስተኛ እሑድ ደብረ ዘይት ተብሎ ይጠራል፡፡ የጌታችን ዳግም መምጣትና የዘመኑ ምልክት የሚነገርበት ቀን በመሆኑ ዕለቱ ደብረ ዘይት ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ጌታችን ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ መምጣቱ ምልክት የተናገረው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በመሆኑ ዕለቱ ደብረ ዘይት ተባለ (ማቴ. 24÷ 3)፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዕለቱን ደብረ ዘይት ብሎ መሰየሙ ብቻ ሳይሆን በዕለቱም ያቀረበው ዝማሬ እንዲህ የሚል ነው፡-

ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወሰ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአን ምድር ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበአእላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእም ኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት

ትርጉም፡-
የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማይና የምድር ሠራዊት ሁሉ ይነቃነቃል። ያን ጊዜ በምድር የሚኖሩ ኃጢአተኞች ሁሉ ያለቅሳሉ፡፡ ጌታችንም ከአእላፍ መላእክት ጋር በትእዛዙና በቃሉ መሠረት ከሰማይ ወደ ምድር ይወርዳል፡፡ የእግዚአብሔር መለከትም ይሰማል፡፡ በዚያች ሰዓት እርሱ ያድነን። እርሱ የሕይወት ባለቤት ነውና።

ቅዱስ ያሬድ የዘመረው የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ነው፡፡ ጌታችን ሲመጣ ፍጥረት እንደማይፀና ኃጢአተኞች ደስታ እንደማይሰማቸው ይገልጣል፡፡ በኃይሉ ፊት ፍጥረት፣ በፍርዱ ፊት ኃጥአን መቆም አይችሉምና፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል። በብሉይ ኪዳን እመጣለሁ ብሎ መጥቷል፡፡ በአዲስ ኪዳንም እመጣለሁ ብሎ ቤተ ክርስቲያንን በተስፋ አስገዝቷታል፡፡ ፍጥረት ሁሉ የሚጠብቀው አንድ ታላቅ እንግዳ ከፊታችን ባለው ባልራቀው ዘመን ይመጣል፡፡ የሚመጣው በትሕትና ሳይሆን በልዕልና ነው፡፡ በከብቶች በረት ሊጣል ሳይሆን በደመና በዙፋን ተገልጦ ይመጣል፡፡ ስምዖን አረጋዊ እንደ ታቀፈው ሆኖ አይመጣም፣ ሰማይና ምድር የማይችሉት ሆኖ ይመጣል፡፡ ከእናቱ ጡትን እየለመነ አይመጣም፣ ለፍጥረት ሁሉ የሩጫውን ዋጋ ለመስጠት ይመጣል፡፡ ከሄሮድስ ፊት የሚሸሽ ሆኖ አይመጣም፡፡ ሰማይና ምድር ሲያዩት ከፊቱ ይሰደዳሉ፡፡ ለእኛ ለክርስቲያኖች መጣልን የምንለው እንግዳችን፣ ፈራጃችን እንጂ መጣብኝ የምንለው አይደለም፡፡
 
የጌታችን ዳግም ምጽአት፡-
1.     የጸሎታችን መልስ ነው።
2.    የፍጥረት ምጥ ዕረፍት ነው።
3.    የዘመናት ናፍቆት መልስ ነው።
4.    የተስፋችን ፍጻሜ ነው።
5.    የእምነታችን ክብር ነው።
6.    የአዲስ ዓለም ጅማሬ ነው።
7.    የዘላለም ሕይወት መክፈቻ ነው፡፡ 

                                የጸሎታችን መልስ ነው

ብዙ ሰዎች ክርስቶስ ዳግም ይመጣል ሲባሉ ይፈራሉ፡፡ ፍርሃታቸው ግን ለንስሐ አያዘጋጃቸውም። ልበ ሙሉ ሆነው ኃጢአት እንዳይሠሩ የመምጣቱ ዜና ስለሚረብሻቸው ነው፡፡ የጌታችን ዳግም ምጽአት በሚታሰብበት ቀን እንኳ ብዙ የኃጢአት መታሰቢያ ሲደረግ ይውላል፡፡ ለብዙ ሰዎች እኩለ ጾም ከሥጋና ከስካር ከተላቀቁ አንድ ወር መሆኑን ለመገናኘትም ወር እንደሚቀራቸው የሚያስቡበት ቀን ነው፡፡ በጊዜያዊ ጨዋነት የሰነበቱትም ሲሰክሩ የሚውሉበት የተውኔት ቀናቸው ነው፡፡ ሃይማኖት የማይሞት ኃይል ነው፡፡ ከሰው ልብ ግን ሊሞት የሚችለው ሰዎች እንደ ባሕል ቆጥረውት ሲኖሩ ነው፡፡

የጌታችን መምጣት ግን የጸሎታችን መልስ ነው፡፡ የምንፈራውና ያርቅልኝ የምንለው ሳይሆን በየዕለቱ መንግሥት ትምጣ እያልን የምንጸልይበት ትልቅ ርዕሳችን ነው፡፡ የዚህ ዓለም መንግሥት በግፍ ተጀምሮ በግፍ የሚጠናቀቅ፣ በውሸትና በሐሰተኛ ተስፋ ሰውን የሚያደክም፣ በጭካኔ ሲወዳደር የሚኖር፣ ደም በደም የሆነ መንገድ ነው፡፡ በዚህ ክፉ ሥርዓት የተጨነቁ ሁሉ ጽድቅና ሰላም የነገሠባትን የክርስቶስን መንግሥት ይናፍቃሉ (ሮሜ. 14÷17)፡፡ የክርስቶስ መንግሥቱ የምትገለጠው ጌታችን ምድራውያን ነገሥታትን አሳልፎ ንጉሠ ነገሥት ሆኖ በሚነግሥበት በዳግም ምጽአቱ ነው፡፡ ዳግም ምጽአቱ ምድራዊውን ሥርዓት አሳልፎ አንድ መንግሥትን በሁሉ የሚያፀና ነው፡፡

የፍጥረት ምጥ ዕረፍት ነው

ሐዋርያው ጳውሎስ፡- የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና ይላል (ሮሜ. 8÷19)፡፡ ዳግመኛም ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና ይላል (.22)፡፡ በሰው ኃጢአት የተጨነቀው ሰው ብቻ ሳይሆን ፍጥረት በሙሉ ነው፡፡ እንስሳቱ አራዊቱ ሁሉ የሰውን ኃጢአት ቅጣት እየተካፈሉ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚያርፉት ክርስቶስ ልጆቹን በክብር በሚገልጥበት በምጽአቱ ቀን ነው፡፡ ስለዚህ ፍጥረት ሳይወድ በግድ የሰውን ማረፍ ይናፍቃል፡፡ የራሱም ዕረፍት ነው፡፡ ዛሬ በብዙ ነገር እናለቅሳለን፡፡ ብዙ ጭንቀቶችም ከበውን እንኖራለን፡፡ የክርስቶስ መምጣት ግን የፍጥረት ምጥ ዕረፍት ነው፡፡

የዘመናት ናፍቆት እርካታ ነው

ማራናታ ማለት ጌታ ይመጣል ወይም ጌታ መጣ ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ 609)፡፡ ይህ ቃል ዮሐንስ ራእዩን ሲዘጋ ተጠቅሞታል፡- አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ  (ራእ. 22÷20) ዮሐንስ በራእዩ ስለሚመጣው የዘመናት ጣር ካየ በኋላ የዚህ ሁሉ ማብቂያው ምንድነው? ብሎ ሲያስብ የጌታ መምጣት ነው፡፡ ስለዚህ ማራናታ አለ፡፡ የጌታችን መምጣት የመከራው ድንበር ነው፡፡ በመጀመሪያ ምጽአቱ ሞት ተገደበ፣ በዳግመኛ ምጽአቱ መከራ ገደብ ያገኛል፡፡

የተስፋችን ፍጻሜ ነው

የምንጠባበቃቸው ብዙ ተስፋዎች ቢኖሩም ትልቁ ተስፋችን ክርስቶስ ነው፡፡ የምንጠብቃቸው ነገሮች ቢሆኑልን እንኳ ሌላ መመኘታችን አይቀርም፡፡ ክርስቶስ ከመጣልን ግን ምንም እስከማያምረን ለዘላለም ያረካናል። ሐዋርያው ጳውሎስ፡- የተባረከው ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር መገለጥ እየጠበቅን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል (ቲቶ. 2÷12-13) ይላል፡፡ ሰዎች ተስፋ ካላቸው ራሳቸውን ከሚጎዳ ነገር ይከላከላሉ፡፡ እንዲሁም ክርስቶስ ተስፋቸው የሆነ ይቀደሳሉ፡፡ በኃጢአት መጫወት ተስፋ መቊረጥ ነው፡፡ የክርስቶስ ምጽአት የተስፋችን ፍጻሜ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን የቀረላት ተስፋ የክርስቶስ መምጣት ነው፡፡  

የእምነታችን ክብር ነው
ጌታችን ዳግመኛ የሚመጣው በናቀን ዓለም ፊት እምነታችንን ሊያከብር ነው፡፡ የዘበቱብንና ያስጨነቁን ለዘላለም ያፍራሉ፡፡ ዛሬ ቃሉን የረገጡ፣ ያን ቀን ፍርዱን መርገጥ አይችሉም፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች የሆንም በዚያን ቀን በዘላለም ክብር ተውበን በጉን እረኛችን አድርገን ወደ ፍስሐ ዓለም እንገባለን፡፡

የአዲስ ዓለም ጅማሬ ነው

በዮሐንስ ራእይ ላይ እንደ ተጻፈው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድርን አየሁ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደፊት የለምይላል (ራእ. 21÷1)፡፡ አዲስ ነገር የሚያስፈልገው ፊተኛው ሲያረጅ ነው። ያረጀ ነገር መልኩ የወየበ፣ ጉልበቱ ያለቀ፣ ወደፊት ሊጠቅም የማይችል ነው፡፡ አሁን ፍጥረት አርጅቷል፡፡ በረዶ እየቀለጠ፣ የምድር ሙቀት እየጨመረ፣ መሬቱ ማዳበሪያ እየፈለገ፣ ሰውም በብዙ መድኃኒት እየኖረ ነው። ይህ የማርጀት ምልክት ነው፡፡ ይህን አዲስ የሚያደርገው የክርስቶስ መምጣት ነው፡፡ ሰውም ሞት ላይዘው በትንሣኤ፣ የሚመጣው ዓለምም ማርጀት ላያገኘው በአዲስነት ይኖራል፡፡

የዘላለም ሕይወት መክፈቻ ነው

ጌታችን ሲመጣ ዘላለማዊት የምትሆን መንግሥተ ሰማያት ትከፈታለች፡፡ ዛሬ በክርስቶስ ያመኑ በበጎ ሥራ የፀኑ አማንያን በጊዜያዊ ማረፊያቸው በገነት ይኖራሉ፡፡ ገነት ጊዜያዊ የነፍሶች ማረፊያ ናት፡፡ ክርስቶስ ሲመጣ ገነትና ሲኦል ያልፋሉ፡፡ መንግሥተ ሰማያትና ገሀነመ እሳት ይከፈታሉ (ማቴ. 25÷34-41)፡፡

የዘላለም ዘመንም ይከፈታል፡፡ ዘወትር አዲስ የሆነውን ጌታ እያየን በዘላለም ደስታ እንኖራለን፡፡
የጌታችን መምጣት ብዙ ትርፎች ያሉት ወደማይነገርም ክብር የምንገባበት ነው፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ የምናየው መከራና ሰቆቃ የምጽአቱ ዋዜማ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ጭንቅ በክርስቶስ መምጣት ይጠናቀቃል፡፡ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ  /ራእ. 22÷20/

19 comments:

 1. Sile tsihufu enamesegnalen Ashenafi. Bruk hun.
  Ewunet gn pente honik yetebalew ewunet new?

  mn yahl endemiwodhina thihufochihn eketatel endenebr kalat ayigeltsewum. Ahun gn gira gebagn...

  ReplyDelete
  Replies
  1. That’s MK's accusation so don't fall for that trap. If you’ve been following up with his writings, then you shouldn't be confused. You have a mind and a brain so test his articles, books, & recorded audios to see if they are indeed as his accusers claim. Do not be gullible because that's the easiest way for Satan to put you under his trap

   Delete
  2. አንብበን መረዳት መዝነን ማወቅ እንጂ ቡድንተኞች የሚያወሩትን እየሰማን መወናበድ ምን ይጠቅማል፡፡ አሸናፊን ሰብእናውን ነው ወይስ ጸጋውን ነው የምንቃወመው? አሁን ያለው አብእናውን መቃወም ይመስላል፡፡ አታንብቡ የሚሉንን አንሰማም የሚነበብ ያቅርቡልን፡፡ ስንት የነውር ጽሑፍ ሳይወገዝ እንዲህ ያለ መልእክትን ማውገዝ የአጋንንት ሥራ ነው፡፡ ስንት ደብተራ ስንት ጠንቋ ተከብሮ እየኖረ ወንጌል የተሸከመ ሰው መገፋቱ ያሳዝናል፡፡ እና ወገኔ አትወናበድ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ፖለቲካ ላደግንበት ግልጽ ነው፡፡ ለምእመናን ግን ግር ይላቸዋል፡፡ የሚባለው ሁሉ እውነት አይደለም፡፡ ሰው በመልኩ ሳይሆን በሥራው ይመዘናል፡፡ አሸናፊ ቢሄድ ሁሉም እልል ብሎ ይቀበለዋል፡፡ እዚህ ስድብ ነው የተረፈው፡፡ የማውቀውን እመሰክርልሃለሁ ፍጹም ውሸት ነው፡፡

   Delete
  3. ደረጃ መዳቢዎች የሚሰጡትን ስም ትተው የሚያስተምረውን ይመርምሩና ለራስዎት ይፍረዱ ፡፡ ንጹህ ወንጌልን የሚሰብክ ትጉህ ክርስቲያን ነው ፡፡ ሌሎች ሌላውን ሲያስተምሩ ፣ ቤተ ክርስቲያን የጐደላትንና የሚያስፈልጋትን አገልጋይ ፣ ለመሙላት የሚደክም ሰው ነው ፤ ይህን ርሱም ይመሰክራል ፡፡ እውነትን ይናገራል ፤ እውነትን ይሰብካል ፤ እውነትን ያስተምራል ፡፡ እውነት ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ እንደሌሎች ቀናዒ ትጉሃን ፣ ቤተ ክርስቲያንን በደፈና አይወቅስም ፤ አያወግዝም ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ሥርዓት ካልተቃወመና ፣ ካልነቀፈ ፣ ወንጌልን ስለማስተማሩ ብቻ ለምን ይጠላል ? ቤተ ክርስቲያንስ በየዕለቱ የምትደክመውና የምትታገለው ወንጌልን ለማስተማርና ለማዳረስ ፣ መንጋዎቿም እንዲስተካከሉና እንዲታረሙ መስሎን ፡፡

   በግል ትዝብት አሸናፊ በድክመትና ተስፋ በመቁረጥ ፣ የወደቀና የዘቀጠውን ወገን በእምነትና በምግባር እንዲታነጽ የሚሠራ የዘመናችን የክርስትና አናፂ እለዋለሁ ፡፡ መጽሐፍቱን ይፈትሹ ፤ ስብከቶቹን ያድምጡ ፤ የድረ ገጽ በራሪ ጽሁፎቹንም ይመዝኑ ፤ ዓለም ለጨለመባቸው ተስፋን የሚሰጡ ፣ ብርሃን የሚፈነጥቁና መንገድ የሚያስቃኙ ናቸው ፡፡ ይኸኛው የደረጃ ምደባ የርሱን ምንነት ይናገርልኛል ፡፡ ሲወቅስም እንኳን የሚወቅሰውንና የሚገስጸውን በቅጡ ይለያል ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሳይሆን ሰነፍ ግለሰቦችን ያመለክታል ፡፡ ቂም በቀል ስለሌለበት ስም ለይቶ አባ እገሌ አይልም ፤ ሰዎች (አገልጋዮቿ) እንደተሳሳቱ ግን የተመለከተውንና የታዘበውን ሳያፍርና ሳይፈራ እንዲታረምና እንዲስተካከል ይጠቁማል ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ነባር ሰላሟን እንዲመልሱ አቤት ይላል ፡፡ ደረጃ ምደባው ይስተካከል

   ይህችን ወቀሳውን ለዓይነት በጥሞና ይመልከቷት
   http://www.ashenafimekonen.blogspot.com/2013/03/blog-post_1943.html#more

   አያንጽም ብለው የሚያስቡ ከሆነ ቃል ያምጡ ፡፡

   Delete
  4. fikir Lezwter Aywdkim wendmae ahunm bfekir nuru. Fikir lezewter Aywdkim Yemlewen D/n Ashenafi Sebket gabzkuh ke you tyub lay semaw

   Delete
  5. Amesegnalehu sewoch lesetachihugn melisoch.Tiru melikit new. Ashenafinim Egziabher yitebkew. most people need a person like him to be in orthodox church & to teach us not on the other denominations. You know he has "leza " in his writings. I am interested in that.I always feel happy from the heart when I read books of him & I feel with hope. Any ways we are obliged to be confused all the time with many people accusations. Miskin hizb.

   Delete
 2. D/N Ashenafi, You are blessed and May God bless you more. Amazing article . Thank you

  ReplyDelete
 3. Amen Amen.May God richly bless you. Please do more writing it help us alot. Thank you. Yes Jesus is coming for us for good.

  ReplyDelete
 4. Amen Geta Eyesus Yemetal. Ahun geen be Amlakenet keberu yemetal. Ye wegut hulu yayutal. Amen Amlakachen hoi tolo naa.

  ReplyDelete
 5. God bless u !!! endih ewunet tmhirt leteman menfkenawun tetachu betsbkun neber yemishalewu!!!

  ReplyDelete
 6. Deacon Ashenafi,
  Please keep it up. The Holly Sprit is working on you!
  Thank you.

  ReplyDelete
 7. god bless you ashenafi

  ReplyDelete
  Replies
  1. Amen Elalehu. Enem endrso

   Delete
  2. እንዲህ በቅንነት መመካከራችን በጣም ጥሩ ነው፡፡ ለተዋህዶም የሚጠቅም ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንንም እግዚአብሔር ወደ ብርሃኑ ያምጣልን፡፡ የታሠሩበት ትብትብ በአስተያየት ብቻ የሚለቅ አይደለም፡፡ በአገልጋዮች ደም የሚታጠብ የኤልዛቤል መንፈስ ነውና በኃይለ አግዚእነ ኢየስስ ክርስቶስ የታሠረ ይሁን፡፡ እነርሱንም እንደ ጳውሎስ የጠሉት መድኃኒት ለፈውስ ይሁንላቸው፡፡ ባለፈው ዘመን 7 ሚሊየን ሕዝብ ወደ ጴንጤ ሄደ ተባለ አብዛኛው የሄደው በማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ አሁንም በር ከፍተው ገፍትረው እያስወጡ ነው፡፡ ለቀጣይ ዐሥር ዓመት 7 ሚሊየን ሕዝብ ይሄዳል፡፡ ከሣር ክዳን ቤት አንድ ቢመዘዝ አያፈስም ብለዋል፡፡ 7 ሚሊየን ሲመዘዝ አያፈስም ወይ? ክርስቶስ የሞተለትን ወገን እንዲህ መግፋት አይገባም፡፡ ከእገሌ ተሐድሶ ጋር ታየህ እያሉ ያሰድዳሉ፡፡ ጳጳሳቱ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት መድረክ ከጴንጤ ከካቶሊክ ጋር ጽዋ ይጠጡ የለም ወይ? ኩራት አድርገውት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዝዳንት እየተባሉ ሲጠሩበት ለምን አያወግዙም፡፡ አይ ማቅ ለድሃ የሚበረታ አሳዛኝ ቡድን ነው...

   Delete
  3. በዲያቆን አሸናፊ መኮንን መጻሕፍት ላይ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ የሚያሳዝን ነው፡፡ መጻሕፍቱን የሚሸጡትን በማስፈራራት ጭምር መጻሕፍቱን ለማጥፋት ማኅበረ ቅዱሳን ዘመቻ ላይ ነው፡፡ በእውነቱ አሳዛኝ ነው፡፡ መጻሕፍቱ ግን በሰው ሼልፍ ላይ ሳይሆን ያሉት በሰው ልብ ውስጥ ነው፡፡ በርትተህ ጻፍ፡፡ ዙሪያህን ሳይሆን ጌታህን የጠራህን አዳምጥ እኛም ከጎንህ ነን...ያነበበ ይፍረደኝ...የፈረንጅ መጻሕፍት እያደነቅን የራሳችንን መግደላችን ...

   Delete
  4. betam new yemitasiku. yihen yahl hizb wode pente geba eyalachihu le orthodox yazenachihu timeslalachihu. wusitachihu eyetedesete. what is the difference in being orthodox with the way you preach (like aba selama) & protestant. no difference at all.except the place. ur mission is that.

   Delete
 8. We need a lot of like Deacon Ashenafi for Ethiopian Orthodox church who teach a clear Gospel not mixing with any thing Just Gospel which is from the BIBLE. Whoever you are accusing Deacon Ashenafi you know it is not from God. Please open your BIBLe to see and understand.

  ReplyDelete
 9. Yehasete mesekere becrestosum meskweral. besewech mewdeke setane selemedesete besewochlay adro yetederege serano. Ewnetune egzyabehare yawtewale. Cefu kemenager enekotabe. Ewnetune entebekw.

  ReplyDelete