Wednesday, May 8, 2013

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 14

«የእውነት ቃል አገልግሎት» ላይ የግንቦቱ (ግንቦት 15/2004 ዓ/ም) ሲኖዶስ ቃለ ጉባኤው ያሰፈራቸውና «ኑፋቄ» ብሎ ካቀረባቸው ነጥቦች መካከል ቀጣዮቹን ነጥቦች መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርገን ኑፋቄ የተባሉት ነጥቦች ኑፋቄ መሆን አለመሆናቸውን እንመረምራለን።

 

«ሀ. ብቃት ያለውን አማላጅነት ትቶ እንደኛው ድካምን የሚለብሱና ለእነርሱ ለራሳቸው የክርስቶስ አማላጅነት የሚያስፈልጋቸውን አማላጅ ማድረግ ወይም በክርስቶስ ላይ ተጨማሪ አማላጅ አድርጎ ማዳበል ትልቅ ውደቀት ነው» በማለት ክርስቶስን አማላጅ አድርጎ የቅዱሳንን አማላጅነት ውድቀት በማለት ተሳድቧል።  መጽሐፈ ሰዓታት በመቅደሱ ሚዛን - ገጽ 64»

ስለአማላጅነት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውና በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሚታመነው የአማላጅነት ትምህርት ፈጽሞ አይገናኝም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳን በሕይወተ ስጋ ሳሉ ምልጃ ሲያቀርቡ እናነባለን፡፡ ካንቀላፉ በኋላ ግን ምልጃ ያቀረቡበት ሁኔታ የለም፡፡ ካንቀላፉ ቅዱሳን ጋር ሕያዋን ቅዱሳን የሚገናኙበት እድል ስለሌለም «ለምኑልን አማልዱን» ብለው ቢጮሁ ሰሚ የሌለው ጩኸት ነው የሚሆነው፡፡

በኑፋቄው ጎራ ያሉት ስለአማላጅነት የሚጠቀሱት በርካታ ጥቅሶች ቅዱሳን በሕይወተ ስጋ ሳሉ ያቀረቡትን ምልጃ የተመለከተ እንጂ ካንቀላፉ በኋላ ስለማማለዳቸው አያሳዩም፡፡ ጥቅሶቹ በአጸደ ስጋ ስላሉት ከሆነ ትክክል ነው፡፡ ስለ አጸደ ነፍስ ምልጃ የሚሆን ማስረጃ ስለሌለ ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰው የኤልሳእ መቃብር ሙት ማስነሳቱና ራእይ ውስጥ «ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ። በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።» የሚለው ነው» (ራእ. 6፡9-10)፡፡  

ይሁን እንጂ ቅዱሳን በክርስቶስ ጽድቅ የጸደቁ በእርሱ ምልጃ የተሸፈኑ እንጂ በራሳቸው ፍጹማን የሆኑ አይደሉም፡፡ በዚህ ምድር ሳሉ ይጸልዩ የነበረውም እግዚአብሔር በሰጣቸው ሞገስ እና በክርስቶስ ስም ነበር፡፡ ስለዚህ ቅዱሳን ካንቀላፉ በኋላ ያማልዱናል በሚል ወደእነርሱ መጸለይና እነርሱን ተስፋ ማድረግ የክርስቶስን መካከለኛነት አሌ ማለት ነው፡፡  ከዚህ አንጻር «ብቃት ያለውን አማላጅነት ትቶ እንደኛው ድካምን የሚለብሱና ለእነርሱ ለራሳቸው የክርስቶስ አማላጅነት የሚያስፈልጋቸውን አማላጅ ማድረግ ወይም በክርስቶስ ላይ ተጨማሪ አማላጅ አድርጎ ማዳበል ትልቅ ውድቀት ነው» የሚለው መልእከት በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘን እውነት እንጂ ሐሰት አይደለም፡፡ ዛሬ እየሆነ ያለው ያንቀላፉ ቅዱሳንን በክርስቶስ የመካከለኛነት ስፍራ ላይ ማስቀመጥ ነው፡፡ ቅዱሳንን በማክበር ስም እየሆነ ያለው ሁሉ አምልኮተ ባእድ ነው፡፡

ተመልካች አጥቶና ሊቃውንቱ አፋቸው ተሸበቦ ነው እንጂ ቅዱሳን ካንቀላፉ በኋላ እንደማያማልዱ በውዳሴ ማርያም አንድምታ ላይ ተጽፏል፡፡ ለሰአሊ ለነ ቅድሰት የተሰጠው ትርጓሜ «ልመና እንኳን በእርሷ በሌሎችም የለባቸውም በቀደመ ልመናዋ ስለምታስምር እንዲህ አለ እንጂ» ነው የሚለው፡፡ ስለዚህ ዛሬ በአጸደ ነፍስ አማላጅነት የለም፡፡ ይሁን እንጂ የማህበረ ቅዱሳን ተረት ስፍራውን እያስለቀቀው ስለመጣ ይህ ትምህርት ዛሬ ኑፋቄ እንጂ ትክክለኛ ትምህርት ተደርጎ አይወሰድም፡፡ በዚህ ትምህርት የተቃኘው ሲኖዶስም እውነቱን አውግዞ ሐሰቱን አጽድቋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በእጅጉ እንደሚቆጭበት የሚነገረውና በምን መንገድ እንዳመለጠው ሳይታወቅ በስሙ ያሳተመው የሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ «ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት» መጽሐፍ ምልጃን በተመለከተ በአንድ በኩል የሚባለውን ቢልም በሌላ ወገን ግን ማቅ የማይለውንና እንዲባልም የማይፈልገውን እውነት አስፍሯል፡፡
«እውነተኛዋና ትክክለኛዋ መዳንንና የዘላለም ሕይወትን የምታሰጠዋ ሃይማኖት የትኛዋ ናት? በማለት እንደ ገና እንጠይቃለን። መልሱም ከላይ በተጠቀሰው ሀይለ ቃል (ዮሐ. 3፥16-18) መሠረት ለእኛ ደህንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ በመጣው በባሕርይ ልጁ ላይ ያለን ሃይማኖትና እምነት ብቻ ነው። ምናልባት መስሎንም ሳይመስለንም ወይም በልዩ ልዩ ምክንያት እምነታችንንና ትውክልታችንን ፣ ፍቅራችንንና አምልኳችንን ከእርሱ ውጭ በሌላ ነገር ላይ አድርገነው እንደ ሆነ የመዳን ተስፋ የለንም። ምክንያቱም ማዳን የእግዚአብሔርና የበጉ ነው ተብሎ ተጽፏልና (ራእ. 7፥10)። ሕዝብንም አሕዛብንም በደሙ የዋጀ የእግዚአብሔር በግ ነውና (ራእ. 5፥8-10)። …… ዛሬም የምንድነውና በረከተ ስጋና በረከተ ነፍስ የምናገኘው በእርሱ በማመን ነው፡፡ «አኮ በተንባል ወአኮ በመልአክ አላ ለሊሁ ያድህኖሙ እስመ ያፈቅሮሙ ወይምህኮሙ ውእቱ ተወክፎሙ ወቤዘዎሙ ወአክበሮሙ በኩሉ መዋዕሊሆሙ ለዓለም፡፡ - እሱ ያድናቸዋል እንጂ በአማላጅ በአለቃ የሚያድናቸው አይደለም፡፡ ይወዳቸዋልና ይራራላቸዋል፡፡ እሱ በረድኤት ተቀብሎ አዳናቸው፡፡ ባለ ዘመናቸው ሁሉ ለዘላለም አከበራቸው» ተብሎ እንደተጻፈው መዳናችንንና መክበራችንን በክርስቶስ የማዳን ሥራ ብቻ ነው፡፡ ኢሳ. 63፡9 ግእዙን ተመልከት፡፡» ብለዋል፡፡ አክለውም የትኞቹ ቅዱሳን ማለት ያንቀላፉት ይሁኑ ሕያዋኑ ሳይለዩ የምልጃን ነገር ከጠቀሱ በኋላ «ለጸሎቱና ለምልጃው አይነትና ገደብ አለው … ሥርዓትና ወሰን አለው፡፡ ስለዚህ ቅዱሳን የሚጸልዩትና የሚያማልዱት «ለሞት የማያበቃ በደል» ለፈጸሙት እንጂ ለሞት የሚያበቃ በደል ለፈጸሙት አይደለም 1ዮሐ. 5፡16-17፡፡ ይኸውም ቢሆን ከንስሀ ጋር እንጂ ያለንስሀ አይፈጸምም፡፡ እንግዲህ ሁሉም ነገር የሚሰምረውና የሚከናወነው እኛ በወደድነውና በፈለግነው መንገድ በመሄድ ሳይሆን እግዚአብሔር ለእኛ ብሎ ያዘጋጀውንና የመረጠውን ብቸኛ መንገድ አውቀንና አምነን ስንሄድ ነው፡፡ የመዳንና የጽድቅን መንገድ ከፈለግን እምነታችንን በእግዚአብሔርና በክርስቶስ ላይ አድርገን ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ እንኑር፡፡ በሃይማኖተ ወንጌል እንጽና» በማለት (ገጽ 293-295) ሰው በላውና ከሐዲው በላኤ ሰብእ በእፍኝ ውሃ በማርያም ስም ሰጠና ዳነ የሚለውን የተአምረ ማርያም ተረት በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ያፈርሱታል፡፡

ታዲያ የሊቃውንት ጉባኤው በማቅ መንፈስ ተቃኝቶ የኖረውንና ባንቀላፉ ቅዱሳን ዘንድ አሁን ልመና የለም የሚለውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ከማውገዝ የበለጠ ለቤተክርስቲያኗ ሌላ ውድቀት አለ ወይ? ከዚህ የምንረዳው ቤተክርስቲያን ከእውነተኛ ትምህርቷ ወደ ማቅ ተረታተረት እንየተንሸራተተች መሆኗን ነው፡፡ ያሳዝናል! ምነው ታዲያ የሊቃውንት ጉባኤ አባላት ዝም አላችሁ?  መቼም ይህን ትምህርት በአፋችሁ እንጂ በልባችሁ እንዲወገዝ ለሲኖዶስ አሳልፋችሁ እንዳልሰጣችሁት ይገባናል፡፡

የእውነት ቃል አገልግሎት ጽሑፍ መጽሐፈ ሰዓታትን ነው የተቸው፡፡ ሰኣታት ያልተተቸ ማን ይተች ይሆን? እውነተኛውንና ሐሰተኛውን አምልኮ አደበላልቆ የያዘ እንደ መጽሐፈ ሰዓታት የት ይገኛል? መጽሐፈ ሰዓታት እኮ በኃጢአት ይዘውን የወደቁትን አዳምንና ሔዋንን እንኳን ሳይቀር «ሰአሉ ለነ ልምኑልን» የሚል ነው፡፡ ምን እነርሱን ብቻ ሕንጻ ቤተክርስቲያንን፣ ሰንበትን የዕንጨት መስቀልን ጭምር አማልዱን የሚል አማልክተ ብዙ መጽሐፍ ነው፡፡ ዛሬስ ዘማሪዎቻችንና ሰንበት ትምህርት ተማሪዎቻችን እዚህ ቅኝት ውስጥ ገብተው አይደለም በየመርሀ ግብሮቻቸው አንድ ለጌታ ሁለት ሶስት ለፍጡራን ዝማሬዎችን እያዘመሩ አምልኮአቸውን የሚቀይጡት? 

ይቀጥላል 67 comments:

 1. የቅዱሳን አማላጅነት እና የኢየሱስ ክርስቶስ አስታራቂነት ልዩነት!!

  አንዳንድ ወንድሞች ነገረ ቅዱሳንን ከነገረ ክርስቶስ ጋር ይቀላቀልባቸዋል፡፡ከሚያነሱዋቸው ሐሳቦች አንዱና ዋነኛውም “ጻድቃን፣ ሰማዕታት እና ቅዱሳን መላእክት ብቃት ያላቸው አማላጆች አይደሉም፤ ይልቁንም ብቃት ያለው አማላጅ (ጠበቃ) ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው” የሚል ይገኝበታል፡፡ነገር ግን ወንድሞቼ የክርስቶስ መካከለኛነትና የቅዱሳን አማላጅነት ልዩነቱ የገባቸው አይመስልም፡፡
  ቤተክርስቲያናችን በቅድስት ድንግል ማርያም፣ በመላእክትና በቅዱሳን አማላጅነት ታምናለች፣ ታስተምራለችም፡፡ ይኼንን ትምህርት የማያምኑ ወንድሞቻችን ግን ለ“ትምህርታቸው” እንደ ማስረጃ ከሚያቀርቡዋቸው ጥቅሶች መካከል “ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፣ እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /1ዮሐ.2፡1/” እና “በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፣ እርሱም ሰው የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /1ጢሞ.2፡5/” የሚሉ ይገኙበታል፡፡
  ቤተክርስቲያናችን በእነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳቦች ላይ ያላት እምነት የሚከተለውን ነው፡፡

  1. የኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃነትና የቅዱሳን ጠበቃነት ፈጽመው የማይገናኙ ነገሮች ናቸው፡፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃችን ነው” ስንል አስታራቂነቱን ፣ ቤዛነቱን መናገራችን ነው፡፡ይህም ማለት እያንዳንዳችን በኃጢአታችን ምክንያት ወደ ገዛ መንገዳችን ስናዘነብል ጌታ የሁላችንን በደል በመሸከም ዕዳችንን ከፍሎ ከአባቱ ጋር ጠበቃ በመሆን አስታርቆናል /ኢሳ.53፡6/፡፡ስለዚህ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ ብቸኛው መካከለኛ (ወልድ ዋሕድ) ነው፡፡አባቱን ያረካ ብቸኛው መሥዋዕት በመሆንም ለምናምን ለኛ በእኛ ፈንታ በመሞት ጠበቃ ሆነልን፡፡ስለዚህ “ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን”፡፡ምክንያቱም ከየትኛውም ዐይነት ኃጢአት መንጻት የምንችለው በጻድቁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ ነውና፡፡

  የቅዱሳን አማላጅነት ግን ኃጢአትን ከማንጻት እና ከቤዛነት ጋር ፈጽሞ የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡እነሱ መካከለኛም አይደሉም ፤ ሊሆኑም አይችሉም፡፡እነሱ መካከለኛ መሆን ቢችሉ ኖሮ በእነ ይስሐቅ፣ በእነ ኢሳይያስ ፣ በእነ ድንግል ማርያም አማካኝነት በዳንን ነበር፡፡ የእነሱ አማላጅነት በእኛ ፈንታ በክርስቶስ ፊት የሚያቀርቡት ጸሎት ብቻ ነው፡፡ምናልባት ከእናንተ መካከል “በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው /ሮሜ.8፡34 እና ዕብ.7፡25/ ተብሎ በደማቅ ቀለም ተጽፎአል” የሚል ሰው ሊኖር ይችላል፡፡እውነት ነው!! ነገር ግን ይህንን ሐሳብ ለመረዳት መጀመርያ የኢየሱስ ክርሰቶስ ሊቀካህንነትን ማወቅ ይጠይቃል፡፡

  የብሉይ ኪዳኑ ሊቀካህን በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት በመግባት ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፡፡ይህም ማለት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ሰዓት ስለ ሕዝቡም ይማልድ ነበር፡፡የሐዲስ ኪዳኑ ሊቀ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፡፡ስለዚህ “ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል” ሲባል ዛሬውኑ ተሰቅሎ ያድናል ማለት እንዳልሆነ ሁሉ “ኢየሱስ ክርስቶስ ይማልዳል” ሲባልም በመስቀል ላይ ሆኖ “ጌታ ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ያለው ቃል ዛሬ ለእኛም ይሠራል ማለት ነው እንጂ አሁንም ይማልዳል ማለት አይደለም፡፡ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር “ሊቀ ካህናት ሲል ብትሰማው ዘወትር የሚያገለግል አይምሰልህ፤ ራሱን አንድ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋ …(ጳውሎስ) ሁል ጊዜ ቆሞ የሚያገለግል እንዳያስመስሉት በማሰብ … ራሱን አንድ ጊዜ እንደሠዋ አስረዳ፡፡አንድ ጊዜ ሰው እንደሆነ አንድ ጊዜ ተሾመ፤ አንድ ጊዜ እንደተሾመ አንድ ጊዜ አገለገለ፤ ሰው በሆነ ጊዜ የሰውነትን ሥራ በመሥራት ጸንቶ እንዳልኖረ ባገለገለም ጊዜ በማገልገል ሥራ ጸንቶ አልኖረም /የዕብራውያን መልእክት ትርጓሜ ድርሳን 13፡184-190/” ብሎአል፡፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ ሁል ጊዜ ይለምናል” ብሎ ማሰብ ክብር ይግባውና ጌታን ደካማ ማድረግ ነው፡፡ምክንያቱም እንደኛ ኃይል የሌለው ነው ሁል ጊዜ የሚለምነው፡፡ አንድም ባለማወቅ ሁል ጊዜ እሱን መስቀል ነው፡፡

  2. የቅዱሳን አማላጅነት ከኢየሱስ ክርስቶስ አስታራቂነት ፍጹም የተለየና ጸሎት ብቻ እንደሆነ ተነጋግረናል፡፡ይህን ዐይነቱ ጸሎት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ አስረግጦ የሚደግፈው ጸሎት ነው፡፡ “እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ /ያዕ.5፡16/” እንዲል፡፡ ቅዱሳን ራሳቸው “ስለኛ ጸለዩ /1ተሰ.3፡1፣ ዕብ.13፡18 ኤፌ.6፡18/” ብለዋል፡፡ታድያ እነሱ እንኳን የእኛ ጸሎት እየፈለጉ እኛ የእነሱን አንፈልግም እንበልን? እንደኛ ተጋድሎአቸውን ያልጨረሱ ወንድሞቻችንን እንኳን እንዲጸልዩልን እየጠየቅን “ከመውጣቴም (ከመሞቴም) በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ /2ጴጥ.1፡15/” ያሉንንና በገነት ከክርስቶስ ጋራ ያሉትን ቅዱሳን እንዲጸልዩልን መጠየቅ አይገባንምን? ከምድር ወደ ገነት ከሄዱ በኋላስ ይህን ባለሟልነታቸው አጥተውታልን? ወይስ “የእነሱን ጸሎት መጠየቅ የሚቻለው ወደ ክርስቶስ እቅፍ ከሄዱ በኋላ ሳይሆን በዚህ ምድር ሳሉ ብቻ ነው” ተብሎ ተነግሮናል? ሰዎች እንዲጸልዩልን ከጠየቅንስ መላእክትን መጠየቅ አይገባምን?

  3. እግዚአብሔር ፃድቅ የሆኑ ሰዎች ስለ ሌሎች ይማልዱ ዘንድ ጠይቆአል፤ እንደሚችሉ አረጋግጦኣል፤ ይህ እዲደረግም ፈቅዶአል፡፡ለምሳሌ፡ አብርሃም ስለ አቤሜሌክ፣ ኢዮብ ስለ ጓደኞቹ፣ አብርሃም ስለ ሰዶም ሰዎች፣ ሙሴ ስለ ሕዝበ እስራኤል ያቀረቡት ምልጃ ይጠቀሳል፡፡እነዚህ በምደር ሳሉ ያቀረቡት ምልጃ ሲሆን ወደ ገነት ከሄዱ በኋላ ያቀረቡ ደግሞ ዳዊት ስለ ሰሎሞን /1ነገ.11፡12-13፣31-34፣ መዝ.132፡10/፣ ጴጥሮስ ስለ ምእመናን /2ጴጥ.1፡15/፣ ሰማዕታት መከራ ስለሚደርስባቸው ምእመናን /ራዕ.6፡10/…ይገኙበታል፡፡
  ጸሎት ብቻ የሆነው የቅዱሳን አማላጅነት እንደ ጥብቅና ከተቆጠረ እና ምንም ተቀባይነት የሌለው ከሆነ እያንዳንዱ ሰው ስለሌላው የሚጸልየው ጸሎትም አላስፈላጊ ጥብቅና ነው፡፡
  ይህ ግን ፈጽሞ የተሳሳተ አካሄድ እና እንግዳ ትምህርት ነው፡፡እግዚአብሔር እያንዳንዱ አማኝ (ከዚህ ምድር የተለየውም ያልተለየውም) ስለሌላው እንዲጸልይ የፈቀደው አንዱ ለሌላው ያለውን ፍቅር የሚገልጽበት ስለሆነ ነው፡፡ስለዚህ በዚህ ምድር ያለንና በገነት ያሉት የክርስቶስ ብልቶች በጸሎት ድልድይ እንገናኛለን፡፡
  ስለዚህ የቅዱሳንን ምልጃ እንጠይቃለን፣ የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደርጋለችና፤
  የቅዱሳንን ምልጃ እንጠይቃለን፣ እግዚአብሔር ይህን ዐይነት ጸሎት ፈቅዶአልና፤
  በቅዱሳን አማላጅነት እናምናለን፣ የሚመጣውን ሕይወት እናምናለንና፤ እነሱም ሕያዋን ናቸውና፤
  በቅዱሳን አማላጅነት እናምናለን፣ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንድነት እናምናለንና፤ ሁላችንም (ከዚህ ምድር የተለዩትም ያልተለየንም) የአንድ ክርስቶስ ብልቶች እንደሆንን እናምናለንና!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰው አይመጣም ብዬ ስደናበር ነበር ፡፡
   ስለ ተሰጠን ትምህርት ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ ፡፡

   Delete
  2. In our liturgy, we always proclaim "የአብ ሊቀ ካህናት የሚሆን እርሱ የሰውን ባሕርይ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ" So this is essential for our salvation. I have met a lot of people & even DVDs released on the name the orthodox church (ex. ኦርቶዶክስ መልስ አላት) that deny this biblical fact because they assume it resembles that of protestant faith. It's so refreshing to see others, like yourself and ምእመን, who tell the truth accordingly. God bless you all

   Delete
  3. ሰላም ወገኔ በክርስቶስ ኢየሱስ ምልጃ/አስታራቂ እና በጻድቃን ምልጃ/አስታራቂ ልዩነት አለ ብለው ነበር የአስታራቂ እና የአማላጅ ትርጉም ልዩነት አለው እንዴ? የጠቀሱአቸው ጥቅሶች (በተራ ቁጥር 2 ላይ) ያዕቆብ፡ ጳውሎስና ጴጥሮስ እርስ በእርስ ጸልዩ ስለእኛ ጸልዩ ብለው ሲጠይቁ በሕይወት እያሉ ነው ? ወይስ ከሞቱ በሁዋላ? እንዲጸልዩ ነው የሚጠይቁት? በተራቁጥር (3) "እግዚአብሔር ፃድቅ የሆኑ ሰዎች ስለ ሌሎች ይማልዱ ዘንድ ጠይቆአል" ብለዋል ግን ሰዎችን ከሌሎች በተለየ መልኩ ጻድቃን የሚያደርጋቸው መለኪያ ምንድን ነው? ደግሞስ እርሶ እንዳሉት የጸደቁት ለጸደቁት ነው? ወይስ የጸደቁት ላልጸደቁት? ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ "እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።"ዮሐ 14፡13 "እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።" ዮሐ15፥16
   "በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።ዮሐ16፥23 መት ተሰጠን በቀጥታ ከአብ የሚያስፈልገንን ለመጠየቅ መልስ ለማግኘት እንድንችል መሆናችን አይደል? እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱሳችን ንባባት አውዱን ጠብቆ ካልተነበበ ስህተት ውስጥ እንገባለን። ታቶ ነኝ

   Delete
  4. ታቶ የእግዚአብሔር ሰላም ካንተ ጋር ይሁን ፡፡ ጥያቄህን መመለስ ባይመለከተኝም እንደ ወገንነቴ እሞክራለሁ ፡፡
   - “በክርስቶስ ኢየሱስ ምልጃ/አስታራቂ እና በጻድቃን ምልጃ/አስታራቂ ልዩነት አለ ብለው ነበር የአስታራቂ እና የአማላጅ ትርጉም ልዩነት አለው እንዴ?”
   አዎ አለው ፤ የፈጣሪና የፍጡር አማላጅነት የሰማይና የመሬት ያህል (በዓይነ ህሊና እንድትቃኘው በማለት) ልዩነት አለው ፡፡ ፈጣሪአችን ያስታረቀን ሰዎች ማስታረቅ ካልቻሉትና ከማይችሉት ጭምር ነው ፡፡ ያስታረቀንም ከራሱ ጋር ፣ ከአብ ጋር ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ነው ፡፡ ቅዱሳንና ጻድቃን ግን በጸሎታቸው በምልጃቸው ወደ ኢየሱስ ያቀርቡናል ፡፡
   - ጳውሎስና ጴጥሮስ እርስ በእርስ ጸልዩ ስለእኛ ጸልዩ ብለው ሲጠይቁ በሕይወት እያሉ ነው ? ወይስ ከሞቱ በሁዋላ? እንዲጸልዩ ነው የሚጠይቁት?
   እነርሱ የተናገሩት በወቅቱ በሥጋ በዚሁ ምድር ላሉ ወገኖቻቸው ነው ፡፡ እኛ ደግሞ ክርስቶስን በመልበሳችንና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ በመሆናችን በመንፈስ ህያው ከሆኑት ጋር /በሥጋ ቢሞቱም በመንፈስ ሕያው ናቸውና/ በጸሎታችን ኃይል የመገናኘት ዕድሉ አለን ፡፡ ሰፋ ያለውን ዝርዝር ወረድ ብለህ ምእመን May 9, 2013 at 10:21 AM ከሚለው ዝርዝር አንብብና ተረዳ ፡፡
   - ሰዎችን ከሌሎች በተለየ መልኩ ጻድቃን የሚያደርጋቸው መለኪያ ምንድን ነው? ደግሞስ እርሶ እንዳሉት የጸደቁት ለጸደቁት ነው? ወይስ የጸደቁት ላልጸደቁት?
   ሰዎችን ጻድቃን የሚያደርጋቸው በአብ መንፈስ ቀዱስ ያላቸው እምነትና ምግባራቸው ነው ፡፡ ጌታችን እንዳስተማራቸውና እንዳስተማረን ጸሎታቸው ሁላችንንም ይቅር በላቸው የሚል እንደሚሆን እገምታለሁ ፡፡ እኛም እንኳን በጸሎታች ወገን ለይተን አንተውም ፡፡
   - በቀጥታ ከአብ የሚያስፈልገንን ለመጠየቅ መልስ ለማግኘት እንድንችል መሆናችን አይደል?
   ከተመረጡት ወገን ከሆንክ በቀጥታ ማናገር ትችላለህ ፤ ርሱም ይሰማሃል ፡፡ እኛ ግን ቅድስናችን የመነመነችብን የጻድቃንና የቅዱሳንን ምልጃ እንሻለን
   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
  5. ሰላም ታቶ...ታቶ
   “Why do I need intercession? I can just pray to God ‎directly.” Of course there is no doubt that you could, but let us give an example. Have ‎you ever asked your friend, for instance, to pray for you so that God might help you at ‎school, or because a family member is ill, for instance? Sure, we probably all have. So, ‎if we ask someone on earth to pray on our behalf, how much more can we ask of the ‎saints and angels, who are in communion with God in heaven. ‎

   ‎”If we believe in the value of praying for one another, then we should believe in the value ‎of intercessions. Not to believe in the intercessions of the saints is either to deny that ‎these saints are alive or to deny that they are capable of praying. Both of these are ‎obviously wrong assumptions as clear from the scripture above. Therefore, denying the ‎value of intercessions is to reject the scriptures”

   Delete
  6. AnonymousMay 8, 2013 at 1:06 PM እውነት ባንተ ኮርቻለሁ እኔ ሳይማሩ ዶክተር በተባለው በአባ ሰላማዎች አባባል እምነት የለሹ፣ የዘዳቬንቺ ኮድ ክህደት ዋና አቀንቃኝ፣ የኦንሊ ጂሰሱ፣ የሰባልዮሱ፣ በምግባረ ብልሹነት ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በተደጋጋሚ በመታገድ የዲሲፕሊን እርምጃ የተወሰደበትና የግለሰቦችን ስም ለማጠፋት በጻፋቸው መጻሕፍቱ ታዋቂ በሆነው መሃይም ዘሪሁን ሙላቱ የተሰበከውን ስብከት ሰምቼ አፍሬ ነበር ግን እንዳንተ እና ምእመን አይነት ልጆችን ቤተክርስትያናችን ወልዳለችና እኮራለሁ ነገር ግን በናታችሁ ይህን አሳፋሪ ስብከት ከ youtube አጥፉት በናታችሁ www.youtube.com/watch?v=kJ1wuJWYp9A ቤትክርስቲያናችንን ያዋርዳል!!!

   Delete
  7. ewnt May 9, 2013 at 3:52 PM u are right ታውቃለህ ግን የቤትክርስቲያናችን ፓስተር ዳዊት ማለት ዘሪሁን ሙላቱ ነው (ፓስተር ዳዊት ነሸጥ ሲያርገው የሚናገረውን አያውቅም)ዘሪሁንም‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ባይሄድ እግዚአብሔርነቱ እኮ ቀረ››.... እያለ የሚዘባርቅ እብድ ነው !!! የተንኮልና የስድብ ጽሁፍ ለመጻፍ ግን የተሳካለት evil “Ghost Writer”እመሰክራለሁ ለምሳለ...የስድብ አፍ፣የጳጳሱ ቅሌት.....

   Delete
  8. ewntMay 9, 2013 at 3:52 1ኛ ዮሐ 2፤1 ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።ድሮም ሆነ ዛሬ በአብ ፊት የሚቆምልን ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ
   ክርስቶስ ነው፡፡ ይህንንም አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ሰዓታት ድርሰቱ ‘እግዚአብሔር በተከላት በምስክር
   ድንኳን ለቅዱሳን የሚቆምላቸው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው’ በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለሙ
   ሁሉ ፍጹም መሥዋዕትን ያቀረበ ዘላለማዊ ሊቀ ካህን መሆኑን ተናግሯል፡፡ ቅዱስ ቄርሎስም የክርስቶስን
   ከአብ ጋር አስታራቂነት በሃይማኖተ አበው ላይ ይናገራል፤ ‘እርሱ ለራሱ ልመናን የሚሻ መስሎ ከጥንት
   ጀምሮ ያገኘንን ፍዳ ከእኛ ያርቅ ዘንድ አብን ማለደው፤ እንደገና ደግሞ እንዲያስበን፣ ከእርሱም እንዳይለየን
   ስለ እኛ አብን ይማልደው ዘንድ ባሕርያችንን ነሥቷልና’ (ሃይ. አበው ዘቄርሎስ ፸፱ ክ፶÷፴፰)፡፡

   Delete
 2. "ካንቀላፉ ቅዱሳን ጋር ሕያዋን ቅዱሳን የሚገናኙበት እድል ስለሌለም «ለምኑልን አማልዱን» ብለው ቢጮሁ ሰሚ የሌለው ጩኸት ነው የሚሆነው፡፡... ይሁን እንጂ ቅዱሳን በክርስቶስ ጽድቅ የጸደቁ በእርሱ ምልጃ የተሸፈኑ እንጂ በራሳቸው ፍጹማን የሆኑ አይደሉም፡፡... ስለዚህ ቅዱሳን ካንቀላፉ በኋላ ያማልዱናል በሚል ወደእነርሱ መጸለይና እነርሱን ተስፋ ማድረግ የክርስቶስን መካከለኛነት አሌ ማለት ነው፡፡"

  This article goes against the Orthodox Church’s view on saints and their intercession. Saint intercession for mankind is not a new teaching; it dates back to the early centuries of the church. Scripture also proves it in multiple places.
  "the four living creatures and the twenty-four elders fell down before the Lamb. Each one had a harp and they were holding golden bowls full of incense, which are the prayers of God’s people." Rev. 5:8

  The church is the body of Christ. Death is the departure of the soul from the body. No where in the bible does it say death separates us from the body of Christ (Church). Jesus said "He is not the God of the dead, but of the living." Mark 12: 27. So there is no shame in asking the saints for their intercession because they are still alive in heaven.

  I don't know why you guys compared Lord Jesus' mediation with the intercession of the saints because it's completely different. No mere creature can replace our Lord. He is the only mediator between God and men; having satisfied the Divine justice required by the Father, and granting men the forgiveness of their sins by dying on our behalf as a propitiation for our sins. He is the sole advocate of mankind. Intercession of the Saints on behalf of men has nothing to do with propitiation and redemption. It is intercession on our behalf before Christ.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ፡፡

   Delete
 3. የኢየሱስን አማላጅነት ወይም አስታራቂነት የሚናገሩ ኃይለ ቃሎች
  - ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ። ኢሳ 53፡12 (አስታራቂነቱ ከልደቱ አስቀድሞ በትንቢት ተነግሮናል ማለት ነው)

  - እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ። ሉቃ 22፡32 (በተዋሕዶ በከበረው ሥጋዊ አካል በመሃላችን በኖርበት ዘመን አብን እየለመነ እንደ አማለደ የሚያስረዳን ነው)፡፡

  ከዚህ በታች የምጠቅሳቸው ቃሎች በአንድነት የሚብራሩ ስለሆኑ ቃሉን በአጠቃላይ ለመረዳት ሁሎችንም በአንድነት እናነባለን ፤
  1 - እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ሮሜ 8፡33-34

  - “እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤” ዕብ 5፡7

  እንደ ቃሉ በትንቢት የተነገረውን የአማላጅነት ወይም የአስታራቂነት ሥራ ከጽንሰት እስከ መስቀለ ሞት በመጓዝ ኢየሱስ ፈጽሞ መደምደሙን ያስረዳል ፡፡ ይህንንም በዕብራውያን መልዕክቱ በሚዳሰስና በሚታይ አካል በነበረበት ጊዜ እንደፈጸመው ሲያስረዳን በስጋው ወራት በማለት ገልጾታል ፡፡ ኢየሱስ አሁን ፣ ከትንሣዔውና ከእርገቱ በኋላ ማለት የአዳምን በበደል የወደቀ ሥጋ አክብሮ ፣ ወደ ጥንት መንበሩ ተመልሶ ፣ ዳግም ለመምጣትና ለመፍረድ ዝግጅት ላይ ነው ፡፡ እንህ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ያለው (ማር 16፡19 ፤ ማቴ 26፡64 ፤ሉቃ 22፡69 ፤ ሥራ 2፡33 ፣7፡55-56 ፤ ቆላ 3፡1 ፤ ዕብ 1፡3 ፣ 8፡1 ፣ 12፡1-2 ፤ 1 ጴጥ 3፡22 ) የሚሉት ቃሎች በክብር ዙፋኑ በእኩልነት ለመፍረድና ይቅር ለማለት ዝግጅት ላይ መሆኑን ያስተምራሉ ፡፡

  ነገር ግን በጌታ የቀረበው መስዋዕት (ዕብ 13፡12) ዘለዓለማዊ ስለሆነ (ዕብ 7፡17፡24 ፣ 9፡12 ፣ 1ዐ፡1ዐ፡12)፣ በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደምና ያቀረበው ሥጋ ፣ ላላመኑና ኢየሱስን ላልተቀበሉ ሁሉ ፣ ዓይናቸው ተገልጦ በሚያምኑ ጊዜ ይድኑበት ዘንድ ግን ዛሬም ሕያው መስዋዕት ሆኖ ይታይላቸዋል (ዕብ 7፡25 ፣ 9፡28)፡፡ ከሞተ በኋላ በጦር ጎኑ ሲወጋ ደም የፈሰሰበት ምሥጢር ፣ ሕያው መስዋዕታችን መሆኑን ያስረዳል ፡፡ ኢየሱስን አምነን ክርስቲያን የተባልን ሁሉ ከርሱ ጋር አንድነትንና ኀብረትን የመሠረትን ስለሆነ ከየዕለት ድክመታችንና በደላችን የምንታደሰው በንስሓና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚያዘውንን በመፈጸም ነው ፡፡ “ስርየት ባለበት ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም” ይላልና ወደ እቅፉና ርሱ ጥበቃ ሥር ከገባን በኋላ ተደጋጋሚ መስዋዕትነቱን ፤ ምልጃውን አንጠብቅም ፤ ዕብ 1ዐ፡18 ። ኢየሱስ አማላጅ ሳይሆን ይቅር ባይ አምላካችን ነው ብለን እናምናለን ፡፡

  ይህንኑ መጽሐፍ ሲያብራርልን ፣ ዕርቁንም ፈጽሞ የጥል ግድግዳው መፍረሱን ሲያበስረን “አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና። እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤ በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።(ኤፌ 2፡13 – 22)” ይላል ፡፡

  ይህንንም አንብበው የጥል ግድግዳውን ከፊት ለፊታቸው ያኖሩ ካሉ ግን አሁንም ዘለዓለማዊ መስዋዕቱ ስላለላቸው በእምነት በመቅረብ ድኀነታቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ ፤ ዕርቁም ይፈጸምላቸዋል ፡፡ በክርስቶስ ነው ያለነው እያሉን አሁንም አማላጅነቱን የሚያምኑና በየዕለቱ የሚጠብቁ ካሉ እውነትም ሃቅን እንዳያስተውሉ ግድግዳው ተጋርዶባቸዋል ማለት ይቻላል ፡፡

  ሥላሴ አንድ መለኮት ፣ አንድ ፈቃድ ፣ አንድ ሥልጣንና ባህርይ ስላላቸው ለአዳም ትውልድ ምሕረትን ለማምጣት ተስማሙ እንጅ በመሃላቸው መከፋፈል ያለ አስመስሎ አንደኛውን ዘላለማዊ ለማኝና አማላጅ ፣ የተቀረውን ደግሞ ተቀያሚ ወይም አኩራፊ ፣ ይቅር ለማለት የማይፈልግ ማድረግ የዶግማን ተፋልሶ ያስከትላል ፡፡ አማለደ የተባለውም በአዳም ላይ የተላለፈ ፍርድን ለመፈጸምና ለማስታረቅ ጌታችን ሰው መሆኑንና ዕዳችንን ለመክፈል ሞታችንን ሞቶ ፣ እኛን ነጻ ማውጣቱን ነው ፡፡ ዕዳችንን በመክፈል ፣ ቤዛነቱን ለማለት ፡፡

  አንድ ሰው የሚታረቀውና ይቅር የሚባለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ፡፡ ነጋ ጠባ ሲታረቅና ይቅር ሲባል አይኖርም ፡፡ በተለይም በሃይማኖት ሲሆን ደግሞ ከፈጠረን አምላክ ያለያየን አዳም የተሰጠውን ትእዛዝ አማክበሩ ነው ፡፡ ይህን ጸብ ጌታችን በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶና ሥጋውን ቆርሶ ፣ ሕይወቱንም አሳልፎ ሰጥቶ የልዩነት ግድግዳውን አፍርሶታል ፡፡ ክቡር ሕይወቱን ስለ እኛ ፍርድ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ዕርቁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተፈጽሟል ፡፡ ማስታረቁን ላመኑት ሰዎች ፣ የውርስ በደላቸውም ሆነ ፣ እርሱን እስከ አመኑበት ዕለት የፈጸሙት ኃጢአት ይሻርላቸዋል ፤ ሌሎች ወደፊት የሚመጡት ትውልዶች ደግሞ ሕያው መስዋዕት ስለሆነ ካመኑበት ሊድኑበት ዘላለም ይኖራል ፤ ይህ ትውልድ በእምነት ድኀነትን እንዳገኘ ሁሉ ፣ ከመቶና ሺህ ዓመትም በኋላ የሚያምነው ህዝብ በቀራንዮ መስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙና በተቆረሰ ሥጋው ድኀነትን ያገኛል፡፡ ዕብ 7፡24-25

  ሁሉንም ለመረዳት ጌታችን ሰው መሆን ያስፈለገው ፣ በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኖ እንዲቀርብ ያስገደደውን በደል ለይተን ማወቅ ጠቃሚ ነው ፡፡ ምክንያቱም ጻድቃን እንደነበሩ መጽሐፋችን ይናገራል ፡፡ እኒህ ጻድቃን ፣ ቅዱሳን ነቢያት የተባሉ ሁሉ ራሳቸውን ከሥጋዊ በደል ቢጠብቁም ፣ ከአዳማዊው በደል ማለትም ከጥንተ አብሶ ግን ራሳቸውን ማጽዳትና ነጻ ማድረግ አልቻሉም ፡፡ የኢየሱስም ወደ እዚህ ምድር በሥጋ መምጣት ይኸን በሰዎች ሊወገድ ያልተቻለውን ኃጢአት ፣ ካሳውን ከፍሎ ለመሻር ነው ፡፡

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ምእመን በእርግጥ ዕብራውያን 5፡7 የሚያወራው ኢየሱስ በስጋው ወራት ስላደረገው ምልጃ ነው። ይህ ክፍል ግን ኢየሱስ ምልጃ ያደረገው በስጋው ወራት ብቻ ነው አይልም። አዎን ኢየሱስ ሊቀካህናት እንደመሆኑ በስጋው ወራት ምልጃ አቅርቧል። ለምሳሌ ሉቃ 22፡31-32። ሆኖም መጽሃፍ ቅዱስ በሌላ ክፍል ደግሞ ኢየሱስ አሁን በእግዚአብሔር ቀኝ ሆኖም ስለ እኛ እንደሚማልድ በግልጽ ያናገራል።

   ሮሜ 8፡34
   የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው

   መጽሃፍ ቅዱስ የሚለውን አንዱን ሳናፍንና የምንፈልገውን ብቻ እየመረጥን ሳንወስድ ሁሉንም ልንቀበል ይገባል። በእኔ ግምት አንዳንዴ በሃይማኖታዊ ተለምዶ ሳንመረምር አስቀድመን የያዝናቸው መጽሃፍ ቅዱሳዊ የሚመስሉ ነገር ግን ያልሆኑ የራሳችን አስተሳሰቦች (preconceived ideas) ናቸው ብዙ ጊዜ ሙሉ ቃሉን እንዳንቀበል የሚያደርጉን። በሎጂክ እኮ ብቻ መሄድ በመጽሃፍ ቅዱስ አያዋጣም። መጽሃፍ ቅዱስ በግልጽ ያማልዳል እያለ አንተ አይ አያማልድም ትላለህ። ይህን የምትለው ከአንተ ሎጂክ ጋር ስላልሄደልህ ነው።

   እስቲ ሮሜ 8፡34ን አንብብ:-
   "የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" ያላል።
   በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ኢየሱስ ስለ እኛ ይማልዳል ይላል። አንተ ታዲያ እንዴት ብለህ ነው አያማልድም የምትለው?

   ዕብራውያን 7፡25ንም አንብብ፦
   "ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል"
   ስለዚህ ከትንሳኤ በኋላ ስላለው የኢየሱስ ህይወት ሲናገር፤ ስለ እነርሱም ሊማልድ ዘወትር በህይወት ይኖራል ነው የሚለው። ታዲያ መጽሃፍ ቅዱስ ኢየሱስ ከትንሳኤ በኋላ በአብ ቀኝም ሆኖ ይማልዳል ብሎ በግልጽ ከጻፈ አንተ ለምን ለመቀበል ይከብድሃል?

   ኢየሱስ አንዴ ነው የተሰዋው ሌላ መስዋእት ሊያቀርብ አያስፈልገውም። ጥያቄው ስለ መስዋእት ሳይሆን ስለ ምልጃና ልመና ነው። ምልጃ ደግሞ ኢየሱስ አሁንም ያደርጋል ይህን መጽሃፍ ቅዱስ በግልጽና በማያሻማ ቃላት የሚናገረው ነገር ነው።

   ከእኛ ሎጂክ ጋር ሄደ አልሄደ፤ መጽሃፍ ቅዱስ ያለውን ሳንጨምር ሳንቀንስ መቀበል አለብን። ከሌሎች ጥቅሶች ጋር የሚጋጭም ቢመስለን እንኳን፡ ከተጻፈው ለመቀነስ ወይም የተጻፈውን ለመለወጥ መሞከር የለብንም። ለቃሉ ታማኝ መሆን የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት መሰረትና ሀሁ ነውና።መጽሃፍ ቅዱስ ያማልድልናል ካለ ሌላ ቲዎሎጂና ሎጂክ አያስፈልግም። ያማልድልናል ማለት ያማልድልናል ማለት ነው በቃ አለቀ! የፈለጋችሁትን ያህል የቃላት ድርደራ ብታደርጉ ቃሉን ልትቀየሩ አትችሉምና አትልፉ።

   ሮሜ 8፡34
   የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው

   ዕብራውያን 7፡25
   ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል ኢየሱስ ሊቀ ካህናችን እንደሆነ ጨርሶ የዘነጉት ይመስላል። አንዱ የሊቀካህን ሥራ ደግሞ ስለ ህዝቡ መማለድ ነው። ሃጢአታቸውን ማሰረይ ብቻ አይደለም። ለምሳሌ ኢየሱስ አልፎ በሚሰጠብት ወቅት ምን አለ፤ "እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ" ይላል። ሉቃ 22፡31-32

   ስለዚህ ምልጃ ሲባል ስለ ሃጢአት ወይም የምንፈልገውን ነገር እግዚአብሔር እንዲሰጠን ብቻ አይደለም። መንፈሳዊ ውጊያንና አደጋንም ያካተተ ነው። በአባታችን ሆይ ጸሎት ላይ "ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን" የምንለው አይነት ጸሎት ማለት ነው። ስለዚህ ምልጃን በጣም አጥብበን ማየት የለብንም።

   ዮሃንስ 14፡13-16 ምን ይላል? ኢየሱስ ወደ አብ እንደሚሄድና አብን እንደሚለምን ይናገራል። "እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል"። ያላል ዕብራውያን 8:1-2 ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፥ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት። በተጨማሪም በአሁን ሰዓት በአብ ፊት ስለእኛ የሚታይልን ኢየሱስ ነው 1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው

   Delete
  2. ሮሜ 8፡ 28-35 ያለውን ቃል ስናነበው የመረጣቸውን፤ ያጸደቃቸውን፤ ያከበራቸውን እነዚህን እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? እያለ ይጠይቅና ቃሉ ለዚህ ጥያቄ እዚያው እንዲህ እያለ መልስ ይሰጣል ፦ መኰነንም ማጽደቅም የሚችለው ኢየሱስ እንደወነ ከሳሾች ግን ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ሲናገር ቁጥር 37 እንዲህ ይላል "በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።" ስለወነም ለዘመናት ሰዎች የራሳቸውን ሎጂክ ጥቅሱን እየተራሱ ያስትላለፉትን ለጊዜው ተውት አድረገን ምእራፉን በሙሉ ቢያነቡት እውነቱ ይበልጥ ይታይዎታል።

   ሃሳቦ በየጊዜው እየቀያየሩ አንዴ ጥቅሱ ብቻ እንይ ከጥቅሱ በላይ ያሉትን እና ሌሎች የመጸሃፍ ቅዱሱ ክፍሎች ለማፈን ከፈለጉ ቃሉ እንኳን አሁን እየማለደ ነው ብሉ አይገልጸውም ምክንያቱም የቃላቱ ዝይቤ እንካን ስናይ፡
   የሞተው፥ ያለፈን ነገር
   ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ ... አሁንም እንደተነሳ ነው ያለው
   በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ... አሁንም በቀኝ ያለው
   ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ... ከላይ "የሞተው" የሚለው ቃል አሁንም ጌታ ሞቶ እንዳለ እንዳማያሳይ ሁሉ የሚማልደው የሚለውም አሁን በሰማይ እይደርገው እንዳለ አይሳይም

   Delete
  3. ለ Anonymous May 9, 2013 at 11:11 PM
   - “ሮሜ 8፡34 ፤ የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው”

   የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ማነው ?
   መልሳችን ኢየሱስ የሚል ነው ፡፡
   የሚማልደውስ ቢባል አሁንም ኢየሱስ ነው ፡፡ ይሄን ቃል እኔም አልቀየርኩትም ፤ ምን ማለቱ እንደሆነ ግን ለማስረዳት አሁንም እጥራለሁ ፡፡

   - “በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ኢየሱስ ስለ እኛ ይማልዳል ይላል። አንተ ታዲያ እንዴት ብለህ ነው አያማልድም የምትለው?”
   ወገኔ አያማልድም ፣ አያስታርቅም የሚል ቃል አልወጣኝም ፡፡

   በጥምቀት ክርስቶስን ስንለብስ ፣ ሞትና ትንሣዔውንም ስንጋራው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አማልዶናል ብያለሁ ፡፡ አምነው ላልተጠመቁና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆን ላልቻሉት ወገኖች ደግሞ ፣ ዛሬም በመስቀል ላይ የሚፈሰው የበጉ ደም ባመኑበት ጊዜ ሊያድናቸው ፣ ሊያማልዳቸው ህያው መስዋዕት ሆኖ ይኖራል ፡፡ ለዛም ነው በዕብራውያን 7፡25 "ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል" ብሎ ያብራራው ፡፡ ህያው ያለውም በመስቀል ላይ የኢየሱስን ጎን በጦር በወጉት ጊዜ ትኩስ ደም ከሞተው ሰው በመፍሰሱ ነው ፡፡ ከላይ የጻፍኩትንና ከወንድም ሽመልስ መርጊያም ትምህርት ያመጣሁትን ጨምረህ መንፈስህን ተቆጣጥረህ ብታነበው በግልጽ ያስተላለፍኩትን መልዕክት ትረዳዋለህ ፡፡ ሥነ አመክንዮ ወይም ሌላ ጥበብ አልተቀላቀለበትም ፡፡

   አዎ ከድክመት ሊርቁ የማያስቡ ፣ ወይም የማይፈልጉ ሰዎች ዘወትር በየዕለቱ ዛሬም እየተንበረከከ ስለ እኛ ጸሎት ያደርሳል ፤ ይለምናል ፤ ያማልዳል ብለው ይመክራሉ ፤ ያስተምራሉ ፡፡ ያ ግን ንስሓ ገብተው ራሳቸውን እንዳይወቅሱ የሚፈጥሩት ትልቅ የስህተታቸው ማስረጃ ነው ፡፡ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያነት ራሳቸውን ካስረከቡ በኋላ ወደ ነበሩበት ክፋት መመለሳቸውና በሚያደርጉትም ላለመጸጸት የሚፈጥሩት የብልጠት ቋንቋ ነው ፡፡

   አሁንም አደራዬ የጻፍኩት በከባድ ቋንቋ ስላልሆነ ፣ እግዚአብሔር በፈቀደ የመጽሐፍን ቃል አስማምቶ ለማስረዳት ቀርቧልና ረጋ ብለህ ተመልከተው ፡፡

   በእርግጠኝነት የምነግርህ ግን አንድ ጊዜ ተጠምቀህ ፣ ሥጋወ ደሙን ተቀብለህ ፣ የኢየሱስን አምላክነትና ሰውነት ፣ ሞትና ትንሣዔውን ፣ ዳግም ምጽዓቱንም ካመንክ በኋላ ግን ዳግም አማላጅነት እንደሌለህ ነው ፡፡ ድክመት ካለብህ ንስሓ ግባ ፤ አንዴ ድኀነት ተፈጽሞልሃልና ዳግመኛ ዕርቅን አትጠብቀ ፡፡ በኤፌሶን መልዕክቱ የጥል ግድግዳው ፈርሷል ፤ ርቀን የነበርነው ቀርበናል እያለን ፣ ሁሌም ሊያስታርቅ መመላለስ አለበት ካልከኝ ግን የኢየሱስን ክቡር ደም የፍየልና የኮርማ አደረግኸው ማለት ነው ፡፡ በክርስትና ህይወት ውስጥ ላለነውም በየጊዜው ፣ በየዕለቱ መስዋዕቱንና ደሙን ማሳየት ፣ ማቅረብም ይኖርበታል ለማለት ልትገደድ ነው ፡፡ ይኸ ደግሞ መጽሐፋችን ከሚያስተምረው ቃል ውጭ ነው ፡፡ የሥጋ ጸባይ ሆኖ ብትሳሳት እንኳን ንሥሓ ግቡ ብሎ አስተምሯልና በንስሓ ወደ ቀደመው ቅድስናህ ትመለሳለህ ፡፡ ይኸ ነው የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ፡፡

   - “ዮሐንስ 14፡13-16 ምን ይላል? ኢየሱስ ወደ አብ እንደሚሄድና አብን እንደሚለምን ይናገራል። "እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል"።”

   ወንድሜ ብትችል ሙሉ ምዕራፉን አለያም ቁጥሩን ቀጠል አድርገህ እስከ ቁጥር 18 አንብበህ ተረዳው ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ ስለሚወጣ ፣ ሰለ መንፈስ ቅዱስ ነው የሚገልጽላቸው ፡፡ ኢየሱስ ወደ አብ ስለሚሄድ “ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም ፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።” አብም ሌላ አጽናኝ እንዲሰጣችሁ እጠይቃለሁ ወይም እለምናለሁ ማለቱ ነው እንጅ ፣ ዛሬም በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀን ፣ ከርሱ ጋር ኀብረትና አንድነት የፈጠርነውን ፣ ሁሌም እንደ እንግዳ ልጆቹ እንድንሆን ይለምንልናል ማለት አይደለም ፡፡ እንዲያውም ብታስታውሰው ይኸ ቃል መንፈስ ቅዱስ ከወልድም ይወጣል ለሚሉ ወገኖችም አስረጅ መልሳችን ስለሆነ ይጠቅምሃል ፡፡

   ከላይ የገለጽኩትን የሚያጠናክርልኝ ደግሞ ወረድ ብሎ ፣ አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል /ዮሐ 14፡26/ በማለት መግለጹ ነው ። መንፈስ ቅዱስ ከወልድ ስለማይወጣ ያንን ከአብ በመጠየቅ ማግኘት ይገባዋል ፡፡

   - "ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል" የሚናገረው በመስቀል ላይ የፈሰሰውን ክቡር ደሙን ነው ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በጦር ሲወጋ ለመሞቱ ማስረጃ እዥ ወይም መጽሐፍ ውሃ ያለው መፍሰሱ ነው ፤ ህያው ለመሆኑ ምስክሩ ደግሞ ትኩስ ደም መፍሰሱ ነው ፡፡ ከሞተ እንስሳም ሆነ ሰው ትኩስ ደም አይፈስም ፡፡ ዮሐንስ በመልዕክቱ እኒህን ምስክሮች ብሏቸዋል /1 ዮሐ 5፡8/

   እግዚአብሔር ይርዳህ ፤ ይርዳን ፡፡ አሜን ፡፡

   Delete
  4. ፡ዕብ.7:24-25 “እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” - - - እነዚህ ጥቅሶች ጌታችንን “አማላጅ” ነው በማለት የሚያስተላልፉት መልእክት የለም፡፡ የሰው ልጆች ሁሉ በክርስቶስ ቤዛነት አምነው ሲመጡ የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ ሆኑ የሚባሉት በስመ ስላሴ ተጠምቀው የክርስቶስን ስጋና ደም ሲቀበሉ ብቻ ነው፡፡ የክርስቶስ ስጋና ደም ደግሞ እንደ ኦሪት መስዋእት በአንድ ቀን የሚያልቅ ፡ በጊዜ ብዛት የሚለውጥ ፡ የሚበላሽ አይደለም ፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜ አዲስና ለዘላለሙ በህይወት የሚኖር ነው፡፡ “ሕያው” መባሉም ነፍስ ስለተዋሃደው ሳይሆን “መለኮት” ስለማይለየው ነው፡፡ - - - ይህ ሕያው ስጋውና ደሙ ሁልጊዜ ሰውን ወደ እግዚአብሄር ሲያቀርብ የሚኖር ከእግዚአብሄርም ጋር የመታረቂያው ብቸኛ መንገድ በመሆኑ አማለደን (አስታረቀን) ሲል ገልፆታል፡፡ “ሊያማልድ በህይወት ይኖራል” የሚለውንም በጥሬ ንባቡ ከሆነ ጌታችን አሁንም በስጋ ህይወት በምድር አለ ያስብልብናልና፡፡

   Delete
  5. thanks AnonymousMay 9, 2013 at 11:38 PM.ምእመን.... tehadsos say that Jesus is the intersesor. The thing is as our father Adam sinned on God the infinite, no finite or limited man could pay the penality, therefore the infinite God Lord Jesus Crisit had to be born in a form of finite body to pay our debit this is considered as intersesion of him with him self.

   Delete
  6. ....The problem as ምእመን clearly put it, some groups say that Jesus is the intersesor. The thing is as our father Adam sinned on God the infinite, no finite or limited man could pay the penality, therefore the infinite God Lord Jesus Crisit had to be born in a form of finite body to pay our debit this is considered as intersesion of him with him self. This means that our Lord is our advocate when we sin having made Himself the propitiation of
   our sins, who paid the wages of sin on our behalf. Christ's ad-
   vocacy with the Father is based on the fact that He has carried -instead of us- the iniquity of us
   all (Is 53:6).In this capacity He stands as a mediator between God and men. As a matter of fact, He is the
   only mediator between God and men; having satisfied the Divine justice required by the Father,
   and granting men the forgiveness of their sins by dying on their behalf as a propitiation for their
   sins.
   This is the meaning of the words of St. John the Apostle for he says: "If any man sin, we have an
   advocate with the Father, Jesus Christ the righteous: And He is the propitiation for our sins: and
   not for our sins only, but also for the sins of the whole world". (1Jn 2:1,2)
   This clearly exemplifies the propitiatory nature of Christ's advocacy. It is an advocacy on behalf
   of a sinful man; "if any man sin". A sinful man needs a propitiation. And the only One who
   offered this propitiation is Jesus Christ the righteous. Only he can be our advocate, through the
   blood He shed on our behalf.
   The same intent appears in St. Paul's designation of the Lord Christ as the only mediator between
   God and men: "one mediator between God and men, the man Christ Jesus; Who gave Himself a
   ransom for all" (1Ti 2:5). He mediates being the Redeemer who gave Himself and paid the
   wages of sin on our behalf.
   No one would argue this unique role of the Lord Christ as sole advocate of man-kind.
   Intercession of the Saints on behalf of men has nothing to do with propitiation and redemption. It
   is intercession on our behalf before Christ.

   Delete
  7. ....yes jesus in intressor but not on the concept of protestants understanding!He functions on our behalf and on God's behalf. Our Lord Jesus Christ is our Mediator!! Who made it possible for us to be reconciled with God through@ His death on the Cross for the forgiveness of our sin. He is now sitting at the right hand of His Father interceding@ for us. Through His intercession, He is able to save all who come to God through Him "Therefore He is also able to save to the uttermost those who come to God through Him, since He always lives to make intercession for them" (Heb 7:25). However, on Judgment Day when the time comes to give an account of our stewardship, when it is past the intercession time, it is our Lord Jesus Christ Who will judge! us.http://www.suscopts.org/q&a/index.php?qid=1384&catid=210

   Delete
  8. AnonymousMay 9, 2013 at 11:11 PM The truth about Christ's intercession or mediation is that he has completed it on earth. Being the High Priest, he entered into the Holy of Holies with His blood and has given us His blood to be able to enter the same place He is in. That blood is the blood He shed on the Cross about 2000 years ago.

   His intercession upto and including His work on the Cross will continue to mediate and intercede all believers with God until the end of the world. Thus, Christ is the eternal High Priest and Intercessor/Mediator because that salvation work on the Cross serves every believer for eternity. Other than that, Christ does not do any special intercession in heaven. His eternal intercession is through the work or intercession He did on the Cross, including His prayers in Getesemanie. He did not do just history, but a life giving work that serves all believers for eternity. Again, that is the only eternal intercession that Christ does. Accomplished, but lives for ever so that we all can be saved. That accomplished work on the Cross makes Christ an eternal intercessor. The author's suggestion that Christ does another intercession in heaven because of His flesh is completely wrong and is a big lie.

   Delete
 4. ቀደም ያሰፈርኩትን መልስ የሚያጠናክር ወይም የሚያሟላልኝ ስለሆነ ሽመልስ መርጊያ የተባሉ ወንድም በሌላ ገጽ ላይ ሲያስተምሩ ካሰፈሩት ተወስዷል ፡-

  “ክርስትና በሞት የምትቋጭ አይደለችም፡፡ እንደውም እኛ ከክርስቶስ ጋር ሞተን በትንሣኤው በመነሣት በሰማያዊ ሥፍራ ውስጥ አለን ፡፡ አሁን እኛ በጻድቃን ጉባኤ ውስጥ ነን፡፡ ክርስቶስ በሰጠን ሕይወት ውስጥ ሞት የለም የሥጋ ሞት ከቅዱሳን ነፍሳት ጋር ያለንን ሕብረት ፍጹም ያደርገዋል እንጂ አያቆራርጠውም፡፡ ሕይወታችንም መንፈስ ቅዱስ ከሆነ ቆየ፡፡ ስለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ “በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን”(ኤፌ.2፡8) እንዲሁም “እንግዲህ ከተነሣችሁ በክርስቶስ በእግዚብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም ፡፡ ሞታችኋልና ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና፡፡”(2ቆላ.3፡1-3) እንዲሁም “ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል ወደ ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም በደስታም ወደ ተሰባሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት በሰማያት ወደ ተጻፉ የበኩራት ማኅበር የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሚሆነው ወደ ኢየሱስ ደም ከአቤልም ደም ይለቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል፡፡”(ዕብ.12፡22-24)ይለናል፡፡ ደርሳችኋል ማለት ምን ማለት ነው? አንድ ሥፍራ ነው ያላችሁት ማለቱ አይደለምን? አንድ ሥፍራ መሆን ብቻ አይደለም “ከእንግዲህ ከቅዱሳን ጋር ባለአገሮች ናችሁና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም፡፡”(ኤፌ.2፡19) ይለናል፡፡ ስለዚህ ቤተሰብ ለቤተሰቡ አባል ማሰቡ ተገቢ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ያለበለዚያ ከአመነም ሰው ይልቅ የከፋ ነው (1ጢሞ.5፡8) ፡፡በእነዚህ ሁሉ መስረጃዎች እኛ ከቅዱሳን ሕብረት ውስጥ እንዳለን ተነግሮአል፡፡ እነዚህ ቅዱሳንም “የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ፡፡(ራእ.20፡6) የተባለላቸው ናቸው፡፡ እንደሚታወቀው ደግሞ የክህነት ሥልጣን በከንቱ አይሰጥም፡፡ ይህ ሁሉ ማስረጃዎች በዙሪያችን አሉ፡፡ ስለዚህ በጥምቀት የተመሠረተውን ሕብረትና አንድ ቤተሰብ መሆንን የሥጋ ሞት አይቆርጠውም እንደውም ይበልጥ ያጠናክረዋል፡፡ ለእናንተ የሥጋ ሞት ትልቁ ቁምነገራችሁ ነው፡፡ ምክንያቱም ገና ሥጋዊያን ናችሁና፡፡ በክርስቶስ የጥምቀት የተሰጠንን ሌላና አዲስ የሆነውን ሕይወት ባሕርይ ባለማወቃችሁ ነው፡፡”

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወደ ዕብራውያን 9፡1-14

   ፊተኛይቱም ደግሞ የአገልግሎት ስርዓትና የዚህ ዓለም የሆነው መቅደስ ነበራት።
   የመጀመሪያይቱ ድንኳን ተዘጋጅታ ነበርና፥ በእርስዋም ቅድስት በምትባለው ውስጥ መቅረዙና ጠረጴዛው የመስዋዕቱም ኅብስት ነበረባት፤
   ከሁለተኛውም መጋረጃ ወዲያ ቅድስተ ቅዱሳን የምትባለው ድንኳን ነበረች፥
   በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበረ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፤ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ፥
   በላይዋም ማስተስሪያውን የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበሩ፤ ስለ እነዚህም ስለ እያንዳንዳቸው ልንናገር አሁን አንችልም።

   ይህም እንደዚህ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል፤
   በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤
   ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል።

   ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፥ እንደዚህም መባና መስዋዕት ይቀርባሉ፤ እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም።

   ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥
   የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።

   የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥
   ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?

   Delete
  2. እግዚአብሔር ይስጥልኝ ፡፡ የራሳቸውን የስሜት ትርጉም ሳይቀላቅሁ ፣ እንዲህ እንዳንተ የወንጌል ቃልን የሚያስነብቡኝ አመሰግናቸዋለሁ ፡፡

   Delete
  3. ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት የሚችለው ሊቀ ካህናት ብቻ ነው - - - ይህንንም በዘሌ16፡2 የተጠቀሰውን ቅዱስ ጳውሎስ ዕብ.9:6-7 “ይህም እንደዚህ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል፤ በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤” በማለት በማያሻማ ሁኔታ ገልፆታል፡፡ ጌታችንም የገባባት ቅድስተ ቅዱሳን በሰው ያልተተከለች በፈቃደ እግዚአብሄር የሆነች ከእርሱም በፊት ከእርሱም በኅላ ማንም ያልገባባትና የማይገባባት ናት፡፡ ሊቀ ካህናት በአመት አንድ ጊዜ ይገባል ፡ እርሱ ግን አንድ ጊዜ ብቻ ገባ ፤ ለዓለምና ለዘላለም መስዋእቱ ሕያው ሆኖ ይኖራል፡፡ እነዚያ በየዓመቱ የሚገቡት ሟች ስለሆኑ መስዋእታቸውም ሙት ነውና ሌላ አዲስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ዕብ.9:11-12 “ ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥ የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።” ተብሎ ተፅፏል፡፡ ጌታችን የገባባት ድንኳን የተባለችው “መስቀል” ናት፡፡ ድንኳን ያላት የዘላለም መስዋእት የሆነው የጌታ ቅዱስ ስጋ የተቆረሰው ክቡር ደሙም የፈሰሰው በመስቀሉ ላይ ስለሆነ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ወደዚች ድንኳን “አንድ ጊዜ ፈፅሞ በገዛ ደሙ ወደ ቅድስት ገባ” በማለት ራሱን መስዋእት አድርጎ የወጣበት መስቀል መሆኑን በግልፅ አስረድቷል፡፡ “በሰው ያልተተከለች” ሲልም አይሁድ መስቀሉን ጌታን ለመግደል እንጂ መስዋእተ እግዚአብሄር ይቀርብበታል ብለው ስላልሆነ ነው፡፡ “ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች” ማለቱም በመስቀል ላይ እራሱን መስዋእት ሊያደርግ የሚችል ሰው የለም ፤ ቢኖርም እንኳ ሌላውን ራሱን ማዳን አይቻለውምና ፡ ለፍጥረት ባልሆነች ብሏታል፡፡

   Delete
 5. Wiiiiiiiiiiy endew minlargachihu? MIEMEN & the above one Anonymous May 8, 2013 at 1:06 PM. ORTHODOX FOR EVER. You explained it very well. Please go on. we are learning alot. Thanks, U help us to know the truth in every post.

  ReplyDelete
 6. ምእመን ስለክርስቶስ ምልጃነት ስንናገር ሰዎች ኢየሱስን ከአብ እንዳሳነስነው ወይም ደግሞ አምላክነቱን ዝቅ እንዳደረግነው ያስባሉ ነገር ግን ኢየሱስ አሁን በሰማይ እንደሚማልድ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተፅፎ እናያለን:: ኢየሱስ እግዝአብሔር እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱሰ በግልፅ ይነግረናል (ዮሐ 1:1; ሮሜ 9:5) ይህ እግዝአብሔር ወልድ በማርያም አድሮ ከማርያም ሥጋ ወስዶ የሰው ማንነት ሲኖረው የሰውን ተፈጥሮ በነበረው የአምላክ ማንነት ላይ ጨመረ ስለእዚህ ከማርያም ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነበር::ምልጃ ማለት ማሰታረቅ ስለሌላ አካል መለመን ማስማማት ማለት ነው፡ እስቲ ስለእዚህ ስለኢየሱስ የማማለድ ተግባር የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚል እንመልከት::ኢየሱስ በምድር ላይ በሰነበተበት የ3አመት ተኩል ጊዚያት፣ በተለያየ ሁኔታ የምልጃ ሥራን ሰርቷል፡

  ጌታ ኢየሱስ በምድር በነበረ ሰዓት ምልጃ ፈጽሟል ለምሳሌ በዮሐ 17 ጌታ ለደቀመዛሙርቱና ከቃላቸው የተነሳ ለሚያምኑ ሁሉ አንድ እንዲሆኑና በዓለምም እንዲጠብቃቸው ፀልዮል
  እንደዚሁም ደግሞ በሉቃስ 22፡31-33 ጌታም «ስምዖን ስምዖን ሆይ እነሆ ሰይጣን እንደስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ እኔ ግን እምነትህ እንደይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ»፡
  ይህም ብቻ ሳይሆን እዛው ሉቃስ 23፡34 «አባት ሆይ የሚያደረጉትን አያወቁምና ይቅር በላቸው» ሲል ለሚሰቅሉት ጸልዮል፡ አንግዲህ የዕብራዊያን ጸሐፊ ስለምልጃውና ስለጸሎቱ ሲናገር እንዲህ ይላል ዕብ 5፡7 «እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትና ምልጃን አቀረበ እግዚአብሔርንም ስለመፍራቱ ጸሎቱ ተሰማለት»ይላል፡፡ነገር ግን አሁን በአባቱ ቀኝ በተቀመጠበት ጊዜ እየሱስ-አያማልድም-ወይ??

  ኢየሱስ እንደ አምላክነቱ ጸሎትን የሚሰማ ተማላጅ አምላክ ቢሆንም እንደ ሰውነቱ በግብሩ (ሊቀ ካህንነቱ) ደግሞ ሥለ እኛ በሰማያዊት መቅደስ ያለ ብቸኛ አማላጅ/አስታራቂ/መካከለኛ ነው፡ የተሰጠውን ተልዕኮ በመፈፀም በምድር አገልግልዋል:: አሁን ደግሞ የዕብራዊያን ጸሐፊ እንደሚናገረው ኢየሱስ በሰማይ በሰው እጅ ባልተሰራችውና በእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው ይለናል (ዕብ 8፣1-2፡)

  ለሰማያዊው መቅደስና አውነተኛ ድንኳን ምሳሌና ጥላ በነበረችው ውስጥ በምድር ሊቀ ካህን በዓመት አንድ ጊዜ መሰዋዕት እያቀረበ ህዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ያሰታርቅ ነበር (ዕብ 9 በሙሉ) ፡ ነገር ግን ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህን ሆኖ በሰው እጅ ወደተሰራችው ሳይሆን ወደ እውነተኛይቱ ድንኳን በእግዚአብሔር ፊት አሁን ስለአኛ ይታይልን ዘንድ ወደ እርሷ ገባ ይላል(ዕብ 9፣24):: “አሁን” የሚለው ቃል ማስተዋል አለብን ምክኒያቱም አሁንም በእግዚአብሔር ፊት ስለአኛ የሚታይልን ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ሌላም ቦታ በሮሜ 8፣34 ላይ ኢየሱስ ካረገ በኋላ ስለምልጃው ሲናገር፡ «የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው»፡፡ አዚህ ላይ ደግመን ማሰተማል ያለብን ነገር… ፣የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው፣ የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ሐላፊ ግዜን ሲሆን ፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ፣ የሚለው ግን አሁንን ነው የሚያመለክተው፣ በዚህም ላይ ጨምሮ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ይላል::የኢየሱስ ክህነት/ምልጃ ዘላለማዊና የማይለወጥ ክህነት/ምልጃ ነው

  «… እርሱ (ኢየሱስ) ግን የማይለወጥ ክህነት አለው…(ዕብ 7:24)፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ / እህቴ ሰላምህ/ሽ ይብዛ ፡፡
   የኢየሱስን ማንነት ማወቅ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ግዴታውና የእምነቱ መሠረት ነው ፡፡ አሁን በቅርቡ ኢየሱስ አምላክ ነው ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አይደለም የሚሉ ክርስቲያን ነን የሚሉ ወንድሞችን በጽሁፍ ተዋውቄአለሁ ፡፡ ስለ ጌታችን ማንነትና ሥራ ጠንቅቀን ካላወቅን ነገ እኛም ሌላ የራሳችንን ኢየሱስ የማናወጣበት ፣ የማንፈለስፍበት ምክንያት አይታየኝም ፡፡ ስለዚህም በሥርዓቱ ወንጌልን ከብሉይ መጽሐፍት እያዛመድን በማጥናት ድክመታችንን እንድናስወግድ እመክራለሁ ፡፡

   ኢየሱስ አማለደ ስለ ተባለ ሥላሴ ወደው ፈቅደው የፈጸመው ነውና ከአብ አያሳንሰውም ፡፡ ለምን ወንድሞች አማለደ አሉ ብዬም ማንንም አልከራከርም ፡፡ ነገር ግን ከምን እንዳማለደን ፣ እንዴት እንዳማለደን እንዲያስረዱኝ እጠይቃለሁ ፡፡ የተሳሳተ ከሆነብኝ ደግሞ የኔን ግንዛቤና የማምንበትን አካፍላለሁ ፡፡ እኛ አማኞቹን ካስታረቀ በኋላ ግን ዛሬም ነገም አማላጄ ነው ሲሉብኝ የተሳሳተ ሃይማኖት ነው እላለሁ ፡፡ ርሱን መካድ ፤ የከፈለውን መስዋዕትነትም ዋጋ ማሳጣት ስለሚሆንም ለማስረዳት እተጋለሁ ፡፡

   ብንማማር በዚህኛው ዘዴ ልሞክር ፡፡
   ኢየሱስ የሚያማልደው በምኑ ነው ?
   መልሳችን ስለ እኛ በተቆረሰው ሥጋውና በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙ የሚል ነው ፡፡

   የቀደመችዋ የመቅደስ ሥርዓት ምን ትመስል ነበር ?
   ከላይ እንደተጠቀሰው ካህኑ ምእመናን የሚያቀርቡለትን ፍየልና ኮርማ እያረደ ደም በመርጨት ያገለግል ነበር ፡፡ መስዋዕቱም ዘለዓለማዊ ስላልሆነ ፣ ይኸንኑ በየዓመቱ መደጋገም ያስፈልገዋል ፡፡

   ኢየሱስ ለእኔ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝና የሚያድነኝ እንዴት ነው ?
   በመስቀል ላይ አንድ ጊዜ ራሱን መስዋዕት አድርጎ በማቅረብ ነው ፡፡ ራሱ ካህን ፣ ራሱ መስዋዕት ፣ ራሱ መስዋዕት ተቀባይ በሆነበት ሥርዓት ነው ያገለገለው ፤ የሚያገለግለው ፡፡

   አንድ ጊዜ ከተሰዋልኝ በኋላ ኢየሱስ መስዋዕቱን እንደ ቀድሞዎቹ ካህናት በየዓመቱ ሊያቀርብልኝ ይገባዋል ?
   መልሴ አይገባውም የሚል ነው ፡፡ ምክንያቱም የርሱ መስዋዕትነት ከፍየልና ከጠቦት የተለየ ዘለዓለማዊ ስለሆነ ነው ፡፡ በክርስትና ጉዞዬ ብሰንፍ እንኳን የንስሓን ሥርዓት መሥርቶልኛልና ፣ ከድክመቴ በንሥሓና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ራሴን አጸዳለሁ ፡፡ እኔም አንዴ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የርሱ ቤተሰብም ሆኛለሁና ፣ ከታረቅሁ በኋላ በየጊዜው እንደ እንግዳ ጸበኛ አልቆጠርም ፡፡

   እናም ስለዚህ አሁን ስለአኛ ይታይልን ዘንድ የሚለው ቃል ምን ያስረዳናል ?
   በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ተጠምቀው እርሱን ላላመኑትና ለሚመጡትም ትውልዶች እንደ ተስፋ ቃል ኪዳን ያገለግላል ፡፡ ኢየሱስ የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ሞቶ ዛሬም ለምናምነው መስዋዕታችን ሆኖልናል ለማለት ነው ፡፡ ለወደፊቱም ትውልድ እስከ ምጽዓት እንዲሁ እያለ ይቀጥላል ፡፡ መስዋዕትነቱ ድሮ በዘመኑ ለነበሩ ወገኖቹ ብቻ አልነበረም ፡፡

   እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡

   Delete
  2. ነገር ግን ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህን ሆኖ በሰው እጅ ወደተሰራችው ሳይሆን ወደ እውነተኛይቱ ድንኳን በእግዚአብሔር ፊት አሁን ስለአኛ ይታይልን ዘንድ ወደ እርሷ ገባ ይላል(ዕብ 9፣24):: “አሁን” የሚለው ቃል ማስተዋል አለብን ምክኒያቱም አሁንም በእግዚአብሔር ፊት ስለአኛ የሚታይልን ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ....ahunm AnonymousMay 9, 2013 at 11:23 PM አንተ እንድታስተውል እምፈልገው ..አሁን...የምትለውን ቃል ነው...ሙሉውን እብራውያን 9ን እናንብበው.... ተከተለኝ..(ዕብ 9:24) ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን@ ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ(በእውነተኛይቱ ሰው በማይገባባት ቅድስተ ቅዱሳን (መስቀል)) አንድ ጊዜ ገባ።

   25 ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ@ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም! የት?((መስቀል))

   26 እንዲህ@(ብዙ ጊዜ ገብቶ ቢሆን ኖሮ) ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ@ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ@ ጊዜ ተገልጦአል(ታየ)።

   27 ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥

   28 እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ( ተሰውቶ ወደ መስቀል ገብቶ ከታየ) በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል። ስለዚህ ስናጠቃልለው ታየ ወደ ሰማይ አሁን ገባ የተባለው አሁን አሁን አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ@ ጊዜ ተገልጦአል ከተባለበት አሁን ጋር ተመሳሳይ ነው ....ጌታችን ታየ ወደ ሰማይ አሁን ገባ ሊባል የተገባው ፍፁም በእውነተኛይቱ ሰው በማይገባባት ቅድስተ ቅዱሳን (መስቀል) አንድ ጊዜ ብቻ ስለገባ ፡ በእርሷም እውነተኛውን መስዋእቱን (ራሱን) ስላቀረበና ሃጢአተ አለምን ስላራቀ ነው፡፡

   Delete
  3. to AnonymousMay 9, 2013 at 11:23 PM
   .... ሊቀ ካህናት ከሰው ተመርጦ ለሰው ይሾማል - - - ዕብ.5:1 ጌታችን ክርስቶስም ፍፁም አምላክ ሲሆን ፍፁም ሰው ነው፡፡ የአብርሃም ልጅ የዳዊት ልጅ ተብሏልና፡፡ማቴ 1፡1 ሊቀ ካህናት ስለሰው እንደሚሾም ጌታችንም ሰው የሆነውና ክህነትን ገንዘብ ያደረገው(ስጋን የተቀባው፣የተሾመው፣ስጋ የለበሰው) ስለ ሰው ነው፡፡ የሊቀ ካህናት ዋናው አገልግሎት መባንና መስዋእትን ማቅረብ ነው፡፡ ጌታችንም የዓለምን ሃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ የተባለበት ዮሐ1፡29 ራሱን መስዋእት አድርጎ ያቀረበ ብቸኛ ሊቀ ካህን ነው፡፡ ራሱ መስዋእት በመሆኑም ሌላ የሚያቀርበው መስዋእት አላስፈለገውም፡፡ ሁለቱንም አንድ ጊዜ መሆን ይቻለዋልና፡፡ ዕብ.9:12 “የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።” ዕብ.10:12 “እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ” እንዲል፡፡ ዕብ.9:26 “- - - አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።” የተባለው ለዚህ ነው፡፡ ዕብ.8:1-3 “ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፥ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት።ሊቀ ካህናት ሁሉ መባንና መሥዋዕትን ሊያቀርብ ይሾማልና፤ ስለዚህም ለዚህ ደግሞ የሚያቀርበው አንዳች ሊኖረው የግድ ነው።” እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ “በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን” “እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፥ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት።” የተባለውበሰው ፈቃድ ያይደለ በእግዚአብሄር ፈቃድ በተተከለች በደብተራ መስቀል ራሱን መስዋእት ፡ መስዋእት አቅራቢውም ራሱ ደግሞም መስዋእቱንም ተቀባይ ራሱ ሆኖ ለቅዱሳን(ለኛ) ሲያገለግል ኑሮ ነበር፡፡ የቀደሙት ሊቀካህናት በሰው በተተከለችው ቅድስተ ቅዱሳን በአመት አንድ ጊዜ መስዋእትን ሊያቀርቡ እንደሚገቡ ያይደለ ለክርስቶስ ግን በእግዚአብሄር በተተከለች ደሙን ባፈሰሰባት ፡ ስጋውን በቆረሰባት ፡ ነፍሱን ካሳ አድርጎ በሰጠባት እውነተኛይቱ መቅደስና ድንኳን በተባለች በመስቀል አንድ ጊዜ ፈፅሞ ገባ ማለት ተሰቀለ፡፡ መስዋእቱን ያቀረበው ክርስቶስ የቀረበው መስዋእት የክርስቶስ ክቡር ስጋው ቅዱስ ደሙ ስለሆነ መስዋእት አቅራቢው እንደሌሎቹ ሊቀካህናት በራሱ ህፀፀ የለበትምና መስዋእቱም የሚበላሽ ፡ የሚሞት ፡ የሚበሰብስ እንደሆነው የቀደመው መስዋእት አይደለምና ነገር ግን ነገር ግን ለዘላለም የሚኖር ክርስቶስ ራሱን መስዋእት አድርጓልና የማስታረቁ ተግባር ፍፁም ነው፡፡ እርሱም ክህነቱ ፍፁም መሥዋእቱም ህያው ስለሆነ እለት እለት መስዋእት ማቅረብ አላስፈለገውም፡፡ይህንን አንድ ጊዜ ፈፅሞ አድርጓልና፡፡ ክቡር ደሙና ቅዱስ ስጋውም ለዘላለም አምነውና በስላሴ ስም ተጠምቀው የሚመጡትን ሰወች ከሃጢአታቸው አጥቦ የዘላለም ህይወትን ሊያወራሳቸው ይችላል ማለት ነው፡፡ ዘወትር (አሁንም) መስዋእትን በሰማይ ያቀርባል ካልን እለት እለት በሰማያት ክርስቶስ ወደ እውነተኛይቱ ድንኳን (መስቀል) ይወጣል ማለት ይሆንብናል (ይህም ይሰቀላል ማለታቸን ነው) - - - ደግሞም የክርስቶስ መስዋእት እንደሌሎቹ ሊቀ ካህናት መስዋእት ድካም አለበት ፍፁም አይደለምና አንድ ጊዜ የሰዋው መስዋእት አልበቃውም ማለት ይሆንብናል፡፡ - - - ሌላም ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሰዋው መስዋእት ሙሉውን የሰው ልጅ እዳ በደል አላቀለለም ማለት ይሆንብናል፡፡ ይህም ሊባል አይገባም ክርስቶስም አንድ ጊዜ ባቀረበው መስዋእት ሰውን ሁሉ ይቅር ብሏል ፡የማስታረቅንም ተግባር ፈፅሟል በሰማያትም በአባቱም ቀኝ ተቀምጧል ይህም መቀመጡን እንጂ ለአገልግሎት መቆሙን አያሳይም፡፡.....

   Delete
  4. መሥዋዕትን አንዴ (አንድ ጊዜ) ያቀረበ ሊቀ ካህናት ነው፡፡ የዘመነ ብሉይ ሊቃነ ካህናት ለኃጢአት ሥርየት የሚያቀርቡት መሥዋዕት ፍጹም ድኅነትን ስለማይሰጥ ዕለት ዕለት ይሠዉ ነበር፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን አንድ ቀን ስለ ዓለም ሁሉ መዳን በቀራንዮ ላይ መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ የዓለምን ኃጢአት ስላስወገደ በእርሱ ያመነ ሁሉ ተረፈ ኃጢአት (የማይደመሰስ ኃጢአት) ስለማይኖርበት በየጊዜው ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡ ዓለም ሁሉ በእርሱ ካመነ በዕለተ ዐርቡ መሥዋዕት ይድናል እንጂ ሌላ ተጨማሪ መሥዋዕት አይቀርብለትም፡፡ የኃጢአተኛ ተለዋጭ ሆኖ የቀረበው የመሥዋዕቱ በግ ክርስቶስ አንድ ነውና /ዕብ.7፡27-28/፡፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ አምነን ተጠምቀን የክርስቶስ ማደርያ ከሆንን በኋላ ክፉ ሐሳብ ወደ ራሳችን ሰብስበን ወይም ደግሞ ሰው አገብሮን ተጋፍቶን በገቢር ብንበድል (ሃይማኖታችንን ክደን ቆይተን ብንመለስ እንኳን) ዳግመኛ ንስሐ ገብተን እንመለሳለን እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ ኃጢአታችንን ለማስተሥረይ ሁለተኛ ጥምቀት ሁለተኛ መሥዋዕት አይቀርብልንም፤ ወልደ እግዚአብሔርንም ዳግመኛ ተሰቀልልን መከራ ተቀበልልን የለምንለው አይደለም /ዕብ.10፡26/፡፡በአብ ቀኝ የተቀመጠ ሊቀ ካህናት ነው፡፡ የዘመነ ብሉይ ሊቃነ ካህናት ወደ ምድራዊቱ ቅድስት ሥፍራ በዓመት አንድ ጊዜ በብዙ ፍርሐትና ረዐድ ይገቡ ነበር፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እንዲህ አልገባም፡፡ ሐዋርያው፡- “ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው፡፡ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፡፡ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት” እንዲል /ዕብ.8፡1-2/፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ እንደ ወረደ ግልጽ ነው /ዮሐ.3፡13/፡፡ ሆኖም ግን “ወረደ” የሚለው አገላለጽ ለምልዓተ መለኰቱ ወሰን ለሌለው ለመለኰታዊ ቃል የሚስማማ አይደለም፡፡ ሰው ሆኖ፣ ሥጋ ለብሶ፣ ባጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት ተወስኖ ለድኅነተ ዓለም መገለጡን፤ ለሕማም፣ ለሞት፣ ለመሥዋዕትነት መምጣቱን የሚገልጽ እንጂ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለዚህ ሲናገር፡- “ወልድ ዋሕድ እንደ መላእክት ቦታውን የለቀቀ አይደለም፤ በአንድ ፈቃድ ከአባቱ ጋር እያለ ነው እንጂ፡፡ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ በተላከ ጊዜ እንደ መላእክት ቦታውን ለቆ የሄደ አይደለም፤ እነዚያ በተላኩ ጊዜ ቦታቸውን ለቀው ይሄዳሉና፡፡ በምልዓት ሳለ እንደ መላእክት ቦታውን ሳይለቅ ሥጋን ተዋሐደ እንጂ” ይላል /ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድር.3፡153-158/፡፡ ልክ እንደዚሁ “ተቀመጠ” የሚለው ቃልም ሥራዉን መጨረሱን፣ ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን፣ ድኅነተ ዓለም መፈጸሙን የሚያመለክት እንጂ እንደተናገርነው ለምልዓተ መለኰቱ ቦታ ተወስኖለት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትም ይህን ሲያመሰጥሩት፡- “ጌታ ከምልዓተ መለኰቱ የተወሰነበት ወቅት ኑሮ መንበረ ክብሩን ተቆጣጠረ ወይም ከመለኰታዊ ክብሩ ተራቁቶ ኑሮ ወደ መለኰታዊ ክብሩ በተመለሰ ጊዜ መለኰታዊ ክብሩን ተቆጣጠረ ማለት ሳይሆን ሰውን ለማዳን ሰው ሆኖ ሰማያዊ ያልነበረውን (ክብር የለሽ የነበረውን) የሰውን ባሕርይ ማክበሩንና በእርሱ ክብር መክበራችን፣ በክብር ቦታ መቀመጣችን፣ የሰው ልጅ ሁሉ በክርስቶስ መክበሩን ነው” ይላሉ /ኤፌ.2፡6-7/፡፡ “በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉ ይሁን” /ራዕ.5፡14/፡፡በገዛ ደሙ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የገባ ሊቀ ካህናት ነው፡፡ የዘመነ ብሉዩ ሊቀ ካህናት ለኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን ለሚቃጠል መሥዋዕትም አውራ በግ ይዞ የዚህ ዓለም (አፍአዊ) ወደ ሆነችው መቅደስ ይገባ ነበር፡፡ አገልግሎቱም ሁሉ ምድራዊ ዓለማዊ ነበር፤ ሥጋን እንጂ ነፍስን መቀደስ የማይቻለው ነበር /ዘሌ.16፡3/፡፡ እንደ ወንበዴ ከወንበዴዎች ጋር የተሰቀለው፣ የተናቀው፣ ገሊላዊ፣ የዓለምንም ኃጢአት ያስወገደው የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እንደተጻፈ በደመ በግዕ በደመ ላህም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የገባ አይደለም፡፡ ራሱ መሥዋዕት፣ ራሱ ተወካፌ መሥዋዕት (መሥዋዕት ተቀባይ)፣ ራሱ ይቅር ባይ ሊቀ ካህናት አስታራቂ መሥዋዕት አቅራቢ ሆኖ ገባ እንጂ /ዮሐ.1፡29, St. Augustine, On Ps. 65./፡፡ ሐዋርያው፡- “ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን የዘለዓለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም” እንዲል /ዕብ.9፡11-13/፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጠቀም ብሎ ሳይሆን ቅዱሳንን ሊያገለግል ደሙን ይዞ የገባባት ቅድስተ ቅዱሳን ማን ናት? ...

   Delete
  5. ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጠቀም ብሎ ሳይሆን ቅዱሳንን ሊያገለግል ደሙን ይዞ የገባባት ቅድስተ ቅዱሳን ማን ናት? ለሚለው ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ሁለት ነው አንዱ ከላይ ያየነው መስቀል ናት የሚል ነው ሁለተኛው ግን....“ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ በምትበልጠውና በምትሻለው በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንጂ በዘር በሩካቤ ባልተከፈለች /ማቴ.1፡20/ በሥጋው መሥዋዕት በኵል /ዕብ.10፡20/ ስለ እኛ ይታይ ዘንድ፣ እንደ አይሁድ ሐሳብ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ዕቅድ መስቀል ላይ በሠዋው አንድ መሥዋዕት ከራሱ ከባሕርይ አባቱና ማኅየዊ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያስታርቀን ዘንድ የገባባት ቅድስተ ቅዱሳን እዝነ አብ (የአብ ጀሮ) ገጸ አብ (የአብ ፊት) ናት” /St.John Chrysostom, Homily on the Epistle Of Hebrews, Hom.15፣ ዕብ.9፡24/፡፡ አስቀድመን እንደተናገርነው ጌታችን ወደ እዝነ አብ ወደ ገጸ አብ አቀረበን ስንል (በሥላሴ ዘንድ ተከፍሎ ስለሌለ) የታረቅነው ከሥላሴ ጋር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ መሥዋዕት ተቀባዩ አብ ብቻ እንዳልሆነ የታወቀ የተረዳ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ሊቃውንትም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ይህን ክፍል በተረጐሙበት አንቀጽ፡- “ለምትመጣው ሕግ ለወንጌል ሊቀ ካህናት ሆኖ የመጣው ክርስቶስ ግን በምክንያተ ዘርዕ ያይደለ እንበለ ዘርዕ ወደተገኘች ወደ ደብተራ ርእሱ፣ በሰው ፈቃድ ያይደለ በእርሱ ፈቃድ ወደ ተተከለች ደብተራ መስቀል ደመ ላህም፣ ደመ ጠሊን ይዞ የገባ አይደለም፤ ደሙን ይዞ አንድ ጊዜ ወደ እዝነ አብ ወደ ገጸ አብ ገባ እንጂ” ብለዋል /የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡ ከነትርጓሜው፣ ገጽ 441/፡፡ ተወዳጆች ሆይ! አንድ ፍጹም ልንረሳው የማይገባ መሠረታዊ ነገር አለ፡፡ እርሱም ምን እንደሆነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይነግረናል፡- “የጌታችን አገልግሎቱ እዚህ ምድር በመስቀል ላይ የተፈጸመ ቢሆንም እንደ ቀደሙት ሊቃነ ካህናት ምድራዊ አገልግሎት አልነበረም፤ ሰማያዊ እንጂ፡፡ ለምን ቢሉ ምእመናን በእርሱ አምነን መጠመቅን ገንዘብ አድርገን የሰማያውያን ሥራ እየሠራን የእርሱ ልጆች እንሆናለንና፡፡ ሐሳባችንም ሀገራችንም መንግሥተ ሰማያት ነውና፡፡ ምስጋናችንም ከመላእክት ጋር ኅብረት አንድነት ያለው ሰማያዊ ነውና፡፡ መሥዋዕታችንም እንጨት ማግዶ እሳት አንድዶ የሚቀርብ የላም የበግ ደም ሳይሆን ሰማያዊው መሥዋዕት (ክርስቶስ) ነውና፡፡ ሕጉም (ወንጌሉም) ክህነቱም ሰማያዊ ነውና፡፡ መሥዋዕታችን እንደ ቀደመው ኪዳን መሥዋዕት አመድና ጢስ እንዲሁም መዓዛ ሆኖ የሚቀር ሳይሆን ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ የሚሆን ክብር ነውና፡፡ ይህን የምናከናውንበት ሥርዓተ ቅዳሴአችንም ሰማያዊ ነውና” /ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድር.14፡58-77/፡፡ የስነ መለኰት ምሁራንም እንዲህ ሲሉ ይህን የቅዱሱ ሐሳብ ያጐለሙሱታል፡- “ምንም እንኳን በምድራዊቷ ድንኳን (ቅድስት ቤተ ክርስቲያን) ብንሆንም ክርስቲያኖች ወደዚሁ ቅዱስ መሥዋዕት (ወደ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ) በምንቀርብበት ሰዓት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንገባለን፤ ማንነታችን ከጊዜና ከቦታ ቀመር ውጪ /Kairos/ ይሆናል፡፡ እዚህ ሆነን የመንግሥተ ሰማያትን ኑሮ እንለማመዳለን፡፡ እንግዲህ በክርስቶስ ሁላችን ሰማያውያን መሆናችን አይደለምን? ሰማያውያን ከሆንን እኛ አስቀድመው በስጋ ከተለዩን ጋር ለመገናኘት ምን ይከለክለናል ፤ ወይንስ ሰማይ ሰፊ ነው የሚል አለን? እንኪያስ በክርስቶስ ሁላችን በእርሱ ግንድነት ቅርንጫፍ ሆነን ተሰርተናል እንላለን ፤ እንግዲህ ቅዱሳን ሁሉ ቅርንጫፍ ሆነው በአንድ ግንድነት ከተተከሉ ፡ እኔም ለዚህ ክብር ከተጠራሁ ፡ ከቅዱሳን ጋር ዘመድ መሆኔ አይደለምን? ወይንስ ዛፍስ ከውጭ ነው የሚለኝ አለን? እንኪያስ በክርስቶስ ሁላችን አንድ ቤተሰብ ሆነናል እላለሁኝ

   Delete
  6. AnonymousMay 9, 2013 at 11:23 PM.....«… እርሱ (ኢየሱስ) ግን የማይለወጥ ክህነት አለው…(ዕብ 7:24)፡አዎ ግንሳ???. የቀደሙት ሊቃነ ካህናት ያለ መሓላ ለተሠራችው ሕገ ኦሪት የተሾሙ ስለ ነበሩ አንድም መዋትያን ስለ ነበሩ ካህናት የሆኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በመሓላ ለተሠራችው ወንጌል የተሾመ ስለሆነ አንድም ሞትን በሞቱ ገድሎ ተነሥቶ በሕይወት የሚኖር ሥግው ቃል ስለሆነ ወራሽ የሌለው አንድ ነው፡፡ ክህነቱም (ኃጢአት የማሥተስረይ ችሎታውም) የባሕርዩ ስለ ሆነ በሞት (ሞት ሊያሸንፈው ስላልቻለ) አይለወጥም፡፡ የባሕርዩ የሆነውን ለእነዚያ በጸጋ ሰጥቷቸው ነበርና ሥጋ ለብሶ በክህነት ሲገለጥ ባሕርያዊ ሥልጣኑ የማይሻር ሆነ፡፡ ሐዋርያውም ይህን አስመልክቶ ሲናገር፡- “እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘለዓለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው” አለን /ዕብ.7፡23-24/፡፡
   ሐዋርያው እንዲህ ይላል፡- “የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና፡፡ ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል” /ዕብ.7፡25/፡፡ ካቶሊክ ሳትታሰብ ፕሮቴስታንትም ሳትታለም ከ325 እስከ 389 ዓ.ም የነበረውና የቀጰዶቅያ አውራጃ ለምትሆን የቂሳርያ ሊቀ ጳጳስ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ይህን ሲተረጕመው እንዲህ ይላል፡- “ይህ ቃል የሚያመለክተን የጌታችን አስታራቂነቱን ነው፡፡… ምክንያቱም መጽሐፍ እንደሚል አንድ እግዚአብሔር አለና፣ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው (ሰው ሆኖ ሰውና እግዚአብሔርን ያስታረቀ) ደግሞ አንድ አለ፣ እርሱም (ለሁሉ ቤዛ አድርጎ ራሱን አሳልፎ ለሞት ለሕማም የሰጠ) ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው /1ጢሞ.2፡5-6/፡፡ አሁንም ይህ ሥግው ቃል ከመቃብር በላይ ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ “በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን” እንላለን /1ኛ ዮሐ.2፡1/፡፡ ሆኖም ግን ይህን በአብ ፊት በመውደቅና በመነሣት የሚያደርገው አይደለም፤ በዕለተ ዐርብ በተቀበለው መከራ ባደረገው ተልእኮ እንጂ” /On The Son, Theological Oration, 4(30):14/፡፡ ከ347 እስከ 407 ዓ.ም የነበረውና የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንዲህ ይላል፡- “የቀደሙት ሊቀነ ካህናት መዋትያን ስለ ነበሩ ብዙ ናቸው፡፡ እርሱ ግን የማይሞት ሕያው ስለሆነ አንድ ነው፡፡ የማይሞትም ስለ ሆነ እርሱን አምነው የሚመጡትን ሁሉ ሊያድናቸው ይቻለዋል፡፡ እንደምንስ ያድናቸዋል? የሚል ሰው ካለም “በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ነው” ብለን እንመልስለታለን፡፡ በሃይማኖት በንስሐ ወደ እርሱ የሚቀርቡትን የሚያድናቸው በዕለተ ዐርብ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚያ በኋላም ጭምር እንጂ፡፡ በወደደበት ጊዜም ለመነላቸው፡፡ ሁል ጊዜ ይለምናል ብሎ የሚያስብስ ከቶ እንደምን ይኖራል? ጻድቃንስ እንኳ አንድ ጊዜ በለመኑት ልመና የሚሹትን የሚያገኙ አይደሉምን?… ሐዋርያውም ሁል ጊዜ ቁሞ የሚያገለግል እንዳያስመስሉት በማሰብ በመትጋት መሥዋዕት አንድ ጊዜ እንደሠዋ አስረዳ፡፡ አንድ ጊዜ ሰው እንደ ሆነ አንድ ጊዜ ተሾመ፤ አንድ ጊዜ እንደ ተሾመ አንድ ጊዜ አገለገለ፡፡ ሰው በሆነ ጊዜ የሰውነትን ሥራ በመሥራት ጸንቶ እንዳልኖረ ሁሉ ባገለገለ ጊዜም በማገልገል ጸንቶ አልኖረም፡፡ አሁን ቢያገለግል ኖሮ ሐዋርያው ቆመ እንጂ ተቀመጠ ባላለ ነበርና፡፡ መሥዋዕቱ ቁርጥ ልመናውን አንድ ጊዜ ወደ እዝነ አብ (በአብ ጀሮ) ወደ ገጸ አብ (በአብ ፊት) የደረሰች ስለሆነች እንደ ቀደሙት ሊቃነ ካህናት ሁል ጊዜ ሊያገለግል አያስፈልገውም” /Homily on the Epistle of Hebrews, Hom.13/፡፡ የኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ትርጓሜም ተመሳሳይ ነው፡- “በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ እስከ ምጽአት ድረስ ሲያድንበት የሚኖር ስለ ሆነ በእርሱ አስታራቂነት ወደ እግዚአብሔር የቀረቡትን ማዳን ይቻለዋል” /የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡ ከነ ትርጓሜው፣ ገጽ 434/፡፡ እንግዲያውስ ተወዳጆች ሆይ! “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል” የሚል ጥሬ ምንባቡን ብቻ በመያዝ እንዳይሳሳቱ ይጠንቀቁ፡፡ ይህ ማለት አስቀድመን እንደነገርንዎት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የዕለተ ዐርብ የማስታረቅ አገልግሎት ከአዳም መፈጠር ጀምሮ እስከ ዕለተ ዐርብ ላሉት ሁሉ ብቻ ሳይሆን እስከ ዕለተ ምጽአት የሚፈጠረው ፍጥረት ሁሉ በዚሁ የዕለተ ዐርቡ የማስታረቅ አገልግሎት እያመነ እንደሚድን ደሙም የማስታረቅ ችሎታ እንዳለው የሚገልጽ ነውና /ዮሐ.17፡20-21/፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ የሠዋው መሥዋዕት እንደ ብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናት መሥዋዕት ተረፈ ኃጢአት (ያልተደመሰሰ ኃጢአት) አስቀርቶበት አሁን ያንን ለማስተስረይ የሚወድቅ የሚነሣ አይደለምና፡፡ ጸሎቱና መሥዋዕቱ ምልአተ ኃጢአትን (ኃጢአትን ሁሉ) ለመደምሰስ አንድ ጊዜ ተፈጽሟልና /ዮሐ.19፡30/፡፡ ስለዚህ ይማልድልናል ስንል “የዕለተ ዐርቡ ቤዛነት፣ ካሣ፣ ሞት፣ ደም መፍሰስ አዲስና በየዕለቱ ንስሐ የሚገቡትን የሚያቀርብ የሚያድን ነው” ማለት መሆኑን ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህም ነው ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች “ከእርሱ ውጪ ሌላ ሊቀ ካህን የለንም፤ ከቅዱስ ሥጋዉና ከክቡር ደሙ ውጪ ሌላ በየቀኑ የምናቀርበው መሥዋዕት የለንም” የምንለው፡፡ ክህነቱ የማይለወጥ፣ መሥዋዕቱም አንድ ጊዜ ቀርቦ በጊዜ ብዛት የማይበላሽ ሕያው አሁንም ትኵስ ነውና፡፡ ትኵስ መባሉም ነፍስ ስላለው ሳይሆን መለኰት የተዋሐደው ስለሆነ ነው፡፡የክርስቶስ ስጋና ደም ደግሞ እንደ ኦሪት መስዋእት በአንድ ቀን የሚያልቅ ፡ በጊዜ ብዛት የሚለውጥ ፡ የሚበላሽ አይደለም ፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜ አዲስና ለዘላለሙ በህይወት የሚኖር ነው፡፡ “ሕያው” መባሉም ነፍስ ስለተዋሃደው ሳይሆን “መለኮት” ስለማይለየው ነው፡፡ - - - ይህ ሕያው ስጋውና ደሙ ሁልጊዜ ሰውን ወደ እግዚአብሄር ሲያቀርብ የሚኖር ከእግዚአብሄርም ጋር የመታረቂያው ብቸኛ መንገድ በመሆኑ አማለደን (አስታረቀን) ሲል ገልፆታል፡፡ “ሊያማልድ በህይወት ይኖራል” የሚለውንም በጥሬ ንባቡ ከሆነ ጌታችን አሁንም በስጋ ህይወት በምድር አለ ያስብልብናልና፡፡

   Delete
  7. ......በእርሱ በኵል (እርሱን አምነው) ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሊያድን የሚችል ሊቀ ካህናት ነው፡፡ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፡- “የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል” /ዕብ.7፡25/፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ጌታችን ራሱ እንዲህ ብሏል፡- “እውነት እውነት እላችኋለሁ እኔ የበጎች በር (ደጅ) ነኝ… በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ (በእኔ ያመነ) ቢኖር ይድናል ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል (ክብረ ሥጋን ክብረ ነፍስን ያገኛል፤ መንግሥተ ሰማያትንም ይወርሳል)” /ዮሐ.10፡7፣9/፤ “እኔ መንገድና እውነት ነኝ (የሕይወትና የጽድቅ መንገዷ እኔ ነኝ) በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም (እኔን ልጅ ካላለ በቀር አብን አባት የሚለው የለም አንድም በእኔ የማያምን ከአብ ጋር መታረቅ አይችልም)” /ዮሐ.14፡6-7/፡፡ እውነት ነው! የሕይወት መሥመር ክርስቶስ ነውና ክርስቶስን አምኖ የሚኖር ሰው ሕይወትን ያገኛል፡፡ ማንም ይሁን ማን ክርስቶስን ካላመነ ቢጾምም ቢጸልይም ያለ ክርስቶስ ዋጋ የለውም፤ በክርስቶስ ካልሆነ በቀር ዓለም በራሱ ሕይወት የለውም፤ በክርስቶስ ቤዛነት የማያምን በሌላ በምንም መንገድ አይድንም፡፡ስለ ራሱ መሥዋዕት የማያሻው ነውር የለሽ ፍጹም ሊቀ ካህናት ነው፡፡ የዘመነ ብሉይ ሊቃነ ካህናት ዕሩቅ ብእሲና እንደ ማንኛውም ሰው ኃጢአተኞች ስለነበሩ ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር በመሥዋዕት በጸሎት ከማስታረቃቸው በፊት ስለ ራሳቸው ቁርባን መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር /ዘሌ.9፡7፣ ዘሌ.16፡6፣ ዕብ.5፡3-4/፡፡ ሊቀካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው በባሕርይው ድካም የሌለበት ቅዱስ፤ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለበት ንጹሕ፤ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን ሳይጐድልበት የሚያድል ባዕለ ጸጋ፤ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የሚያርቅ ቡሩክ፤ ከኃጢአተኞችም የተለየና ነውር የሌለበት ፍጹም ስለሆነ “እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈለገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና” /ዕብ.7፡27/፡፡ የሚምር ሊቀ ካህናት ነው፡፡ መጽሐፍ ይህን ሲመሰክር፡- “የአብርሃምን ዘር ይዟል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም፡፡ ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን በነገር ሁሉ ወንድሞቹን መምሰል ተገባው” ይላል /ዕብ.2፡16-17/፡፡ አዎ! የዘመናት ጌታ እንደ ሰዎች ዘመን ተቈጠረለት፤ በልደት በሕማም በሞት ወንድሞቹን መምሰል ተገባው፡፡ ባሕርያችንን የተዋሐደው ሌላ ምንም ምን ምክንያት የለውም፡፡ እኛን ከማፍቀሩ የተነሣ ዘመድ ሊሆነን አንድም እኛን ይቅር ለማለት ኃጢአታችንንም ለማስተስረይ እንጂ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል፡- “ተመለከተን፤ እነሆም ጠላቶቹ ሆነን ተገኘን፡፡ ወደ እርሱ ያቀርበን ዘንድ የሚችል ኪዳንም ቢሆን መሥዋዕትም ቢሆን ፈጽሞ አልነበረንም፡፡ ስለዚህም አዘነልን፤ ራራልን፡፡ ከመላእክትም ይሁን ከኃይላት ወገን ሊቀ ካህናት አልሾመልንም፤ እርሱ አንዱ ወደዚህ ዓለም ወርዶ ባሕርያችንን ባሕርይ አድርጐ የሚምር ሊቀ ካህናት (አስታራቂ) ሆነን እንጂ” /ሃይማኖተ አበው 62፡13/፡፡ ይህም በመዋዕለ ሥጋዌው ተመልክተነዋል፡፡ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ሲፈርዱባቸው የነበሩ ሰዎች፣ “Public Sinners” ብለው ከማኅበረሰቡ ያገለሉዋቸውን ሰዎች አዛኙ ሊቀ ካህናችን ሲያገኛቸው ግን “እኔም አልፈርድብሽም”፤ “ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል” ይላቸዋል /ዮሐ.8፡11፣ ሉቃ.7፡48/፡፡ ስለዚህ ሊቀ ካህናችን መሓሪ ነው፡፡

   Delete
  8. .....1/ደሙ ከሞተ ሥራ ሕሊናን የሚያነጻ ሊቀ ካህናት ነው፡፡ የዘመነ ብሉይ ሊቃነ ካህናት መሥዋዕቶች የጊደሮች፣ የኮርማዎች፣ የፍየሎች የሆነ ደመ እንስሳ ነበር፤ የዘመነ ሐዲስ ግን በደመ ክርስቶስ የተደረገ ነው፡፡ የዘመነ ብሉይ መሥዋዕቶች ያለ ፈቃዳቸው ያለ ውዴታቸው የሚሞቱ እንስሳት ነበሩ፤ የዛሬው ግን ሞት ይሁንብኝ ይደረግብኝ ብሎ ያለ ኃጢአቱ እንደ ኃጢአተኛ ተቈጥሮ በፈቃዱ እስከ ሞት ድረስ የታዘዘ የእግዚአብሔር በግ ነው፡፡ የእነዚያ መሥዋዕት ነውርና ነቀፋ ባለባቸው አገልጋዮች የሚቀርብ ነበር፤ የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት ግን ነውርና ነቀፋ በሌለበት በንጹሑ ኢየሱስ የተከናወነ ነው፡፡ የእነዚያ መሥዋዕት ሞት በሚይዛቸው በእንስሳት ደም የሚከናወን አገልግሎት ነበር፤ የሐዲስ ኪዳኑ መሥዋዕት ግን ትንሣኤና ሕይወት በሆነው በክርስቶስ የተከናወነ አገልግሎት ነው፡፡ የመጀመርያው ኪዳን ለጊዜው የሆነ ንጽሕናን የሚሰጥ ነበር፤ የሊቀ ካህናችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ግን ከጊዜና ከቦታ ቀመር ውጪ (Beyond Time) የሆነ ዘለዓለማዊ ንጽሕናን የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡ የቀደመው ኪዳን በምሳሌና በጥላ በሆነ በደመ እንስሳ የሚከናወን ነበር፤ የዛሬው ግን አማናዊ በሚሆን በንጹሑ በደመ ክርስቶስ ተደርጓል፡፡ የቀደመው መሥዋዕት እሳት አንድዶ እንጨት ማግዶ የሚሠዋ ነበር፤ የዛሬው ግን በመንፈስ ቅዱስ እሳትነት የተደረገ ነው፡፡ እንዲህም ስለ ሆነ የእነዚያ መሥዋዕት ደመ ነፍስን (ሥጋን) ብቻ የሚቀድስ ነበር፤ የዛሬው ግን… ደመ ክርስቶስ ግን ሕያው መሥዋዕት ስለሆነ ሁለንተናን ሕያውና ቅዱስ የሚያደርግ ነው፤ ሕሊናን ከሞተ ሥራ የሚያነጻ ልዩ መሥዋዕት ነው፡፡ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፡- “ደመ ላህም ደመ ጠሊ የጊደርም አመድ ሥጋዊ ኃጢአትን የሚያነጻ ከሆነ፣ በኃጢአት ያደፉትን የሚያከብራቸው ከሆነ በመንፈስ ቅዱስ እሳትነት ራሱን ለእግዚአብሔር ነውር ነቀፋ የሌለበት የዘለዓለም መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበ የኢየሱስ ክርስቶስ ደምማ ከኦሪት፣ ከኃጢአት፣ ከፍዳ፣ ከፍቅረ ንዋይ ልቡናችንን እንደምን ያህል ያነጻ ይኾን?” /የዕብ.9፡13-14 ትርጓሜው፣ገጽ.441/፡፡ ስለዚህ ደሙ ከሞተ ሥራ ሕሊናን የሚያነጻ ሊቀ ካህናት አለን፡፡
   2. የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ (ምርጥ) ሊቀ ካህናት ነው፡፡ ሐዋርያው “ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው” ይላል /ዕብ.9፡15/፡፡ እውነት ነው! ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለወንጌል መምህር ለመንግሥተ ሰማያትም አስታራቂ የሐዲስ ኪዳን ብቸኛው መካከለኛ ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን ክፍል በተረጐመበት አንቀጽ ምን ማለት እንደሆነ እንዲህ ያብራራልናል፡- “መካከለኛ ማለት ምን ማለት ነው? መካከለኛ መካከለኛ ለሆነለት ነገር ባለቤት (ተጠቃሚ) አይደለም፡፡ ለምሳሌ አማጭ (መካከለኛ) ለሚያገባ ሰው ሚስት ለማግባት አጋዥ ይሆነዋል እንጂ እርሱ የሚያገባ ሙሽራ አይደለም፡፡ በጌታም ዘንድ እንዲህ ነው (የተሠዋው እጠቀም ብሎ አይደለም)፡፡ ወልድ ዋሕድ ጌታ በአባቱና በእኛ መካከል አስታራቂ ሆነ፡፡ አብ በሠራነው ኃጢአት ፈርዶብን መንግሥቱን ሊያወርሰን አልወደደም ነበርና ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የባሕርይ ልጁ በእርሱና በእኛ መካከል አስታራቂ ሆነ፡፡ እርሱንም ደስ አሰኘው፡፡ ከዚያም እኛን ወደ ልጅነት ልጅነትንም ወደ እኛ ጠራ፤ በሞቱ ከአብ ዘንድ መንግሥተ ሰማያትን አስገኘልን፡፡ ሕጉን በማፍረስ በነበርን ጊዜ ሞት ተገባን፤ እርሱ ግን ስለ እኛ በሞተ ጊዜ ሳይገባን ለመንግሥተ ሰማያት የበቃን አደረገን፡፡ አባት ለልጁ እንደሚሰጥ ቀድሞ ልጅነትን ሳንጥር ሳንግር እንዲያው ሰጠን” /ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድር.16፡33-48/፡፡ አዎ! በበደልነው ጊዜ ሕጉ (ኦሪት) እንደ ፍርድ ሆነብን (የሚያስፈርድብን ሆነ)፡፡ ለማዳን የሚሞት አንድ ስንኳ ጠፋ፡፡ ሊቀ ካህናችን ግን ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከራሱና ማኅየዊ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያስታርቀን ዘንድ የባርያውን መልክ ይዞ (የእኛን ባሕርይ ነሥቶ) ትምክህታችን ከምትሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው ሆነ፤ አምላክ የሆነ ሰው ሰውም የሆነ አምላክ (መካከለኛ) ሆነ፤ በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ የሆነ ሥግው ቃል (Incarnated Word)፣ አምላክ ወሰብእ (መካከለኛ) ሆነ፡፡ አስቀድመን እንደተናገርነው በሥግው ቃልነቱ ስለ እኛ ባይሞት ኖሮ ኦሪት ደካማ ከመሆኗ የተነሣ ባልዳንን ነበር፡፡ ስለዚህ እንደ ሰውነቱ ዘመዳችን እንደ መለኰትነቱ ፈጣርያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዲስ ሕግ ለወንጌል መምህር ለመንግሥተ ሰማይ አስታራቂ ሆነ፤ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ብቸኛ መካከለኛ ሆነ፡፡
   3. ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን የሻረ ሊቀ ካህናት ነው፡፡ ደጋግመን እንደተናገርነው የቀደመው ሊቀ ካህናት ብዙ ጊዜ ብዙ መሥዋዕት ሠዋ፤ ሊቀ ካህናችን ግን አንድ ጊዜ ራሱን ሠዋ፡፡ የቀደመው ሊቀ ካህናት ገንዘቡ ባይደለ በሌላ ደም አገለገለ፤ የዛሬው ግን እውነት ገንዘቡ በሚሆን በራሱ ደም አስታረቀ፡፡ ምሥዋዑ እርሱ ነውና፤ የሠዋው እርሱ ነውና፤ የተሠዋውም እርሱ ነውና በራሱ ደም አገለገለ፡፡ ፈቃዱን እንደ ካህን ሥጋው እንደ መንበር አድርጎ ነፍሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፡፡ “አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ (ኑሮ ኑሮ አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም) ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር (ያጠፋት ዘንድ) አንድ ጊዜ ተገልጦአል” /ዕብ.9፡26/ ተብሎ እንደተጻፈ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደው ራሱን በመሠዋት እንጂ የጊደርና የኮርማ ደም በማፍሰስ አይደለም፡፡

   Delete
  9. i find the english version from some protestant website therfore u must agree with it....የኦሪት ሊቃነ ካህናት ወደ ለእግዚአብሔር መስዋት በመስዋት ሐጢያትን ያስተሰርዩ ነበር። በተለይም በአመት አንድ ጊዜ ካህኑ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ደም ይዞ በመግባት ስለህዝቡና ስለራሱ በእግዚአብሄር ፊት ይታይ ነበር ይሁንና ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤ ዕብ ፱፡፯ አሁንጌታ ኢየሱስ አማላጂ ነዉ ካልን አሁን ደም ይዞ እየታየ መሆን አለበት ሆኖም ጌታችን ደሙን ያፈሰሰዉ በመስቀል ላይ በሰማይ አይደለም ዕብ ፯፤፪፯ እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና። ዕብ ፩፤፫፫ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤ ብ ፱፤፪፮፡፪፯ ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል። ለበለጠ ማስረጃ የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ስርዐተ መሠዋት እንመልከት 1. Once a year, on the Day of Atonement, the following ceremony took place.

   2. Two perfect male goats were chosen by the priests.

   3. Both were presented to God.

   4. Lots were cast( ዕጣ ይጣላል,) and the sacrificial goat was chosen.

   5. The sacrificial goat was kept to be sacrificed as a blood sacrifice for sin.

   6. None of its bones were broken

   7. The other goat, the scapegoat, was sent into the wilderness, with a red cord tied around its horns.

   8. The throat of the sacrificial goat was cut outside the Temple, and its blood collected in a special basin(ሳህን)

   9. The high priest then entered the Holy of Holies, wearing special priestly garments, and carrying the basin of blood from the sacrificial goat.

   10. The high priest remained in the Holy of Holies, in pitch darkness, for a total of three hours.

   11. The high priest then prayed before the Ark of the Covenant, asking God to forgive the Jewish people for their sins over the previous 12 months.

   12. The high priest then poured the blood of the sacrificial goat onto the Eastern or right hand side of the Mercy Seat.

   13. God then appeared in Shekinah Glory between the two Cherubim over the Mercy Seat.

   14. God forgave the sin of the Jewish people.

   15. The high priest then stood up, and cried out, "It is finished".

   16. The Old Covenant was fulfilled, by the sacrifice of the sacrificial goat, the prayer of repentance by the high priest on behalf of the Jewish people, and the appearance of God in Shekinah Glory over the Mercy Seat. continue...

   Delete
  10. ...ያዳነን ጌታችን እየሱስ ፥ግን የሀዲስ ሊቀ ካህናችን በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።as there was a high priest every year who celebrated the Old Covenant *** Jesus Christ is The High Priest of the New Covenant for Eternity
   ***The priests chose two perfect adult male goats Jesus Christ and Barabbas were chosen by Pontius Pilate
   ***The two goats were presented by the priests outside the Temple *** Jesus Christ and Barabbas were presented to the crowds outside the Praetorium***
   The scapegoat was chosen by lots*** Barabbas was chosen by the crowds***
   The scapegoat later received the Rite of Atonement, and was set free *** Barabbas was set free, which is a picture of the Gospel***
   The sacrificial goat was then sacrificed, and the High Priest then entered the Holy Place with the blood of the sacrificial lamb *** Jesus Christ was the High Priest, and the Crucifixion Site became the Holy Place of the New Covenant. Jesus Christ was sacrificed by God on the Cross, as the Lamb of God.***
   The High Priest was completely alone in the Tabernacle Jesus Himself was the only High Priest of the New Covenant once and for all in Eternity***
   The High priest spread blood on the horns of the altar in the Holy Place *** The Blood of Jesus Christ was smeared all over the Cross
   The High Priest prayed to God to forgive the sins of the people *** Jesus Christ prayed for God to forgive the sins of the people
   There was a confession of sin by the high priest over the scapegoat *** Jesus Christ, the High Priest of the New Covenant, did NOT confess sin, because He was without sin. Instead, Jesus Christ became the Blood Sacrifice to take away sin.
   The scapegoat bore all the sins of the people to an uninhabited land *** In the New Covenant, "The blood of Jesus Christ His Son cleanses us from all sin," I John 1, 7
   The blood of the sacrificial goat was sprinkled onto the Mercy Seat of the Ark of the Covenant, in the Holy of Holies The high priest then removed his ceremonial linen garments*** When Jesus Christ was crucified all four of his priestly garments were removed
   The Temple Sacrifice happened every year on the Day of Atonement ** Jesus Christ was crucified on Passover, AD 33, on one occasion only***
   On the Day of Atonement the high priest made atonement for the Jewish people *** On the Day of Crucifixion, Jesus Christ died for the sins of the whole world***
   By Rabbinic tradition, the high priest spent 3 hours in the Holy of Holies, in the pitch darkness*** Jesus Christ spent 3 hours in total darkness on the Cross, and the darkness was world wide***
   During this 3 hour period, God appeared in Shekinah Glory between the Cherubim, over the Mercy Seat*** During this 3 hour period, Jesus Christ was rejected by God the Father, and atoned for the sins of the world***
   By Rabbinic tradition, at the end of this period of 3 hours, the high priest stood up and said, "It is finished" ***At 3 pm, after 3 hours of darkness all over the world, Jesus Christ stood up on the Cross to announce His 7th announcement from the Cross. He said, "It is finished".

   ስለዚህ በዚህ ንፅፅር መሰረት መስዋትና ምልጃ የተፈፀመዉ በመስቀል ላይ ነዉ ንዲህ ባ ይሆንስ ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር ሆኖምአሁንም ጌታ ኢየሱስ ሊቀ ካህናችን ነው፥፥ ሊቀ ካህንነቱ ግን በእግዚአሄር በሆነው ነገር ሁሉ ይቅር ለማለትና ለመማር እንጅ ለመለመን አይደለም፥፥ዕብ ፱፤፪፮፡፪፯ ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባምና፤
   ፩ ሃጢያትን ለማስተረይ ነው ፥አንድ ጊዜ ያፈሰሰው ደሙ ፣ አዲስ አምነው ለሚጠመቁት ድነትን ይሰጣል

   Delete
  11. እንደ(ሊቀ ካህንነቱ).... ሥለ እኛ በሰማያዊት መቅደስ ያለ ብቸኛ አማላጅ/አስታራቂ/መካከለኛ ነው፡ የተሰጠውን ተልዕኮ በመፈፀም በምድር አገልግልዋል:: አሁን ደግሞ የዕብራዊያን ጸሐፊ እንደሚናገረው ኢየሱስ በሰማይ በሰው እጅ ባልተሰራችውና በእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው ይለናል (ዕብ 8፣1-2፡)....oh god ...በእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው... «ተሐድሶ» «የአይሁድ ንጉሥ» የምትለዋን ቃል ከሰብአ ሰገል ሲሰማ ብዙ የማይመለስ ጥፋት እንዳጠፋ ሄሮድስ «ሊቀ ካህናት» «አስታራቂ» የሚለውን ቃለ ሲሰሙ ይደናበሩና ራሳቸውን ሌሎችንም ይዘው ለጥፋት ይፋጠናሉ፡፡፡ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር “ሊቀ ካህናት ሲል ብትሰማው ዘወትር የሚያገለግል አይምሰልህ፤ ራሱን አንድ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋ …(ጳውሎስ) ሁል ጊዜ ቆሞ የሚያገለግል እንዳያስመስሉት በማሰብ … ራሱን አንድ ጊዜ እንደሠዋ አስረዳ፡፡አንድ ጊዜ ሰው እንደሆነ አንድ ጊዜ ተሾመ፤ አንድ ጊዜ እንደተሾመ አንድ ጊዜ አገለገለ፤ ሰው በሆነ ጊዜ የሰውነትን ሥራ በመሥራት ጸንቶ እንዳልኖረ ባገለገለም ጊዜ በማገልገል ሥራ ጸንቶ አልኖረም /የዕብራውያን መልእክት ትርጓሜ ድርሳን 13፡184-190/” ብሎአል፡፡

   Delete
  12. Do we have any single verse in Holy Scripture that teaches us to pray to the saints in heaven? The Holy Bible clearly teaches us to pray to each other on earth (St. James, St. Paul). Do we really know the situation of the saints in heaven between their departure and the resurrection?

   No, the saints do not possess attributes of deity; they only know what God reveals to them.

   The Holy Bible did not mention the word earth either when teaching us to pray for one another. In Holy Book of Jeremiah 15:1 we read, "Then the Lord said to me, "Though Moses and Samuel stood before me, yet my heart would not turn toward this people. Send them out of my sight, and let them go!" At the time of Jeremiah Moses and Samuel were in paradise not on earth.

   The saints are in Paradise, a resting place, awaiting the second coming of our Lord Jesus Christ when they will hear Him say, “Come, you blessed of My Father, inherit the kingdom prepared for you from the foundation of the world” (Mt 25:34)

   Delete
 7. Christ is the only “Paraclete” (the One Who is called upon), the only “mediator” and “saviour” (John I 2:1, John 14 6:13-14, Timothy I 2:5, Acts 4:12); reconciliation can only be attained with the blood of Christ (Peter I 1:18-19). The “other Paraclete” (One Who is called upon), i.e. the Holy Spirit, activates -through the holy Sacraments- the endowments of Christ: i.e., through Holy Baptism it makes us members of the Body of Christ, the Church (Galatians 3:27, Corinthians I 12:3); through Holy Communion, it nurtures us with the “bread of life” (John6:48-3). Thus, in this absolute context, there cannot be another savior, or a second mediator.

  And yet, the Scripture does mention the mediation of people and angels, through prayer and supplication (Genesis 18:23-33, 20:3-18, 32:9-14, Job 42:8-10, Proverbs 15:8, Zechariah 1:12-13, Jeremiah7:16). There are certain people who are referred to as “ambassadors” (Corinthians II 5:18-20, Ephesians 6:20) and also as “saviors”, but only in the sense that they lead us towards the only true Savior, Christ (Corinthians I 9:22). God assures the prophet that even if one holy man were to be found, for his sake alone, the entire city would be saved (Jeremiah 5:1, Ezekiel 22:30).

  Well, could it be that “mediation” -in a relative context- pertains only to living people? “No”, was God’s reply to the prophet Jeremiah: “Not even if Moses and Samuel were to stand before me, would my soul be swayed towards them” (Jeremiah 15:1). This suggests that in other instances, God did respond to the supplications of holy men who prayed for the population. In Revelation, we read of the celestial, triumphant Church (=the 24 elders) holding “vials filled with incense, which were the prayers of the saints”, in other words, of the living faithful who were still on earth – which incense/prayers they united with their own prayers. (Revelation 8:5)

  ReplyDelete
 8. አማላጅነት ፡ ሁሉ በክርስቶስ አንድ የመሆኑ ምልክት

  አስቀድመን በክርስቶስ የድኅነት ተግባር ሁላችን ክርስቲያኖች አንድ መሆናችንን እናስታውስ ፡ አይሁድ የለ ፡ ግሪካዊ ፡ አረማዊ የለ አህዛብ ሁላችን በክርስቶስ አንድ ሆነናል፡፡ በክርስቶስ አምኖ የሞተ ይሁን አሁን በስጋ ያለ ሁሉ አንድ ሆኗል፡፡ ይህንስ ለስጋ አእምሮ እናገራለሁ እንጂ ሞትማ በክርስቶስ ሞቶ የለምን? ነገር ግን ይህን አሁን አናይም ፡ በክርስቶስ የሞቱ ግን ስለክርስቶስ ህያዋን ናቸው፡፡ እንግዲህ ሁላችን አንድ ከሆን ወዲያ ስለክርስቶስ በፍቅር እንመላለስ ዘንድ አለንና ፡ ከዚህ አንፃር አማላጅነት ምንድን ነው? ኢምንት መሆኑን አይደለምን? ነገር ግን ስለክርስቶስ ፀጋወች ሁሉ ክቡራን ናቸው፡፡

  ነገር ግን ምስጢሩ እያለ ስለምን በፊደሉ ላይ እስከመቼ ልባችንን አጨልመን እንጓዛለን? እስከመቼ በስጋ ስንመላለስ እንኖራለን? ክርስቶስ ለዚህ ጠርቶናልን? የስጋ ህይወት ፡ የስጋ ኑሮማ በኦሪት ዘመን ቀረ ፤ በክርስቶስ ብርሃንነት መንፈሳዊነት ተገለጠች ፡ ሩቅ ሰማይ ቀረበች ፡ የጥል ጨለማ ተገፈፈች ፡ የሞት አገልግሎት ተሻረች ፡ ምድር ከሰማይ ቀረበች ፡ ቅዱሳን ሁሉ ከአንድ ማእድ ሊቋደሱ ተጠሩ ፡ ከአንድ አብ ከአንድ ወልድ ከአንድ መንፈስ ቅዱስ የህይወት ማእድ ሊቋደሱ ፡ በአንድ መሶብ ሊቋደሱ ፡ በአንድ ምስጋና ሊያወድሱ ፡ በአንድ ፀሃይ ሊያበሩ ፡ ተጠሩ፡፡ እንዲህማ ካልሆነ የክርስቶስ መምጣት ሃይል በምን ይታወቅ ነበር፡፡

  እንግዲህ መራራቅ ወዴት ነው? በክርስቶስ ቅርብ ሆኗን፡፡ እንግዲህ መከፋፈል ወዴት ነው? በክርስቶስ አንድ ሆኗል ፤ እንግዲህ መጠላላት ወዴት ነው? በክርስቶስ ተዋዷል ፤ እንግዲህ ባእድነት ወዴት ነው? በክርስቶስ ሁሉ ዘመድ ሆኗል፡፡ ወይንስ ሞት ወዴት ነው? እርሱም በክርስቶስ ድል ተነስቷል ፤ በምድር በስጋ ያሉት ስለክርስቶስ ሰማያውያን ሆነዋል ፡ በነፍስ በሰማይ ያሉት ስለክርስቶስ ምድራውያን ሆነዋል ፤

  እንግዲህ በክርስቶስ ሁላችን ሰማያውያን መሆናችን አይደለምን? ሰማያውያን ከሆንን እኛ አስቀድመው በስጋ ከተለዩን ጋር ለመገናኘት ምን ይከለክለናል ፤ ወይንስ ሰማይ ሰፊ ነው የሚል አለን? እንኪያስ በክርስቶስ ሁላችን በእርሱ ግንድነት ቅርንጫፍ ሆነን ተሰርተናል እንላለን ፤ እንግዲህ ቅዱሳን ሁሉ ቅርንጫፍ ሆነው በአንድ ግንድነት ከተተከሉ ፡ እኔም ለዚህ ክብር ከተጠራሁ ፡ ከቅዱሳን ጋር ዘመድ መሆኔ አይደለምን? ወይንስ ዛፍስ ከውጭ ነው የሚለኝ አለን? እንኪያስ በክርስቶስ ሁላችን አንድ ቤተሰብ ሆነናል እላለሁኝ ፡ እንግዲህ የቤተሰቤ አካል ስለእኔ ሊጨነቅ ፡ ስለእኔ ሊያስብ ምን ይከለክለዋል? ወይንስ እኔ ለቤተሰቤ ችግሬን ለመንገር ምን ይከለክለኛል? ወይንስ በአንድ ቤትም ሰፊ ነው ፡ መደማመጥ ይቸግራል የሚል አለን? እንኪያስ በክርስቶስ አካልነት ሁላችን ብልቶች ሆነን ተሰርተናል ብየ እመልስለታለሁ፡፡ እንግዲህ አይን ስለአፍንጫ አይገደውምን? ይህስ ከአፈር ለተሰራ ሰውነት ይገደዋል ፡ ይህስ ከሆነ በክርስቶስ አዲስ ተፈጥሮ ለታደሰ ሰማያዊ አካልማ እንደምን ከዚህ ይበልጥ ግድ አይለው?

  እንግዲህ ከዚህ ሰማያዊ ምስጢር ይልቅ አማላጅነትን ለማሳነስ ጥቅስን ስለመፈለግ ሰው ቢደክም ስጋዊ መሆኑ አይደለምን? የክርስቶስን ክቡር የመስቀሉን ስራ ለሚረዳ ግን ከፊደል ይልቅ ምስጢሩን ይረዳል ፡ ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊውን ፡ ከስጋዊው ይልቅ መንፈሳዊውን ያስባል ፡፡

  ልቦና ይስጥልን::ንስሃ ግቡ ወግኖች::የፕሮቴስታንት እምነት አታራምዱ::ለነገሩ ከለየላችሁ ቆይታችኅልና ቤተክርስቲይንን ይቅርታ መጠየቅ : ንስሃ መባት ከከበዳችሁ እነሱኑ ብትቀላቀሉ!!!አቤቱ እግዚአብሄር ሆይ ከውስጣችን ሆነዉ ከሚጎዱን አንንተ ጠብቀን::አሜን

  ReplyDelete
  Replies
  1. .....በዘመነ ብሉይ እግዚአብሔርን ከሕዝቡ ጋር ሕዝቡንም ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኙ ማለትም የሚያስተራርቁ ብዙ ነብያትና ካህናት ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ሙሴ በእግዚአብሔርና በሕዝበ እስራኤል መካከል ሆኖ ያገለገለ ታላቅ ነብይ ነበር /ዘዳ.5፡5/፡፡ እንደዚሁም አሮንና ከቤተ አሮን የሆኑ ካህናት በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ሆነው ያገለግሉ ነበር /ዕብ.5፡1-4/፡፡ ሆኖም ግን አገልግሎታቸው ሊመጣ ላለው ለሐዲስ ኪዳን ምሳሌና ጥላ ስለነበረ ዘላለማውያን አልነበሩም /ዕብ.8፡5/፡፡ ሞት ስለከለከላቸውም እንዲህ የተሾሙ ብዙዎች ናቸው /ዕብ.7፡23/፡፡ በዘመነ ሐዲስ ግን ሞት የማይሽረው ይልቁንም ሞትን በሞቱ የገደለ አንድ ሊቀ ካህን አለን፡፡ እርሱም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል /ዕብ.4፡14-15/፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው “የሃይማኖታችን ሐዋርያና ሊቀካህን” የሚለን /ዕብ.3፡1/፡፡ ቀሳውስት አባቶቻችን ጸሎታቸውን ሲጨርሱና ሲባርኩን፡- “ኃጢአትን የሚያስተሠርይ በደልን የሚደመስስ ካህን ሊቀካህናት የሆነው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅር ይበላችሁ፤ ይፍታችሁ፤ ያንጻችሁ፤ ይቀድሳችሁ” የሚሉንም ስለዚሁ ነው፡፡

   የብሉይ ኪዳን ካህናት በቤተ መቅደስ ውስጥ ያገለግሉ ነበር /ዘሌ.1፡5-7፡35/፡፡ አገልግሎታቸውም በየተራ ነበር /ሉቃ.1፡8-9/፡፡ ቤተ መቅደሱን የሚያስተዳድር፣ ካህናቱን የሚቈጣጠር፣ ሸንጐአቸውን በሊቀመንበርነት የሚመራ፣ የማስተስርያ ቀን በሚባለውና በዓመት አንድ ጊዜ በሚውለው በዓል ላይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ብቻውን በመግባት ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ መሥዋዕት የሚያቀርብ ደግሞ ሊቀ ካህናት ይባላል /ዕብ.9፡7፣ ዘሌ.4፡27-29፣ ዘሌ.16፡1-34/፡፡ አስቀድመን እንደተነጋገርነው ሊቃነ ካህናቱ ይሠዋው የነበረው ደመ በግዕ፣ ሥጋ በግዕ፣ ደመ ጠሊ፣ ሥጋ ጠሊ፣ ደመ ላህም፣ ሥጋ ላህም ይመጣ ዘንድ ላለው የዓለምንም ኃጢአት ለሚያስወግደው አማናዊው መሥዋዕት የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ ነበር /ዕብ.10፡11-16/፡፡ ሆኖም ግን ይህ ሊቀ ካህናት (ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ) እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሊቀ ካህናት መሥዋዕትን (ራሱን) ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም /ዕብ.9፡25/፡፡

   ይህን እውነታ አጥብቃ የያዘች ርትዕት ሃይማኖት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቀ ካህናችን የኢየሱስ ክርስቶስ የማስታረቁ ትምህርት አብዝታ ታስተምራለች፡፡ ይህም ከሚከተሉት ምሳሌዎች መረዳት ይቻላል፡፡
   © “ለሐዲስ ኪዳንም አስታራቂ ሆነ” /ቅ.ኤፍሬም በእሑድ ውዳሴ ማርያም/፡፡
   © “ወደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር አቀረበን” /ቅ.ኤፍሬም በቅዳሜ ውዳሴ ማርያም/፡፡
   © “በእኛና በአባትህ መካከል ፍቅርን አደረግህ፤ በመካከልም ሆነህ አስታረቅኸን” /ኪዳን/፡፡
   © “ወደ አባቱ ለመሄድ መንገድ፣ ለመግባትም በር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” /አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ሰዓታት/፡፡
   © “የአብ ሊቀ ካህናት የሰውን ወገን ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ” /አመክንዮ ዘሐዋርያት/፡፡
   © “ሰው የሆነው ዘመድ ሊሆነን ብቻ አይደለም፤ ፈጽሞ ይቅር አለን፤ ኃጢአታችንን ለማስተሥረይ ከአብ ጋር ለማስታረቅ ሊቀ ካህናትም ይሆነን ዘንድ ወደደ እንጂ፡፡ ስለዚህም ሰዎችን ሊመስላቸው ይገባል ባለው ነገሩ ላይ ጨምሮ በሁሉ አዛኝ የሕዝቡንም ኃጢአት ለማስተሥረይ በእግዚአብሔር ዘንድ የታመነ አስታራቂ ይሆናቸው ዘንድ ወደደ አለ” /ሃይማኖተ አበው.63፡13/፡፡
   © “በጐ ሥራ ለመሥራት የምንቀና ደግ ወገን አድርጐ ገንዘብ አደረገን፤ ለእኛ ማልዶልናልና (ሐዋርያው ጳውሎስ) የምናምንበት ሊቀ ካህናት (አስታራቂ) አለው” /ሃይማኖተ አበው 63፡26/፡፡
   © “እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያስማማ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ሁለቱንም አስታረቃቸው /ሃይማኖተ አበው. 68፡21/፡፡
   © “የሰው ሁሉ ነጻነት የተጻፈበት ቅዱስ ማኅፀን እንደምን ያለ ነው? በእኛ ሠልጥኖ የነበረ ሞትን የሚቃወመው የጦር ዕቃችን (ክርስቶስ) ያደረበት ብሩክ ማኅፀን እንደምን ያለ ነው? እንደ ዕፀ ሠሉስ (ማክሰኞ እንደተፈጠሩት ዕጽ) ያለ ዘር በባሕርዩ ሁሉን በሚያስገኝ በመንፈስ ቅዱስ ጌታን ያስገኘችልን የተመረጠች ገራህት (ማርያም) እንደምን ያለች ናት? እግዚአብሔር እንደ ቸርነቱና እንደ ይቅርታው እንደ መልከ ጼዴቅ ባለ ሹመት ለማገልገል ሥጋን ለብሶ ባሕርዩ ሳይለወጥ ታላቅ ካህን የሆነበት መቅደስ እንደምን ያለ ነው? /ሃይማኖተ አበው. 112፡23/....

   Delete
  2. AnonymousMay 10, 2013 at 6:40 AM ይብላኝ ላንተ እንጂ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ማህበረ ቅዱሳን ቢቆጣጠራት እንኩዋ ጴንጤ አልሆንም።የግብጽ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ሆነ ሌሎች ኦርቶዶክሶች እየሱስ አማላጅ እንደሆነ ያምናሉ ቅዱሳንም እንደሚያማልዱ ያምናሉ ይህንን ገጽ ተመልከት According to the Holy Book of Romans 8:34, is Christ an intercessor or a judge?

   Our Lord Jesus Christ is God the almighty Who does not have just one role in our lives. He functions on our behalf and on God's behalf. Our Lord Jesus Christ is our Mediator Who made it possible for us to be reconciled with God through His death on the Cross for the forgiveness of our sin. He is now sitting at the right hand of His Father interceding for us. Through His intercession, He is able to save all who come to God through Him "Therefore He is also able to save to the uttermost those who come to God through Him, since He always lives to make intercession for them" (Heb 7:25).....However, on Judgment Day when the time comes to give an account of our stewardship, when it is past the intercession time, it is our Lord Jesus Christ Who will judge us.

   Delete
 9. EGEZIABHER yebarekeh!!" le enante ye sega mot teleku kumnegerachu new:: mekniyatum gena segaweyan nachuhena::" betam tekekel GETACHEN MEDEHANITACHEN EYESUS KRESTOS gen ye heyawan ye mutamn Amelak mehonun MUSE ena Eliyasen terto asayetonal!! Saol menafeset teriwan Samuelen endetekesekeselet adergo Samuel be Saol lay yemihonewn hulu negrotal! Abereham Alazaren be ekefu adergo le Newe teyake melse sesetew yeneberew be meder aly eko aleneberem! mute selehone menem bayake noro yehenen madereg balechale neber!!tehetena selelelachu new enji tehetena binorachu noro yehchi yekudsan meseret yehonechewen BETECHERESTIYAN bedeferet lemenkef beferachu neber!! pawelos endalew gen Lezih alem endemimech lerasachew memheranen yazagajalu!! endalew ye BETCHERSTIYANEN hege ende alemawi sereat lesew be misemama melku mekeyer tefelegalachu!!


  ReplyDelete
  Replies
  1. አንድ አስተያየት ብሰነዝር በታም ደስ ይለኛል ነቀፌታ የምትሰነዝሩ ሰዎች ነቀፈታችሁ መጽሃፍቅዱሳዊ ቢሆን ትሩ ነው ይህ መድረክ ብዙ የደብተራን ሴራ እያወቅንበት ያለ መድረክ ነው!!! ወስብሃት ለእግዚአብሄር አሜን! ይቆየን

   Delete
 10. A lot of Reformers here in Ethiopia used to misinterpret this verse of the Apostle Paul in Hebrews 7:25 & Rome 8:34. But what does it mean in its Orthodox meaning? What does the Ancient Fathers say about it? Let’s hear its interpretation from one of our Oriental Orthodox Holy Fathers, St. John Chrysostom
  For as there were many priests, because they were mortal, so [here is] The One, because
  He is immortal. “By so much was Jesus made a surety of a better covenant,” inasmuch as He sware to Him that He should always be [Priest]; which He would not have done, if He were not living. “Wherefore He is able also to save them to the uttermost, that come unto God by Him, seeing He ever liveth to make intercession for them.” Thou seest that he says this in respect of that which is according to the flesh. For when He [appears] as Priest, then He also intercedes. Wherefore also when Paul says, “who also maketh intercession for us” ( Rom. viii. 34 ), he hints the same thing; the High Priest maketh intercession. We have clearly seen this when Our Lord was saying ‘’Father, forgive them; for they know not what they do’’ (Luk.23:34).
  The question is that for He “that raiseth the dead as He will, and quickeneth them,” ( John v. 21 ), and that “even as the Father” [doth], how [is it that] when there is need to save, He “maketh intercession”? ( John v. 22.) He that hath “all judgment,” how [is it that] He “maketh intercession”? He that “sendeth His angels” ( Matt. xiii. 41, 42 ), that they may “cast” some into “the furnace,” and save others, how [is it that] He “maketh intercession”?
  Wherefore (the Apostle says) “He is able also to save.” For this cause then He saves, because He dies not. Inasmuch as “He ever liveth,” He hath (he means) no successor: And if He have no successor, He is able to aid all men. For there [under the Law] indeed, the High Priest although he were worthy of admiration during the time in which he was [High Priest] (as Samuel for instance, and any other such), but, after this, no longer; for they were dead. But here it is not so, but “He” saves “to the uttermost.” What is “to the uttermost”? He hints at some mystery which is the Holy Eucharist. Not on the day of the Good Friday only (the Apostle says) but there also He saves them that “come unto God by Him” through confession and this Holy Communion. If you asketh How does He save? I say unto you “In that He ever liveth” (the Apostle says) “to make intercession for them.” Thou seest the humiliation? Thou seest the manhood? For he says not, that He obtained this, by making intercession once for all, but continually, and when so ever it may be needful to intercede for them...

  ReplyDelete
 11. ...To the uttermost.” What is it? Not for a time only, but there also in the future life. ‘DOES HE TEHEN ALWAYS NEED TO PRAY? Yet how can [this] be reasonable? Even righteous men have oftentimes accomplished all by one entreaty, and is He always praying? NO! If He need to pray always why then is He throned with [the Father]?’ Thou seest that it is a condescension. The meaning is: Be not afraid, nor say, Yea, He loves us indeed, and He has confidence towards the Father, but He cannot live always. For He doth live always. “For such an High Priest also became us, who is holy, harmless, undefiled, separate from the sinners.” Thou seest that the whole is said with reference to the manhood. (But when I say ‘the manhood,’ I mean [the manhood] having Godhead; not dividing [one from the other], but leaving [you] to suppose what is suitable.) Didst thou mark the difference of the High Priest? He has summed up what was said before, “in all points tempted like as we are yet without sin.” (Heb. iv. 15.) “For” (the Apostle says) “such an High Priest also became us, who is holy, harmless.”
  “Harmless”: what is it? Without wickedness: that which another Prophet says: “guile was not found in His mouth” ( Isa. liii. 9 ), that is, [He is] not crafty. Could anyone say this concerning God? And is one not ashamed to say that God is not crafty, nor deceitful? Concerning Him, however, in respect of the Flesh, it might be reasonable [to say it]. “Holy, undefiled.” This too would anyone say concerning God? For has He a nature capable of defilement? “Separate from sinners.” Does then this alone show the difference, or does the sacrifice itself also? How? “He needeth not” (he says) “daily, as the High Priest, to offer up sacrifices for his sins, for this He did once for all, when He offered up Himself” ( Heb.7: 27) .“This,” what? Here what follows sounds a prelude concerning the exceeding greatness of the spiritual sacrifice and the interval [between them]. He has mentioned the point of the priest; he has mentioned that of the faith; he has mentioned that of the Covenant; not entirely indeed, still he has mentioned it. In this place what follows is a prelude concerning the sacrifice itself through the Holy Eucharist.
  Do not then, having heard that He is a priest, suppose that He is always executing the priest’s office. For He executed it once, and thenceforward “sat down.” ( Heb. x. 12.) Lest thou suppose that He is standing on high, and is a minister, he shows that the matter is [part] of a dispensation [or economy]. For as He became a servant, so also [He became] a Priest and a Minister. But as after becoming a servant, He did not continue a servant, so also, having become a Minister, He did not continue a Minister. For it belongs not to a minister to sit, but to stand.
  Glory be to God Amen!
  ( Source:-
  ü St. John Chrysostom: Homily on the Epistle of Hebrews, Homily 13:6-9, English Version).
  ü ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን 13፡123-191(Dirsan zekidus Yohans Afewerk)- which is the Ethiopic Version of the above reference.)
  mekrezzetewahdo.com

  ReplyDelete
 12. በነገራችን ላይ የግብጽ ኦርቶዶክስ አሁን በአብ ቀኝ ኢየሱሥ አማላጅ እንደሆነ ታምናለች!Our Lord Jesus Christ is God the almighty Who does not have just one role in our lives. He functions on our behalf and on God's behalf. Our Lord Jesus Christ is our Mediator Who made it possible for us to be reconciled with God through His death on the Cross for the forgiveness of our sin. He is now sitting at the right hand of His Father interceding for us. Through His intercession@, He is able to save all who come to God through Him "Therefore He is also able to save to the uttermost those who come to God through Him, since He always lives to make intercession@!!! for them" (Heb 7:25). However, on Judgment Day when the time comes to give an account of our stewardship, when it is past the intercession time, it is our Lord Jesus Christ Who will judge us. ይህ መሆኑ ግን ቅዱሳንን አማላጅ አይደሉም ማለት አይደለም! http://www.suscopts.org/q&a/index.php?qid=1086&catid=210

  ReplyDelete
 13. Protestants and tehadsos do not distinguish between mediation and intercession. We believe that our Lord Jesus Christ is the One and Only Mediator between us and God the Father "For there is one God and one Mediator between God and men, the Man Christ Jesus" (1 Tim 2:5). By His death on the cross, our Lord Jesus Christ gave Himself as ransom for all and no one else can claim this role.

  Intercession, on the other hand, is the asking of someone to pray for you before the Lord. Whether that person is alive on earth or have departed, should not make a difference since we believe that the departed are not dead but are alive; for the Holy Scriptures says, "I am the God of Abraham, the God of Isaac, and the God of Jacob'? God is not the God of the dead, but of the living" (Mt 22:32).

  Now, why would asking someone to pray or intercede for us before God diminish or take away the glory of God? Our Lord Jesus Christ asked us to love one another and to pray for those who persecute us "Pray for those who spitefully use you and persecute you" (Mt 5:44). This prayer is definitely an intercessory prayer for people who do not pray for themselves, are disobedient to God’s commandments and are away from God. It is this prayer of intercession that the Lord will hear when we pray for them and will lead them to have a change of heart. St. Paul says, "Therefore I exhort first of all that supplications, prayers, intercessions, and giving of thanks be made for all men" (1 Tim 2:1).

  Furthermore St. James says, "Pray for one another, that you may be healed. The effective, fervent prayer of a righteous man avails much" (James 5:16). Who is more righteous than the saints who had lived on earth in a godly manner to the end and departed to be with the Lord in Paradise? They are those whom we ask to pray for us. If we accept that people on earth can pray and intercede for us, we should likewise believe that those who have departed are not dead but are alive and can intercede for us before the Lord; for their prayers are effective and heard by the Lord.

  ReplyDelete
 14. Do the saints in heaven hear our prayers? Do they know our situation on earth; if yes, how; any biblical verse? Do they hear more than one prayer at once?

  The answer to these three questions is affirmative. Our knowledge in the other world will increase and many secrets will be revealed to us when we put off the material body which restricts the spirit. In addition, there will be what God reveals to the spirit, which comes within the scope of divine revelation. "For now we see in a mirror, dimly, but then face to face. Now I know in part, but then I shall know just as I also am known" (1 Cor 13:12).

  The Holy Book of Revelation tells us that the twenty-four elders "each having a harp, and golden bowls full of incense, which are the prayers of the saints" (Rev 5:8). This proves that they know these prayers and raise them before God.

  In the story of the rich man and Lazarus our father Abraham said to the rich man "But Abraham said, 'Son, remember that in your lifetime you received your good things, and likewise Lazarus evil things" (Luke 16:25) how did our father Abraham come to know the evil Lazarus suffered and how could he say about the rich man’s family 'they have Moses and the prophets’ though he departed earth hundreds of years before Moses and the other prophets.

  In the Holy Book of 2 Chronicles 21:12 we read about King Jehoram who after killing all his brothers receives a letter from Elijah the prophet, who had departed from earth and ascended to heaven many years previous to that, warning him that the Lord would strike him. Also in the event of transfiguration, Moses and Elijah appeared with the Lord Jesus Christ and were speaking about His departure (Luke 9:31).

  ReplyDelete
 15. የሰው ልጅ ከውድቀቱ በኃላ በተሰጠው ሕግ ተመርቶም ይሁን በሌላ እድንበታለሁ ብሎ ባሰበው መንገድ ከኃጢኣት ሞትና ከዘላለማዊ ኩነኔ ሊድን ፈጽሞ አልተቻለውም። የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ጽድቅም ቢሆን እንኳን ለሌሎች ተርፎ ከዘላለም ኩነኔ ለማዳን ይቅርና ለራሳቸውም እንደመርገም ጨርቅ ሆኖባቸው ነበር። (ኢሳ 64፥6) ምናልባት እግዚአብሔርን በመፍራታቸውና በትእዛዙ በመሄዳቸው በሰው ሚዛን ሲመዘኑ ቅዱሳንና ጻድቃን ተብለው ቢጠሩም ሕግን ሁሉ ስላልፈጸሙና የኣዳም ልጆች በመሆናቸው ምክንያት አዳማዊ ኃጢአት ስላለባቸው ከተጠያቂነት ነጻ አልነበሩም። (ኢዮ 15፥7፤ 10፤ 25፥4-6፤ ማቴ 12፥34፤ መዝ 50፥5፤ ሮሜ 3፥11፤ 23፤ 5፥12፤ ኢሳ 48፥8)
  ሊቁ አቡሊዲስም እንዲህ ብሏል፦
  ፦ «ሰው ዓለምን ለማዳን አይችልም፤ የሰው መሞትም ከኃጢአት አያነጻም። - - - ዳዊት «ሕያው ሆኖ የሚኖር ሞትንም የማያይ ሰው ማነው? ከሲኦል አጅስ ነፍሱን የሚያድን ማነው?» ሲል እንደተናገረ ሞትን ያጠፋ ዘንድ ሕወትንም ያበራ ዘንድ የሚቻለው ከሰዎች ይገኛልን? ነፍሱን ለማዳን ያልቻለ ከሆነማ ሌላውን ለማዳን እንዴት ይችላል? እንዱን ለማዳን ካልቻለስ መላውን ዓለም እንዴት ሊያድን ይችላል? ኃጢአት በሰው ውስጥ አድሮአልና። ሞትም ይከተለዋል። - - - አዳም በበደለ ጊዜ ሰውን የወለደው በራሱ አምሳል ነው።» (ሃይ አበ ምዕራፍ 42 ክፍል 8 ቁ 5፤7-8፤ ዘፍ 5፥3፤ ኤር 3፥24-25)
  የሰው ዘር በሙሉ በኃጢአት መበከሉን በዚህም የኃጢአት ብክለት በራሱም ሆነ በሌላ ነጻ መሆን እንደማይችል የተረዳው ደራሲ እንኳ። «ከኩነኔ ነፍሳቸውን ማዳን ነቢያት እንኳ አልቻሉም» በማለት በሰው አመለካከት ብቁ መስለው የሚታዩት ነቢያት ሌላውን ቀርቶ ራሳቸውን እንዳላዳኑ ተናግሯል።
  ወደፊት ለሚመጣው ፍጹም አዳኝ እንደጥላ ምሳሌ ሆኖ ያገለገለው የኦሪት ካህናት ምልጃና ጸሎት እንዲሁም መሥዋዕት ኅሊናን ሊያነጻ፤ ጊዜያዊ ስርየት ከማሰጠትም በቀር በኃጢአት ምክንያት የተቋረጠውን የእግዚአብሔርንና የሰው ግንኙነት እንደገና እንዲቀጥል ሊያደርግ አልተቻለውም። (ዕብ 9፥13-14)
  በዕርቅ ላይ የሁለቱም ጥለኞች ወገኖች መገኘታቸው የግድ ነው፤ አሊያ ግን እውነተኛ ዕርቅ አይወርድም። ቅዱሳን አበው፥ ካህናትና ነቢያት ሰው ብቻ ናቸው። ፍጹምነት ይጎድላቸዋል። ይህም ሆኖ ሊወክሉ የሚችሉት እንደ እነርሱ ኃጢአተኛ የሆነውን ሰውን ብቻ እንጂ እግዚአብሔርን የሚወክሉ ስላልሆነ የሰውና የእግዚአብሔር ዕርቅ በሰው አስታራቂነት በኩል የማይሞከር ሆነ።
  ቅዱሳን መላእክትን ብንመለከት ደግሞ እግዚአብሔርንም ሰውንም የመወከል ወገናዊነት የሌላቸው ረቂቃን መናፍስት ስለሆኑ ለማስታረቅ አልበቁም። እግዚአብሔርም እነርሱን አስታራቂ አድርጎ አልሾመልንም። የዮሐንስ አፈወርቅንና የጵርቅሎስን ምስክርነት እንጥቀስ፦
  ትርጓሜ፦ «እርሱ ተመልክቶን አነሆ ለእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነን ተገኘን። ሀብቱን ለማግኘት ኪዳንም ቢሆን፤ መሥዋዕትም ቢሆን፥ ወደ እርሱ ያቀርበን ዘንድ የሚችል ፈጽሞ አልነበረንም፤ ስለዚህ ይቅር አለን። ዙፋኑን ከብበው ከሚቆሙ ከመላእክት ከኃይላትም ወገን አስታራቂ አልሾመልንም፣ (ሃይ አበ ምዕራፍ 62 ክፍል 2 ቁ 15) በዚህ ክፍል ግእዙን ወደ አማርኛ የመለሱት ክፍሎች የፈጸሙት ስውር ደባ አለ። በግእዙ «ሊቀ ካህናት» ያለውን ወደ አማርኛ ሲመልሱ አልተረጎሙትም። እንደ ግእዙ «ሊቀ ካህናት»ነው ያሉት። በሌላ ስፍራ ላይ ግን «ሊቀ ካህናት» የሚለውን ግእዙን ወደ አማርኛ ሲመልሱ «አስታራቂ» ብለው ተርጉመውታል። ለዚህም በዚሁ ክፍል ቁ 14 ላይ በግእዙ «መኑ ውእቱ ሊቀ ካህናት ወምእመን ዘእንበሌሁ» ያለውን ወደ አማርኛ የመለሰው «ከእርሱ በቀር - - - የታመነ አስታራቂ ማነው?» ማለቱ ምስክር ሊሆነን ይችላል።
  የጵርቅሎስ ምስክርነት ደግሞ እንዲህ ይላል፦ ፦ «ወራዳው ሰው የገዛ ራሱ ከእኛ ጋር ዕዳን ስለሚከፍል ሊያድነን ባልቻለም፤ መልአክም ቢሆን ስለእኛ ቤዛ የሚሆንበት ሥጋ ስለማይኖረው ሊዋጀን አልቻለም (ስምዐ ጽድቅ ብሔራዊ ገጽ 150)

  አንባቢ ሆይ፤ ሰውስ በድሏልና ሊያስታርቅ አልቻለም። ቅዱሳን መላእክት ግን አልበደሉም ነበር። ነገር ግን ለማስታረቅ ያለመቻላቸው ምስጢር ግልጽ ሆነልን?

  ከላይ በተመለከትነው መሠረት ማንኛውም ፍጡር ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርበን አለመቻሉ የተረጋገጠ ነገር በመሆኑ ከዚህ በኋላ ድኅነታችን በፍጡር አማላጅ ወይም በመልእክተኛ (መልአክ) መሆኑ ቀርቶ በራሱ በሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ይከናወን ዘንድ የግድ ሆነ። ይህን ሲያስረግጥ ቄርሎስ እንዲህ ብሏል፦
  ፦ «ነቢይ ኢሳይያስ ሰው ሆኖ ያዳነን እርሱ ራሱ ጌታ ነው እንጂ ሌላ አማላጅ ወይም መልአክ አይደለም። በባዕድ ደም በዕሩቅ ብእሲም ሞት አላዳነንም። ራሱ በደሙ አዳነን እንጂ» (ሃይ አበ ምዕራፍ 77 ክፍል 46 ቁ 13፤ ኢሳ 63፥9 ግእዙን ተመልከት)

  ስለዚህ እኛን ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቅና ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርበን ሰው ሆኖ የመጣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢአት ንጹሕ የሆነ፥ በሰውነቱ ሰውን በአምላክነቱ ደግሞ እግዚአብሔርን ሊወክል የቻለ፥ እንደ ኦሪት ካህናት አስታራቂነቱ በሞት የማይሻር ሕያውና ዘላለማዊ ሊቀ ካህናት ሆነ። (ኤፌ 2፥12-13፤ ዕብ 7፥23-25

  አንዱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርንና ሰው ስለሆነ ተበድያለሁ የሚል እግዚአብሔርና በድያለሁ የሚል ሰው በእርሱ ተገናኙ። ይህም በመካከላችን የነበረውን ጥል አስወግዶ ዕርቃችንን ፍጹም አድርጎታል። በመጽሐፈ ምዕላድ የሚከተለው ተጽፎአል፦
  ፦ «ሥጋ ከመልበሱ በፊት በሁለቱም ወገን ንጹሕ የሆነ አስታራቂ ታጥቶ ነበር። ከእንግዲህ ወዲህ ግን በመለኮቱ ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሆኖ ኃጢአትን ይሰርይ ዘንድ ተገብቶታል። በሰውነቱ ንጹሕ አስታራቂና የሚጸልይ ሆኗል።» (ስምዐ ጽድቅ ብሔራዊ ገጽ 112)
  ኃጢአትን ሳይቀጣ እንዲሁ ማለፍ ለጻድቅ ባሕርዩ የማይስማማው ቅዱስ እግዚአብሔር የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ተሸክሞ በቤዛነት የሚሞትና የቁጣውን ትኩሳት የሚያበርድበት በእግዚአብሔር በግ የተመሰለው ልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነውና ስለኃጢአታችን አሳልፎ ሰጠው። (የሐ 1፥29፤ 1ቆሮ 5፥7፤ ኢሳ 53፥7፤ ራእ 7፥14፤ ኢሳ 53፥10)

  እኛን ከራሱ ጋር ለማስታረቅ እግዚአብሔር በልጁ በኩል ጣልቃ መግባት ያስፈለገው በፍጡራን ለመታርቅ ስላልተቻለ ነው። (ኢሳ 59፥16፤ 2ቆሮ 5፥19) ስለዚህም ኤፍሬም ሶርያዊ «ወኮነ ዐራቄ ለሐዲስ ኪዳን» «የዐዲስ ኪዳን አስታራቂ ሆነ» ብሎ እንደመሰከረ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዐዲስ ኪዳን ብቸኛ አስታራቂ ነው። (ውዳሴ ማር ዘእሑድ)

  ዐዲስ ኪዳን አንድ ዕለት ብቻ አይደለም። በጌታችን መገለጥ ተወጥኖ በፈሰሰው ደሙ የጸናና እስከ ዳግም ምጽአቱ ድረስ ያለው ጊዜ ነው።

  ክርስቶስ የዐዲስ ኪዳን ብቸኛ አስታራቂ መሆኑን ሲገልጽ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ፦

  ፦ «ከእርሱ በቀር ራሱ ብቻውን ኃጢአትን ማስተስረይ የሚቻለው የታመነ አስታራዊ ማነው? ለማስታረቅ ኃጢአትን ለማስተስረይ ያቀረበው መሥዋዕትስ ምንድነው? መሥዋዕት ለመሆን የነሳው ሥጋው ብቻ ነው እንጂ» ብሏል። (ሃይ አበ ምዕራፍ 62 ክፍል 2 ቁ 14)

  ReplyDelete
 16. Why do you have to reject the Saints in order to accept Christ Jesus INTERSSESION?ANCIENT FATHERS INCLUDING ST JHON CHRYSTOM PREACH CHRIST IS INTRESSESOR(MEDIATOR) ON OUR BEHALF BUT AT THE SAME TIME THEY PREACH ABOUT SAINTS INTERSSESION!!!

  ReplyDelete
 17. መካከለኛ፤ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ ተብሏል ሆኗልም። የኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኝትም ስለሁለት ነገሮች ነው።
  ሀ. ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሲሆን ሰው በመሆኑ መካከለኛ ተብሏል። ኢየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን አምላክ እየተባለ በወለድነቱ ይከበር ይመለክ የነበረ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔርነቱን ካላይ እንደተመለው ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ ከመምጣቱ በፊት እግዚአብሔር ነው፤ በስጋ ማርያም ከመጣም በሗላ እርሱ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እግዚአብሔር ቢሆንም ግን የሰውን ገንዘብ ገንዘብ አድርጓል ማለትም ሰው ሆኗል። ኢየሱስ ሰው ብቻ አይደለም አምላክም ጭምር ነው እንጂ። አስቀድመን እንደተናገርነው ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍጹም አምላክ ነው። በክርስቶስ ስጋ የመለኮትን ባህሪይ ገንዘብ አደረገ፤ መለኮትም የሰውነትን ባህርይ ገንዘብ አደረገ። በዚህም መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትን ከአምላክነት ጋር አዋህዶ ስለያዘ መካከለኛ ተብሏል። 1ጢሞ 2፤5 አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ደግሞ መካከለኛ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ራሱን ስለሁሉ ቤዛ ሰጠ።

  ለ. በሰውና በእግዚአብሔር፤ በህዝብና በአህዛብ፤ በሰውና በመላእክት መካከል የነበረውን የጸብ ግድግዳ አፍርሶ ራሱን ስለሁሉ ቤዛ አድርጎ በማስታረቁ መካከለኛ ተብሏል።
  አስቀድመን እንደተናገርነው ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው አለምን ለማዳን ነው። ዓለምን ማዳን ሲባልም ቆሽሾና ረክሶ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቶ የነበረውን አለም አድኖ ከአባቱና ከራሱ ጋር አስታርቆ ለመሄድ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክንና ሰውን ብቻ ሳይሆን ያስታረቀው በእግዚአብሔር የሚያምኑ የነበሩ ህዝብ የተባሉና በእግዚአብሔር የማያምኑ አህዛብ በእርሱ በማመናቸው ምክነያት ለድህነት የሚበቁበትን መንገድ ሊከፍት ስለመጣ መካከለኛ ተብሏል። ኢየሱስ መካከለኛ ነው ስንል በመካከል ያለውን ጸብ በተጣሉት መካከል ገብቶ በማስታረቁ፤ ጠቡን በማስወገዱ ነው።
  እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ኤፌ 2፤14-16 በዚህ ጥቅስ እንደምናየው ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከል ያለውን ልዩነት ያጠፋው በመሞቱ እንደሆነ ነው። ስለዚህ ለህዝብና ለአህዛብ ሞቶ እነርሱን በአንድነት ያለምንም ልዩነት ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዲገቡ ስላዘጋጃቸው መካከለኛው ተብሏል ሆኗልም። 1ጢሞ 2፤5 አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ደግሞ መካከለኛ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ራሱን ስለሁሉ ቤዛ ሰጠ።ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ዘለዓለማዊ ነው ነገር ግን አንድ ጊዜ ራሱን መስዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ የተፈጸመ ነው። መስዋዕቱ ዛሬ ያው ነው ለሚያምኑበት ሁሉ ያለ የማያልፍ ነው ሐዋርያው የኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ከአይሁድ ሊቀ ካህንነት የተለየ እንደሆነ ሲናገር ዕብ 7፤27 እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ያቀርቡ የነበረው የእንስሳትን ደም ነበር ኢየሱስ ግን ያቀረበው የራሱን ደም ነው
  የኦሪት ሊቃነ ካህናት ወደ እግዚአብሔር እየለመኑ ሐጢያትን ያስተሰርዩ ነበር። በተለይም በአመት አንድ ጊዜ ካህኑ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ደም ይዞ በመግባት ስለህዝቡና ስለራሱ ጸሎት ያቀርባል። ዘጸ 30፤10 ይህንን አንዱ ሊቀ ካህን ሲሞት በሌላው እየተካ መስዋዕትን ያቀርባል። ዕብ 9፡7 በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤
  ለዚህ ነው ሐዋርያው ዕብ 9፤25 12 የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም። ያለው።በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎች ወይም በጥጆች ደም አይደለም። የሌላውን ደም ሳይሆን የራሱን ደም ነው ያቀረበው። በእንስሳት ደም አይደለም ዓለም የዳነው በእርሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንጂ።
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት በልመና በእንስሳት ደም ሐጢያትን ያስተሰርዩ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ በደሙ በራሱ ነው ሐጢያትን ያስተሰረየው
  ዕብ 1፤33 እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ሞትና እርጂና ነበረባቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ለሊቀ ካህንነቱ ሽረት /መለወጥ/ የለበትም
  የኦሪት ሊቃነ ካህናት ድካም ነበረባቸው ሐጢያት ይሰራሉ በሌላ በኩል ሰዎች ስለሆኑ ለዘለዓለም መኖር አይችሉም። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እርሱ ከሐጢያት የራቀ ፍጹም ነው እርሱም ለዘለዓለም የሚኖር የማያልፍ ነው። ዕብ 7፡28 ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል።
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት በእየጊዜው እግዚአብሔር ይቅር እንዲል መለመን ነበረባቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን አንድ ጊዜ ባደረገው የመስቀል ስራ /ሊቀ ካህንነት/ አዳነን
  ዕብ 9፤26-27 ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።
  ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ያደረገው የማዳን ስራ እስከዘለዓለም በስሙ ለሚያምኑ ሁሉ የተከፈለ ዋጋ ነው።

  ReplyDelete
 18. እኔ የሚገርመኝ ግን በዚህ ሁሉ ትግል(ARGUMENT) ላይ እይታገልን ያለነው እኛው ተራ ምእመናን ነን እና MKIDUSAN MEMBERS ጋሻ ጃግሬዎቹ እና የመንፈሳዊ ኮለጅ ምሩቃን መምህራን ወዘተ ምን እየሰራችሁ ነው???? !!!! ምን እየሰሩ ነው ወይስ እነርሱ መውያየት ይፈራሉ????ENE MKIDUSAN ብዙ WEBSITE ቢኖራቸውም ምንም ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም ምላሽ መስጠት ካልቻላችሁ ምላሽ መስጠት የሚችሉትን እና እኛን ለቤተክርስትያን ልጆች እንድንሆን ያደረጉንን ...እነ በጋሻውን፣አሰግድን፣ዘርፌን... ETC ማሳደድ አቁሙ!!! ወይ ፍረድ ወይ ውረድ ያለው ማን ነበረ????

  ReplyDelete
 19. I think you are not followers of the Orthodox Church. Why do not you just continue your mission reaveling that you part of the PROTESTANT MISSIONARIES.!

  ReplyDelete
 20. እግዚአብሔር በቅዱስ ቃሉ ውስጥ እንደገለጸው ለዐዲስ ኪዳን ጥላና ምሳሌ ሆኖ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሕዝቡን ሲያስተዳድርና ሲመራ የኖረው በሕዝቡና በእርሱ መካከል መካከለኛ አድርጎ ባቆማቸው ተቀብተው በተሾሙ ካህናት፥ ነቢያትና ነገሥታት አማካኝነት ነበር። በዐዲስ ኪዳን ግን ለተለያዩ ነገዶችና ግለሰቦች ተሰጥተው የነበሩትን እነዚህን ሦስቱን ሹመቶች ሊቀ ካህንነትን፥ ነቢይነትንና ንጉሥነትን ሰው ሆኖ የተገለጸው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠቅልሎ ይዟቸዋል።

  «ክርስቶስ» የሚለው የግሪክ ቃል የጌታችን የሹመት ስሙ ነው። ትርጉሙ በዕብራይስጥ መሲሕ በአማርኛ የተቀባ፥ ቅቡዕ እንደ አሮንና እንደ ዳዊት ተመርጦ የተሾመና የነገሠ ማለት ሲሆን መቀባትም ለሦስቱ ሹመት ነው። ካህን ነቢይና ንጉሥ ለመሆኑ። (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ 549-550)

  አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ሰውነቱ ካህንነትን ነቢይነትንና ንጉሥነትን ገንዘብ ማድረጉን ሊቃውንተ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርገው አስተምረዋል።

  አባ መልከ ጼዴቅ በ 1984 ዓ/ም ባሳተሙት «ትምህርተ ክርስትና» 2ኛ መጽሐፍ ላይ ያሰፈሩትን እንመልከት፦ «ሦስቱ የድኅነት መሣሪያዎች በሦስቱ መዓርጋት የተፈጸሙትን የድኅነት ሥራዎች የሚገልጡ ናቸው። ሦስቱ መዓርጋት የተባሉትም ነቢይነት፥ ሊቀ ካህንነትና ንጉሥነት ናቸው። እነዚህንም ሦስቱን የማዕረግ ስሞች ክርስቶስ የማዳን ሥራውን የፈጸመባቸው ስለሆኑ የእርሡ መጠሪያ ስሞች ሆነዋል።ሊቁ ቄርሎስ (በሃይማኖተ አበው ም 81 ክፍል 52 ቁ 8 ላይ) እንደመሰከረው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው በመሆኑ፦ ብእሲ፥መሲሕ፥ ኢየሱስ፥ ታቦት፥ አስታራቂ፥ ስሙታን በኩር፥ ከሙታን ወገን ለሚነሣም በኩር የቤተ ክርስቲያን (የምእመናን) ራስ ተብሏል። በነዚህም ስሞች ይጠራል።

  እርሱ ፍጹም አምላክ ብቻ ሳይሆን ፍጹም ሰውም ነውና ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን ቢመስልም (ዕብ 4፥15) የአምላክነቱ ክብር ለቅጽበት እንኳ አልተቀነሰም። ክቡር አምላክ ሲሆን በፈቃዱ ራሱን ስለኛ ዝቅ አደረገ እንጂ በተዋሕዶ ምስጢር አንድ የሆነው እርሱ የአምላክነቱንም የሰውነቱንም ሥራ ሠርቷል። (1ጴጥ 3፥18)«በመለኮቱም ኃጢአትን ሁሉ የሚያጠፋ እርሱ ሰው በመሆኑ አስታራቂ ሆነን» (ሃይ አበ ምዕ 79 ክፍ 50 ቁ 68)ማስታረቅ የሚባለው በሁለት ሰዎች በኩል የሚቀርበውን አቤቱታ አዳምጦና ጥፋተኛው ማን እንደ ሆነ መርምሮ የዝምድና ውሳኔ የሚሰጥበትና በዕርቅ እንዲፈጸም የሚደረግበት ተግባር ሲሆን፥ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ሁኔታ የተስተዋለ እንደ ሆነ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ ዐጥፊው ሰው እንጂ እግዚአብሔር አይደለም ለምሳሌ ያህል ሁለት የተጣሉ ቡድኖች ወይም ግለ ሰቦች ባልና ሚስትም ቢሆኑ ለየራሳቸው የሚመርጧቸውን ሰዎች በማቅረብ አንድ አስታራቂ ኮሚቴ ወይም የቤተ ዘመድ የሽምግልና ጉባኤ ይሰይማሉ፡፡ የተሰየመው ጉባኤ እንደ አንድ አካል ሆኖ የሁለቱን ቡድኖች ወይም ግለ ሰቦች ጒዳይ ይመረምራል፤ አንዱ በደለኛ ሆኖ ከተገኘ ለተበደለው እንዲክስ ይወስናል፡፡ ተበዳዩ ለበደለኛው ይቅርታ እንዲያደርግ ይማልዳል፤ ያስታርቃል፡፡ “በቀድሞ ዘመን በአስታራቂነት የተመደቡት አሮንና ልጆቹ ሰውንና እግዚአብሔርን የማስታረቁን ኀላፊነትና ተግባር በፍጹምነት ደረጃ ለመወጣት ያልቻሉበት ጒድለት በግልጽ ሊታየን ይገባል፡፡ ሰዎች ብቻ እንደ መሆናቸው መጠን ለሰው ዘር ወኪሎች መሆን ቢችሉም እግዚአብሔርነት አልነበራቸውምና በአስታራቂው አካል የእግዚአብሔር ውክልና አልነበረበትም ማለት ነው፡፡ ስለ ሆነም የዚህን የሥራ መደብ ደረጃ በዚህ በመጨረሻው ዘመን እግዚአብሔር ወደ ፍጹምነት አሳደገው፡፡ ፍጹም እግዚአብሔር የሆነው ቃል ፍጹም ሰው ሆኖአልና በሊቀ ካህናትነትም ተመድቦአልና፡፡ እግዚአብሔርና ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስም የማስታረቁን ሥራ በፍጹምነት አከናወነው፤ ኀላፊነቱንም በብቃት ተሸከመው፡፡ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተለያዩ ሰዎች ይከናወኑ የነበሩትን የነቢይነትን፥ የንጉሥነትን ሥራዎች ከክህነት ጋር አዋሕዶ ተሾሞባቸዋል፡፡ እግዚአብሔርና ሰው በአንድ አካል ተዋሕደው ለሁለቱም እኩል ዝምድና ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ስለዚህም ይህ ማእከላዊነት በተዋሕዶ የጸና ዘላለማዊ እንጂ በጊዜያዊነት እንደ ተሰየመ ኮሚቴ የሚፈርስ አይደለም፡፡ በ1ጢሞ. 2፥5 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ፤ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛም አንድ እንደ ሆነ ይነግረናል፡፡ ይህም መካከለኛ ራሱን ለሁሉ ቤዛ የሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው «እርሱ ለራሱ ልመናን የሚሻ መስሎ ከጥንት ጀምሮ ያገኘንን ፍዳ ከእኛ ያርቅ ዘንድ አብን ማለደው። እንደገና ደግሞ እንዲያስበን ከእርሱም እንዳይለየን ስለእኛ አብን ይማልደው ዘንድ ባሕርያችንን ነስቷልና» (ሃይ አበ ም 79 ክፍል 50 ቁ 38)

  ReplyDelete
 21. “እንግዲህ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም፤ ነገር ግን፡- አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ያለው እርሱ ነው፤ እንደዚሁም በሌላ ሥፍራ ደግሞ፡- አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ይላል። እርሱም በሥጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትና ምልጃን አቀረበ፣ እግዚአብሔርን ስለመፍራቱም ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በሁዋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለተጠራ ለሚታዘዙለት የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው። ዕብ.5፡5-10በብለይ ኪዳኑ ሥርዓትና አገልግሎት የክህነቱ ሥልጣን የሌዊን ዘር ብቻ ተከትሎ የሚሄድ ሲሆን፣ ነገሥታት የሚሾሙት ደግሞ ከይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር። በዚህ በአዲሱ ኪዳን መንፈሳዊ ሥርአት ግን አንዱ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለቱንም ማለትም ንጉሥነቱንም ሆነ ክህነቱን በአንድነት የጠቀለለበት ምክንያት፣ የክህነት ሹመቱ በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት በመሆኑ ነው። በእግዚአብሔር ልጅ የተመሰለው መልከ ጼዴቅ ደግሞ “የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን” ነው። (ዕብ.7፡1-3)

  ስለዚህ እግዚአብሔር “አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ የማለለት አንድያ ልጁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዙፋን ላይ ሲቀመጥ የነገሥታት ንጉስ ወይም ፈራጅ ሆኖ ብቻ ሳይሆን፣ ስለሕዝቡ ድካም የሚማልድ ሊቀ ካህንም ሆኖ ነው ማለት ነው። ይህ የከበረ እውነት ከብዙ ወንድሞቻችን አእምሮ በመሰወሩ ምክንያት ነው “ዛሬ ክርስቶስ የሚፈርድ ንጉሥ እንጂ የሚማልድ ካህን አይደለም” ወደሚል ስሕተት ውስጥ የገቡት። የገዛ ስህተታቸውን ለማጽደቅ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ በግልጽ የተጻፉትን ቃላት እስከ መለወጥ የሚደርስ ሌላ ትልቅ ስህተት መፈጸማቸው ግን ወደ ፍርድ የሚመራ ድፍረት በመሆኑ “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለው ሐዋርያዊ ምክር ከዚህ ፍርድ እንዲያድናቸው እንጸልያለን።

  በራዕይ መጽሐፍ ምዕራፍ አምስት ላይ እንደምናነበው፣ መጽሐፉን የዘረጋውና ማሕተሙን የፈታው ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፤ በዙፋኑ፣ በአራቱ እንሰሶችና በሽማግሌዎቹ መካከል እንደታረደ በግ ቆሞ መታየቱ የሚገርም ነው። አንበሳው በግ ነው፤ በጉም አንበሳ ነው። ንጉሡ ካህን ነው፣ ካህኑም ንጉሥ ነው። የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የነገሥታት ንጉስና የካህናት አለቃ ነው። እነዚህ ሁለት መጠሪያዎች ግን የተሰጡት ያለ አገልግሎት አይደለም። በአብ ቀኝ የተቀመጠው የነገሥታት ንጉሥ የአካሉ - የቤተ ክርስቲያን ራሰ በመሆኑ አካሉን በመንፈሱ እየገዛና እያስተዳደረ መሆኑ የማያጠራጥር እውነት እንደሆነ ሁሉ፤ ይህቺኑ አካል ነውርና ነቀፋ የሌላት ቅዱስ አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ እየተጋ መሆኑም ልንረዳው የተገባ እውነት ነው። በሰማያት በግርማው ቀኝ የተቀመጠውና በመልከ ጼዴቅ ሹመት የዘላለም ሊቀ ካህን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ “የእውነተኛይቱ ድንኩዋን አገልጋይ” የሆነበትም ምሥጢር ይኸው ነው። ሆኖም አገልግሎቱን የሚፈጽምባት ማለትም በንግሥናው የሚገዛትና በክህነቱ የሚያነጻት ይቺ ድንኩዋን ከብዙዎች ዓይን ተሰውራለች።

  “ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፣ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኩዋን የዘላለም ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም። የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፣ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን??” (ዕብ.9፡11-14)

  ReplyDelete
 22. ...ከላይ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማያዊ ሊቀ ክህነት ለምን በመልከ ጼዴቅ ሹመት ወይም ሥርዓት እንደሆነ በጥቂቱ ለማየት ሞክረናል። መልከ ጼዴቅ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካሕን በመሆኑ፣ በሰማያት በግርማው ቀኝ የተቀመጠው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎትም እነዚህን ሁለት የአገልግሎት ሹመቶች ማለትም ንግሥናንና ክህነትን የያዘና ያጠቃለለ እንደሆነም ተመልክተናል። ጨምረንም ሰማያዊው ሊቀ ካህን ይህን ሰማያዊ አገልግሎቱን የሚፈጽምባት ማለትም በንግሥናው የሚገዛትና በክህነቱ የሚያነጻት፤ የምትበልጥ፣ የምትሻል፣ በሰው እጅ ያልተተከለችና ያልተሰራች፣ ለዚህ ፍጥረት ያልሆነች… የተባለችው “እውነተኛይቱ ድንኩዋን” ከብዙዎች ዓይን እንደተሰወረች እንመልከታለን በሥጋው ወራት ይፈጽመው ዘንድ ከአባቱ የተቀበለውን ሥራ ፈጽሞ በምድር ያከበረው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ዛሬም በሰማያት በግርማው ቀኝ የተቀመጠ የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኩዋን አገልጋይ ነው። እግዚአብሔር በክርስቶስ ይፈጽመው ዘንድ የጀመረው የከበረ ሥራ የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ ልጁን ወደዚህ ምድር በላከበት ወቅት የተጠናቀቀ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱሳችንን ጠጋ ብለን ስናነብ፤ እግዚአብሔር ዓለማትን ሁሉ የፈጠረው በክርስቶስና ለክርስቶስ (በልጁና ለልጁ) መሆኑን፣(ቆላ.1፡15-16 ዕብ.1፡2) በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ከእርሱ ተለይቶ የነበረውን ፍጥረቱን ሁሉ ወደራሱ የመለሰውም ቤዛውን በከፈለው አንድያ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ፣ እንዲሁም ደግሞ “በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል”(ኤፌ.1፡10) መሆኑን እንረዳለን። ታድያ ከዚህ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ አንጻር፣ እርሱ በክርስቶስ ሊያደርገው ያሰበው ሥራ ሁሉ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ በሥጋ ሆኖ በተመላለሰባቸው 33 ½ ዓመታት ውስጥ ተጠቃሎ ተፈጽሞአል ማለት ይቻላል?? ነቢዩ ዳዊት በመዝ.(40) ላይ ስለ ክርስቶስ በተናገረው ትንቢት መሠረት፣ ክርስቶስ የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ በተዘጋጀለት ሥጋ ወደዚህ ምድር ሲመጣ፣ “እነሆ አምላክ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ” ማለቱ ተጽፎአል። ታድያ ክርስቶስ በሥጋ በመምጣቱ የፈጸመው የእግዚአብሔር ፈቃድ ምንድነው?? ይህን ጥያቄ እጅግ ሰፊ በሆኑ የተለያዩ መልሶች መመለስ ቢቻልም፣ ዋናው ግን ራሱን ስለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቅበትንና ወደ እግዚአብሔር የሚመለስበትን ቤዛ ለመክፈልነው። (ዕብ.10፡5-10) ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣበትን የእግዚአብሔር ፈቃድና ዓላማ ለማጠናቀቅ በተቃረበበት ጊዜ እንዲህ አለ፡- “እኔ ላደርገው ዘንድ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርኩህ፤ አህንም አባት ሆይ ዐለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።” (ዮሃ.17፡4-5)

  ታድያ ክርስቶስ በምድር ይሠራው ዘንድ ከአብ የተቀበለውን ሥራ ከፈጸመ በሁዋላ ነገር ሁሉ አበቃ ማለት ነው?? አይደለም። የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ሁሉ ሞትን ከቀመሰ በሁዋላ እግዚአብሔር ከሙታን ሲያስነሳው፤ “ጠላቶችህን ሁሉ ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” የሚል ተስፋ ሰጥቶት እንደሆነ በመጽሐፋችን በግልጽ ተጽፎ እናገኛለን። አሁን ሁሉ ከእግሩ በታች እንደተገዛለት ገና አናይም። ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስ ዛሬም በግርማው ቀኝ በተቀመጠበት የሊቀ ክህነት አገልግሎቱ በሥራ ላይ ነው የምንለው። በተደጋጋሚ እንዳልነው፣ ክርስቶስ በምድር - በሥጋው ወራት የሠራው ሥራ ስለኃጢአት ሥርየት የሚሆነውን ፍጹም መሥዋዕት አንድ ጊዜ ማቅረብ ነው። ይሄ ዛሬ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ ያለው ሰማያዊ ሥራውና አገልግሎቱ ግን፣ በዚህ አንድ ጊዜ ባቀረበው ፍጹም መሥዋዕት በኩል ወደእግዚአብሔር ለሚቀርቡት ሕይወትን ማካፈልና መስጠት ነው። ከእግዚአብሔር ጋር መታረቃችን በሞቱ፣ መዳናችን ደግሞ በሕይወቱ በማያልፍ ሕይወት ኃይል በመልከ ጼዴቅ ሹመት የዘላለም ሊቀ ካህን ተብሎ በተጠራበት ሰማያዊ አገልግሎቱ የሆነበትም ምክንያት ይኸው ነው።

  “ስለእነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና፤ ስለዚህ በእርሱ ወደእግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” (ዕብ.7:25)
  “ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፣ ይልቁንም ከታረቅን በህዋላ በሕይወቱ እንድናለን።" (ሮሜ.5፡10)
  ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሳኤው ኃይል የሞትን መውጊያ ሰብሮ በሰማያት በግርማው ቀኝ ከተቀመጠበት ጊዜ ጀምሮ እጁን አጣምሮ የመላዕክትን ዝማሬ እየሰማ አይደለም። ይልቁንም በሥጋው ወራት ቤዛውን ከፍሎ ጠላቶች የነበርነውን እኛን ከእግዚአብሔር ጋር በማስታረቅ የጀመረውን የመዋጀት፣ የመቀደስና የማንጻት ሥራ እየሰራ ነው። ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን - የኣካሉ ራስ ነው ስንል፣ አካሉን የሚገዛና የሚያስተዳድር ነው ማለታችን ብቻ ሳይሆን፤ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን በፍጥረቱ መካከል የምታወርድ - የምትገልጥ መቅደስና ድንኩዋን እንድትሆን፤ በሕይወቱ ሙላት፣ በቅድስናው ውበት፣ በጽድቁ ልክና መጠን… የሚያንጻትና የሚያዘጋጃትም እርሱ ራሱ ነው ማለታችን ነው። በሞቱ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀንን እኛን በሕይወቱ ያድነናል - ቅዱሳንና ፍጹማን አድርጎም በአባቱ ፊት ያቀርበናል። ይሄ ደግሞ የማንም ልመናና ምልጃ የሚፈጽመው ሳይሆን፣ ክርስቶስ ራሱ በሰማያት (በመንፈሳዊ ክብሩ) ባለው የሊቀ ክህነት አገልግሎቱ ብቻ የሚከናወን ነው።
  ይህንንም አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ሰዓታት ድርሰቱ ‘እግዚአብሔር በተከላት በምስክር ድንኳን ለቅዱሳን የሚቆምላቸው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው’ በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለሙ ሁሉ ፍጹም መሥዋዕትን ያቀረበ ዘላለማዊ ሊቀ ካህን መሆኑን ተናግሯል፡

  ReplyDelete
 23. ክርስቶስ ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ከማቅረቡ ባሻገርም በሊቀ ካህንነቱ ጸሎትና ምልጃን አቅርቧል። ይህም የሆነው፥

  1) በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከመሞቱ በፊት በነበረው ጊዜ (ዮሐ 17፤ ሉቃ 22፥31-32) «አንቃዕደወ ሰማየ ኅበ በቡሁ ወአስተምሐረ ወላዲሁ ወአማኅጸነ አርዳኢሁ ከመ ይዕቀቦሙ እምኩሉ እኩይ» ትርጉም « ወደ ሰማይ ወደ አባቱ ቀና ብሎ አየ፤ ወላጅ አባቱንም ማለደ፤ ደቀ መዛሙርቱንም ከክፉው ሁሉ ይጠብቃቸው ዘንድ አደራ አስጠበቀ፣» (ቅዳ ማር ቁ 113)

  2) በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ (ኢሳ 53፥12፤ ሉቃ 23፥34፤ ዕብ 5፥7) « ወሰአሎ ለአብ ያኅልፍ እምኔነ መዓተ ዘረከበነ እምቅድም ከመ ዘለሊሁ ይኌልቊ ስእለተ ሎቱ እስመ ውእቱ ነሥአ አምሳሊነ ከመ ይስአሎ ለአብ በእንቲአነ ከመ ምዕረ ዳግመ ይዝክረነ ወኢይኅድገነ እምኔሁ» ትርጉም «እርሱ ለራሱ ልመናን የሚሻ መስሎ ከጥንት ጀምሮ ያገኘንን ፍዳ ከእኛ ያርቅ ዘንድ አብን ማለደው። እንደገና ደግሞ እንዲያስበን ከእርሱም እንዳይለየን ስለእኛ አብን ይማልደው ዘንድ ባሕርያችንን ነስቷልና» (ሃይ አበ ም 79 ክፍል 50 ቁ 38)

  3) ከትንሣኤውና ከእርገቱ በኋላ (ሮሜ 8፥34፤ ዕብ 7፥25፤ 1ዮሐ 2፥1) «ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ አዐርግ ሰማየ ኅበ አቡየ ወእስዕሎ በእንትአክሙ» ትርጉም «ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ አባቴ ዐርጋለሁ ስለእናንተም አለምናለሁ አላቸው።» (የፋሲካ ድጓ ገጽ 291 3ኛው ዓምድ ላይ)

  «ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ አዐርግ ሰማየ ኅበ አቡየ ኀበ እስእል ምሕረተ በእንተ አሊአየ» ትርጉም «ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን የኔ ስለሆኑት ምሕረትን ወደምለምንበት ወደ አባቴ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ አላቸው» (የሠኔ ሚካኤል ዚቅ (ዓራራይ))

  «ወልድ ሆይ እንደታመመ ሰው አስምተህ ተናገር። ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ በል። በአፋቸውም ውስጥ ሳለ አባ አባቴም ሆይ፤ ሥጋዬን የበሉትን ደሜን የጠጡትን ማራቸው ይቅር በላቸው በል» (ቅዳ አትናቴዎስ ቁ 144)

  ቀደምት አባቶቻችን በዚህ መልክ የክርስቶስን ዘላለማዊ ሊቀ ካህንነት ቢመሰክሩም በኋላ የተነሡት አንዳንዶች ግን አስተባብለውታል። ደግሞም የጌታ ሊቀ ካህንነት ያለፈ ድርጊት ብቻ እንጂ ቀጣይነት እንዳለው አይናገሩም። ይህም ዘላለማዊ ሊቀ ካህንነቱን የሚቃወም አመለካከት ነው። (ዕብ 5፥7) ይህን እውነት ለማጣመም የተጠቀሙበት ዘዴ የተለያየ ሲሆን ዋናው ግን የግእዝ መጻሕፍትን ሲተረጉሙ ለንባቡ የማይስማማ ትርጉም በመስጠት እንደሆነ ተደርሶበታል። ለምሳሌ ያህልም በሃይማነተ አበው ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ የተናገረውንና በግእዙ «እስመ ውእቱ ይተነብል በእንቲአነ» «እርሱ ስለኛ ይማልድልናል።» የሚለውን በቀጣይ ድርጊት የተገለጸውን ገጸ ንባብ ያለ አንቀጹ በኃላፊ ድርጊት «ማልዶልናል» ብለው ተርጉመውታል። (ሃይ አበ ም 63 ክፍል 2 ቁ 26)

  በሮሜ 8፥34 የግእዙ ዐዲስ ኪዳን «ወይትዋቀሥ በእንቲአነ» «ስለእኛ ይከራከራል» የሚለውን ያለፍቺው «ስለእኛ ይፈርዳል» ብለው ተርጉመውታል። «ተዋቀሠ» ስለሚለው ግስ የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዘገበ ቃላት የሚሰጠው ፍቺ «በቁሙ (ተዋቀሠ) ተሟገተ፥ ተከራከረ» የሚል ነው እንጂ ፈረደ አይልም። (ገጽ 401) ስለጌታ ፈራጅነት በሌላው ስፍራ ሲናገር የግእዙ ዐዲስ ኪዳን የሚጠቀመው ግስ «ኮነነ» የሚለውን ነው። (ዮሐ 5፥27 ግእዙን ተመልከት)

  መቼም ለጥቂት ጊዜ ካልሆነ በቀር ሁልጊዜ መዋሸት አይቻልም። አሁን አሁን ግን ከየአቅጣጫው ጫናው እየበዛና አውነቱ እየተገለጠ ሲመጣ ሮሜ 8፥34ን በፊት «ይፈርዳል» እያሉ የተረጎሙ ሁሉ «ይከራከራል» ወደሚለው ሐቅ ነው። ለዚህ አለቃ አያሌው ታምሩ ተጠቃሽ ናቸው። በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ እንዲህ ብለዋል፦ «እንግዲህ ቅ/ጳውሎስ «ለእመ ለሊሁ ያጸድቅ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ኢየሱስ ዘሞተ ወተንሥኦ እምውታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ወይትዋቀሥ በእንቲአነ» «እርሱ ቢያጸድቅ የሚኮንን ማነው? ሞቶ የተነሣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በአብ ቀኝ ተቀምጦአል ስለኛ ይከራከራል» (ሮሜ 8፥34) (ምልጃ ዕርቅና ሰላም 1992 ዓ/ም ገጽ 27)

  በ1ኛ ዮሐ 2፥1 ላይ «ወእመኒ ቦ ዘአበሰ ጰራቅሊጦስ ብነ ኅበ አብ ኢየሱስ ክርስቶስ» ይህም ማለት «የበደለ ሰው ቢኖር ከአብ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃ አለን» ማለት ነው። ነገር ግን የግእዙ «ጰራቅሊጦስ ብነ» ያለውን በአማርኛ ዐዲስ ኪዳን ትርጉማቸው ላይ «ጰራቅሊጦስ አለን» በማለት የክርስቶስን ጠበቃነት ለማስካድ ተሞክሯል። የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዘገበ ቃላት «ጰራቅሊጦስ» የሚለው ቃል በግሪኩ (ፓራክሊቶስ) እንደሆነና ትርሩሙም፦ አማላጅ፥ አስታራቂ፥ አፍ፥ ጠበቃ . . . . እንደሆነ ይናገራል። (ገጽ 907) የግእዙ ዐዲስ ኪዳን የገሪኩን ቃል ወደ ግእዝ ሳይተረጉም እንዳለ ነው የተጠቀመበት አማርኛው ዐዲስ ኪዳን ግን በመተርጎም «ጠበቃ» ብሎት እናነባለን።

  ReplyDelete
 24. ዛሬ በእግዚአብሔር ፊት ጽድቅ ሆኖ ያለኃጢአት የሚኖረው በመስቀል ላይ ሥራው ጠላቶች የሆኑትንና በእርሱ አምነው በአስታራቂነቱ በኩል የመጡትን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ መሆኑን ቄርሎስ እንዲህ ሲል ይገልጠዋል፥
  «ዛሬስ በምን ሁኔታ በእግዚአብሔር ፊት ተገለጠ (ታየ)? አምላክ የሆነ ቃል እንደኛ ሰው ሆኖ በዐዲስ ሥራ ታየ። ዛሬ ስለኛ በእግዚአብሔር ፊት በእኛ ባሕርይ በአስታራቂነት ታየ። . . . ዛሬ ስለኛ በእግዚአብሔር ፊት እንደታየ የምንናገረው ነገር ይህ ነው። በአዳም ትእዛዝ ማፍረስ ምክንያት ተዋርዶ የነበረ የሰውን ባሕርይ ገንዘብ አድርጎ በአባቱ በእግዚአብሔር ፊት ገልጦታልና በገንዘቡ ግብር በእግዚአብሔር አብ ፊት አቆመው ቀድሞ እንደነበረው አይደለም። ሰው ሆኖ ታየ እንጂ ዳግመኛ ወደ አባቱ ያስገባን ዘንድ» (ሃይ አበ ምዕ 79 ክፍ 50 ቁ 72-73)

  ክርስቶስ ምትክ የሌለው የዐዲስ ኪዳን ብቸኛ አስታራቂ እንዲሆን ካደረጉት ምክንያቶች አንዱና ዋነናው ሕያውና የማይሞት መሆኑ ነው። ሌሎች ቅዱሳን ሰዎችን ስንመለከት የማስታረቅ አገልግሎታቸውን የሚያከናውኑት እስኪሞቱ ድረስ ነው። ከሞቱ በኋላ ግን አይችሉም ነበር። የብሉይ ኪዳን ካህናት በቁጥር የበዙበት ምክንያትም ይኽው ነው። ካህኑ አሮን ከሞተ በኋላ ማስታረቅ ቢችል ኖሮ ሌላ ካህን ልጁ አልዓዛር መተካት አያስፈልገውም ነበር (ዘኍ 20፥22፤ ዕብ 7፥23)

  የማስታረቅ አገልግሎታቸው በሞት የመገደቡ ነገር ቁጥራቸውን አበራክቶታል። ሕያው ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ግን ለዘለዓለም አይሞትምና የሚተካው አላስፈለገውም።

  «እርሱ አንድ ባይሆን ኖሮ የማይሞት ባልሆነም ነበር። የኦሪቱ ካህናት ግን የሚሞቱ ስለሆኑ ብዙ ናቸው። እንደዚሁም ሁሉ ይህ አንድ የሆነው የማይሞት ስለሆነ ነው። ሐዋርያው በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ዘወትር ሊያድናቸው ይችላልና ለዘላለም የማይሞት ሕያው ስለሆነ፤ ስለእነርሱም ይማልድላቸዋል። ወዳጅ ሆይ፤ ይማልድላቸዋል ብሎ ያለው ሰው ስለመሆኑ እንደሆነ ተረዳህን? ሊቀ ካህናት በመሆኑ ያን ጊዜ ይማልድላቸዋል አለ . . . ለዘላለም ሕያው ስለሆነ ለዘወትር ያድናቸው ዘንድ ይችላልና አለ። ከእርሱ በኋላም የሚተካ የለም» (የዮሐንስ አፈወርቅ የዕብራውያን መልእክት ትርጓሜ 13ኛ ድርሳን ቁ 129-131፤ 135-136)

  ReplyDelete
 25. ክህነት (ካህን) በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሆኖ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ነው ፡፡ስለዚህ በዚህ ውይይታችን ክርስቶስ በዙፋን ላይ የተቀመጠ ሊቀ ካህን የሆነበትን ምክንያት መረዳቱ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ “ሊቀ ካሕናት” ተብሎ የተጠራበት ሥርዓት የአሮን ሳይሆን የመልከ ጼዴቅ መሆኑ ይህን የከበረ እውነት ለመረዳት የሚያስችለንን አንዳች ምሥጢር ይዞአል።መልከ ፄዴቅ ማነው? መልከ ጼዴቅ በምድር ላይ የሥጋ ዘመድ አልነበረውም። የተወለደበት አድራሻውም አይታወቅም።
  የትውልድ ሀረግ የለውም።ከዘር፣ ከጎሳ፣ ልክስክስ ነገር የጸዳ ነበር። የሰው ልጅ የዳነበት የክርስቶስ ክህነት የተገለጸበት ምሳሌ መልከ ጼዴቅ ነው።- ዕብ.7:3 “አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።” ይህ ሲባል መልከ ፄዴቅ ሰው አይደለም ማለት አይደለም ፡ ዘሩ አልተገለፀም ለማለት ነው፡፡ በብለይ ኪዳኑ ሥርዓትና አገልግሎት የክህነቱ ሥልጣን የሌዊን ዘር ብቻ ተከትሎ የሚሄድ ሲሆን፣ ነገሥታት የሚሾሙት ደግሞ ከይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር።አሮን ሊቀ ካህናት እንዲሆን በመመረጡ ከሌዊ ወገን ካህናት የመጀመሪያው ሆነ (ዘጸ 28, 1) ፡፡ ልጆቹም ካህናት እንዲሆኑ ተቀደሱ (ዘሌ 8, 12- 13, 30) ፡፡ በ123 ዓመቱ ሲሞት ሊቀ ካህናትነቱ ለልጁ ለአልዓዛር ተሰጠ (ዘኁ 20, 22-29 ፣ 33, 38 ፣ ዘዳ 10, 6) ፡፡ ...

  በዚህ በአዲሱ ኪዳን መንፈሳዊ ሥርአት ግን አንዱ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለቱንም ማለትም ንጉሥነቱንም ሆነ ክህነቱን በአንድነት የጠቀለለበት ምክንያት፣ የክህነት ሹመቱ በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት በመሆኑ ነው። በእግዚአብሔር ልጅ የተመሰለው መልከ ጼዴቅ ደግሞ “የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን” ነው። (ዕብ.7፡1-3)መልከ ጼዴቅ ማለት ራሱ የጽድቅ ንጉሥ ማለት ነው፡፡ የሳሌም ንጉሥ ነበር ፡፡ ይህም የሰላም ንጉሥ ማለት ነው ፡፡ የእግዚአብሔርም ካህን ነበር (ዕብ 7, 1)-በሌላ አባባል መልከ ጼዴቅ ካህኑ ንጉስ( the priest king) ይባል ነበረ ማለት ነው!!!ክህነቱ በእርግጥም ከአሮን ክህነት እንደሚበልጥ ተጽፎለታል ፡፡ ይህም አንደኛ በሥጋዊ ትውልድ ሳይሆን በእግዚአብሔር መሐላ በመሾሙ (ዕብ 5, 5-6 ፣ 7, 13-17) ፡፡ ሁለተኛ በሞት ሳይወሰን ለዘለዓለም በማገልገሉ ነው (ዕብ 6, 20 ፣ 7, 3 እና ከ23-25 ፡፡ ክርስቶስ እንደ መልከ ጼዴቅ በእግዚአብሔር ሊቀ ካህናት በመባሉ የአሮንን ክህነት አስቀርቷል (ዕብ 5, 7-10 ፣ 7, 11-19) ፡፡ ክርስቶስ እንደ መልከ ጼዴቅ ካህን ሆኖ ለኃጢአት ሁሉ የሚበቃውን መሥዋዕት አቅርቧልና የአሮን ክህነት አስቀርቷል (ዕብ 7, 11-28) ፡፡ የክህነቱን ሥራ የፈጸመው በምድራዊ መቅደስ ሳይሆን በሰማያዊ መቅደስ ፣ በእንስሳት ደም ሳይሆን በራሱ ደም ነው (ዕብ 9, 11-12) ፡ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት በመሆን ራሱን አንድ ጊዜ ሠውቶ ወደ ሰማያዊ መቅደስ ገብቷልና የሊቀ ካህናት ሥራ በአዲስ ኪዳን ቀርቷል (ዕብ 9, 1-28 ፣ 10, 12-21)


  ReplyDelete
 26. የዕብራውያን ጸሐፊ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን “የአዲስ ኪዳን መካከለኛ” ብሎታል። አዲሱ ኪዳን የዘመኑ እርዝመት ከመቼ እስከ መቼ ይሆን?? አዲሱ ኪዳን በጸናበት ዘመን ሁሉ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱሰ ክርስቶስ የኪዳኑ መካከለኛ ነው። ሐዋርያው ጳወሎስም “አንድ እግዚአብሔር አለና፣ በእግዚአብሔር በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፤(እዚህ ላይ ልብ በሉ!! ‘በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የነበረው መካከለኛ ደግሞ አንድ ነበር’ አላለም) እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” በማለት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኝነት የነበረና ዛሬም ያለ እንዲሁም ከእግዚአብሔር የተለየው ፍጥረት ሁሉ ወደእግዚአብሔር ተመልሶ ፍጻሜ እስከሚሆን ድረስ ወደፊትም የሚቀጥል እንደሆነ ነግሮናል። ታድያ በዚህ መልዕክቱ ላይ ጳወሎስ “ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ” በማለት ስለአንድ ያለፈ፣ ያለቀና የተጠናቀቀ ሂደት በሚጠቁም ቃል የተናገረው ስለምንድነው?? ስለመካከለኝነቱ?? በጭራሽ!!! ራሱን ለሁሉ ቤዛ አድርጎ ስለመስጠቱ ነው እንጂ!!! “…ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፣ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፣….”

  የዛሬ 2000 ዓመት አካባቢ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በመምጣቱ የተፈጸመና የተጠናቀቀ የእግዚአብሔር ሀሳብ አለ። ይሄ ክርስቶስ ከአብ የተሰጠውና በሥጋ በመምጣቱ የፈጸመው የከበረ ሥራ ደግሞ ነፍሱን ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ አድርጎ በመስጠት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን ጠላትነት በሞቱ ያስወገደበት የማስታረቅ ሥራ ነው። ይሄ የማስታረቁ ሥራ አንድ ጊዜ የተጠናቀቀና የማያዳግም ሥራ ነው። ደግሞም ይህን በሥጋ የመጣበትን ስራ ፈጽሞ በክብር በአባቱ ቀኝ ከተቀመጠበት ጊዜ ጀምሮ፣ “የኁዋለኛው ጠላት” የተባለው ሞት ከእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ላይ ተሽሮና እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ሆኖ ፍጻሜ እስከሚሆን ድረስ፣ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ ባለው የሊቀክህነት አገልግሎቱ የሚፈጽመውና ገና ያልተጠናቀቀ የማዳን ሥራ አለ። ይሄ እውነት ሲበራልን ነው፣ የክርስቶሰ የአዲሰ ኪዳን መካከለኝነት በሥጋ በመምጣቱና ቤዛውን በመክፈሉ ብቻ “ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ” የተጠናቀቀ እንዳልሆነ የምንረዳው።

  “ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፣ ይልቁንም ከታረቅን በህዋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ይህም ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።” (ሮሜ.5፡10-11)ልብ በሉ!! መታረቃችን በሞቱ የተጠናቀቀና የተፈጸመ ነው፣ ክርስቶስ ኢየሱሰ ዛሬ ስለመታረቃችን አንዳች የሚያደርገው ነገር የለም፣ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ ያለው ሊቀ ካህን እንደቀደሙት ካህናት ዕለት ዕለት ስለበደልና ስለኃጢአት የሚሆን ማናቸውንም አይነት መስዋዕት አያቀርብም፣ ለመስቀል ሞት ራሱን አሳልፎ ሲሰጥ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታል፣ እግዚአብሔርም ይህንን መስዋዕት ወዶ ተቀብሎታል፣ እንዲያውም እርሱ ራሱ በክርስቶስ ሆኖ ዐለሙን ሁሉ ከራሱ ጋር አስታርቆአል፣ ከእንግዲህ የማንንም በደል አይቆጥርም….. እኛም ዛሬ ሰዎች ሁሉ ይህን በመስቀል ላይ የተከፈለላቸውን ዋጋ እንዲያዩና፣ በእነርሱና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው ጠላትነት በክርስቶስ ሞት እንደተወገደ እንዲረዱ የተሰቀለውን ክርስቶስን እየሰበክን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ እንላለን። ስለዚህ የክርስቶስ የማስታረቅ ሥራ የተጠናቀቀ ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ግን መካከለኝነቱ ተጠናቅዋል ማለት ነው?? አይደለም!!! “… ይልቁንም ከታረቅን በህዋላ በሕይወቱ እንድናለን!!”

  መታረቃችን በሞቱ ነበር። መዳናችን ግን በሕይወቱ ነው። ለመታረቃችን መካከለኛ የነበረው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ዛሬም ለመዳናችን መካከለኛ ነው። መዳናችን በሕይወቱ - “በማያልፍ ሕይወት ኃይል” በመልከ ጸዲቅ ሹመት የዘላለም ሊቀ ካህን በሆነበት ሰማያዊ አገልግሎቱ ነው። ለዚህም ደግሞ “የእውነተኛይቱ ድንክዋን አገልጋይ” ተብሎአል። እዚህ ላይ ጨምረን ልናውቅ የሚገባው፣ ምልጃውም ከማያልፈው ሕይወቱና በግርማው ዙፋን ቀኝ ካለው ሰማያዊ አገልግሎቱ ጋር የተቆራኘ መሆኑ ነው፤ “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፣ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” እንዲሁም፣ “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ በእርሱ ወደእግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” የተባልነውም በዚሁ ምክንያት ነው ። (ሮሜ.8፡34 ዕብ.7፡25)

  ReplyDelete
 27. ማማለድ፤ ማስታረቅና መካከለኛ መሆኑን አምኖ መቀበል ከሌለ ፍጹም ሰው እንደሆነ ማመን በፍጹም ሊመጣ አይችልም። በመለኮታዊ ሥልጣኑ ማዳን እየቻለ ሥጋ መልበስ ያስፈለገው በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ ማፍረስ የሚችል ከኃጢአት ሁሉ ንጹህ የሆነ የእግዚአብሔር ልጅ በመካከል እንዲገባ በማስፈለጉ እንደሆነ አምኖ መቀበል የግድ ነው። ያለበለዚያ ነገረ ድኅነት የሚባል አስተምህሮ አይመጣም።
  ቀድሞ ሰውና እግዚአብሔርን ሲያገናኝ የቆየው ሕግ ነበር። ሕጉ የሚያዘውን ሁሉ የሚያስፈጽሙ መካከለኞች ደግሞ ካህናቱ ናቸው። በሕግ ተቀባዮች በሕዝቡና በሕግ ሰጪው በእግዚአብሔር መካከል ያሉት መካከለኛ የሕግ አስፈጻሚዎቹ ራሳቸው ንጹህ መሆን ይጠበቅባቸው ነበር። ይህንንም የስርየት መስዋዕት በማቅረብ መንጻት ግዴታቸው ነው። ከዚያም የሕዝቡን ሥርየት ሕጉን በመተግባር ያስፈጽማሉ። እንግዲህ ይህ መስዋዕት ዕለት ዕለት የሚደረግ ነው። እንደዚያም ተደርጎ ለሕጉ ፈጻሚዎች ዘላለማዊ የሆነ ስርየትን ማስገኘት አይችሉም። ይህ መስዋዕት ምድራዊ ነው። ምክንያቱም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ትዕዛዝን የማፍረስ የጥል ግድግዳ በቀዳማዊው ሰው ጥፋት የተነሳ ተተክሎ ነበርና።

  ይህ የጥል ግድግዳ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍረስ ነበረበት። በሕዝቡና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ በብቃት ለማፍረስ ደግሞ ኃጢአት የማያውቀው ሰው ያስፈልጋል። ክህነቱም ፍጹም ሊሆን ይገባል። ይህንንም ለማሟላት አምላክ ሰው በመሆን ያንን ደካማ ሥጋችን በመልበስ ከውድቀት ማዳን ነበረበት። በዚህም የተነሳ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ በፈቃዱ የአብ የባህርይ ልጅ ሆኖ ሥጋችንን ለመልበስ በግብረ መንፈስ ቅዱስ በመካከላችን አደረ። እንደሰውነቱ ኃጢአት አያውቀውም። እንደካህንነቱ ዘላለማዊ ካህን ነው። እንደአዳኝነቱ ሞት አያሸንፈውም። እንደልጅነቱ የአባቱን ፈቃድ የሚፈጽም ነው። እንደስርየት መስዋዕትነቱ አንዴ፤ ግን ለሁል ጊዜ የሚሆን ነው። ይህም የነበረውን ጥል አፍርሶ በአብ የተወደደ መካከለኛና ለሕዝቡ ኃጢአት ዘላለማዊ ሥርየትን ማስገኘት የሚችል ሊቀ ካህን ሆኗል።


  ማማለድ ወይም ማስታረቅ ማለት ይህ ነው። መካከለኛ ማለትም ይህ ነው። በኃጢአት ምክንያት በተሰደደው ሕዝብና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን ጥል አፍርሶ እንደሰውነቱ ፍጹም ልጅ ሆኖ ያስታረቀ/ ያማለደ/ የሚያደርጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ያለ፤ ስለጩኸቱም ድምጹ የተሰማለት ልጅ ማለት ይህ ነው። ይህንን ወልድ ሥጋ የመልበሱን አስፈላጊነትና የነገረ ድኅነት ምስጢር በመተው ወይም ለመቀበል ሳይፈልጉ መዳን የሚባል ነገር ፈጽሞ ሊታሰብ አይቻልም። አምላክነቱን እንደመተው ሳይቆጥር ፍጹም ሰው ሆነ ማለት ለማስታረቅ/ ለማማለድ/ ካልሆነ ሌላ ለምን? በመለኮታዊ ሥልጣኑማ ሰው መሆን ሳያስፈልገው በለይኩን ቃሉ ማዳን ይቻለው አልነበረምን? ሐዋርያው ጳውሎስም በግልጽ የወንጌል ቃል እንዲህ አለን።

  «እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው። ስለ እርሱም የምንናገረው ብዙ ነገር አለን፥ ጆሮቻችሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልንተረጕመው ጭንቅ ነው» ዕብ ፭፣፯-፲፩

  አዎ ሐዋርያው እንዳለው አምላክ ሰው ሆኖ ማማለዱንና ማስታረቁን ጆሮአቸው ለመስማማት በፈዘዙ ሰዎች መካከል መናገር ጭንቅ ነው። ሊቀ ካህን መሆኑን እያመኑ የሊቀ ካህን ሥራ ምንድነው ተብለው ሲጠየቁ እውነቱን ለመሸሽ በመፈለግና አምላክነቱን ከማንም በላይ መናገር እንደሚችሉ እየተኩራሩ እስከመስቀሉ ድረስ ብቻ ነው ሲሉ ይደመጣሉ። ከዚያ በኋላስ በሥጋው አላረገም? አሁን በአብ ቀኝ የተቀመጠው በሥጋው አይደለም? እንደመልከ ጼዴቅ ሥርዓት ዘላለማዊ ሊቀ ካህን አይደለም? ከመስቀል በኋላ ግሪካዊው መነኩሴ አውጣኪ እንዳለው ሥጋውን አረቀቀ ካልተባለ በስተቀር እግዚአብሔር ወልድ ዛሬም በሥጋው በዙፋኑ አለ። ክህነቱም ዘላለማዊ ነው። እንግዲህ በሰማያት ያሉትን የሚመስለው ነገር በዚህ ሊነጻ እንጂ በሰማያት ያሉቱ ራሳቸው ከእርሱ ይልቅ በሚበልጥ መስዋዕት ሊነጹ የግድ ነበረ። ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ» ዕብ ፱፤፳፫-፳፬ ይላል።

  ስለማን ሊታይ? ስለእኛ!!! በሰው እጅ ባልተሰራች ሰማያዊ መቅደስ በእርሱ ያመንን ሁሉ መግባት ይቻለን ዘንድ አንድ ጊዜ ባፈሰሰው ደሙ እርሱ አስቀድሞ ስለእኛ ገባ። ዘላለማዊ ሊቀካህናችን የምንለው ለዚህ ነው። ፍጹም በሆነ ፍቅሩ የመላእክትን ሳይሆን የእኛን ሥጋ የመልበሱ ምክንያትም ይህ ነው። እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር በልጁ በኩል በመግለጽ ወደመቅደሱ ለመግባት በሊቀካህናችን በኩል ድፍረት እንዲኖረን ያደረገበት ምስጢር ነው ኤፌ ፫፤፲-፲፪ «እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል። እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና» ዕብ ፯፤፳፪-፳፯ ሊያማልድ ዘወትር የሚኖረው እንዴት ሆኖ ነው?

  ዛሬ መስዋዕት ሆኖ የሚፈተተው ሥጋና ደም አንድ ጊዜ ቀራንዮ ላይ የተሰዋው እንጂ ክርስቶስ ዕለት ዕለት እየሞተ ነው ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ማለት ነው። ይህን «ማማለድ» የሚለውን ቃል መስማት የሚያቅለሸልሻቸው ሰዎች የክርስቶስን አምላክ መሆን አሳንሶ የሚያሳይ ሆኖ ስለሚሰማቸው ባደረባቸው ቅንዓት ስለተነሳ ዝም ብሎ አርጓል በሉ እንጂ ዛሬም ሊቀ ካህን ነው አትበሉ ይሉናል። እንደምድራዊው ሊቀ ካህን ዘላለማዊው ሊቀ ካህን የዘወትር መስዋእት የሚያቀርብ ሳይሆን አንዴ ባቀረበው የዘላለም እርቅ ወደአብ የሚመጡትን ሁሉ ያድናቸዋል። ምክንያቱም ሐዋርያው በላይኛው ጥቅስ ውስጥ እንደተናገረው «ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሊያድን ይችላል። ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታልና» ብሏል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Are you saying like the Protestants "ኢየሱስ አሁንም በሰማይ በአባቱ ቀኝ ሆኖ አሁንም ይለምናል፤ ይጸልያል...? Please make your point clear.

   Holy Bible says " የ2ኛ ቆሮ 5፤ 14-20
   " ... አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ...ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ...በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 20 እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።"

   ጌታ በስጋው ወራት ያደርገው የማስታረቅ አገልግሎት ለዘለአለም (እስከ አለም ፍጻሜ) ህያው ወኖ ይሰራል (ዕብ 7: 27)። ሆኖም ግን ጌታ በምድር ያደርገው እንደነበረው አሁንም በአባቱ ቀኝ ወኖ አባቱን ይለምናል፤ ይጸልያል ማለት፦ ኢየሱስን አሁን ባለው ፍጹም አምላዊ ክብር አለማየት ወይም አለመርዳት፤ በሰማያት በግርማው አንደተቀመጠም ኣለማመን ነው ዕብ1÷3-4።

   Jesus Christ Lords of Lord Kings of King, Our Savior. He is God.
   Praise His Name!

   Delete
 28. ወደ ዕብራውያን 7:27

  እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።

  Jesus Christ, Lords of Lord Kings of King, He doesn't cry to Save us anymore. He did It! ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።

  Praise His Name!

  ReplyDelete
 29. I just like this kind of teaching God bless you all. God the father the son and holy sprit.

  ReplyDelete

 30. የዮሐንስ ወንጌል 16፤26

  "በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም... ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ።"

  ጌታ አብን የምለምንላቹ አይደለሁም አለኮ።

  የ2ኛ ቆሮ 5፤ 14-20
  " ... አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ...ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ...በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 20 እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።

  + ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም!

  +በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ!

  ReplyDelete
 31. ኢየሱስ:- ፈራጅ ወይንስ አማላጅ?
  አንድ ወንድሜ፥ “ጌታ በመስቀል ላይ ሁኖ ዓለሙን ከፈጣሪ ሲያማልድ በዚያው ቅጽበት በዙፋኑ ላይ ሁኖ የዚህ ዓለም ገዥም ፈራጅም ነው። ዛሬም በዙፋኑ ላይ ሁኖ ይህን ዓለም ሲገዛ ለጠፋው ዓለም አማላጅም ፈራጅም ነው። ነገም በዙፋኑ ላይ ሁኖ በዚህ ዓለም ሲፈርድ ለቀረው ዓለም አማላጅም ገዥም ነው።” አለኝ። እንዴት ፈራጅም አማላጅም... መሆን ይቻላል? ስለው “የአምላክን ሥራ በጊዜና በቦታ ወስነን የምናየው አይደለም። በእርሱ ዘንድ ሁሉ ነገር አሁን ነው። ትላንት፥ ነገ የሚባል የለም። እንደሰው ግን ዛሬም ለዘለዓለሙም፤ አማላጅም ፈራጅም ነው እንላለን” አለኝ። ምን ልመልስለት...?

  ReplyDelete