Thursday, May 23, 2013

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 15

የግንቦቱ ሲኖዶስ በእውነት ቃል አገልግሎት ላይ ያቀረበውን የ“ኑፋቄ” ነጥቦች መመልከታችንንና በእግዚአብሔር ቃል መመዘናችንን በዚህ ጽሑፍም እንቀጥላለን፡፡ ለዛሬው የምንመለከታቸው የሚከተሉትን ሁለት ነጥቦች ይሆናል፡፡

“ለ. ‘ቤዛ ዓለም ኢየሱስ ብቻ እንጂ ማርያም ቤዛ ዓለም መባል አይገባትም’ በማለት በአማላጅነቷ ቤዛ የሆነችን የእመቤታችን አማላጅነት ይቃወማል፡፡ መጽሐፈ ሰዓታት በመቅደሱ ሚዛን ገጽ 12 እና 13”
“ሐ. ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳ - የሚለውን ጸሎት ‘እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሣ ያደረገውን የማዳን ሥራና የከፈለውን መሥዋዕትነት የሚቃወም ልመና ነው’ በማለት በቤተ ክርስቲያናችን የሚጸለየውን የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ያጥላላል፡፡ መጽሐፈ ሰዓታት በመቅደሱ ሚዛን ገጽ 20”

“ቤዛ” የሚለውን የግእዝ ቃል የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት የሚፈታው በቁሙ (ቤዛ) ዋጋ፣ ካሳ፣ ለውጥ፣ ምትክ፣ ዐላፊ፣ ዋቢ፣ ዋስ፣ መድን፣ ተያዥ፣ ጫማ፣ ጥላ፣ ጋሻ የመሰለው ሁሉ” ነው በማለት ነው፡፡ (ገጽ 266) የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ደግሞ “ቤዛ የተያዘን ወይም የተወሰደን ነገር ለማስመለስ የሚከፈል ዋጋ፣ ካሳ፣ ለውጥ” ነው ይላል፡፡ (ገጽ 116) ቤዛ የሚለው ቃል ካለው ይህን መሰል ፍቺ አንጻርና እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትም “ቤዛ” የሚለው ስም የሚቀጸለው ለእውነተኛው ቤዛ ማለትም ስለ ሰው ልጆች ምትክ ሆኖ ለሞተውና ሕይወቱን ሰጥቶ ያመኑበትን ነጻ ላወጣው ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም ይህን በግልጥ ይመሰክራል፡፡ ከእርሱ በቀርም ለሰው ልጆች ቤዛ አለ አይልም፡፡

“…የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።” ማቴ. 20፡28

“የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤” ሉቃ. 1፡68

“በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።” ሮሜ 3፡24

“ነገር ግን፥ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።” 1ቆሮ. 1፡30-31

ቤዛ መባል ለኢየሱስ ክርስቶስ የተቀጸለው እንዲሁ አይደለም፤ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ምትክ በመሞት ተለዋጫችን ወይም ቤዛችን ስለሆነ ነው፡፡ ቤዛ መባል ለእርሱ ብቻ ይገባል፡፡ ከእርሱ በቀር ለእኛ ቤዛ የሆነ ፈጽሞ የለም፡፡ ስለዚህ የእውነት ቃል አገልግሎት “ቤዛ ዓለም ኢየሱስ ብቻ እንጂ ማርያም ቤዛ ዓለም መባል አይገባትም” በማለቱ የተናገረው ኑፋቄ የለም፡፡ እንዲያውም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን “ማርያምን ቤዛዊተ ዓለም” የሚለውን ኑፋቄ ነው የተቃወመው፡፡ ታዲያ ኑፋቄ የተናገረውና መወገዝ ያለበት ማነው? ማርያምን ቤዛዊተ ዓለም ያለው ክፍል? ወይስ ማርያም ቤዛዊተ ዓለም መባል አይገባትም ያለው የእውነት ቃል አገልግሎት? ምን ያደርጋል ዘመኑ እውነተኛ ትምህርት የሚወገዝበት ኑፋቄ የሚወደስበት በመሆኑ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ የሊቃውንቱ ጉባኤ የማርያምን ቤዛነት ማጽደቁና የጳጳሳቱም ጉባኤ በእርሱ ላይ ተመሥርቶ ማውገዙ ቤተክርስቲያኗ “ቤዛዋን ክርስቶስን በእናቱ ቤዛነት መለወጧን በጉባኤ ያረጋገጠችበት ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡

ለመሆኑ ማርያም ቤዛ የተባለችው በምን መልኩ ለሰው ልጆች ተለዋጭ ወይም ምትክ ሆና መስዋእትነትን ከፍላ ነው? የሚለውን ጥያቄ ግን ማንም ሊመልስ አይችልም፡፡ የሲኖዶሱ ቃለ ጉባኤው “በአማላጅነቷ ቤዛ የሆነችን የእመቤታችን አማላጅነት ይቃወማል፡፡” በማለት ያስረዳው ማርያም ቤዛ የሆነችው በአማላጅነቷ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ነገር ግን አማላጅነት እንዴት ተደርጎ ነው ቤዛነት የሚሆነው? ይህ ውድ ሕይወትን በመሰዋት የተገለጠውን ቤዛነትን ዝቅ አድርጎ መመልከት ነው የሚሆነው፡፡ ማርያም ቤዛ ናት የሚሉ ክፍሎች እርስዋ ለሰው ልጆች የከፈለችው መስዋእትነት የቱ እንደሆነ በተጨባጭ ሊያስረዱን ይገባል፡፡ ነገር ግን ቤዛ የሆነችበት አንድም አጋጣሚም ሆነ ምክንያት የለም፡፡ አሊያ ቤዛ የሚለው ስም አለቦታው የሚወድቅ ይሆናል፡፡ ደሃውን ሰው ሀብታሙ ብሎ እንደመጥራት የሚቆጠር ፌዝ ነው፡፡ ይህን ፌዝ ወደ ቤተ ክርስቲያን ያገባው አምልኮተ ማርያምን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የተከለውና ያስፋፋው አጼ ዘርአ ያዕቆብ መሆኑ አይካድም፡፡ ሊቃውንቱ ይህን ስህተት ማረም ሲገባቸው በጭፍን በአማላጅነቷ ቤዛ ሆነችን ብለው ስህተትን ማጽደቃቸው ቤተክርስቲያኒቱ ከድጡ ወደማጡ መግባቷን በተጨባጭ ያመላከተ ውሳኔ ነው፡፡

“ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳ - የሚለውን ጸሎት ‘እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሣ ያደረገውን የማዳን ሥራና የከፈለውን መሥዋዕትነት የሚቃወም ልመና ነው’ በማለት በቤተ ክርስቲያናችን የሚጸለየውን የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ያጥላላል፡፡” የተባለው ክስም እጅግ አስቂኝ ነው፡፡ “የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ መዓት ያድነን” የሚለው “ጸሎት” “እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሣ ያደረገውን የማዳን ሥራና የከፈለውን መሥዋዕትነት የሚቃወም ልመና ነው” ተብሎ በእውነት ቃል አገልግሎት የተሰጠው ማስተካከያ ተገቢ እንጂ ስህተት አይደለም፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ምህረት በተገለጠበትና በአንድያ ልጁ የሚያምን ሁሉ እንዲድን እግዚአብሔር በወንጌሉ በሚጠራበት በዚህ ዘመን ማርያምን ርህሩህ ልጇን ደግሞ ጨካኝ አድርጎ ማቅረብ በቀጥታ የእርሱን አዳኝነት መቃወም ነው፡፡

የተዘረጋውን የእግዚአብሔር ምሕረት ንቆ በሌላ መንገድ እድናለሁ ብሎ ማሰብ ከንቱ ልፋት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣ በክርስቶስ በማያምኑ ላይ እንደሚኖር ተጽፏል፡፡ “በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።” (ዮሐ. 3፡36)፡፡ ታዲያ ይህ የጌታ ቃል ሐሰተኞች በደረሱት ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ድርሰት ሊለወጥ ይችላልን? በፍጹም አይችልም!! ዛሬ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በዳግም ምጽአቱ በእርሱ ካላመኑ በቀር ከቁጣው የሚያስመልጥ ምልጃና ጸሎት የለም፡፡ “ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና። እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤” (2ተሰ. 1፡6-8) ስለዚህ ከሚመጣው ቁጣ ለማምለጥ በልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያዋጣናል እንጂ ሌላ የመዳኛ መንገድ የለም፡፡ ስለዚህ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ጸሎትም ሆነ ልመና በልማድ ከመደጋገም ይልቅ የምጸልየው ምንድነው የሚለው? እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ነው ወይስ ከፈቃዱ ውጪ ነው? ብለን መጠየቅ አለብን፡፡ የቃሉን ምክር እንስማ፦

“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።” (1ዮሐ. 5፡20-21)

15 comments:

 1. ደጅ ሰላሞች ! ጥሩ ጽሁፍ ነው ። ነገር ግን የ እኛ ቤተ ከርስቲያን ሰባኪ ነን ባዮች በተለይም መምህር ዘበነ ለማ ና ዲያቆን አንዷአለም “ያለ ወላዲተ አምላክ ዓለም አይድንም ” የሚሉት ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነወይ ? የ ሐዋ 4: 12 አላዩት ይሁን በተጨማሪም “ቤዛዊት ዓለም” እያሉ መስበካቸው እንኴን ቲዎሌጅ ት/ቤት የገባ በበሩ ያለፈም ይህን የምንፍቅና ትምህርት አይናገርም ። በዚህ አይነት አስተምህሮ የ ተያዙ ብዙ ጀቢራ ሐሰተኛ ወንድሞች አሉና ተግሳጽ ይገባቸዋል።  ReplyDelete
  Replies

  1. ***አንተ ሲጀመር የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባል አይድለህም : ምክንያቱም የነ መምህር ዘበነ ተቃዋሚዎች እነማን እንድሆኑ ለኛ ግልጽ ነዉ : አንድም ተኩላው ነህ ምክንያቱም ለምድህን ገፎታልና ወይንም ተሀድሶ የሚባልው የዘምኑ ክፉ መንፍስ ነህ ! እናንተ የቤተክርስቲያን ጠላቶች እንድምትሉን አይደለም አምላካችንና መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ክምን እንዳዳነን ጠንቅቀን እናዉቃለን : ቤ/ክ ፈጽሞ የክርስቶስን የማዳን ስራ ለማርያም ሰጥታ አታውቅም ይህ እናንተ የምታውሩት የጠላት ወሬና መንጋዉን የለሉተር መንፈስ ተከታይ ይሆን ዘንድ ለመበተን የምታድረጉት ጥረት ነዉ : እግዚአብሔር ግን ሁሉን ያውቃል : የቤተክርስቲያን እንጀራ እየበላችሁ ለጠላት ታስማማታላችሁ : ይሆነብንን እርሱ ይመልከት:-

   እናም አስተዉል የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዲህ ነዉ :-

   ***ድንግል ማርያምን ስለምን የአለም ቤዛ እንላታለን? ቅድስት ድንግል ማርያም ለኛ መዳን ምክንያት ስለሆነች ነው።እግዚአብሔር ለአለም መዳን በድንግል ማርያም ታላቅ ስራን አድርጉአልና ቤዛዊት ዓለም እንላታለን።የድንግል ማርያም በእምነት መታዘዝ ለዓለም መዳን ምክንያት ሀናለች ።አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ስለተቤዤ ቤዛዊት ዓለም እንላታለን።ቤዛ የሚለው ቃል ለሙሴም ተሰጦት እናነባለን። ( የሐዋ ሥራ 7:35) በመልአክ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።

   *** የድንግልን የቤዛነት አገልግሎት በግልፅ ለመረዳት ይህን ሙሴን ለወገኖቹ የፈፀመውን የመታደግ አገልግሎት እንመልከት ፦ በሙሴ ጊዜ እስራኤላውያን በሰሩት ሃጢአት እግዚአብሄር ሊያጠፋቸው ተነስቶ ሳለ በሙሴ ፀሎት( የቤዛነት ፡ የታዳጊነት ፡ የዋስነት ፡ የባለሟልነት ስራ) ሃይል ከመጥፋት የዳኑትን ባየን ጊዜ ሙሴ ለእስራኤላውያን ቤዛ መሆኑ አይደለምን? (ዘጸ.32:11) ዳዊትም “ሙሴ በእግዚአብሄር ፊት ባይቆም ኖሮ” ሲል የገለፀው ይሄንኑ ነው፡፡ እንግዲህ ይህ የፍጡር ቤዛነት የእግዚአብሄርን ቤዛነት ይሽራልን? አይደለም፡፡ እንዲያውም ቸር እግዚአብሄር ለወዳጆቹ የሚሰጠውን የባለሟልነት ስጦታ ብዛት ይገልፃል እንጂ፡፡ እንግዲህ ሙሴ ወገኖቹን ከመጥፋት እንደምን አዳናቸው(ተቤዣቸው)(ታደጋቸው)? እንደክርስቶስ ደሙን በማፍሰስ ነውን? አይደለም በእግዚአብሄር ዘንድ የተወደደ ፀሎቱን በማቅረብ እንጂ ፡ ስለዚህም የፃድቅ ሰው ፀሎት በስራዋ እጅግ ሃይልን ታደርጋለች ተብሏል፡፡
   *** ”ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር» በማለት ያስረዳል፡፡ ራዕይ 5.5፣ ዮሐ. 7፣42፡፡ «ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፣ ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል» ኢሳ. 11፣1፡፡ ይህ ትንቢት የተነገረው ለእመቤታችን ሲሆን በትር ደረቅ እንደ መሆኑ መጠን ያፈራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይህችኛዋ ከእሴይ ግንድ ከዳዊት የተገኘችው በትር እመቤታችንም ድንግል ሳለች ያለ ወንድ ዘር ቁጥቋጦ የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስን የመውለዷ ምስጢር ነው፡፡እንግዲህ የአለም ቤዛ ክርስቶስ ከሆነ ድንግል ማርያምስ ቤዛዊት አለም መባሏ ስለምን ነው ቢሉ ፦

   አንድም ክርስቶስ አለምን ሁሉ ከሞት ወደህይወት ያሻገረበት ፡ ሃጢአታችንን ሁሉ የደመሰሰበት ፡ የሚደመስስበትም ክቡር ደሙ ፡ ቅዱስ ስጋው ከእመቤታችን ስለነሳው ነው ፤ በዚህም ክርስቶስ ከመወለዱ አንስቶ ፡ በቤተልሄም የከብት ግርግም ተጀምሮ ፡ በግብፅ ስደቱ ፡ በቀራኒዮ ስቃዩና ሞቱ ሁሉ አብራው አለችና በክርስቶስ የድህነት ስራ ውስጥ የእመቤታችን ስራ ጉልህ ሆኖ ይታያልና ነው፡፡ ስለዚህ የክርስቶስ ደሙ ህይወት ነው ፡ ደሙ መድሃኒት ነው ፡ ደሙ እረፍት ነው ፡ ደሙ የሚቤዥ ነው ፡ ደሙ ያረጋጋል ፡ ደሙ ሃይል ይሰጣል ፡ ደሙ የህይወት መጠጥ ነው ፡ ስጋውም የህይወት ምግብ ነው ፤ ይሄውም ከእመቤታችን የነሳው ነው እንጂ ከሰማይ ይዞት የወረደው አይደለም ፡ የመላእክትንም አልወሰደም ፡ ከአብርሃም ልጅ ከዳዊት ልጅ ከድንግል ብቸኛዋ እናቱ ስጋን ነሳ እንጂ (ቃል ስጋ ሆነ እንዲል )፡፡

   *** ወይንስ ምን እንላለን? ቅዱሳን ሃዋርያት ክርስቶስ ብርሃን ሲሆን ብርሃን አድርጓቸው ፡ መልካም እረኛ እርሱ ሲሆን እረኛ አድርጓቸው ፡ መምህር ክርስቶስ ሲሆን መምህር አድርጓቸው ፡ ለመንጋው ሁሉ እያሰቡ ፡ በቅዱስ ተምሳሌትነታቸው ለዲያቢሎስ ሲገብሩ የነበሩትን ለክርስቶስ እንዲገዙ ማድረጋቸው ፡ ከእሳት ላይ እንኳን እየነጠቁ ወደህይወት ሰውን መምራታቸው ፡ በስጋ ደዌ የተያዙትን እየፈወሱ ፡ ያዘኑትን እያፅናኑ ፡ የተጨነቁትን እያረጋጉ ፡ ተስፋ የቆረጡትን እያበረቱ ህይወታቸውን ሁሉ ስለአለም ሁሉ ህዝብ መዳን ገዷቸው ፡ በእስር የተንገላቱት ፡ በመግረፊያ የተገረፉት ፡ የታረዙት ፡ የተጠሙት ፡ በስለት የተወጉት ፡ በእሳት የተለበለቡት ፡ በሰይፍ የተሰየፉት ፡ በመጋዝ የተተረተሩት ፡ በገመድ የታነቁት ፡ መሬት ለመሬት የተጎተቱት ፡ በአራዊት የተበሉት ራሳቸውን ህያው መስዋእት አድርገው ለክርስቶስ በማቅረባቸው ይህን ሁሉ ያደረጉት ስለህዝብ ሁሉ መዳን ገዷቸው አይደለምን? ከክርስቶስ ጋር መሄድን እየናፈቁ ነገር ግን ለመንጋቸው የሚገዳቸው በአለም ስላሉት ሁሉ ሃኪም በመሆናቸው አይደለምን? ስለዚህም ለአለም ሁሉ ብርሃን ሆነው አበሩ ፡ እንደጧፍ እየነደዱ ፡ እንደሻማ እየቀለጡ ፡ ህዝቡን ሁሉ ታደጉት ፡ አዳኑት ፡ ወደህይወት ጎዳና አቀኑት ፡ በዚህም ክርስቶስ “እኔን ምሰሉ” ያለውን ቃል ፈፀሙ ፤ ክርስትና ይህቺ ናት፡፡   አንድ አምላክ ለቦና ይስጥልን !
   ክብርና ምስጋና አምላክን ለወለደችልን ለድንግል ማርያም ይሁን አሜን።

   Delete
  2. ለAnonymous May 29, 2013 at 11:32 AM

   Do you even know the difference between ransom (ቤዛ) & savior (አዳኝ)? It seems you twist the true definition to fit your distorted interpretation. Ransom is to redeem someone from captivity or bondage by paying the price. How was the Virgin Mary a ransom for humanity? Did she die on behalf of the whole world? What price did she pay to save the world? Don't tell me "ለኛ መዳን ምክንያት ስለሆነች ነው". The question is not whether she's "ምክንያተ መድህን" or not. We already know she is because the incarnate Son of God took a flesh from her to become a man like us. To be a "Ransom for humanity" & "ምክንያተ መድህን" are two completely different assertions.

   Delete
 2. musaen beza bilotal metsahf kidus ye hawaryat sira lay yih mebalu metsaf kidus tesasito yihon?

  ReplyDelete
 3. እመቤታችንን በጥንተ አብሶ ወይም በውርስ ኃጢአት የሚጠረጥር ሰው በእርግጠኝነት እግዚአብሔርን እንደ እግዚአብሔርነቱ አያውቀውም አያምነውምም፡፡ በመሆኑም በውጭ ካሉት መናፍቃን እስከ ውስጥ ካሉት ከሐዲያን ልብሳቸውና ቆባቸው እንጂ ልባቸው ክርስቲያን ያልሆነ ያልጰጰሰ ወይም ያልመነኮሰ፣ ቆዳቸው እንጂ ልባቸው ያልተቀባ፣ ሳይጠሩ የመጡ፣ ሰይጣን ለተልእኮው ያስገባቸው፣ የዲያብሎስ የግብር ልጆች እንደሆኑ ቅዱሱ ሐዋርያ ዮሐንስ በራዕዩ ተናግሯል “እግዚአብሔርንም ለመሳደብ፣ ስሙንና ማደሪያውንም፣ በሰማይ የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ” ራዕ.13፥6

  ‹‹ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን ዘመናትም የዘመንም እኩሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ሥፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተኋላዋ አፈሰሰ፡፡ ምድሪቱም ሴቲቱን እረዳቻት፤ ምድሪቱም አፏን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን፣ የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን፣ ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሔደ፡፡ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ” ዩሐ ራእ 12÷13-18 ክርስቲያኖችና መናፍቃንም ይህ ጥቅስ ለማን አንደተነገረ ያለ ልዩነት ይስማማሉ ወይም ስለ ወላዲተ አምላክና ስለ አማኑኤል እንደሆነ ያምናሉና የሚያነታርከን ነገር አይኖርም ማለት ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ የጥቅሱን ትርጉም በስሱ እንይ፡-
  ዘንዶው በመናፍቃን ልቦናና አንደበት አድሮ የሚያፈሰውን የስድብ፣ የዘለፋ፣ የክሕደትና የኑፋቄ ቃል ምዕመናን ሰምተው እንዳልሰሙ በልቦናቸው ሳያሳድሩ ንቀው በማለፍና በኑፋቄው ባለመሰናከል ባለመውደቅና ባለመመረዝ ቅድስት ድንግል ማርያምን የሚገባትን ያህል ክብር በመስጠት የዘንዶውን ድካም ከንቱ ያደርጋሉና፡፡ “ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን፣ የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን፣ ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ” ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ ማለት ድንግል ከአምላክ በተሰጣት የማማለድ፣ የማስታረቅ፣ የመራዳት ጸጋና በረከት በልጇ ስም አምነው የተጠመቁትን ክርስቲያኖችን ወይም ምእመናንን ትራዳለችና፣ ትደግፋለችና፣ ታነሣለችና፡፡ በዚህ አገልግሎቷ ዲያብሎስ ተቆጥቶ “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን” አለ የአንዲቱ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ዐሥርቱ ትእዛዛትን፣ ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን ሳይለዩ ሳይነጥሉ ይጠብቃሉና፤ “የጌታ ኢየሱስም ምስክር ያላቸውን” አለ ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡ በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል፡፡ የዚያን ጊዜም ከቶ አላውቃችሁም እናንተ ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ፡፡›› አለ ጌታ በወንጌል ማቴ.7፥21-23፡፡ስሙን ከጠሩ ከዚያም አልፈው በስሙ ተአምራትን የሚያደርጉትን እንዴት አላውቃቹህም ይላቸዋል ያልን እንደሆነ ዛሬ ክርስትና ሃይማኖት ነኝ የሚለው ቁጥሩ ከ30 ሽህ ካለፈ ቆይቷል ይሄ ሁሉ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ባይ ነው ከዚህ ሁሉ ሃይማኖት ነኝ ባይ ግን ክርስቶስ ኢየሱስን በትክክለኛ ማንነቱ የምታምን የምትገልጽ የምትመሰክር አንዲቷ ብቻ ናት ፡፡ ቃሉም የሚለው አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት አንድ ጌታ በመሆኑ ኤፌ.4፣5 ስለሆነም የተቀሩት ሁሉ የሚጠሯቸውና የሚሰብኳቸው የሚያምኑባቸውም ኢየሱሶች ሐሰተኞች ኢየሱሶችን ወይም ክርስቶሶችን ማቴ.24፣24 እና ኢየሱስ ነኝ ብሎ የሚመጣውን አውሬውን ነው ፡፡ሰይጣንም ለክፋቱ ለተንኮሉ ለዓላማው በእነኝህ ሐሰተኞች ክርስቶሶች ስም ተአምራትን ያሠራቸዋል፡፡በመሆኑም ነው የድንግል ልጅ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን ፣በስምህ አጋንንትን አላወጣንምን፣ በስምህ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ሲሉት ከቶ አላውቃቹህም እናንት ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ ብሎ የሚመሰክርባቸው ፡፡ ዘንዶው የተቆጣው በሴቲቱ ላይ ነውና የሚዋጋውም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን፣ የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን፣ ከዘርዋ የቀሩትን ነውና “ከዘርዋ የቀሩትን” አለ የወላዲተ አምላክ የሥጋ ዘመድ የሆኑትን ማለት ሳይሆን የጌታችንን የአምላካችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በሐዋርያው ዮሐንስ አማካኝነት ለክርስቲያኖች ሁሉ ከጌታ ለእኛ የተሰጠችንን የመስቀሉ ሥር የእናትነት ስጦታና በልጅነታችንም እንንከባከባት እንጠብቃትም ዘንድ የጣለብንን የአደራ ቃል ተቀብለን ወላዲተ አምላክን እናታችን ያደረግንና የእናትነት አገልግሎቷን የምናገኘውን እሷም ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌላዊው ዮሐንስ እማካኝነት ‹‹እነሆ ልጅሽ›› በሚለው አምላካዊ ቃል በተሰጣት የእናትነት አደራ ልጆቸ የምትለንን እንደ ልጅ የምትንከባከበንን የምታገለግለንን ማለት ነው፡፡ እንደሚታወቀው ልጅነት ወይም የክርስቶስ ወገንነት የሚኮነው የሚገኘው በዘር ኃረግ ሳይሆን እሱን በማመን የሚገኝ ነውና፡፡ በመሆኑም ወላዲተ አምላክን ትምክህታቸው ያደረጉትንና ንጽሕናዋን ቅድስናዋን የሚያውቁትንና የሚያምኑትን እናታችን የሚሏትን የአንዲቱን ቤተ ክርስቲያን የተዋሕዶ ልጆችን ( የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁትን ፣ የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ፣ከዘሯ የቀሩትን ) ተብሎ የተነገረላቸው የዚህች ቤተክርስቲያን ልጆች ብቻ ናቸው ፡፡ ቀደም ሲል በቀረበው ማብራሪያ መሠረት ከዘሯ ያልተቆጠረ የኢየሱስ ምስክር የለውምና ፣የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቅ አይደለምና ፡፡ እነዚህንም ሊዋጋ ሔደ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ አለ፡፡ አሸዋ በእምነት ያልጸና ተጠራጣሪና የከሐዲ ልብ ምሳሌ ነው፡፡ “ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓላት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል፡፡ ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው በዓለት ላይም ስለተመሠረተ አልወደቀም፡፡ ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል፡፡ ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ (ሰውን ከእግዚአብሔር የሚለዩ ፈተናዎች ኑፋቄ ክሕደት መከራ ደረሰበት) ያንም ቤት መታው ወደቀም አወዳደቁም ታላቅ ሆነ /በእምነት የጸና አይደለምና ኑፋቄ ክሕደት አለበትና ወደቀ አወዳደቁም የከፋ ሆነ/›› ማቴ.7፥24-27

  በመሆኑም በባሕር አሸዋ ላይ ቆመ አለ በመናፍቃን ልቦናና አንደበት ላይ አደረ ክርስቲያኖችን ያሳድድ፣ ይዋጋ፣ መከራም ያደርስባቸው ዘንድ ማለቱ ነው፡፡

  እናም ክርስቲያኖች ይህ ኑፋቄ ምን ያህል ከባድና አጋንንታዊ መሆኑን ቤተ ክርስቲያን ከሐዋርያት ባገኘችው ትምህርት ካረጋገጠች ቆይቷልና በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ብዥታ የለባትም፡፡ ከዘንዶው አፍ በሚፈሰው ኑፋቄ እንዳንመረዝ የወላዲተ አምላክ ረድኤት የልጇ ጥበቃ አይለየን አሜን፡፡ ይቆየን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህን አስተያየት የሰጠኸው ሰው በጣም የምትገርም ነህ፡፡ በቅድሚያ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ እመቤታችን ተሰድባለች ብለህ ጽፈሃል፡፡ ነገር ግን የልጇ ስምና ክብር ለእርሷ መሰጠቱና ቤዛዊተ ዓለም መባሏ ትልቅ ኑፋቄ ነው መባሉ ትክክል እንጂ ስሕተት አይደለም፡፡ ስድብም ሊሆን አይችልም፡፡ ይልቁንም ያልሆነችውን ነች ብለህ እየሰድብካት ያለኸው አንተ ነህ፡፡ ይህን መሞገትና በስሕተትና ባለማወቅም ቤዛዊተ ዓለም መባሏን መስረዳት እንጂ እንዲህ ያሉ የማስተካከያ ጽሑፎችና ሐሳቦች በቀረቡ ቊጥር ማርያም ተሰደበች ማለት፣ “ቅኔ ሲያልቅበት ቀረርቶ አለበት” የሚሉትን አይነት ነው የሚሆንብህ፡፡ ማርያም ተሰደበች ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ ያልከው ቤዛዊተ ዓላም መሆኗን በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት መሠረት ማስረዳት ስላቃተህ ነው፡፡ ምክንያቱም ቅዱሳት መጻሕፍት ኢየሱስን እንጂ ማርያምንም ሆነ ሌሎቹን ቅዱሳን “ቤዛ” ብለው አይጠሩም፡፡ ስለዚህ ወደ ልብህ ተመለስ ያለን ቤዛ አንድ ብቻ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ከእርሱ ውጪ ሌላ ቤዛ አናውቅም፡፡

   Delete
 4. Sometimes I am just wonder how we get in to this messed up believe? The Gospel of Jesus Christ was clear he is the only way the truth and the life .The whole Holy Bible is about him only about him how is it possible people start to believe in so many unnecessary believes? Even the Bible said Believe comes from hearing the word of God the word of God is the Bible so where did they get the idea to even think salvation is by Mary the mother when the Bible said salvation is only by Jesus alone. I hope the new generation which means our children learn the truth of Gospel about Jesus Christ.

  ReplyDelete
 5. ማርያምን ርህሩህ ልጇን ደግሞ ጨካኝ አድርጎ ማቅረብ በቀጥታ የእርሱን አዳኝነት መቃወም ነው፡፡

  ReplyDelete
 6. .የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።(1ዮሃ.5፡20)በየዘመናቱ የተነሱና ዛሬም ያሉ የወንጌል ባለአደራዎችስ “እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል??” እያሉ ለሚጠይቁአቸው የዚህ ዓለም ጎሰቁዋሎች ሁሉ፤ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፣ አንተና ቤተሰቦችህም ትድናላችሁ” እያሉ መልካሙን የምሥራች ይሰብካሉ። በእውነት የክርስቶስ ኢየሱስ ምስክሮች የሆኑና የቃሉ ባለአደራዎችስ “መዳን በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” የሚለውን ግልጽና የማያሻማ የመዳን መንገድ ለሰዎች ሁሉ ያሳያሉ። በእውነት በእግዚአብሔር የተጠሩ የመንግሥቱ ሠራተኞች፤ ለሚጠይቁአቸው ሁሉ መልስ የሚሰጡት በልባቸው ውስጥ ተሰውሮ ከተቀመጠው ዘላለማዊው “የጥበብና የእውቀት መዝገብ” ነው እንጂ፣ በሕይወት በኖሩበት ጥቂት ዘመን የተናገሩት ነገር እውነት ይሁን ሐሰት ከማይታወቁ ሰዎች ማስታወሻ ላይ አይደለም። እነዚህ የወንጌል ባለአደራዎች ስብከታቸው ስለመተላለፋችን ቆስሎ ስለበደላችን የደቀቀው ፣ ደግሞም “ደዌን የሚያውቅ - የህማም ሰው” የተባለውና በድካማችን ሁሉ ሊራራልን የሚችለው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “እናንት ደካሞች ሸክም የከበደባችሁ ሁሉ፣ ወደእኔ ኑ ፣ እኔም አሳርፋችሁዋለሁ” እያለ የዚህ ዓለም ደካሞችን የሚጣራ የርህራሄ ድምፅ = ታላቁ አምላካችንንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

  “በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆረጬ ነበርና።” (1ቆሮ.2፡2)

  ReplyDelete
 7. .የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።(1ዮሃ.5፡20)በየዘመናቱ የተነሱና ዛሬም ያሉ የወንጌል ባለአደራዎችስ “እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል??” እያሉ ለሚጠይቁአቸው የዚህ ዓለም ጎሰቁዋሎች ሁሉ፤ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፣ አንተና ቤተሰቦችህም ትድናላችሁ” እያሉ መልካሙን የምሥራች ይሰብካሉ። በእውነት የክርስቶስ ኢየሱስ ምስክሮች የሆኑና የቃሉ ባለአደራዎችስ “መዳን በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” የሚለውን ግልጽና የማያሻማ የመዳን መንገድ ለሰዎች ሁሉ ያሳያሉ። በእውነት በእግዚአብሔር የተጠሩ የመንግሥቱ ሠራተኞች፤ ለሚጠይቁአቸው ሁሉ መልስ የሚሰጡት በልባቸው ውስጥ ተሰውሮ ከተቀመጠው ዘላለማዊው “የጥበብና የእውቀት መዝገብ” ነው እንጂ፣ በሕይወት በኖሩበት ጥቂት ዘመን የተናገሩት ነገር እውነት ይሁን ሐሰት ከማይታወቁ ሰዎች ማስታወሻ ላይ አይደለም። እነዚህ የወንጌል ባለአደራዎች ስብከታቸው ስለመተላለፋችን ቆስሎ ስለበደላችን የደቀቀው ፣ ደግሞም “ደዌን የሚያውቅ - የህማም ሰው” የተባለውና በድካማችን ሁሉ ሊራራልን የሚችለው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “እናንት ደካሞች ሸክም የከበደባችሁ ሁሉ፣ ወደእኔ ኑ ፣ እኔም አሳርፋችሁዋለሁ” እያለ የዚህ ዓለም ደካሞችን የሚጣራ የርህራሄ ድምፅ = ታላቁ አምላካችንንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

  “በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆረጬ ነበርና።” (1ቆሮ.2፡2)

  ReplyDelete
 8. በመጀመሪያው አዳም መተላለፍ ምክንያት እግዚአብሔር ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ በኪሩቤልና በምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍ ጠብቆት ወይም ዘግቶት ነበር። በብሉይ ኪዳን የነበሩ መስዋዕቶች ሁሉ ይናገሩ የነበረውም ይህ የተዘጋ የሕይወት መንገድ ሊከፈት የሚችለው በመስዋዕት ብቻ እንደሆነ ነበር። “ኋለኛው አዳም” እና “ሁለተኛው ሰው” የተባለው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ለኃጢአት ሥርየት የሚሆን ቅዱስና ሕያው መሥዋዕት አድርጎ በመስቀል ላይ ያቀረበውም ይህንን የሕይወት መንገድ ለመክፈት ነበር ። እጅግ በጣም የሚገርመው እውነት ደግሞ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን የሕይወት መንገድ በሞቱ መክፈቱ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድም ሆነ እየቆረስን የምንበላው ሕይወት ራሱ መሆኑ ነው። “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ…” ማለቱም ለዚህ ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሲሞት በኢየሩሳሌም የነበረው የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከታች ለሁለት መቀደዱ፣ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ የመፍረሱ ምልክት ከመሆኑም በላይ፣ ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ መከፈቱን የሚያመለክት ነው። ለዚህም ነው የዕብራውያን ጸሐፊ፣ ክርስቶስ በደሙ መርቆ በከፈተልን “በአዲስና በሕያው መንገድ” እግዚአብሔር ወዳለበት፣ ዕረፍትና ዘላለማዊ ሕይወት ወደምናገኝበት መንፈሳዊ ሥፍራ ለመግባት ድፍረት እንደሆነልን የጻፈው። (ዕብ.19-22)

  እንግዲህ ክርስትና ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደው የዚህ አዲስና ሕያው መንገድ መገለጫ ነው። ጅማሬውም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምኖ የሞቱንና የትንሣዔውን ፋይዳ በመገንዘብ፤ ማለትም በሞቱ የኃጢአት ሥርየትና ይቅርታ፣ በትንሣዔው ደግሞ ፍጹም የሆነ አዲስ ሕይወት እንደሚገኝ በማመንና ይህንንም በውኃ ጥምቀት መስክሮ ከእግዚአብሔር ዳግመኛ በመወለድ ነው። በዚህም ሂደት ውስጥ ያለፈ አንድ ሰው በአዳም ከሆነው ኃጢአት፣ ሞትና ጨለማ፤ በክርስቶስ ወደሆነው ጽድቅ የተትረፈረፈበት ሕይወትና ወደሚደነቅ ብርሃን ይሻገራል። በኃጢአትና ባለመታዘዝ የወደቀውን ሰው በባርነት ጠፍንጎ ከያዘው የሰይጣን ሥልጣንና አገዛዝ ተላቆ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ወደሚገዛበትና፤ ፍቅርና ሰላም፣ መንፈሳዊ ደስታና ሰማያዊ ዕረፍት ወደሞላበት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መፍለስ ይሆንለታል። “የሞት መውጊያ” ከተባለው ኃጢአትና ከሥጋ ሥራ ነጻ እየወጣ፣ ወደ እግዚአብሔር መንግስት በሙላት ለመግባት የሚያስችለውን የመንፈስ ፍሬ በሕይወቱ ማፍራት ይጀምራል። በኃጢአት የተበላሸው ሕይወቱ ከላዩ እየተገፈፈ፣ ፍጹምና አዲስ የሆነ ሰማያዊ ሕይወት መልበሰ ይጀምራል። ወንድማችን ጳወሎስ በቆሮንቶስ ለሚገኙ ክርስቲያኖች በጻፈው ሁለተኛ መልዕክቱም የገለጠልን ይህንን እውነት ነው። “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፣ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።” (2ቆሮ.5፡17)
  ይሄ ስም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ከሚጠሩት ስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ብቻ ሳይሆን፣ በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያለውን ፍጥረት ሁሉ ለእግዚአብሔር የመዋጀትና የማዳን ኃይልና ጉልበት ያለው ስም ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊሊጲስዩስ ክርስቲያኖች በጻፈው መልዕክቱ ውስጥ በግልጽ እንደተናገረው፤ በሰማይም ሆነ በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከካሉ፣ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል።
  “ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናል” (ሮሜ.10፡9-10)

  ልብ በሉ!! ይህ ስም የሚጠራው በምድር ብቻ አይደለም፤ በላይ በሰማይም፣ከምድር በታችም ነው። ከምድር በታች ምን አለ ይሆን??? ይህ ስም የሚጠራው በዚህ ዓለም ወይም በዚህ ዘመን ብቻ አይደለም፤ በሚመጡትም ዓለማትና ዘመናት ጭምር እንጂ!!! አስተውሉ!!!! ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚንበረከክ ጉልበት ያለው በምድር ብቻ አይደለም፤ በሰማይም፣ ከምድር በታችም ነው እንጂ!!! ከምድር በታች ምን ይኖር ይሆን???

  ReplyDelete
 9. Most of you said it well Jesus is the only way the truth and life. There is no other way.God bless you all.

  ReplyDelete
 10. God bless you those who teaching salvationis only by our Lor Jesus Christ alone.

  ReplyDelete