Tuesday, May 14, 2013

ልደታ በአታ እና ኪዳነ ምሕረት ማናት?

ይህ ጥያቄ ላልተማሩ ካህናትና ምእመናን ቢቀርብ “እመቤታችን ናታ!” እንደሚሉ አያጠራጥርም፡፡ ምክንያቱም “ልደታ” “በአታ” እና “ኪዳነ ምሕረት” በሚሉ ስሞች ጽላት ተቀርጾአል፤ ቤተክርስቲያን ታንጿል፤ መጽሐፍም ተጽፎ ሊሆን ይችላል፡፡ ሊቃውንቱና የተማሩ ምእመናን ግን እነዚህ ስያሜዎች በሂደት የማርያም መጠሪያ ስሞች ተደርገው ተወሰዱ እንጂ ልዩ ልዩ ተግባራት የተከናወኑባቸውን ዕለታት ለማሰብ የተሰጡ ስያሜዎች እንደሆኑ ሊነግሩን ይችላሉ፡፡ አክለን “ቤተክርስቲያንን የሚመሯት ሊቃውንቱ ናቸው ወይስ ያልተማሩና ትምህርተ ሃይማኖት የሌላቸው ካህናትና ደባትራን?” ብለን ብንጠይቅ ደግሞ ምላሹና እውነታው ለየቅል ይሆንብናል፡፡ ምክንያቱም ሊቃውንቱ ናቸው ካልን ማርያም የተወለደችበትን ቀን ለማሰብ ቀን መለየታቸው ልክ ባይሆንም ልክ ይሁን እንበልና ለዚህ መታሰቢያነት በተለየው ቀን ስም ጽላት መቅረጽንና ቤተክርስቲያን ማነጽን ግን ምን አመጣው? የሚል ጥያቄ ያስከትላል፡፡ ምክንያቱም ዕለቱ ከመታሰብ አልፎ በሴት ስም ተሰይሞ ወደመመለክ እየተሸጋገረ ነውና፡፡ ስለዚህ ሊቃውንቱ ይህን ሊያደርጉ እንደማይችሉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ካደረጉ ግን ሊቃውንት የሚል የሙያ ስም ሊሰጣቸው አይገባም፡፡

እመቤታችን ተወለደች የተባለበት ቀን ግንቦት አንድ፣ ቤተመቅደስ ገባች የተባለበት ቀን ታህሳስ ሶስት ቀን፣ ቃል ኪዳን ተቀበለች የተባለበት ቀን ደግሞ የካቲት አስራ ስድስት ቀን ነው፡፡ ቀኑ በተሰጠው ስያሜ መሰረት ማርያም ትሁን ሌላ ብቻ ዛሬ ልደታ ናት፣ ዛሬ በአታ ናት፣ ዛሬ ኪዳነ ምህረት ናት እየተባለ ልዩ ልዩ አምልኮ ይፈጸማል፡፡ ስንቱ ሰው ነው ማርያምን ብቻ ሳይሆን ልደታ በአታ ኪዳነምህረት ተብለው የተሰየሙ ቀናትን እያመለከ ያለው? ባእድ አምልኮው የሃይማኖት ጭንብል አጥልቆ ብቻ ሳይሆን በግልጽ ባዕድ አምልኮ ሆኖ የሚከናወንበት ልማድ በህዝቡ ዘንድ አለ፡፡ ይህም በተለይ በግንቦት ልደታ “አድባር” በሚል ስም የተጀመረና ከቤት ውጪ ዛፍ ስር ወይም አንድ ለስርአቱ አመቺ በሆነ ስፍራ ንፍሮ በመቀቀል፣ ቂጣ ጋግሮ ቅቤ በመለቅለቅ፣ ቡና በማፍላትና ከብት በማረድ፣ ቂጣና ንፍሮ እየተበተነ ደም እንዲፈስስ እየተደረገ በማርያም ልደት ስም ባእድ አምልኮ እየተፈጸመ ይገኛል፡፡ ይህን ክርስቲያናዊ ያልሆነ አምልኮ ባእድ ቤተክርስቲያን በስብከት መልክ ስታወግዘው ቢታይም ጉዳዩ እየባሰበት መልኩን እየቀየረና ዘመናዊ መልክ እየያዘ መጥቷል፡፡

ዛሬ  አልተማሩም በልማድ ነው የሚመላለሱት በሚባሉ ምእመናን መካከል ብቻ ሳይሆን ዘመናዊ ናቸው የሚባሉ ክፍሎች ጭምር የግንቦት ልደታን በአዲስ መልክ እያከበሩና አምልኮ ባእድን እያስፋፉ ይገኛል፡፡ አሁን አሁን በየመንደሩ የሚታየው የአንድ መንደር ሰዎች ገንዘብና መብልና መጠጥ በማዋጣት በጋራ ሆነው ማታ ላይ ሙዚቃ ወይም መዝሙር ከፍተው እየበሉ እየጠጡ እየጨፈሩ እየሰከሩና እየተሳከሩ የሚያከብሩ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ስለት የሚሳሉበት ፕሮግራምም አለ፡፡ ከተሳታፊዎች መካከል እኔ ለሚቀጥለው ልደታ እንዲህና እንዲያ ካደረገችልን አንድ ጠርሙስ አረቄ እሰጣለሁ፣ አንድ በግ እገዛለሁ፣ ወዘተ የሚሉ ስለቶችን መስማት የተለመደ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የባእድ አምልኮ መገለጫ ነው፡፡ ስለት መሳል ያለብን ለእግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንማራለን፡፡ ከእግዚአብሔር ውጪ ለሌላ አካል ስእለት መሳል ባእድ አምልኮ ነው፡፡ የልደታ ተከታዮች ግን ስእለት የሚሳሉት ለልደታ ነው፡፡

በተለይ ይህ የግንቦት ወር ባእድ አምልኮ የሚፈጸምበት ወር ነው፡፡ መነሻው ደግሞ የሃይማኖት ጭንብል ያጠለቀ ትረካ መሆኑ ነገሩን አሳሳች አድርጎታል፡፡ ቤተክርስቲያን እንዲህ እንዳይደረግ የምትሰብክበት አጋጣሚ ባይጠፋም አብዛኛው ህዝብ ግን ከዚህ ነጻ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ለዚህ ሁሉ ችግር መነሻው ልደታ ተብሎ የተሰየመውና በሂደት የማርያም የልደት ቀን ሳይሆን የማርያም ሌላ ስም ተደርጎ የተወሰደው የበዓለ ቀን ነው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን እንዲህ ያለውን ለባእድ አምልኮ መነሻ የሚሆን ችግር ከስሩ ነቅላ ልትጥል ይገባታል፡፡

ለዚህም ልደታ በኣታ ኪዳነ ምህረት የምትባል ማንነት ያላት ሴት አለመኖሯን ማሳየትና እነዚህ ስሞች ማርያምን እንደማይወክሉ ማስተማር ይጠበቅባታል፡፡ በመጨረሻም ምንም ይሁን ምን በተለይ በልደታ ስም ንፍሮ መቀቀል፣ ቂጣ መጋገርና እንስሳ አርዶ አድባር አውግር እየተባለ ዘመናዊ በሚመስል መልክም በሙዚቃና በስካር የታጀበና ስለት ለልደታ የሚቀርብበትን የባእድ አምልኮ ዘርፍ ልታስቆም ድርጊቱንም ልታወግዝ ይገባታል፡፡

26 comments:

 1. dinkem mirmir!!!

  ReplyDelete
 2. synodosu gin eskemechie new zim yemilew? abatoch eko yezih hulu nefs baleda nachew.

  ReplyDelete
 3. ነገር ግን ወንድሞች ሆይ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን መለያየትንና መሰናከያ የሚያደርጉትን እንዳት መለከቱ እለምናችኋለሁ።ከእነርሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ፣እንደ አነዚህ ያሉ ሰዎች ለገዛ ሆዳቸዉ እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እይገዙምና።በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግር ተንኮል የሌለባቸዉን የዋሁን ህዝብ ልብ ያስታሉና።” ሮሜ. 16፡17-19

  መጽሀፉ እንድህ ስለምለን ያለማወቃቸዉን ስህተታቸዉን የዕዉቀት ጎደሎነታቸዉን አምነዉ ቀርበዉ ባይጠይቁንም “መጻህፍትንና የእገዚአብሔርን ኃይል አታዉቁምና ትስታላችሁ”እንዳላቸዉ የቅዱሳት መጻህፍትን ትርኋመያቸዉን ካለማስተዋላቸዉ ከመሳታቸዉ ከመዉደቃቸዉም አልፈዉ ጥራዝ ነጠቅ ዕዉቀታቸዉን ገልጸዉ የስድብ አፋቸዉን በመክፈት የእግዚአብሔር ስሙንና ማደርያዉን (ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ክዱሳን ጻድቃንን፣ሰማዕታትን፣መላእክትን እና የቃል ክዳኑን ታቦት) በመሳደብ “በእግዚአብሔርና በስሙ ላይ፣በማደርያዉም ላይ፣በሰማይም በሚኖሩት ላይ የስድብን ቃል ይናገር ዘንድ አፉን ከፈተ” ራዕ.13፡6-7 የተባለዉ አባታቸዉን(ዘንዶዉን ድያብሎስን) መስለዉ (ዮሐ.8፡40) ወደ ዉድቀት መቀመቅ አየተሯሯጡ ላሉት ይህን ጻፍኩላቸዉ።

  1. መጽሀፍ ቅዱስን እንድሁ በግርድፉ ከላይ ከላይ ብቻ እየሸመደዱ እየከነፉ (ሩጫዉ የት ለመድረስ እንደሆነ ባይገባኝም!)ትርጉሙን ምሥጢሩን ያልተረዱት እራሳቸዉ ሆነዉ ሳለ፣ “የኦርቶዶክስ አማኞች ከመሳለም በቀር መጽሀፍ ቅዱስን ማንበብ አያዉቁም “ ይላሉ ‘ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች’ ነዉ ከነ ተረቱ።እኛስ በሊቃዉንት መምህራን ብሉያቱ ከአድሳቱ ጋር በመልእክት በምሥጢር ተገናዝቦ ተተርጉሞ ተምረነዉ ተረድተነዉ ለበረከት ለሕወት(ቃሉ ለምያምኑት ሕይወት ነውና) ተሳለምነዉ በእምነት! ማንበብ(ፊደል) ብቻዉን ይገድላል መተርጎም(በመንፈስ) ያድናልና 2ኛ ቆሮ.3፡6-7።ልክ እንደ እነሱ መጽሀፍ ቅዱስን በገዛ ፍቃድ እንድሁ መተርጎም አይቻልምናን ።ዳሩ ግን መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን(የቀደሙ አባቶቻችንን) መርቶ ገልጾላቸዉ እንዳጻፋቸዉ አሁንም ሊቃዉንት አባቶችን መርቶአቸዉ ማስተርጎም የሚችለዉም እርሱ ነዉና።/1ዼጥ.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሞ

   የስሕተት አስተማሪዎች ሐሰተኛ ትምህርት የሚያስተምሩት ወይም
   አንዳንድ ክርስቲያን አስተማሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ አፈታት
   የሚጋጩትና በተሳሳተ ሁኔታ ቃሉን የሚፈቱት ለቃሉ አፈታት በጣም
   ጠቃሚ የሆኑ መሠረታዊ መርሆችን ባለመረዳትና ትኩረት ባለመስጠት
   ነው።
   መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉው ምስጢራዊ ነውና ይፈታል ማለት ትክክል
   አይደለም። በአብዛኛው መጽሐፍ ቅዱስ በጣም ግልጽ በሆኑና ምንም
   ፍቺ በማይፈልጉ ምንባቦች የተሞላ ነው። አንተን የሚደግፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ስትተረጉም literal method ትጠቀማለህ፤ ማለትም ያው የተጻፈውን እንዳለ ትቀበላለህ እንጂ፤ "ይሄ ስዕላዊ አባባል ነው" ወዘተ አትልም። ከአንተ ጋር የማይሄዱ ዓረፍተ ነገሮችንና ስንኞችን ግን መተርጎም ፤ ጸሐፊው ለምን ጻፈ? ምናልባት እኔ የማላውቀውና ያልገባኝ ነገር ሊያስተላፍ ፈልጎ ይሆን? ብለህ ከመመርመር ይልቅ ትርጉሙን (allegory method) በመጠቀም ሁለት የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ መተርጎሚያ methods ትጠቀማለህ። አንተን የሚደግፈህን ክፍሎች ሁሉ በ ቃል በቃል ትተረጉመዋለህ፤ አንተን የማይስማማህን ደግሞ ከliteral ወጥተህ ትርጉሙን ትጠቀማለህ።እንደዚህ ካደረግን እኮ የፈለግነውን ነገር መጽሐፍ ቅዱስን ብሏል ልንል እንችላለን። ምክንያቱም ዓወደ ምንባቡንና የደራሲውን ሰፋ ያለውን ሃሳብና ያንን ቃል ለምን እንደተጠቀመ ከመመርመ ይልቅ፤ የሆነ ቦታ ተመሳሳይ ቃል ፈልገን "ይሄው ቃሉ እዚህ ጋ እንዲ ተብሏል" ካልን፤ የፈለግነውን ነገር ደራሲውን ማስባል እንችላለን። ይሄ ግን መጨረሻው confusion (ባቢሎን) ነው።እባክህን መጽሐፍ ቅዱስ ሥዕላዊ ቋንቋ አይጠቀምም እያልኩ አይደለምና ስዕላዊ በሆነ መንገድ ልንረዳቸው የሚያስፈልጉ ክፍሎችን እንዳትደረድርልኝ።ነገር ግን ከእኛ አመለካከት ጋር ስላልሄዱ ብቻ የግድ በሥዕላዊ መንገድ መተርጎም አለባቸው የምንለው ነገር ትክክል አይደለም። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ለመረዳት ጥረት የሚጠይቁ ክፍሎች ደግሞ ያሉበት መሆኑ ግልጽ ነው።ይህ ጥረት ክፍሉ በየትኛው ኪዳን ውስጥ ከመገኘቱ ጀምሮ እስከ
   መጽሐፉ ዓይነት፥ ከቋንቋው እስከ ዳራው፥ ከዐውደ ምንባቡ እስከ
   ቀጥተኛ ወይም ምሳሌያዊ አገላለጡ፥ ወዘተ፥ ፍተሻ የሚጠይቅ ነው።
   በመጀመርያ አዲስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይየሚቀጠልና መጽሐፍ ቅዱስ ጋር እኩያ ሥልጣን ያለው ቃል የለም፤አይኖርምም።የቃሉ ፈቺ ቃሉ ነው።በሥዕላዊ አተረጓጎም መተርጎም ያለባቸው እንደ ራእይ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን፤ ያ ሥዕል ወይም ምሳሌ ምን ማለት እንደሆነ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው የሚተረጉመው እንጂ፤ ከሆዳችን የፈለግነውን እየፈጠርን አይደለም።1. ግልጽ ያልሆነው ጥቅስ ወይም ክፍል ያንን ጉዳይ በተመለከተ ግልጽ
   ሆነው በተጻፉት ጥቅሶች መብራራት አለበት። 2. ታሪካዊ የሆኑት የማይደጋገሙ ክስተቶች ያንን በሚመለከቱ
   ትምህርታዊ በሆኑ ክፍሎች መፈታት አለባቸው። ለምሳሌ፥ በሐዋ. 19፥6
   ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው
   በልሳኖችም ተናገሩ፥ ትንቢትም ተናገሩ...የሚል ጥቅስ እናገኛለን። ይህ
   የሆነ፥ ነ፥ የተፈጸመ ታሪካዊ ክስተት ነው።
   3. አዲስ ኪዳን በብሉይ ሳይሆን ብሉይ ኪዳን በአዲስ ማብራሪያነት
   መፈታት አለበት። አሮጌ አዋጅ ኃይልና ሥልጣን ቢኖረውም አዲስ አዋጅ
   ሲኖር በዚያ ይሻራል ወይም ይተረጎማል። እንዲሁ የቀደመውን ኪዳን
   ሕግና ትምህርት በአዲሱ ኪዳን እንፈታዋለን ወይም እናገናዝበዋለን
   እንጂ አዲሱን ኪዳን በቀደመው አንፈታውም።...

   Delete
  2. ... መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አንዳንድ ጉዳዮች የሚናገራቸው ነገሮች አድማጮችን
   የሚያስቆጡና የሚረብሹ ከሆኑ አለማንሳትና አለማውሳት የምዕራቡ
   ዓለም ዘዬ ሆኖአል። Political Correctness ይባላል። የአሜሪካው
   ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በመጀመሪያው ምርጫ ወቅት እንደ
   ‘ክርስቲያንነቱ’ መጠን ስለ ግብረ ሰዶማውያን ምን እንደሚል ተጠይቆ
   ሲመልስ ግልጽ ካልሆኑት የጳውሎስ መልእክቶች ይልቅ ግልጽ የሆነውንና
   ጌታ ስለ ፍቅር የተናገረውን እንደሚቀበል ተናግሮ ነበር። የተጠየቀው
   ጥያቄ ግልጽ ነው። ሰውየው ይህን ጥያቄ የሸሸው ለፖለቲካዊ ትክክልነት ነው። ፖለቲካዊ ትክክልነት ሰዎችን ላለማስቆጣትና ላለማበሳጨት ወይም ለዘለቄታው ላለማስቀየም እውነቱ በአንድ ስፍራ ቢኖርም ያንን እውነት አለመናገርና መመሳሰል ነው።
   መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱስ እግዚአብሔርን ባህርይው ስለሚገልጥና ሰውን
   በዚያ መስፈሪያ ስለሚለካ የሚያስቆጣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ
   በአመዛኙ በአንድ ባሕላዊ፥ ሕዝባዊ፥ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ መዋቅር
   ውስጥ የተጻፈ ነው። ዘላለማዊ እውነቱ በምንም ድንበር የማይከለል
   ይሁን እንጂ የተጻፈበት ከባቢ ካለንበት በጊዜ ብቻ ሳይሆን በስነ ልቡናም
   የራቀ ነው። ስለዚህም ቃሉን እንደ መጽሐፋቸው አድርገው ከሚቆጥሩቱ
   እንኳ ይዘቱን ለዘመናዊው አንባቢና አእምሮ ምቹና ለስላሳ ለማድረግ
   ተብሎ ጠቅላላው ይዘቱ መፋለስ እንዳለበት የሚመስላቸው አሉ።
   መጽሐፍ ቅዱስን ባልለሰለሰበት ስፍራ የሚያለሰልሱትና ያላለውን
   እንዲል ከሚገምዱት መካከል ለፖለቲካዊ ትክክልነት ዘብ የሚቆሙ
   ሰዎችም ናቸው። መዳን በክርስቶስ ብቻ በኩል መሆኑ የሚያስቀይማቸው አሉ። ጁወል ኦስትን (Joel Osteen) የተባለ ትምህርት አስተማሪ በCNN
   ቴሌቪዥን ቀርቦ ሳለ ጠያቂው፥ “ታዲያ አሁን መዳን የሚገኘው በኢየሱስ
   ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው ትላለህን? እስላሞችስ? ሌሎች
   ሃይማኖተኞችስ? እንደኔ ያሉ አይሁዶችስ?” ብሎ ሲጠይቀው በሁለት
   ደቂቃዎች ያህል መልሱ አምስት ጊዜ ያህል ደጋግሞ፥ “እኔ እንጃ፥ እም. . .
   ማለቴ . . . እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው፤ እኔ እንጃ. . . እኔ
   አላውቅም . . . እኔ የሰው ልብ ፈራጅ አይደለሁም” ነበር ያለው። ይህ
   ታዋቂና በአንዳንዶች ዘንድ እንደ ትልቅ ‘ቤተ ክርስቲያን’ መጋቢ
   የተቆጠረ ሰው ለምን እንዲህ አለ? ላለማስቆጣት! እውነት ያስቆጣል።...http://good-amharic-books.com/images/PDFs/ezmag018.pdf

   Delete
 4. Selam Egizihbirar Kenanitegar Yun.
  Lideta mariam malet Embetashin Yetweldsibt Kenin lemast Lemariam Yeteste Kitsil new enig sim Ayidelm Awiko awenabagi nachu .......Behata Lemariam malet wedebet mekides Yegabashibet yeminasitawisibet Ayidel.....Eniqual Yeamilak einat lidet yikirena yetera sew lidet yikeber yel Yebaster Daniel lidetm Yikeberal I know very well all the family.......Libona Yisitashu

  ReplyDelete
 5. God help us to open our eyes.If only pray to God he will listen all the time.only God is the one he hear prayer with out any return.

  ReplyDelete
 6. ጥሩ ቁም ነገር ያለው ሐሳብ ነው።ያለውቁት ማሳወቅ ለሌው ማስተማርና መማማሪ መልካም ነው። የባዕድ አመልኮ ከመንፈሳዊ ህይወት ጋር ተቀላቅሎ መገኙት እውነት ነው ከዚህ በሽታ መንጻት ያስፈልጋል። ነገር ግን የእመቤታችን ልድት ቀኑዋን ማክብር ክፋት የለዉ።በዘመናችን ሁሉ ሰው የልደት ቀኑን በድምቀት ባለው አቅሙ ያከብራል።ታዲያ የአምለካን እናት ለእኛም በመስቀል ላይ እናት እንድትሆነን የሰጥን እውነተኛው ጌታ ነው። የግንቦት ልደታ የምናከብረቅ በጥንቆላ መልክ መሆኑ እጅግ ስህተት ነው።ነገር ግን may ወር በፈረነጆቹ ዘንድ የእናቶች ቀን ተብሎ የሚከበረው ከዚህ ከቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በዓል ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠበብቶች ይናገራሉ።እጅግ ደስ ያሰኛል። እርሱዋ ለእኛ እናት በመሆኑዋል ስለምናም አግባብ ባለው ሥርዓት በጠቀ መንግድ ማሰብ አስፈላግ ነው።

  ReplyDelete
 7. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !May 15, 2013 at 8:27 AM

  Thank you so much, our church have many many problems. If we are the true believer (orthodox), we shall died to sin and alive to God. However, instead of following the words of God, we follow human practices. When the day we worship God with out adding or adapting human belief?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጥሩ ቁም ነገር ያለው ሐሳብ ነው።ያለውቁት ማሳወቅ ለሌው ማስተማርና መማማሪ መልካም ነው። የባዕድ አመልኮ ከመንፈሳዊ ህይወት ጋር ተቀላቅሎ መገኙት እውነት ነው ከዚህ በሽታ መንጻት ያስፈልጋል። ነገር ግን የእመቤታችን ልድት ቀኑዋን ማክብር ክፋት የለዉ።በዘመናችን ሁሉ ሰው የልደት ቀኑን በድምቀት ባለው አቅሙ ያከብራል።ታዲያ የአምለካን እናት ለእኛም በመስቀል ላይ እናት እንድትሆነን የሰጥን እውነተኛው ጌታ ነው። የግንቦት ልደታ የምናከብረቅ በጥንቆላ መልክ መሆኑ እጅግ ስህተት ነው።ነገር ግን may ወር በፈረነጆቹ ዘንድ የእናቶች ቀን ተብሎ የሚከበረው ከዚህ ከቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በዓል ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠበብቶች ይናገራሉ።እጅግ ደስ ያሰኛል። እርሱዋ ለእኛ እናት በመሆኑዋል ስለምናም አግባብ ባለው ሥርዓት በጠቀ መንግድ ማሰብ አስፈላግ ነው።

   Delete
  2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !May 17, 2013 at 4:54 PM

   I don't have any problem with my mother Kidist Denegle Mariam. She is selected by God, I can't denied that.I also believe that culture is very important to keep the religion, it is good tool to transfer the religion from generation to generation. look the western are loosing their religion since they did not related with culture. look killing the sheep and eat together is not bad, if you can able to teach the gospel or telling the story of the story of the bible, about the rule of God in referencing the bible only, the Judgement day and etc.

   May be two or three times back in the day wrongly celebrated ye kidist Denglen birth day with family, but we corrected that. I will travel next week to Addis, I will celebrate with praising Lord Jesus only. Geta Leholanchenem Lebona yesten. AMEN!

   Delete
 8. Ewnet new...Besemen Ethiopia hek=je beneberebet Gize yihen bdenib Ayichalehu. Abzagnaw sew Areqe ina bira be mahiber gezto Yixexal..bicha...Igziabher Yemayixerabet be'al new...mastewal yabzalin

  ReplyDelete
 9. ለዚህም ልደታ በኣታ ኪዳነ ምህረት የምትባል ማንነት ያላት ሴት አለመኖሯን ማሳየትና እነዚህ ስሞች ማርያምን እንደማይወክሉ ማስተማር ይጠበቅባታል፡፡

  Why do not you directly say there is no need for celebrating Virgin Mary's life?

  ReplyDelete
 10. Yemeberehan kuta ande geze kegemerech memelesha yelewemna neseha betolo geba kemeder getse satetefa

  ReplyDelete
 11. በተለይ ይህ የግንቦት ወር ባእድ አምልኮ የሚፈጸምበት ወር ነው፡፡ መነሻው ደግሞ የሃይማኖት ጭንብል ያጠለቀ ትረካ መሆኑ ነገሩን አሳሳች አድርጎታል፡፡ ቤተክርስቲያን እንዲህ እንዳይደረግ የምትሰብክበት አጋጣሚ ባይጠፋም አብዛኛው ህዝብ ግን ከዚህ ነጻ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ለዚህ ሁሉ ችግር መነሻው ልደታ ተብሎ የተሰየመውና በሂደት የማርያም የልደት ቀን ሳይሆን የማርያም ሌላ ስም ተደርጎ የተወሰደው የበዓለ ቀን ነው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን እንዲህ ያለውን ለባእድ አምልኮ መነሻ የሚሆን ችግር ከስሩ ነቅላ ልትጥል ይገባታል፡፡

  ለዚህም ልደታ በኣታ ኪዳነ ምህረት የምትባል ማንነት ያላት ሴት አለመኖሯን ማሳየትና እነዚህ ስሞች ማርያምን እንደማይወክሉ ማስተማር ይጠበቅባታል፡፡ በመጨረሻም ምንም ይሁን ምን በተለይ በልደታ ስም ንፍሮ መቀቀል፣ ቂጣ መጋገርና እንስሳ አርዶ አድባር አውግር እየተባለ ዘመናዊ በሚመስል መልክም በሙዚቃና በስካር የታጀበና ስለት ለልደታ የሚቀርብበትን የባእድ አምልኮ ዘርፍ ልታስቆም ድርጊቱንም ልታወግዝ ይገባታል፡፡

  ReplyDelete
 12. it's good discourse you have gone through to show the origin of the names, 'Lideta' 'Be-ata', and 'Kidanemehert' which belong to the Holy Virgin Mary; and the true children of the church know it carefully and they call the dates dedicated to Her to venerate their Mother, the Mother of all.
  Be watchful God, Jesus Christ, the Head of the Church leads the Church, and enlightens the heart of all the faithful if there is firm belief

  the faithful and true children of the Church strongly reject unncessary practices which go contrary to the teaching and belief of the church whose Head is Christ the crucified, and the Son of the God Father and Holy Virgin Mary whose birthday as well as the dates on which She entered the Temple and She received covenant from Her beloved Son, you mentioned above.
  the church, its true children, venerate Holy Virgin Mary for ever, and ever, and ever. The Church, true children of the Church, honor Holy Virgin Mary on the date She was born as She begot True Bread of Life and Drink of Life; true children of the Church honor Holy Virgin Mary on the date She came to the Temple as per the promise her chosen parents had made and this came to be so becuase the Almighty God had prepared Her for His abode before the world was created (Glory to Him); true children of the church honor Holy Virgin Mary on the date She received covenant from Her Beloved Son, Savior Christ Jesus, King of Kings. the true children of the churc have had such blessings from the Lord through our Mother given to St. John on Good Friday that She will be a Mother of all for ever. Remember the word, "Behold your Mother."
  Be watchful, the issue is not calling the dates, it is about venerating the Queen of Queens, the Mother of all, the Mother of the Almighty God, Who on the Holy Cross broke His flesh that He had taken up from Holy Virgin Mary. Don't mix up the issue of calling the personified dates from names with the misleading teaching by the discourse.
  we all need to be watchful

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለ አስተያየትህ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ፡፡
   "እመቤታችን ተወለደች የተባለበት ቀን ግንቦት አንድ፣ ቤተመቅደስ ገባች የተባለበት ቀን ታህሳስ ሶስት ቀን፣ ቃል ኪዳን ተቀበለች የተባለበት ቀን ደግሞ የካቲት አስራ ስድስት ቀን ነው፡፡" ይህነን ተማሩ ብለው ነው ያቀረቡልን ፤ የወቀሱ እየመሰላቸው አንዳንዶች የማያውቁትን ትምህርት እያስተላለፉ ነው ያለው፡፡ ቤተ ክርስቲያን መወቀስ ይገባት የነበረው በነዚህ መታሰቢያ ቀናት ቤተ ክርስቲያን አድባር ብላ ባዕድ አምልኮን ሰብካ ቢሆን ነበር ፡፡ የተለመደ ክስ ስለሆነ ብዙ አይደንቅም ፡፡

   Delete
  2. something tells me you don't know what "church" means..

   Delete
  3. ቀላቸው "ስለዚህ ቤተክርስቲያን እንዲህ ያለውን ለባእድ አምልኮ መነሻ የሚሆን ችግር ከስሩ ነቅላ ልትጥል ይገባታል፡፡" ይላልና ከዚህ ተጨማሪ ትርጉሙን አስተምረን ፡፡

   Delete
 13. Ekehdeke seitan

  ReplyDelete
 14. aba diablos go to hell tehadiso!!!

  ReplyDelete
 15. you are clearly justifying your being Tehadso, because you are trying to bring us a new thing which is totally out of the one and perfect religion orthodox tewahdo teachings .
  likachu yematawuku, sileman endemititsifu enquan tenkikachu yematawuku senefoch ena kihidetin yemitastemiru kehadiwoch lemehonachu ke friachu aweqnachu, Egziabher yikir yibelachu, wede betum yimelisachu
  silezih kibir lemigebaw kibir situ, bemilsiratwan ena twfitwan tebika lenorech lezich l andit betekristyan meseret Getachin ena medhanitachin eyesus kirstos mehonun atirsu, timbit yifetsem zend tiqawemu yihon enji yemafires hayil gin qintat tahil yelachum, silezih likachun ewequ, atizebariqu, degmo liqawintin metechet min ametaw alawaqinetachu ena tanashnetachu kezih maweq yichalal.
  egziabher Betekirstianin yitebiq, enantenim wedenisiha yimelisachu

  ReplyDelete
 16. Enkef!!!!!!!!!!!!!!!!!!Enkef!!!!!!!!!!!!!!Enkef!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 17. besime ab wewelde wemenfeskudus.Wendimie egziabher ayne libonah yabralih, ewketih lewengel mastemar bitawle endiet bamare, yilik geta bedemu lemeseretat betekristaian lemafres kemerot,eyaregkew yaleh wengel mastemar sayhon betekriastain mafres new. Seitan eskemechersha fird gizie endihu betekriastian mekawem silatanu siletegefefe sewochin lay adro yemiyadergew mukera yiktlal. Ante wendimie gin yemitaregewn bemastewal yihun.

  ReplyDelete
 18. Where is my comments Dn. Yonatan .

  ReplyDelete
 19. ekihideke seytan !!! ekihideke Tehadiso

  ReplyDelete