Friday, May 31, 2013

በዘርፈ ብዙ ችግሮች ለተተበተበችው ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ያስፈልጋታል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ያወራንላትና ያስወራንላት፣ ብዙ ምዕት ዓመታትን ያስቆጠረች፣ ብዙ ሊቃውንትን ያፈራች፣ ለአገር ትልቅ ባለውለታ የሆነች ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ይህ ማንነቷ እየተሸረሸረ መጥቶ፣ ሊቃውንቷ ዝም እንዲሉ የተደረገባት፣ እንናገራለን ካሉም “ተሐድሶ-መናፍቅ” የሚሰኙባት፣ ከዚህ የተነሳ የስሕተት ትምህርቶች ያለአንዳች ከልካይ እንዳሻቸው የሚናኙባት፣ በሃይማኖት ትምህርት ረገድም ቢሆን ሊቃውንቱ ሳይሆኑ ህዝባውያኑ የሚመሯት፣ በከፍተኛ ደረጃ የምግባር ልሽቀት የሚታይባት፣ ዘረኛነት፣ ሙስናና ብልሹ አስተዳደር የሰፈነባት፣ እግዚአብሔር የማይፈራባት ሰው የማይታፈርባት የጉቦና የዝርፊያ ቤት ሆናለች፡፡ በብዙ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ችግሮች የተተበተበች ሆና ስናያት ታዲያ መታደስ ብቻ ሳይሆን ከተቻለ ፈርሳ መሠራት ያለባት ቤተ ክርስቲያን መሆኗ አያጠራጥርም፡፡

አምና እውነተኞችንና እውነተኛ ትምህርታቸውን ፍትሐዊና መንፈሳዊ ባልሆነ መንገድ ያወገዘው ፍርደ ገምድሉ ሲኖዶስ፣ አሁን ደግሞ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መሪነት በሙስና ላይ ዘመቻ ሊከፍት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ሙስና የተባለው ወንጀል የተለያዩ ስሞች እየተሰጡትና በተለያዩ ስሞች እየተጠራ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የሕጋዊነት ያህል ቦታ ተሰጥቶት ሲሰራበት የኖረና አሁንም ድረስ ያለ በመሆኑ ዘመቻውን እንዲህ ቀላል አያደርገውም፡፡ መጠኑና የመጠየቂያው መንገድ ይለያይ እንጂ ሙስና አንዳንዶች እንደሚሉት በአቡነ ጳውሎስ ዘመን የተጀመረ አይደለም፡፡ ባይሆን ወደላቀ ደረጃ ከፍ ብሎ ሊሆን ይችላል፡፡
 
የቤተ ክርስቲያኗን ታሪክ ለመረመረ ሰው ሩቅ ሳይሄድ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስትም የነበረ መሆኑን ይረዳል፡፡ ልቦለድ ጽሑፍ የገሃዱ ዓለም ነጸብራቅ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ በ“ፍቅር እስከ መቃብር” ላይ ሐዲስ ዓለማየሁ የዚያን ዘመን የቤተክርስቲያን አገልጋይ ቅጥር እንዴት እንደሚከናነወን በዛብህ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ሥራ ያገኘበትን መንገድ በመጥቀስ አስቃኝተውናል፡፡ በዛብህን ከአለቃው ጋር በማገናኘት ጉቦ ያቀባበለውን ደብተራ መንበሩንም አንረሳውም፡፡ የሩፋኤል አለቃ ከግብር ሲወጡ በተገናኙ ጊዜ ደብተራ መንበሩ በዛብህን አስተዋውቆ አለቃው ጥቂት አነጋግረውት ደብተራ መንበሩን “ነገ እቤት ይዘኸው ና” ካሉት በኋላ ተሰነባብተው ሲለያዩ፣ ደብተራው በዛብህን “እንኩዋን ደስ ያለህ እንግዴህ ምንድነው የደስደስ የምትሰጠኝ?” ነበር ያለው፡፡ በዛብህ የተጠየቀውን አንድ መቶ ብር (በዚያን ጊዜ ትልቅ ገንዘብ ነው) አንድ ጀምብ ማርና አንድ ጀምብ ቅቤ ነጋድራስ ሁነኛው ሰጥተውለት እርሱም ከራሱ 20 ብር ሰጥቶ ተቀጠረ፡፡ የደስደሱ እንግዲህ ከዚህ ወጪ ጉቦ አቀባባዩ የሚቀበለው ግልገል ጉቦ መሆኑ ነው፡፡ ያኔ መሽዋሚያና የደስደስ እየተባለ ከተቀጣሪው ሰው ለቀጣሪውና ለአቀባባዩ የሚጠየቀው ጉቦ ዛሬ በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከቶች በጠራራ ፀሐይ ይህን ያህል ሺህ ትከፍላለህ ተብሎ ተመን ይጣልበታል፡፡ ከዚያ ለቀጣሪነት ሥልጣን ያላቸው እስከ ጉቦ አቀባባዩ ያን ብር ይከፋፈሉታል፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ይህ በገሃድ እየተሠራ በገሃድ የሚታወቅና በገሃድ የሚወራ ቢሆንም ቤተክህነቱም ሆነ ቤተ መንግስቱ ምንም እርምጃ ሲወስዱ አልታየም፡፡ ይህም ሁኔታ የልብ ልብ የሰጣቸው የሚመስሉት የአህጉረ ስብከቶቹ ባለሥልጣናት ጉቦን እንደቋሚ የገቢ ምንጭ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ በትምህርት ቤት ሲማር ደክሞ የመጣውን አገልጋይ እየበዘበዙበት፣ የመክፈል አቅም የሌለው ወይም ጉቦ ሰጥቼስ አልቀጠርም ያለውን እውነተኛ ምሁርና አገልጋይ ደግሞ እያጉላሉት፣ ጉቦ የሰጠውንና የቤተክህነት ትምህርት የሌለውን ሰው ግን በሚፈልግበት ቦታ የሚመድቡበትን የሙስና ስርአት ዘርግተዋል፡፡  በአንዳንድ ሁኔታ የአንዳንዶች አይን አውጣ አካሄድ ሲነቃባቸው ክስ ሳይመሰረትባቸውና ሳይጠየቁ ወደሌላ ክፍል መዛወራቸውም፣ ለሌላው ተረኛ “የፈለግሁትን ያህል ብዘርፍ ግፋ ቢል መዛወር ነው” በሚል የልብ ልብ እንደሚሰጠውና “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የሚለውን አጥፊ ተረት እየተረተ እርሱም የቻለውን ያህል አፍሶ ወደ ሌላ ክፍል እንደሚዛወር ምንም አያጠራጥርም፡፡ ይህ ግን የሚቀጥለው እስከ መቼ ይሆን?

ሙስናው በሀገረ ስብከት ደረጃ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በአድባራትና በገዳማት ደረጃም የሚሰራበት ነው፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ በደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ከአስተዳዳሪው እስከ ሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮቹ ድረስ የተፈጸመውንና እየተፈጸመ ያለውን ሙስናና የገንዘብ ብክነት እንመልከት፡፡ በቅድሚያ የደብሩ አስተዳዳሪ ቄስ ልሳነ ወርቅ ከቱሉ ዲምቱ ጊዮርጊስ 120 ሺህ ብር መንትፈው ከዚያ ቢባረሩና የተዘረፈው ደብር ወኪሎች ወንጀሉንውን ጠቅሰው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በማስፈቀድ የአለቃው ስም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በር ላይ ተለጥፎ ነበረ፡፡ ሀገረ ስብከቱ እንዲለጠፍ የፈቀደው ግን የሰውዬው ጥፋት አሳዝኖትና ለቤተክርስቲያን ተቆርቁሮ ሳይሆን ከዘረፋው የሚያገኘው ፈሰስ ስላነሰበት ነው፡፡ ቄስ ልሳነ ወርቅም መለጠፉን ሲያዩ ይጨምራሉ በሚል ስሌትም ነው፡፡ ስሌቱም ሰርቶ የተለጠፈብኝ ወረቀት የሚገነጠልልኝ ከሆነ እጨምራለሁ በማለታቸው ለሀገረ ስብከቱ ባለስልጣናት 80 ሺህ ብር ጉቦ ሰጥተው ወረቀቱን ለማስገንጠልና አሁን ወዳሉበትና አዲስ አበባ ሰሜን ገበያ ወደሚገኘው እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ለመዛወር ችለዋል ነው የተባለው፡፡

አስተዳዳሪው ቄስ ልሳነ ወርቅ ከደመወዛቸው ሌላ ከህንጻ አሰሪው ኮሚቴ ጋር ባላቸው ግንኙነት በየወሩ ለትራንስፖርት በሚል 5 ሺ ብር ይሰጣቸዋል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ የህንጻ አሰሪው ኮሚቴ እስካሁን ኦዲት ተደርጎ አያውቅም፡፡ ለዚህም ኮሚቴው ከአስተዳዳሪዎች ጋር ያለው ሙስናዊ ግንኙነት ኦዲት እንዳይደረግ ሽፋን እየሰጠው መሆኑ ይነገራል፡፡ ከዚህ ቀደም በበዓላት ለአገልጋዮች ቦነስ ይሰጥ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ግን ቦነስ እንዲሰጥ አስተዳዳሪውን ቢጠይቁም ከህንጻ አሰሪው ጋር ባላቸው ትስስርና እርሳቸው 5 ሺህ ብር ስለሚያገኙ አፋቸው ተይዞ ሌላው አገልጋይ እንዳያገኝ አስከልክለዋል ተብሏል፡፡ በዚህም ከደብሩ ካህናት ጋር ቅሬታ ውስጥ ገብተዋል ነው የተባለው፡፡ 

የደብሩ አለቃ ቄስ ልሳነ ወርቅና የማቅ ተላላኪ ከሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች ጋር በመሆንም ሌላ ሙስናዊ ተግባር መፈጸማቸው እየተነገረ ነው፡፡ ለዘንድሮው የትንሳኤ በዓል በሆስፒታል ለተኙ ሕሙማን መድኀኒት መግዣ ገንዘብ ይዋጣ ብለው በአውደምህረት ላይ ከህዝቡ 33 ሺህ ብር የሰበሰቡ ሲሆን፣ ዜናውም በሸገር ሬዲዮ እንዲነገር ተደርጓል፡፡ ዋናው የማቅ ተላላኪና የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሊቀመንበር ዮናስ መኮንን የተሰበሰበው 30 ሺህ ብር መሆኑን በመድረክ ላይ የተናገረ ሲሆን፣ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግን ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተኙት ህሙማን ስም የተሰበሰበው ገንዘብ በሙሉ እንዳልተሰጠና የተሰጠው 5 ሺህ ብር ብቻ ነው፡፡ ሮማን ለተባለች የማቅ አባል፣ የዮናስ ገርል ፍሬንድና የዩኒቨርስቲ ተማሪ አከፋፍዪ ተብላ 1000 ሺህ ብር ተሰጥቷታል ተብሏል፡፡ ለተባለው ክፍል መድረሱን ግን ብዙዎች ይጠራጠራሉ፡፡ ይህ ሁሉ ድርጊት እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና ከሕዝቡ በኩል የተሰበሰበውን ገንዘብ ድራሹን ባጠፉት ላይ ግፊቱ እያየለ ሲመጣ የሶስት ህሙማንን ፎቶ ለማሳየት እየሞከሩ ነው ተብሏል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ የተፈጠረው ቀውስ ከገንዘብ ብክነትና ዝርፊያ ጋር ተገናኝቷል፡፡ የአሁኖቹ አመራሮች ከቀድሞው ስራ አመራር እጅ የተረከቡት ገንዘብ፣ እንዲሁም ለጥምቀት ዱላና የሰሌን ኮፍያ ተሸጦ የተሰበሰበው ገንዘብ ተዘርፏል ነው የሚባለው፡፡ ስራ የሌለው የማቅ ተላላኪው ዮናስ መኮንን እየተጠቀመበት መሆኑን የሚያውቁ ከ50 በላይ የሚሆኑ የደብሩ ሰንበት ተማሪዎች ለደብሩ አስተዳደርና ለሀገረ ስብከቱ ተፈጸመ ያሉትን የገንዘብ ብክነት አሳውቀዋል፡፡  ሰሚ ያገኙ ይሆን?

ከቅጥር ጋር በተያያዘ እዚያው ደብር የተፈጸመ ሌላ በሙስና የተፈጸመውን የስራ እድገት እንስጥቀስ፡፡ በደብሩ ውስጥ በዲቁና የሚሠራና የሟቹ የአቡነ ይስሐቅ ተላላኪ የነበረ በግሉ መስቀልና ታቦት የሚቀርጽ ዲ/ን ማርቆስ የተባለውን ሰራተኛ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የደብሩ ምክትል ጸሀፊ አድርገው የደረጃ እድገት ሰጥተውታል፡፡ ይህ የተደረገውም ለአቡነ ዳንኤል ጽላት በመቅረጹ እንደሆነ ራሱ ሲናገር ከአንደበቱ የሰሙ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ አቡነ ዳንኤል ታቦት የተባለውን ቅርጽ እንደሌሎቹ ጳጳሳት ሁሉ ለራሳቸው ማምለኪያ ይሁን ቤተክርስቲያን ሊያስተክሉበት ለጊዜው ባይታወቅም፣ በቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ በቀራጺ ዲያቆን ማርቆስ የተጠረበው፣ ታቦት ተብሎ የተጠራውና የሚመለከው ዝርግ ሰሌዳ በዚህ መንገድ የሚመረትና ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑን እነ አቡነ ዳንኤልም እንኳ ገና አላስተዋሉም፡፡ ሕዝቡማ እንዴት አድርጎ ሊያስተውል ይችላል፡፡ 

ይህን ደብር ጠቀስን እንጂ በተለይ በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት በተመሳሳይ መንገድ ከፍተኛ የቤተክርስቲያን ገንዘብ በጥቂቶች እየተመዘበረና ጥቂቶች ከላይ እስከታች በጥቅም ተሳስረው አለአግባብ እየከበሩበት ይገኛል፡፡ የሚዘረፈው ገንዘብ ምንጭም የተለያየ ሲሆን፣
·        ከሕንጻ ኪራይ፣
·        ከሙዳየ ምጽዋት፣
·        ከስለት፣
·        በልዩ ልዩ ምክንያት መድረክ ላይ ከሚለመን፣
·        ያለ ደረሰኝ አየር ባየር የሚሰበሰብ፣
·        ያለ ገልጽ ጨረታ ከሚካሄድ የንብረት ሽያጭ የሚሰበሰብ፣
·        ለስራ ማስኬጃ እየተባለ የሚወጣ፣
·        ለልማት ስራ በሚል ለምሳሌ ለትምህርት ቤት፣ ለሕንጻ መሣሪያ ወዘተ፣
·        ለክብረ በዓል ድግስ የሚወጣ፣
·        ለቅጥርና ለዝውውር የሚከፈል ጉቦ (ይህ ደብር ላይ በተለይ በአስተዳዳሪዎች በኩል ሀገረ ስብከት ላይም የተለመደ ነው) ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እነዚህ የገንዘብ ዝርፊያ የሚካሄድባቸው የመዝረፊያ መንገዶች ናቸው፡፡

የግንቦቱ ሲኖዶስ ዋና መነጋገሪያ ይኸው የሙስና ጉዳይ መሆኑ ደግሞ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ፓትርያርክ አባ ማትያስ በሙስና ላይ ይዘው የቀረቡት ወቅታዊ አጀንዳ በመሆኑ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡ ይህም አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት በሙስና ተጠርጥረው ስለተያዙ ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሙስናው ጋር ተያይዞ ጩኸቱ እያየለ በመምጣቱም ጭምር ነው፡፡ የሙስናውን መረብ ለመበጣጠስ የሚደረገው ትግል ፈታኝ ቢሆንም ቁርጠኛ አቋም ሊያዝበትና የማያዳግም ውሳኔ ሊተላለፍበት ይገባል፡፡ እርምጃው በቀጣይ በሚፈጸሙ ሙስናዎች ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን ያለፉትንና ከሙስና ጋር ስማቸው ተያይዞ የሚነሣውን የቤተክህነት ባለሥልጣናት የደብር አስተዳዳሪዎችና የቀሩትንም በአምስቱ ከለባት ውስጥ የተፈረጁትን ሙሰኞችን ሁሉ ሊመለከት ይገባል፡፡

ምንም እንኳ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ተቋም እንደመሆኗ ተሐድሶው መጀመር ያለበት ከመንፈሳዊ ችግሮቿ ቢሆንም ከዚህ መጀመሩም ክፉ አይደለም፡፡ መሠረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ግን ቤተክርስቲያኗ እነዚህን ሙሰኞች ያፈራውን አስተምህሮዋን፣ ሥርአቷን፣ አምልኮዋን ሁሉ ልትፈትሽና መንፈሳዊ ተሐድሶ በማምጣት የአገልጋዮቿንና የምእመናኗን ደኅነንት ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ልታመጣ ይገባታል፡፡

14 comments:

 1. Now I clearly know who you are and what your aims are.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ok so what are you gonna do about? Are you plotting a terrorist attack or something? Who are you and what's your aim? To kill the last hope of this miskin church. So who's doing this church a favor!? I think the pick is fairly simple.

   Delete
 2. our church needs ONLY the administrative reformation NOT the religious reformation. religious reformation is strongly required for protestants who become BLIND by 'nufake'. they(you) carry bible, but know nothing about bible; they ( you ) seem to be christian, but no way you (they ) are, religious reformation is the order of the day for you and your colleagues.

  ReplyDelete
 3. ኀይማኖት አይታደስምJune 1, 2013 at 1:10 AM

  በማር፤የተለወሰ፤መርዝ...በክርስቶስ፤ደም፤ላይ፤የተመሰረተች፤ስለሆነች፤አትፈርስም፤፤ ልቦና ይስታቹህ

  ReplyDelete
 4. i taken from some blog..መናፍቅ ማለት ምን ማለት ነው?ቃሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባር ላይ የዋለስ መቼና በማን ነበር? በመሠረቱ አንድን ሰው በትምህርቱ ኑፋቄ ተገኝቶበታል ተብሎ ከቤተ-ክርስትያን ህብረትም ሆነ ከማኅበረ-ምእመናን የሚለየው ምን ዓይነት አስተምህሮ አምኖ (ተቀብሎ) የተገኘ እንደሆነ ነው? ይህም ሆኖ የማውገዝም ሆነ የመለየት ህጋዊ ሥልጣን ያለው ማን ነው?መናፍቅ ማለት “ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል።” መናፍቅ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ኢየሱስን የሚሰብክ ሳይሆን የሚያስክድ ነው!“ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው። ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።” (1ኛ ዮሐ. 2፥22,23) መናፍቅ ማለት ይህ ነው “መጻህፍትን ብትመረምሩ እነርሱም ስለ እኔ ይመሰክራሉ” ስለተባለለት ሰለርሱ የምሥራች የማይናገሩ ናቸው።

  ReplyDelete
 5. ....እንግዲህ “መናፍቅ” ተብሎ በታሪክ ስሙና ዝናው የጠፋ ታላቁ የጌታ ሐዋርያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስና ትምህርቱን ስንመለከት ደግሞ ይህን ይመስላል።
  የታሪኩ መነሻ የምናገኘው በሐዋ. ሥራ ምዕ. 24፥4-6 ሲሆን ሙሉ የቃሉ ይዘት ደግሞ ይህን ይመስላል። “ይህ ሰው በሽታ ሆኖ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ ሁከት ሲያስነሣ፥ የመናፍቃን የናዝራውያን ወገን መሪ ሆኖ አግኝተነዋልና፤ መቅደስንም ደግሞ ሊያረክስ ሲሞክር ያዝነው፥ እንደ ሕጋችንም እንፈርድበት ዘንድ ወደድን።” እንዲል በዚህ ቃል መሰረት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በአይሁዳውያን ከቀረቡለት 3ት ዓበይት ክሶች አንዱ ኃይማኖታዊ ይዞታ ያለው ክስ ነው ይኸውም “የመናፍቃን የናዝራውያን ወገን መሪ ሆኖ አግኝተነዋልና” ሲሉ። መናፍቅ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ይዘው ክስ የመሰረቱ አይሁዳውያን ሲሆኑ ይህን ስም ተሎጥፎበት በንጉሡ ፊት የቀረበ ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነበር።
  እውነት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “መናፍቅ” ነው ወይ? ከተባለስ ምንፍቅናው በማን ላይ ነበር በሰዎች (በድርጅት) ላይ? ወይስ በእግዚአብሔር ላይ ነበር? በሰዎች ዘንድ መናፍቅ ተብሎ መሰደቡ ትርጉም ባይሰጠው ነው እንጂ እንዲህም ባላለ ነበር “ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ” ሲል የማያመቻምች መልስ የሰጠ።
  “መናፍቅ” የተባለው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ማለት ከልጅነት ዕድሜው ጅምሮ በአይሁዱ የመጻህፍት ምሁር (አዋቂ) በገማልያ እግር ሥር ቁጭ ብሎ ብሉያትን የተማረ፣ የሙሴን ህግ ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ መጻህፍትን በሰባት አቅጣጫ አንብቦ የሚተረጉም ብልህ ጭምትና አዋቂ፣ በተአምራታዊ መንገድ የጌታ ሐዋርያ የሆነ ሰው ነበር “መናፍቅ” የተባለ። ጥያቄው ይህ ሰው “መናፍቅ” ከተባለ እውነተኛ አማኝ ማን ሊሆን ነው? “ነፍስ እውቀት የሌላት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም” ያለ ራሱ እግዚአብሔር ነውና ደንቆሮው ሊሆን አይችልም። ታድያ ማን ነው? እርስዎስ አፍ አውጥተው መናፍቅ የሚሉት ማንን ነው? በእምነቱና በእውቀቱ ብልጫ ያለው ወይስ … ?
  ኑፋቄና የቤተ-ክርስትያን ታሪክ፦ በቤተ-ክርስትያን ታሪክ ሰፊና የጎላ ታሪክ ካላቸው ክስተቶች መካከል አንዱ ነው በተላያዩ ዘመናት የተለያዩ ሰዎች በተለይ በክርስቶስ ኢየሱስ ፍጹም አምላክነትና ክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ያለውን ግኑኝነት በተመለከተ ቤተ-ክርስትያን ብዙ ሰጣ ገባ አሳልፋለች እነሆም ይህ ሁሉ ፈታኝ ታሪክ ተሻግራ ዛሬ ደረሰች እስከ ክርስቶስ መምጣትም ጸንታ ትኖራለች።
  በቤተ-ክርስትያን መካከል ከተፈጠሩ የስህተት ትምህርቶች አንዱን ስንመለከት በ325 ዓ.ም የተነሳ አንድ በእስክንድርያ ቤተ-ክርስትያን ይገኝ የነበረ አርዮስ የተባለ ሰው ቀዳሚ ሰው ሆኖ እናገኘዋለን ትምህርቱም “ወልድ ፍጡር ነው” የሚል መነሻ ኃሳብ ኑሮት በአጠቃላይ ትምህርተ ሥላሴን የሚቃወም ሰው ነበር። አርዮስ ቀደም ብሎ ይህን ትምህርት አንግቦ ስቶ ስያስት ከስህተት ትምህርቱ አንዲመለስ በተደጋጋሚ የተመከረ ቢሆንም “እምነቴ ነው!” በማለት አሻፈረኝ ብለዋል የቤተ-ክርስትያን አባቶችና ሊቃውንት በተገኙበት በ325 ዓ.ም በኒቅያ በተሰየመ ጉባኤም ይህንኑ እምነት ይዞ ነበር የቀረበው አሁንም ቢሆን ከዚህ የስህተት ትምህርት እንዲመለስ ለቀረበለት ጥያቄ እንቢ በማለቱ ከቤተ-ክርስትያን ህብረት እንዲወገዝ ተደረገ።
  ሌሎችም በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ ጉባአያትም ተመሳሳይ ታሪክ ነው ያላቸው። በ381 ዓ.ም በቁስጥንጥንያ የተካሄደው ጉባኤም ክህደቱ የሥላሴን ህልውና ማዕከል ያደረገ የመንፈስ ቅዱስ ፍጹም ገጽና ፍጹም አምላክነት የሚቃወም ነበር ይህንን ትምህርት በቤተ-ክርስትያን ተወገዘ።

  ReplyDelete
 6. .... ቤተ-ክርስትያን የዛሬን አይድርገውና ከጥንት
  ጀምራ በመኸከልዋ ለሚፈጠረው የአስተምህሮ ችግር ስትፈታ እንዲሁ በዋዛ ፈዛዛም አልነበረም። ኑፋቄ አለበት የስህተት ትምህርት ተገኝቶበታል የሚባል ሰው የተገኘም እንደሆነ በሚመለከታቸው አካላት ተጠይቆ የተባለውን ሁሉ ነኝ ብሎ ቢገኝ እንኳ ትመክራለች ትገስጻለች እንጂ ለመፍረድ አትቾኩልም እንዲህ ዓይነት ውሳኔ የወሰደችበትም በታሪክ አናገኝም። በምክርዋና በተግሳጽዋ አልመለስ ብሎ ራሱን የገለጠ እንደ ሆነ ግን ለተቀሩት ንጹሐን ተከታዮችዋ ደህንነት ስትል ይህን ታደርጋለች።
  ኑፋቄና የዘመናችን ቤተ-ክርስትያን፦ ቤተ-ክርስትያን ያው ቤተ-ክርስትያን ናት በደሙ የመሰረታት ጌታ “ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።” (ዕብ. 13፥8) ተብሎ ተጽፎአልና። የቤተ-ክርስትያን ባለቤት ስህተት የማያውቀ ፍጹም አምላክ ከመሆኑ የተነሳ ቤተ-ክርስትያን በራስዋ ትናንት ችግር እንዳልፈጠረች ሁሉ ዛሬም ለወደፊቱም ችግር አትፈጥርም። በቤተ-ክርስትያን ባለቤትና በደሙ በዋጀው ህዝብ ፊት የሚቆሙ ባለአደሮች ድክመትና አደራን በአግባቡ አለመወጣት የተነሣ ግን ችግር እንዲፈጠር ቀዳሚ ሚና ይጫወታል።
  አፈር በዱቄት ይስቃል ሆነና ነገሩ ጣታቸው ሳይማሩ በተማሩ ላይ፣ ዓይናቸው ሳይጠሩ በተጠሩ ላይ፣ ሁለ መናቸው ሳይቀቡ በተቀቡ ላይ ተነስተው ሳይወገዙ አውጋዞች የሆኑ ሸማቂዎች ይህን ዓይነቱ ክፍት የሥራ ዕድል አግኝተው እንጀራቸው መጋገር ከጀመሩ ዓመታት አስቆጥረዋል።

  ReplyDelete
 7.  መናፍቅ ያልተገራ ልብ ይዞ በለዘበ ምላሱ የሚታወቅ ገዳይ ነው።
   መናፍቃን በፍርድ መንፈስ ተሞልተው የምህረት በር የሚዘጉ አረመኔዎች ናቸው።
   መናፍቃን እግዚአብሔር ልብን እንደሚመዝን ዘንግተው በሰው ፊት የሚትጉ አስመሳዮች ናቸው።
   መናፍቃን በመንፈሳዊነት ሥም ሥጋዊ ኃሳባቸው የሚፈጽሙ ሸማቂዎች ናቸው።
   መናፍቃን ሰማያዊ እውቀት የሚያሳድዱ ደንቆሮዎች ናቸው።
   መናፍቅ ማለት የራሱ የሆነ ነገር የሌለው በተውሶ በትር የሚክለፈለፍ ኮብላይ ነው። ersu manew!

  ReplyDelete
 8. ኧረ ጉድ ነው ኧረ አይጣል ነው የማይሰማ የለም ሥጋዊውም ጉቦኛ መንሳዊ ተብዮውም ጉቦኛ፤ ካህኑ እንደሕዝቡ
  ሕዝቡ እንደካህኑ ከሆነ የፈጣሪ የሥራ ድርሻ ከምን ላይ ነው? በትንቢተ ሕዝቅኤል 9. 6-7 ላይ የተጻፈው
  የሥራው ድርሻ መሆኑ ግልጽ ነው አስቅድሞ በዋናው ቤተ መቅደስ ቀጥሎም በቅርንጫፎቹ ተግብሮታል አሁንም
  ይዋል ይደር ይሰንብት እንጂ ባንድ ወይም በሌላ መንገድ መተግበሩ አይቀሬ ነው፡፤ ስንኳንስ መንፈሳውያኑ ጉበኞች ሥጋውያኑ ጉበኞችም አይቀርላቸውም። አንተሳ ይቀርልሃል? የሚል ሐሳብ ይነሣል አዎን ተገቢ ነው
  መልሱ (በጉቦና በነገር አካሄድ የሚሠቃዩትን ወገኖች ባላግዛቸውና አይዟችሁ ክፉ ቀን ያልፋል ደግ ዘመን ይመጣል ባልላቸው ዕንኳ እንዳስጨናቂዎቹ ባለማስጨነቄ እንደሚሠውረኝ አምንዋለሁ፡፤ አባ ሰላማዎች ግን
  ዕውነትን በእውነት ስለምትጽፉ ቀኙ(እድ የማናይ) ከናተ ጋር ይሁን።

  ReplyDelete
 9. ይገርማል! መናፍቃኖቹ መናፍቃን አጋንንቶቹ አጋንንት እያሉ ሰዎችን ለመንቀፍ ይሞክራሉ አዬ ጉድ የራሷን አበሳ በሰው አብሳ ወይም ግልብ ቀደማ ይላሉ ሽማግሎች ለመሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስና ፈሪሳውያኑ(ቅዱሳኑ)
  ምን ተባባሉ?አብርሃም ሳይወልድ(ሳይፈጠር) ነበርሁ ቢላቸው አሁን ጋጌን እዳለብህ አወቅን ብለውታል
  ነቅፈውታል፤ እና ራሳቸው መናፍቃኑ(አጋንንቱ)ሌሎችን አጋንንት መናፍቃን ቢሉ የራሳቸውን የውስጣቸውን
  ጋኔናዊ ጠባይ ከመግለጽና ትዝብት ከማትረፍ በስተቀር ትርፍ የላቸውም ከዜሮ(ባዶ)በታች ናቸው
  ልብ ቢገዙ መልካም ይሆናል።

  ReplyDelete
 10. This blog has opened the door for genuine discussion on some mind bogling issues we all have related to ETOC. sadly some blindly go wild on ranting to prevent any discussion, but thanks to this blog for bring it on. It is enlightning as it cast light on the truth.

  ReplyDelete
 11. As far as I am concerned the teaching of the Tehadso is a carbon copy of the protestant one. So people, if you think the EOTC is full of teret teret now, then please just leave the church alone and go to the protestant camp. Those of us who are okay with the EOTC will stick to it. So atibetbitu! If you think the EOTC is now in the wrong path interms of its doctrines just leave the church and organize yourself on your own or join your protestant roots. Other than that, please let us be!

  ReplyDelete
 12. We have heard from Dereje Tekle who wrote 460 KENAT BEMENBERE PATREYAREK how the church men grabbing the church wealth. One day they will pay it back.

  ReplyDelete
 13. PLEASE ETHIOPIAN ORTHODOX DONOT WAST YOUR TIME FOLLOW THE BIBLE AND READ IT. ETHIOPIAN ORTODOX BENN LOST FOR SO MANY YEARS WITH OUT THE BIBLE. NOW IS TIME TO READ BECAUSE OUR CHILDEREN CAN READ NOW WE ARE NOT GOING TO BE LOST AGAIN THANK GOD.DO NOT BLAME THE PROTESTANT BECAUSE THEY READ THE BIBLE UNLIKE YOU.GOD HAVE MERCY ON ETHIOPIAN ORTHODOX FOLLOWERS.

  ReplyDelete