Friday, May 17, 2013

የማቅ ታማኝ አገልጋይ አባ ኅሩይ ወንድ ይፍራው ከሥራ አስኪያጅነታቸው ታገዱ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለ4 ከተከፈለ በኋላ የምዕራብ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት አባ ሕሩይ ወንድይፍራው ከስራ አስኪያጅነታቸው መታገዳቸውን የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ለመነኩሴው በጻፈው የእግድ ደብዳቤ አስታወቀ፡፡ በደብዳቤው እንደ ተገለጸው ለአባ ሕሩይ መታገድ ምክንያቶቹ የተመደበቡበትን የሥራ ሃላፊነት በአግባቡ አለመወጣትና ከሊቀ ጳጳሱ መመሪያ ሳይቀበሉና ትእዛዝ ሳይሰጥ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር የተጋለጡ የሰራተኛ ቅጥር፣ የደመወዝ ጭማሪና የሰራተኛ ዝውውር ማድረግን እንደሚመለከት ለማወቅ ተችሏል፡፡ እነዚህን ህገወጥና ከፍተኛ ጉቦ የሚበላባቸውን ተግባራት ሲፈጽሙ መቆየታቸው ስለተደረሰበት ከስህተታቸው እንዲታረሙ በየደረጃው ከቃል እስከ ጽሑፍ ምክርና ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም አባ ሕሩይ ማስጠንቀቂያውን ከቁብ ሳይቆጥሩ በተበላሸ አሰራራቸው በመቀጠላቸው ምክንያት የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁእ አቡነ ሕዝቅኤል ከሥራ አስኪያጅነት እንዳገዷቸው ደብዳቤው ያመለክታል፡፡


ብፁዕነታቸው ብዙ እሮሮ እየተሰማበት ያለውን የምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ብልሹ አሠራር ለማስተካከል እየወሰዱ ያለው እርምጃ የሚበረታታ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የአባ ህሩይ ጸሀፊ ሆኖ በተመሳሳይ ሙስናዊ አሰራር ተሰማርቶ የነበረውንና አለሞያው “መጋቤ ሥርአት” የሚል ሹመት የተሰጠውን ጨዋውን አቶ ደስታን ማገዳቸው የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በብልሹ አሰራር የተገኙ እንደ አቶ ደስታና አባ ህሩይ ያሉትን ተጠርጣሪዎች ከአንዱ ክፍል ወደሌላው ክፍል ከማዛወር የዘለለ እርምጃ ባለመወሰዱ ቤተክርስቲያን ለከፍተኛ የሀብት ምዝበራ ተጋልጣለች፡፡ ስለዚህ ከሃላፊነት ማንሳት ብቻም ሳይሆን በሕግ የሚጠየቁበትን አሰራር ዘርግቶ ቤተክርስቲያንን ከሙስናና ከዝርፊያ መታደግ ይገባል፡፡ መንግስትና የሚመለከታቸው እንደ ፀረ ሙስና ኮምሽን ያሉ አካላትም የቤተክርስቲያንን ሀብትና ንብረት ከዝርፊያ ለመታደግ መንቀሳቀስ ያለባቸው ሰአት አሁን ነው እንላለን፡፡ አሊያ የጠገበውን ሹመኛ አንስቶ የተራበውን መተካቱ በየተራ ዝረፉ ከማለት የተለየ አይደለምና፣ በአባ ህሩይ ላይ ክስ ሊመሰረትና በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል፡፡

አባ ሕሩይ ወንድይፍራው ከአሜሪካ የዓመታት ቆይታ በኋላ ለቤተክርስቲያን ሊጠቅሙ ይችላሉ ተብለው በአባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ምትክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ ሆነው ተሾመው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በተሾሙ በወሩ ማኅበረ ቅዱሳንን አደብ ማስገዛት ሲገባቸው ይባስ ብለው ማኅበሩ በቤተክርስቲያን ስም የተያያዘውን መጠነ ሰፊ ንግድ ለማጠናከር የቲን ቁጥር እንዲሰጣቸው ደብዳቤ መምራታቸውና ሌሎችም ከማኅበሩ ጋር ያላቸው የጥቅም ትስስር ስለተደረሰበት ጉዳዩ ያሰጋቸው የቀድሞው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከመምሪያው አንስተዋቸው እንደ ነበር ይታወሳል፡፡ በአቡነ ገሪማ በኩልም ንብረት እንዲያስረክቡ ሲጠየቁም ሌላ ያልጨረሱትና ለማኅበሩ የሚጠቅም ደብዳቤ በማኅተሙ ያወጡ ይመስል ማኅተም ይዘው ተሰውረው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

አባ ሠረቀ ብርሃን ማቅን በተገቢው መንገድ ተንቀሳቀስ በሚል ወደ ሕጋዊ መንገድ ለማስገባት ጥረት ያደርጉ በነበረ ጊዜ ማቅ ከላይ መመታቴ አይቀርም ስለዚህ ስልት መለወጥ አለብኝ ብሎ በአዲስ አበባ የሚገኙ ወደ 150 የሚጠጉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉትን ጀሌዎቹን በማሰባሰብና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አስተባባሪ ኮሚቴ በአየር ላይ እንዲመሰርቱ በማድረግ ስማቸውን ተጠቅሞ ጊዜ ለመግዛት ሲንቀሳቀስና ሁከት ሲፈጥር መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ራሱ ያዘጋጀውንና ለኢትዮጵያ ባለውለታ የሆኑ ታላላቅ ሊቃወንትን አውግዙልኝ ብሎ በሁለተኛው የክስ ፋይል ስማቸውን ለሲኖዶስ አቅርቦ ወደ ሊቃወንት ጉባኤ የተመራውንና እዚያው ሰጥሞ የቀረውን ክስ በስማቸው ያስገቡትና ለጥያቄ እንኳ ብቅ ያላሉት እነዚሁ የማቅ ተላላኪዎች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ለብዙ ወጣቶች ከቤተክርስቲያን መበተንና ወሮበሎችን የሰንበት ተማሪ አስመስሎ በማስረግ ከዚህ ቀደም ቤተክርስቲያን ውስጥ የተነሡ ሁከቶችን የመሩት እነዚሁ በዚህ ኮሚቴ ውስጥ የታቀፉት የማቅ አባላት ናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ በተለይ ሄኖክ አስራት፣ ሰለሞን አስፋው፣ ዋሲሁን ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በግንባር ቀደምትነት በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙት መካከል የግቢ ገብርኤል ሰንበት ተማሪ የሆነው ሄኖክ አስራት በፓትርያርክ ምርጫ የማቅ አባል ሆኖ ሳለ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን እንዲወክል ተደርጎ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ አባ ህሩይ ከሄኖክ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸውና ብዙ ጊዜም የማይለያዩ መሆናቸው ሲታወቅ ፍቅራቸውን ያጸናውም የማቅን ጉዳይ ለማስፈጸም የተሰለፉበት የጋራ አላማ እንደሆነ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ለዚህ አንድ ማሳያ ብለው የሚያቀርቡት የአራቱም አህጉረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያዎች የራሳቸው ቢሮ ሳይኖራቸው ለአቶ ሄኖክ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሕንጻ ውስጥ አንድ ክፍል ቢሮ መሰጠቱ እስካሁን አነጋጋሪ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ሄኖክ ማታ ማታ ከማቅ ሰዎች ጋር የሚዶልትበትን ቢሮ እንደያዘ እንዲዘልቅ ያደረጉትም አባ ህሩይ እንደሆኑ ይነገራል፡፡

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በወሰዱት እርምጃ ደስ ያልተሰኘችው ሀራ ዘተዋህዶ ብሎግ የከረመና ከእውነት የራቀ ሐሰተኛ ዘገባ አባ ገብረ መድኅን በተባሉ የአሲራ መቲራ ገዳም አበምኔት ላይ በማውጣት ብፁዕነታቸውን “ከምስጉን አቋማቸው የመንሸራተት ስጋት” ይታይባቸዋል ሲል ወርፏቸዋል፡፡ ይህም በማቅ ጥቅም ላይ ያነጣጠረ ውሳኔ ከማሳለፋቸው ጋር እንደሚያያዝ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ በአባ ሕሩይ ላይ ውሳኔ ማሳለፋቸውን ተከትሎም የአሲራ መቲራ ገዳም አበምኔት አባ ገብረመድኅን ማቅ በገዳማት ስም እየነገደ ያለውንና ተቆጣጣሪ የሌለበትን ንግድ ለማስቆም ከሚያስተዳድሩት የደቂቀ እስጢፋኖስ ገዳም በመጀመር እየታገሉ ያሉ በመሆናቸው መነኩሴውን በልዩ ልዩ መንገድ ስማቸውን ሲያጠፋ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ መነኩሴው በማቅ ዋና የገቢ ምንጭ በገዳማት እንቅስቃሴ ላይ በመቆማቸውም ሰሞኑን ማቅ በሀራ ዘተዋህዶ ብሎጉ ላይ ባለ በሌለ ሀይሉ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቶባቸዋል፡፡   
2 comments:

  1. mk egziabher yitalachu...mak albeso yawardachu....I hate mk from the bottom of my heart..wenbedewoch...woshetamoch...menfes kidus yerakachu...

    ReplyDelete