Monday, May 20, 2013

“ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” የተሰኘ አዲስ ብሎግ ሥራ ጀመረ

ተሐድሶ ከእግዚአብሔር መንገድ የወጡ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መንገድ የሚመለሱበት የንስሐ መንገድ ነው፡፡ ተሐድሶ የእግዚአብሔር ሐሳብ ቢሆንም ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር ሕግ ከመመራት ይልቅ በራሳቸው ፈቃድ መመራትና መኖር የሚፈልጉ ሰዎች የተሐድሶን ግብር ሲቃወሙ ኖረዋል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ግብሩን ብቻ ሳይሆን ስሙንም ጭምር እየጠሉና እያስጠሉ፣ ቀንድና ጭራም እያበቀሉለት እየተቃወሙት ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በመነሣት ተሐድሶ የሚለው ስም በአሉታዊና በአፍራሽ መልኩ እንዲታሰብ፣ አዲስ ሃይማኖት ተደርጎም እንዲቆጠር ለማድረግ እየጣሩና ተሐድሶ የእግዚአብሔር ክቡር ሐሳብ መሆኑን ያልተረዱ ወገኖችን እያሳሳቱ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

የእግዚአብሔር ሐሳብ የሆነውን የቤተ ክርስቲያንን ተሐድሶ እውን ለማድረግ ተሐድሶን በትክክለኛ ገጽታው ማቅረብ ጊዜው የሚጠይቀው ዓቢይ ተግባር በመሆኑ የብሎጉ መከፈት ተሐድሶን በተሳሳተ መንገድ እያቀረቡ ያሉ ክፍሎችን የተዛባ አመለካከት ሚዛን እንደሚያስጠብቅና የቤተክርስቲያንን መታደስ ለማፋጠን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ብሎጉን ለመጎብኘት የሚከተለውን አድራሻ ይጫኑ http://www.tehadeso.com

18 comments:

 1. Cheap Burberry Handbags These furnishings certainly are a
  good choice. People of each class and level can easily
  get these because their price is of every range.
  What most are finding are imitation, fake UGG Boots.


  Feel free to visit my site - www.jouhingucchihandbags.com

  ReplyDelete
 2. 'ezam bet esatu yinedal' if you open one menafkan blog, we can open more than that to still blacken the deeds of 'tehadiso menafkan'

  ReplyDelete

 3. Temesgen, Ellllllllllll!!!!!!!!

  ReplyDelete
 4. God is great.Thank you God we able to see real God's work. I pray for this thing to happen. Now hear it is the truth come out.No matter what God stand with the truth.God bless whoever posted this article.

  ReplyDelete
 5. I thank you God the truth of Gospel will preach in ethiopia from now on.So far cltur was blind our eyes but now the truth Gospel of Jesus Christ will open our eyes. It is a choice if any body will stay blind it is up to the person but the truth is alwyes the truth.God almighty bless the whole world.

  ReplyDelete
 6. "genzeb be memeget betefetere neger yerebubachuhal"2petros 2:3 wulude aganint hula men betebezu enante ga kalut egaga yalut yebeltalu derom ke abatachu ke deabilos nachu BETE KRESTIYAN ATETADESEM !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!1

  ReplyDelete
 7. Geta Yerdachehu

  ReplyDelete
 8. yegna betekrstian hulem adis nech menafkan hulu yaw betezewawary protestant nachu ye sinde wust enkrdad endenante aynetu new

  ReplyDelete
 9. ብዙ ጊዜ ዝጎ የኖረ እቃ ብዙ ውልወላ ያስፈልገዋልና አዳሾቹ ታዳሾችን ለማደስ ጊዜ ይወስዳልና በትግዕሥት
  እንደ ጀመራችሁ በትግሥት ትፈጽሙት ዘንድ አደራ ትባላላችሁ።

  ReplyDelete
 10. No no way እናንተን ማን በተክርስቲያን አዳሽ አደረጋቹ ለራሳቹ ጥቅም የምትሮጭ ሁላ ያልተነቃብሽ መስሎሻል.... በሀይማኖት ሽፋን ገንዘብ መሰብስብ እና ሰውን የመለያየት ስራ !!! አረ በቃን ተቃጠልን እስኪ ተውን አንፈልግም !

  ReplyDelete
 11. እናንተን ማን በተክርስቲያን አዳሽ አደረጋቹ ለራሳቹ ጥቅም የምትሮጭ ሁላ ያልተነቃብሽ መስሎሻል.... በሀይማኖት ሽፋን ገንዘብ መሰብስብ እና ሰውን የመለያየት ስራ አረ በቃን ተቃጠልን እስኪ ተውን አንፈልግም

  ReplyDelete
 12. ኧረ ተው አይሆንም ቢቻል ለቤት እድሳቱ መትጋት ባይቻል ዝም እንጂ ተቃጠልን አይባልም
  ከበረታ ደግሞ ቀዝቃዛ መጠጣትና በዕውነተኛው የሕይወት ውሀ መጠመቅ ይገባል።

  ReplyDelete
 13. tehadeso, ye egziabhare hig aytadesem sew yeseraw aydelem new bate krstian gnbatawn new yemtadsut . degmo egna orthodoxian aydenkenem mekneyatum aryosem ab natim lalochem menafekan yewetut weyem yteferut kegnaw kerasachen selehone aydenkenem tomun eyeferu zemedoche aleku gen yehe yehymanot gebru aydelem seyef tor mekuakuam chemer new

  ReplyDelete
 14. እኛ ደግሞ ያለንበት ዘመን ጥሩ ነው፡፡ በሐይማኖት የተነሳ የሚደርስብን ተጽኦኖ እንደሐዋርያትና እንደቅዱሳን አባቶቻችን ያህል ድካምና መከራ ብዙ የለብንም፡፡ ይህችን ጊዜ በአንድ መንፈስ በአንድ ልብ፣ በፍቅር፣ በመተሳሰብና በመማማር ከአባቶቻችን በመማር እንነሳ፡፡
  ሐይማኖት አይታደሰም፤ ምክንያቱም ሐይማኖት የተገለጠች፣ የተቀበልነው፣ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጠች ፣ የምንጠብቃት፣አንዲት ናት እውነትም አንድ ነው፣ የሚታዘዙላት እንጂ የማናዛት፣የሚታደሱባት እንጂ የማትታደስ እንደሆነች ነው መጽሐፍ ቅዱስ የነገረን ዩሐ 1፣18 1ኛ ጢሞ 6፣16 3ኛ መቃ 9፣26 መዝ 17፣ 9-11 ዘፀ 3፣17 ዘሌ 9፣23 እብ 8፣5 እብ፣9፣5 ይሁዳ 1፣3 የሐ.ወ.17፣18፤ የእግዚአብሔር ቃል አይታደሰም፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱን ደግሞ እንድሳለን ብሎ መነሳት ደግሞ የክህደት ክህደት ነው፡፡ የቃሉ እናቱም አባቱም የነገሩን እርሱን ስሙት እንጂ እርሱን ያሚላችሁን አድሱት አልተባልንም፡፡ እያደሳችሁ ተጠቀሙ አልተባልንም፡፡ ጌታም አንድ ነው፣ ጥምቀትም አንድ ነው፣ ሐይማኖት አንዲት ናት፤ ስለዚህ መታደስ ሲያቅታችሁ በራሳችሁ ተነስታችሁ እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ የሰጠውን ሐይማኖት እናድሳለን ማለት ልክ እግዚአብሔር እናግኘው ብለው እንደተነሱት ባቢሎያውን መሆን ነው፡፡ የዚህ ደግሞ ውጤቱ ግልጽ ነው፡፡ የእናንተን አመለካከት ይዘው የተነሱትን እነማርቲ ሉተርን እንመልከት ለጊዜው ለአውሮኘያውኑ የስጋ አመለካከትና የእደገትና የአስተሳሰብ ለውጥ አምጥቷል ለዛሬው ያሉበት ደረጃ ትልቁን አስተዋጽኦ ማድረጉን ግልጽ ቢሆንም ነገር ግን ትውልዱ ስንመለከት ከመንፈሳዊ በረከት የወጡና እግዚአብሔር የለሽ ትውልድ ነው ያተረፉት፡፡ ይህ የሚያሳየው የተነሱበት አመለካከት የእግዚአብሔርን ቃል ሰው በራሱ መተርጎም ይችላል በማለት የተነሳበት አመለካከት ትልቁ የትውልዱ የውድቀት መሰረት ነው፡፡ 1ኛ ጴጥ 1፣21 ያለውን ቃል በመጣስ ነው ይህንን ያደረጉት፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ማንም ሰው ከራሱ አስተሳሰብ ተነስቶ ሊሆን ይችላል፣እንደዚህ ይመሰለኛል፣ እየተባለ የሚመራ ሐይማኖት ከእግዚአብሔር ዘንድ አልተሰጠንም እና እባካችሁ ሐይማኖትን ለማደስ ከመነሳት እራሳችን ታድሰን በውስጣችን የተቀበረችውን አንዲቷን ሐይማኖት በቃሉ ሕይወት ዘርተን ትንሳኤዋን እናውጅ፡፡ መለያየት የትም አያደርስም፡፡ ሐዋርያት በአንድ ልብ ሆነው በፍቅርና በመተሳሰብ ስለተነሱ ነው ክርስትና ብዙ ፈተና አልፋ እኛ ጋር የደረሰችው፡፡

  ReplyDelete
 15. ሀገራችንን ትልቅ ለማድረግ የሚረዳን ትልቁ ስራ መሆን ያለበት በመንፈሳዊ በረከት ውስጥ የሚያልፍ ትውልድ ማፍራት ስንችል ነው፡፡ ከበፊቱ ትውልድ የምንማረው ይህንኑ ነው፡፡ ሀገራችንን እየቀበራት የመጣው ከመንፈሳዊ በረከት የወጡ ትውልዶች እየበዙ ስለመጡ ነው፡፡ እኛ ደግሞ አዲስ ለወጥ ለመፍጠር መነሳት ካለብን በዚህኛው አካሄድ ሳይሆን መሰረታችንን ይዘን ነው፡፡ አውሮፓውያኑ እንደዚህ አይነት ትውልድ እንዲፈጠር ያደረጋቸው መሰረታቸው ጣኦት የሚያመልኩ፣ ከዚያም ደግሞ የተነሱበት መንፈሳዊ በረከት ደግሞ ልክ እንደዚህ ዓይነት ስለሆነ ምንም እንኳን ለስጋ የሚታይ ነገር ጥሩ ቢሆንም ውስጣቸው ግን ግልጽና የሚታይ ነው፡፡ እኛ ደግሞ እንደዚህ አይነት ትውልድ ማፍራት የለብንም፡፡ የሚሰራ፣ ሀገሩንና ሐይማኖት በአንድ የሚያስብ፣ የሚከባበር ትውልድ ማፍራት እንድንችል የአባቶቻችን አካሄድ እንረዳ፡፡ የእነርሱን መንፈሳዊ ጉዞ፣ ተረት ነው፣ እንደዚህ ነው እያሉ መሳደብ፣ ማዋረድ፣ የእውቀት ሁሉ መጀመሪያ አናድረገው፡፡ የእውቀት መጀመሪያ እግዚአብሔር መፍራት ነው መሆን ያለበት፡፡ አህዛብ፣ ምናምን የተስማሙበት መጽሐፍ እያልን አካሄዳችን ሁሉ በጨለማ አናድርገው፡፡ ሰው የሚያይልን አምላክ ማምለክ እናቁም፡፡ አባቶቻችን ያዩትን አምላክ ማየት የምንችለው እንደዚህ ባለው አካሄድ አይደለም፡፡ እነርሱ በአባቶቻቸው እግር ስር ተቀምጠው የእውቀታቸው መጀመሪያ እግዚአብሔርን በማድረጋቸው ነው፡፡ ገድሎቻቸ ሲነበብ ተአምር እየሰራ የምናየው፡፡ ለእናንተም ተረት የሆነባችሁ፡፡ ተረት ሆኖ ግን አይደለም እውነት ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ እውነት መሆኑን እኮ ለማረጋገጥ እነርሱ የሄዱበትን መንገድ እንሂድና እንመልከተው፡፡ በቃ፡፡ ወንጌል ተጨባጭ ናት፡፡ የወደቁትን አንመልከት የተነሱትን ነው መመልክት፡፡ ይሁዳን ትተን ቅዱስ ጴጥሮስን እንመልከት፡፡ ዴማስን ትተን አጰሎስን እንመልከት፤ የጌሮስየን ሰፈር ትተን የእነ ማርታ ሰፈርን እንመስርት፤ ካራንን ትተን ከነአን እንግባ፡፡ የጥንቷን ኢትየጰያንንና ተዋህዶን በአንድ ተመልክተን ቤታችንን እንስራና አዲሲቷን ኢየሩሳሌምን እንመልከት፡፡ ማስተዋል ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 16. ለትንሳኤያችን የሚሰራ ትውልድ እግዚአብሔር እንዲፈጥርልን ተግተን እንጸልይ፡፡ እንደአባቶቻችን ለእግዚአብሔር የሚያገለግሉ ትውልድ ያስነሳልን፡፡ ትንሳኤ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይሁን፡፡ ተዋህዶ ለዘለዓለም ትኖር፡፡ ተሀዶሶን፣ ኘሮቴስታንቱን፣ አህዛቡን፣በአጠቃላይ መናፍቁን ቢፈቅድ ማስተዋል አለበለዚያ ደግሞ ያስታግስልን፡፡ አሜን፣ አሜን፣አሜን

  ReplyDelete
  Replies
  1. Sasbais, ቃለ ህይወት ያሰማልን ተዋህዶ ሀይማኖታችንን ይጠብቅልን: ክተዋህዶ በረት የወጡትን አይነ ልቦናቸውን አብርቶ ማስተዋልን አድሎ ይመልስልን::

   Delete