Sunday, May 26, 2013

ሐራ ለምን ተቈጣች?

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሐራ ዘተዋሕዶ የተባለችው የደጀሰላምና መሰሎቿ ታናሽ እህት በብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ላይ ከፍተኛ ዘመቻ ከፍታለች፡፡ ዘመቻው በምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተንሰራፋውን ሙስና የታከከ ሆንም በዋናነት ግን የማቅ ዋና መጠቀሚያ የነበሩትና ሀገረ ስብከቱን በሙስና ያስቸገሩትን አቶ ደስቢታ እና አባ ኅሩይ ከሀላፊነታቸው መነሣታቸው እንደሆነ ከሐራ ቁጣ የተሞላበት ሀተታ መረዳት ይቻላል፡፡ እውነት ነው፤ ሙስናና ብልሹ አሰራር ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ በተለይም በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በሙስና እየተጠረጠሩ ጩኸት ሲበዛ ከቦታቸው የሚነሱ ሰዎች በሌላ ሹመት ወደሌላ ክፍል መዛወራቸው ከዚህ ቀደም እንዳልነው የጠገበውን አንስቶ የተራበውን የመተካትና የአበላሉን ስልት ረቂቅ ማድረግ ነው፡፡ ሐራ እንደጻፈው አባ ሕዝቅኤል በሙስና መዘፈቃቸውን ካወቀ እስከ ዛሬ ለምን ዝም አለ? ለምን በጊዜው ይፋ አላደረገም? ለምን የእነአባ ህሩይን መነሳት ምክንያት አድርጎ ሊከሳቸው አሰበ? የሚሉትና ይህን የመሳሰሉት ጥያቄዎች በሐራ ላይ ይነሳሉ፡፡
 
ምንም እንኳን የማቅን ታዛዞች እንአባ ህሩይን በማንሳታቸው አባ ሕዝቅኤልን መኮነናቸው ማቅ የሚያሞግሳቸውንና በከንቱ ውዳሴ የሚጠልፋቸውን “ብፁዓን አባቶች” በጥቅሙ ሲመጡበት ጊዜ ጠብቆ የሚያጠቃ አድቢ አውሬ ለመሆኑ የሰሞኑ የሐራ ዘገባ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ “ብፁዕ” “ቅዱስ” እያለ የሚያሞግሳችሁ አባቶች ሆይ በትክክለኛው ጥፋታችሁ መሠረትና  በጊዜው ሳይሆን በማቅ ጥቅም ላይ የመጣችሁ ቀን፣ ለክፉ ቀን ይሆነኛል ብሎ የያዘውን ደካማ ጎናችሁን አዲስ አስመስሎ ያወጣባችኋልና ከማቅ ጋር ያላችሁን ግንኙነት፣ ማቅን ራሱንም ከአሁን መሥመር ብታስይዙትና ከአቡነ ሕዝቅኤልና ከአቡነ ፊልጶስ ብትማሩ ሳይሻል አይቀርም፡፡ የሐራ ታላላቆች እነደጀሰላም ትናንት “ጀግናዬ” እያሉ ሲያሞግሷቸውና በየመድረኩ የፀረ ተሐድሶ ዘመቻው ህገ ወጥ የሆቴል ቤቶች ስብሰባዎችን ባራኪ አድርገዋቸው በነበሩት አባ ፊልጶስ ላይም ተመሳሳይ ውንጀላ መክፈቱን የMay 23, 2013ቱ ዘገባዋ ያስረዳል፡፡
አባ ሕዝቅኤል አባ ህሩይን ካነሱ ወዲህ በተለይ ተጠናክሮ በቀጠለው ዘመቻ ላይ ሐራ እንደገለጸችው፣ አባ ህሩይ አቡነ ሕዝቅኤልን ፓትርያርኩ ላይ መክሰሳቸውንና እግዱ እንዲነሣ ከፓትርያርኩ መመሪያ ቢሰጥም ፓትርያሪኩ እግዱ ተነሥቶ /አስኪያጁ ወደ ሓላፊነታቸው እንዲመለሱና የእግዱ አግባብነት እንዲጣራ ለጠ//ክህነቱ /ቤት የሰጡት መመሪያ አልተፈጸመም፤ ዋ//አስኪያጁ እግዱን ለማስፈጸም ዳተኛ ሲኾኑ ሊቀ ጳጳሱ ደግሞ ላልተገባ ርምጃቸው ድጋፍ ለማግኘት የሀ/ስብከቱን አጥቢያ አብ/ክርስቲያን ሓላፊዎች ነገ ስብሰባ ጠርተዋል” በማለት የሌለ ታሪክ ለመፍጠር ሞክሯለች፡፡ ፓትርያርኩን ከዚህ ቀደም ውሳኔ በመስጠት ላይ ዳተኛ ናቸው ስትል እንዳልነበረ አሁን ደግሞ ለአባ ህሩይ አፋጣኝ መልስ ቢሰጡም አባ ፊልጶስና አባ ሕዝቅኤል ጉዳዩን አፈኑት አይነት ወሬ አሰራጭታለች፡፡ ዳተኛ የሚለውን ስምም ከፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ ወደስራ አስኪያጁ አቡነ ፊልጶስ አዛውራለች፡፡ የሚገርመው ደግሞ አባ ህዝቅኤልን “ሊቀ ጳጳሱ ደግሞ ላልተገባ ርምጃቸው ድጋፍ ለማግኘት የሀ/ስብከቱን አጥቢያ አብ/ክርስቲያን ሓላፊዎች ነገ ስብሰባ ጠርተዋል” ማለቷ ነው፡፡ ስብሰባ መጥራታቸው እውነት ቢሆንም የአባ ህሩይ መነሳት ቤተክህነቱን ያመሰ ትልቅ ጉዳይ መስሎ እንዲቀርብ የሚጥረው ማቅ አባ ህዝቅኤል ስብሰባውን የጠሩት አባ ህሩይን ፈርተው ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው የሚለው ማንንም የማያሳምን ስንኩል ምክንያት ነው፡፡ የአባ ህሩይ መታገድ የማቅን መንደር አምሶ ይሆናል እንጂ ቤተክህነቱ ውስጥ የፈጠረው አንዳች ነገር አይኖርም፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ አባ ህዝቅኤል በጠሩት ስብሰባ ላይ የተናገሩትም ዋና ነገር “በየደብራችሁ የሚጠበቅባችሁን ፐርሰንት ለሀገረ ስብከቱ እነዲከፈል አድርጉ” የሚል ነው እንጂ የአባ ህሩይ ጉዳይ ከቁብ ተቆጥሮ ፈጽሞ አልተነሳም፡፡
ሌላው የማይታመነውና በአባ ሕዝቅኤል ላይ የተነዛው የሐራ የቁጣ ማብረጃ ወሬ ለፓትርያርክነት በተደረገው ምርጫ ላይ አባ ህሩይ ድምጽ አልሰጠኝም በሚል ጠምደዋቸዋል የሚል ነው፡፡ ሐራ በወቅቱ ስለአባ ሕዝቅኤል ያሰራጨው ወሬ ‘አቡነ ህዝቅኤል እኛ መናጆ አንሆንም አሉ’ የሚልና እንኳን ምርጫውን እጩነቱንም እንዳልተቀበሉት የሚጠቁም ዘገባ ነበር፡፡ አሁን ግን ምክንያት ሲያጣባቸው ድምጽ ስለነፈጓቸው ከስራ አገዷቸው በማለት በአንድ አንገት ሁለት ምላስ የሚያሰኛትን ወሬ አሠራጭታለች፡፡ ሐራ ይህን በምን አወቀች? ነው ወይስ አባ ህሩይ እንደማቅ አገልጋይነታቸው ድምጹ የማቅ ዕጩ ለነበሩት ለአባ ማቴዎስ እንዲሰጥ በማቅ በኩል ለተሰራው የምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሎቢ ስራ ዋና ተዋናዩ አባ ህሩይ ነበሩ እንበል?
ንቡረ እድ ኤልያስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅነታቸው በሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ሲታሙ የነበሩና ጩኸት የበረታባቸው፣ የጉቦውን እስኬልም ከፍ ያደረጉ በስልጣን ጊዜያቸው በአንዳንድ ደብሮች ካህናት እስከመጋደል የደረሱበት አስከፊ ሁኔታ የተፈጠረባቸው ሰው መሆናቸው ስውር አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ከማቅ ጋር ያጋጫቸው በዋናነት ይህ ሳይሆን ለማቅ በብዙ መንገድ ስላልተመቹትና የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ኮሚቴ ተብዬውና ማቅ በአምሳሉና በአርኣያው የጠፈጠፈው ስብስብ አመራሮች ከሆኑት ዋናዎቹ ቀን ከእነሄኖክ አስራት አንዳንዶቹ የመንግስት ሰራተኞች በመሆናቸው ከሥራ ሰዓት ውጪ በሀገረ ስብከቱ ሕንጻ ውስጥ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ወደ ተሰጣቸው፣ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች ተሐድሶ መናፍቃን የሚል ስም ለጥፈው ላይ ወደሚዶልቱበትና ሴራ ወደሚጠነስሱበት ቢሮ እንዳይገቡ ማገዳቸው መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ሰሞኑን በአባ ሕዝቅኤልና በአባ ፊልጶስ ላይ ሴራው የሚሸረበውም ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ተብሎ በተሰጠው ነገር ግን የማቅን ጥቅም ለማስጠበቅ በቆሙት በአባ ህሩይና በጓደኞቻቸው በእነሄኖክ አስራት አማካይነት በዚሁ ቢሮ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ማክሰኞ ጠዋት ላይ አቶ ደስታ፣ ሰለሞን አስፋውና ሄኖክ አስራት ከሌሎች አፍቃርያነ ማቅ ግለሰቦች ጋር በመሆን የአባ ህሩይን መኪና ከበው ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በቡድን ሆነው ታይተዋል፡፡ በእነርሱ አስተባባሪነት “አባ ህሩይ ወደስራቸው ይመለሱ” የሚሉ ደጋፊዎቻቸው ድምጻቸውን አሰምተዋል ለማለት የሞከሩ የዳዳቸው ሲሆን፣ “ላይፍ” የተባለው መጽሔት በግንቦት 2005 እትሙ “ሙስና በቤተ ክርስቲያን” በሚል ርእስ ባስነበበው ጽሑፍ “በአባ ህሩይ ከኃላፊነት መነሳት በመደሰት ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት ባሳለፍነው አርብ የመጡ ጥቂት የማይሰኙ ሰዎች ‘በሕግ የሚጠየቁበት መድረክ ሊመቻች ይገባል ብለዋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ አዲስ አበባን በአራት ሀገረ ስብከቶች መክፈሉን ያስተዋሉት እነዚሁ የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪዎች ‘እርግጥ ነው ሙስና እየተከናወነ የሚገኘው በምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ብቻ አይደለም፡፡ ሲኖዶሱ ሀገረ ስብከቶቹን የማጥራት ስራውን በማስፋፋት ሰሜን ደቡብና ምሥራቅ ሀገረ ስብከቶችንም መመርመርና ውሳኔ ማሳለፍ ይገባዋል’ ብለዋል’’ (ላይፍ መጽሔት ገጽ 21)፡፡ ታዲያ ሐራ ለምን ተቆጣች? ቢባል አባ ሙሰኛው አባ ህሩይ ለምን ተነኩብኝ በሚል ነው፡፡

9 comments:

 1. ሃቅ እዩ አሉ የሰሜን ሰዎች

  ReplyDelete
 2. When will this evil MK leave our church alone? MK is a disgusting political party trying to cover itself under the umbrella of the EOTC. But the government of Ethiopia is well aware of MK"s true intentions.

  MK is opening so many churches across the USA and is trying to control the whole church. At least MK dispensing one church in every state with "priests" who have no formal knowledge about church services. MK is a collection of fake deacons and fake priests. They have no roots in the hearts of the Ethiopian communities fortunately and people are waking up to see the true evil face of MK.

  ReplyDelete
 3. አንተ ተሃድሶውስ ለምን ተቆጣህ ተንገበገብክ ሲባልስ? መልሱ ምን ይሆን?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Antes lemetades yaletaadeleke betebales?

   Delete
 4. both the bishop and the monks /abba hiruy/ are useless; even the management committee of Addis Ababa diocese are very tribal even the young generations; pls give the place for the theologians that you previously mentioned

  ReplyDelete
 5. በሙስና ራሳቸውን አቡነ ሕዝቅኤልን በሲሚንቶ የተነሳ ስታብጠለጥላቸው የነበረ ይችው አባ ሰላማ ናት አሁን ደግሞ እሳቸውን ጸረ ሙሰኛ አድርገሽ ማቅረብሽ ስለምን ይሆን። ይልቅስ ከዓላማሽ አብረው የሄዱትን ስም እየሰጠሽና ከማቅ ጋራ እያዛመድሽ ማማትሽን ቀጥይበት።

  ReplyDelete
 6. በሙስና ራሳቸውን አቡነ ሕዝቅኤልን በሲሚንቶ የተነሳ ስታብጠለጥላቸው የነበረ ይችው አባ ሰላማ ናት አሁን ደግሞ እሳቸውን ጸረ ሙሰኛ አድርገሽ ማቅረብሽ ስለምን ይሆን። ይልቅስ ከዓላማሽ አብረው የሄዱትን ስም እየሰጠሽና ከማቅ ጋራ እያዛመድሽ ማማትሽን ቀጥይበት።

  ReplyDelete
 7. Aba selama, u'r report clash one another.

  ReplyDelete