Thursday, May 30, 2013

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለምን ተሐድሶ ያስፈልጋታል?

ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር እና በክርስቶስ ደም የታደሱና የተቀደሱ የምእመናን ጉባኤ ናት፡፡ ይህቺን አማናዊት ቤተ ክርስቲያን ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ታሪኳን ስናጠና በእግዚአብሔር ሐሳብ ውስጥ የሰው ሐሳብ እየተቀላቀለ እና ጤናማውንና ርቱዕ የሆነውን አስተምህሮ የሚያደፈርሱ ሰብኣዊ፣ አጋንንታዊና ዓለማዊ ሐሳቦች በተለያየ ሁኔታና መንገድ ወደ አማናዊቷ ቤተ ክርስቲያን ዘልቀው እየገቡ እውነተኛ የሆነውን መንፈሳዊ ትምህርትም ሲያደፈርሱ እናያለን፡፡ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ያሉ ለእውነተኛው የእግዚአብሔር ሐሳብ ቀናዕያን የሆኑ ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ሐሳብ በሚያደፈርሱ አስተሳሰቦች እና ግለሶቦች ላይ ጠንከር ያለ ተግሣጽ ሲሰጡና አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ ሲወስዱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናነባለን፡፡ ምክንያቱም ተሐድሶ አዲስን ነገር አፍልቆ ማምጣትና በነበረ እውነት ላይ መጨመር ሳይሆን ከጌታችንና ከሐዋርያት የተቀበልነውን የሚያድነውን መለኮታዊ መገለጥ (አስተርእዮ) የሚጋርድ ትምህርትና ድርጊት ሲከሠት መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ትምህርት ለመጠበቅ የሚወሰድ የእርምት እርምጃ ስለሆነ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያናችንም ሐዋርያዊት በመሆኗ የተመሠረተችበት የእምነት መሠረት አማናዊ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ነገር ግን በየጊዜው ምንጫቸው የማይታወቅ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ዲያብሎስንና ሰብእን ከእውነት ይልቅ ሐሰትን የሚያገለግሉ አስተሳሰቦች እና አስተምህሮዎች በመስኮት እውነተኛው የእግዚአብሔር ሐሳብ ወደ ጎን ተትቶ መንፈሳዊ ሕይወታችን ታውኮ በእውነተኛው ትምህርት ላይ ሐሰት ተቀላቅሎበት መንፈሳዊ ቁመናዋ ተበላሽቶ እንመለከታለን፡፡
ይህንን መንፈሳዊ ዝቅጠት የተመለከቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና መምህራን በየዘመናቱ እርምት እንዲወሰድበት ሲታገሉና ሲያስተምሩ ቢኖሩም ከእግዚአብሔር ያልሆነው ከቅዱሳት መጻሕፍት (ከአሥራው መጽሐፍት) የሚቃረነው አዲስ ትምህርት እንዳይታረም በነገሥታቱ ተደግፎና ታግለውለት ሲቆይና ሌላ ጊዜ ደግሞ ጨዋው ከአባቶቼ የተቀበልኩት ትምህርት ስለሆነ በማለት በእውነተኛ የክርስትና ትምህርት ላይ እንደ እራፊ የተለጠፈውን ባዕድ ትምህርት ለማስጠበቅ ሊቃውንቱንና መምህራኑን አፉን ሞልቶ “መናፍቃን ናችሁ” ብሎ መከራና ስደት እንዲነሣባቸው በማድረጉ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ብዙዎች ስለቤተ ክርስቲያንና ስለእግዚአብሔር እውነት በብዙ መከራ ሕይወታቸውን መሥዋዕት አድርገዋል፡፡ ሌሎችም ተሰድደዋል፤ ተደብድበዋል፤ ታስረዋል፤ ተራቁተዋል፡፡
ይህ በመሆኑና ዛሬም በወንጌል ትምህርት ላይ የተጨመረ አሳሳች ትምህርትን እንደ ዶግማ የሚቆጥሩ የተደራጁ የእውነት ጠላቶች በመኖራቸው ብዙ የማስፈራሪያ ድምፅ ስለሚያሰሙ መምህራኑ አፋቸው ተለጉሞ በመከራ አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ይህ አደጋ ክፉውን መንፈስ ሊያገለግሉ በቆረጡ ደጋፊዎቹ ታጅቦ ሙሉ በሙሉ የመንፈስ ቅዱስን ሐሳብ የሚዋጋ የዲያብሎስ ጦር ሆኖ ይታያል፡፡ እንዲህ ያለውን አደጋ ገልጦ ማሳየት እና ቤተ ክርስቲያን ወደ አማናዊው የክርስቶስ ሐሳብ እንድትመለስ ማድረግ የማንኛውም ጤናማ አእምሮ ያለው ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ግዴታ ነው፡፡ ከዚህም በመነሣት ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ሐሳብ በመቅናት፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን በመስማት ቤተ ክርስቲያናችን ለምን ተሐድሶ እንደሚያስፈልጋት አስረጅ የሆኑ ምክንያቶችን እናቀርባለን፡፡
1.    በቤተ ክርስቲያኒቱ እንግዳ ትምህርቶች ስለበዙ
ክርስትናን በተመለከተ ከመሥራቹ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርትና ከእርሱም ቀጥሎ ከእግሩ ሥር ቁጭ ብለው ከተማሩ ሐዋርያት ትምህርት የበለጠና የተሻለ ትምህርት አይገኝም፡፡ እነዚህ ትምህርቶች ለክርስትናችን ቋሚ መሠረት ሆነው የሚታዩና በምንም ሌላ እንግዳ ትምህርት ሊተኩ የማይችሉ ናቸው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “እኛም ብንሆን ወይም የሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን” ብሎ በጻፈልን አምላካዊ ቃል ሙሉ በሙሉ መስማማት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው (ገላ. 1÷8)፡፡ ወደ ፊት በስፋት እና ነጥብ በነጥብ የምንተችበት ቢሆንም በአንዳንድ ገድላት፣ ድርሳናት እና ተአምራት ላይ ተጽፈው የሚገኙ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በቀጥታ የሚጋጩ እንግዳ ትምህርቶችን ቤተ ክርስቲያኒቱ በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ራስዋ ተመልክታ ልታስተካክላቸው ስለሚገባ ወደ እውነተኛውና ከአምላኳ ወደተቀበችው ትምህርት እንድትመለስ ተሐድሶ ያስፈልጋታል፡፡
እንግዳ ትምህርቶቹ መወገድ የሚገባቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህች ምድር ወርዶ የሰው ልጆችን ለማዳን በመስቀል ላይ የሠራውን ሥራ ስለሚያቃልሉ እና እነዚህን ትምህርቶች እውነት ናቸው ብለው የተቀበሉት ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ባለመቻላቸው አንዳንዶች እነዚህን እንግዳ ትምህርቶች የኢትዮጵያዊነት መለያ አድርገው ቢወስዱዋቸውም፣ እንደ እውነት ቢከራከሩላቸውም፣ የሰው ልጆችን ከኀጢአት እስር ፈትቶ የዘላለም ርስታቸውን መንግሥተ ሰማያትን እንዲወርሱ ያደረገው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው እንጂ ሌላ ምንም ነገር ስላይደለ ከሲኦል እስር ከዲያብሎስ ቁራኛነት ለመላቀቅ ከቃሉ ውጭ የሆኑ ሐሳቦችን ሽረን ለወንጌሉ እንግዳ የሆኑ ትምህርቶችን ትተን በጠራው የመስቀል መንገድ ላይ በእምነት መጓዝ በዚህ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን ወሳኝ ጊዜ ስለሆነ ይህን ውድቀቷን በቃለ እግዚአብሔርና በመንፈስ ቅዱስ ምርመራ ከእንግዳ ትምህርቶች ልትለይ ይገባልና ተሐድሶ ያስፈልጋታል፡፡
2.   የእግዚአብሔር ቃል ተገቢውን ስፍራ ስላጣ
ሌላው ቤተ ክርስቲኒቱ ተሐድሶ እንደሚያስፈልጋት አስረጅ የሆነው እውነት ቅዱስ ወንጌል በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ተገቢውን ስፍራ ማጣቱ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉን መጽሐፍ ይመረምራል፣ ይመዝናል፤ እርሱ ግን  በየትኛውም መጽሐፍ አይመረመርም፤ አይመዘንም፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የተለየ ሐሳብ ያለው ማንኛውም በቤተ ክርስቲያን የምንገለገልበት  መጽሐፍ ሌላ ምንም አይነት አንድምታ ሳያስፈልገው ከስህተት ትምህርት ጎራ ሊካተት ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የሁሉ ዳኛ በሆነው በእግዚአብሔር መንፈስ በመጻፉና የእግዚአብሔርን እውነት በመያዙ ነው፡፡ አሁን  ግን ምንጫቸው የማይታወቅ እና በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረኑ መጻሕፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ እኩል መሳ ለመሳ በመቀመጣቸው እና መጽሐፍ ቅዱስን በመገዳደራቸው በእውርነት ልምራችሁ የሚሉንን መጽሐፎች ተገቢውን ስፍራቸውን ማሳወቁ አግባብ ስለሆነ ተሐድሶ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አስፈላጊ ነው፡፡
ሌላው ቀርቶ በስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር ወቅት ንጹሑን ወንጌል መስበክ እንደ መናፍቅነት እየተቆጠረ ስለመጣ አገልጋዮች የግድ የእግዚአብሔርን እውነት የሚጋፉ መጻሕፍትን እየጠቀሱ እነርሱም አገልግሎታቸውም የእግዚአብሔርን መንግሥት እውነተኛ ሐሳብ የሚቃረኑ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ የእውነተኛ ኦርቶዶክሳዊነት መሠረቱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በሐዋርያት አባቶች የተሰበከውን ቃል በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ማብራራት መሆኑ እየቀረ ድርሳነ ባልቴትን መተረክ እየሆነ ይገኛል፡፡
እንዲህ ያለው አስተሳሰብ በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ትክክለኛውን ተሐድሶ ካላገኘ እና ቤተ ክርስቲያኒቱ ሙሉ በሙሉ መመሪያዋ እንዲሆናት ወደ እግዚአብሔር ቃል ካልተመለሰች አሁንም ቢሆን በየዕለቱ እየጨመረ የመጣውን የምእመናን ፍልሰት ማስቆም ይቸግራታል፡፡ ሰውን በስፍራው ለማጽናት የተሻለው እና እግዚአብሔርም የሚደሰትበት ትክክለኛው መንገድ የእውነትን ቃል በእውነት ሳያፍሩ እና ሳይሸሽጉ እንደ ጥንት አባቶቻችን ለሕዝቡ መግለጥ ነው፡፡ ለዚህም ቤተ ክርስቲያን ጤነኛ በሆነ የተሐድሶ ኣስተሳሰብ ልትቃኝ ያስፈልጋታል፡፡
3. የመዳንን እውነት የሚገዳደሩ ትምህርቶችን ማስተናገድ ስለጀመረች
የልጅ ቡኮ ዕለቱን ነው
ቢጋግሩት ነቀፋ ነው
ቢቀምሱትም የከረፋ
ቢጨብጡት ወዮ አበሳ
እንደተባለው መንፈስ ቅዱስን ሳያማክሩ ለአሸናፊው የእግዚአብሔር ሐሳብ ብቻ መገዛትን ትተው የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምሮ በማያውቁ እና ለስሜታቸው ባሪያ በሆኑ ሰዎች እየተፈጠሩ ያሉት አዳዲስ አስተምህሮዎች ሀይ ባይ ከልካይ አጥተው የክርስቶስን መስቀል እየወጉ ይገኛሉ፡፡ እኛም እንደ ቤሪያ ምእመናን “ነገሩ እውነት ይሆንን?” በማለት ለመመርመር ከመሞከር ይልቅ “ከኛ ወገን ያለ ሁሉ የሚለው ሁልጊዜ እውነት ነው” በሚል በጨዋ ምእመን አመክንዮ ተይዘን ለስህተት ትምህርቶች ተገዝተን እንገኛለን፡፡ እነዚህ የስህተት ትምህርቶች የመዳንን እውነት ቀስ በቀስ እየሸረሸሩ አሁን ፊት ለፊት መዋጋት ጀምረዋል፡፡ “ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም” የሚለውና እርሱን የመሰሉ ጥንተ ተፈጥሮዋቸው አጋንንታዊ የሆኑ እና “መዳን በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” (የሐዋ.ሥራ 4÷12) የሚለውን የመንፈስ ቅዱስ አዋጅ የሚሽሩ እንግዳ ትምህርቶች በመጽሐፍ ደረጃ ታትመው እስከ መሰራጨት ደርሰዋል፡፡
በእግዚአብሔር ቃል የተገለጸውን “መዳን በሌላ በማንም የለም” ተብሎ የተዘጋውን የጽድቅ ማኅተም የሚከፍቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተገለጸው እውነት ውጭ  ሌላ አማራጭ አለ ብለው የሚያስተምሩ ሁሉ ለሰው መዳን ሳይሆን መጥፋት በአጋዥነት የሚሠሩ ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር የተያያዙ እና በዝክር፣ ወንዝ በማቋረጥ፣ ገዳማት በመሳለም፣ በቀብር ቦታ እና በሌሎችም ብዙ መንገዶች ሰው ሊድን ይችላል፡፡ ብለው የሚያስተምሩ ደፋር ብዕር የገለበጣቸው አጋንንታዊ ሐሳቦች ያሉባቸው ገድላት እና ተአምራት በመኖራቸው ሕዝቡ ያዳነውን ጌታ በእውነተኛ ማንነቱ ሳይረዳ በዋል ፈሰስ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
መዳን የህልውና ጉዳይ ስለሆነ በቀላሉ ሊታይ የሚችል አይደለም፡፡ እናቶቻችን እንደሚሉት “እስቲ ይሁና!! ምን ይታወቃል የአንድዬ ሥራ” በማለትም በቀላሉ ሊታለፍ የሚችል ነገርም አይደለም፡፡ የአንድዬ ሥራ የሚታወቅ እና በአደባባይ በመስቀል ላይ የተከናወነ ነው፡፡ አንድዬ ለመዳናችን ከደሙ የተሻለ አማራጭ አልሰጠንም፡፡ በመስቀል ላይ የፈሰሰውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ደም ለኔ ስለኃጢአቴ የተከፈለ ቤዛነት ነው ብሎ አምኖ መቀበል ለመዳን ዋነኛውም ብቸኛውም አማራጭ ነው፡፡
ነገር ግን ህዝቡ ይህንን እውነት አምኖ እንዳይቀበል የሚከለክሉ ሌላም አማራጭ አለህ ብለው የሚያስተምሩ በክርስቶስ የተሰጠንን መዳን ቀብረው ማሳሳቻ የሚሰብኩ ስለበዙ ቤተክርስቲያናችን ወደ ሐዋርያት ትምህርት እንድትመለስ መታደስ አለባት፡፡ መዳን በክርስቶስና በመስዋዕታዊ ሞቱ በማመን መሆኑን መቀበልና ማስተማር አዲስ ትምህርት የሚመስላቸው አሉ ግን አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እና በተደጋጋሚ የተቀመጠ፣ ሐዋርያት የሰበኩት እስከ ዘመናችን ድረስ እውነተኛውን መንገድ የተከተሉ እንደ እነ ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ ያሉ አባቶቻችን መዳን በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ የሆነ እና በክርስቶስ በማመን ብቻ የምንቀበለው ነው፡፡ ብለው ያስተማሩት ትምህርት ነው፡፡(ትምህርተ ሀይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት )
ስለዚህ በእነዚህ እና በሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች ተሐድሶ ለቤተክርስቲያኒቱ ያስፈልጋታል ብለን እናምናለን፡፡ ለእናት ቤተክርስቲያናችን መታደስም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ እናገለግላለን፡፡
ይቀጥላል

8 comments:

 1. wishetamoch. tsere tikikilegna aymanot nachu enante. Tenektobachuwal min lemadreg endeasebachu.Emebetachin tsadkan semaetat regtachu yewnet afachun meltachu demo taweralachu.Lemanegnaw? Egziabher kezih kihdet yawtachu. wede Tikikilegnawa Orthodoxawita Tewahido Haymanot Yimelsachu.Yealem medanit Egziabheramlak yikir yibelachu.


  ReplyDelete
 2. keep on your dreaming. you will succeed as you have become successful for the past some 10 years

  ReplyDelete
 3. go to hell, why don't you just preach your own doctrine why you talk and write abt the reformation of our religion we never hear and accepted ur says.

  ReplyDelete
 4. I am not fanatic who go wild on big orthodox conservatism.
  I am just a simple Orthodox Tewahido Christian who loves our church. Saying this I just could not help why somebody opose a reformation? got Lots of things that have nothing to do with the dogma which are obscure and confusing. " listening to Tamere Maiam during the reading is a substitute for a communion"?? Da! I do not think the oriental sister churchs would go with this. I found out on Fetha Negest we do not eat pork because it was considered as a sin, but after Christ we hold on this as our culture. I have been taught quite the contrary in the daily church teachings . Went on google and searched what other Oriental Orthodox say. Interestingly amazing! I said catch 22 for ETOC. The reason why many defected to the Protestant Church is partly because it was not adequately addressed to them the right Orthodox teachings and dogma. Reformation is needed in this dynamic world to go with the time and condition with out altering the dogma.

  ReplyDelete
  Replies
  1. May God bless you and enlighten you on the search for the truth! I was also on the same path as you. I started questioning everything about our orthodox faith (literally everything). I started reading multiple sources to find out if the things I was taught from childhood were the word of God or just a mere man-made ideologies. There are a lot of truth in our church but don't swallow everything you hear. Question it; See if it lines up with the Bible; Read what the early church fathers taught on that particular matter; See what our sister churches believe. I can assure you with the help of God, the missing puzzles will suddenly appear to you. The problem is, most of us in Ethiopian orthodox church are scared to challenge some of the teachings. This is faith, why are we scared? You know our eternal life depends on it. If we mess up on this life, the wrath of God will be upon us. So I say to you dear brother, be humble and continue your search. As our Lord Jesus said it himself ''the truth shall make you free''.

   Delete
 5. ye beg lemd lebsew kemimetubin hasetegnoch nebiyat enitenkek!

  ReplyDelete
 6. enante sewoch egziabher yibarkachihu yehenin miskin hizb adnut, yehenin yeminredabet neger kale asawikun

  ReplyDelete
 7. anonymous#3 You will learn a whole lot if you really aspire to read, to listen to look things in perspective. May God bless you.

  ReplyDelete