Saturday, June 1, 2013

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው ስደተኛው ሲኖዶስ ሌሎች ጳጳሳትን ለመሾም ወሰነ።

በቴክሳስ ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተናጋጅነት ከግንቦት 19 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አርብ ግንቦት 23 ዕለት ተጠናቀቀ። በጉባኤው ሊቃነ ጳጳሳት፥ መነኮሳት፥ ካህናት፥ ዲያቆናት መምህራነ ወንጌል፣ የቦርድ አባላትና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የተሳተፉበት ነው ተብሏል። በአጀንዳ ከተያዙት መዋያያ ርዕሶች መካከል ዋናዋናዎቹ የተቋረጠው የእርቅ ሂደት፤ የሊቃነ ጳጳሳት ሹመት፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት መቋቋም፤ የዲሲ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን እና የኦክላንድ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ናቸው።

የተቋረጠው የእርቅ ጉዳይ እንዲቀጥል አስፈላጊ መሆኑ ቢታመነብትም ተስፋ የሚሰጥ ውሳኔ የተወሰነ አይመስልም። የተሻረው ቀኖና እስከተከበረ ድረስ እርቁን እንቀጥላለን የሚል የጥንቱ አቋም እንደተያዘ ነው። ጉዳዩም ከመንግሥት ጋር የተቆራኘ በመሆኑ እርቁ ከመንግሥት ጋርም መሆን እንዳለበት ታምኖብታል። ሲኖዶሱ ይዞታውን ለማስፋትና ጠንከር ያለ እንቅሥቃሴ ለማድረግም ሌሎች ተጨማሪ ሊቃነ ጳጵሳትን ለመሾም እና ወደ አፍሪካና አውሮፓ አውስትራሊያ ለመላክ ውሳኔ አስተላልፏል።

ለቅዱስ ፓትርያርኩ የግል መኖሪያ ቤት ለመሥራትና ጠቅላይ ጽ/ ቤት ለማቋቋም ልዩ ኮሜቴ የተመደበ ሲሆን ለፓትርያርኩም ልዩ ጸሐፊ ተሹሟል። በአዲስ ሥራ አስኪያጅ እና በአዲስ ጸሐፊ የሚመራ ጠቅላይ ቤተ ክህነትም ተቋቁሟል። በዚህ አጀንዳ ላይ ዶክተር ነጋ የተባለው የዲሲ ቅዱስ ገብርኤል የቦርድ ሊቀ መንበር እና መርጌታ ተስፋየ የተሰኙት የዲሲ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ ተቃውሞ አቅርበዋል። በተለይም ዶ/ር ነጋ የፓትርያርኩን የግል መኖሪያ ቤትና የጠቅላይ ጽ/ቤት መቋቋምን አጥብቆ ተቃውሟል።  ሆኖም ግን ለተቃውሞው በቂ ምክንያት ባለማቅረቡ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።  

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የሚያስተዳድሩት የኦክላንድ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያንና በቅርቡ የተመሠረተው አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ የሚያስተዳድሩት የኦክላንድ መካነ ሰላም ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሌላው አጀንዳ ነበር። አቡነ መልከ ጼዴቅ መካነ ሰላም ኢየሱስን አልቀበልም ያሉ ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩና ሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት ግን ተቀብለውታል። ቅዱስ ፓትርያርኩ የእውቅና ደብዳቤ የሰጡ መሆናቸውንና ሌሎች ጳጳሳትም ቀድሰው ባርከው ማጽደቃቸውን አረጋግጠናል። የጠቡ ምክንያት ግን ውስብስብ ያለ ነው፤ አንዳዶች የመድኀኔ ዓለም ቦርዶች ለሃያ ዓመት ሙሉ ከሥልጣን አንወርድም በማለታቸውና አቡነ መልከ ጼዴቅም ቦርዶች ከሥልጣን እንዳይወርዱ በመደገፋቸው ምዕመናን አኩረፈው ወጡ የሚሉ ሲሆን፤ ሌሎች ደግም የቦርድ አባላት በአባ ቃለ ጽድቅ ላይ የፈጸሙት በደል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ ቃለ አዋዲ መከበር አለበት የሚል ጠንካራ አቋም በመያዛቸው እንዲባረሩ በመደረጋቸው ነው ይላሉ። ይህን ጉዳይ እያጣራን ስለምንገኝ እውነተኛውን መረጃ ወደ ፊት ለማቅረብ እንሞክራለን። ጉዳዩ በሽማግሌዎች ስለተያዘ በዚያው እንዲቀጥል ተወስኗል። ሁኔታው በሰላም እንደሚያልቅና እርቅ እንደሚፈጸም ይጠበቃል።

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጸሐፊን መምረጥ በሚለው አጀንዳ ቀሲስ መላኩ ባወቀን ከጸሐፊነት ለማውረድ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ያቀረቡት ሐሳብ ተቀባይነት አላገኘም። ሊቃነ ጳጳሳቱና ካህናቱ በአንድነት ሆነው የቀሲስ መላኩን ጸሐፊነት አጽድቀዋል። የካህናት ጉባኤ ጸሐፊ መምህር ተከስተ ጫኔን ከጸሐፊነቱ እንዲወርድ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ያቀረቡት ሐሳብም ተቀባይነት አላገኝም። ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የሁለቱም ማለት የቀሲስ መላኩ እና የመምህር ተከስተ ጫኔ ወዳጅ የነበሩ ሲሆን ቀሲስ መላኩ መካነ ሰላም ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ኦክላንድ ሄዶ በመስበኩ፤ መምህር ተከስተ ጫኔም ከአቡነ መልከ ጼዴቅ ጋር ሲኖር ሳለ ጠቡን ምክንያት በማድረግ ትቷቸው በመሄዱ መበቀል ፈልገው ነው እንጂ ሌላ ጥፋት ተገኝቶባቸው እንዳይደለ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።


በመጨረሻም ሲኖዶሱ የሲያትሉን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስን የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንና የቴክሳስ ስቴት ጳጳስ አድርጎ በመሾም ጉባኤው ተጠናቋል።     

18 comments:

 1. guys I was there in the meeting . I saw so many problems . I have doubt on aba melekthidik. He was man of attack. The bishop came to the meeting to attack those who oppose him. The bishop
  1. lead by dictator boards
  2. He has no dream for the synod
  Any way it was dominated by others but I understood that on thgis exile synod there are some problems.

  ReplyDelete
 2. aye abune melek thedek derom lebetekerseteyan gareta yehonu erso not senodos yemeleyayetu meseter yerso derama new meche yehon be edmewot burakea ena mereket setew yemeyalefut?????????????

  ReplyDelete
 3. የምትገርሙ ናችሁ። በቦታው የነበሩ ሰዎች ይታዘቡናል ብላችሁ አለማሰባችሁ ይገርማል። ስለ ጉዳዮቹ ማን ምን አለ ብሎ አንባቢ ይጠይቃል። እናንተ ግን የራሳችሁን ተረት ትጽፋላችሁ። ይህንንም ያደረጋችሁት ሆን ብላችሁ በቦታው ባልነበሩ ሰዎች ለማመካኘት ነው። ዶር ነጋ በፓትርያርኩ የቤት ግዢ ላይ ምንም የሰጠው አስተያየት እንደሌለ በቦታው አይተናል። ስሙን ለማጣፈጫ ለመጠቀም ፈልጋችሁ ከሆነ ትክክል አይደለም። እስከ አሁን ስትጽፉት የነበረው ሁሉ ሀሰት መሆኑን ይህ ጽሁፋችሁ ያረጋግጣል። ለምን ብትሉ በቦታው የነበሩት ያዩትና የሰሙት ነገር እናንተ ካላችሁት በጣም የተለየ ነው። ኧረ እግዚአብሔርን ፍሩ!! ተኝታችሁ ማደር የምትችሉት ከእውነት ጋር ስትኖሩ ነው። ምነውይህን ያህል ጥላቻ ኖራችሁ? ጥላቻ ያለው ሰው ሙሉ ጉልበቱን መጠቀም አይችልም፣ እግዚአብሔርም አያግዘውም። ስለዚህ የጥላቻ ነገራችሁን ለእራሳችሁ ስትሉ ተውት።

  ReplyDelete
 4. aye maferia nachehu endaw menem batenageru yeshalchual yegziabhere fired endeh bekelal aylekachehum beteley yabene merkorios endeh endeashangulit yemetchawotubache aye egziabehaer firduen yestachehu.

  ReplyDelete
 5. ኤፌሶን 6:18 በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤
  Ephesians 6:18 - "Praying always with all prayer and supplication in the Spirit, and watching thereunto with all perseverance and supplication for all saints;"

  ReplyDelete
 6. ለእኔስ በሲኖዶሱ ውስጥ ያለው ችግር ብዙም አያስደንቀኝም። ምክንያቱም ሲኖዶሱ ሲፈጠር ምንጩ የማይደርቅ ችግር አብሮ በመፈጠሩ ነው። የችግሩ ምንጭም አባ መልከ ጼዴቅ መሆናቸውን የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ችግር በውል ለሚገነዘቡት ሁሉ ግልጽ ነው።
  በአባ መልከጼዴቅ እምነት ሲኖዶስ ማለት
  1. የጨካኞች በትር
  2. የጎጠኞች መታወቂያ
  3. የበቀልና የቂም ማራገቢያ
  4. የአምባገነን እና የንትሪክ አደባባይ ነው።

  ReplyDelete
 7. I am under the Addis holy synod . I do not believe about the North America synod . Aba melekthisidk is the cause to split the synod in to two .
  The bishop is the only dictator and racist . Dejeselam please drop his picture on you blog

  ReplyDelete
 8. እውን አቡነ መርቆሪዎስ ስደተኛውን ሲኖዶስ እየመሩት ነው ወይንስ ሌላ ስውር አካል ቅዱስነታቸውን መውጫ ቢዛ አድርጎ ሲኖዶሱን እያሽከረከረው ነው?

  ReplyDelete
 9. አስተያየት ከመስጠቴ በፊት ማሳወቅ የምፈልገው በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን በጎሳ ከፋፍሎ እየገዛ ያለው መንግሥት ደጋፊ አለመሆኔን ነው።

  ከዚህም በላይ በጎሳ በሽታ የተለከፈውና በአባ ጳውሎስ ሲመራ የነበረው ሲኖዶስ ለኢኦተቤ/ክ መልካም መንፈሳዊ አመራር ይሰጣታል የሚል ከንቱ እምነትም የለኝም:: ስደተኛ ነኝ የሚለውም ሆነ ሀገር ቤት ያለው ቡደን ሁለቱም የመሪያቸውን የኢየሱስን ትዕዛዝ በግል ጥቅምና በገንዘብ የለወጡ መንፈሳዊነት የሌላቸው ቡድኖች መሆናቸውን ተረድቻለሁ::

  ከዚህ ውጭ ግን አቡነ መርቆሬዎስ ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው ለሚለው ከሁሉ አስቀድሞ በደርግ አገዛዝ የጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ እነ ሻለቃ መላኩ ተፈራ በሕዝቡ ላይ ያን መሳይ መከራ ሲያወርዱበት ምንም ሳይናገሩ በዝምታ በማሳለፋቸው ላደረጉት መልካም ትብብር የተቸራቸው ስጦታ እንጂ ለቦታው የሚመጥኑ አባት ሆነው አልነበረም። ይህንንም አሁን በሕይወት ያሉት ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ ይመሰክራሉ።

  የኢሕአዴግ አገዛዝ ሥልጣን እንደያዘ ምን ሊደርስባቸው እንደሚችል በመጠርጠር በነ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ አማካሪነት ታምሜአለሁ ብለው ከመንበረ ፕትርክና ረብሻ ሳያስነሱ ይውረዱ ተብለው በተመከሩት መሰረት ወደውና ፈቅደው ያለማንም አስገዳጅነት ለቀቁ። እውነቱ ይህ ለመሆኑ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ የጻፉትን መጽሐፍ ማንበብ በቂ ማስረጃ ነው። አሁን ወደ ኋላ ተመልሶ በሌለ ሥልጣን ሕጋዊው ፓትርያርክ ብሎ መጥራት የሕጻናት ጨዋታ ነው። እራሱ ሕጋዊው ፓትርያርክ የሚለው አጠራር የቀልድና የሃሰት መሆኑን ያሳያል። እውን አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመን እሳቸውን ፓትርያርክ አድርጎ ይቀበላል ብሎ የሚያምን ወገን አለ? በሕልም ዓለም መኖር ይፈቀዳል። አሜሪካ ሰው ያለመውን ሊያገኝ ይችላል ቢባልም እንደዚህ ያለውን ቅዠት ግን ሕልም ልንለው አይገባም።

  በአጭሩ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው መንበሩ ላይ ይቀመጡ የሚሉት ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተማርያም ወርቅነህ ናቸው እንጂ (ይኸውም በእጅ አዙር የምቆጣጠረው እኔ ነኝ ከሚል ምኞት በመነጨ አሠራር) ራሳቸው አቡነ መርቆሬዎስ ቢጠየቁ እንደማይስማሙ የተረጋገጠ ነው። አይ የምትለው ትክክል አይደለም የሚል ሰው ካለ እስቲ ከአቡነ መርቆሬዎስ አንደበት እውነቱን እንስማ።

  እንዴት የሚያሳዝን ነው እነዚህ ናቸው የመንጋው እረኞች? እውን እነዚህ የመንፈሳዊ መሪዎች ሆነው ቤተ ክርስቲያኒቱ ታድጋለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን?

  ReplyDelete
 10. Some of the negative comments are from the local MK. p/s do not pay any attention to them. They have this pick the bone ill wish to the exile Synod.

  ReplyDelete
 11. የኢትዮጵያውያን የ15ኛው ክፍለ ዘመን ገዳማት በሊባኖስ ተገኙ

  የጽሑፍ መጠን ኢሜይል DISQUS_COMMENTS
  шаблоны RocketTheme
  Форум вебмастеров

  • በዋሻው የተገኙት የግእዝ ጽሑፍና ሥዕሎች ማረጋገጫ ሆነዋል

  ኢትዮጵያውያን መነኮሳት በ15ኛው ክፍለ ዘመን በሊባኖስ ቀዲሻ ሸለቆ (Holy Valley) ይገለገሉባቸው የነበሩ አራት ገዳማት ከግእዝ ጽሑፍና ሥዕሎች ጋር ተገኙ፡፡

  ኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲና ካፑቺን ፍራንቸስካዊ የምርምርና የሥልጠና ማዕከል ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋራ ባዘጋጁት የግእዝና የሱርስጥ (የሶርያ ቋንቋ) ጥናቶች ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ጥናታቸውን ያቀረቡት አብዶ በድዊ፣ በገዳማቱ በድንጋይ ላይ የተጻፈው ጽሑፍና የቅዱሳንና የመስቀል ሥዕሎች መገኘታቸው ገዳማቱ የኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ያሳያሉ ብለዋል፡፡

  ‹‹አሕባሽ›› የሚል መጠርያ የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን መነኮሳት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች መሆናቸውንና በ15ኛው ክፍለ ዘመን በሰሜን ሊባኖስ ተራራዎች በተለያዩ አጥቢያዎች የኖሩ ናቸው፡፡ ገዳማቱም ማር ያዕቆብ በኢሕደን (Ehden)፣ ማር ጊዮርጊስ በሐድቺት (Hadchite)፣ ዴር ኤል ፍራዲስ እና ማር አስያ ናቸው፡፡

  ጂኢአርኤስኤል የተሰኘ የጥናት ቡድን እ.ኤ.አ በ1991 የግእዝ የድንጋይ ላይ ጽሑፍና የተለያዩ መንፈሳዊ ሥዕሎች ማግኘቱን ሊባኖሳዊው አብዶ በድዊ ተናግረዋል፡፡

  መነኮሳቱ በደብረ ሊባኖስ እንዴት ሊገኙ እንደቻሉ የተለያዩ መላምቶች እንዳሉ ያወሱት አጥኚው፣ አንዱ በእምነት የሚመስሏቸውን የግብፅ ኮፕቲኮችን የወንጌል መልዕክተኛነትን ለማገዝ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

  መነኮሳቱ ሊባኖስ ተራራ (ደብረ ሊባኖስ) የደረሱት በ1470 እና 1488 መካከል መሆኑን በሥፍራው የነበሩትን የማሮናይት እምነት ተከታዮችን በስብከታቸው ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት መለወጣቸው ይነገራል፡፡ ከነዚህም አንዱ በኋላ ላይ የያዕቆባውያን ፓትርያርክ የሆኑት የብቆፋው ኖኅ (Nouh of Bqoufa) ይገኙበታል፡፡

  በአካባቢው አጠራር ኢትዮጵያውያንን ለመጥራት በሚጠቀሙበት አሕባሽ የሚጠሩት ኢትዮጵያውያን በ15ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ከደረሰባቸው ጥቃት የሸሹ ****ደቂቀ እስጢፋኖስ******* መሆናቸውን ተመራማሪዎች እንደደረሱበት አብዶ በድዊ ተናግረዋል፡፡

  ‹‹በርካቶች እንደሚያምኑት፣ ከነዚህም መካከል ኢቫ ዊታኮውስኪ (Eva Witakowsky) እንደሚሉት መነኮሳቱ ደቂቀ እስጢፋኖስ ናቸው፡፡ በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ወገኖቻቸው ከደረሰባቸው ፍጅት አምልጠው ኢየሩሳሌም፣ ቆጵሮስ፣ ሊባኖስ፣ ሶርያና አርመን ድረስም የተሰደዱ ናቸው፡፡ ሊባኖስ እንደደረሱ በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል በተለያዩ አጥቢያዎች ቀዲሻ (ቅዱስ) ብለው በሰየሙት ቦታ መኖር ጀምረዋል፡፡››

  የግድግዳ ላይ ሥዕሎችና የግእዝ ጽሑፍ ከሱርስት ቋንቋ ጽሑፍ ጋር የተገኙት በማር አስያ፣ ማር ጊዮርጊስና ማር ዮሃና ገዳማት መሆኑን ያወሱት አቅራቢው፣ ከተገኙት ሥዕሎች አንዱ የፈረሰኛው ቅዱስ ጊዮርጊስ ምስል ላሊበላ ይምርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ካለው ጋር ይመሳሰላል ብለዋል፡፡ በማር ሙሳ አልሐበሺ ያለውም ጋይንት ቤተልሔም (ደቡብ ጎንደር) ካለው ጋር ተመሳስሎ እንዳለውም ጠቅሰዋል፡፡

  የግእዝ ጽሑፉ ከፊሉ የጠፋ ሲሆን፣ ያሉትን የግእዝ ቃላት የቋንቋው ፕሮፌሰሮች ባደረጉት ጥናት ኃይለ ቃሉ ጸሎት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹መሐረነ እስከ ለዓለመ ዓለም አሜን›› (ለዓለም እስከ ዘለዓለም ማረን አሜን) ይላል፡፡

  በጉዳዩ ላይ ቀጣይ ጥናት እንደሚደረግበትም አብዶ በድዊ ሳይናገሩ አላለፉም፡፡

  አስኮ በሚገኘው የካፑቺን ፍራንቸስካዊ የምርምርና የሥልጠና ማዕከል ከግንቦት 19-22፤ 2005 ዓ.ም. ድረስ በተካሄደው የግእዝና የሱርስጥ ጥናቶች ዓለም አቀፍ ጉባዔ ከኢትዮጵያ ሌላ ከሩቅ ምሥራቅ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የመጡ ምሁራን 25 ጥናቶችን አቅርበዋል፡፡

  ://www.ethiopianreporter.com/index.php/news/item/2019-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8B%8D%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8B%A815%E1%8A%9B%E1%8B%8D-%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%88%88-%E1%8B%98%E1%88%98%E1%8A%95-%E1%8C%88%E1%8B%B3%E1%88%9B%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%88%8A%E1%89%A3%E1%8A%96%E1%88%B5-%E1%89%B0%E1%8C%88%E1%8A%99

  ReplyDelete
 12. abune Merkorios be-melaku Tefera zemen papas neberu ende? gonders neberu ende?? yemiak sew yemelselgn.

  ReplyDelete
  Replies
  1. BeShaleqa Melaku Tefera merinet Gonder westt berkata yechikane tegbarat beteftsemubachew ametat yeGondar liqe Papas yeneberut Abune Endrias sihonu, bezyan gize Abune Merqorios yeHarar liqe Papas neberu. Abune Merqorios keJijiga wede Gondar yetezewawerut yeQeyu Shibir zemen kalefena beGondar antsarawi selam ketegegne behuala neber.

   Delete
 13. Abune Merkorios bemelaku gizie yeGondar like papas honew Gondar neberu. Patriark honew yeteshomutime gondar eyalu beserut sira new yibalal.

  ReplyDelete
 14. Dn. Andualem Bewnet egziabheren ymetefera kehone mechem azaze honehal Abene merkoriosen Ethiopia sededuachew ena erefte segachewn ezach betekedesech ager yehone ende Aba zina Markose bechaka ataskeruachew. Yanta bate Aba Habte(Abune Melekesidike) Behiwotachew Melame neger sertew Ayawkume. Hule Bekefatena betenkole bebekele yetemolu TEHADESO Nachew.

  ReplyDelete
 15. ውይ አባ ሰላማ የማምነው የቤተክርስቲያን ድህረ ገፅ ነበር አሁን ግን ከደጀ ሰላም ጋር አንድ መሆናችሁን ተረድቻለሁ። እኔ ስብሰባው ላይ ስለነበርኩኝ ነው በጣም የገረመኝ ነገር ውሸተሰሞቸረ መሆናችሁ ነው። መረጃ ከሚመለከተው ክፍል መጠየቅ ትችሉ ነበር እኮ ዝምብላችሁ የመሰላችሁትን ከምትፅፉ። ስብሰባውን ሙሉ በሙሉ ቀድቼዋለሁ እየደጋገምኩም ሰምቼዋለሁ ያላችሁት ነገር ውሸት መሆኑን ተገንዝቤአለሁ።

  ReplyDelete
 16. kirubel send merej do not talk

  ReplyDelete
 17. ሰደተኛው ሲኖዶስ ስደተኛ የሚለውን ትቶ እንደ ደቂቀ እስጢፋኖስ እውነተኛውን የወንጌል ቃል
  በመስበክ እና በማደራጀት ራሱን ቀዋሚ የምእመናን ተስፋ (አለኝታ)ለማድረግ መጣጣር ይኖርበታል
  መቸውንም ቢሆን ሰው ሰውጂ ተቀይሮ መላክ የሆነበት ጊዜ አልነበረም ከቀድሞ ጀምሮ በሀገራችን
  የተለያዩ ውዝግቦች ነበሩ ተወዛጋቢዎችም ደቂቀ ኤዎስጣቴዎስ ደቂቀ ተ/ሀይማኖትና ደቂቀ እስጢፋኖስ ናችው። በዚህም ምክንያት አባ ኤዎስጣቴዎስ ተሰደው አርመንያ ሄደው ደብረ ምርምህናም ተቀበሩ
  ይለናል ታሪክ ሌሎችም ተሰደው በባድ ሀገር የቀሩ ትቂቶች አይዶሉም የስደታቸው ምክንያት ሥጋዊና
  መንፈሳዊ ውዝግብ ነበር።

  ReplyDelete